አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ቼክ ተከፋይ (payee) የሆነ ሰው ቼኩን ያገኘበትን ውል የማስረዳት ሆነ በውሉ መሰረት ክፍያ እንዳልተፈጸመለት የማስረዳት ግዴታ የለበትም።
ይልቁንስ ለቼኩ መውጣት ምክንያት ነው የሚለዉን የግል ግንኙነትን በመከላከያነት በማንሳት ክፍያ ለመክፈል እንደማይገደድ የሚከራከር የቼኩ አውጪ (drawer) በቼኩ ክፍያ የማይፈጽምበት ህጋዊ ምክንያት ስለመኖሩ በቀዳሚነት የማስረዳት ሸክም (ግዴታ) አለበት።
ከዚህ አኳያ ፍርድ ቤት በቀዳሚነት መመርመር የሚገባዉ ጉዳይ የቼኩ አውጪ ለቼኩ መውጣት ምክንያት ነዉ ያለውንና ክፍያ የማይፈጸምበት ምክንያት መኖር አለመኖሩን እና በተገቢው ማስረጃ ማስረዳት መቻል አለመቻሉን መለየት ነዉ።
#habeshaadvocatesllp
የኢትዮጵያ ሕጎችና የሰበር ውሳኔዎች ዳታቤዝ ተሻሽሏል!

ሕጎችን እና የሰበር ውሳኔዎችን በፒዲኤፍ” በቀላሉ ማግኘት የሚያስችለዎትን ዳታቤዝ አሻሽለው አቀርበውልናል።

We are thrilled to announce the release of the beta version of our new Legal search engine! This powerful tool is designed specifically for legal professionals and researchers, providing fast and accurate results for all of your legal queries. With our comprehensive database and intuitive search interface, you'll be able to find the information you need quickly and easily.

Try it out today and let us know what you think!

https://pocketlaw.abyssinialaw.com
*ለሁሉም ጊዜ አለው።
ጊዜውን ዋጁ‼️
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
የድል ቀን እንጂ የነፃነት ቀን አናከብርም !!!
We don't Celebrate Indipendence day
We do celebrate Victory day !!!

ክብር ለአባቶቻችን በደም እና በአጥንታቸው እናት ኢትዮጵያን ላቆዮልን !!!

እንኳን ለ 127ኛው አድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ::
#Adwa Victory #African Victory
ቅጽ 25 መዝገብ ቁጥር 188881
******
ከሳሽ የከተማ ባዶ ቦታ መሸጡን አምኖ ውሉ እንዲፈርስ ሲጠይቅ ተከሳሽ ደግሞ ውሉ ከአስር ቆርቆሮ ቤትጋ የተደረገ ነው ውሉ ይናገራል በሚል ተከራክሯል።

በግራ ቀኙ መሀከል የተደረገው ውል በውል አዋዋይ ፊት ያልተደረገ ስለሆነ ሽያጩ ከ10 ቆርቆሮ ቤትጋር ስመደረጉ ውሉ ቢያሳይም ባዶ ቦታ ላይ የተደረገ ውል ነው፣ የት ቦታ ያለ ቤት ነው.....የሚል አከራካሪ ነገር ካለ ውሉ ታምኗል ሊባል የማይችል መሆኑን እና ለቤት መስሪያ የሚሆን ቦታ ላይ ከሆነ ውሉ የተደረገው በከሳሽ ምርጫ አፍርሶ መውሰድ ወይም የመስሪያ ዋጋውን(book value) መጠየቅ ይችላል።
የሰበር መዝገብ ቁጥር 207446 ቅጽ 25
ስለ ማስመሰል ውል ስለ አጭበርባሪነት ውል (የፍ/ህ/ቁ1988-2000) ተይዞ የህግ ትርጉም የተሰጠበት።

አንድ ሰው ለምሳሌ ከውል ውጭ በሆነ ክስ የሚወሰንበትን በመፍራት፣ የእቁብ እዳ ይኖርበት እና ላለመክፈል ወይም በሌላ ክስ ባለእዳ ንብረቱን ለማሸሽ የሚጠቀምባቸው መንገዶች
ፍርድ ቤት ላይ ባለእዳው ለከሰሰው ሰው አዎ ቤቱን ሸጫለው ብሎ ያምን እና ቤቱ ለከሳሽ ይወሰናል።

