አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Forwarded from አለሕግAleHig ️
የጋብቻ ምዝገባ-ግለሰባዊ ጥቅሞች

ጋብቻ ለመከሰቱ ህጋዊ ማስረጃ በመሆን

ጋብቻዉ ህጋዊ መሆኑን ለማረጋገጥ፣

የተጋቢዎቹን ዝምድና እና ግንኙነት ለማረጋገጥ፣

የጋብቻ ውጤት ለሆኑት ህፃናት በቤተሰብነት የመጠበቅ ህጋዊ መብትን ለማረጋገጥ፣

ህጋዊ ወራሽነትን ለማረጋገጥ፣

ለቤተሰብ ድጎማ ለመንግስት ጥያቄ ለማቅረብ፣

ከተጋቢዎች አንዳቸው ቢሞቱ ቋሚው የኢንሹራንስ ጥያቄን ለማቅረብ፣

ጋብቻ በሚፈርስበት ጊዜ የልጆችን አስተዳደግ ለመወሰን፣

ወደ ውጪ ሃገር ለመጓጓዝ ፓስፖርት የማግኘት ፈቃድን ለማቅረብ፣

የልጆችን ህጋዊነት ለማረጋገጥ፣

የራስን ልጆች ህጋዊነት ለመመስረት እንዲሁም ከሌላ የተወለዱትን ለማስመዝገብ፣

የዜግነት ቅያሬን ለመጠየቅ፣

ጋብቻዉ የተፈፀመበት ጊዜ እና ቦታ በማሳወቅ ህጋዊ መረጃ በመሆን፣

Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!

በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍161👏1
ገንዘብ ስለሌላችሁ ጠበቃ ማቆም ላቃታችሁ ወገኖቼ እስቲ በነፃ ጠበቃ እንዴት እንደምታገኙ ልጠቁማችሁ


1) ተከላካይ ጠበቃ;-ይህ በፍ/ቤቶች የሚታወቅና ጉዳያችሁ የወንጀል ከሆነ ተከላካይ ጠበቃ ይቁምልኝ ብላችሁ ፍ/ቤቱን በመጠየቅ ብቻ የምታገኙት የጠበቃ አይነት ነው

2) ዐ/ህግ:- የፌዴራልም ይሁን የክልል ዐ/ህጎች ገንዘብ የመክፈል አቅም ለሌላቸው (የድህነት ማስረጃ ለሚያቀርቡ) ዜጎች በነጻ የፍ/ ብሔር ጉዳዮችን የመሟገትና የሚከራከር ግዴታ እንደተጣለባቸው ሕጉ ይደነግጋል።

3) የሴቶች እና ህጻናት ጸ/ቤት የመሬት እና ይዞታ ጉዳዮችን ሴቶችን ሕጻናትን በመወከል ችሎት ቀርበው መከራከር እንደሚችሉ  በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 20 (5)፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6(4) (8) (11)፣ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥ ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 199/1992 እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች የሥነ- ምግባር ደንብ ቁጥር 57/1992 እንዲሁም የክልሎች ተመሳሳይ ሕጎች ተደንግጓል።


Tip: የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማሕበር ‚የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር, በሕግ ጉዳይ የሚሰሩ ግብረሰናይ ድርጅቶች እና ትምህርት ቤት ያሉባቸው ዩኒቨርስቲዎች ነጻ የሕግ ማዕከላት ነጻ የሕግ ምክር አገልግሎት አንዳንዴም ጠበቃ ሊቀጥሩላችሁ ይችላሉ።

እስቲ ሃሳብ ስጡበት


Firdaweke Aklilu
Attorney At Law at Office

Alternative legal enlightenment
/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!


በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍121
የኢሚግሬሽን አዋጅ ማሻሻያ፤
“የፍርድ ቤትን መሰረታዊ
ስልጣን የሚወስድ ነው” በሚል ተተቸ


ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣንን ለኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ኃላፊ የሚሰጠው የአዋጅ ማሻሻያ፤ “የፍርድ ቤትን መሰረታዊ ስልጣን የሚወስድ ነው” በሚል ተተቸ። ማሻሻያው “ከኢሚግሬሽን ተልዕኮና ባህሪ የሚመነጩ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ እንጂ”፤ ፍርድ ቤት የሚያከውናቸውን ስራዎች “ደርቦ ለመስራት በማሰብ” የቀረበ እንዳልሆነ የመስሪያ ቤቱ አመራሮች ገልጸዋል።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት አመራሮች ይህን የገለጹት፤ ትላንት አርብ ሰኔ 7፤ 2016 በተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደ ይፋዊ የህዝብ ውይይት ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው። የምክር ቤቱ የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጠራው በዚህ ውይይት፤ ከሁለት ሳምንት በፊት ለፓርላማ በቀረቡ ሶስት የአዋጅ ረቂቆች ላይ የህዝብ ጥያቄ እና አስተያየቶች ተስተናግደዋል።

