አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የዲጂታል መታወቂያ ምንነት እና የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 1284/2015 ዋና ዋና ገጽታዎች

ዘመናዊ የመታወቂያ ስርዓት በአንድ ሀገር ውስጥ ተግባራዊ ሲደረግ መሰረታዊ የሚባሉ ጠቀሜታዎች ያሉት ሲሆን፣ ከነዚህ ጠቀሜታዎች መካከልም ሃገራዊ ልማትን በአግባቡ ለማቀድ፣ ምጣኔ ሃብታዊ ሽግግር ለመፍጠር፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ የሀብት ብክነትን ለመቀነስ፣ ወንጀልን ለመከላከል፣ ፖሊሲዎች ሲቀረጹ እና የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ድግግሞሽን ለመቅረፍ እና አካታችነትን ለማጎልበት የሚረዳ መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡ በኢትዮጵያም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የበለፀገ፣ ዘርፍ ተሻጋሪ፣ መሠረታዊ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መዘርጋት አሰፈላጊ መሆኑ ታምኖበት የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ተቋቁሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት በግንባታና በሙከራ ሂደት ላይ ቆይቷል። በዚህ ሂደት ውስጥ ከተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች ጋር ለማስተሳሰር የሙከራ ትግበራ ስራዎችን በማከናወን ወደ 1.4 ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎችን መዝግቦ አብዛኞቹን የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ ተችሏል።

በዚህ የሙከራ ትግበራ ወቅት ከተከናወኑ ተግባራት ውስጥ ሌላው የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ማዘጋጀት ሲሆን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ "የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 1284/2015" አድርጎ አፅድቆታል፡፡ አዋጁ ከሌሎች ሀገሮች የመታወቂያ አዋጆች አንፃር ዘግየት ብሎ የወጣ በመሆኑ በሌሎች ሀገሮች የታዩ ክፍተቶችን ለመድፈን በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ዘመኑ የደረሰበትን የዲጂታል መታወቂያ በዘመናዊ መልኩ ለነዋሪዎች ለመስጠት እና ለማስተዳደር በማለም የወጣ ነው፡፡ አዋጁ በርካታ ጉዳዮችን የያዘ ሲሆን፣ በዝርዝር በሌላ ፅሁፍ የምንመለስበት ሲሆን፣ በዚህ ክፍል የአዋጁን ዋናዋና ድንጋጌዎች በተለይም ከዓላማዉ ጋር በማገናኘት ለማየት እንሞክራለን፡፡

1. የዲጂታል መታወቂያ ምንነት እና አገልግሎት

በየትኛውም ሀገር የሚገኝ የመታወቂያ ሥርዓት በሁለት የሚከፈል ሲሆን እነሱም አገልግሎት ተኮር መታወቂያ (Functional ID) እና መሰረታዊ መታወቂያ (Foundational ID) ናቸው፡፡ አገልግሎት ተኮር የመታወቂያ (Functional ID) ማለት የተወሰነ አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል መታወቂያ ነው። እንዲህ አይነት መታወቂያ፣ ከተሰጠበት አገልግሎት ውጭ ለሌሎች ነዋሪነትን እና ማንነትን በማረጋገጥ ለሚሰጡ አገልግሎቶች ተቀባይነት ላይኖራቸው ይችላል፡፡ መሰረታዊ መታወቂያ (Foundational ID) ማለት በተሰጠበት ሀገር ውስጥ በየትኛውም ቦታ ተቀባይነት ያለው እና ማንነትን በማረጋገጥ ለሚሰጡ የትኛውም አገልግሎቶች ተቀባይነት ያለው የመታወቂያ አይነት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ መሰረታዊ መታወቂያ (Foundational ID) ለአገልግሎት ተኮር መታወቂያዎች (Functional ID) እንደመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል፡፡

