አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ፍቺ ከፍርድ ቤት ውጭ፡- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔዎች አጭር ዳሰሳ
በ፦ ተክለኃይማኖት ዳኜ በላይ

ይህ ጽሑፍ የሰበር ሰሚ ችሎት በኮ/መ/ቁ 14290፣ በ31891 እና 102662 ጋብቻ ከተፈጸመ በኋላ ለረጅም ጊዜ ተለያይቶ መኖር እና በዚህ ጊዜ ውስጥ ሌላ ጋብቻ መስርቶ መኖር ፍርድ ቤት መቅረብ ሳያስፈልግ ጋብቻውን ለማፍረስ በቂ እንደሆነ የሰጣቸው ውሳኔዎች የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሰበር ችሎቱ ውሳኔዎች ከሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 50(5)፤ አንቀጽ 55 እንዲሁም አንቀጽ 79(3) ጋር የሚቃረን ነው በማለት ሽሯቸዋል።

ጸሐፊው የሰበር ውሳኔዎቹን እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ከቤተሰብ ሕጉ ከሕገ መንግሥቱ እና ከሌሎች አግባብነት ካለቸው ሐሳቦች ጋር በማገናዘብ የራሱን ሐሳብ ያሰፍራል።

መልካም ንባብ!
https://www.abyssinialaw.com/blog/divorce-out-of-court-a-brief-survey-of-federal-supreme-court-decisions-and-federal-council-decisions
👍16👏3
የመኖሪያ ቤት  አከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ሰኔ አንድ ይጀምራል

የመኖሪያ ቤት  አከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ሰኔ አንድ እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ 1320/2016 ን ለመፈፀም የአከራይና ተከራይ ውል ከሰኔ አንድ ጀምሮ በየወረዳዎቹ ምዝገባ እንደሚጀመር ገልጿል።

የቢሮ ኃላፊዋ  ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ ምዝገባውን ለማካሄድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገናል ብለዋል።

አከራዮች ከተከራዮቻቸው ጋር በመሆን  ከሰኔ አንድ ጀምሮ በየወረዳቸው በመገኘት መመዝገብ እንደሚችሉ ተናግረዋል። 

ምዝገባውን ከስራ ሰአት ውጭ ለማከናወን እንደታቀደም ጠቁመዋል።

አዋጁና መመሪያው የአከራይ እና ተከራይን ሚዛናዊ ተጠቃሚነት የሚያስጠብቅ መሆኑንም ተናግረዋል።

ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ላይ እና የማስፈፀሚያ መመሪያ ላይ ውይይት መካሄዱን አስረድተዋል።
አማራጭ የሕግ እውቀት
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
👍15
#ሞት_ተፈርዶበታል !

ከአባቱ ጋር በገባበት " #የጥቅም_ግጭት " መላው ቤተሰቦቹን በጥይት ገድሎ ሊጨርስ የነበረው ግለሰብ በሞት ተቀጣ።

ተከሳሽ ከፍታ ካፋላ ይባላል።

በጋርዱላ ዞን የሃይበና ቀበሌ ነዋሪ ነው።

ግለሰቡ ቤተሰቦቹ በሚኖሩበት በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ሠገን ገነት ቀበሌ በመሄድ በ4 ቤተሰቦቹ ላይ የጥይት እሩምታ ይከፍታል።

በዚህም ሶስቱን ሲገድል አንዱን አቁስሏል።

በጥይት እሩምታ የገደላቸው ፦
- #አባቱ
- #እናቱ
- #አጎቱ ሲሆኑ የመቁሰል አደጋ የደረሰበት የ9 አመት ታናሽ ወንድሙ ነው።

ግለሰቡ ይህን ፈጽሞ ከአካባቢዉ ቢሰወርም የጸጥታ ኃይሉ ከማህበረሰቡ ጋር ተባብሮ ባደረገዉ ክትትል ከ5 ወራት በኋላ ሊያዝ ችሏል።

ፖሊስም ስራውን አጠናቆ ለፍርድ ቤት አቅርቧል።

ተከሳሹም ፤ ከወላጅ #አባቱ ጋር በገባበት ' የጥቅም ግጭት ' ምክኒያት ወንጀሉን እንደፈጸመ ለፍርድ ቤቱ አምኖ ቃሉን ሰጥቷል።

ይህም ቃሉም ከቀረበበት የሰውና የሰነድ ማስረጃ ጋር ተዳምሮ የፍርድ ሂደቱን ቀላል እንዳደረገዉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