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህግ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አሮን ደጎል፤ በኢሚግሬሽን አዋጅ ማሻሻያ ላይ “ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣንን” በተመለከተ ስለተቀመጠው ድንጋጌ ጥያቄ አንስተዋል። “ከዚህ በፊት የነበረው ድንጋጌ፤ ማንኛውም ሰው ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ ሊታገድ የሚችለው ወይ የመዘዋወር መብቱ ሊገደብ የሚችለው በፍርድ ቤት እና በፍርድ ቤት ውሳኔ ብቻ [ነበር] የሚለው” ሲሉ አቶ አሮን አስታውሰዋል።

ለፓርላማ በቀረበው የአዋጅ ማሻሻያ ላይ ግን “የፍርድ ቤትን መሠረታዊ ስልጣን የመውሰድ አካሄድ ነው የሚታየው” ሲሉ ዳይሬክተሩ ተችተዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን የወከሉት አቶ ኖህ የሱፍ የተባሉ ተሳታፊ፤ “አዋጁ የህግ የበላይነትን በህግ የመገደብ አካሄድ ያለው ይመስላል” ሲሉ ተደምጠዋል።

🔴 ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/13339/

Alternative legal enlightenment
/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!

በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍11
Foolow Alehig/አለሕግ https://vm.tiktok.com/ZMrFUckwf/
የፌደራል_መንግስት_ሠራተኞች_ረቂቅ_አዋጅ_አጭር_ማብራሪያ_1.pdf
468.8 KB
የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ በጠየቃችሁን መሠረት የተላከ

Source: @tikvahethiopia
👍6
የመኖሪያ_ቤት_ኪራይ_ቁጥጥር_እና_አስተዳደር_መመሪያ_ቁጥር_7_2016.pdf
814 KB
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 የፀደቀው ከመጋቢት 24 2016 ዓ.ም ጀምሮ ነው።

ይህን አዋጅ ለማስፈፀም የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር መመሪያ ቁ 7/2016 ወጥቷል::

በዚህ አዋጅ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው አከራይ በተከራይ መልካም ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር ከቤት ማስወጣትም ሆነ ኪራይ መጨመር አይቻልም። አከራዮች ከተከራይ ፍቃድ ውጪ በተከራዩ ላይ ይሄን አድርገው የተገኙ ከሆነ አከራዩ የሶስት ወር የቤት ኪራይ ተቀጪ እንደሚሆን በግልጽ ተቀምጧል። ስለዚህ አከራዮችም ሆነ ተከራዮች ይሄን ተረድተው  መብታቸውን የማስጠበቅ እንዲሁም ግዴታቸውን የመወጣት ሀላፊነት አለባቸው። ሙሉ መመሪያው ከላይ ተያይዟል::
👍111
#ኢትዮጵያ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ፤ " ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ስለማስመለስ " ምን ይላል ?

➡️ #ማንኛውም_ሰው በቀጥታ ሆነ #በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው አሁን ላይ ባለበት ወይም አስቀድሞ በነበረበት ስራ ወይም በሌላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ እና የንብረቱን ወይም የኑሮ ደረጃውን ምንጭ በተመለከተ ምክንያታዊ የሆነ የወንጀል ጥርጣሬ በኖረ ጊዜ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ #ይወረሳል

➡️ ህጋዊ ገቢ እንዳለው የሚያስረዳ የተመዘገበበት ስርዓት የሌለው ወይም ገቢው እነስተኛ በመሆኑ #ከግብር_ነጻ የሆነ ሰው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ ይወረሳል፡፡

➡️ " በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ያፈራው ንብረት " ማለት ፦

° በራሱ ስም የሚገኝ ንብረት፣

° በራሱ ስም ባይሆንም ለራሱ ጥቅም ሲያዝበት ወይም ሲቆጣጠረው የነበረው ንብረት ፣

° የተጠቀመው ወይም ደግሞ ያስወገደው ንብረት፣

° በሽያጭ ፣ በስጦታ ወይም በማንኛውም ሁኔታ #ያስተላለፈውን ንብረት ይጨምራል፡፡

➡️ ዐቃቤ ሕግ " #ምንጩ_ያልታወቀ_ነው " ብሎ የጠረጠረውን ማንኛውንም ንብረት ዝርዝር እና የተገኘበትን አግባብ የሚያሳይ መግለጫ እንዲያቀርብ በፅሁፍ ጥያቄ የቀረበለት ማንኛውም ሰው ጥያቄው በደረሰው በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ለዐቃቤ ህግ ዝርዝር ማስረጃዎችን በማያያዝ በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርበታል።

➡️ የንብረቱን ምንጭ እንዲያስረዳ የተጠየቀው ሰው የንብረቱን ምንጭ ለማስረዳት የሚያቀርበው ማስረጃ ሀጋዊ መሆን አለበት።

ተጨማሪ ....

