አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
አለሕግAleHig ️
Public #Access To #Legal #Information In Ethiopia 🎙Key Note Speaker: Mikias Melak Public access to legal information in Ethiopia encompasses the availability and accessibility of legal resources like laws, cases, policies, and institutions for the general…
To overcome these challenges, diverse initiatives by the government, civil society, and development partners aim to enhance public access to legal information. The Ethiopian Institutions of Ombudsman (EIO) leads the implementation of the 2008 Freedom of Expression and Access to Information Proclamation, monitoring progress and ongoing efforts. Additionally, Public Information Noble (PIN) Ethiopia collaborates with IEYA ongoing advocacy to ATI focuses on training, manuals, procedures, and awareness campaigns to address both demand and supply aspects of access to information.

The Alehig/አለሕግ platform is set to contribute significantly by providing searchable databases of Ethiopian laws, cases, and legal resources. It also includes audio files tailored for lawyers with visual impairments, ensuring inclusivity in legal information access.
Mikias Melak Birhanie
Attorney & consultant at law
https://t.me/lawsocieties
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚደረግ
የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱ
አንድ ሀገር በኢኮኖሚ እድገት የሚያሳየው፣ ዜጎች በትጋት ምርታማ (productive) ሆነው ስራቸውን መስራት ሲችሉ እና በአንፃሩ መብትና ጥቅማቸው በህግ አግባብ መከበር ሲችል ነው። በአሰሪና ሰራተኞች መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት ለማስተዳደር ሁለቱንም አካል ሊገዛ የሚችል ህግ መውጣት እንዳለበት እሙን ነው። ሠራተኞችና አሠሪዎች የየራሳቸውን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅና ግዴታዎቻቸውን በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችላቸው የኅብረት ስምምነት ድርድር በማድረግ፤ በመካከላቸው የሚነሱ የወልም ሆነ የግል የሥራ ክርክሮች፣ የማኅበራዊ ምክክር ሥርዓትን ጨምሮ በተጨማሪ አማራጭ መድረኮች በተቀላጠፈ ሁኔታ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ነው። በመሆኑም መሠረታዊ የሥራ ላይ መብቶችንና ግዴታዎችን ለመጠበቅ እንዲቻል የአሰሪና ሰራተኛ ህግ በኢትዮጵያ ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል፡፡
በዚህ አጭር ጽሁፍም በግል በተቋቋሙ ድርጅቶችና መንግስታዊ በሆኑ የልማት ድርጅቶች ተቀጥረው በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚነት ባለው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ ተደንግጎ የሚገኘውን የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱን እንመለከታለን።
የሰራተኞች ቅነሳ መቼ ይደረጋል?
የሰራተኞች ቅነሳ በአንድ ድርጅት ውስጥ ሊደረግ የሚችለው የድርጅቱን ድርጅታዊ አቋም ወይም የሥራ እንቅስቃሴ በሚመለከት በሚከተሉት ምክንያቶች የሥራ ውል ሲቋረጥ ነው:-
አለሕግAleHig ️
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚደረግ የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱ አንድ ሀገር በኢኮኖሚ እድገት የሚያሳየው፣ ዜጎች በትጋት ምርታማ (productive) ሆነው ስራቸውን መስራት ሲችሉ እና በአንፃሩ መብትና ጥቅማቸው በህግ አግባብ መከበር ሲችል ነው። በአሰሪና ሰራተኞች መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት ለማስተዳደር ሁለቱንም አካል ሊገዛ የሚችል ህግ መውጣት እንዳለበት እሙን ነው።…