መሰረታዊ መታወቂያ በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ ስያሜዎች ሊኖሩት የሚችሉ ሲሆን ብሄራዊ መታወቂያ ወይም የዲጂታል መታወቂያ በብዛት መሰረታዊ መታወቂያ የሚጠራባቸው ስያሜዎች ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት ተግባራዊ ለማድረግ በሙከራ ላይ የሚገኘው የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት (Foundational ID) መሰረታዊ መታወቂያ የሚሰጥበት ስርዓት ነው፡፡ የዲጂታል መታወቂ ማለት ማንኛውም በሀገሪቱ ውስጥ የሚኖር ሰው ተቋሙ ወይም በተቋሙ ውክልና የተሰጠው አካል በሚያደርገው የምዝገባ ሂደት የባዮሜትሪክ እና ዲሞግራፊክ መረጃዎችን በመስጠት ከተመዘገበ በኋላ ማንነቱን ለማረጋገጥ የሚሰጥ ልዩ ቁጥር(Unique Number) ነው፡፡ ይህ ልዩ ቁጥር ወይም ዲጂታል መታወቂ የሚመነጨው ከግለሰቡ የባዮሜትሪክ እና ዲሞግራፊክ ዳታ በመሆኑ፣ ግለሰብን በልዩ ሁኔታ ለመለየት የሚስያስችል አስተማማኝ የመታወቂ ስርዓት ነው፡፡

ይህን የመታወቂያ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ እና የህግ ድጋፍ እንዲኖረው ለማስቻል በብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ፅ/ቤት የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ከተዘጋጀ በኋላ ረቂቁን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1284/2015 አድርጎ አፅድቆታል፡፡ በአዋጁ አንቀፅ 14 ላይ በግልፅ እንደተመለከተው የዲጂታል መታወቂያ የአንድን ነዋሪ ማንነትን ለማስረዳት ወይም ለማረጋገጥ እንደ ህጋዊ እና በቂ ማስረጃ ተደርጎ እንደሚወሰድ እና ማንኛውም ተጠቃሚ አካል ለነዋሪው ለሚሰጠው አገልግሎት የዲጂታል መታወቂያ እንደ አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ የሚያደርግ አሠራር በሚመለከተው ተቆጣጣሪ አካል ፍቃድ መዘርጋት እንዳለበት ተደንግጓል፡፡ ስለሆነም አሁን በኢትዮጵያ ተግባራዊ የሚደረገው ዲጂታል መታወቂያ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ተቀባይነት ያለው እና ማንነትን በማረጋገጥ ለሚሰጡ አገልግሎቶች እንደ አስገዳጅ የመታወቂያ አይነት የሚወሰድ ሲሆን፣ በዚህ መታወቂያ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆነ ማንኛውም ሰው በወንጀል እንደሚጠየቅ አዋጁ አንቀፅ 21/1/ በሚከተለው መልኩ ደንግጓል፡፡

"በዚህ አዋጅ እና ይህን አዋጅ ተከትለው በሚወጡ ደንቦች እና መመሪያዎች መሠረት ስልጣን ባለው አካል የተሰጠን ዲጂታል መታወቂያን እንደ ህጋዊ መታወቂያ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆነ ወይም ማንነትን ብቻ በማረጋገጥ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት ፍቃደኛ ያልሆነ ወይም በዚህ አዋጅ አንቀፀ 19 ላይ የተመለከተውን የመተባበር ግዴታ የተላለፈ ማንኛውም ሰው ከአስር ሺህ እስከ አንድ መቶ ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል"
ከላይ እንደተገለጸው ዲጂታል መታወቂያ የሚባሉው ልዩ ቁጥሩ ሲሆን፣ ይህንን መታወቂያ በካርድ መልኩ መያዝ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ተገቢውም ክፍያ በመፈፀም ከተቋሙ ወይም ተቋሙ ውክልና ከሰጠው ማንኛውም አታሚ ድርጅት የመታወቂያ ካርዱን ማግኘት የሚቻልበት ስርዓት ተዘርግቷል፡፡