በዚህም በኃላ ጉዳዩን ሲመረምር የነበረዉ የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተከሳሽ ከፍታ ካፋላ #በሞት እንዲቀጣ ወስኗል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
👍252😢2
አለሕግAleHig ️
የመኖሪያ ቤት  አከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ሰኔ አንድ ይጀምራል የመኖሪያ ቤት  አከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ሰኔ አንድ እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ 1320/2016 ን ለመፈፀም የአከራይና ተከራይ ውል ከሰኔ አንድ ጀምሮ በየወረዳዎቹ ምዝገባ…
ማንኛውም የመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራይ በምዝገባ ወቅት ማሟላት ያለባቸው👇

👉በህግ አግባብ የተዘጋጀ የመኖሪያ ቤት
    ውል ሰነድ

👉የአከራይና ተከራይ የነዋሪነት መታወቂያ ፣ የመስሪያ ቤት መታወቂያ ፣ መንጃ ፍቃድ ፣ ፓስፖርት ፣ የጠበቃ ፍቃድ ፣ የሰራተኞች ጡረታ መታወቂያ ፣ የዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ ተማሪ የሙያ ስራ ፍቃድ ኦርጅናል ኮፒ ፤

👉የመኖሪያ ቤት ውሉ የሚመዘገበው በወኪል ከሆነ ህጋዊ ውክልና የሁለት ምስክሮች የታደሰ መታወቂያ ኦርጅናል ኮፒ፤

👉አከራይ የመኖሪያ ቤቱን ለማከራየት የሚያስችል መብት እንዳለው የሚያሳይ ህጋዊ ሰነድ :-

    - የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ

    -  ሰነድ አልባ ይዞታዎች መሆኑን    
      ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ወይም

   - በፍርድ አፈፃፀም የተሸጠ ንብረት  
    ሰነድ ወይም

    - የተከራየው ቤት በውርስ የተገኘ ሆኖ
     ስም ዝውውር ካልተፈፀመ የወራሽነት
     ማረጋገጫ

ኦርጅናል እና ኮፒ ይዘው  መገኘት አለባቸው

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

አማራጭ የሕግ እውቀት
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

ለተከራይ እና አከራይ ሼር ማድረጉን አትርሱ የአለ ሕግ ቤተሰቦቻችን
👍6
ለባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶች እውቅና የሚሰጥና ከዘመናዊ የፍትህ ሥርዓት ጋር እንዲጣጣሙ የሚያስችል ሞዴል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2016፦ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶች እውቅና የሚሰጥና ከዘመናዊ የፍትህ ሥርዓት ጋር እንዲጣጣሙ የሚያስችል ሞዴል ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን የፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ።

የፍትህ ሚኒስቴር "ማኅበረሰብ አቀፍ የፍትህ አገልግሎት ሚና በኢትዮጵያ የፍትህ ዘርፍ" በሚል መሪ ኃሳብ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት አካሂዷል።

በመርኃ ግብሩ የፌደራልና የክልል የፍትህ ዘርፍ አመራሮች እንዲሁም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ተወካዮች ተገኝተዋል።

የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት ግጭቶችን ለማርገብና የተረጋጋ ማኅበረሰብ ለመፍጠር አይነተኛ ሚና አላቸው።

ይሁንና ዘርፉ በፍትህ ሥርዓቱ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርግ ከዘመናዊ የፍትህ ሥርዓቱ ጋር የተጣጣመ በማድረግ ረገድ ክፍተት መኖሩን ነው ያስረዱት።

ይህንን ችግር ለመቅረፍና ዘርፉ ለፍትህ ሥርዓቱ መጎልበት ያለውን ሚና ከግምት በማስገባት የባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶችን ለማጠናከር እየተሰራ ነው ብለዋል።

ይህንንም ተከትሎ አሁን ላይ ዘመናዊው የአዋጅ ሥርዓትን ከባህላዊ የፍትህ ሥርዓት ጋር ማሰናሰን የሚያስችል ሞዴል ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