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚደረግ
የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱ
አንድ ሀገር በኢኮኖሚ እድገት የሚያሳየው፣ ዜጎች በትጋት ምርታማ (productive) ሆነው ስራቸውን መስራት ሲችሉ እና በአንፃሩ መብትና ጥቅማቸው በህግ አግባብ መከበር ሲችል ነው። በአሰሪና ሰራተኞች መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት ለማስተዳደር ሁለቱንም አካል ሊገዛ የሚችል ህግ መውጣት እንዳለበት እሙን ነው። ሠራተኞችና አሠሪዎች የየራሳቸውን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅና ግዴታዎቻቸውን በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችላቸው የኅብረት ስምምነት ድርድር በማድረግ፤ በመካከላቸው የሚነሱ የወልም ሆነ የግል የሥራ ክርክሮች፣ የማኅበራዊ ምክክር ሥርዓትን ጨምሮ በተጨማሪ አማራጭ መድረኮች በተቀላጠፈ ሁኔታ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ነው። በመሆኑም መሠረታዊ የሥራ ላይ መብቶችንና ግዴታዎችን ለመጠበቅ እንዲቻል የአሰሪና ሰራተኛ ህግ በኢትዮጵያ ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል፡፡
በዚህ አጭር ጽሁፍም በግል በተቋቋሙ ድርጅቶችና መንግስታዊ በሆኑ የልማት ድርጅቶች ተቀጥረው በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚነት ባለው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ ተደንግጎ የሚገኘውን የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱን እንመለከታለን።
የሰራተኞች ቅነሳ መቼ ይደረጋል?
የሰራተኞች ቅነሳ በአንድ ድርጅት ውስጥ ሊደረግ የሚችለው የድርጅቱን ድርጅታዊ አቋም ወይም የሥራ እንቅስቃሴ በሚመለከት በሚከተሉት ምክንያቶች የሥራ ውል ሲቋረጥ ነው:-
• ሠራተኞች የተሰማሩባቸው ሥራዎች በከፊልም ሆነ በሙሉ በቀጥታና ለዘለቄታው የሚያስቆም የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ሁኔታ ሲከሰት፤
• በአዋጁ አንቀጽ 18(5) እና (6) ላይ የተቀመጡት ከስራ ውል የሚመነጩ መብቶችና ግዴታዎች ለጊዜያዊ የሚታገዱበት ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ አሠሪው በሚያመርታቸው ምርቶች ወይም በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተፈላጊነት መቀነስ ምክንያት የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ በመቀዝቀዙ ወይም ትርፍ እየቀነሰ በመሄዱ የሥራ ውል ማቋረጥ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፤
• የድርጅቱን ምርታማነት ለማሳደግ የአሠራር ዘዴዎችን ለመለወጥ ወይም በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሲባል የሚደረግ የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ውሣኔ ናቸው፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ነው ሊያስብል የሚችለው ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ቁጥራቸው ከድርጅቱ ሠራተኞች ቢያንስ ከመቶ አሥር የሚያህለውን ወይም የሠራተኞች ቁጥር (የአንድ አመት አማካኝ የሰራተኞች ቁጥር) ከሀያ እስከ ሀምሳ በሆነበት ድርጅት ቢያንስ አምስት ሠራተኞችን የሚመለከት ከአሥር ተከታታይ ቀናት ላላነሰ ጊዜ የሚቆይ የሥራ ውል መቋረጥ ሲከሰት እንደሆነ በአስሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 29 ላይ በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ሂደት
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት የሰራተኞች ቅነሳ ሲደረግ አሰሪ በራሱ ጊዜ የፈለገውን ሰራተኛ መቀነስ የማይችል ሲሆን ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች የሰራተኞች ቅነሳ ሲደረግ በመጀመሪያ አሠሪው ከሠራተኞች ማኅበር ወይም ተወካይ ጋር በመመካከር የሥራ ችሎታ ያላቸውና ከፍተኛ የምርት ውጤት የሚያሳዩ ሠራተኞች በሥራቸው ላይ እንዲቆዩ ያደርጋል ወይም ከማይቀነሱ ሰራተኞች መካከል ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን በድርጅቱ ውስጥ ተመሳሳይ የሥራ ችሎታ ያላቸውና ተመሳሳይ የምርት ውጤት የሚያመርቱ ሠራተኞች በሚኖሩ ጊዜ የሰራተኞች ቅነሳ የሚደረገው በሚከተለው ቅደም ተከተል መሠረት ይሆናል:-
