አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ሠ/መ/ቁጥር 211841 ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ/ም
በአንድ ወገን ብቻ የሚደረግ ዉል መሠረዝ (Unilateral cancellation of contract) ተግባራዊ ሊሆን የሚችለዉ በፍ/ብ/ሕጉ ከቁጥር 1786 እስከ 1889 ከተደነገጉት አራት ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ ተሟልቶ ሲገኝ ነዉ፡፡እነዚህም ቅድመ ሁኔታዎች፡-(1) የዉል ማፍረሻ የሚሆኑ የዉል ቃሎች በዉሉ ተገልጸዉ ሲገኙና ይሄዉ ሁኔታ ተፈጽሞ ሲገኝ ፤(2) ቁርጠኛ የሆነ የዉል መፈጸሚያ ጊዜ በዉሉ ከተመለከተ፣በማስጠንቀቂያዉ ላይ በተሰጠዉ ጊዜ ወይም በፍርድ ቤት በተሰጠ የችሮታ ጊዜ ዉስጥ ተዋዋዩ ግዴታዉን ካልተወጣ ፤(3) ከተዋዋዮቹ አንደኛዉ ወገን የገባበትን ግዴታ ለመፈጸም የማይቻለዉ ሆኖ ከተገኘና በዚህ ምክንያት የዉሉ መሰረታዊ ስምምነት ከተነካ ፤ እንዲሁም (4) ከተዋዋዮቹ አንዱ ወገን የዉል ግዴታዉን የማይፈጽም ስለመሆኑ ግልጽ በሆነ መንገድ ሲያሳዉቅ የሚሉ ናቸዉ፡፡ሕጉ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች በመስፈርትነት ያስቀመጠዉ በተቻለ መጠን በሕግ አግባብ የተደረጉ ዉሎች እንዲፈጸሙ ጥበቃ ለማድረግና በተናጠል የሚደረገዉ የዉል መሰረዝ የመፍትሄ አማራጭ በልዩ ሁኔታ በተወሰኑ ሁኔታዎች ብቻ ተፈጻሚ እንዲሆን በመፈለግ ነዉ፡፡ ስለሆነም አንደኛዉ ተዋዋይ ወገን ሌላዉ ወገን ግዴታዉን ባለመወጣቱ ዉሉን በተናጠል ሰርዣለሁ በማለት በተከራከረ ጊዜ ከተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ቢያንስ አንዱ መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
March 21, 2023
ታክስን/ግብርን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት

ታክስዎን/ግብርዎን በወቅቱ ሲከፍሉ ከብዙ እንግልት ከመዳንዎ በተጨማሪ አላስፈላጊ ቅጣት ከመቀጣት ይድናሉ፡፡ ግብርን በወቅቱ ከከፈሉ ደግሞ ለሀገርዎ እና ለእርስዎ የሚጠቅመውን በወቅቱ እና በአስፈላጊው ወቅት እንዳደረጉ ይቆጠራል፡፡

ታክስዎን በተለያየ ምክንያት ሳይከፍሉ ካዘገዩ ከሚደርስብዎት ውጣ ውረድ በተጨማሪ ቅጣቶችንም ለማስተናገድ ይገደዳሉ፡፡ ከነኚህ ቅጣቶች ውስጥ ለእርስዎ ለግንዛቤ ይረዳዎት ዘንድ የሚከተሉት ተቀንጭበው ቀርበዋል፡፡

ማንኛውም ታክስ ከፋይ በታክስ መክፈያ ጊዜው ውስጥ ታክስ ሳይከፍል ከቀረ ለዘገየበት ጊዜ፦
1. ለአንድ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ 5% (አምስት በመቶ)፤ እና
2. ከዚያ በኋላ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ ተጨማሪ 2% (ሁለት በመቶ)፤ ቅጣት ይከፈላል፡፡
I. የሚጣለው የቅጣት መጠን ከዋናው የታክስ ዕዳ መብለጥ የለበትም፡፡
II. መከፈል በማይገባው ታክስ ላይ ሳይከፈል በዘገየበት የተጣለ ቅጣት ለታክስ ከፋዩ ይመለሳል፡፡
III. ታክስን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ተቀንሶ ከሚከፈል ታክስ ጋር በተገናኘ የሚጣል ቅጣት በሚመለከተው ያልተከፈለ ታክስ ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
March 21, 2023
222680.pdf
869 KB
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ላይ የሚገኘው parol evidence rule በውል አዋዋይ ፊት ተረጋግጦ ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል መኖሩ በሚታመንበት ጊዜ ተፈጻሚነት የለውም። የውሉ ይዘት ለምሳሌ የገንዘቡ መጠን፡ በውሉ ላይ ያለው ቀን ወዘተ በሌላ ውጫዊ ማስረጃ ሊስተባበል ይችላል።
በውል አዋዋይ ፊት ተረጋግጦ ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል መኖሩ ታምኖ የውሉ ይዘት ፊርማን ጨምሮ በአከራከረ ጊዜ በምን አይነት ማስረጃ ሊረጋገጥ ይገባል? የሚለው ጥያቄ በተመለከተ የሰበር ችሎት የሚከተለውን የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
የቤት ሽያጭ ውል በሕግ ሥልጣን በተሰጠው ውል አዋዋይ ፊት መደረግ አለበት በሚል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር የተደነገገበት አንዱ አላማ ውሉ በጽሁፍ በሰፈረው አግባብ በእርግጥ የተደረገ ስለመሆኑ እና ይዘቱም እምነት የሚጣልበት መሆኑን ለማረጋገጥ ነው፡፡በመሆኑም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ስር በጽሑፍ ሰነድ ላይ የሚገኝ የስምምነት ቃል እንዲሁም በላዩ ላይ የተጻፈው ቀን በፈራሚዎቹ መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ነው የሚለው በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1678/ሐ፣1719/2 እና 1723/1 ስር በተደነገገው መሰረት በሕግ የታዘዘውን የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትሎ ለተደረገ ውል እንጂ ለማንኛውም ውል አይደለም፡፡
March 24, 2023
🔹The Commercial Bank of Ethiopia New Vacancy

Position :1 Senior Attorney
Position :2 Senior Legal Advisor
Position :3 Legal Surveillance Officer

Education  : LLM/LLB Degree in Law , Banking, Financial Institutions or other Business Organizations.Diploma in police science or Diploma in social science fields

Date March 27, 2023 - April 05, 2023.

How to Apply
   👇👇👇
https://ethiolatestjobs.com/job/commercial-bank-of-ethiopia/

Share for your friends
     👇👇👇
https://t.me/shegarjob
March 25, 2023
በምስሉ ላይ የምትመለከቱት Ricky Jackson ይባላል። Cleveland, Ohio ነዋሪ ሲሆን ገና በ18 አመቱ በለጋ እድሜው ባልሰራው ወንጀል የሞት ፍርድ ተፈርዶበት 39 አመት ከታሰረ በኋላ (አብዛኛውን ግዜ የሞት ፍርድ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር ካላፀደቁት ወደ እድሜ ልክ ይለወጣል)፣ ትክክለኛው ወንጀል ፈጻሚ በመገኘቱ ዳጎስ ያለ ካሳ ተከፍሎት በነፃ የተለቀቀ ሰው ነው።

እናም ልክ ከእስር ቤት ተለቆ ሲወጣ ያሳሰረውን ሰው አገኘውና ... «ይቅር ብዬሃለው» .... ብሎ አቀፈው።

ቃለ መጠይቅ ላደረጉለት ጋዜጠኞች ደግሞ እንዲ ሲል ተናገረ :-

....«እስር ቤት ውስጥ ነህ ማለት እስረኛ ነህ ማለት አይደለም»....

ነጻነት ያለው ያላችሁበት ስፍራ ላይ ሳይሆን አይምሯቹ ውስጥ ነው። የቂምና የጥላቻ እስረኛ እንዳትሆኑ ይቅር በሉ!!
ይቅር በሉ፣ መራመድ አታቁሙ ፣ ጉዳታችሁ ላይ አትቆዩ! ህይወት ሰፊና ፣ ብዙ ደርዝ ያላት የጉዞ ሃዲድ ናት!!


ይቅርታ ለራስ የሚሰጥ ድንቅ ስጦታ ነው ሰው ይቅር ማለት ሲጀምር ህይወት ይጀምራል።
የበደለንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሣይሆን ፍቅርን ማስተማር ፣ ቀንነትን መዝራት ፣ ህይወትን ማደስ ነው።

ፈጣሪ ይቅርታን የሚጠይቅ አንደበትና ይቅር የሚል ብሩህ ልብ ይስጠን!
ምንጭ ከአንቂ መጻሕፍት ገፆች
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
March 25, 2023
Urgent Vacancy
                                              
1. Driver
Full time

Work station: Addis Ababa

👉Having experience is advisable.

