አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ማስረጃ ለመመዘን ሥልጣን የተሠጠው ፍርድ ቤት ማስረጃ ሲቀበል የተከራካሪዎችን እኩል የመደመጥ መብት ካላከበረ፣ የማስረዳት ሸክም (burden of production) የማን ነው የሚለውን ካልለየ፣ የማስረጃ ተቀባይነትና ተገቢነት ላይ መከተል የሚገባውን ሥርዓት ካልተከተለ፣ በምዘና ጊዜ የሁሉንም ተከራካሪዎች ማስረጃ አብሮ ካልመዘነ፣ ከማስረዳት ደረጃ (standard of proof) አንጻር በሚጠይቀው ደረጃ ልክ መረጋገጡን ካላሳየ እና
በመሠረታዊ ሕግ ሆነ በሥነ-ሥርዓት ሕግ ያሉትን የማስረጃ ሕጎችና መርሆች ካላከበረ ጉዳዩ የማስረጃ ምዘና ሳይሆን የሕግ አተረጓጎም ስህተትና ፍርድ ቤት ያለበትን ኃላፊነት አለመወጣት ስለሚሆን የሰበር ሰሚ ችሎቱ የሚመለከተው ነው።
ሰ/መ/ቁ. 217634 ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ/ም
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ሳይመዘገብ በተወካይ አማካይነት የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል ውሉ ስለመደረጉ በተወካዩ ታምኖ ሆኖም ወካዩ ውል መኖሩን ከካደ ህጋዊ ውጤት አይኖረውም።

ውሉ ፈርሶ ተዋዋዮች ወደነበሩበት መመለስ ይኖርባቸዋል።

ሰ/መ/ቁጥር 215444
ጥቅምት 02 ቀን 2015 ዓ/ም

#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ግብር/ታክስ

ያልተከፋፈለ ትርፍ

• በአንድ የግብር ዓመት ግብር ከተከፈለ በኋላ ለአባላቱ ያልተከፋፈለ እና መልሶ ኢንቨስት ያልተደረገ የተጣራ የድርጅት ትርፍ 10% ግብር ይከፈልበታል፡፡

በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት አማካኝነት ወደ ወጭ የሚላክ ትርፍ

• በኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት አማካኝነት የንግድ ስራ የሚያከናውን በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ካለው በቋሚነት ከሚሰራ ድርጅት በሚላክለት ትርፍ ላይ 10% ግብር ይከፈልበታል፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
231571.pdf
822 KB
ፍርድ ቤት የንብረት አስተዳዳሪ ስለሚሾምበት አግባብ
ሰ/መ/ቁ 231571 ጥር 29 ቀን 2015 ዓ/ም
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 166(1)(ሀ) ስር እንደተደነገገው ፍርድ ቤቱ የሚመችና ትክክለኛ መሆኑን የገመተ እንደሆነ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ወይም ከሰጠ በኃላ ማናቸውንም ንብረትና ሀብት ተቀብሎ የሚጠብቅ ሰው መርጦ መሾም ይችላል፡፡ እንዲህ አይነቱን ማመልካቻ ፍርድ ቤቱ የሚቀበለው ከሆነ ትዕዛዝ ሊሰጥ የሚገባው አመልካቹ የጠየቀውን አቤቱታ፣ ተሿሚው ሊሰበስብ ወይም ሊያገኝ የሚችለውን፤ አስተዳዳሪውን ለመሾም ሚደረገውን ወጪ በማመዛዘንና በተለይም ምርመራ እንዲደረግበት ሌላም ተጨማሪ ነገር ቢኖር አብሮ እንዲጣራ በማድረግ ስለመሆኑ ከድንጋጌው ንዑስ ቁጥር 2 መገንዘብ ይቻላል።
ከተጠቀሰው ድንጋጌ መረዳት እንደሚቻለው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን ለመስጠትና ላለመስጠት ፍቅድ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል፡፡ ፍርድ ቤቱ በዚህ መልኩ በህጉ የተሰጠውን ፈቅድ ስልጣን ተጠቅሞ ሲወስን ከግምት ውስጥ ሊገቡ የሚገባቸውን ጉዳዩች ሁለ ተመልክቶና አረጋግጦ ሊወስን እንደሚገባ በህጉ ተመልክቷል፡፡ ስለሆነም አንደኛው ተከራካሪ ንብረትና ሀብት ተቀብሎ የሚጠብቅ ሰው ተመርጦ እንዲሾም ስለጠየቀ ብቻ የነገሩ ሁኔታ ሳይመዘን ንብረት አስተዳዳሪ እንዲሾም ማለት እንደማይቻል ሁሉ የነገሩ ሁኔታ ታይቶ የሚመችና ትክክለኛ መሆኑን ፍርድ ቤቱ የገመተ እንደሆነ ንብረትና ሀብት ተቀብሎ የሚያስተዳድር ሰው ሊሾም አይገባም የሚባልበት የህግ ምክንያትም የለም፡፡
Abrham Yohanes Law Corner
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
1287_2015_የኤክሳይዝ_ታክስ_አዋጅ_ማሻሻያ_.pdf
7.6 MB
#ETHIOPIA