1. በድርጅቱ ውስጥ ለአጭር ጊዜ ያገለገሉ ሠራተኞች፤
2. አነስተኛ ቁጥር የሆነ ጥገኞች ያሏቸው ሠራተኞች፤
3. ከተራ ቁጥረ (4) እስከ (7) ከተዘረዘሩት የሠራተኛ ክፍሎች ውጭ የሆኑ ሠራተኞች ቅነሳው በመጀመሪያ ደረጃ የሚመለከታቸው ይሆናል፤
4. አካል ጉዳተኛ የሆኑ ሠራተኞች፤
5. በድርጅቱ ሳሉ በሥራ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሠራተኞች፤
6. የሠራተኞች ተጠሪዎች፤
7. ነፍሰጡር ሠራተኞች ወይም ከወለዱ እስከ 4 ወር ድረስ የሆናቸው ሴት ሠራተኞች ናቸው፡፡
በልዩ ሁኔታ የኮንስትራክሽን ስራ ማለትም ሕንጻ፣ መንገድ፣ የባቡር ሐዲድ፣ የባሕር ወደብ፣ የውሃ ግድብ፣ ድልድይ፣ የመሣሪያ ተከላና ሌላም ተመሳሳይ ሥራ የመሥራት የመለወጥ፣ የማስፋፋት፣ የማደስና የመጠገን ሥራ ተከታታይነት እያለቀ ሲሄድ የሥራው መጠን በመቀነሱ ምክንያት ተቀጥረው በሚሰሩ ሠራተኞች ላይ ቅነሳ ሲደረግ አሠሪው በዚህ ከላይ የተመለከቱትን የሠራተኞች ቅነሳ ሥነ ሥርዓት መከተል አይጠበቅበትም፡፡ ነገር ግን ሰራተኞች የተቀጠሩበት ሥራ ከማለቁ በፊት ከሆነ የሰራተኛ ቅነሳ ሲደረግ በአዋጁ ላይ የተገለጸውን ሥነ-ሥርአት መከተል የግድ ይለዋል። በተጨማሪም ቅነሳ ለማካሄድ አሰሪው የሁለት ወር ቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሚቀነሱት ሰራተኞች የመስጠት ግዴታ አለበት (አንቀፅ 35/1/መ)፡፡ እንዲሁም ድርጅቱ የሚወስደው እርምጃ፣ ከሰራተኞች ጋር የህብረት ስምምነት ካለው ይህንኑ እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በዚህ ረገድ የሚያወጣውን መመሪያ ያከበረ መሆን አለበት፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ያለው ውጤት
አንድ ሰራተኛ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 29 መሰረት በሰራተኞች ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ ሲቋረጥ የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት አለው። የስራ ስንብት ክፍያ መጠንን በተመለከተ ለመጀመሪያው የአንድ ዓመት አገልግሎት የሠራተኛው ማለትም የተቀነሰው ሰራተኛ የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዙ በ30 ተባዝቶ ይከፈለዋል፡ከአንድ ዓመት በታች አግልግሎ ለተቀነሰ ሰራተኛ ግን እንደአገልግሎት ጊዜው እየተተመነ ተመጣጣኝ ክፍያ ያገኛል፡፡ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎ በሰራተኛ ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ የተቋረጠበት ሠራተኛ ከላይ በተጠቀሰው ክፍያ ላይ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ የአገልግሎት ዓመት ከላይ የተጠቀሰው ክፍያ አንድ ሦስተኛ እየታከለ የስራ ስንብት ክፍያው ይከፈለዋል፡፡ ነገር ግን ጠቅላላው ክፍያ ከሠራተኛው የ12 ወራት ደመወዝ መብለጥ የለበትም፡፡
በሰራተኞች ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ ተቋርጦ ከስራ የተሰናበተ ሰራተኛ ከላይ ከተጠቀሰው የስራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ የሠራተኛው የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዝ በ60 ተባዝቶ እንደሚከፈለው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 40 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ከዚህ ባለፈ አለመግባባት የሚፈጠር ከሆነ ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ሰላም ለመፍጠር፣ ምርታማነትን ለማሻሻል ብሎም የሰራተኞች ህጋዊ መብቶች ለማስክበር በስራና ክህሎ ሚኒስቴር በሚመደብ አስማሚ ችግሩ እንዲፈታ መመልከት ወይም ይህን መሰል ጉዳይ የወል ስራ ክርክር በመሆኑ ለአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ዳኝነት መጠየቅ ይቻላል፡፡
Federal Justice and Law Institute
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴

https://alehig.wordpress.com/blog-2/
#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
🛑በጡረታ መገለል🛑
👆👆👆👆👆👆👆👆

ዋቢ ህጎች

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011

የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 715/2003

የመንግሥት የሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 243/ በሕግ በተደነገገው መሠረት የሥራ ውልን ስለማቋረጥ ብሎ በጡረታ መገለልን እንደ አንድ ውል የሚቋረጥበት መንገድ ያስቀምጠዋል፡፡ 24(3) ሠራተኛው አግባብ ባለው ሕግ መሠረት በጡረታ ሲገለል፤

በጡረታ መገለል
👇👇👇👇
የመንግሥት የሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀፅ 18(1) /ሐ መሰረት የጡረታ መውጫ ዕድሜ 60 ዓመት ነው፡፡ የመንግስት ሰራተኞች የጡረታ መውጫ ዕድሜ (በእንግሊዝኛው ቅጂ ላይ retirement age) ስድሳ ዓመት እንዲሆን ተወስኗል፡፡ ጡረታ መውጣት ማለት በህጉ የተወሰነው የስድሳ ዓመት እድሜ ላይ መድረስ ማለት ነው፡፡

በህግ የተቀመጠው የጡረታ ዕድሜ 60 ዓመት ሲሆን የሚሰላውም ሠራተኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀጠር በቅድሚያ የመዘገበውን የልደት ዘመን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ሠራተኛው በህግ የተወሰነው የ60 ዓመት የጡረታ መውጫ እድሜ ላይ ሲደርስ የሥራ ውሉን ያቋረጠው ህግ እንጂ አሠሪው ባለመሆኑ የሥራ ውሌ ከህግ ውጪ ተቋርጧል በሚል የሚያነሳው ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
“ሠራተኛው አግባብ ባለው ህግ መሠረት በጡረታ ሲገለል” የሥራ ውሉ በሕግ በተደነገገው መሰረት ይቋረጣል፡፡
ሠራተኛው የጡረታ እድሜ ላይ ደርሶ ከተቀጣሪነት ወደ ተጧሪነት ሲሸጋገር የሥራ ውሉም ያለ ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ ወዲያውኑ ያበቃለታል፡፡ ያ ማለት ግን ከጡረታ በኋላ እንደገና በአዲስ መልክ ተቀጣሪ ለመሆን አይችልም ማለት አይደለም፡፡ ጡረተኛው ካካበተው የረጅም ጊዜ የሥራ ልምድ እና ተሞክሮ አንጻር በተለይ በአንዳንድ የሥራ መስኮች ላይ ተፈላጊነቱ ይጨምራል፡፡ ሆኖም በቋሚነት (ላልተወሰነ) ጊዜ የመቀጠር እድል የለውም፡፡
በአዲሱ አዋጅ ቁ.714/2003 ብሎም በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ 715/2003 አንድ ሠራተኛ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ከመድረሱ በፊት ጡረታ የሚወጣበት ወይም በጡረታ የሚገለልበት ስርዓት የለም፡፡ ሆኖም ዕድሜው ለጡረታ ሳይደርስ የጡረታ አበል ባለመብትና ተጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ በአዋጅ ቁ. 345/1995 አንቀጽ 12(2) እንደተደነገገው ቢያንስ 20 ዓመት አገልግሎት ያለው የመንግስት ሠራተኛ በራሱ ፈቃድ ወይም በአዋጁ ከተጠቀሱት ውጪ በሆነ ምክንያት አገልግሎት ካቋረጠ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ሲደርስ የአገልግሎት ጡረታ አበል እስከ ዕድሜ ልኩ ይከፈለዋል፡፡ ድንጋጌው ሠራተኛውን የጡረታ አበል ተጠቃሚ ወይም ተከፋይ ሳይሆን የጡረታ ባለመብት ያደርገዋል፡ በዚህ መልኩ የሚገኝ የጡረታ ባለመብትነት በአዋጅ ቁ 714/2003 እና በአዋጅ 715/2003 ላይም በተመሳሳይ መልኩ ተደንግጓል፡፡ ሆኖም የሥራ ውሉ የተቋረጠው ሃያ አምስት ዓመት አገልግሎት ከሰጠ በኋላ ከሆነ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ሊደርስ አምስት ዓመት ሲቀረው የጡረታ አበል ተጠቃሚነት ወይም ተከፋይነት መብት ይኖረዋል፡፡

https://telegram.me/lawsocieties
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Hello AleHig family I need your help on finding a case of defamation in civil and Criminal case which held for the public interst (defamation took place over a public interst).
I hope you'll show me your support I'll compensate.
@Hubu_alnafs or 0945614343.
Vacancy Notice for 16 Round Training.pdf
11.8 MB
Amhara  regional state judicial training vacancy 2024
Vacancy Notice for 16 Round Training.pdf
11.8 MB
13/5/2016ዓ.ም
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስር በሚገኙ ወረዳዎች እና ንዑስ-ወረዳዎች ዳኛ ወይም ዐቃቤ-ሕግ ሆኖ ለመሥራት በዕጩ ዳኛነት እና በዕጩ ዐቃቤያነ-ሕግነት ተመልምለው የቅድመ-ሥራ ስልጠና ለመሰልጠን ለሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ የወጣ ማስታወቂያ