          👉 How to Apply 👈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
consultantentrust@gmail.com

Deadline
March, 30/2023


Share for your friends
     👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
March 26, 2023
ህግ ፣ኅግ ወይስ ሕግ?
Anonymous Poll
33%
ህግ
2%
ኅግ
65%
ሕግ
March 26, 2023
March 28, 2023
March 29, 2023
የመገናኛ ብዙኃን በችሎት ዘገባ ጊዜ ሊከተሏቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

መገናኛ ብዙኃን ዘርፈ ብዙ መረጃዎችን ለህዝብ የሚያቀርቡ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ለህዝብ ከሚያቀርቧቸው መረጃዎች መካከል የፍርድ ቤት ክርክሮችን የተመለከቱ መረጃዎች ይጠቀሳሉ፡፡ በህግ መሰረት እንይገለፁ ከተከለከሉ ወይም የፍርድ ቤት ነፃነትን የሚጋፉ ካልሆነ በቀር የሚሰጡ ውሳኔዎች፣ ትእዛዞች እንዲሁም ሌሎች ሂደቶች ለህዝብ ግልፅ በመሆናቸው መገናኛ ብዙህን መረጃዎቹን ለህዝብ ያደርሳሉ፡፡ መገናኛ ብዙኃን እነዚህ ግልፅ የሆኑ የችሎት ሥራዎች እና የክርክር ሂደቶች ሲዘግቡ ግን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የመገናኛ ብዙኃን ምንነት፣ መገናኛ ብዙኃን በችሎት ዘገባ ጊዜ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች እና የሥነ ምግባር ሁኔታዎች ይዳሰሳሉ፡፡
የመገናኛ ብዙኃን ምንነት
በመገናኛ ብዙኃን በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀፅ 2(1) መሠረት መገናኛ ብዙኃን ማለት በየጊዜው የሚወጣ ህትመትን የብሮድካስት አገልግሎትን እና የበይነመረብ የመገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም የዜና እና የፕሮግራም አገልግሎት ለሕዝብ ለማቅረብ የተቋቋሙ አካላት ሲሆኑ ይህም መፃሕፍትን፣ ማኅበራዊ መገኛኛ ብዙኃንን፣ ጦማሮችን እና በየጊዜው የሚወጣ ህትመት አካል ያልሆኑ ፎቶ፣ ስዕልና ካርቱን ሳይጨምር የዜና አገልግሎት ድርጅቶችን የሚያካትት ነው፡፡
በችሎት ዘገባ ወቅት ሊደረጉ የሚገቡ ጥንቃቄዎች
1. የተከሳሽን ንፁህ ሆኖ የመገመት መብት ማክበር
ማንኛዉም ተከሳሽ የጥፋተኝነት ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት ከወንጀል ንፁህ ሆኖ የመገመት መብት እንዳለው በህግ መንግስቱ አንቀፅ 20/3/ ስር ተመላክቷል፡፡ ምክንያቱም ከክርክር በኋላ ተከሳሹ ነፃ ሆኖ ሊገኝም ስለሚችል ነው፡፡ በመሆኑም ጋዜጠኖች የችሎት ዘገባዎችን ሲሰሩ የጥፋተኝት ፍርድ ያልተሰጠበትን ተከሳሽ ጥፋተኛ አድርጎ ከመዘገብ መቆጠብ አለባቸው፡፡
2. ሚዛናዊ መሆን
መገናኛ ብዙኃን በክርክር ላይ ባለ እና ውሳኔ ባልተሰጠው ጉዳይ ላይ አንዱ ወገን አሸናፊ በሚያስመስል መልኩ ወይም ለአንዱ ተከራካሪ ወገን በማዳላት ሚዛናዊ ባልሆነ አግባብ መዘገብ የለባቸውም፡፡ የሚያቀርቧቸው ዘገባዎችና ትንተናዎች ፍርድ ቤት አከራክሮ ውሳኔ ሊሰጥበት በሚገባው ጉዳይ ከፍርድ ቤቱ አስቀድሞ ውሳኔ መስጠት በሚመስል መልኩ የሚቀርቡ መሆን የለባቸውም፡፡
3. የምስክሮች ከጥቃት የመጠበቅ መብት
ማንኛውም ምስክር ለፍትህ እርዳት የመስጠት ህጋዊ ግዴታ አለበት፡፡ ጥቆማ ወይም ምስክርነት በመስጠቱ ምክንያት በምስክሮችና በቤተሰቦቻቸው ህይወት ወይም ንብረት ላይ አደጋ የሚፈጠር ከሆነ የምስክሮች ማንነት፣ አድራሻ፣ ንብረት እንዳይገለፅ በማድረግ የህግ ጥብቃ ይደረግላቸዋል፡፡ በመሆኑም መሰል ሁኔታዎች ሲኖሩ የምስክሮች ህይወት ወይም ንብረት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በችሎት የተገኙ ምስክሮችን ማንነት በመገናኛ ብዙኃን ከመግለፅና በዘገባ ዉስጥ ከማካተት መቆጠብ ይገባል፡፡
4. የጉዳዩን ፍሬ ነገር እንዳይዛባ መጠንቀቅ
መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችን ሲሰሩ በችሎት ሂደት የነበረውን ሁኔታ ሳይጨምሩና ሳይቀንሱ በመዘገብ የጉዳዩ ፍሬ ነገሮች እንዳይዘቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም አንዳንድ ጊዜ ህግ የራሱ የሆኑ ልዩ ባህሪያት ያሉት በመሆኑ ዘገባዎች የተዛቡ እንዳይሆኑ ከህግ ባለሞያ ማብራሪያ በመጠየቅ ቢሰሩ ተሻለ ይሆናል፡፡
5. ችሎት ማክበር
ችሎት የራሱ ሥነ ሥርአት አለው፡፡ ማንኛውም በችሎት የሚገኝ ሰው ይህን የችሎት ሥርአት ማክበር ያለበት በመሆኑ ዘጋቢዎች ዘገባ ለመስራት በችሎት ሲገኙ የፍርድ ቤትን የችሎት ሥነ ሥርአት ጠንቅቆ ማወቅ እና ችሎት ማክበር ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. የግል ህይወት መብትን ማክበር
የግል ህይወት መከበር በህገ መንግስቱ አንቀፅ 26 መሠረት በህግ ጥበቃ የተደረገለት ሰብዓዊ መብት ነው፡፡ ይህም መብት የአንድ ሰው የግል ሕይወት፣ ሰዉነት፣ ንብረት እንዲሁም የሚፃፃፋቸው ድብዳቤዎች የተጠበቁ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ይህ መብት ለሀገር ሰላም፣ ወንጀልን ለመከላከል፣ ለህዝብ ጤና እና ሞራል ሲባል በልዩ ሁኔታ በህግ መሰረት ብቻ ሊገደብ የሚችል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የሚሰሩ ዘገባዎች የተከራካሪ ወገኖችንም ሆነ የማንኛውንም ዜጋ የግል ነፃነትና መብት የሚጋፉ መሆን የለባቸውም፡፡
7. ሥነ ምግባር
እያንዳንዱ ሙያ የሚጠይቀው የራሱ የሆነ ሥነ ምግባር አለ፡፡ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያ መሆንም የሚጠይቀው የራሱ የሆነ የሙያ ሥነ ምግባር አለው፡፡ ለአብነትም ከአድሎ የፀዳ እና የተለያዩ ሀሳቦችን በእኩል የሚያስተናግድ ሊሆን ይገባል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም የችሎት ዘገባ የሚሰራ ባለሞያ የሙያ ሥነ ምግባሩን በጥብቅ ማክበር ይጠበቅበታል፡፡
ማጠቃለያ
መገናኛ ብዙኃን የችሎት ዘገባዎችን ጨምሮ ሌሎች መረጃዎችን ለዜጎች በሚያደርሱበት ወቅት ሊከተሏቸው የሚገቡ የሥነ ምግባር ደንቦችን ማክበር ይገባቸዋል፡፡ በተለይ ችሎት ውስጥ መረጃ ሲሰበሱቡም ሆነ ሲዘግቡ በፍርድ ቤት የተቀመጡ የችሎት መመሪያዎችንና የችሎት ሥነ ሥርአት በጥንቃቄ ሊያከብሩ የሚገባ ከመሆኑም በተጨማሪ ለህዝብ የሚደርሱ ዘገባዎች የተከራካሪ ወገኖችን መብትና ነፃነትን የሚያከብሩ፣ የምስክሮችን ደህንነት የሚያስጠብቁ እንዲሁም የፍርድ ቤትን ነፃነት የማይጋፉ መሆን ይገባቸዋል፡፡

FDRE Ministry of Justice/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
March 29, 2023
ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች

/ክፍል ሁለት/

ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎችን በተመለከተ ክፍል አንድ መረጃ አቅርበን ነበር የመረጃውን ቀጣይ እና የመጨረሻ ክፍል እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

የሚከተሉት ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነፃ ይሆናሉ፡-¬

ልብ ይበሉ:- ሚኒስትሩ በዚህ ፊደል ተራ በቁጥር (1) ፣(2) ፣(3) እና (5) በተመለከቱት ላይ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 1/2011 መሰረት ያደረገው ገደብ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለተቀጣሪው የሚከፈሉ የሚከተሉት ገቢዎች ከገቢ ግብር ነፃ ናቸው፡-

1. በሥራ ውል መሠረት ለሠራተኛው የሚከፈል የትራንስፖርት አበል፤
2. በሥራ ቦታው ወይም በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈል አበል፤
3. ሠራተኛው ከመደበኛ ሥራው ውጪ ሥራውን ለማከናወን ሲንቀሳቀስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ እና የውሎ አበል፤
4. የመጓጓዣ ወጪው በቅጥር ውሉ መሠረት የተከፈለ ከሆነ ከሥራ ቦታው ውጪ ተመልምሎ ለተቀጠረ ሠራተኛ ወደ ሥራው ሲመጣ ወይም ሥራውን አጠናቆ ሲመለስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ፣ እንዲሁም የውጭ ሀገር ሠራተኞች ከሀገራቸው ሲመጡና ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የሚከፈል የመጓጓዣ ወጪ፤
5. የማዕድን ማውጣት፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የግብርና የንግድ ሥራ የሚሠራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብና መጠጥ፤
6. የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በውጭ አገር ለሚመድባቸው ሠራተኞች የሚከፈል አበል፤
7. ለሠራተኛው ጥቅም ተብሎ ከተቀጣሪው የወር ደመወዝ 15 % (አሥራ አምስት በመቶ) ባልበለጠ መጠን በየወሩ በቀጣሪው የሚዋጣ የጡረታ መዋጮ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ፤
8. በተቀባዩ ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም በሌላ ሰው ሞት ምክንያት የሚከፈል ካሳ፤
9. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 59 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ስጦታው የመቀጠር፣የኪራይ ወይም የንግድ ሥራ ገቢ ካልሆነ በስተቀር በስጦታ ወይም በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፤
10. ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ጋር የማይገናኝ የንግድ ሥራ ገቢን ሳይጨምር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የሚያገኘው ገቢ፤
11. ገንዘብ በሚቆጠርበት ጊዜ ለሚደርሰው ጉድለት ማካካሻ በሚሆን መጠን ብቻ ቀጣሪው ለተቀጣሪው የሚከፍለው እና ለዚሁ ዓላማ መዋሉ የተረጋገጠ የጥሬ ገንዘብ ማካካሻ ክፍያ፤
12. በኢትዮጵያ ፀንቶ በሚሰራበት ሕግ መሠረት በተለይ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረገ ገቢ፤
13. ለመኖሪያ ቤት ሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ፤
14. በነዳጅ ሥራ ላይ የተሰማራ ሥራ ተቋራጭ ለንዑስ ሥራ ተቋራጮች የሚፈፅመው ክፍያ፡፡
15. ለሠራተኛ የሚከፈል የትራንስፖርት አበል፤ በሥራ ቦታው ወይም በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት የሚከፈል አበል፤ ሠራተኛው ከመደበኛ የሥራ ቦታ ውጪ ሲንቀሳቀስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ እና የውሎ አበል፣ የማዕድን ማውጣት፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የግብርና የንግድ ሥራ የሚሠራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብና መጠጥ ከግብር ነጻ የሚሆነው የገንዘብ መጠን ልክ የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡
16. የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ለኢኮኖሚ፣ ለአስተዳደራዊ ወይም ለማህበራዊ ምክንያቶች አንድን ገቢ ከገቢ ግብር ነፃ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ገቢዎች
March 30, 2023
የዲጂታል መታወቂያ ምንነት እና የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 1284/2015 ዋና ዋና ገጽታዎች

