አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
📣 Bunna Insurance

Position: LEGAL OFFICER


📚ትምህርት ዓይነት እና ደረጃ:
LLB Degree in Law

🇪🇹የስራ ቦታ ፡ Addis Ababa

🧭የምዝገባ ጊዜ፡ እስከ ኅዳር 14, 2016

ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት  እና ለማመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ👇
https://tikusjobs.com/job/legal-officer-4/
ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ተገልጋዮች ጥራቱን የጠበቀ ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ከብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
ይህንን ጥረት ከግብ ለማድረስ ተገልጋዮች ስለሚፈልጉት አገልግሎት እና ማሟላት ስላለባቸው መስፍርቶች በቂ መረጃ እንዲኖራቸው ያስፈልጋል፡፡
ለዚህም ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ጠቃሚ መረጃዎችን በተከታታይ በዚሁ ገጽ ላይ የምናስተላልፍ ይሆናል ፡፡
ክቡራን ተገልጋዮቻችን መረጃዎችን ለሌሎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ ዜጎችን ከእንግልትና ከሙስና እንዲታደጉ በማክበር እንጠይቃለን፡፡
ውልና ማስረጃ ምን አለhttps://t.me/EntrustConsultant
በየትኛውም ቦታ ሁነው ሰነዶች ማረጋገጫ(ውልና ማስረጃ) ጉዳይ አላችሁ
👉ውክልና
👉 ብድር ውል
👉 የሺያጭ ውል
👉ቃለ ጉባዔ
👉ሼር መግዛት /መሸጥ........
ወ.ዘ.ተ
ሌሎችንም አገልግሎት በአካል መገኘት ሳይጠበቅብዎች በአሉበት ቦታ ሁነው መረጃውን ይሰጡና በባለሙያ ተፅፎ  በቴሌግራም፣ ዋትስአፕ ወይም በኢሜል ይላክላችኋል።
ከእናንተ የሚጠበቀው ፕሪንት አድርጎ ወደ አቅራቢያ ሰነዶች ማረጋገጫ በመሄድ ምን ጊዜ ሳያባክኑ አገልግሎት ማግኘት ብቻ።
ስለ አስፈላጊ ሰነድ መረጃ በነፃ ይገኛሉ።
ይደውሉ:- 0909039999
የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት (ውልና ማስረጃ) ሲፈልጉ
Emails:-
admin@entrustconsult.com
info@entrustconsult.com
consultantentrust@gmail.com
Forwarded from አለሕግ🔵AleHig
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አማራጭ የህግ እውቀት  https://www.youtube.com/@Lawsocieties
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለ_ህግ Ale_Hig
አለህግ Alehig
@Lawsocieties

@Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
የከፋው ጊዜ የሚመጣው የሞራል ህግ የጠፋ ጊዜው ነው!
Anonymous Poll
88%
እውነት
7%
ሀሰት
6%
የተለየ መልስ
አለሕግAleHig ️
Photo
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አለሕግAleHig ️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የግል ድርጅት ሠራተኞችን አስተዳደራዊ በደል የማየት ሥልጣን ተሰጠው
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የማሻሻያ አዋጅ የግል ድርጅት ሠራተኞችን አስተዳደራዊ በደል የማየት ሥልጣን የሚሰጥ መሆኑ ተገለጸ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን የማሻሻያ አዋጅ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

የምክር ቤቱ የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቱ አለነ፤ የተቋሙን የማሻሻያ አዋጅ ዝርዝር ሁኔታና አስፈላጊነቱን በሚመለከት ለምክር ቤቱ አባላት በዝርዝር አቅርበዋል።

የተደረገው ማሻሻያ የአስተዳደር በደሎችን ለመከላከል እና ተፈጽሞ ሲገኝ ምርመራ በማካሄድ በደሎች በአፋጣኝ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል።

በተሻሻለው አዋጅ መሠረት የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሹመት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑ ቀርቶ በዕንባ ጠባቂ ጉባዔ የሚመደብ መሆኑንም አስረድተዋል።

የተቋሙ መርማሪ በምርመራ ሥራ ላይ እያለ ዋና ዕንባ ጠባቂ ሳይፈቅድ ወይም ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር አይያዝም፤ አይከሰስም፤ እንዲሁም ያለመታሰር መብት እንዳለው በአዋጁ መደንገጉንም ገልፀዋል።

በተደረገው ማሻሻያ መሠረትም በመርማሪዎች ላይ ይደርስ የነበረውን ያልተገባ ጫና በማስቀረት ነፃነታቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በግል ድርጅቶች የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎችን የማየት ሥልጣን እንዳልነበረው አስታውሰው፤ በተሻሻለው አዋጅ ግን የማየት ሥልጣን የተሰጠው መሆኑን ገልፀዋል።