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገቢዎች ሚኒስቴር አሳውቋል።

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 ከየካቲት 5/2012 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለ ሲሆን ይህ አዋጅ የታክሱን መሰረት በማስፋት እና የታክሱን አስተዳደር ስርዓት በመቀየር ከፍተኛ ጠቀሜታን ማስገኘቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ጉባኤው በአዋጁ ላይ የቀረቡ ማሻሻያዎችን ታሳቢ በማድረግ የአዋጁ ማሻሻያ ተደርጓል ሲል አስታውሷል።

የአዋጁ ማሻሻያ ታሰቢ ያደረገው ፦

- #ተደራራቢ የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ምርቶች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ፣

- ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ላይ የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፈል ለማድረግ፣

- የኤክሳይዝ ታክስ ተጥሎባቸው የነበሩት አንዳንድ ምርቶች ላይ ታክሱን ለማንሳት መሆኑ ተመላክቷል።

ምክር ቤቱ በአስተዳደር ምክንያት የተደረጉ ማስተካከያዎችን እና የማሻሻያውን ዋና ዋና ምክንያቶችን ከመረመረ በኋላ የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1287/2015 እንዲጸድቅ አድርጓል፡፡

በመሆኑም ገቢዎች ሚኒስቴር የአዋጁ ማሻሻያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል እንዲደረግ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ፣ የንግዱ ማህበረሰብ ሁሉ እንዲያውቁት መመሪያ ሰጥቷል።

(የአዋጁ ማሻሻያ ከላይ በ #PDF ተያይዟል)

#የገቢዎች_ሚኒስቴር
#tikvahethiopia
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ሳይፋቱ ፍቺ (Defacto Divorce)

ጋብቻ የቤተሰብ መሰረት በመሆኑ በህግ እውቅና የተሰጠው እና ከምስረታው ጀምሮ ጥበቃ የሚደረግለት ተቋም ነው፡፡ በዚህም የሚፈርስበት ሁኔታ ጭምር በቤተሰብ ህጉ በግልፅ ተመላክቷል፡፡ በተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ እንደተደነገገው ጋብቻ የሚፈርሰው ከተጋቢዎች አንዱ ሲሞት ወይም በፍርድ ቤት የመጥፋት ውሳኔ ሲሰጥ፣ ጋብቻ ለመፈፅም መሟላት ካለባቸው ሁኔታዎች አንዱ በመጣሱ ምክንያት በህግ መሰረት ጋብቻ እንዲፈርስ ሲወሰን ወይም የፍቺ ውሳኔ ሲሰጥ ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ በቤተሰብ ህጉ ፍቺ የሚፈፀምባቸውን ሁኔታዎች እና በፍርድ ቤት ሳይወሰን ተለያይቶ መኖር በህጉ የሚስተናገድበትን ሁኔታ እንመለከታለን፡፡

ፍቺ የሚፈፀምበት ሁኔታ

ጋብቻ በፍቺ እንዲፈርስ ሊወሰን የሚችለው ባልና ሚስት በስምምነት ለመፋታት ሲወስኑና ይህንኑ ለፍርድ ቤት አቅርበው ውሳኔያቸው ተቀባይነት ሲያገኝ እና ከተጋቢዎቹ አንዱ ወይም ሁለቱም ተጋቢዎች በአንድነት ጋብቻቸው በፍቺ እንዲፈርስ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ሲያቀርቡ ነው፡፡ ጋብቻ በስምምነት ሲፈርስ ፍርድ ቤት የፍቺ ስምምነቱን የሚያፀድቀው የባልና ሚስቱ ትክክለኛ ፍላጎት መሆኑን እንዲሁም ስምምነቱ ከህግና ሞራል ጋር የማይቃረን መሆኑን ሲያምን ነው (የቤተሰብ ህግ አንቀፅ (አንቀጽ 80 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2)፡፡
https://t.me/lawsocieties
ሳይፋቱ ፍቺ (Defacto Divorce)
ፍርድ ቤቱ የፍቺን ስምምነት ያፀደቀው እንደሆነ ስለፍቺው ውጤት ያደረጉትንም ስምምነት አብሮ ሊያፀድቀው የሚችል ሲሆን ባልና ሚስቱ ስለፍቺ ውጤት ያደረጉት ስምምነት የልጆቻቸውን ደህንነትና ጥቅም በበቂ ሁኔታ የማያስጠብቅ ወይም የአንደኛውን ተጋቢ ጥቅም የሚጎዳ ሆኖ ካገኘው ፍርድ ቤት የፍቺውን ስምምነት ብቻ በማፅደቅ የፍቺውን ውጤት በተመለከተ ጉድለቶቹ እንዲስተከካሉ ተገቢ መስሎ የታየውን ውሳኔ ይሰጣል (የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 80/3)። በመሆኑም ጋብቻ በፍቺ የሚፈርሰው ፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ ሲሰጥ መሆኑን መረዳት ይቻላል::