ወይም ውል አዋዋይ ፊት ቀርበው ውል ይፈጽማሉ፣

ባል እና ሚስት ሆነው በስምምነት ይፋቱ እና ንብረቱን እዳ ለሌበት ወገን የግል እዲሆን ተስማምተናል ይላሉ፣

የተወሰነውን እና ዋናውን የቤት ክፍል ልጁን አምጥቶ ተፈቅዶልኝ በግል ገንዘቤ ነው የሰራሁት እንዲል ያደርጋል።

ብቻ አይቱ ብዙ የሆነ ባለእዳ ገንዘቡን ላለመክፈል መንገድ ይጠቀማል።

እንዲህ ያለውን ተግባር እንዴት መመራት እንዳለበት የሚያመላክት የሰበር ውሳኔ ነው በንባብ እና በስራ ቢዳብር።
ስለ ታክስ ተመላሽ አፈጻጸም

የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ ስለሚደረግበት ሁኔታ ለመወሰን በወጣ መመሪያ ቁጥር 148/2011 መሰረት፡-

1. ማንኛውም ታክስ ከፋይ የንግድ ፈቃድ ከተሰረዘ በኋላ በሚያከናውነው ግዥ ላይ ለከፈለው ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመላሽ ጥያቄ ማቅረብ አይችልም፤
2. ለህንጻ ግንባታ በሚውል ግብዓት ላይ የተከፈለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ የሚደረገው የህንጻው ግንባታ ተጠናቆ ገቢ ማመንጨት በተጀመረበት የመጀመሪያው የሂሳብ ጊዜ ከሰበሰበው ታክስ ላይ እንዲቀናነስ ከተደረገ በኋላ ቀሪ ሂሳብ ካለ ታክስ ከፋዩ ገቢ ማመንጨት ከጀመረበት ወር ቀጥሎ ባለው ወር ውስጥ ይሆናል፤
3. በተራ ቁጥር ሁለት የተገለጸው ቢኖርም ለህንጻው ግንባታ በዋለ ግብዓት ላይ የተከፈለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ግንባታው ተጠናቆ ታክስ የሚከፈልበት ገቢ ማመንጨት ከመጀመሩ በፊት በተደረጉ ሌሎች ታክስ የሚከፈልባቸው ግብይቶች ላይ ከተሰበሰበ ታክስ ጋር ሊቀናነስ አይችልም፤
4. ማንኛውም የተመዘገበ ታክስ ከፋይ በግብዓት ላይ የከፈለው ታክስ የካፒታሉ አካል ሆኖ ከተመዘገበ እና የእርጅና ቅናሽ ወጪ እንዲታሰብለት ከተደረገ ታክሱ ተመላሽ አይደረግም፤
5. የልዩ መብት ተጠቃሚ የታክስ ተመላሽ ጥያቄ በሚያቀርቡበት ጊዜ የልዩ መብት ተጠቃሚው የፊርማ ናሙና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ለታክስ ባለስልጣኑ መላክ አለበት፡፡
6. ባለ ልዩ መብቶች ለገዙት ዕቃ ወይም አገልግሎት ክፍያ የፈጸሙት ከNT ወይም ከNR የኮምፒውተር አካውንት ላይ ከሆነ ታክሱ ተመላሽ የሚደረገው ገንዘቡ ወጪ በተደረገበት አካውንት መልሶ በማስገባት ነው፡፡
7. ማንኛውም ባለ ልዩ መብት በዕቃ ወይም በአገልግሎት ግዥ ላይ የከፈለው ታክስ ተመላሽ የሚደረገው የተመላሽ ጥያቄውን ባቀረበ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሲሆን በማንኛውም ሁኔታ ለግብይቱ ክፍያ ከተፈጸመ ከአንድ አመት በኋላ የሚቀርብ የታክስ ተመላሽ ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
የወጭና_ኪሳራ_አስተዳደር_በኢትዮጵያ_የፍትሐብሄር_ስነስርዓት_ህግ_.pdf
393.2 KB
“የወጭና ኪሳራ አስተዳደር በኢትዮጵያ የፍትሐብሄር ስነ-ስርዓት ህግ”

