አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
👆👆👆👆👆👆👆 የቀጠለ ........

6. እንደ ባለቤት አንሁን

በውል ከተስማማንበት ጉዳይ ውጭ በተዋስነው ንብረት መገልገል አይፈቀድልንም። ለምን እንደምንጠቀምበት በውሰት ውሉ ላይ ባንስማማም እንኳን የዕቃው ተፈጥሮ ከሚፈቅደው ውጭ መጠቀም አንችልም።

ሌላ አንድ ነገር እናስታውሳችሁ፤ ምንም ያህል ደግ ብትሆኑ የተዋሳችሁትን ዕቃ አዋሻችሁ ካልፈቀደ በስተቀር ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠት አይቻልም።

በተዋስነው ዕቃ ከመጠን በላይ በመገልገላችን ወይም ለሌላ ሰው ያለአግባብ በመስጠታችን ዕቃው ከተበላሸ የመተካት ወይም ብልሽቱን የማስጠገን ግዴታ አለብን።

ሆኖም እኛ የተዋሽነት ግዴታችንን ብንወጣም ዕቃው ከመበላሸቱ እንደማይድን በቂ ማስረጃ ካቀረብን ለብልሽቱ ተጠያቂነት ሊቀርልን ይችላል። በጣም ከአቅም በላይ ችግር ገጥሞን ከራሳችን ዕቃ እና ከተዋስነው አንዱን መምረጥ ግድ ሆኖብን የራሳችንን ዕቃ አትርፈን የተዋስነው ዕቃ ከጠፋ ለራሳችን አድልተነልና ኃላፊነቱ አይቀርልንም። የትውስት ውሉ የዕቃውን ዋጋ ከጠቀሰ ዕቃው በማናቸውም መልኩ ቢጠፋም ተጠያቂ ነን። የዕቃው ዝርዝር በውሉ ላይ ካልተጠቀሰ ግን ስትረከበው በመልካም ሁኔታ እንደነበረ ይቆጠራልና በተረከብነው መልኩ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ማስረከብ አለብን።

7. የተዋሽ እና የአዋሽ መብት

እንበልና ለ6 ወር የተዋስነውን ዕቃ በ2ኛው ወር ጉዳያችንን ስለጨረስን በቃን። የግድ 4 ወር ሙሉ መጠበቅ የለብንም፤ ለባለቤቱ መመለስ እንችላለን። ሆኖም ዕቃውን ያለጊዜው መመለሳችን ባለውለታችን የሆነው አዋሻችን ላይ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ ባንፈልገውም የተዋስንበት የጊዜ ቆይታ እስኪያልቅ መጠበቅ ሊኖርብን ነው።

አዋሻችን ደግሞ የተዋስንበት ጊዜም ባያልቅ ከፈቀደልን ሁኔታ ውጭ በዕቃው ከተጠቀምን፣ ዕቃውን ካበላሸን፣ ለሌላ አሳልፈን ከሰጠን ወይም አዋሻችን ለራሱ በአስቸኳይ እና በድንገት ዕቃውን ከፈለገው እንድንመልስለት ሊያስገድደን ይችላል።

8. ሞት ከመጣስ?

አያድርገውና የተዋስነውን ነገር ሳንመልስ ከሞትን አዋሻችን ለረጅም ጊዜ ፈቅዶልን የነበረ ቢሆንም ጊዜው ሳይደርስ ወራሾችን ዕቃውን እንዲመልሱለት መጠየቅ ይችላል። አዋሹ ያዋሰው ዕቃ ሳይመለስ ከሞተ ደግሞ ውርሱ ሲጣራ ያዋሰው ዕቃ መኖሩ ከታወቀ ወደ ውርሱ ሀብት ተካቶ ለወራሾች ይከፋፈላል።

አዋሽም ሆነ ተዋሽ ጋብቻ ካላቸው ከ500 ብር በላይ የሆነ ነገር ለማዋስም ሆነ ለመዋስ የባልየው ወይም የሚስትየው ስምምነት እንደሚያስፈልግ በተሻሻለው የፌዴራሉ የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 68 (መ) ላይ ተደንግጓል።

በመጨረሻም በዚህ መልዕክት ጽሑፋችንን እንቋጨው፤

ስንዋዋስ ምስክር ባለበት፣ የፈቀድነውን የአገልግሎቱን ዓይነት ጠቅሰን፣ መቼ እንደሚመለስ ተስማምተን ቢሆን ይመረጣል። የምንዋዋሰው ትንሽ ዋጋው ጠንከር ያለ ንብረት ከሆነ ደግሞ የዕቃው ዋጋ እና ልዩ መለያው ቢጠቀስ፣ የውሰት ውሉም በጽሑፍ ቢሆን ጥሩ ነው።