ሳይፋቱ ፍቺ (Defacto Divorce) ምንነት

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በ1999 ዓ.ም በሰበር መዝገብ ቁጥር 20938 ሰጥቶት በነበረው ውሳኔ መሰረት ሳይፋቱ ፍቺ ማለት በፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ ሳይሰጥበት ባልና ሚስት ለበርካታ ዓመታት ተለያይተው በመኖር፣ የየራሳቸውን ሕይወት እየኖሩ (አግብተው ወይም ሳያገቡ) ከቆዩ፣ ምንም እንኳን ቀደም ብሎ የተፈጸመ ጋብቻ የነበራቸው ቢሆንም ሁለቱም በየፊናቸው የየራሳቸውን ሕይወት መጀመራቸው ከተረጋገጠ ጋብቻቸው እንደፈረሰ የሚቆጠርበትን ሁኔታ የሚያመለክት ነው፡፡

ሳይፋቱ ፍቺ (Defacto Divorce) በኢትዮጵያ ህግ የሚታይበት ሁኔታ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጠው ውሳኔ በሥር ፍርድ ቤቶች ላይ አስገዳጅ በመሆኑ ምክንያት ችሎቱ የሰጠው የህግ ትርጉም ሥራ ላይ ሲውል የቆየ ቢሆንም በርካታ ሴቶች ሀብት ንብረታቸውን እንዳሳጣቸው ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል፡፡ ይኸውም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 79 ሕግ የመተርጎም ሥልጣን ለፍርድ ቤት፣ በአንቀጽ 55 ደግሞ ሕግ የማውጣት ሥልጣንን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰጠ ቢሆንም ሰበር ሰሚ ችሎት ግን ከሕጉ ዓላማ ውጪ የሆነ አስገዳጅ ትርጉም መስጠቱ ሕገ መንግሥቱን እንደሚቃረን በመጥቀስ ለህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አቤቱታ ቀርቧል፡፡

ሰበር ሰሚ ችሎት በውሳኔው ጋብቻ ሊፈርስ የሚችልባቸውን ምክንያቶች በተመለከተ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 75 እና 82 የተመለከቱ ድንጋጌዎችን በማለፍ አራተኛ ምክንያት ማስቀመጡም ተገቢ አለመሆኑ፣ የጋብቻን ፍቺ የመወሰንና የጋብቻው በፍቺ መፍረስ የሚያስከትለውን ውጤት የመወሰን ሥልጣን የፍርድ ቤት ብቻ ሆኖ የተደነገገበት የራሱ ዓላማ ያለው መሆኑን፣ ጋብቻ በፍቺ ሲፈርስ የተጋቢዎችን የንብረት ክፍፍልና የሕፃናትን የአስተዳደግ ሁኔታ አገናዝቦ ውሳኔ መስጠት ያለበት ፍርድ ቤት መሆኑ እንዲሁም ተጋቢዎች ተለያይተው በመኖራቸውና የየራሳቸውን ሌላ ሕይወት በመጀመራቸው ‹‹ጋብቻቸው ፈርሷል›› የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ተጋቢዎች በቸልተኝነት ጋብቻቸውን ከፍርድ ቤት ዕውቅና ውጪ በፍቺ መልክ እንዲያቋርጡ መንገድ የሚከፍትና ሕገ-ወጥነትን የሚያበረታታ መሆኑ ቅሬታው ተቀባይነት እንዲያገኝ ያስቻሉ ምክንያቶች ናቸው፡፡