ዘመናዊ የመታወቂያ ስርዓት በአንድ ሀገር ውስጥ ተግባራዊ ሲደረግ መሰረታዊ የሚባሉ ጠቀሜታዎች ያሉት ሲሆን፣ ከነዚህ ጠቀሜታዎች መካከልም ሃገራዊ ልማትን በአግባቡ ለማቀድ፣ ምጣኔ ሃብታዊ ሽግግር ለመፍጠር፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ የሀብት ብክነትን ለመቀነስ፣ ወንጀልን ለመከላከል፣ ፖሊሲዎች ሲቀረጹ እና የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ድግግሞሽን ለመቅረፍ እና አካታችነትን ለማጎልበት የሚረዳ መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡ በኢትዮጵያም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የበለፀገ፣ ዘርፍ ተሻጋሪ፣ መሠረታዊ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መዘርጋት አሰፈላጊ መሆኑ ታምኖበት የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ተቋቁሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት በግንባታና በሙከራ ሂደት ላይ ቆይቷል። በዚህ ሂደት ውስጥ ከተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች ጋር ለማስተሳሰር የሙከራ ትግበራ ስራዎችን በማከናወን ወደ 1.4 ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎችን መዝግቦ አብዛኞቹን የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ ተችሏል።

በዚህ የሙከራ ትግበራ ወቅት ከተከናወኑ ተግባራት ውስጥ ሌላው የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ማዘጋጀት ሲሆን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ "የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 1284/2015" አድርጎ አፅድቆታል፡፡ አዋጁ ከሌሎች ሀገሮች የመታወቂያ አዋጆች አንፃር ዘግየት ብሎ የወጣ በመሆኑ በሌሎች ሀገሮች የታዩ ክፍተቶችን ለመድፈን በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ዘመኑ የደረሰበትን የዲጂታል መታወቂያ በዘመናዊ መልኩ ለነዋሪዎች ለመስጠት እና ለማስተዳደር በማለም የወጣ ነው፡፡ አዋጁ በርካታ ጉዳዮችን የያዘ ሲሆን፣ በዝርዝር በሌላ ፅሁፍ የምንመለስበት ሲሆን፣ በዚህ ክፍል የአዋጁን ዋናዋና ድንጋጌዎች በተለይም ከዓላማዉ ጋር በማገናኘት ለማየት እንሞክራለን፡፡

1. የዲጂታል መታወቂያ ምንነት እና አገልግሎት

በየትኛውም ሀገር የሚገኝ የመታወቂያ ሥርዓት በሁለት የሚከፈል ሲሆን እነሱም አገልግሎት ተኮር መታወቂያ (Functional ID) እና መሰረታዊ መታወቂያ (Foundational ID) ናቸው፡፡ አገልግሎት ተኮር የመታወቂያ (Functional ID) ማለት የተወሰነ አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል መታወቂያ ነው። እንዲህ አይነት መታወቂያ፣ ከተሰጠበት አገልግሎት ውጭ ለሌሎች ነዋሪነትን እና ማንነትን በማረጋገጥ ለሚሰጡ አገልግሎቶች ተቀባይነት ላይኖራቸው ይችላል፡፡ መሰረታዊ መታወቂያ (Foundational ID) ማለት በተሰጠበት ሀገር ውስጥ በየትኛውም ቦታ ተቀባይነት ያለው እና ማንነትን በማረጋገጥ ለሚሰጡ የትኛውም አገልግሎቶች ተቀባይነት ያለው የመታወቂያ አይነት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ መሰረታዊ መታወቂያ (Foundational ID) ለአገልግሎት ተኮር መታወቂያዎች (Functional ID) እንደመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል፡፡

መሰረታዊ መታወቂያ በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ ስያሜዎች ሊኖሩት የሚችሉ ሲሆን ብሄራዊ መታወቂያ ወይም የዲጂታል መታወቂያ በብዛት መሰረታዊ መታወቂያ የሚጠራባቸው ስያሜዎች ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት ተግባራዊ ለማድረግ በሙከራ ላይ የሚገኘው የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት (Foundational ID) መሰረታዊ መታወቂያ የሚሰጥበት ስርዓት ነው፡፡ የዲጂታል መታወቂ ማለት ማንኛውም በሀገሪቱ ውስጥ የሚኖር ሰው ተቋሙ ወይም በተቋሙ ውክልና የተሰጠው አካል በሚያደርገው የምዝገባ ሂደት የባዮሜትሪክ እና ዲሞግራፊክ መረጃዎችን በመስጠት ከተመዘገበ በኋላ ማንነቱን ለማረጋገጥ የሚሰጥ ልዩ ቁጥር(Unique Number) ነው፡፡ ይህ ልዩ ቁጥር ወይም ዲጂታል መታወቂ የሚመነጨው ከግለሰቡ የባዮሜትሪክ እና ዲሞግራፊክ ዳታ በመሆኑ፣ ግለሰብን በልዩ ሁኔታ ለመለየት የሚስያስችል አስተማማኝ የመታወቂ ስርዓት ነው፡፡

ይህን የመታወቂያ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ እና የህግ ድጋፍ እንዲኖረው ለማስቻል በብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ፅ/ቤት የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ከተዘጋጀ በኋላ ረቂቁን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1284/2015 አድርጎ አፅድቆታል፡፡ በአዋጁ አንቀፅ 14 ላይ በግልፅ እንደተመለከተው የዲጂታል መታወቂያ የአንድን ነዋሪ ማንነትን ለማስረዳት ወይም ለማረጋገጥ እንደ ህጋዊ እና በቂ ማስረጃ ተደርጎ እንደሚወሰድ እና ማንኛውም ተጠቃሚ አካል ለነዋሪው ለሚሰጠው አገልግሎት የዲጂታል መታወቂያ እንደ አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ የሚያደርግ አሠራር በሚመለከተው ተቆጣጣሪ አካል ፍቃድ መዘርጋት እንዳለበት ተደንግጓል፡፡ ስለሆነም አሁን በኢትዮጵያ ተግባራዊ የሚደረገው ዲጂታል መታወቂያ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ተቀባይነት ያለው እና ማንነትን በማረጋገጥ ለሚሰጡ አገልግሎቶች እንደ አስገዳጅ የመታወቂያ አይነት የሚወሰድ ሲሆን፣ በዚህ መታወቂያ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆነ ማንኛውም ሰው በወንጀል እንደሚጠየቅ አዋጁ አንቀፅ 21/1/ በሚከተለው መልኩ ደንግጓል፡፡

"በዚህ አዋጅ እና ይህን አዋጅ ተከትለው በሚወጡ ደንቦች እና መመሪያዎች መሠረት ስልጣን ባለው አካል የተሰጠን ዲጂታል መታወቂያን እንደ ህጋዊ መታወቂያ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆነ ወይም ማንነትን ብቻ በማረጋገጥ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት ፍቃደኛ ያልሆነ ወይም በዚህ አዋጅ አንቀፀ 19 ላይ የተመለከተውን የመተባበር ግዴታ የተላለፈ ማንኛውም ሰው ከአስር ሺህ እስከ አንድ መቶ ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል"
ከላይ እንደተገለጸው ዲጂታል መታወቂያ የሚባሉው ልዩ ቁጥሩ ሲሆን፣ ይህንን መታወቂያ በካርድ መልኩ መያዝ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ተገቢውም ክፍያ በመፈፀም ከተቋሙ ወይም ተቋሙ ውክልና ከሰጠው ማንኛውም አታሚ ድርጅት የመታወቂያ ካርዱን ማግኘት የሚቻልበት ስርዓት ተዘርግቷል፡፡

2. የአዋጁ ዓላማ

የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 1284/2015 ዋና ዓላማው የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መዘርጋት ነው፡፡ የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ምንድን ነው የሚለው ሰፊ ትንታኔ የሚፈልግ ሲሆን፣ ጠቅላላ የሆነ ትርጓሜውን ግን ከዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ዓላማ ከሚለው ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በመሆኑም በአዋጁ አንቀፅ 5 ላይ እንደተመለከተው የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ዓላማ ነዋሪዎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ሲንቀሳቀሱ በቀላሉ የመታወቅ መብታቸው እንዲረጋገጥ በማድረግ ለሰብአዊ መብቶቸ አከባበር እና ለመልካም አስተዳደር መሻሻል አስተዋፅኦ ማድረግ፣ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ግለሰቦችን በቀላሉ ለመለየት የሚያስችል የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት በመዘርጋት በአገልግሎት ሰጪ እና አገልግሎት ተቀባይ መካከል እምነት እንዲጎለብት ማድረግ፣ ሕገ-ወጥ ተግባራትን መከላከል፣ ሀገር አቀፍ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት በማደራጀት ሀገራዊ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እና እቅዶች ሲቀረጹ እና የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ድግግሞሽን መቅረፍ፣ በዚህም የሀብት ብክነትን መቀነስ እና አካታችነትን ማጎልበት፣ የነዋሪዎችን የዲሞግራፊክ እና ባዮሜትሪክ መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል ሥርዓት በመዘርጋት፣ ለሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ አካላት የመታወቂያ ሥርዓት መረጃ ምንጭ ሆኖ ማገልገል እና አገልግሎት ተኮር የሆኑ የመታወቂያ ሥርዓቶች ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት እንዲሸጋገሩ ማጠናከር መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡

3. የዲጂታል መታወቂያ የማግኘት መብት እና ዲጂታል መታወቂያ ለማግኘት ስለሚሰበሰቡ መረጃዎች
April 4, 2023
በአዋጁ አንቀፅ 7 ላይ በግልፅ እንደተመለከተው ማንኛውም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ሰው የባዮሜትሪክ እና ዲሞግራፊክ መረጃዎችን በመስጠትና በመመዝገብ የዲጂታል መታወቂያ የማግኘት መብት አለው፡፡ ነዋሪው የዲጂታል መታወቂያ ለመውሰድ እሱነቱን ለማረጋገጥ የሚያገለግሉ የመታወቂያ ሰነዶች እና ሌሎች በተቋሙ ተቀባይነት ያላቸውን ሰነዶች ወይም የሰው ምስክር ማስረጃዎችን በመጠቀም በማረጋገጥ መመዝገብ ይችላል፡፡ ከላይ እንደተመለከተው ወደ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓት የሚገባ የግል መረጃ የእያንዳንዱን ተመዝጋቢ የዲሞግራፊክ መረጃ እና ባዮሜትሪክ መረጃን ያካተተ መሆን ያለበት ሲሆን፣ የዲሞግራክ መረጃ የሚባሉትም ስም ፣ የአባት ስም ፣ የአያት ስም ፣ ወይም በዚህ መልክ የተደራጀ ህጋዊ ስም ለሌለው ተመዝጋቢ ተቋሙ ህጋዊ የሆነውን ስያሜ ወይም ተመዝጋቢው በአካባቢው ማህበረሰብ የሚጠራበትን ስም፣ ዜግነት፣ የትውልድ ቀን፣ ወር እና ዓመት፣ ፆታ፣ መኖሪያ አድራሻ ሲሆኑ እንደአስፈላጊነቱ ስልክ ቁጥር፣ የኢሜይል አድራሻ እና ፖስታ አድራሻንም ሊያካትት ይችላል፡፡ የሚሰበሰቡት የባዮሜትሪክ መረጃዎች ድግሞ የአስር ጣት አሻራ፣ የሁለቱም አይኖች ብሌን እና የፊት ገፅታ ናቸው፡፡ እነዚህን የባዮሜትሪክ እና ዲሞግራፊክ መረጃዎች የሰጠ ማንኛውም ሰው የዲጂታል መታወቂያ ማግኘት ይችላል፡፡

አንዳንድ ጊዜ የባዮሜትሪክ መረጃዎችን ለመስጠት የሚቸገሩ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ጣት የሌለው ሰው፣ በእርጅና እና በተለያዩ ምክንያቶች አሻራቸው የማይነበብ ሰዎች በሚኖሩበት ጊዜ እና መሰል ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ፣ በዲሞግራፊክ መረጃ ብቻ መታወቂያውን መስጠት የሚገባ ስለመሆኑ በአዋጁ ተደንግጓል፡፡

4. የዲጂታል መታወቂያ ከሌሎች መታወቂያዎች፣

የባንክ አካውንቶች እና መሰል ማንነትን ለማረጋገጥ ከሚያገለግሉ ሰነዶች ጋር የሚኖረው ግንኙነት
የዲጂታል መታወቂያ ራሱን የቻለ መታወቂያ ቢሆንም፣ ሌሎች መታወቂያዎችን የሚያጠናክር የመታወቂያ አይነት ነው፡፡ ሁሉም ከላይ በርዕሱ ላይ የተመለከቱን ማንነትን ለማረጋገጥ የሚያገለግሉ ሰነዶች ወደ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓት እንዲገቡ የሚደርግ አሰራር ተዘርግቷል፡፡ ለምሳሌ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤቱ ከብሄራዊ ባንክ ጋር በመተባበር ከሁሉም በሀገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች ጋር ስምምነት ላይ በመድረስ፣ ሁሉም ባንኮች ደንበኞቻቸውን ወደ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ለማስገባት ስራ ጀምረዋል፡፡ እንዲሁም ፅህፈት ቤቱ እና ገቢዎች ሚኒስቴር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ሁሉንም ግብር ከፋይ የታክስ ከፋይነት መለያ ቁጥሩን መሰረት በማድረግ ወደ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ለማስገባት የሚስችል ስራ ተጀምሯል፡፡ ከዚህ መገንዘብ የምንችለው የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ሌሎች መታወቂያ ስርዓቶችን እያጠናከረ የሚሄድ የመታወቂያ አይነት መሆኑን እና ራሱንም ችሎ ማናቸውንም አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል የመታወቂያ አይነት መሆኑን ነው፡፡

5. የመረጃ አጠባበቅ ስርዓት

የዲጂታል መታወቂያ ለማግኘት የሚሰበሰቡ መረጃዎች በተለይም የባዮሜትሪክ መረጃዎች በጥንቃቄ ካልተያዙ ለተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ሊያጋልጡ ይችላሉ፡ ስለዚህ ለዲጂታል መታወቂያ የተሰበሰቡ መረጃዎች በጥንቃቄ መያዝ ያለባቸው በመሆኑ አዋጁ ተቋሙ የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት የግል መረጃን በአስተማማኝነት የሚይዝ ጠንካራ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት አለበት፤ በሚል የደነገገ ሲሆን፣ አሰራርና ህግን ጠብቆ በዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ለተሰበሰበ የማንኛውም ተመዝጋቢ ግላዊ መረጃ ያለ ተመዝጋቢው ፈቃድ ለሌላ ሰው መግለጽ ፣ ማስተላለፍም ሆነ እንዲለወጥ መፍቀድ የተከለከለ መሆኑን ህጉ በግልፅ አስቀምጧል፡፡ ይህን ክልከላ መተላለፍም በወንጀል የሚስጠይቅ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጥፅ 25 ላይ ተደንግጓል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ለፍትህ ስራ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በህግ ስልጣን ለተሰጠው ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረት የግል መረጃው ለሚመለከተው ህጋዊ አካል ሊገለጽ ወይም ሊተላለፍ እንደሚችል የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 1284/2015 አንቀፅ 16 ተደንግጓል፡፡

በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
April 4, 2023
የደምዳሚ (ድምዳሜ) ማስረጃ /conclusive evidence/ 5 የሰበር ችሎት ትርጓሜዎች

1//// የተሟላና ሙሉ ዕምነት የሚጣልበት ማስረጃ

የልዩ አዋቂ /expert/ የሚደርስበት የመጨረሻ አስተያየት ከሚኖረው ሙያዊ ዕውቀት አድማስ፣ ከሚታገዝበት መሣሪያና ከመሳሰሉት ጋር የተሟላና ሙሉ ዕምነት የሚጣልበት ማስረጃ /conclusive evidence/ ሊሆን ስለማይችል በዓይን ምስክሮች የተነገረን ፍሬ ነገር ለማስተባበል የሚያበቃ አቅም አይኖረውም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 43453 ቅጽ 12

የትራፊክ ፖሊስ የአደጋ ፕላን ሪፖርት የባለሙያ ሙያዊ አስተያየትን በወረቀት ላይ ስዕላዊ በሆነ መንገድ የሚያስቀምጥ በባለሙያ የሚረጋገጥ ሰነድ በመሆኑ እንደ ማንኛውም የልዩ አዋቂ የምስክርነት ቃል በተገቢው መንገድ ሊመዘን የሚገባው የማስረጃ አይነት እንጅ ሁልጊዜ ድምዳሜ ማስረጃ (Conclusive Evidence) ያለመሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 92141 ቅጽ 17

2//// አሳሪ ማስረጃ

በአስተዳደር አካል የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ነው ተብሎ የምስክር ወረቀት መስጠት ማስረጃውን ደምዳሚ ወይም አሳሪ (Conclusive Evidence) የሚያደርገው አይደለም፡፡ ይልቁንም ይኸው ማስረጃ የተሰጠበት አግባብ በፍ/ህ/ህ/ቁ. 1195 ድንጋጌ ስር በተመለከቱት ሁኔታዎች መሰረት ስለመሆኑ ማስረዳት ከተቻለ በፍ/ህ/ቁ. 1195 ስር የተመለከተው ሕጋዊ ግምት ሊስተባበል የሚችል (rebuttable legal presumption) መሆኑን ከድንጋጌዎቹ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 64014 ቅጽ 13

3//// ማስተባበያ ሊቀርብበት የማይችል ወሳኝ ማስረጃ

አንድ ለማይንቀሳቀስ ንብረት የተሰጠ የባለሃብትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባለሃብትነትን በተመለከተ የህግ ግምት የሚያሰጥ ቢሆንም በሌላ ተቃራኒ ማስረጃ ሊስተባበል፣ በተቃራኒው ከሚቀርቡት ማስረጃዎች ጋር ሊመዘን የሚችል እንጂ እንጅ ማስተባበያ ሊቀርብበት የማይችል ወሳኝ /conclusive evidence/ ያለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 67011 ቅጽ 13 

4//// የመጨረሻ ማስረጃ

የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ማስረዳት ከተቻለ ፍ/ቤት ልጅ ነው ሲል የሕግ ግምት ሊወስድ የሚችል መሆኑን የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 157/1/ ያመለክታል፡፡ ከአንቀፁ መረዳት እንደሚቻለው የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ማረጋገጥ የመጨረሻ ማስረጃ (conclusive evidence) ሳይሆን የሕግ ግምት ብቻ ነው፡፡ ግምቱም ቢሆን አስገዳጅነት ያለው የሕግ ግምት አይደለም፡፡ ግምቱን የሚቃወም ወገን ማስረጃ በማቅረብ ማፍረስ እንደሚችል ንዑስ አንቀፅ 2 ይደነግጋል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 42648 ቅጽ 10