በተሻሻለው አዋጅ መሠረት የአስተዳደር በደል አቤቱታዎችን የመቀበል፣ የመመርመር እና ምክረ-ሃሳብ የማቅረብ ሥልጣን የተሰጠው መሆኑንም አስረድተዋል።

በተሰጠው ማብራሪያ ላይ ሰፊ ውይይት ያደረጉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የአዋጁን ማሻሻያ ተገቢነት በማመን በሙሉ ድምፅ አፅድቀውታል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ አዋጅ ቁጥር 1142/2011 በአዋጅ ቁጥር 1307/2016 ተሻሽሎ በምክር ቤቱ ፀድቆ ሥራ ላይ ውሏል።

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የሠራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።

የጋዜጠኝነት ሥራ በባህሪው በየትኛውም ሰዓት ሥራ ላይ መሆንን የሚጠይቅ በመሆኑ እነሱን የሚመለከት ድንጋጌ ባካተተ መልኩ መሻሻሉ አስፈላጊ መሆኑ ተብራርቷል።

ኢቢሲ ብቃት ያላቸውን ሠራተኞች ይዞ ለማቆየት እና አዳዲስ ልዩ ችሎታና ክህሎት ያላቸውን ሠራተኞች ለመቅጠር እንዲችል ደንቡን ማውጣት አስፈላጊ መሆኑ ተነስቷል።

በዚህም መሠረት የኢቢሲ የሠራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብን ደንብ ቁጥር 1/2016 ሆኖ በምክር ቤቱ በሁለት ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል።

ህዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም
****,
(ኢ ፕ ድ)
አማራጭ የህግ እውቀት  https://www.youtube.com/@Lawsocieties
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለ_ህግ Ale_Hig
አለህግ Alehig
@Lawsocieties

@Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
አዲስ አበባ ሥራ አጦች📈

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ አጦች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ።

በመዲናዋ የሥራ አጦች ቁጥር በመቶኛ እየጨመረ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱትሪ ልማት ቢሮ የሥራ ዕድልና የሥነ ምግብ ዋስት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሃ ጥበቡ ሰምቷል።

ለሥራ አጦች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ረገድ ያሉ ተግዳሮቶች ምን እንደሆኑ እንዲያስረዱ ከቲክቫህ ኢትዮጵያና ሌሎች ሚዲያዎች ጥያቄ የቀረበላቸው ኃላፊው ተከታዮችን ነጥቦች አንስተዋል።

- ሥራ አጡ በጣም ሰፊ ነው።

- አዲስ አበባ የአገሪቱ ዋና ከተማ እደመሆኗ መጠንና አጎራባች አካባቢ ካለው የጸጥታ ችግርም አንፃር በመደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ወደ ከተማ ውስጥ በሰፊው የሚገቡ አሉ። እዚህም የከተማውን ማህበረሰብ ከሥራ ዕድልም አንፃር የሚሻሙ ናቸው።

- የከተማው ወጣት አለ። የከተማው ሥራ አጥ የሥራ ዕድል በጥራትም በስፋት እዲፈጠርለት ይፈልጋል፤ በዚህ መካከል እኛ መፍጠር የምንችለው የሥራ እድል እና ከተማ ውስጥ ያለው የሥራ አጦች ቁጥር አይጣጣምም።

- የራሱ የከተማው ነዋሪ አለ፣ በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማ ውስጥ የሚገባም አለ። እነዚህን ሁለቱን አጣጥሞ የሚጠበቀውን ያክል የሥራ ዕድል መፍጠር በጣም ፈታኝ ነው።

- የሥራ አጥ ቁጥሩ አምና ስንጀምር ስብጥሩ በጣም ዝቅተኛ ነበር። ወደ 17 በመቶ አካባቢ የነበረው አሁን አድጎ ወደ 22 ነጥብ 8 በመቶ ደርሷል የሥራ አጥ ቁጥር ምጣኔው።

- እኛ በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ወደ አንድ ድርጅት እናወርዳለን ብለን ነው እየሰራን ያለነው ነገር ግን እየጨመረ ነው የሚያሳየው። የዚህ መጨመር ምክንያቱ የተለያየ ቢሆንም አንደኛው ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር ያለመቻልን ያሳያል።