ሞዴል ረቂቅ አዋጁ የፍትህ ሥርዓቱን በማሳለጥ ረገድ አገራዊ አበርክቶው የላቀ መሆኑን አብራርተዋል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት በበኩላቸው በኢትዮጵያ መደበኛ ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት አገልግሎት ከፍላጎት ጋር መጣጣም አለመቻሉን ገልጸዋል።

ፍርድ ቤቶች ከሰው ሃይል፣ ከመሰረተ ልማትና ከኃብት አኳያ ውስንነት ያለባቸው በመሆኑ በአግባቡ ተደራሽ መሆን እንዳልቻሉ ጠቁመው መሰል ችግሮችን ለመፍታት ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶች ቁልፍ ሚና አላቸው ብለዋል።

ባህላዊ ፍርድ ቤቶች በመደበኛው ፍርድ ቤቶች ላይ የሚፈጠረውን ጫና እንዲቀንስ ከማስቻላቸውም በላይ ዜጎች በቋንቋቸውና በነባራዊ ሁኔታቸው እንዲዳኙ የሚያስችል መሆኑንም አስረድተዋል።

በመሆኑም ዘርፉን ማጠናከር የሁሉም ባለድርሻ አካል ድርሻ ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ከዚህ አኳያ የሚጠበቅበትን ሚና እንደሚጫወት አረጋግጠዋል።

በፍትህ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አማኑኤል ታደሰ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ለሚገኙ የባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶች እውቅና ለመስጠት የተዘጋጀው ሞዴል ረቂቅ አዋጁ ክልሎች ለሚያዘጋጁት ረቂቅ ሕግ መነሻ እንደሚሆን ተናግረዋል።

ሞዴል ረቂቅ አዋጁ በተለይም ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶች ከመሰረታዊ የሰብዓዊ መብት መርህ ጋር እንዳይጣረሱ ለማድረግ ያለመ መሆኑም አክለዋል።

ሞዴል ረቂቅ አዋጁ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶች ለአገራዊ የፍትህ ሥርዓቱ ተጨማሪ አቅም እንዲሆኑና የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ለመደገፍ ያለመ መሆኑም ተናግረዋል።

በውይይት መድረኩ የሲዳማ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት "አፊኒ" በተሞክሮነት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።(ኢዜአ)
አማራጭ የሕግ እውቀት
      👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
👍141
1322 SEZ Technical Correction final መማ 21.pdf
1.8 MB
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፫፻፳፪/፪ሺ፲፮
የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጅ
Proclamation No 1322/2024
Special Economic Zone Proclamation
👍3
ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍ/ሕ/ቁ  2035(2)
Ignorance of the law is no excuse. civil code article 2035(2)


ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!

                                                                                             
 ምንም ውሳኔ ከመወሰንዎ በፊት አማራጭ የሕግ እውቀት ያግኙ::
   
0920666595


👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍8
According to Labour Proclamation No. 1156/2019, what is the minimum working age?
Anonymous Poll
23%
18
75%
15
4%
17
👍13
 
ስለኪራይ ውል

የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት እንደወሰነው "የኪራይ ውል የተለየ ፎርም መከተል እንዳለበት የሚያስገድድ የህግ ድንጋጌ የሌለ በመሆኑ በሁለት ተዋዋይ ወገኖች መካከል የሚፀና ውል ህጋዊ ውጤት ያለው ውል ለመመስረት በሁለቱም መካከል ስምምነት መኖሩ ብቻ በቂ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1719(1),-1930,2898(3) በማጣቀስ በቅፅ 7 በመቁ 25938 አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።

እንዲሁም ደግሞ ከኪራይ ቤቶች አስተዳደር ጋር የተደረገን የኪራይ ውል መሠረት በማድረግ የተያዘ ቤትን ያለአከራይ ፍቃድ ለሌላ ወገን ማስተላለፍ ለኪራይ ውሉ መሠረዝ በቂ ምክንያት ስለመሆኑ በቅፅ 7 በመ/ቁ 24221 ላይ አስገደዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
#ethiolawtips
https://t.me/lawsocieties
👍8
Forwarded from ስለፍትሕ (Lawyer Mikias Melak 🔊 ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ)
አስደሳች ዜና!
🔴🔴 የአጭር ጊዜ ስልጠና!🔴🔴
ሳያመልጥዎ ቶሎ ይመዝገቡ!
👇👇👇👇👇👇👇
https://forms.gle/HthGiWNazet4tMBF7

መስራት በተሰኘው በገበያ ፣ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን እና በአጋሮቻቸው ጥምረት ለተመሠረተው ፕሮግራም ከዘ-ኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዪዝ አሶሲዬሽን ጋር በመተባበር ነፃ ስልጠና አዘጋጅተዋል
ስልጠናውም በቀላሉ በስልኮ ቴለግራም ቦት (TELEGRAM BOT) ላይ የሚሰጥ ሲሆን ሲጨርሱ ባጅና ሰርተፍኬት ያገኛሉ !