2. የአዋጁ ዓላማ

የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 1284/2015 ዋና ዓላማው የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መዘርጋት ነው፡፡ የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ምንድን ነው የሚለው ሰፊ ትንታኔ የሚፈልግ ሲሆን፣ ጠቅላላ የሆነ ትርጓሜውን ግን ከዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ዓላማ ከሚለው ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በመሆኑም በአዋጁ አንቀፅ 5 ላይ እንደተመለከተው የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ዓላማ ነዋሪዎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ሲንቀሳቀሱ በቀላሉ የመታወቅ መብታቸው እንዲረጋገጥ በማድረግ ለሰብአዊ መብቶቸ አከባበር እና ለመልካም አስተዳደር መሻሻል አስተዋፅኦ ማድረግ፣ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ግለሰቦችን በቀላሉ ለመለየት የሚያስችል የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት በመዘርጋት በአገልግሎት ሰጪ እና አገልግሎት ተቀባይ መካከል እምነት እንዲጎለብት ማድረግ፣ ሕገ-ወጥ ተግባራትን መከላከል፣ ሀገር አቀፍ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት በማደራጀት ሀገራዊ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እና እቅዶች ሲቀረጹ እና የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ድግግሞሽን መቅረፍ፣ በዚህም የሀብት ብክነትን መቀነስ እና አካታችነትን ማጎልበት፣ የነዋሪዎችን የዲሞግራፊክ እና ባዮሜትሪክ መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል ሥርዓት በመዘርጋት፣ ለሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ አካላት የመታወቂያ ሥርዓት መረጃ ምንጭ ሆኖ ማገልገል እና አገልግሎት ተኮር የሆኑ የመታወቂያ ሥርዓቶች ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት እንዲሸጋገሩ ማጠናከር መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡

3. የዲጂታል መታወቂያ የማግኘት መብት እና ዲጂታል መታወቂያ ለማግኘት ስለሚሰበሰቡ መረጃዎች
በአዋጁ አንቀፅ 7 ላይ በግልፅ እንደተመለከተው ማንኛውም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ሰው የባዮሜትሪክ እና ዲሞግራፊክ መረጃዎችን በመስጠትና በመመዝገብ የዲጂታል መታወቂያ የማግኘት መብት አለው፡፡ ነዋሪው የዲጂታል መታወቂያ ለመውሰድ እሱነቱን ለማረጋገጥ የሚያገለግሉ የመታወቂያ ሰነዶች እና ሌሎች በተቋሙ ተቀባይነት ያላቸውን ሰነዶች ወይም የሰው ምስክር ማስረጃዎችን በመጠቀም በማረጋገጥ መመዝገብ ይችላል፡፡ ከላይ እንደተመለከተው ወደ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓት የሚገባ የግል መረጃ የእያንዳንዱን ተመዝጋቢ የዲሞግራፊክ መረጃ እና ባዮሜትሪክ መረጃን ያካተተ መሆን ያለበት ሲሆን፣ የዲሞግራክ መረጃ የሚባሉትም ስም ፣ የአባት ስም ፣ የአያት ስም ፣ ወይም በዚህ መልክ የተደራጀ ህጋዊ ስም ለሌለው ተመዝጋቢ ተቋሙ ህጋዊ የሆነውን ስያሜ ወይም ተመዝጋቢው በአካባቢው ማህበረሰብ የሚጠራበትን ስም፣ ዜግነት፣ የትውልድ ቀን፣ ወር እና ዓመት፣ ፆታ፣ መኖሪያ አድራሻ ሲሆኑ እንደአስፈላጊነቱ ስልክ ቁጥር፣ የኢሜይል አድራሻ እና ፖስታ አድራሻንም ሊያካትት ይችላል፡፡ የሚሰበሰቡት የባዮሜትሪክ መረጃዎች ድግሞ የአስር ጣት አሻራ፣ የሁለቱም አይኖች ብሌን እና የፊት ገፅታ ናቸው፡፡ እነዚህን የባዮሜትሪክ እና ዲሞግራፊክ መረጃዎች የሰጠ ማንኛውም ሰው የዲጂታል መታወቂያ ማግኘት ይችላል፡፡

አንዳንድ ጊዜ የባዮሜትሪክ መረጃዎችን ለመስጠት የሚቸገሩ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ጣት የሌለው ሰው፣ በእርጅና እና በተለያዩ ምክንያቶች አሻራቸው የማይነበብ ሰዎች በሚኖሩበት ጊዜ እና መሰል ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ፣ በዲሞግራፊክ መረጃ ብቻ መታወቂያውን መስጠት የሚገባ ስለመሆኑ በአዋጁ ተደንግጓል፡፡