5///// ክርክር ሊነሳበት የማይችል፣ ሙሉ እምነት ሊጣልበት የሚችል ማስረጃ

ልጅነት የሚረጋገጥበት ዋናው ማስረጃ የልደት ምስክር ወረቀት እንደሆነ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 154 ላይ ተመልክቷል፡፡ ይህ ማለት ግን የልደት ምስክር ወረቀት ክርክር ሊነሳበት የማይችል ሙሉ እምነት ሊጣልበት የሚችል /Conclusive/ ማስረጃ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 33440 ቅጽ 5
April 5, 2023
Federal Judges Code of Conduct and Disciplinary Procedure Regulation
Regulation Number 1/2013
link: bit.ly/40yp2Jy



📌📌Note
: This translation was undertaken by volunteer Year III students of Addis Ababa University School of Law for the benefit of fellow students who are not native Amharic speakers.
April 5, 2023
The degrees that make students cry: A look at the most challenging courses in the world

What are the hardest degrees in the world
1. Aerospace Engineering
2. Biomedical Engineering
3. Law 👈
4. Chartered Accountancy
5. Architecture
6. Medicine
7. Nursing
8. Dentistry
9. Psychology
10. Artificial Intelligence

Law 👈👈🙏 Respect for lawyers
Speak to any of  your friends who are studying law, and they might share with you a common complaint: there’s too much to read. 
https://www.studyinternational.com/news/hardest-degrees-in-the-world/

https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
April 5, 2023
#የጥብቅና #ፈቃድ
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥብቅና ፈቃድ፣

ምዝገባ እና ፈተና መቼ እንደሆነ እስከ አሁን የታወቀ ነገር የለም።
አዲስ ነገር ሲኖር የምናሳውቅ ይሆናል።
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
April 5, 2023
የመሸሸግ ወንጀል

በንብረት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን አስምልክቶ በወንጀል ህጉ ከተደነገጉ በንብረት ላይ ከሚፈፀሙ ወንጀሎች መካከል የመሸሸግ ወንጀል አንዱ ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የመሸሸግ ወንጀልን ምንነት እና የሚያስከትለውን ተጠያቂነት እንመለከታለን፡፡

የመሸሸግ ወንጀል ምንነት

በወንጀል ህጉ አንቀፅ 682 መሰረት መሸሸግ ማለት ዕቃው የተገኘው በአንድ ንብረት ላይ በተፈፀመ ወንጀል ምክንያት መሆኑን እያወቁ ወይም ማወቅ ሲገባ ይህንኑ ዕቃ በመግዛትም ሆነ በተውሶ፣ በስጦታ፣ በመያዣነት መቀበል ወይም በማናቸውም ይህን በመሳሰለ አኳኋን መውሰድ፣ መገልገል፣ ማስቀመጥ ወይም መደበቅ፣ አሳልፎ መሸጥ ወይም በመሸጥና በመለወጥ ስምምነት ውስጥ አገናኝ በመሆን መርዳት እንዲሁም የወንጀል ተግባር ባስገኘው ፍሬ የመጣ መሆኑን እያወቁ በዚሁ በወንጀል ድርጊት በተገኘ ዕቃ ምትክ በልዋጭ የተገኘውን ወይም በሽያጭ ዋጋ የተገዛውን ሌላ አይነት ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ መቀበል ነው፡፡

በዚህ መሰረት የመሸሸግ ወንጀል ተፈፅሟል ለማለት
 ተሸሽጎ የተገኘው ዕቃ በአንድ ንብረት ላይ በተፈፀመ ወንጀል ምክንያት የተገኘ ወይም የወንጀሉ ተግባር ባስገኘው ፍሬ የመጣ መሆን
 ሸሻጊው ዕቃው በወንጀል ምክንያት መገኘቱን ማወቅ ወይም መገመት ሲገባው በቸልተኝነት ወንጀሉን የፈፀመ መሆን
 በወንጀል ተግባር የተገኘን ዕቃ የገዛ፣ የተቀበለ፣ የወሰደ፣ የተገለገለ ወይም በመሰል ድርጊት ውስጥ የተገኘ መሆን አለበት፡፡

የመሸሸግ ወንጀል የህግ ተጠያቂነት
ከላይ በተገለፀው ሁኔታ የመሸሸግ ወንጀል አስቦ የፈፀመ ማንም ሰው በቀላል እስራት ወይም ከባድ በሆነ ጊዜ ከአምስት አመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትና በመቀጮ ይቀጣል፡፡ ድርጊቱ በቸልተኝነት የተፈፀመ እንደሆነ ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ ይሆናል፡፡

ከባድ መሸሸግ

የመሸሸግ ወንጀል የተፈፀመው
 በሰዎች ወይም በንብረት ላይ ወንጀል ለመፈፀም የተቋቋመ ቡድን አባልነት እንደሆነ
 ወንጀል ፈፃሚው የተሰጠውን የሥራ ወይም የንግድ ፍቃድ በወንጀል የተገኘን ንብረት ለመሸሸግ ተገልግሎበት እንደሆነ
 ወንጀል ፈፃሚው የሸሸገው ንብረት የውንብድና፣ የዘረፋ፣ የባህር ውንብድና፣ የቅሚያ፣ የማስፈራራት ፍሬ መሆኑን ወይም ዕቃው የተገኘው ከመከላከያ ሠራዊት ንብረት ወይም በጠቅላላው ከመንግስት ሀብት ውስጥ መሆኑን እያወቀ እንደሆነ
ወንጀሉ ከባድ የመሸሸግ ወንጀል የሚሆን ሲሆን ፈፃሚውም አስራ አምስት አመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና እስከ ብር ሀያ ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ እንደሚችል ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ህብረተሰቡ በማወቅም ወይም በቸልተኝነት በእንድ የወንጀል ድርጊት አማካኝነት የተገኘን ንብረት መግዛት፣ መዋስ፣ በስጦታ ወይም በመያዣነት መቀበል ወዘተ በወንጀል የሚያስቀጣ መሆኑን በመገንዘብ ዕቃዎችን ሲገዛም ሆነ በተለያዩ መንገዶች ሲቀበል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
April 7, 2023
ጎረቤቶችን እንቅልፍ በመንሳት የተከሰሰው አውራ ዶሮ እንዲታረድ የናይጄሪያ ፍርድ ቤት ወሰነ

ናይጄሪያ ውስጥ ጉዳዩ ፍርድ ቤት የደረሰው ጩኸቱ ጎረቤቶችን ሰላም የነሳው አውራ ዶሮ በድምጽ ብክለት ምክንያት እንዲታረድ ተፈረደበት።

በአንድ አውራ ዶሮ ምክንያት እንቅልፍ አጣን ያሉት ናይጄሪያውያን ለፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ነው ባለቤቱ አውራ ዶሮውን እስከ መጪው አርብ ድረስ እንዲያርደው መወሰኑን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን የዘገቡት።

በሰሜናዊ ናይጄሪያ ካኖ ግዛት ውስጥ የሚገኘው ፍርድ ቤት ሁለት ሰዎች የአውራ ዶሮው የማይቋረጥ ጩኽት ሰላም አሳጣን፣ እንቅልፍ ነሳን በማለት ነበር የቀረበለትን ክስ ተከትሎ ነው ብይን የሰጠው።

በዶሮው እና በባለቤቱ ላይ ክስ ካቀረቡት ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆነው ግለሰብ ዩሱፍ ሙሐመድ፣ የአውራ ዶሮው ጩኽት በቤቱ ውስጥ የሰላም እንቅልፍ የማግኘት እና የማረፍ መብቱን እንደጣሰበት ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል።

የአውራ ዶሮው ባለቤት ኢሲያኩ ሹይቡ የቀረበውን ክስ ተከትሎ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው ዶሮውን በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ነገ አርብ ለሚከበረው የስቅለት በዓል ለቤተሰቦቹ እንደገዛው እና ብዙ ጊዜ አለመቆየቱን ተናግሯል።

የአውራ ዶሮው ጩኽት ሰላም አሳጣን ያሉት ጎረቤቶቹም ዶሮው ለበዓሉ አርብ ዕለት የሚታረድ በመሆኑ ጥቂት ቀናት ብቻ እንዲታገሱት ጠይቋል።
https://bbc.in/3ZONkxY
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
April 7, 2023
April 7, 2023
ታክስ የመጣል ሥልጣን

ለአንድ መንግስት ከታክስ የሚሰበሰብ ገቢ ለህልውና እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ታክስ የመጣልና የማስከፈል ሥልጣን ለመንግስት ብቻ የተሰጠ ሥልጣን ነው፡፡ ለግለሰብ ወይም ለሌላ አካል የዚህ ዓይነት ሥልጣን በየትኛውም ዓለም አይሰጥም ፡፡
ለፌደራል መንግስት በህገ መንግስቱ በተሰጠው ታክስ የመጣልና የማስከፈል ሥልጣን መሠረት ሁለት መሠረታዊ የታክስ አጣጣል ዓይነቶች አሉ፡-

1. ነዋሪነትን እና
2. የገቢ ምንጭን መሠረት ማድረግ ናቸው፡፡

እነዚህን መሠረት በማድረግ፡-

1. የኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች በዓለም ዙሪያ በሚያገኙት ገቢ እንዲሁም
2. ኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎች የኢትዮጵያ ምንጭ በሆነ ገቢ ላይ ታክስ የሚጣልባቸው ይሆናል፡፡

ነዋሪነት በሶስት ከፍሎች ይከፈላሉ

1. ነዋሪ የሆነ ሰው/ግለሰብ
2. ነዋሪ የሆነ ድርጅት
3. ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የመንግስት ተቋማት

አንድ ግለሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ ነው የሚባለው ፡-

1. በኢትዮጵያ ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ ያለው ከሆነ
2. የኢትዮጵያ ዜግነት ያለውና ውጪ ሀገር በኮንሱላር በዲፕሎማቲክ ወይም በመሳሰሉት ስራ ተመድቦ የሚሰራ
3. በኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሳያቀርጥ ወይም በመመላለስ ከ183 ቀናት በላይ ከኖረ ነው፡፡