ይህ እድል ለኢትዮጵያ ወጣቶች

በነፃና ባሉበት ቦታ ሆነው እንዲከታተሉት የቀረበ ሲሆን የዲጂታል ችሎታዎን ለማሻሻል እና የ ኢ-የመማሪያ ምህዳር እንዲያገኙ ዕድል ይሰጣል፡፡

መርጃውን ከየት አገኙት?👇👇👇

ከዘ-ኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሲዬሽን

ሪፈራል ኮድዎን  ያስገቡ:- 👉 0103

ስልጠናውን እና በሰርተፊኬት የሚያገኙት
በዚህ ፎርም ሲመዘገቡ ብቻ እንደሆነ ማሳወቅ እንፈልጋለን!!

ሲመዝገቡ ለሚጠይቅዎት ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከዚህ በታች የተሰጠውን መልስ ያስገቡ፣

መርጃውን ክየት አገኙት?
መልስ👇👇👇👇
ከዘ-ኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሲዬሽን

ሪፈራል ኮድዎን በ IEYA**** ቅርጸት ያስገቡ:-
መልስ👉👉 0103


እጅግ በጣም ጠቃሚ እና የስራ እድል የሚፈጥር ስልጠና ነው ተጠቀሙበት።

Your referral code is 0103.

Here is the link👇👇👇👇

https://forms.gle/HthGiWNazet4tMBF7


በጎግል (Google) እና ቴሌግራም (Telegram) ቦት ላይ መመዝገብ አለቦት።
መረጃዎን በጎግል(Google) ከሞሉ በኋላ ወደ ቴሌግራም ቦት የሚመራዎትን አገናኝ ሊንክ (Link) ያገኛሉ እና ኮርሱን ይውሰዱ።
👍151
AHRE is looking for a qualified trainer to provide training in Amhara region Bahir Dar city. Find the details of the call with the following link http://www.ahrethiopia.org/post_detail/269
Forwarded from አለሕግAleHig ️
የጋብቻ ምዝገባ-ግለሰባዊ ጥቅሞች

ጋብቻ ለመከሰቱ ህጋዊ ማስረጃ በመሆን

ጋብቻዉ ህጋዊ መሆኑን ለማረጋገጥ፣

የተጋቢዎቹን ዝምድና እና ግንኙነት ለማረጋገጥ፣

የጋብቻ ውጤት ለሆኑት ህፃናት በቤተሰብነት የመጠበቅ ህጋዊ መብትን ለማረጋገጥ፣

ህጋዊ ወራሽነትን ለማረጋገጥ፣

ለቤተሰብ ድጎማ ለመንግስት ጥያቄ ለማቅረብ፣

ከተጋቢዎች አንዳቸው ቢሞቱ ቋሚው የኢንሹራንስ ጥያቄን ለማቅረብ፣

ጋብቻ በሚፈርስበት ጊዜ የልጆችን አስተዳደግ ለመወሰን፣

ወደ ውጪ ሃገር ለመጓጓዝ ፓስፖርት የማግኘት ፈቃድን ለማቅረብ፣

የልጆችን ህጋዊነት ለማረጋገጥ፣

የራስን ልጆች ህጋዊነት ለመመስረት እንዲሁም ከሌላ የተወለዱትን ለማስመዝገብ፣

የዜግነት ቅያሬን ለመጠየቅ፣

ጋብቻዉ የተፈፀመበት ጊዜ እና ቦታ በማሳወቅ ህጋዊ መረጃ በመሆን፣

Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!

በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍161👏1
ገንዘብ ስለሌላችሁ ጠበቃ ማቆም ላቃታችሁ ወገኖቼ እስቲ በነፃ ጠበቃ እንዴት እንደምታገኙ ልጠቁማችሁ


1) ተከላካይ ጠበቃ;-ይህ በፍ/ቤቶች የሚታወቅና ጉዳያችሁ የወንጀል ከሆነ ተከላካይ ጠበቃ ይቁምልኝ ብላችሁ ፍ/ቤቱን በመጠየቅ ብቻ የምታገኙት የጠበቃ አይነት ነው

2) ዐ/ህግ:- የፌዴራልም ይሁን የክልል ዐ/ህጎች ገንዘብ የመክፈል አቅም ለሌላቸው (የድህነት ማስረጃ ለሚያቀርቡ) ዜጎች በነጻ የፍ/ ብሔር ጉዳዮችን የመሟገትና የሚከራከር ግዴታ እንደተጣለባቸው ሕጉ ይደነግጋል።

3) የሴቶች እና ህጻናት ጸ/ቤት የመሬት እና ይዞታ ጉዳዮችን ሴቶችን ሕጻናትን በመወከል ችሎት ቀርበው መከራከር እንደሚችሉ  በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 20 (5)፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6(4) (8) (11)፣ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥ ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 199/1992 እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች የሥነ- ምግባር ደንብ ቁጥር 57/1992 እንዲሁም የክልሎች ተመሳሳይ ሕጎች ተደንግጓል።


Tip: የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማሕበር ‚የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር, በሕግ ጉዳይ የሚሰሩ ግብረሰናይ ድርጅቶች እና ትምህርት ቤት ያሉባቸው ዩኒቨርስቲዎች ነጻ የሕግ ማዕከላት ነጻ የሕግ ምክር አገልግሎት አንዳንዴም ጠበቃ ሊቀጥሩላችሁ ይችላሉ።

እስቲ ሃሳብ ስጡበት


Firdaweke Aklilu
Attorney At Law at Office

Alternative legal enlightenment
/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!


በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍121
የኢሚግሬሽን አዋጅ ማሻሻያ፤
“የፍርድ ቤትን መሰረታዊ
ስልጣን የሚወስድ ነው” በሚል ተተቸ


ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣንን ለኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ኃላፊ የሚሰጠው የአዋጅ ማሻሻያ፤ “የፍርድ ቤትን መሰረታዊ ስልጣን የሚወስድ ነው” በሚል ተተቸ። ማሻሻያው “ከኢሚግሬሽን ተልዕኮና ባህሪ የሚመነጩ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ እንጂ”፤ ፍርድ ቤት የሚያከውናቸውን ስራዎች “ደርቦ ለመስራት በማሰብ” የቀረበ እንዳልሆነ የመስሪያ ቤቱ አመራሮች ገልጸዋል።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት አመራሮች ይህን የገለጹት፤ ትላንት አርብ ሰኔ 7፤ 2016 በተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደ ይፋዊ የህዝብ ውይይት ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው። የምክር ቤቱ የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጠራው በዚህ ውይይት፤ ከሁለት ሳምንት በፊት ለፓርላማ በቀረቡ ሶስት የአዋጅ ረቂቆች ላይ የህዝብ ጥያቄ እና አስተያየቶች ተስተናግደዋል።

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህግ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አሮን ደጎል፤ በኢሚግሬሽን አዋጅ ማሻሻያ ላይ “ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣንን” በተመለከተ ስለተቀመጠው ድንጋጌ ጥያቄ አንስተዋል። “ከዚህ በፊት የነበረው ድንጋጌ፤ ማንኛውም ሰው ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ ሊታገድ የሚችለው ወይ የመዘዋወር መብቱ ሊገደብ የሚችለው በፍርድ ቤት እና በፍርድ ቤት ውሳኔ ብቻ [ነበር] የሚለው” ሲሉ አቶ አሮን አስታውሰዋል።

ለፓርላማ በቀረበው የአዋጅ ማሻሻያ ላይ ግን “የፍርድ ቤትን መሠረታዊ ስልጣን የመውሰድ አካሄድ ነው የሚታየው” ሲሉ ዳይሬክተሩ ተችተዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን የወከሉት አቶ ኖህ የሱፍ የተባሉ ተሳታፊ፤ “አዋጁ የህግ የበላይነትን በህግ የመገደብ አካሄድ ያለው ይመስላል” ሲሉ ተደምጠዋል።

🔴 ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/13339/

Alternative legal enlightenment
/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!

በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍11
Foolow Alehig/አለሕግ https://vm.tiktok.com/ZMrFUckwf/