4. የዲጂታል መታወቂያ ከሌሎች መታወቂያዎች፣

የባንክ አካውንቶች እና መሰል ማንነትን ለማረጋገጥ ከሚያገለግሉ ሰነዶች ጋር የሚኖረው ግንኙነት
የዲጂታል መታወቂያ ራሱን የቻለ መታወቂያ ቢሆንም፣ ሌሎች መታወቂያዎችን የሚያጠናክር የመታወቂያ አይነት ነው፡፡ ሁሉም ከላይ በርዕሱ ላይ የተመለከቱን ማንነትን ለማረጋገጥ የሚያገለግሉ ሰነዶች ወደ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓት እንዲገቡ የሚደርግ አሰራር ተዘርግቷል፡፡ ለምሳሌ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤቱ ከብሄራዊ ባንክ ጋር በመተባበር ከሁሉም በሀገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች ጋር ስምምነት ላይ በመድረስ፣ ሁሉም ባንኮች ደንበኞቻቸውን ወደ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ለማስገባት ስራ ጀምረዋል፡፡ እንዲሁም ፅህፈት ቤቱ እና ገቢዎች ሚኒስቴር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ሁሉንም ግብር ከፋይ የታክስ ከፋይነት መለያ ቁጥሩን መሰረት በማድረግ ወደ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ለማስገባት የሚስችል ስራ ተጀምሯል፡፡ ከዚህ መገንዘብ የምንችለው የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ሌሎች መታወቂያ ስርዓቶችን እያጠናከረ የሚሄድ የመታወቂያ አይነት መሆኑን እና ራሱንም ችሎ ማናቸውንም አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል የመታወቂያ አይነት መሆኑን ነው፡፡

5. የመረጃ አጠባበቅ ስርዓት

የዲጂታል መታወቂያ ለማግኘት የሚሰበሰቡ መረጃዎች በተለይም የባዮሜትሪክ መረጃዎች በጥንቃቄ ካልተያዙ ለተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ሊያጋልጡ ይችላሉ፡ ስለዚህ ለዲጂታል መታወቂያ የተሰበሰቡ መረጃዎች በጥንቃቄ መያዝ ያለባቸው በመሆኑ አዋጁ ተቋሙ የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት የግል መረጃን በአስተማማኝነት የሚይዝ ጠንካራ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት አለበት፤ በሚል የደነገገ ሲሆን፣ አሰራርና ህግን ጠብቆ በዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ለተሰበሰበ የማንኛውም ተመዝጋቢ ግላዊ መረጃ ያለ ተመዝጋቢው ፈቃድ ለሌላ ሰው መግለጽ ፣ ማስተላለፍም ሆነ እንዲለወጥ መፍቀድ የተከለከለ መሆኑን ህጉ በግልፅ አስቀምጧል፡፡ ይህን ክልከላ መተላለፍም በወንጀል የሚስጠይቅ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጥፅ 25 ላይ ተደንግጓል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ለፍትህ ስራ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በህግ ስልጣን ለተሰጠው ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረት የግል መረጃው ለሚመለከተው ህጋዊ አካል ሊገለጽ ወይም ሊተላለፍ እንደሚችል የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 1284/2015 አንቀፅ 16 ተደንግጓል፡፡

በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
የደምዳሚ (ድምዳሜ) ማስረጃ /conclusive evidence/ 5 የሰበር ችሎት ትርጓሜዎች

1//// የተሟላና ሙሉ ዕምነት የሚጣልበት ማስረጃ

የልዩ አዋቂ /expert/ የሚደርስበት የመጨረሻ አስተያየት ከሚኖረው ሙያዊ ዕውቀት አድማስ፣ ከሚታገዝበት መሣሪያና ከመሳሰሉት ጋር የተሟላና ሙሉ ዕምነት የሚጣልበት ማስረጃ /conclusive evidence/ ሊሆን ስለማይችል በዓይን ምስክሮች የተነገረን ፍሬ ነገር ለማስተባበል የሚያበቃ አቅም አይኖረውም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 43453 ቅጽ 12

የትራፊክ ፖሊስ የአደጋ ፕላን ሪፖርት የባለሙያ ሙያዊ አስተያየትን በወረቀት ላይ ስዕላዊ በሆነ መንገድ የሚያስቀምጥ በባለሙያ የሚረጋገጥ ሰነድ በመሆኑ እንደ ማንኛውም የልዩ አዋቂ የምስክርነት ቃል በተገቢው መንገድ ሊመዘን የሚገባው የማስረጃ አይነት እንጅ ሁልጊዜ ድምዳሜ ማስረጃ (Conclusive Evidence) ያለመሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 92141 ቅጽ 17

