አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ይግባኝ ማስፈቀጃ/ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድ የሚቀርብ አቤቱታ
#በሕጉ የተቀመጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድ የሚቀርብ አቤቱታ
አንድ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈበት ምክንያት በቂ መሆኑን ሲረዳ ይግባኙ እንዲቅርብ ሊፈቅድ እንደሚገባ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 326/1/ ስር ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ፍ/ቤቱ የቀረበለት ምክንያት በቂ መሆን አለመሆኑን በአግባቡ ሊመረምረው ይገባል፡፡ በእርግጥ በቂ ምክንያት የሚባሉት ነገሮች ሕጉ ዘርዝሮ ያላስቀመጣቸው በመሆኑ ለመወሰን አስቸጋሪ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም የምክንያቱ በቂ መሆን አለመሆን በእያንዳንዱ ጉዳይ ከሚቀርቡ ፍሬ ነገሮች ጋር ተገናዝበው ሊመዘኑ ይገባል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 38145 ቅጽ 8፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 326/1/
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ መሠረት ለአንድ ፍርድ ቤት መዝገብ ሹም የተሰጠው ሥልጣን ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ማለፍ አለማለፉን በመመልከት ይግባኝ መዝገቡ እንዲከፈት ማድረግ ሲሆን ይግባኙ ጊዜውን ጠብቆ ያልቀረበ ከሆነ ማመልከቻውን መመለስ፣ ማመልከቻው የተመለሰበት ወገን የይግባኝ ጊዜው ያለፈበት ሕጋዊ ምክንያት ካለው ማስፈቀጃ አቤቱታውን በማቅረብ ይኸው ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድለት ራሱን የቻለ አቤቱታ አቅርቦና ይህ መዝገብ ተከፍቶ ጉዳዩ ለችሎት ቀርቦ ችሎቱ የይግባኝ ማስፈቀጃውን በመመርመር በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 መሠረት ተገቢ ነው ያለውን ትእዛዝ የሚሰጥበት ነው፡፡
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 ድንጋጌዎች ጋር አንድ ላይ ሲነበቡ የመዝገብ ቤት ሹም ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለችሎት እንዲቀርብ የመፍቀድ ስልጣን የሌለው መሆኑን የሚያሳዩ ሲሆን ፋይሉ ተከፍቶ ቀርቦ ከሆነም ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ ይግባኙ የቀረበው ጊዜው ከአለፈ በኋላ ነው በማለት መዝገቡን ከመዝጋት የሚከለክለው አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 61843 ቅጽ 11፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 324-326
የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎች ድምጽ ገጽ ተገኘ
#የሕግመረጃ #አለሕግ #Alehig
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig