አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የህገመንግስት እና ህግ ልዩነት ምንድነው?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀድሞ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ እና የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ሰለሞን አረዳ።
https://t.me/lawsocieties
ኢትዮጵያ - የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች

[ ሪፖርተር ጋዜጣ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ በርኦ ሐሰንን ቃለ መጠይቅ አድርጎ ካወጣው ዘገባ የተወሰደ ]

• መስከረም ወር ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ካደረገው በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች የታክስ ማሻሻያ በኋላ ከ7,000 በላይ ተሽከርካዎች አገር ውስጥ ገብተዋል።

• ከብሔራዊ ባንክ ጋር የኤሌክትሪክ አውቶብሶች እንዲጉ መግባባት ላይ ተደርሶ እንቅስቃሴዎች የተጀመረ ሲሆን በቅርቡ 1,300 የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ወደ አገር ቤት ይገባሉ።

• የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የአሥር ዓመት ዕቅድ 48,000 የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ፤ በተጨማሪም 148,000 የኤሌክትሪክ #አውቶሞቢሎችን አገር ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ ነው።

#ማስታወሻ

በመስከረም ወር ይፋ የሆነው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ ማስገቢያ ማሻሻያ ፦

1ኛ. ሙሉ በሙሉ ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ አውቶሞቢሎች ከጉምሩክ ቀረጥ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ ናቸው።

2ኛ. በከፊል ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ የኤሌክትሪክ የቤት አውቶሞቢሎችን 5 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ ናቸው።

3ኛ. ሙሉ ለሙሉ ተገጣጥመው ያለቀላቸው የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ሲገቡ 15 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ ናቸው።
Via - tikvahethiopia
ተወካይ ተጠያቂ የሚሆንበት አግባብ
የድርጅቱን አስተዳደር በሚመለከት በውክልና ያለው ሰው ያስተላለፈ መሆኑ እና ተወካዩም በተቀበለው ውክልና መሠረት ሥራውን የሚያከናውን መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ግብይት ማከናወኑ ሲረጋገጥ ተጠያቂ የሚሆነው ውክልናውን ተቀብሎ ስራውን በውክልና የሚያስተዳድረው ሰው እንጂ ስራ አስኪያጁ ወይም የድርጅቱ ባለቤት ሊሆን አይገባም፡፡
የሰ.መ.ቁ 211028/ያልታተመ/  - ፍርድ ቤት ቅጣት እንዲገደብ የቀረበ ጥያቄ ካለ ምክንያት ሳይሰጥ ተቀባይነት የለውም በሚል ውደቅ ማድረጉ አግባብነት ያለው የውሳኔ አሰጣጥ አይደለም።
በአዋጅ ቁጥር 285/94 በአዋጅ ቁጥር 609/2001 እንደተሻሻለው አንቀጽ 56/1/ አንቀጽ 22/1/ እና አንቀጽ 50/ለ/1 መሠረት የአንድ የንግድ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ በወንጀል ተጠያቂ የሚሆነው እሱ የሚመራው ድርጅት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ግብይት ማከናወኑ ሲረጋገጥ እንደሆነ፤ የድርጅቱ ሃላፊነት ከተረጋገጠ የሥራ አስኪያጁ ሃላፊነት የሕግ ግምት የሚወሰድበት ስለመሆኑ እንገነዘባለን፡፡ ሆኖም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ የድርጅቱን አስተዳደር በሚመለከት በውክልና ያለው ሰው ያስተላለፈ መሆኑ እና ተወካዩም በተቀበለው ውክልና መሠረት ሥራውን የሚያከናውን መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ተጠያቂ የሚሆነው ውክልናውን ተቀብሎ ስራውን በውክልና የሚያስተዳድረው ሰው እንጂ ስራ አስኪያጁ ወይም የድርጅቱ ባለቤት ሊሆን አይገባም፡፡