2//// አሳሪ ማስረጃ

በአስተዳደር አካል የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ነው ተብሎ የምስክር ወረቀት መስጠት ማስረጃውን ደምዳሚ ወይም አሳሪ (Conclusive Evidence) የሚያደርገው አይደለም፡፡ ይልቁንም ይኸው ማስረጃ የተሰጠበት አግባብ በፍ/ህ/ህ/ቁ. 1195 ድንጋጌ ስር በተመለከቱት ሁኔታዎች መሰረት ስለመሆኑ ማስረዳት ከተቻለ በፍ/ህ/ቁ. 1195 ስር የተመለከተው ሕጋዊ ግምት ሊስተባበል የሚችል (rebuttable legal presumption) መሆኑን ከድንጋጌዎቹ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 64014 ቅጽ 13

3//// ማስተባበያ ሊቀርብበት የማይችል ወሳኝ ማስረጃ

አንድ ለማይንቀሳቀስ ንብረት የተሰጠ የባለሃብትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባለሃብትነትን በተመለከተ የህግ ግምት የሚያሰጥ ቢሆንም በሌላ ተቃራኒ ማስረጃ ሊስተባበል፣ በተቃራኒው ከሚቀርቡት ማስረጃዎች ጋር ሊመዘን የሚችል እንጂ እንጅ ማስተባበያ ሊቀርብበት የማይችል ወሳኝ /conclusive evidence/ ያለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 67011 ቅጽ 13 

4//// የመጨረሻ ማስረጃ

የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ማስረዳት ከተቻለ ፍ/ቤት ልጅ ነው ሲል የሕግ ግምት ሊወስድ የሚችል መሆኑን የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 157/1/ ያመለክታል፡፡ ከአንቀፁ መረዳት እንደሚቻለው የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ማረጋገጥ የመጨረሻ ማስረጃ (conclusive evidence) ሳይሆን የሕግ ግምት ብቻ ነው፡፡ ግምቱም ቢሆን አስገዳጅነት ያለው የሕግ ግምት አይደለም፡፡ ግምቱን የሚቃወም ወገን ማስረጃ በማቅረብ ማፍረስ እንደሚችል ንዑስ አንቀፅ 2 ይደነግጋል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 42648 ቅጽ 10

5///// ክርክር ሊነሳበት የማይችል፣ ሙሉ እምነት ሊጣልበት የሚችል ማስረጃ

ልጅነት የሚረጋገጥበት ዋናው ማስረጃ የልደት ምስክር ወረቀት እንደሆነ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 154 ላይ ተመልክቷል፡፡ ይህ ማለት ግን የልደት ምስክር ወረቀት ክርክር ሊነሳበት የማይችል ሙሉ እምነት ሊጣልበት የሚችል /Conclusive/ ማስረጃ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 33440 ቅጽ 5
Federal Judges Code of Conduct and Disciplinary Procedure Regulation
Regulation Number 1/2013
link: bit.ly/40yp2Jy



📌📌Note
: This translation was undertaken by volunteer Year III students of Addis Ababa University School of Law for the benefit of fellow students who are not native Amharic speakers.
The degrees that make students cry: A look at the most challenging courses in the world

What are the hardest degrees in the world
1. Aerospace Engineering
2. Biomedical Engineering
3. Law 👈
4. Chartered Accountancy
5. Architecture
6. Medicine
7. Nursing
8. Dentistry
9. Psychology
10. Artificial Intelligence

Law 👈👈🙏 Respect for lawyers
Speak to any of  your friends who are studying law, and they might share with you a common complaint: there’s too much to read. 
https://www.studyinternational.com/news/hardest-degrees-in-the-world/

https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
#የጥብቅና #ፈቃድ
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥብቅና ፈቃድ፣

ምዝገባ እና ፈተና መቼ እንደሆነ እስከ አሁን የታወቀ ነገር የለም።
አዲስ ነገር ሲኖር የምናሳውቅ ይሆናል።
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
የመሸሸግ ወንጀል

