አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Women have the fundamental right to move freely and safely from one place to another, including in their use of public transportation services.

ሴቶች የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎቶችን መጠቀምን ጨምሮ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በነፃነት እንዲሁም ደህንነታቸው ተጠብቆ የመንቀሳቀስ መሰረታዊ መብት አላቸው።
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
ለ:- ሁሉም መገናኛ ብዙሃን ተቋማት በሙሉ
አዲስ አበባ

ጉዳዩ:- የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጠን ስለመጠየቅ
ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ተቋማችን የፌዴራል የፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት ከተለያዩ ባለ ድርሻ ካላት ጋር በመሆን ʺበኢትዮጵያ እና ሶማሌ ላንድ መካከል የባሕር ዳርቻ በሊዝ ለመጠቀም የተደረገው የመግባቢያ ስምምነት አለም አቀፍ ሕጋዊ ተቀባይነት እና አንደምታˮ በሚል ርዕስ የውይይት መነሻ ጥናት ጽሑፍ የሚቀርብበትና ውይይት የሚደረግበት መድረክ የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ ቸርቸር ጎዳና የሚገኘው ግራንድ ኤሊያና ሆቴል የሚያካሄድ ይሆናል፡፡
በመሆኑም የተለያዩ የፍትሕ ዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢንስቲትዩታችን ባልደረቦች፣ ዳኞች፣ አቃቤ-ህጎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የሕግ ባለሙያዎች የሚገኙበትን መርሃ ግብር ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ቸርቸር ጎዳና በሚገኘው ግራንድ ኤሊያና ሆቴል በመገኘትና ሪፖርተሮችን ወደ ስፍራው በመላክ እንዲዘግቡልንና እና በሚዲያችሁ እንድታሰራጩልን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ይግባኝ ማስፈቀጃ/ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድ የሚቀርብ አቤቱታ
#በሕጉ የተቀመጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድ የሚቀርብ አቤቱታ
አንድ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈበት ምክንያት በቂ መሆኑን ሲረዳ ይግባኙ እንዲቅርብ ሊፈቅድ እንደሚገባ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 326/1/ ስር ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ፍ/ቤቱ የቀረበለት ምክንያት በቂ መሆን አለመሆኑን በአግባቡ ሊመረምረው ይገባል፡፡ በእርግጥ በቂ ምክንያት የሚባሉት ነገሮች ሕጉ ዘርዝሮ ያላስቀመጣቸው በመሆኑ ለመወሰን አስቸጋሪ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም የምክንያቱ በቂ መሆን አለመሆን በእያንዳንዱ ጉዳይ ከሚቀርቡ ፍሬ ነገሮች ጋር ተገናዝበው ሊመዘኑ ይገባል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 38145 ቅጽ 8፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 326/1/
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ መሠረት ለአንድ ፍርድ ቤት መዝገብ ሹም የተሰጠው ሥልጣን ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ማለፍ አለማለፉን በመመልከት ይግባኝ መዝገቡ እንዲከፈት ማድረግ ሲሆን ይግባኙ ጊዜውን ጠብቆ ያልቀረበ ከሆነ ማመልከቻውን መመለስ፣ ማመልከቻው የተመለሰበት ወገን የይግባኝ ጊዜው ያለፈበት ሕጋዊ ምክንያት ካለው ማስፈቀጃ አቤቱታውን በማቅረብ ይኸው ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድለት ራሱን የቻለ አቤቱታ አቅርቦና ይህ መዝገብ ተከፍቶ ጉዳዩ ለችሎት ቀርቦ ችሎቱ የይግባኝ ማስፈቀጃውን በመመርመር በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 መሠረት ተገቢ ነው ያለውን ትእዛዝ የሚሰጥበት ነው፡፡
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 ድንጋጌዎች ጋር አንድ ላይ ሲነበቡ የመዝገብ ቤት ሹም ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለችሎት እንዲቀርብ የመፍቀድ ስልጣን የሌለው መሆኑን የሚያሳዩ ሲሆን ፋይሉ ተከፍቶ ቀርቦ ከሆነም ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ ይግባኙ የቀረበው ጊዜው ከአለፈ በኋላ ነው በማለት መዝገቡን ከመዝጋት የሚከለክለው አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 61843 ቅጽ 11፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 324-326
የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎች ድምጽ ገጽ ተገኘ
#የሕግመረጃ #አለሕግ #Alehig
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
የትዳር አጋሩን የተለያየ የሰውነት ክፍል በቢላዋ በመውጋት ህይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ተከሳሽ በፅኑ አስራት ተቀጣ