- እኛ እየፈጠርን ያለነውና የሥራ ስምሪት ውስጥ የሚገባው ሥራ አጥ ቁጥሩ ሰፊ ነው ይሄ አልተመጣጠነም።

- የሰው ሀይላችን እስኪልድ ማን ፓወር አይደለም በጣም የሰለጠነ ብቁ ሞያተኛ የሆነ የሰው ሀይል እጃችን ላይ የለም።

-  የሰው ሀይላችን ሥራ አጡ በተለይ የትምህርት ደረጃው ዝቅተኛ ነው፤ ይህን ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ያለው የሰው ኃይል አሰልጥኖ የክህሎትና የሙያ ባለቤት አድርጎ ወደ ኢንስትሪዎቹ ማስተሳሰርን ይጠይቃል።

በሌላ በኩል ፤ ሥራ ያገኙ ሰዎች ቀጣሪ ኢንዱስትሪዎች የሚከፈላቸው #ደመወዝ_በጣም_አነስተኛ በመሆኑ የቤትና ኪራይና አስቤዛ እንኳ ማሟላት እንደማይችል በተደጋጋሚ ቢገልጹም መፍትሄ እያገኙ እንዳልሆነ፣ ሥራ አጥ የሆኑትም የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ይደመጣል።

ይህንን በተመለከተ አቶ ፍስሃ ምን አሉ ?

" ኢንዱስትሪዎቹ የሚከፍሉት ደመወዝ ዝቅተኛ ነው የእነርሱ ምክንያት ደግሞ እምታቀርቧቸው ሰዎች ሙያቸው ከዚህ በላይ አያስከፍልም የሚል ጥያቄ ያነሳሉ "  ብለዋል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ማብራሪያ ያገኘው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኅዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ኅዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሪካ አመራር  ልህቀት አካዳሚ አዘጋጅቶት በነበረው የውይይት መድረክ ለተገኙት አቶ ፍስሃ ጥበቡ ጥያቄ አቅርቦ ነው)

ጥንቅሩ በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።
@tikvahethiopia
አማራጭ የህግ እውቀት 
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለ_ህግ Ale_Hig
አለህግ Alehig
@Lawsocieties

@Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
የውሰት ነገር በሕግ ዓይን
“ዕቃ ከተዋሱ፣ መመለስ አይርሱ!”

“ስትዋስ ያሳየኸውን ትህትና ስትመልስም አትርሳ።”

እነዚህን ጥቅሶች የደጎቹ አዋሾች ምሬቶች ይወለዷቸው ይመስላሉ።

አዋሾች ደጎች ናቸው። የጠየቅናቸውን ነገር አልከለከሉምና ለውለታቸው መርቀናቸው መዋዋስን ወደ ሚመለከቱት በፍብሔር ሕጋችን ላይ ከቁጥር 2767 እስከ 2777 የተደነገጉት አንቀፆች ስለ ውሰት ሕጋዊ ግንኙኑት የሚሉንን እንመልከት።

1. የትውስት ውል

የምናውቃትን መዋዋስ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2767 በሌላው ስሟ ‘የመገልገያ ብድር’ ይላታል። መገለጫዋ አዋሽ ለተዋሹ አንድን የሚንቀሳቀስ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረቱን በነፃ እንዲገለገልበት የውል ግዴታ የሚገባባት ውል መሆኗ ነው። አውሳለሁ ብሎ ክፍያ መጠየቅ አይቻልም። ኪራይ ትከፍላለህ የሚል ቃል ካለ ነገሩ ውሰት ሳይሆን ኪራይ ነው።

2. የተዋስነው ነገር የማን ነው?

አደራ የኛ እንዳይመስለንና እንዳንዘናጋ! በእኛ እጅ (ይዞታ) ላይ ይቆይ እንጂ ባለቤቱ አዋሻችን ነው። ስለዚህ ጊዜው ሲደርስ ይመለሳል።

3. መቼ ይመለስ?

ከተዋስን መመለሳችን አይቀርም። መቼ ለሚለው በውሰት ውላችን ላይ የተስማማንበት ጊዜ ሲያልቅ ነው የምንመልሰው።

4. አዋሹ እንዲሁ በዝምታ ካዋሰንስ?

ይህም ቢሆን አንመልሰውም ማለት አይደለም። ልማዳዊ አሠራር ካለ ለምሳሌ ዕቃውን የፈለግንበት ጉዳይ ሲጠናቀቅ መመለስ አለብን። መቼ እንደምንመልስ የሚጠቁም ልማዳዊ አሠራር ከሌለ ደግሞ አዋሹ እስኪጠይቀን መጠቀም እንችላለን። እንደጠየቀን ግን ወዲያውኑ መመለስ አለብን።

5. አጠቃቀም

የተዋስነውን ዕቃ በሚገባ መጠበቅ አለብን። ወጪ የሚያስወጣ ከሆነም ወጪውን የምንችለው ተዋሾች ነን።
👇👇👇👇👇