በመሆኑም የሰበር ሰሚ ችሎቱ አስገዳጅ ውሳኔ ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 ከተመለከተው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር፣ በአንቀጽ 51 ከተመለከተው የፌዴራል መንግሥት ሥልጣንና ተግባር ድንጋጌዎች ጋር የሚጋጭ ሆኖ ስላገኘው የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥበት ጉባዔው በሙሉ ድምፅ በመወሰን በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 84(1) እና በአዋጅ ቁጥር 798/2005 አንቀጽ 3(1) ለመጨረሻ ውሳኔ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳቡን አቅርቧል፡፡ ፌዴሬሽን ምክር ቤትም የቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ በመቀበልና ይሁንታ በመስጠት አስገዳጁን የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ሰርዞ ጋብቻ ሊፈርስባቸው ከሚችሉ ሦስት በህግ ከተመለከቱ ምክያቶች ውጪ ዝም ብሎ መለያየትና መቆየት ጋብቻን ሊያፈርስ እንደማይችል በፌደሬሽን ምክር ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 5ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባዔ መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም የመዝገብ ቁጥር 49/10 ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ለማጠናከርና ሥልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር በወጣው አዋጅ ቁጥር 251/93 አንቀጽ 11/1 እና 56 መሰረት በህገ-መንግስት ትርጉም ላይ ምክር ቤቱ የሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ አጠቃላይ ውጤት የሚኖረው ሲሆን ወደፊት በሚወሰኑ ተመሳሳይ ህገ-መንግስታዊ ጉዳዮች ላይ የአስገዳጅነት ባህርይ ይኖረዋል፡፡ ስለሆነም ምክር ቤቱ በቀረበለት ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ሲሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች ውሳኔውን የማክበርና የመፈፀም ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡

በአጠቃለይ የጋብቻ መፍረስ በልጆች እና በንብረት አስተዳደር ላይ ውጤት ያለው በመሆኑ በህጉ የተቀመጡትን የጋብቻ መፍረስ ምክንያቶች ብቻ መከተል ግዴታ መሆኑን የፌደሬሽን ምክር ቤት ከሰጠው የህገ-መንግስት ትርጉም መረዳት ይቻላል፡፡ ስለሆነም በጋብቻ ውስጥ ያሉ ሰዎች መለያየት ከፈለጉ በህጉ መሰረት ፍቺ መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ከኤክሳይዝ ታክስ ነጻ

ግንቦት 11፣2015 (ገቢዎች ሚኒስቴር)