የልዩነት ሃሳብ- አንድ ስራ አስኪያጅ ከአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 132/1/ከተመለከተው የወንጀል ሀላፊነት ነፃ ሊሆኑ የሚችለት ወንጀሉ የተፈፀመው ሳይፈቅዱ ወይም ሳያውቁ መሆኑን አሊያም በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ያለና ነገሮችን በጥንቃቄ የሚያይ ሰው የጥፋቱን መፈፀም ለመከላከል ይወስዳቸዋል ተብለው የሚገመቱ ጥንቃቄዎችን ለማድረግ ተገቢውን ትጋትና የአሰራር ጥበብ የተሞላበት እርምጃ መውሰዳቸውን በአንቀፅ 132/2/ አግባብ ሲያስረዱ ቢሆንም በዚህ አግባብ ለማስረዳታቸው የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ አያሳይም፡፡
Via #Danielfikadu law office
https://t.me/lawsocieties
የኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልዩ የሕግ ሰውነት በ1960 የፍትሐብሔር ሕግ አንቀፅ #394 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች የተገኘ ነው።
#አለ_ህግ #ale_hig
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ምክር ቤቱ የ3 ሚኒስትሮችን ሹመት አፀደቀ
......
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ9ኛ መደበኛ ጉባዔው የ3 ሚኒስትሮችን ሹመት አጽድቋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-

1. ዶ/ር አለሙ ስሜ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር
2. ዶ/ር ግርማ አመንቴ የግብርና ሚኒስትር
3. ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ የማዕድን ሚኒስትር ሆነው በ2 ድምፀ-ተአቅቦ በ10 ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ የተሾሙ ሲሆን፤ ተሿሚዎችም በጉባዔው ፊት ቀርበው የተጣለባቸው ኃላፊነት እንደሚወጡ ቃለ-መሃላ ፈጽመዋል፡፡

ጉባዔው በሌሎች ለዕለቱ በተያዙ አጀንዳዎች ላይ ውይይቱን ቀጥሏል፡፡
https://t.me/lawsocieties
በማህበራዊ ሚዲያ ጥላቻና ሐሰት መልዕክት ስያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ

ወላይታ ሶዶ፤ ጥር፣15/2015 ዓ.ም በወላይታ ዞን በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ በማህበራዊ ሚዲያ ጥላቻና ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ህብረተሰቡን ስያወክ የነበረ ግለሰብ ሰባት ወርና 3 ሺህ እንድቀጣ ተወስኗል።

ተከሳሽ አቶ ዳሳለኝ ደግፌ የተባለ ግለሰብ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከለከልና ለመቆጣጠር የወጠውን አዋጅ .1185/2012 በመተላለፍ የተለያዩ ስያሜ ያላቸውን ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንት በመጠቀም ከአንድ ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ በተለያዩ ቀናትና ጊዜያት በህዝብና መንግሥት መካከል እምነት እንዳይኖርና ሁከትና ግጭት እንዲነሳ በማሰብ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ተከሳሹ ግለሰብ በአከባቢው የሚገኙ ግለሰቦች ስብዕና የሚነኩ፣ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎችና የመንግስት ተቋማትን ሰብዓዊ ክብራቸውን የሚነኩና ስማቸውን የሚያጠፉ በሀሰተኛ አካውንቶች ሐሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨቱም ተመላክቷል።

በቀን 29/01/2015 ዓ.ም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በተደረገው ብርበራ ዉጤት መሰረት ህዝብና መንግስትን የሚያጋጩ ጽሑፎችና መረጃዎች ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዟል።

ሀሰተኛ መረጃዎ በማሰራጨት ወንጀል ተከሶ ፍ/ቤት የቀረበ ሲሆን ግራ ቀኙ ስያክራክራ የቆየው የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍ/ቤት በቀን 15/5/2015 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹን ሆነ ሌላዉን ማህብረሰብ ያስተምራል ያለዉን በተከሰሱበት ድንጋጌ ጥፋተኛ በማለት በ3000 ብር መቀጮ ወይም የሰባት ወር እሥራት እንድቀጣ ወስኗል።
ወላይታ ሶዶ
https://t.me/lawsocieties
የሚከተሉት ከተርን ኦቨር ታክስ ክፍያ ነፃ ናቸው፡-

1. ቢያንስ ሁለት ዓመት ያገለገለ መኖሪያ ቤት ሽያጭና የመኖሪያ ቤት ኪራይ፤
2. የፋይናንሰ አገልግሎቶች፤
3. ለሳንቲሞችና ሜዲሊያዎች ጥናት አገልግሎት ከሚውሉት በስተቀር የአገር ውስጥና የውጪ አገር ገንዘቦችና የዋስትና ሰነዶች ማሰራጨት፤
4. በኃይማኖት ድርጅቶች የሚሰጡ የእምነት ወይም ከአምልኮ ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች፤
5. የሕክምና አገልግሎትና አግባብ ባለው የመንግስት መ/ቤት በሚወጣ መመሪያ መሠረት በሐኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶች፤
6. በትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የማስተማር አገልግሎቶች እንዲሁም ለሕፃናት ጥበቃ በመዋዕለ ሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶች፤
7. የኤሌክትሪክ፣ የኪሮሲን የውሃ አቅርቦት፤
8. የትራንስፖርት አገልግሎት፤
9. ማናቸውንም የሥራ እንቅስቃሴ ለማከናወን ለሚሰጥ ፈቃድ ለመንግስት የሚፈፀም ክፍያ፤
10. 60% እና ከዚያ በላይ ሠራተኞቹ አካል ጉዳተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ድርጅት የሚያቀርባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች፤
11. መጽሐፍት፤
12. ሌሎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የሆኑ ሁሉ ናቸው፡፡
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ለህግ ተመራቂዎች
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከዚህ በታች በተጠቀሱት የሥራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት (7) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ (Link) https://recruitment.insa.gov.et/ በመጠቀም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
https://t.me/lawsocieties
ነፍሰ ጡር ሴት ለባሏ እንዲህ በማለት ትጠይቀዋለች:- ምን የምንወልድ ይመስልሃል -ወንድ ወይስ ሴት ልጅ?
ባል - " ምንም ቢሆን ግድ የለኝም። ፈጣሪ የሰጠንን በደስታ እቀበላለሁ ነገር ግን ወንድ ልጅ ከወለድን ሂሳብ አስተምረዋለሁ፣ ስፖርት እንዲሰራ አደርገዋለሁ፣ ሌሎች ጠቃሚ የሆኑ ክህሎቶችን አስተምረዋለሁ።’’ሚስት - "ሃ.. ሃ.. እና ሴት ልጅ ብትሆንስ?"ባል - ‘’ሴት ልጅ ከወለድን ምንም ነገር ማስተማር አይጠበቅብኝም። ምክንያቱም ሁሉንም ነገር የምታስተምረኝ እሷ ትሆናለች። እንደአዲስ እንዴት መልበስ እንዳለብኝ፣ እንዴት መመገብ እንዳለብኝ፣ ምን መናገር እንዳለብኝና እንደሌለብኝ ....ወዘተባጭሩ ሁለተኛ እናቴ ትሆናለች። ምንም የተለየ ነገር ባላደርግም እንደ ጀግናዋ ትቆጥረኛለች፣ የሆነ ነገር ስከለክላት ሁሌም ትረዳኛለች። ሁልጊዜ ባሏን በመልካም ነገር ሁሉ ከእኔ ጋር ታወዳድራለች..ዕድሜዋ ምንም ያህል ቢሆን ሁልጊዜ እንደ ልጅነቷ እንዳደርግላት ትፈልጋለች.. ለእኔ ስትል ከአለም ጋር ትጣላለች እና አንድ ሰው እኔን ቢጎዳ ያንን ሰው በጭራሽ ይቅር አትለውም።’’ሚስት - "ታዲያ ሴት ልጃችን ያን ሁሉ ነገር ስታደርግ ወንድ ልጃችን ግን አያደርገውም እያልክ ነው?’’ባል - "አይ ..እንደዛ ማለቴ አይደለም! ምናልባት እሱ እንዲሁ ሊያደርግ ይችላል ነገር ግን እነዚህን ነገሮች ለማዳበር ይማራል። ሴት ልጆች ከእነዚህ ነገሮች ጋር አብረው ይወለዳሉ። በአጭሩ የሴት ልጅ አባት መሆን ለማንኛውም ወንድ ኩራት ነው። “ሚስት - "ነገር ግን ለዘላለም ከእኛ ጋር አትቆይም። “ባል - "አዎ! ግን ከእሷ ጋር በልቧ ለዘላለም እንሆናለን። እሷ የምትሄድበት ቦታ ምንም ለውጥ አያመጣም። “ ሴት ልጆች ልዩ ስጦታ ናቸው...ቅድመ ሁኔታ ከሌለው ፍቅር እና እንክብካቤ (Unconditional Love & Care).....ጋር አብረው የተወለዱ። በሴት ልጅ/ልጆች ለተባረኩ ለሁሉም እድለኛ አባቶች መታሰቢያ ይሁንልኝ!!ከማህበራዊ ሚዲያው አግኝቸው ስለወደድኩት ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ በመቀየር አካፈልኳችሁ።
https://t.me/lawsocieties
የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው እቃዎች ከተመረቱ በኋላ በመጋዘን ስለማስቀመጥ ወይም ስለማስረከብ