ለማንኛውም የጠንካራ ማኅበራዊ ሕይወታችን መገለጫ ነውና መዋዋሳችን እንቀጥላለን። ቸር እንሰንብት!
EBC
አማራጭ የህግ እውቀት 
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለ_ህግ Ale_Hig
አለህግ Alehig
@Lawsocieties

@Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
ማስታወቂያ
በረዳት ዳኝነት ተመዝግባችሁ መስፈርቱን በማሟላት ተመርጣችሁ ስማችሁ ከዚህ በታች የተገለፀው አመልካቾች ለህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 3፡30 ለፈተና እንድትቀርቡ የተጠራችሁ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን
ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለ_ህግ Ale_Hig
አለህግ Alehig
@Lawsocieties

@Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
ማስታወቂያ👇👇👇👇👇👇👇👇
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በዕጩ ዓቃቤ ሕግነት አወዳድሮ ለመቅጠር በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማውጣቱን ተከትሎ  መስፈርቱን ያሟሉ አመልካቾችን መመዝገቡ ይታወቃል።
በመሆኑም እሁድ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በቦሌ ክፍለከተማ ቅጥር ጊቢ ውስጥ  ፈተና የሚሰጥ  መሆኑን ተመዝጋቢዎች ይህንን ተገንዝባችሁ በተባለው ቀን እና ቦታ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያችሁን በመያዝ እንድትገኙ  እንገልፃለን።
አማራጭ የህግ እውቀት 
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለ_ህግ Ale_Hig
አለህግ Alehig
@Lawsocieties

@Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Legal Solutions for Everyone, Provided by Legal Experts.
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ህግ ባለሙያዎች መገኛ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ተቀጥሮ መስራትን የማያበረታታው ነጩ ካፒታሊዝም /Pure Capitalism/ በኢትዮጵያ፣

በሚኪያስ መላክ ብርሀኔ
እና
አቤል ወንድሙ ኃይሌ
በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀፅ 12 (3) መሠረት ማንኛውም ተቀጥሮ የሚሰራ ሠራተኛ መክፈል የሚኖርበትን ግብር አሠሪው ከሠራተኛው ገቢ ላይ ሳይቀንስ የሠራተኛውን ግብር ራሱ አሰሪው በሙሉ ወይም በከፊል የከፈለለት እንደሆነ ፣ በአሰሪ የተከፈለው የግብር መጠን ሠራተኛው ከመቀጠር ከሚያገኘው ግብር በሚከፈልበት የገንዘብ መጠን ላይ ተደምሮ ግብሩ ይሰላል፡፡
እንዲሁም፤
በገቢ ግብር አዋጅ አንቀፅ 10 (3) መሠረት ተቀጣሪው በመቀጠር የሚገኘውን ገቢ ለማግኘት የሚያወጣውን ማንኛውም ወጪ በተቀናሽ ሊያዝለት አይችልም፡፡
ነገር ግን
በዚሁ በገቢ ግብር አዋጁ አንቀፅ 15 (1) ፣ (5) እና (7) መሠረት ግብር የሚሰላበት የኪራይ ገቢ ነው የሚባለው ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ ውስጥ ቤት በማከራየት ካገኘው ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ላይ ለግብር ከፋዩ የተፈቀደው ጠቅላላ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎ የሚቀረው ገቢ ነው፡፡
በተጨማሪም፤
በገቢ ግብር አዋጁ አንቀፅ 20 ፤ 22 እና ሌሎችም ተያያዥ ድንጋጌዎች መሠረት አንድ ነጋዴ ገቢ ለማግኘት የሚያወጣው ወጪ ተቀናሽ እንዲደረግላቸው ሕጉ በግልጽ አስቀምጧል።