በተሻሻለው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1287/2015 መሰረት ከላይ የኤክሳይዝ ታክስ ይከፈልባቸው የነበሩ እቃዎች እና አገልግሎቶች ከኤክሳይዝ ታክስ ነጻ ተደርገዋል፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የማስረጃ ህግ ትርጉምና ጠቀሜታ በአንድ ክርክር ሂደት
ማስረጃየሚለው ቃል የላቲን ቃል ሲሆን መሠረቱም "Evidence evader" የሚለው ነው፡፡
የዚህቃል ትርጉም በግልፅማሳየት፣ ለዕይታ ግልፅ ማድረግ፣ግልፅሆኖእንዲወጣ ማድረግ፣ በግልፅ የተረጋገጠ እንዲሆን ማድረግ፣ ማስረዳት የሚል ትርጉም ያለው ነው፡፡
በፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩትሕዳር 1996 የተረቀቀው የማስረጃ ሕግየማስረጃን ትርጉምእንደሚከተለውአቅርቦታል፡-
“ማስረጃ” ማለት እውነተኛነቱ እንዲመረመር የቀረበ ማናቸውም የታወቀ ነው የተባለ ነገር የሚረጋገጥበት ወይም ውድቅ የሚሆንበት ማንኛውም ዘዴ ሲሆን፤ ይኽውም የምስክሮችን ቃል፣ በተከራካሪዎች የሚሰጥን የእምነት ቃል፣ ሰነድ፣ የፍርድ ቤት መዝገብ፣ ማስታወቂያ፣ በሕግ የተወሰደ የህሊና ግምት (Legal Presumption)፣
የአንድን ነገር አፈጣጠር እና ሂደትማሳያ (Demonstration) እንዲሁም
ፍርድቤቱ በዓይነት እንዲመለከታቸው የሚቀርቡለትን ነገሮች (exhibits) ይጨምራል፡፡
(የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የማስረጃሕግየመጀመሪያረቂቅ)
ይሁንና ማስረጃ ተብሎ የተነገረ ሁሉ ለፍትህ አሰጣት ዓላማ ወይም በሕግ አጠቃቀም ማስረጃ ላይሆን ይችላል፡፡በሕግ አግባብ ማስረጃ የሚባለው በፍ/ቤት ፊት ወይም በፍትህ ሰጭው አካል ፊት ቀርበው የፍትህ አፈፃፀሙን በተገቢው እንዲከናወን የሚያስችል መሆን ሲችሉ ነው፡፡ ከዚህም አኳያ አግባብ ያለው ማስረጃከ ተራ ማስረጃ የተለየ ነው፡፡
በቴክኒካዊ አነጋገር ማለትም በሕግ አግባብ ወይም በተለመደው የሕግ አጠቃቀም ማስረጃ
የተባለው የአንድ አከራካሪ ነገር መኖር ወይም አለመኖር /existence or non- existence/ በማሳየት የዳኛው አእምሮ እንዲያምን የሚያደርግ ነው፡፡በአጠቃላይ ዳኛው ከፊቱ የቀረቡለትን ጥያቄ እውነት ወይም ሐሰት መሆኑን ለመረዳት ከውሳኔ ላይ ለመድረስ ግምት ለመውሰድ አእምሮ የሚመራበት ነገር የያዘነው፡፡
1. #የማስረጃአይነቶች
የማስረጃ ዓይነቶች ከሚታወቀው ተለምዷዊ አከፋፈል ሂደት በአራት ክፍሎች ተከፍለው እናገኛቸዋለን፡፡ እነሱም ተጨባጭ ማስረጃ /Real evidence/ ገላጭ ማስረጃ /Demonstrative evidence/ የሰው ማስረጃ/Testimonial evidence / የሰነድማስረጃ/Document evidence / በመባል ይታወቃሉ፡፡ ይሁንና እነዚህ ማስረጃ ለአገልግሎት በሚውሉበት ጊዜ ሂደታቸውን ገዢ የሆኑ ስረዓቶች መኖራቸው ይታወቃል፡፡እነዚህም የማስረጃ ሕግ ስረዓቶች /Rules of evidence/ በመባል የሚገለፁ ሲሆኑ እነሱም እነዚህም በሁሉም ማስረጃዎች ላይ እንደአስፈላጊነታቸው የሚያገለግሉ ይሆናሉ፡፡
2. #ተጨባጭማስረጃ