የአብክመ የፍትሕ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ እና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት የወረዳ/የንዑስ- ወረዳ ዳኛ እና ዐቃቤ-ሕግ ሆኖ ከመሾም በፊት የሚሰጠውን የቅድመ-ስራ ስልጠናን በ2016 ዓ.ም ለ16ኛ ዙር ለመስጠት ያቀደ ሲሆን ስልጠናውን ለመሰልጠን የሚፈልጉ የዩንቨርሲቲ የሕግ ተመራቂዎችን በቅድመ-ስራ ሰልጣኞች ምልመላ አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 11/2011 እና ይህን መመሪያ ለማሻሻል በወጣው መመሪያ ቁጥር 01/2016 መሰረት አወዳድሮ በመመልመል ለማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከታች የተገለጹትን መስፈርቶች ሊያሟሉ የሚችሉ ተወዳዳሪዎች በውድድር ጥሪ ማስታወቂያው መሰረት እንዲወዳደሩ ይጋበዛሉ፡፡

የሥራ መድቡ መጠሪያ፡- ዕጩ የወረዳ ዳኛ እና ዐቃቤ-ሕግ

2. ተፈላጊ ችሎታ ወይም መስፈርት፡-

➢ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ያላት ሆኖ ከሰኔ ወር 2003 ዓ.ም ጀምሮ የተመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ስርዓት ከተጀመረ በኋላ የተመረቁ ስለሆነ የመውጫ ፈተና ያለፉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
የተከሳሽ_በተከላካይ_ጠበቃ_መወከል_መብት.pdf
346.8 KB
የተከሳሽ በተከላካይ ጠበቃ የመወከል መብት (በፍትሕ ሚኒስቴር ንቃተህግ ክፍል የተዘጋጀ)
Follow our LinkedIn page:
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/
አቤቱቱታ ስለ ማሻሻል - የፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርአት ህግ ቁጥር 91

አቤቱታ ማለት ለፍርድ ቤት የሚቀርብ ክስ/መልስ/ይግባኝ/ወይም ሌላ ማንኛውም አይነት አንድ ባለ ጉዳይ ከፍ/ቤት የሆነ ዳኝነት እንዲወሰንለት በመጠየቅ የሚያቀርበው ማመልከቻ ነው፡፡

አቤቱታ ላይ ያቀረበው ሰው የሚጠየቅው ዳኝነት እና ይህንን ዳኝነት ሊያገኝ የሚገባውን ጉዳይ አብራርቶ መጠየቅ ያለበት ሲሆን ክስ ከቀረበ በኋላ ወይም ጉዳዩ ከጀመረ በኋላ በአቤቱታው ላይ መገለጽ የነበረበት እና አለመገለጹ ባለ ጉዳዩን የሚጎዳ፤ ትክክለኛ ውሳኔ እንዳይሰጥ ሊያደርግ የሚችል እና ለፍትህ አሰጣጥ የሚስቸግር ከሆነ ባለ ጉዳዩ ይህንን አቤቱታ አሻሽሎ ወይም የተጓደለውን አሟልቶ እንዲያቀርብ እንዲፈቀድለት ለፍ/ቤት ሊያመለከት ይቻላል፡፡

አቤቱታ ሲሻሻል ነገሩን በይበልጥ ወይም በተሻለ መንገድ ማብራራት እንጂ በመጀመሪያው ዳኝነት ላይ ያልተጠየቀ እና ፈጽሞ የተለየ ጉዳይ ወይም ዳኝነት ይፈጸምልኝ የሚል ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም፡፡
ነገረ ፈጅ Negere Fej
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
Screenshot_20240126-171710.png
53.5 KB
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ምድብ ችሎቶች እና አድራሻቸው
ሰ/መ/ቁጥር 211167 ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ/ም
@Abrham Yohanes
የሙና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 13 (1) እና (2) ባለማድረግ (Omission) ይልቅ በማድረግ (Comission) የተፈጸመ ወንጀልን ለመቅጣት የተደነገገ ነው።

የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 13(2) በአንቀፅ 13(1) ከፊደል ሀ እሰከ ሐ የተመለከቱን ዝርዝር የህግ ነጥቦች መሰረት በማድረግ የከበደ የወንጀል ሀላፊነትን ለመጣል የተቀመጠ ሲሆን አንቀፅ 13(1) ከፊደል ሀ እስከ ሐ የተመለከቱትን ዝርዝር ሁኔታዎች ጥቅም መውሰድን ወይም ጥቅም የሚያስገኝን ውል መዋዋልን፤ ውል ማቋረጥን፤ የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅትን ጥቅም የሚጎዳ ተግባርን መፈፀምን ለመቅጣት የተደነገጉ መሆናቸው አንቀፅ 13 ከመነሻውም ካለማድረግ (Omission) ይልቅ ማድረግን (Comission) ለመቅጣት በህጋችን የተካተተ መሆኑን ያሳያል፡፡