☑️ አንድ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ አውጥቶ የሚሰራ ነጋዴ ወይም ድርጅት ሕጋዊ ገቢው ተብሎ የሚገመተው ለተገቢው ባለስልጣን በወሩ ወይም በአመቱ ከንግዱ ያገኘሁት ብሎ ያሳወቀው የገቢ መጠን ሲሆን ወይም ተገቢው ታክስ የተከፈለባቸው ገቢዎች ሆነው ሲገኙና የታክስ ደረሰኝ ሲቀርብ ሲሆን ከዚህ ውጪ ህጋዊ ታክስ ያልተከፈለባቸው ገቢዎች ከህጋዊ ገቢ ውጪ ያፈራው ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ተብሎ ሊወሰን ይችላል።

☑️ ምንጩን ሲያስረዳ " ከውጪ የተላከለኝ ገንዘብ ነው " የሚል ማንኛውም ግለሰብ ገንዘቡ በሕጋዊ መንገድ #በባንክ_ሥርዓት ውስጥ ያለፉ ግብይቶች ወይም ክፍያዎች ስለመሆናቸው በተገቢው የባንክ ደረሰኝ አስደግፎ ማቅረብ የሚገባው ሲሆን ከዚህ ውጪ ያለው ግን እንደ ምንጩ ያልታወቀ ገቢ ተደርጎ ይቆጠራል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ #ምንጩ_ያልታወቀ_ንብረት ክስ የሚቀርብበት ጊዜ እና የገንዘብ መጠን ተደንግጓል፡፡

በዚህም አዋጁ ወደኋላ 10 ዓመታት ተመልሶ የሚሠራ ሲሆን ይህንንም ለመክሰስ የ5 ሚሊዮን የገንዘብ ገደብ ተቀምጧል፡፡

ይህ የገንዘብ ገደብ የተቀመጠበት ዋነኛው ምክንያት በአሁኑ ወቅት ላይ በሀገሪቱ ያለውን የሰው ሃይል ፣ የመክሰስ አቅም እና የፋይናንስ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት አነስተኛ የሃብት መጠን ያላቸውን ግለሰቦች በመተው ከፍተኛ ንብረት ያላቸውን ተጠያቂ ለማድረግ እንደሆነ ተብራርቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ሕጉ ወደኋላ (10 ዓመታት) ተመልሶ እንደመስራቱ በሀገሪቱ #ኢኮኖሚ#ማሕበራዊ እና #የፋይናንስ_ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ ያደርሳሉ ተብሎ የሚገመቱትን ግለሰቦችና ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶችን ተጠያቂ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ተብራርቷል።

አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ተጠያቂነት ያለምንም የገንዘብ መጠን ተፈጻሚ ይደረጋል።

ስለ ረቂቅ አዋጁ አጭር ማብራሪያ ⬇️
https://t.me/tikvahethiopia/88313

ረቂቅ አዋጁ⬇️
https://t.me/tikvahethiopia/88314

@tikvahethiopia
👍122😱1
Project Officer Migration Management and Forced Displacement 

At  European Union
👇👇👇👆👆👆
https://etcareers.com/job/49057/project-officer-migration-management-and-forced-displacement/?utm_source=job-alert&utm_medium=email&utm_campaign=job-alert&alert_id=


በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍1
Zemen Insurance Share Company would like to invite qualified and competent applicants to apply for the following vacant post.

Position:4. Legal Officer I

Position:5. Senior Legal Officer

Position:6. Legal Service Manager


How to Apply          
  👇👇👇                                
https://shegerjobs.com/2024/06/19/zemen-insurance-share-company-vacancy-announcement-2/

Deadline: June 22, 2024


በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
Dear Ethiopians, there are 10 selected websites that will help you before taking the IELTS test.

If you know anyone preparing to take the IELTS, tell them to try one of these platforms. I know how excruciating prep can be; these resources helped a lot of peoples.