በንብረት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን አስምልክቶ በወንጀል ህጉ ከተደነገጉ በንብረት ላይ ከሚፈፀሙ ወንጀሎች መካከል የመሸሸግ ወንጀል አንዱ ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የመሸሸግ ወንጀልን ምንነት እና የሚያስከትለውን ተጠያቂነት እንመለከታለን፡፡

የመሸሸግ ወንጀል ምንነት

በወንጀል ህጉ አንቀፅ 682 መሰረት መሸሸግ ማለት ዕቃው የተገኘው በአንድ ንብረት ላይ በተፈፀመ ወንጀል ምክንያት መሆኑን እያወቁ ወይም ማወቅ ሲገባ ይህንኑ ዕቃ በመግዛትም ሆነ በተውሶ፣ በስጦታ፣ በመያዣነት መቀበል ወይም በማናቸውም ይህን በመሳሰለ አኳኋን መውሰድ፣ መገልገል፣ ማስቀመጥ ወይም መደበቅ፣ አሳልፎ መሸጥ ወይም በመሸጥና በመለወጥ ስምምነት ውስጥ አገናኝ በመሆን መርዳት እንዲሁም የወንጀል ተግባር ባስገኘው ፍሬ የመጣ መሆኑን እያወቁ በዚሁ በወንጀል ድርጊት በተገኘ ዕቃ ምትክ በልዋጭ የተገኘውን ወይም በሽያጭ ዋጋ የተገዛውን ሌላ አይነት ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ መቀበል ነው፡፡

በዚህ መሰረት የመሸሸግ ወንጀል ተፈፅሟል ለማለት
 ተሸሽጎ የተገኘው ዕቃ በአንድ ንብረት ላይ በተፈፀመ ወንጀል ምክንያት የተገኘ ወይም የወንጀሉ ተግባር ባስገኘው ፍሬ የመጣ መሆን
 ሸሻጊው ዕቃው በወንጀል ምክንያት መገኘቱን ማወቅ ወይም መገመት ሲገባው በቸልተኝነት ወንጀሉን የፈፀመ መሆን
 በወንጀል ተግባር የተገኘን ዕቃ የገዛ፣ የተቀበለ፣ የወሰደ፣ የተገለገለ ወይም በመሰል ድርጊት ውስጥ የተገኘ መሆን አለበት፡፡

የመሸሸግ ወንጀል የህግ ተጠያቂነት
ከላይ በተገለፀው ሁኔታ የመሸሸግ ወንጀል አስቦ የፈፀመ ማንም ሰው በቀላል እስራት ወይም ከባድ በሆነ ጊዜ ከአምስት አመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትና በመቀጮ ይቀጣል፡፡ ድርጊቱ በቸልተኝነት የተፈፀመ እንደሆነ ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ ይሆናል፡፡

ከባድ መሸሸግ

የመሸሸግ ወንጀል የተፈፀመው
 በሰዎች ወይም በንብረት ላይ ወንጀል ለመፈፀም የተቋቋመ ቡድን አባልነት እንደሆነ
 ወንጀል ፈፃሚው የተሰጠውን የሥራ ወይም የንግድ ፍቃድ በወንጀል የተገኘን ንብረት ለመሸሸግ ተገልግሎበት እንደሆነ
 ወንጀል ፈፃሚው የሸሸገው ንብረት የውንብድና፣ የዘረፋ፣ የባህር ውንብድና፣ የቅሚያ፣ የማስፈራራት ፍሬ መሆኑን ወይም ዕቃው የተገኘው ከመከላከያ ሠራዊት ንብረት ወይም በጠቅላላው ከመንግስት ሀብት ውስጥ መሆኑን እያወቀ እንደሆነ
ወንጀሉ ከባድ የመሸሸግ ወንጀል የሚሆን ሲሆን ፈፃሚውም አስራ አምስት አመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና እስከ ብር ሀያ ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ እንደሚችል ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ህብረተሰቡ በማወቅም ወይም በቸልተኝነት በእንድ የወንጀል ድርጊት አማካኝነት የተገኘን ንብረት መግዛት፣ መዋስ፣ በስጦታ ወይም በመያዣነት መቀበል ወዘተ በወንጀል የሚያስቀጣ መሆኑን በመገንዘብ ዕቃዎችን ሲገዛም ሆነ በተለያዩ መንገዶች ሲቀበል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
ጎረቤቶችን እንቅልፍ በመንሳት የተከሰሰው አውራ ዶሮ እንዲታረድ የናይጄሪያ ፍርድ ቤት ወሰነ