ጸሐፊ፡- አያሌው አባተ (ዶ/ር)
ጋብቻ እና ፍቺ ባለፉት 6 ወራት በአዲስ አበባ
 
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 6 ወራት 1ሺህ342 ፍቺዎች እና 14ሺህ 136 ጋብቻዎች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታውቋል።

አል ዐይን
ገና ዛሬ አይደል እንዴ አውራሪስ ምን እንደሚመስል ያየሁት!🙈
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
ፎቶ መላክ የሚጠበቅባቸው update.pdf
1.6 MB
ፎቶ ግራፍ መረጃ ላላሟላችሁ ጠበቆች
**
የኢ
.ፌ.ጠ.ማ  የአባልነት ማረጋገጫ  ደረጃውን የጠበቀ መታወቂያ  ለማሰራት  በዝግጅት  ላይ መሆኑን እና በምዝገባ ወቅት መረጃ  ያላሟላችሁ  እንድታሟሉ  ከአሁን በፊት አሳውቀናል።

በመሆኑም  እስካሁን ድረስ ፎቶ ግራፍ  ያልሰጣችሁ  ጠበቆች ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረ ስለሆነ ለመጨረሻ ጊዜ  እስከ ሐሙስ መጋቢት 08 ቀን 2015  ዓ.ም ድረስ  ከማህበሩ መ/ቤት  አራዳ ምድብ የፌዴራል ፍርድ ቤት በሚገኘው የፍትህ አካለት ህንፃ 9ኛ ፎቅ  በአካል በመምጣት እና በስልክ ቁጥር 0913- 661578/ 0912432335  በመጠቀም በቴሌግራም የተሟላ መረጃ (ፎቶ፣ መሉ ስም በአማረኛና እንግሊዘኛ፣ ጥብቅና ቁጥር፣ TIN No)  እንድትልኩ እናሳውቃለን ለመጨረሻ ጊዜ።

ሁሉም የማህበሩ አባል  መረጃውን የሰማ፤ ላልሰማ በማጋራት  ኃላፊነታችሁን እንድትወጡና ትብብር እንድታደርጉ አደራ ማለት እንወዳለን።
መጋቢት 06 ቀን 2015  ዓ.ም
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
ስልጣን ባለው አካል ፊት መረጋገጥና መመዝገብ ስላለባቸው ውሎች
ሰዎች በማኅበራዊ ህይወት ውስጥ ሲኖሩ በግብይ መልክ ያላቸውን ይሰጣሉ የሌላቸውን ይቀበላሉ፡፡ በዚህም የተለያዩ ህጋዊ ልውውጦችን ያካሂዳሉ፡፡ በመሆኑም ሂደቱ አስተማማኝ እንዲሆን፣ በሀብትና ንብረቶቻቸው ላይ ያሏቸው መብቶች ዋስትና እንዲያገኙ የልውውጡን ሥርዓት የሚገዛ ሕግ ያስፈልጋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ውል አንዱ ነው፡፡ ውሎች በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1731 መሠረት በሕጉ አግባብ የተቋቋሙ ውሎች ባቋቋሟቸው ሰዎች ላይ ሕግ ናቸው፡፡ ይህም ለሕግና ለሞራል እስካልተቃረነ ድረስ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ጸንቶ የሚቆይ መሆኑን ያሳየናል፡፡ ከነዚህ ውሎች መካከል ሕግ ባለ ጊዜ እና ተዋዋይ ወገኖች ሲፍቀዱ በጽሁፍ እና ሥልጣን ባለው አካል ፊት መደረግ ያለባቸውና መመዝገብ ያለባቸው ውሎች ብዙ ናቸው፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ የውሎች ምዝገባ ሥርዓት አሥፈላጊነትና ጠቀሜታ፣ መረጋገጥና መመዝገብ ስለሚገባቸው ሰነዶች፣ ውሎችን የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጣቸው የመንግስት አካላት እና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሚመለከቱ ውሎችን አረጋግጦ ስለ መመዝገብ የሚሉትን እንመለከታለን፡፡