ተጨባጭ ማስረጃተብሎ የሚታወቅ በጭብጥ የተያዘውን አከራካሪ ፍሬ ነገር መኖር ወይም ያለመኖር ዳኛውን ለማሳመን ሲባል በስሜት ሕዋሳቱ አማካይነት /senses/ በቀጥታ እንዲያገኛቸው በማቅረብ ነገሮች የሚከናወንበት ነው፡፡ ይህም ዕቃዎችንና ቁሳዊ ነገሮችን /ፎቶግራፎች፣ የቴፕ ክሮች፣ ፊልሞችን፣ የኮምፒዩተር አንሜሽኖች ወዘተ ይጨምራል/ እነዚህ ተጨባጭ ማስረጃዎች ግኡዝ ነገሮችን ብቻ ሣይሆን የሚያካትቱት እንደእንሰሳት የመሳሰሉትን ነፍስ ያላቸውን ነገሮች የሚጨምር ነው፡፡
በአጠቃላይ በወንጀል አጠቃቀም ገላጭ ማስረጃማለት ፍ/ቤት በማስረጃነት የሚቀርብከወንጀሉ ድርጊት ጋርግንኙነት ያላቸው የሚታዩ፣ የሚዳሰሱ፣ የሚሸተቱ፣ የሚቀመሱ ወይም የሚሰሙ ለአንድ ወንጀል ተግባር የዋሉ ወይም ያገለገለወይም ሊውሉ የተዘጋጁ የተከማቹ ለወንጀል መጠቀሚያ ወይም ማስፈፀሚያ ወይም የተፈፀመውን ወንጀል ውጤት ያስገኙ ነገሮችናቸው፡፡
እነዚህ ወንጀል የተሰረባቸው ነገሮች እንደ ጩቤ፣ ደም የነካው ልብስ፣ የጦርመሳሪያ፣ ጥይት፣ ቀለህ፣ መርዝ፣ ግጭት የደረሰበት ተሽከርካሪ፣ ካርታ፣ ፎቶግራፍ፣ ቴፕ፣ የቪዲዮ ክር፣ ጨርቃጨርቅና ክራክሮች፣ ፀጉር፣ የእግር ዱካ፣ የጣት አሻራ፣ ተንቀሳቃሽ ፊልም ... ወዘተ ናቸው፡፡
2.1. #የተጨባጭ ማስረጃዎችጥቅም /Uses of Physical Evidence/
ተጨባጭ ማስረጃ አንድ የተፈፀመ ወንጀል በትክክል መፈፀሙ ንና አለመፈፀሙ ን ወይም በወንጀል ስራ የተጠረጠረው ሰው በስፍራው መኖሩንና የድርጊቱ ተካፋይ/አድራጊ መሆኑን ሊያስረዱ የሚችሉ የማስረጃ አይነቶች ናቸው:: ይህ ማስረጃ የአንድን ተጨባጭ ነገር ምንነትና አመጣጡን በእርግጠንነት ሊያስረዳ የሚችልየማስረጃአይነት ነው፡፡
2.2. #ተጨባጭ ማስረጃዎች ከወንጀል ምርመራ አንፃር አከፋፈል ተጨባጭ ማስረጋጃ ከወንጀል ምርመራ አኳያ ሲተነተን በሁለት ክፍሎች ተከፍሎ ይታል እነሱም ፡-
የግልባህሪን የሚያሳዩ ተጨባጭ ማስረጃና
የቡድን ባህሪን የሚሳዩ ተጨባጭ ማስረጃዎች ተብለው ይከፈላሉ
የግል ባህሪን የሚያሳዩ ተጨባጭ ማስረጃዎች የአንድን ነገር ግላዊነት ወይም ከዛ ከተገኘው ማስረጃ ጋር የሚመሳሰለው አንድ ተጠርጣሪ ካልሆነ በስተቀር ከሌላ ተጠርጣሪ ማስረጃ ጋር በፍፁም ሊመሳሰሉ የማችሉ ሲሆኑ ወይም በድጋሚ በሌላው ሰው ወይም ነገርላይሊገኙ የማይቸሉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የጣት አሻራ፣ የእጅ መዳፍ፣
DNA የመሳሰሉት ናቸው፡፡
የቡድን ባህሪን የሚያሳዩት ተጨባጭ ማስሰረጃዎች የጋራ የሆነ ባህሪ ያላቸው ማስረጃዎች ማለት ነው፡፡ለምሳሌ ጥጥ /ጨርቃጨርቅ/ ቤንዚን፣ አፈር የመሰሰሉት ናቸው፡፡
ማስረጃዎች እንደ ባሕሪያቸው ሲከፋፈሉ
የቡድንባህሪ የግልባህሪ
አደገኛዕ ፅዋቶች የጣት አሻራ
ክራክር የእጅ መሳሪያ ምልክቶች
ፀጉር የእጅ ፅሁፍ
ደም እብለበራሄ / DNA/
መስታዎት የጦርመሳሪያ
አፈር የእግርዱካ/የጫማ ዱካ
3. ቀጥተኛማስረጃ/Testimonial Evidence/
ይህ የማስረጃ በቀጥታ በአይነት የታየን ወይም የተሰማ ማለትም ከአምስቱ የስሜት እዋሶቻችንመሃከል በአንዱ ወይም ከአንድ በላይ በሆነየስሜት ህዋስአማካኝነት የሚገለፁ ለፍረድአሰጣጥ ስረዓቱ በእማነኝነትየሚቀርብማስረጃነው፡፡
4. #የተጨባጭ ማስረጃና የሰው ምስክርነት ሲወዳደር
4.1.#የተጨባጭ ማስረጃ ጠንካራ ጎን
አይዋሹም፣ አይሞቱም፣ አይረሱም፣ አያፍሩም አይሸማቀቁም ወዘተ
ጊዜ የማያልፍባቸው ከሆኑና ወይም ተመርምረው ውጤታቸው አንዴ ከተጠናቀቀ በኋላአይለወጡም
ደካማ ጎን እንደሰው በንግግር ስሜታቸውን ለፍትህ ሰሚው አካል መግለፅ አይችሉም ምስክርነታቸውየሚገለፀው በሙ ያተኛአማካነትነው፡፡