ናይጄሪያ ውስጥ ጉዳዩ ፍርድ ቤት የደረሰው ጩኸቱ ጎረቤቶችን ሰላም የነሳው አውራ ዶሮ በድምጽ ብክለት ምክንያት እንዲታረድ ተፈረደበት።

በአንድ አውራ ዶሮ ምክንያት እንቅልፍ አጣን ያሉት ናይጄሪያውያን ለፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ነው ባለቤቱ አውራ ዶሮውን እስከ መጪው አርብ ድረስ እንዲያርደው መወሰኑን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን የዘገቡት።

በሰሜናዊ ናይጄሪያ ካኖ ግዛት ውስጥ የሚገኘው ፍርድ ቤት ሁለት ሰዎች የአውራ ዶሮው የማይቋረጥ ጩኽት ሰላም አሳጣን፣ እንቅልፍ ነሳን በማለት ነበር የቀረበለትን ክስ ተከትሎ ነው ብይን የሰጠው።

በዶሮው እና በባለቤቱ ላይ ክስ ካቀረቡት ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆነው ግለሰብ ዩሱፍ ሙሐመድ፣ የአውራ ዶሮው ጩኽት በቤቱ ውስጥ የሰላም እንቅልፍ የማግኘት እና የማረፍ መብቱን እንደጣሰበት ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል።

የአውራ ዶሮው ባለቤት ኢሲያኩ ሹይቡ የቀረበውን ክስ ተከትሎ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው ዶሮውን በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ነገ አርብ ለሚከበረው የስቅለት በዓል ለቤተሰቦቹ እንደገዛው እና ብዙ ጊዜ አለመቆየቱን ተናግሯል።

የአውራ ዶሮው ጩኽት ሰላም አሳጣን ያሉት ጎረቤቶቹም ዶሮው ለበዓሉ አርብ ዕለት የሚታረድ በመሆኑ ጥቂት ቀናት ብቻ እንዲታገሱት ጠይቋል።
https://bbc.in/3ZONkxY
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
ታክስ የመጣል ሥልጣን

ለአንድ መንግስት ከታክስ የሚሰበሰብ ገቢ ለህልውና እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ታክስ የመጣልና የማስከፈል ሥልጣን ለመንግስት ብቻ የተሰጠ ሥልጣን ነው፡፡ ለግለሰብ ወይም ለሌላ አካል የዚህ ዓይነት ሥልጣን በየትኛውም ዓለም አይሰጥም ፡፡
ለፌደራል መንግስት በህገ መንግስቱ በተሰጠው ታክስ የመጣልና የማስከፈል ሥልጣን መሠረት ሁለት መሠረታዊ የታክስ አጣጣል ዓይነቶች አሉ፡-

1. ነዋሪነትን እና
2. የገቢ ምንጭን መሠረት ማድረግ ናቸው፡፡

እነዚህን መሠረት በማድረግ፡-

1. የኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች በዓለም ዙሪያ በሚያገኙት ገቢ እንዲሁም
2. ኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎች የኢትዮጵያ ምንጭ በሆነ ገቢ ላይ ታክስ የሚጣልባቸው ይሆናል፡፡

ነዋሪነት በሶስት ከፍሎች ይከፈላሉ

1. ነዋሪ የሆነ ሰው/ግለሰብ
2. ነዋሪ የሆነ ድርጅት
3. ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የመንግስት ተቋማት

አንድ ግለሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ ነው የሚባለው ፡-

1. በኢትዮጵያ ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ ያለው ከሆነ
2. የኢትዮጵያ ዜግነት ያለውና ውጪ ሀገር በኮንሱላር በዲፕሎማቲክ ወይም በመሳሰሉት ስራ ተመድቦ የሚሰራ
3. በኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሳያቀርጥ ወይም በመመላለስ ከ183 ቀናት በላይ ከኖረ ነው፡፡