ስለሆነም ተከሳሹ በስራ ሀላፊነቱ መሰረት ሊከታተለውና ሊቆጣጠረው ሲገባ ግዴታውን ባለመወጣት የደረሰ ጉዳት በአዋጁን አንቀፅ 13(2) መሰረት የወንጀል ክስ ከቀረበ የህጉን ዝርዝር ሁኔታ መሰረት ያላደረገ ክስ ነው።
በስራ መዘርዝር መሰረት የመከታተልና የመቆጣጠር ሀላፊነትን ባለመወጣት የሚፈጸም ወንጀል የሚያስጠይቀው በወ/ህ/አ.420(2) መሰረት የስራ ሀላፊነትን ባለመወጣት የወንጀል ድርጊት እንጂ በጸረ-ሙስና አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 13(2) አይደለም
የፍትሐብሔር_ጉዳዮችን_የሚመለከቱ_ፎርሞች.doc
1.2 MB
የፍትሐብሔር ጉዳዮችን የሚመለከቱ ከ180 በላይ የክስ፣ የመልስ፣ የይግባኝ፣ የአፈጻጸም፣ የሰበር፣ የውሳኔ እና የትዕዛዝ ፎርሞች፡፡
#ነገረሕግ
እሁድ እሁድ ስናካሂድ የነበረውን ከምሽቱ 2:30 የእሁድ ችሎት ነፃ ውይይት፣
Anonymous Poll
79%
እንደገና ይጀምር
3%
አሁን ጊዜው አይደለም
4%
ትንሽ ይቆይ
3%
በፍፁም አያስፈልግም
26%
መቋረጥ አልነበረበትም
ሰ/መ/ቁ/211987
ለግዴታ አፈጻጸም ዋስ የሆነ ሰው ባለዕዳው ግዴታውን ባለመፈጸሙ ምክንያት ዕዳውን ለባለገንዘቡ ሲከፍል ወለድ እና ወጪ ሊጠይቅ የሚችለው ከባለገንዘቡ ጋር ክርክር ተደርጎ ዋሱ ከዋናው ገንዘብ በተጨማሪ ወለድ እና ወጪ ጨምሮ መክፈሉ ሲረጋገጥ ነዉ፡፡ በተጨማሪም ዋሱ የኪሳራ ጥያቄ ሊያቀርብ የሚችለው ለባለዕዳው ማስጠንቀቂያ መስጠቱ እንዲሁም በባለእዳዉ በኩል የተፈጸመ ጥፋት ወይም ቸልተኝነት መኖሩን ጭምር በማስረዳት ነው።
አብርሃም ዮሀንስ
CMSPs.pdf
593 KB
የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎችን
በተመለከተ የቀረበ አጭር ማብራሪያ
መግቢያ


የኢትዮጰያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት መካከል ቁጥጥር ለደረግባቸው የሚገቡ የካፒታል ገበያ ተግባራትን መወሰን፣ ስካIta ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃደ መስጠት እና ስራቸውንም መቆጣጠር ይ7ኝበታል፡፡

በዚህም መሰረት ባለሰልጣኑ ለካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ የሚሰጥበትና የሚቆጣጠርበትን መመሪያ አዘጋጀ±ል፡፡ "phIta ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች የፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 980/2016" Πλ.6.8.6tC+oon C 9 3 2016 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ ውሏል። በዚህም መሠረት ባለስልጣኑ በቅርቡ የአገልግሎት ፈቃድ ማመልከቻዎችን መቀበል ይጀምራል፡፡

ይህን በማስመልከt በዚህ አጭር ጽሁፍ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ምን ማለት ነው ፣ ምን ምን ተግባራትን ያከናውናሉ፣ ምን አይነት ሀላፊነቶች አስባቸው፣ ፈቃድ ለማግኘትስ ምን አይነት መሰፈርቶችንና መመዘኛዎችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል የሚሉት ጉዳዮች ላይ አጠር ያስ ማብራሪያ ቀርቧል፡፡
Alternative legal enlightenment (ALE)
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/