4.2.#የሰው ምስክርነት ደካማ ጎን
ሊቀየር ወይም ሰውየው በፍርድ ቤት ቀርቦ እንዲመሰክር በሚፈለገበት ጊዜ ላይኖር ይችላል፣በወንጀልድርጊት ጊዜ ሁኔታዎችን የመመልከትና ያዩትን ደግሞ የማስረዳት ችግር ሊፈጠር ይችላል፣ የማየት፣ የመስማት፣ የማሽተት ውስንነት ወዘተ
ይዋሻል በገንዘብ ሊደለል ይችላል ይፈራል ይረሳልወዘተ ጠንካራ ጎን
ያለውን ሁኔታ በመግለፅ ፍርድ ቤቱን ማሳመን ይችላል በአጠቃላይም ማስረጃዎች እንደነገሩ ሁኔታ የራሳቸው ጠንካራናደካማ ጎንእናዳለቸው ተመልክተናል ይሁንና የዓይን ምስክርንበተመለከተ ያለው ሁኔታ ከእርግጠኝነት ጋር ተያዞ የሚከተለውን እንመልከት የዓይን ምስክርነትን እርግጠኝነት በተመለከተ በአሜሪካ አገርው ስጥ አርባ የሚሆኑ ችሎቶች ትክክለኛ ያልሆነ ብይን በአይን ምስክር ሳቢያ ሰጥተዋል፡፡በዚህም ሂደትሞት የተፈረደባቸው እድሜ ልክ እስር የተበየነባቸውና እንደየጥፋት እርከኑ ቅጣት የተጣለባቸው ሰዎች ተገኝተዋል:: ይሁንና በአካላዊ ማስረጃ ግን እነዚህን ስህተቶች ሲቀንሱ ተስተውለዋል፡፡ይሁንናየዓይንምስክር እረግጠኛነት እንዴሁኔታው የሚለያይ መሆኑንየዘርፉ ባለሙ ያዎች በጥናታቸው ይስማሙ በታል፡፡ ከዚህም አኳያ እውክታ
ከሚፈጥሩት ነገሮች
የምስክሮች ባህሪ ማለትም ፆታ እናእድሜ
ምስክርነታቸውን የሚሰጡበት የጊዜ እርዝመት ወንጀሉ ከተፈፀመ በኋላ
ወንጀሉ ሲፈፀም የነበረው የብርሃንሁኔታ
የምስክሩየማየት ሁኔታ የተከለለነበርማለትም ተፈጥሮአዊበሆነሁኔታም ይሁንበሌላ ምክንያት
ወንጀልከሚፈፀምበት ስፍራ ምስክሩያለበትእርቀት
እነዚህና ሌሎችም ሁኔታዎች ተጨምረው የዓይን ምስክርን እውነታነት እንደወንጀል አፈፃፀሙ ሁኔታ ተአማኒነቱንየለያየዋል
5.#ገላጭ ማስረጃ/Demonstrative Evidence/
ገላጭ ማስረጃከስሙ እንደምንረዳው የተፈፀመውን ድርጊት የሚገልፅወይም የሚያብራራና የማስረጃ ዓይነት ነው፡፡ይህም ማስረጃ ተቀባይነት የሚኖረው የሚፈለጉትን ተገቢነት አሟልቶ በሚገኝበት ጊዜ ሲሆን በዚህ ማስረጃነት የሚታወቁት ምሳሌ እንደ ካርታ፣ የወንጀልስፍራንድፍ ፣አንሜሽን፣ ፎቶግረፍ፣ የቪዲዮ ፊልሞችና ወዘተ ናቸው፡፡
6.#የሰነድ ማስረጃ/Documentary Evidence/
የሰነድ ማስረጃከተጨባጭ ማስረጃዎች አይነቶች አንዱ ሲሆንይህም ማስረጃው በፅሁፍ መልክለፍረድ ቤቱየሚቀርብነው፡፡ይኸውም የሁለት ተዋዋይወገኖች የውል ስምምነት፣ በመንግስትመስሪያቤት ወይም በግልድርጅት ተፅፈው የሚገኙ ለጉዳዩአግባብነትያላቸው ፅሁፎች፣ ልዩ ልዩ ጋዜጣዎች፣ መፅሔቶች፣ መፅሐፍቶች፣ ላንግድ ስራ የተዘጋጁ ልዩልዩ ፅሁፎች ወዘተ የመሳሰሉት ሲሆኑ እነዚህን ማስረጃዎች ፍርድ ቤቱ እራሱ በማንበብ የሚረዳቸው የማስረጃ አይነቶች ናቸው፡፡
7.#ኤግዚቪት ትርጉም (Exhibit)
አግዚቪት ማለት ከአንድ የወንጀል ድርጊት ጋር ግንኙነት ያላቸው ልዩልዩንብረቶች ጥሬ ገንዘብ፣ወንጀል የተፈጸመባቸው መሳሪያዎች፣በህገወጥ መንገድ በተጠርጣሪው እጅ የተገኙ ልዩልዩዕቃዎች፣ወንጀል ከተፈፀመበት ቦታ የተሰበሰቡናከወንጀል ድርጊት ጋርግንኑነት ያላቸው ለፍርድ ቤት በማስረጃነት የሚቀርቡ የሚታዩ፣ የሚዳሰሱ የሚሸተቱና የሚቀመስ ለወንጀልመፈፀሚ ወይንም ማስፈፀሚ ያየዋሉ ወይም የወንጀል ውጤት የሆኑ ቁሳዊ ነገሮች ናቸው፡፡
#Legal_Service
©Tsegaye Demeke -Lawyer
☑️1. ህግ ህገ መንግስት
☑️2. አዋጅ/
የአለም አቀፍ ስምምነቶች
☑️3. ደንብ
☑️4. መመሪያ