ከሌላ ወንድ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለሽ በሚል ምክንያት የትዳር አጋሩን በቢላዋ ጭቅላቷን፣ አንገቷን፣ ፊቷን፣ የግራ ክንዷንና ጣቷን፣ ደረቷንና ጀርባዋን በመውጋት የገደለው ግለሰብ በፅኑ እስራት መቀጣቱን የፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ስሜነህ ግርማ በለጠ የተባለው ተከሳሽ ሕዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 2፡20 ሲሆን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስኮ ሰፈረ ወርቅ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው የትዳር አጋሩ የሆነችው ሟች ማህሌት ፍቃዱ ላይ ወንጀሉን የፈፀመ መሆኑ ተገልጿል።

ግልሰቡ ይህንን በማድረጉ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ የቆየ ሲሆን ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ ባለማቅረቡና የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ምክንያት ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ነው በማለት ተከሳሽ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል።
#TikvahethMagazine
#አለሕግ #Alehig
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
የህዝብ ሮሮ አሁንም የሚሰማበት ተቋም
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
ፓስፖርት ፈልገው ወይም በሥራ ምክንያት ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጎራ ካሉ ረዥም ሰልፍ እና መጨናነቅ ማየት የተለመደ ነው። የሰልፍ አሰላፊዎች ዱላም ሊያጋጥም ይችላል።
ወጣት፣ ሴት፣ ወንድ፣ ልጅ ያዘሉ እናቶች እንዲሁም «ፓስፖርት ፈልገው ነው?» እያሉ እግር በእግር የሚከተሉ ሕገወጥ ደላሎችም በአካባቢው ውር ውር ይላሉ። የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደቱን ለመመልከት በመሥሪያ ቤቱ የተገኙት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎችም ይህንን መመልከት ችለዋል፣ ሆኖም በወቅቱ መረጃ ለመሰብሰብ ያደረጉት ሙከራ በፖሊሶች ክልከላ ምክንያት አልተሳካም።
አገልግሎቱ 24 ሰዓት የፓስፖርት ህትመትና በበይነ መረብ ምዝገባ አሠራር ዘርግቻለሁ ቢልም አሁንም በርካታ ተገልጋዮችን አገልግሎቱ ደጃፍ ላይ መመልከት አልቀረም።
ተገልጋዮች ዐሻራ ለመስጠት እና ፎቶ ለመነሳት በመሥሪያ ቤቱ መገኘት ግዴታቸው በመሆኑ ከተለያዩ አካባቢዎች መጥተው...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=121413
ሳይናዘዝ የሞተ ሰዉ ወራሾች ተዋረድ(hierarchy of intestate succession)

በ/ፍ/ሕ/ቁ አንቀፅ 842 መሰረት ልጆች የመጀመሪያ ደረጃ የሟች ወራሾች ናቸው። ወራሾቹም የሟችን ድርሻ እኩል እንደሚካፈሉ ይሄ ድንጋጌ ያሳያል።  ከልጆቹ አንዱ ሞተዉ እንደሆነና ልጆች አፍርተው እንደሆነ ልጆቻቸውን በሟች እግር ተተክተዉ እንደሚወርሱ የዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ 3 ያመለክታል።

ሟች ምንም አይነት ወደታች የሚቆጠር ተወላጆች ከሌሉት አባት እና እናቱ በሁለተኛ ደረጃ ወራሽነት ይጠራሉ። እናትና አባትም የሟችን ንብረት እኩል እንደሚካፈሉ ከፍ/ሕ/ቁ 843 እና 844(1) መገንዘብ ይቻላል። ከሟች ወላጆች አንዱ ቀድመዉ የሞቱ እንደሆነ ልጆቻቸው ወይም የነርሱ ተወካዮች በእነርሱ እግር ተተክተው ይወርሳሉ።