1. GlobalExam: https://global-exam.com/en

2. IELTS Simon: https://lnkd.in/ehvaNaQh

3. IELTS Advantage: https://lnkd.in/em6ytDkp

4. ielts-exam. net: https://lnkd.in/eyfpkz3R

5. IELTS Tutorials: https://lnkd.in/eRx5ghTP

6. IELTS Mentor: https://lnkd.in/eyCeQVtP

7. IELTS Liz: https://ieltsliz.com

8. IELTS Buddy: https://www.ieltsbuddy.com

9. Road to IELTS: https://lnkd.in/eUVcZjvy

10. IELTS up: https://lnkd.in/eWzP5vec

Via Dagem Worku

በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍3🍓1
Stanford University Knight Hennessy Scholarship

University:  Stanford University
Degree level:  Masters, PhD, MBA, MFA, MD, JD
Scholarship coverage:  Fully Funded
Eligible nationality:  All Nationalities
Award country:  United States

List of Available Study Fields:

•  School of Engineering (All Fields)
•  School of Humanities and Sciences
•  School of Earth, Energy and Environmental Sciences
•  Graduate School of Education
•  School of Medicine
•  School of Law
•  Graduate School of Business
•  School of Medicine Biosciences
•  Continuing Studies.

Official link: https://knight-hennessy.stanford.edu/admission

Deadline: 9 October 2024


Connect with us for updates and more:

📱 TikTok: https://vm.tiktok.com/ZMrFUckwf/
👍52
በአከራይ ተከራይ መመሪያ 7/2016 ዙሪያ አንቀፅ 22 ስለአስተዳደራዊ እርምጃ እና ቅጣት ለግንዛቤ የተወሰደ

አስተዳደራዊ ቅጣት 👇

ማንኛውም አከራይ ሲከራይ የቆየ የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ የመኖሪያ ቤት ያለ አገልግሎት እንዲቀመጥ ያደረገ እንደሆነ:-

ሀ/ ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት 5%፤
ለ/ከሁለት በላይ እስከ ሶስት ዓመት 10%፤
ሐ/ከሶስት በላይ እስከ አራት ዓመት 15%፤
መ/ከአራት እስከ አምስት ዓመት 20%፤
ሠ/ ከአምስት አመት በላይ 25%፤