ህግ ህገ መንግስቱ ነው ማለት ነው፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያወጣቸው ህጎች ማለትም አዋጆች ይከተላሉ፡፡

የአለም አቀፍ ስምምነቶችን የህግ ተዋረድ በተመለከተ ወጥ የሆነ መግባባት ባይኖርም በህገ መንግስቱ ኢትዮጵያ የፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የአገረቱ ህግ አካል ይሆናሉ ስለሚል ከአዋጅ ጋር ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ይቀመጣሉ የሚል ሀሳብ አለ፡፡

በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚወጡት ደንቦች እና በሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የሚወጡት መመሪያዎች በቅደም ተከተል ናቸው፡፡
በሌላ በኩል በተመሳሳይ ተዋረድ (hierarchy) ላይ ባሉ ህጎች መካከል መቃረን ሲኖር ተፈፃሚ የሚሆነው በጊዜ ዘግይቶ የወጣው ህግ (latest prevails) ነው፡፡ ይህ ማለት ዘግይቶ የወጣው ቀድሞ ከወጣው ይልቅ ተፈፃሚ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ልዩ ህግ (special law) ከጠቅላላ ህግ ይልቅ ቅድሚያ ተቀባይነት (special law prevails over general law) ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties

በፌስቡክ FB
https://www.facebook.com/lawsocieties/

በቴሌግራም
https://t.me/lawsocieties

https://t.me/lawsocieties
203888.pdf
826.7 KB
የአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 16(1)(ሀ) እና (ለ) ላይ በሠው ላይ ለሚደርስ የአካል ጉዳት ወይም ሞት የኃላፊነት ጣሪያው በተጎጂው ሠው ቁጥር ልክ መሆኑ በሕጉ በግልጽ ተመልክቶ በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 16(1)(ሐ) መሠረት በንብረት ላይ ለሚደርስ ኪሣራ ግን የኃላፊነት ጣሪያው ከብር 100,000.00 ያልበለጠ ተብሎ መደንገጉ፤ ጉዳት በንብረት ላይ በሚደርስ ጊዜ ጉዳት የደረሠባቸው የባለንብረቶች ቁጥር ግምት ውስጥ ሳይገባ በጠቅላላው አንድ ጊዜ ለተከሠተ አደጋ በንብረት ላይ ለሚደርስ ኪሣራ የተገለጸ ጣሪያ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 203888 የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#ከኢፕድ_ማህደር ‼️
ጠጉሩን ሹሩባ ተሰርቶ የተያዘው ወንድ ልጅ ከእስሩ ነጻ ሆነ
አፍሮ ጠጉሩን ሹሩባ ተሰርቶ በመገኘቱ ለባህል ተቃራኒ የሆነ ድርጊት ፈጽሟል ተብሎ ከተከሰሰ በኋላ በቅርቡ ታስሮ የነበረው አበበ ወልደፃድቅ ከክሱ ነጻ ሆኖ መዝገቡ የተዘጋ መሆኑን የአዲስ አበባ አውራጃ ፍርድ አቃብያን ህግ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
አበበ ክስ ቀርቦበት ሊታሰር የቻለው በቅርቡ አፍሮውን ሹሩባ ከተሰራ በኋላ አዲስ አበባ ከተማ አፍንጮ በር አካባቢ 50...https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid02iQuLEVfPQVVhW1guLe227x24WgNghLDZpqnT5pxVMS72WrFWYFhCrgUrejqp3qSsl
የኢትዮጵያ የንግድ ህግ ስለ ሞግዚት ምን ይላል?
የኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 ምዕራፍ ሦስት ከ አንቀጽ 11 እስከ 13 የሚከተሉትን ይደነግጋል
1.  ሞግዚት የሆነ ሰዉ አካለ መጠን ባልደረሰው ሰው ስምና ስለእርሱ ሆኖ የንግድ ሥራ ሊሠራ አይችልም፤
2.  አካለ መጠን ባልደረሰ ሰው ሀብት ውስጥ የንግድ ድርጅት የተገኘ እንደሆነ ሞግዚቱ የንግድ ድርጅቱን ስራ የሚቀጥል ሰለመሆን አለመሆኑ አግባብነት ባለው ህግ በተመለከተው መሰረት ይሆናል
3.  የዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 እና 2 ድንጋጌዎች በፍርድ ለተከለከለ ሰው ሞግዚትም ተፈፃሚነት አላቸው፡፡
4.  አግባብነት ባለው ሕግ መሰረት ከሞግዚት አስተዳደር ነፃ የወጣ አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ የንግድ ስራ ሊሰራ ይችላል፣
5.  አንድ የንግድ ስራ የሚሰራ አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ አካለ መጠን እንደደረሰ አድርጎ ራሱን በንግድ መዝገብ አስገብቶ ከተገኘ አካለ መጠን ያልደረሰ መሆኑን ምክንያት አድርጎ በሦስተኛ ወገኖች ላይ መከራከሪያ ሆኖ ሊቀርብ አይችልም፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን:-
Email: fdremotri@gmail.com
fdremotri@motri.gov.et
facebook:- Ethiopianministryof tradeandregionalitegration
For trade license : www.etrade.gov.et
website: www.motri.gov.et