የውሎች ምዝገባ ሥርዓት አሥፈላጊነትና ጠቀሜታ
የውሎች ምዝገባ አስፈላገነት ከማየታችን በፊት ስለ ውል (ሰነድ) ትርጉም ማየቱ ተገቢ ነው፡፡ "ሰነድ መመዝገብ" ማለት አንድን ሰነድ ለዚሁ በተዘጋጀ መዝገብ መለያ ቁጥር በመስጠት መመዝገብና ማስቀመጥ ወይም በሕግ መሠረት በሰነድ አረጋጋጭና መዝጋቢ ተቋም ዘንድ እንዲቀመጥ የተባለ ሰነድን ተቀብሎ መመዝገብና ማስቀመጥ ነው በማለት የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 922/2008 አንቀጽ (2) ንዑስ አንቀጽ (3) ደንግጎት እናገኘዋለን፡፡

ውሎች በጽሁፍ የሚደረጉት አንድም አንዳንድ በባህሪያቸው ለየት ያሉ የውል ዓይነቶች የግድ በጽሁፍ መደረግ አለባቸው የሚሉ አዛዥ ደንቦች በሚኖሩበት ጊዜ አለያም ተዋዋዮቹ ራሳቸው ውላቸውን በጽሁፍ ለማድረግ በሚስማሙበት ጊዜ ነው፡፡ አንዳንድ ልዩነቶች እንዳሉ ሆነው ሁሉም ዓይነት የጽሁፍ ሰነዶች የሚጋሩት የውል ባህርይ በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2005 የተመለከተውና የጽሁፍ ሰነዶች በላያቸው ላይ ስለ ሰፈረው ፍሬ ነገር በተዋዋዮቹ መሀከል ሙሉ እምነት የሚጣልባቸው በቂ ማስረጃዎች ናቸው ይላል፡፡ የዚህ ደንብ ዝርዝር የአፈጻጸም ሥርዓቶችና ልዩ ሁኔታዎች በዚሁ ሕግ ከቁጥር 2006 እስከ 2019 በተመለከቱት ደንቦች ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ ሌላው ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፊት (በባለሥልጣን ፊት) የተደረገ (authentic deed) በግል ከተደረጉ ጽሁፎች (non-authentic deeds or private acts) በይዘት፤ በቅርጽ፤ ይልቁንም ተአማኒነቱና ህጋዊነቱ የበለጠ አስተማማኝ ነው፡፡ መንግስት በአንድ በኩል በእርሱና በዜጎቹ መካከል ያለውን ግንኙነት በሌላ በኩል ደግሞ ዜጎች የግለሰቦችን እርስ በእርሳቸው የሚያደርጓቸው ግንኙነቶች የህግ አግባብ የተከተለና ሥርዓት ባለው መልኩ እንዲመሩ፣ ለእነዚህ ግኑኝነቶች ህጋዊ ጥበቃና ዋስትና መስጠት ካለው ሀላፊነት አንፃር የሚመነጭ በተለይም ለፍትህ ሥርዓቱ አስተዳደር እና ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ የበኩሉን እገዛ ያደርጋል፡፡

የውሎች ምዝገባ ሥርዓት ወንጀል ከመከላከልና የማጭበርበር ተግበራትን በመከላከል ረገድም አይነተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ የውሎች ምዝገባ የሚካሄዱት የንግድም ሆነ ሌሎች ተግባራትን (transactions) ሥርዓት ባለው መልኩ እንዲካሄድ የተዋዋይ ወገኖች ማንነት በማረጋገጥ ተዋዋዮች በሚዋዋሉት ተግባር የተሟላ ግንዘቤ እንዲኖራቸውና ውጤቱን አውቀውና ፈቅደው እንዲገቡ በማስቻል፣ ሲፈርሙ እርግጠኛ ሁነው እንዲፈርሙ በማድረግ አመኔታ ያለው የንግድና ሌላም ህጋዊ ተግባራት እንዲካሄዱ ያግዛል፡፡ ስለዚህ የውሎች ሥልጣን ባለው አካል በመመዝገብ ሂደት ማጭበርበር (forgery)፣ የማይመለከተው በማሳሳት (misrepresentation)፣ ማስገደድን ለማስወገድ እና ግድፈቶችን (omission) ለመከላከል ውጤታማ እገዛ አለው፡፡ ስለዚህ የውሎች ምዝገባ ሥርዓት በሚከተሉት ሁኔታዎች የንብረት ማጭበርበርን የመመዝገብ ሥልጣን ባለው አካል ፊት በመገኘትና በመፈፀም ዜጋው ያልሆኑ ተግባራትን እንዳይፈጽም ይከላከላል፡፡ በዚህም እጅግ ወሳኝ የሆኑ ቀጣይ ዋስትናዎችንም በንብረት ማስተላለፉ ሂደት ያካሄዳል፡፡