አንድ ድርጅት ነዋሪ ነው የሚባለው፡-

1. በኢትዮጵያ ውስጥ ከተቋቋመ ወይም ከተመሠረተ
2. የድርጅቱ ወሳኝ የሆነ አመራር የሚያከናውንበት ስፍራ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እንደሆነ ነው
April 7, 2023
ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ፍሰት ማነቆ የሆኑ 80 ህጎች ማሻሻሏን አስታወቀች


የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እንዳለው ለንግድ እና ኢንቨስትመንት አመቺ ያልሆኑ ህጎች መሻሻላቸውን አስታውቋል፡፡
https://am.al-ain.com/article/ethiopia-says-revises-investment-laws
April 11, 2023
Forwarded from የፍቅር ሰው
በየትኛውም ህግ ነው ተማሪዎች apparentship ወተው የተግባር ልምምድ ሳያደርግ የሚመረቁት
ከምንም በላይ የወራቤ ተማሪዎች ፍትህን ይፈልጋል።
በአሁኑ ሰዓት ተማሪዎቹ በመንከራተት ላይ ይገኛሉ
እንደሚታወቀው ይህ ወክት ተማሪዎች ለመውጫ ፈተና የሚዘጋጅበት ጊዜ ነው። በተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት ከንባብ ሙድ እየወጡ ይገኛሉ።

ውድ የአለ ቤተሰቦች ለሚመለከተው አካል በማስተላለፍ እንድትተባበሩ እንጠይቃለን።
ስለሚታደርጉት ትብብር ከልብ እናመሰግናለን።
April 12, 2023
አባቱን ገድሏል የተባለው ተከሳሽ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ።

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወላጅ አባቱን ገድሏል በተባለው አቶ መሐሩ ዮሐንስ በተባለ ተከሳሽ ላይ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ፍርድ አስተላልፏል።

ድርጊቱ የተፈጸመው በከምባታ ጠምባሮ ዞን በሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ ሌሾ ማዞሪያ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሙጉንጃ ተብሎ በሚጠራበት ቦታ ጥር 2 ቀን 2015 ዓ/ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ነው።

የዞኑ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እንዳስታወቀው ግለሰቡ ድርጊቱን ከመፈጸሙ በፊት "የሰበሰብከውን ንብረት አትበላም" እያለ ሲዝት እንደነበርና ምሽት ላይ ሟች ተኝቶ ባለበት በዘነዘና ጭንቅላቱን በመቀጥቀጥ ግድያውን መፈጸሙን ገልጿል።

አቃቤ ህግም በሰውና በሰነድ ማስረጃ አረጋግጦ ተከሳሽ ክሱን እንዲከላከል ቢታዘዝም መከላከያ ማስረጃ የሌለው መሆኑን በጽሑፍና በቃል ማስረጃ የለኝም ብሎ በማረጋገጡ ሚያዝያ 3 ቀን በዋለው ችሎት ተከሳሹ በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡

@tikvahethmagazine
April 12, 2023
Ethiopia is the third most expensive country to live in based on cost of living .

The high cost of living is a major concern for many individuals and families around the world. It is an issue that affects people of all income levels and can significantly impact their quality of life. Several factors contribute to the high cost of living in a country, including economic policies, inflation, and the cost of essential goods and services.

One of the primary reasons for the high cost of living in a country is the state of its economy. Countries with a strong economy tend to have a higher cost of living due to the high demand for goods and services. This is because when people have more money to spend, they are willing to pay more for the things they need and want.

Inflation is another factor that contributes to the high cost of living. Inflation occurs when the general price level of goods and services increases over time. This means that people have to spend more money to buy the same goods and services they could buy for less in the past. Inflation can be caused by various factors, such as increases in the money supply, changes in government policies, or external factors like global supply chain disruptions.

Based on the analysis Ethiopia reason of higher cost of living is not due to strong economy which creates strong demand rather due to high inflation which rocken the economy badly.

Rank Country Cost of living index Local purchasing power
1. Senegal 46.4 21.7
2. Ivory Coast 42.7 7.8
3. Ethiopia 42.3 11.6
4. Mauritius 42.2 30.8
5. Zimbabwe 40.8 18.7
6. South Africa 37.8 83.9
7. Namibia 35.8 51.3
8. Botswana 34.4 63.6
9. Cameroon 33.6 18.4
10. Kenya 32.4 32.8

EII.
April 13, 2023
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተዘጋጀ የፍትሐብሔር ክስ ለማቅረብ የሚከፈል የዳኝነት ክፍያ መጠንን ለማስላት የሚያስችል ሲስተም፡፡