በሦስተኛ ደረጃ ወራሽነት አያቶች የሚጠሩ ሲሆን ይህም የሚሆነው ሟች ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ወይም አባትና እናት ወይም የነርሱ ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ከሌለዉ እንደሆነ ከ/ፍ/ሕ/ቁ 845(1) መገንዘብ ይቻላል።

ከላይ የተጠቀሱት ወላጆችም ሆነ ተወላጆች በማይኖሩበት ጊዜ ቅድመ-አያቶች በአራተኛ ደረጃነት ለዉርስ እንደሚጠሩ ከፍ/ሕ/ቁ 847 እንገነዘባለን።

በመጨረሻም ምንም  አይነት ዘመዶች የሌሉ እንደሆነ የሟችን ሀብት የወራሽነት መብት ለመንግስት/ሐገር ይተላለፋል።

በሕሊና ጌታቸው የሕግ ቢሮ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
Forwarded from ሕግ ቤት
ውጤትዎን ይመልከቱ!

በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።

ውጤትዎን ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://result.ethernet.edu.et/

#tikvahuniversity
#ይህ ሕግ ለሁሉም የሚሰራ ሕግ ነው። የግል ሆነ የመንግሥት ሠራተኛ ተግባራዊ የሚሆን መብት ነው።
#የማንኛውም ሠራተኛ ደመወዙ
1. በሠራተኛው ስምምነት ወይም
2. በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይም
3. በሕግ በተደነገገው መሠረት ካልሆነ በስተቀር ሊያዝ ወይም ሊቆረጥ አይችልም።
#ይግባኝምክረሕግ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
አፋጣኝ መፍትሔ የሚሻው የዕገታ ወንጀል
***************
(ኢ ፕ ድ)
... ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር (Enforced Disappearance) ወንጀል እየጨመረ መጥቷል።

የሰዎች በታጣቂዎች የመታገት ዜና እንግዳ መሆኑ ከቀረ ሰነባብቷል። ክስተቱም በተወሰኑ መጥፎ ዕጣ በገጠማቸው ሰዎች ላይ የሚከሰት ሳይሆን፣ በተለያዩ አካባቢዎች በተደጋጋሚ እና በብዛት የሚያጋጥም ስጋት ሆኗል።

እንደ ሀገር ዕገታ ተፈጸመ ሲባል መስማት የተለመደ ወደ መሆን ተሻግሯል፡፡ የጭነትም ሆነ የሰው መጓጓዣዎች የዕገታ ሰለባ ስለመሆናቸው በሰፊው ይሰማል፡፡ ከኢንዱስትሪዎች እስከ ቤተ እምነቶች የዕገታ ወንጀል ተቃጣባቸው መባሉ ተለ ምዷል ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=121860
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ሳይመዘገብ በተወካይ አማካይነት የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል ውሉ ስለመደረጉ በተወካዩ ታምኖ ሆኖም ወካዩ ውል መኖሩን ከካደ ህጋዊ ውጤት አይኖረውም። ውሉ ፈርሶ ተዋዋዮች ወደነበሩበት መመለስ ይኖርባቸዋል።

ሰ/መ/ቁጥር 215444 | ጥቅምት 02 ቀን 2015 ዓ/ም


👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
Forwarded from ሕግ ቤት
ሰ/መ/ቁጥር 220553 ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ/ም
ከተሽከርካሪ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ተከሳሽ ጉድለት ያለበትን ተሽከርካሪ ስላስረከበኝ በተሽከርካሪው ሰርቼ ማግኘት ያለብኝን ገቢ እንዲከፍለኝና ውሉ እንዲሰረዝ በሚል በከሳሽ የተጠየቀ ዳኝነት እንደውሉ ባለመፈጸሙ ምክንያት ለደረሰ ጉዳት ካሳ እንዲከፈልና እና ውሉ እንዲሰረዝ (actions for cancellation of a contract and damage) የቀረበ ክስ በመሆኑ በክሱ ላይ ተፈጻሚነት ያለዉ የይርጋ ጊዜ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1845 ስር የተደነገገዉ የ 10 ዓመት የይርጋ ጊዜ እንጂ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2298 ስር የተደነገገዉ አይደለም።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የትምህርት_ማስረጃ_ማረጋገጫ_እና_የአቻ_ግመታ_መመሪያ_990.pdf
5.5 MB
Educational Credentials Authentication and Equivalency Directive No 990/2024
ትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