በመሆኑም፤
የኢትዮጵያ የገቢ ግብር አዋጅ እና ሌሎችም ሕጎች ተቀጥሮ መስራትን የማያበረታቱ የነጩ ካፒታሊዝም /Pure Capitalism/ ርዕዮተ ዓለም መገለጫዎች ይመስላሉ።
ከኢኮኖሚ አቅም አንፃር ስናየው ነጋዴ እና አከራይ የተሻለ ገቢ የሚያገኙ እና በአንፃራዊ የተሻሉ የኢኮኖሚ አቅም ያላቸው ሆነው እያለ ግብር የሚሠላበትን ገቢ ለማግኘት ያወጡት ወጪ ተቀናሽ ተጠቃሚ ሲሆኑ ፤ ይህ ተጠቃሚነታቸው በኢኮኖሚው ውስጥ ነጋዴውና የኪራይ ንብረት ባለሀብቶች የሚያደርጉትን የነቃ ተሳትፎ ለማበረታታት አስፈላጊነቱ የሚታመንበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ በተቃርኖ ግን ድሀው እና ለፍቶ አደሩ አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ገቢው እዚህ ግባ የማይባል የወር እና ቀን ገቢ አነስተኛው ተከፋይ ሠራተኛ ገቢውን ለማግኘት የሚያወጣው ወጪ ተቀናሽ የማይደረግለት ሲሆን ይባስ ብሎ አሰሪ ግብሩን ቢከፍልለት እንኳ እንደ ተጨማሪ ገቢ ተቆጥሮበት ግብር እንዲከፍልበት ሕጉ ያስገድዳል።
እናንተስ ምን ትላላችሁ?
Alternative legal enlightenment
(ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለሕግ Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
ክፍት ስራ ማስታወቂያ
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለሕግ Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
የኮንትሮባንድ ንግድ ለምን ?
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለሕግ Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
The African Court has jurisdiction over cases related to the interpretation and application of the African Charter on Human and Peoples' Rights and other international human rights instruments. Join the conversation on #GovernanceRoadshow. Learn more at: https://www.african-court.org
East African Community
African Union
Pan African Parliament
Network of African National Human Rights Institutions - NANHRI
Pan African Lawyers Union - PALU
African Committee of Experts on the Rights and Welfare of the Child
African Union ECOSOCC
The African Institute of International Law
African Commission on Human and Peoples' Rights
African Legal Information Institute
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለሕግ Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
ብሔራዊ ነፃ ህግ ድጋፍ አገልግሎት ስትራቴጂ መፅደቁን ተከትሎ የማብሰሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ፍትህ የማግኘት መብትንና እኩልነት ላይ የተመሰረተ ፍትሕን ብሎም ሌሎች መሰረታዊ መብቶችንናነጻነቶችን ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡ በዚህ መነሻነት አገልግሎቱን ለሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት አገልግሎቱ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ነገር ግን አገልግሎቱን ተደራሽ፣ ወጥነት፣ቀጣይነት እና ጥራት ባለው መልኩ ከመስጠት እና በአገልግሎቱ ሰጪ እና ባለድርሻ አካላት መካከል ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር ከመዘርጋት አንፃር ክፍተቶች ሲስተዋሉ ቆይተዋል፡፡ ይህን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ስትራቴጂ መቀረጽ እንዳለበት ተወስኖ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ስትራቴጂውን የማዘጋጀት ስራ ሲሰራ ቆይቶ እንዲፀድቅ ተደርጓል።

የስትራቴጂውን መፅደቅ ተከትሎ ወደትግበራ ለማስገባት የሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የማብሰሪያ መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡

በመድረኩ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት በፍትህ ሚኒስቴር የመንግስት ህግና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው የመድረኩ ዓላማ ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ስትራቴጂን ወደስራ ለማስገባት መፅደቁን ማስተዋወቅ እና በቀጣይ የጋራ የስራ አቅጣጫ ለመያዝ መሆኑን ገልፀው ዜጎች ፍትህ የማግኘት መብታቸዉ በህገ መንግስቱ የተደነገገ ቢሆንም ጠበቃ አቁሞ ለመከራከር የገንዘብ አቅም የሌላቸው በመሆኑ እና በተለያዩ አጋጣሚዎች በተለይ ሴቶች፣ ህፃናት እና አካል ጉዳተኞች ለመብት ጥሰት ተጋላጭ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

አክለውም ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት በአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች እና በሀገራችን ህገ መንግስት የተካተተ መብት መሆኑን፣ መብቱን ተግባራዊ ለማድረግ በተለያዩ አካላት ሲሰራ መቆየቱን፣ የሚሰጠው አግልግሎት የተቀናጀ አለመሆኑን፣ ይህን ችግር ለመቅረፍ ስትራቴጂው እንዲዘጋጅ መደረጉን እና በቀጣይ ስትራቴጂውን ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችና አሰራሮች እንደሚዘጋጁ አመላክተዋል፡፡

በሌላ በኩል በውይይት መድረኩ ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትን በመወከል በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የረጅም ዘመን ዳኝነት አገልግሎት ያላቸው እና አሁንም በማገልገል ላይ የሚገኙት የተከበሩ አቶ ብርሃኑ አመኑ ሀገራችን ባፀደቀቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች ትኩረት ከተሰጣቸው መብቶች መካከል ፍትህ የማግኘት መብት አንዱ መሆኑን፣ የተከሰሱ ሰዎች ጠበቃ ማቆም ባለመቻላቸው ፍትህ የሚጓደል ከሆነ በመንግስት በነጻ ጠበቃ ሊመደብላቸው እንደሚገባ በህግ መደንገጉን አስረድተዋል፡፡ እንዲሁም በፍርድ ቤቶች ስር የተደራጀው የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት በከባድ ጉዳዮች ላይ ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየ እና ህፃናትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ለህጻናት አገልግሎት ለመስጠት ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ አክለውም ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎቱን ለማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት ያለ ቢሆንም የተደራሽነት ችግር ያለ መሆኑን፣ ያለውን የአቅም ውስንነት፣ የተደራሽነት፣ እና በዘርፉ ያሉ ችግሮችን እልባት ለመስጠት ስትራቴጂው መፍትሔ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

በመቀጠል የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኦሞድ ሰዎች በተፈጥሮ የሚያገኟቸውን መብቶችና ነፃነቶች ተግባራዊ ለማድረግ ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልፀው ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ልዩ ድጋፍ የሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎች (ህጻናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች) ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አንጻ ከፍተኛ አስተዋዕፆ አለው ብለዋል፡፡ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉደዮች ሚኒስቴር ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ልዩ ድጋፍ በሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይተዋል ያሉት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም አገልግሎቱ በሚፈለገው ደረጃ ጥራት ያለው እና ተደራሽ ነው ለማለት አይቻልም ብለዋል፡፡

አክለውም አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሸ ለማድረግ እና ጥራቱን ለማሻሻል ስትራቴጂ ቀርፆ ተግባራዊ ማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው እና ስትራቴጂው የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎችን ከመለየት እና የቅንጅታዊ አሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ለሴቶች፣ ህጻናት፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ያለው ትርጉም ትልቅ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡ በመጨረሻም ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎቱንነ በተሻለ ሁኔታ ለመስጠት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመቀጠል በስትራቴጂው ይዘት ዙሪያ ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ገለፃውን ያደረጉት በፍትህ ሚኒስቴር የህግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳሬክቶሬት ጄኔራል ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ አዲስ ጌትነት ሲሆኑ በገለፃቸው እስካሁን ሲሰጥ የነበረው ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ምን እንደሚመስልና የሚስተዋሉትን ችግሮች፣ የተዘጋጀው ስትራቴጂ ዓላማ፣ የያዛቸው ዋና ዋና ጉዳዮች እና ማስፈፀሚያ ስልቶችን አብራርተዋል፤ የመድረኩ ተሳታፊዎችም የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን አንስተው ውይይት የተደረገ ሲሆን ተሳታፊዎች በዋናነት ስትራቴጂው መፀደቁ በዘርፉ ያለውን ችግር ለመፍታት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው እና ለመተግበርም ቁርጠኛ መሆናቸውን በተለያየ መንገድ ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው እና ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኦሞድ መድረኩን እየመሩት በቀረበው ገለፃ ላይ በተሳታፊዎች ውይይት የተደረገ ሲሆን ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎቱ መፅደቁ በተለይ ለመብት ጥሰት ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰቡ ክፍሎች ፋይዳው የጎላ መሆኑን አንስተው ለተግባራዊነቱ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅትና በትብብር እንዲሰሩ የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በመጨረሻ መድረኩን የዘጉት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው በማጠቃለያቸው ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ስትራቴጂውን ለመተግበር በቀጣይ የህግ ማዕቀፍ የማዘጋጀት እና የአሰራር ሥርዓቶችን የመዘርጋት ስራ እንደሚሰራ፣ ስትራቴጂውም ታትሞ በቅርብ ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚሰራጭ፣ ህብረተሰቡ ስለነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት እና ህጎች ግንዛቤ እንዲኖረው የንቃተ ህግ ትምህርት የመስጠት ስራ በሰፊው እንደሚሰራ ገልጸው የዜጎችን የፍትህ ጥያቄ ለመመለስ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በጋራ እንዲሰሩ እና ለስትራቴጂው ትገበራ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈው መድረኩ ተጠናቋል።
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለሕግ Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ማሳሰቢያ ለዕጩ አቃቢያነ ህግ ተፈታኞች 👈👈👈👈👈👈
በነገው እለት ወደፈተና ስትቀርቡ ቀጥሎ የተዘረዘሩ መፅሐፎችን ይዛችሁ መግባት ምትችሉ መሆኑን ቢሮው ፈቅዷል።
፨ የፍታብሔር ህግ
፨ የፍታብሔር ስነስረአት ህግ
፨ የወንጀል ህግ
፨ የወንጀል ስነስረዓት ህግ

መልካም እድል!
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለሕግ Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
https://t.me/lawsocieties