👉  https://www.fsc.gov.et/Court-Services/Registry-Services/Court-Forms-and-Fees
April 13, 2023
አለአግባብ መበልጸግ በኢትዮጵያ ህግ
=============================⤵️
ያለአግባብ መበልፀግ ህግ የውል፣ የንብረት እና ከውል ውጭ ያለ ሃላፊነት ህግ ክፍል በተጨማሪ የፍታብሔር ግንኙነትን የሚገዛ የህግ ክፍል ነው፡፡ ይህ የህግ ክፍል የውል፣ የንብረት እና ከውል ውጪ ያለ ሃላፊነት ህጎች የማይገዙትን የሰው ግንኝኑነት ክፍተት ለመሙላት በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ህግ ሲሆን ከዚህ ባሻገር ይህ የህግ ክፍል የሰዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ከመግዛት አኳያ ሰፊ ድርሻ ያለው ነው፡፡
ያለአግባብ መልፀግ ህግ በመሰረታዊነት የሚመነጨው ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው ኪሳራ ወይም ጉዳት ምክንያት መበልፀግ የለበትም ከሚለው መርህ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛው ሰው በሌላ ሰው ጉዳት ወይም ኪሳራ ምክንያት ያለአግባብ የበለፀገ እንደሆነ ጉዳት ወይም ኪሳራ ለደረሰበት ሰው ካሳ የመክፈል ግዴታ እንደሚኖርበት ይህ የህግ ክፍል ያስገድዳል፡፡
አጠቃላይ መርሆዎች
የዚህ ህግ ዋንኛ አላማ ሰዎች በገንዘባቸው፣ በንብረታቸው እና በጉልበታቸው ላይ ሚኖራቸውን ህጋዊ መብት መጠበቅ ነው፡፡ ስለሆነም የፍታብሔር ህጋችን በቁጥር 2162 ስር ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው የስራ ድካም ወይም የሌላ ሰው ሀብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ እና ባለሀብቱ ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ጥቅም ባገኘበት ልክ ለባለሀብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ካሳ የመክፈል ግዴታ እንዳለበት ያስቀምጣል፡፡ ይህ ድንጋጌ በስሩ የያዛቸው ነጥቦችን ስንመለከት ያለአግባብ የመበልጸግ ህግ ማንኛውም ሰው (ማለትም የተፈጥሮ ወይም የህግ ሰውነት ያለው ሰው) ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን እንደመጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ በዚህ ህግ ተጠያቂ የሚሆን ሰው የገንዘብ ወይም የንብረት ጥቅም ሊያገኝ ይገባል፡፡ ይህም ማለት ጥቅሙ በንብት ላይ የተቋቋመ (right in rem) ወይም ከሌላ ሰው የሚጠየቅ መብት (right in personam) ወይም የነበረ እዳ የመሰረዝ፣ ግዴታ የመቅረት አይነት ወይም የኪሳራ መቅረት አይነት ጥቅም ሊሆን የሚችል ሲሆን ይህ ጥቅም ያለአግባብ የመበልፀግ የህግ ክፍል ስር ሊያስቀጣ የሚችለው ጥቅሙ የህሊና እርካታ ሊያስገኝ የሚችል ብቻ ሳይሆን በገንዘብ ሊለካ የሚችል ሲሆን ብቻ ነው፡፡ በተጨማሪም ይህ የተገኘው የገንዘብ ወይም የንብረት ጥቅም በሌላ ሰው የሚንቀሳቀስ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም ስራ ምክንያት የተገኘ መሆን ያለበት ሲሆን ጥቅሙን ያገኘው ሰው ጥቅሙን ላገኘበት ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት የሌለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ስለሆንም በዚህ የህግ ክፍል ተጠያቂ የሚያደርግ ክስ የቀረበበት ሰው ጥቅሙን ላገኘበት ማንኛውም ህጋዊ ምክንያት ያቀረበ እንደሆነ ካሳ መክፈል ግዴታ አይኖርበትም፡፡ ሌላው በህጉ የተቀመጠው ቅድመሁኔታ በተከሳሽ ድርጊት ምክንያት ከሳሽ የሚታወቅ ኪሳራ ወይም ድህነት ሊደርስበት ሚገባ ሲሆን የከሳሽ ጥቅም ማጣት (ኪሳራ) እና የተከሳሽ ጥቅም ማግኘት ምክንያት አንድ መሆን አለበት፡፡ ይህም ማለት በደረሰው ኪሳራ እና በተገኘው ጥቅም መካከል የውጤት እና የምክንያት ግንኝነት መኖር አለበት፡፡
ከላይ የተዘረዘሩ ሁኔታዎች ከተሟሉ በኋላ ሃላፊነትን የሚወስድ ሰው በምን ያህል መጠን ከሳሽን የመካስ ግዴታ አለበት የሚለውን በተመለከተ የተገኘው ጥቅም እና የደረሰው ኪሳራ እኩል በሚሆንበት ግዜ ምንም አይነት ችግር ሊገጥም አይችልም ምክንያቱም ተከሳሽ አለአግባብ የበለፀገበት መጠን እና ከሳሽ ላይ የደረሰው ጉዳት እኩል ስለሆነ በዚሁ ልክ ካሳ እንዲከፍ ይደረጋል፡፡ ሆኖም በአንዳንድ ሁኔታዎች ያለአግባብ የተገኘው ብልፅግና ከደረሰው ጉዳት ሊያንስ ወይም ሊበልጥ ይችላል፡፡ እንዲህ አይነት ሁኔታ በሚያጋጥምበት ግዜ ምንም እንኳን የደረሰው ጉዳት ከተገኘው ብልፅግና የሚያንስ ቢሆንም ህጉ በግልፅ ተከሳሽ መክፈል ያለበት ኪሳራ ያለአግባብ ባገኘው ብልፅግና መጠን መሆን እንደሚገባው ያስቀምጣል፡፡ በተመሳሳይ ያለአግባብ የተገኘው ብልፅግና ከደረሰው ጉዳት የሚያንስ ከሆነ ወይም ጉዳቱ ከብፅግናው የሚበልጥ በሚሆንበት ግዜ የተከሳሽ ተጠያቂነት መጠን በተገኘው ብልፅግና ልክ ብቻ በመሆኑ ካሳ እንዲከፍል የሚገደደውም በዚሁ መጠን ብቻ ይሆናል፡፡
በአጠቃላይ ያአለአግባብ መበልፀግ በመሰረታዊነት ሶስት ሁኔታዎችን ያካተተ ሲሆን አንድን ሰው በዚህ የህግ ክፍል በመክሰስ ካሳ ለማስከፈል እነዚህ ሶስት ሁኔታዎች በድምር መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ የመጀመሪያው ተከሳሽ በገንዘብ ሊለካ የሚችል ጥቅም ያገኘ መሆኑ ሁለተኛው ይህ ጥቅም የተገኘው በከሳሽ ኪሳራ ወይም ጉዳት ምክንያት መሆኑ እንዲሁም ሶስተኛው የተገኘበት መንገድ አለአግባብ ወይም ምንም አይነት ህጋዊ መንገድ/ምክንያት የማይቀርብበት መንገድ መሆኑ ናቸው፡፡
ያለአግባብ የመበልፅ ክሶችን ይበልጥ ለመረዳት ፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 34406 የሰጠውን ውሳኔ መመልከት ይቻልል፡፡ በዚህ መዝገብ በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ የሆኑት ሰዎች ባለቤት እና አባት የሆኑት ግለሰብ መኖሪያ ቤታቸውን ያከራዩት ሰው ለተከሳሽ ቤቱን አስረክቦ ይጠፋል፡፡ የቤቱ ህጋዊ ዋራሽ ከሳሾች ቤቱን ለተረከቡት ግለሰብ ቤቱን ለቀው እንዲያስረክቧቸው ቢጠይቋቸውም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው አለአግባብ የያዙትን ንብረት እንዲያስረክቡ እና ንብረቱን በያዙበት ወቅት ያለክራይ በመኖር ያገኙትን ያለአግባብ ብልፅግና እንዲከፍሉ ክስ አቅርበዋል፡፡ ተከሳሽም በሰጡት መልስ ቤቱን ያለአግባብ ይዛለች ከተባለ እንኳን ይህን ካወቁ 10 ዓመት በላይ ስለሆነ በይርጋ ይታገዳል፣ የደረሰባቸው የጥቅም ጉዳት ከውል ውጪ እንደመሆኑ የኪራይ ማስከፈል ጥያቄአቸው ሁለት አመት ካለፈው በይርጋ ይታገዳል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል፡፡ የስር ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን ከመረመሩ በኋላ ተከሳሽ ያለአግባብ የያዙትን ንብረት እንዲመልሱ እና ከንብረቱ ያለአግባብ የተጠቀሙትን መጠን ካሳ እንዲከፍሉ ወስነው ተከሳሽም በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለሰበር ሰሚ ችሎቱ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ የሰበር ሰሚ ችሎቱም ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ የሆኑት ግለሰቦች ይዞታችን በሃይል ተወስዷል ወይም በይዞታችን ላይ ሁከት ተፈጥሯል በማለት ያቀረቡት ክስ የለም ክሣቸው በኪራይ የተረከቡትን ቤት ተከሳሽ መብት ሣይኖራቸው ገብተው አልወጣም ብለዋልና አለአግባብ የያዙትን ንብረት እንዲለቁ የቀረበ ክስ ስለሆነ 10 ዓመት ቢያልፈው እንኳን በይርጋ አይታገድም፡፡ በጨማሪም ተከሳሽ የቀረበው የካሣ ጥያቄም ቢሆን በይርጋ ቀሪ ይሆናል በሚል ያቀረቡት ክርክር በተመለከተ ማንኛውም በሌላ ሰው የስራ ድካም ወይም በሌላ ሰው ሃብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ ሰው ጥቅም ባገኘበት መጠን ለባለሃብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ኪሣራ መክፈል እንዳለበት በፍ/ህ/ቁ. 2162 ሥር ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ከሳሽ በቤቱ አላግባብ በበለፀጉበት መጠን ኪሣራ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸው ህጉን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የካሣ ጥያቄ ሊቀርብ የሚገባበት የጊዜ ገደብ በተመለከተ ክርክር ቀርቧል፡፡ ያለአግባብ ስለመበልፀግ የሚናገረው ምእራፍ የካሣ ጥያቄ የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ አይናገርም፡፡ ነገር ግን አላግባብ ስለመበልፀግና ከውል ውጪ ስለሚደርስ ሃላፊነት የሚናገሩት ድንጋጌዎች በአንድ አንቀጽ ውስጥ ተካትተው መገኘታቸው እንዲሁም ያለአግባብ መበልፀግም ከውል ውጪ የሚደርስ ሃላፊነት በመሆኑ ከውል ውጭ የሚደርስ ሃላፊነት ሥር የተመለከተው የይርጋ ዘመን በተመሣሣይ
April 13, 2023
አላግባብ መበልፀግ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት ሊኖረው ይገባል፡፡ በዚህ መሰረት ከውል ውጭ ሃላፊነትን በተመለከተ ተበዳዩ ክስ ማቅረብ የሚችለው ካሣ የሚጠይቅበት ጉዳት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 2 አመት ድረስ መሆኑ በፍ/ህ/ቁ 2143/1/ ሥር ተመልክቷል፡፡ ስለሆነም ተከሳሽ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ኋላ ላሉት ሁለት አመታት አላግባብ በቤቱ በተገለገሉበት መጠን እንዲከፈሉ የተጠየቁት ካሣ በይጋ የሚታገድ አይሆንም:: ሆኖም ከዛ በፊት ያሉት ግዜያት የተጠቀሙት ክፍያ ግን በይርጋ ቀሪ የሚሆኑ ናቸው በማለት ወስኗል፡፡