በንብረት ግብር ክፍያ ላይ ተጨማሪ እንደ ቅጣት እንዲከፍል ይደረጋል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
6
Forwarded from ስለፍትሕ (Entrust and PIN)
አዲሱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ሞዴል ውል.pdf
262.4 KB
👍6
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሚኒስትሮች ም/ቤት ፀድቀው ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እየቀረቡ ያሉ አዳዲስ አዋጆች እናየአዋጅ ማሻሻያ ሃሳቦች በተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ላይ ጫና የሚያደረጉ፤ የአስፈፃሚዉን አካል ሥልጣን ከሚገባው በላይየሚያጠናክሩ፤ በአንፃሩ ደግሞ የዳኝነት አካሉን ሚና ዝቅ የሚያደርጉ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡
👍131
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ-መንግስት ለፌደራል መንግስት ተለይተዉ በተሰጡ ጉዳዮች ሕግ የማዉጣትሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡(ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55)፡፡ ም/ቤቱ ይህንኑ ሓላፊነቱን ሲወጣ እንደማንኛዉም የመንግስትአካል፣ ምናልባትም በበለጠ ትኩረት እና ጥንቃቄ በሕገ-መንግስቱ የተደነገጉትን መርሆች በሙሉ በሚገባ መከተል ይጠበቅበታል፡፡በመሆኑም ፓርላማዉ አዳዲስ ሕጎችን በሚያወጣበት ጊዜም ሆነ ያሉት እንዲሻሻሉ ረቂቅ ሲቀርብለት አዲስ የሚወጣዉም ይሁንየሚሻሻለዉ ሕግ በሃገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘላቂ ሰላም እንዲሁም ዋስትና ያለዉ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን አበርክቶዉ ከፍ ያለመሆኑን ማረጋገጥ ያለበት ከመሆኑም በላይ ሕገ-መንግስቱ የሃገሪቱ የበላይ ሕግ መሆኑን (ሕገ-መንግስት አንቀጽ 9)፤ ሰብዓዊመብቶች ከሰዉ ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ፤ ማይጣሱ እና የማይገፈፉ መሆናቸዉን (ሕገ-መንግስት አንቀጽ10)፤ ይህን ምክር ቤትጨምሮ በማንኛዉም ደረጃ የሚገኙ የፌደራል መንግስትና የክልል ሕገ አዉጪ፤ ሕግ አስፈፀሚ እና የዳኝነት አካሎችበሕገ-መንግስቱ ምዕራፍ ሦስት ስር የተካተቱትን የሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የማክበር እና የማስከበር ግዴታእንዳለባቸዉ (ሕገ-መንግስት አንቀጽ13) እና የመንግስት አሠራር ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን እንዳለበት(ሕገ-መንግስት አንቀጽ 12) ለአፍታም ሊዘነጋ አይገባም፡፡
    ከዚህ አንፃር ባለፉት ጥቂት ወራት በሚኒስትሮች ምክር ቤት እየፀደቁ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እየቀረቡ ያሉ አዳዲስ ሕጎችእና ማሻሻያዎች በም/ቤቱ እየተስተናገዱ ያሉበት ሁኔታ ሕጎቹ ይዘዋቸዉ እየመጡ ካሉት አዳዲስ እና አነጋጋሪ ሃሳቦች አንፃርለዉይይት በቂ ጊዜ በማይሰጥ ጥድፊያ እና ምናልባትም የምክር ቤቱ ዓመታዊ የሥራ ጊዜ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ የቀሩትመሆኑ ብቻ ታሳቢ ያደረጉ ከመሆናቸዉም በላይ በሕጎቹ ወይም በማሻሻያዎቹ ተካተዉ እየቀረቡ ያሉት አዳዲስ ሃሳቦችም በተለያዩየሰብዓዊ መብቶች ላይ ጫና የሚያደርጉ፤የአስፈፃሚዉን አካል ሥልጣን በቀላሉ ባልተገባ መንገድ ጥቅም ላይ እንዲዉል ሰፊ እድልበሚሰጥ ደረጃ የሚያጠናክሩ እና በአንፃሩ ደግሞ የሰብዓዊ መብቶች መከበር የመጨረሻዉ ዋስትና እንደሆነ የሚታመነዉንየዳኝነት አካሉን ሚና ዝቅ የሚያደርጉ መስለው ታይተዋል፡፡
    እነዚህ ሕጎች ወይም ማሻሻያዎች በዋነኛነት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 354/1995ን ለማሻሻልየቀረበዉን የማሻሻያ ረቂቅ እና የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጁን የሚመለከቱ ሲሆን ሌሎች ለም/ቤቱ እየቀረቡ ያሉ በዜጎችመብቶች ላይ ጫና ሊያደርጉ የሚችሉ አዋጆችም ከመጽደቃቸዉ በፊት በቂ ሕዝባዊ ዉይይት እንዲደረግባቸዉ ሰፊ ዕድልእንዲመቻች ድርጅታችን አጥብቆ ይጠይቃል፡፡
https://lhrethiopia.org/new-proclaimation-and-ammendments/
በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
5👍5
በሴራሊዮን ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጃገረዶችን ማግባት እስከ 15 ዓመት እስራት ሊያስቀጣ ነው፤ በኢትዮጵያስ?

የሴራሊዮን ፓርላማ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጃገረዶችን ማግባት እስከ 15 ዓመት እስራት በሚደርስ የወንጀል ጥፋት እና ከ2,000 ዶላር ጋር የሚመጣጠን ቅጣት የሚጥል ህግ አጽድቋል።

በተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) መሰረት በሴራሊዮን ከሚገኙት ወጣት ሴቶች መካከል አንድ ሶስተኛ ያህሉ የተዳሩት 18 ዓመት ሳይሞላቸው ነው።

እንደ ዩኒሴፍ መረጃ በሀገሪቱ 800,000 የሚሆኑ እድሜያቸው ሳይደርስ የተዳሩ ሴቶች ያሉ ሲሆን 400,000 የሚያህሉት ጋብቻ የፈጸሙት ከ15 ዓመታቸው በፊት ነው።

የሴራሊዮን ፓርላማ ያጸደቀው ህግ ከኢትዮጵያ ሲነጻጸር፦

እንደ ዩኒሴፍ መረጃ በኢትዮጵያ ከ15 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ እድሜያቸው ሳይደርስ የተዳሩ ሴቶች ያሉ ሲሆን 6 ሚሊየኑ ጋብቻ የፈጸሙት ከ15 ዓመታቸው በፊት ነው።

በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ መሰረት ለጋብቻ ዝቅተኛው እድሜ ለሁለቱም ጾታዎች 18 ዓመት ሆኖ ተቀምጧል። የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ደግሞ ያለ እድሜ ጋብቻ ላይ ከ3 እስከ 7 ዓመት እስራት የሚደርስ ቅጣት ያስቀምጣል።

@tikvahethmagazine
👍13