አንድ ድርጅት ነዋሪ ነው የሚባለው፡-

1. በኢትዮጵያ ውስጥ ከተቋቋመ ወይም ከተመሠረተ
2. የድርጅቱ ወሳኝ የሆነ አመራር የሚያከናውንበት ስፍራ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እንደሆነ ነው
ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ፍሰት ማነቆ የሆኑ 80 ህጎች ማሻሻሏን አስታወቀች


የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እንዳለው ለንግድ እና ኢንቨስትመንት አመቺ ያልሆኑ ህጎች መሻሻላቸውን አስታውቋል፡፡
https://am.al-ain.com/article/ethiopia-says-revises-investment-laws
Forwarded from የፍቅር ሰው
በየትኛውም ህግ ነው ተማሪዎች apparentship ወተው የተግባር ልምምድ ሳያደርግ የሚመረቁት
ከምንም በላይ የወራቤ ተማሪዎች ፍትህን ይፈልጋል።
በአሁኑ ሰዓት ተማሪዎቹ በመንከራተት ላይ ይገኛሉ
እንደሚታወቀው ይህ ወክት ተማሪዎች ለመውጫ ፈተና የሚዘጋጅበት ጊዜ ነው። በተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት ከንባብ ሙድ እየወጡ ይገኛሉ።

ውድ የአለ ቤተሰቦች ለሚመለከተው አካል በማስተላለፍ እንድትተባበሩ እንጠይቃለን።
ስለሚታደርጉት ትብብር ከልብ እናመሰግናለን።
አባቱን ገድሏል የተባለው ተከሳሽ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ።

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወላጅ አባቱን ገድሏል በተባለው አቶ መሐሩ ዮሐንስ በተባለ ተከሳሽ ላይ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ፍርድ አስተላልፏል።

ድርጊቱ የተፈጸመው በከምባታ ጠምባሮ ዞን በሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ ሌሾ ማዞሪያ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሙጉንጃ ተብሎ በሚጠራበት ቦታ ጥር 2 ቀን 2015 ዓ/ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ነው።

የዞኑ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እንዳስታወቀው ግለሰቡ ድርጊቱን ከመፈጸሙ በፊት "የሰበሰብከውን ንብረት አትበላም" እያለ ሲዝት እንደነበርና ምሽት ላይ ሟች ተኝቶ ባለበት በዘነዘና ጭንቅላቱን በመቀጥቀጥ ግድያውን መፈጸሙን ገልጿል።

አቃቤ ህግም በሰውና በሰነድ ማስረጃ አረጋግጦ ተከሳሽ ክሱን እንዲከላከል ቢታዘዝም መከላከያ ማስረጃ የሌለው መሆኑን በጽሑፍና በቃል ማስረጃ የለኝም ብሎ በማረጋገጡ ሚያዝያ 3 ቀን በዋለው ችሎት ተከሳሹ በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡

@tikvahethmagazine
Ethiopia is the third most expensive country to live in based on cost of living .

The high cost of living is a major concern for many individuals and families around the world. It is an issue that affects people of all income levels and can significantly impact their quality of life. Several factors contribute to the high cost of living in a country, including economic policies, inflation, and the cost of essential goods and services.

One of the primary reasons for the high cost of living in a country is the state of its economy. Countries with a strong economy tend to have a higher cost of living due to the high demand for goods and services. This is because when people have more money to spend, they are willing to pay more for the things they need and want.

Inflation is another factor that contributes to the high cost of living. Inflation occurs when the general price level of goods and services increases over time. This means that people have to spend more money to buy the same goods and services they could buy for less in the past. Inflation can be caused by various factors, such as increases in the money supply, changes in government policies, or external factors like global supply chain disruptions.

Based on the analysis Ethiopia reason of higher cost of living is not due to strong economy which creates strong demand rather due to high inflation which rocken the economy badly.

Rank Country Cost of living index Local purchasing power
1. Senegal 46.4 21.7
2. Ivory Coast 42.7 7.8
3. Ethiopia 42.3 11.6
4. Mauritius 42.2 30.8
5. Zimbabwe 40.8 18.7
6. South Africa 37.8 83.9
7. Namibia 35.8 51.3
8. Botswana 34.4 63.6
9. Cameroon 33.6 18.4
10. Kenya 32.4 32.8

EII.