1. በአካል መቅረብን (personal appearance) ህጎችና አሰራሮች ተዋዋይ ወገኖች ንብረትን ሲያስተላልፉ በአዋዋዩ ፊት ቀርበው ፈቃዳቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
አረጋጋጩ ፊት ያልቀረበና ያልተፈረመ ፊርማ ተቀባይነት የለውም፡፡ በስሚስሚ (Hearsay) ማረጋገጥ የለበትም፡፡ ቀደም ሲል አንደኛው ወገን ፈርሟል በሚልም የሚደረግ ማዋዋል አይኖርም፡፡ በዚህም የአረጋጋጩ ሁሉም ተግባራት ወይም አገልግሎት ሰነዶችን የሚፈርሙ ሁሉም ወገኖች በአካል በመቅረባቸው ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

2. ማንነትን መለየት (identification) ፈራሚው በአረጋጋጩ ፊት በአካል ከቀረበ በኋላ አረጋጋጩ የፈራሚው ግለሰብን ማንነት በጥንቃቄ ያጣራል፡፡ የፈራሚው ማንነት ማረጋገጥ ፈራሚው አስመሳይ አለመሆኑንና ታማኝ ባልሆነ ሰነድ እንዳያጭበረብር ዋስትና ነው፡፡

3. መሰረታዊ ግንዛቤ መፍጠርና የኃይል አለመኖር ማረጋገጥ (basic awareness and absence of duress):: የፈራሚዎችን ማንነት በማረጋገጥ ሂደት አረጋጋጩ ፈራሚዎች ስለ ጉዳዩ ተጠንቅቀውና ዕውቅና ኖሯቸው ያለምንም ማስገደድ ወይም ፍርሃት እየፈረሙ ለመሆናቸው ይታዘባል፣ የረጋግጣል፣ ጥርጣሬ እያለውና ተዋዋዮች አውቀውና በነፃ ፍቃዳቸው የገቡበት ተግባር መሆኑን በጥንቃቄ ያረጋግጣሉ፡፡

4. ሰነዶችን መመዘገብ (paper trail) አረጋጋጮች በህግ ወስደው ከመልካም ልምድ (best practice) መሰረት እያንዳንዱ የሚያረጋግጡት ሰነድ መመዝገብ ወይም ሪከረድ ማድረግ ይጠበቀባቸዋል፡፡ ይህም ሰነድ የህግ መዝገብ ስለሚሆን የማጭበርበር ተግባር ወይም የማጭበርበር ወንጀል በሚኖር ጊዜ ለዓቃቢ ህግ አይነተኛ ማስረጃ ይሆናል፡፡

5. የተሟላ ሰነዶች መቅረብ (complete documents) አረጋጋጮች ሰነዶች የተሟሉ መሆናቸውና በባዶ ሰነዶች (blanck cheque) እንዳያረጋግጡ ሁሉንም ሰነዶችና ገጾችን መመርመር ማጣራት ይኖርባቸዋል፡፡

የንግድ እንቅስቃሴ ከተጀመረበት ዘመን ጀምሮ የማጭበርበር ወንጀልም አብሮ የነበረ ነውና ይህን ለመቀነስ ወይም ለመከላከል፡-
• የተፃፉ ውሎችን በመመስረት እንዲረጋገጡ ማድረግ፣
• ወሳኝ የሆኑ ውሎችና ተግባራት በተዋዋይ ወገኖች ወይም ፈራሚዎች በዕውቀትና በነፃ ፈቃድ እየተፈፀሙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የውሎች ምዝገባ ሥርዓት ጊዜ የፈቀደው ሂደት መሆኑን መገንዘብ፣
• ቋሚና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን (Real-estate) መመዝገብ ግልጽ የሆነ ህዝብ ሪከርድ (መዝገብ) ስለሆነ መንግስትና ተዋዋይ ወገኖች የሚተማመኑበት ሰነድ ነው፡