ሌላው መታየት ያለ ጉዳይ አንድ ሰው ያለአግባብ በልፅጓል ተብሎ ክስ በሚቀርብበት ወቅት ይህ አለመሆኑን ስለሚያሳይበት መንገድ ነው፡፡ የፍታብሔር ህጋችን በቁጥር 2163 ያለአግባብ መበልፀግ ስለሚቀርበት ሁኔታዎች የሚደነግግ ሲሆን በዚህም መሰረት ያለአግባብ በልፅገሃል ተብሎ የተከሰሰ ሰው ንብረቱን መልስ በሚባልበት ግዜ ላለመበልፀጉ ማስረጃ ያቀረበ እንደሆነ ማሰረጃ ባቀረበበት ልክ ኪሳራ እንዲከፍል አይጠበቅበትም፡፡ ይህም ማለት ምንም እንኳን ከሳሽ ተከሳሽ በእርሱ ኪሳራ መበልፀጉን ማስረዳት ቢችልም ተከሳሽ ክሱ በቀረበበት ወቅት የተገኘው ብልፅግና ከእርሱ ጋር እንደሌለ (ወይም ለሌላ ሰው የተላለፈ መሆኑን) ማስረዳት ከቻለ ካሳ መክፈል ላይኖርበት ይችላል፡፡ ሆኖም ተከሳሹ በክፉ ልቦና ተነሳስቶ ወይም መመለስ እንዳለበት እያወቀ ንብረቱን ወይም ዕቃውን ሌላ ሰው አስተላልፎ ከሆነ ምንም እንኳን የተገኘው ብልፅግና እርሱ ጋር የሌለ ቢሆንም ካሳ የመክፈል ግዴታ እንደሚኖርበት የፍታብሔር ህጉ በቁጥር 2163(2) ስር ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን ተከሳሽ ያለአግባብ የበለፀገበትን ሀብት ለሶስተኛ ወገን ያስተላለፈው ያለ ዋጋ እንደሆነ ከሳሽ ይህን ሶስተኛ ወገን ያለ ዋጋ የወሰደውን ንብረት እንዲመልስለት ሊጠይቀው ይችላል፡፡
መክፈል የማይገባውን ክፍያ ስለመክፈል
ማንኛውም ሰው ሊከፍል የማይገባውን ነገር የከፈለ እንደሆነ ያለአግባብ የከፈለው ክፍያ እንዲመለስለት መጠየቅ ይችላል፡፡ ይህም ማለት ማንም ሰው በስዕተት ሊከፍል የማይገባውን ክፍያ የፈፀመ እንደሆነ ይህ የከፈለው ገንዘብ እንዲመለስልት ካሳ መጠየቅ የሚችል ሲሆን ክፍያውን የተቀበለው ሰው በእምነት ማጉደል ሀሳብ ተነሳስቶ የተቀበለ እንደሆነ ክፍያውን የፈፀመው ሰው ክፍያው ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ የከፈለው ነገር የሰጠውን ፍሬ ወይም ህጋዊ ወለድ ጨምሮ መጠየቅ እንደሚችል ህጉ ይደነግጋል፡፡ ሆኖም ሰውየው የከፈለው መክፈል የማይጠበቅበትን ክፍያ ቢሆንም እንኳን በሚከተሉት ሁኔታዎች የከፈለው ክፍያ እንዲመለስለት መጠየቅ አይችልም፡-
• ክፍያውን የፈፀመው ዕዳ እንደሌለበት እያወቀ ወይም ይህን ሁኔታ በግልፅ እየተረዳ በፍቃደኝነት ከሆነ፤
• ግለሰቡ የሚከፈለውን ነገር ያለዋጋ የመስጠት የህግ ችሎታ ያለው ሆኖ ክፍያውን የፈፀመው በይርጋ የታገደውን ዕዳውን ወይም የሕሊና ግዴታውን እና የበጎ አድራጎት መንፈሱን ተከትሎ እንደሆነ፤
ክፍያውን ከፈፀመለት ሰው የከፈለው እንዲመለስለት መጠየቅ እንደማይችል የፍታብሔር ህጉ በቁጥር 2165 እና 2166 ስር ያስቀምጣል፡፡
በሌላ በኩል ያለአግባብ የተከፈለውን ክፍያ የተቀበለ ሰው የተከፈለውን ነገር ከመመለስ የሚድንበት መንገድ ህጉ በቁጥር 2168 ስር ያስቀመጠ ሲሆን በዚህም መሰረት የማይገባውን ገንዘብ የተቀበለ ሰው በሌላ ሰው ላይ ያለው ገንዘቡ የተከፈለው መስሎት በቅን ልቦና የብድሩን ሰነድ አበላሽቶ ወይም ዋሶቹን ከዕዳው ነፃ አድርጎ ወይም ከእውነተኛ ባለዕዳ ሊቀበል የሚገባውን ገንዘብ በይርጋ አሳልፎ እንደሆነ፤ ያለአግባብ የተቀበለውን ገንዘብ የመመለስ ግዴታ ማይኖርበት ሲሆን እንዲህ ባለው ሁኔታ ክፍያውን ያለአግባብ የከፈለው ግለሰብ ክፍያው እንዲመለስለት ለመጠየቅ የሚችለው ከዋናው ባለዕዳ ብቻ ነው፡፡
በሌላ ሰው ንብረት ላይ የወጣ ወጪን ስለማስመለስ
ይህ የህግ ክፍል የሌላ ሰው ንብረት ያየዘ ሰው ንብረቱ በሚመልስበት ግዜ ንብረቱን ለመጠበቅ ያወጣውን ወጪ እንዲመለስለት ስለሚጠይቅበት አግባብ ወይም ንብረቱ በግለሰቡ ቁጥጥር በነበረበት ወቅት ያስገኘውን ጥቅም የራሱ ስለሚያደርግበት መንገድ የሚደነግግ የህግ ክፍል ነው፡፡ ዋናው ያለአግባብ መበልፀግ ህግ አላማ ማንኛውም ሰው መክፈል የማይገባውን ክፍያ እንዳይከፍል ወይም ማውጣት የሌለበትን ወጪ እንዳያወጣ ይህን ካደረገም ተገቢው ካሳ ተከፍሎት ፍትሀዊነት እንዲሰፍን ማድረግ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ሰው የራሱ ባልሆነ ንብረት ላይ በቀና ልቦና ያወጣው ወጪ ሳይቀናነስ ንብረቱን ለባለቤቱ መልስ መባሉ ተገቢ አይደለም፡፡ የፍታብሔር ህጉ በቁጥር 2168 ስር አንድ ሰው ለተወሰነ ግዜ በእጁ የቆየውን ዕቃ እንዲመለስ የተገደደ እንደሆነ የሕግ ወይም የውል ተቃራኒ የሚሆን ድንጋጌ ከሌለ በቀር ይህ ሰው የተባለውን ዕቃ ከመለዋወጥ የተነሳ ያሉት መብቶችና ግዴታዎች በዚህ የህግ ክፍል እንደሚገዛ ያደነግጋል፡፡
በዚህም መሰረት ማንኛውም ሰው በእጁ የነበረውን የሌላ ሰው ንብረት እንዲመልስ በሚገደድበት ወቅት ዕቃው እንዳይጠፋ ወይም እንዳይበላሽ ለማድረግ ያወጣውን ወጪ እንዲመለስለት ለመጠየቅ እንደሚችል በቁጥር 2168 ስር ተቀምጧል፡፡ ሆኖም ይህ ወጪ የወጣው ዕቃውን እንዲመልስ በተገደደው ሰው ወይም እርሱ ሃላፊነትን በሚወስድለት ሰው ጥፋት ምክንያት ከሆነ ወጪው እንዲመለስለት ለመጠየቅ አይችልም፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው በውል ህግ መሰረት በተቃራኒው ካልተዋዋሉ ወይም ወጪው አላስፈላጊ ካልሆነ ወይም ወጪው ዕቃውን እንዲመልስ በተገደደው ሰው ጥፋት ምክንያት የተፈፀመ እስካልሆነ ድረስ የሌላን ሰው ንብረት እንዳይጠፋ ወይም እንዳይበላሽ ለማድረግ ያወጣው ወጪ እንዲመለስለት የመጠየቅ መብት እንዳለው ህጉ ያስቀምጣል፡፡
ነገርግን ይህ የሌላ ሰው ንብረት እንዲመልስ የተገደደ ሰው በውል በሌላ መልኩ ካልተዋዋሉ በስተቀር በማንኛውም መልኩ ለዕቃው አጠባበቅ ያወጣው ወጪ ወይም በንብረቱ ይዞታ ምክንያት የከፈለው ግብር እንዲመለስለት ለመጠየቅ አይችልም፡፡ ይህ መርህ መሰረት ያደረገው ህጉ የሌላ ሰው ንብረትን የያዘ ሰው ንብረቱን በእጁ በሚያስገባበት ወቅት ምንም አይነት መብት የሌለው መሆኑን የሚያውቅ ካልሆነ በስተቀር ንብረቱ ከሚያፈራው ፍሬ እንዲጠቀም መብት የሚሰጥ በመሆኑ ይህ ግለሰብ ፍሬ ያፈራለትን ንብረት ለመጠበቅ ያወጣው ወጪ ይመለሰልኝ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ ነው፡፡ ስለሆነም በእጁ ያለው ዕቃ እንዲመልስ የተገደደ ሰው የተቀበለው ዕቃ ያፈራውን ፍሬ የማስቀረት ህጋዊ መብት ያለው ሲሆን ዕቃውን በይዞታው ስር ባደረገበት ወቅት በዕቃው ላይ ምንም ዓይነት የውልም ሆነ የህግ መብት እንደሌለው እያወቀ ድርጊቱን ከፈፀመ ግን ይህን የንብረቱን ፍሬ ለራሱ የማስቀረት መብቱ ቀርቶ ለትክክለኛው የንብረቱ ባለቤት ዕቃው በእሱ ይዞታ ስር በነበረበት ወቅት ያፈራው ፍሬ ግምት ልክ የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል፡፡
ሌላው የሌላ ሰው ንብረት እንዲመልስ ከተገደደ ሰው መብት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ይህ ግለሰብ ንብረቱ በእጁ በነበረበት ወቅት በቅን ልቦና በመነሳሳት ወጪ አውጥቶ የዕቃውን ዋጋ ከፍ በሚያደርግበት ግዜ ስለሚኖረው ህጋዊ መብት ነው፡፡ የፍታብሔር ህጉም በቁጥር 2171 ስር በሌላ ሰው ዕቃ ላይ የተደረገ ወጪ የዕቃውን ግምት ከፍ አድርጎት ከሆነ ዕቃውን እንዲመልስ የተገደደው ሰው ለዚሁ ጉዳይ ያወጣው ወጪ የዕቃውን ዋጋ ከፍ ባደረገው መጠን ብቻ ሊመለስለት እንደሚገባ ያስቀምጣል፡፡
April 13, 2023
በዚህም መሰረት ይህ ንብረቱን እንዲመልስ የተገደደ ሰው የዕቃውን ዋጋ ከፍ ለማድረግ ያወጣው ወጪ እንዲመለስለት የሚከተሉትን ነገሮች ማስረዳት ይጠበቅበታል፡-
• በዕቃው ላይ ወጪ ያወጣ መሆኑን፤
• የዕቃውን ዋጋ መጨመሩን እና የዕቃው ዋጋ የጨመረው እሱ ባወጣው ወጪ ምክንያት መሆኑን፤
• የዕቃው ዋጋ መጨመር ንብረቱ እንዲመለስ በተጠየቀመት ግዜ የሚታይ መሆኑን፡፡
ነገር ግን እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ተሟሉ ማለት ሰውየው በዕቃው ላይ ያወጣው ወጪ በእርግጠኝነት ይመለስለታል ማለት አይደለም፡ ከነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች በተጨማሪ የቅን ልቦና መኖር አስፈላጊ ነው፡፡ ምንም እንኳን ወጪውን በማውጣት ሂደት ቅን ልቦና አለ የሚለው ግምት የሚወሰድበት ቢሆንም ይህ ግን ተቃራኒ ማስረጃ ሊቀርብበት የሚችል ነው፡፡ የፍታብሔር ህጉም በቁጥር 2172 ስር ወጪው በተፈፀመበት ግዜ ዕቃውን እንዲመልስ የተገደደው ሰው ዕቃውን የመመለስ ግዴታ ያለበት መሆኑን ያውቅ እንደነበር ወይም የማወቅ ግዴታ ያለበት መሆኑን ማስረዳት ከተቻለ የወጪው ኪሳራ እንዳይከፈል ወይም የንብረቱ ባለቤት ኪሳራውን የመክፈያ እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ ግዜ እንዲሰጠው ዳኞች ለመወሰን እንደሚችሉ አስቀምጧል፡፡

https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
April 13, 2023
የታክስ አይነቶች

ቀጥታ ታክስ

የደመወዝ ገቢ ግብር
የኪራይ ገቢ ግብር
የንግድ ሥራ ገቢ ግብር
የሌሎች ገቢዎች ግብር

ቀጥታ ያልሆኑ ታክሶች

የተጨማሪ እሴት ታክስ ( Value Added Tax )
ኤክሳይዝ ታክስ ( Excise Tax )
ተርን ኦቨር ታክስ ( Turnover Tax )
የቴምብር ቀረጥ ( Stamp Duty )
የጉምሩክ ቀረጥ ( Customs Duty )
ሱር ታክስ ( Surtax )

ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በፌስቡክ፡- ministryofrevenuesofethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር/
በዩትዩብ፦ ministryofrevenuesofethiopia
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ማታ ከ 2፡30 ጀምሮ
ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኃላ
ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ
በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ
በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን
እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ
ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን!
April 13, 2023