1/የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው እቃዎች የማምረት ተግባር ከተጠናቀቀ በኋላ የኤክሳይዝ ታክስ እቃዎች ማከማቻ በመባል ወደ ሚታወቀው ክፍል መዘዋወር እና በመመሪያ መሰረት ከተፈቀደለት ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውጭ እስከሚደረጉ ድረስ በዚሁ ክፍል ውስጥ መቀመጥ አለባቸው፡፡ ሆኖም የተጣራ አልኮል መቀበያ ጋኖች የኤክሳይዝ ታክስ ዕቃዎች ማከማቻ እንደሆኑ ይቆጠራል፡፡
2/ የኤክሳይዝ ታክስ ዕቃዎች ማከማቻ ክፍል በር ላይ “የኤክሳይስ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች ማከማቻ ክፍል” የሚል ጽሁፍ መለጠፍ አለበት፡፡
3/ የኤክሳይዝ ታክስ ዕቃዎች ማከማቻ ክፍል የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው የተመረቱ ዕቃዎች ከማከማቻነት ወጪ ለሌላ ለማናቸውም ተግባር እንዲውል ማድረግ አይቻልም፡፡
4/ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው እቃዎች ለቆጠራ በሚያመች አኳኋን በኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው እቃዎች ማከማቻ ክፍል ውስጥ መቀመጥ አለባቸው፡፡
5/ ማንኛውም ሰው የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልበት እቃ መያዣ ጠርሙስ ወይም ማሸጊያ አምራቹን ለይቶ ማወቅ የሚያስችለው ልዩ ምልክቱ(ሌብል) የአምራቹ ስም፣ የተመረተበት ቦታ እና ቀን፣ አድራሻው፣ የተከታታይ ምርት ቅጥር፣ የባር ኮድ ወይም ሌላ ተጨማሪ ምልክት ሳይደረግበት በፊት ከኤክሳይስ ታክስ እቃዎች ማከማቻ ክፍል ማውጣት ወይም እንደወጣ ማድረግ ወይም መፍቀድ የለበትም፡፡
https://t.me/lawsocieties
👇👇👇👇👇👇👇
........
6/ ለውጭ ገበያ ወይም ከኤክሳይዝ ታክስ ነጻ ሆነው ሊሸጡ የተመረቱ ዕቃዎች ለቁጥጥር እና ለክትትል በሚያመች መንገድ ከሌሎች እቃዎች ተለይተው መቀመጥ አለባቸው፡፡
7/ የተፈቀደለት አምራች ከተሸጡ በኋላ ወደ ተመረቱበት ፋብሪካ የተመለሱ እቃዎች የሚቀመጡበት የተለየ መጋዘን ሊኖረው ይገባል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር
#አለ_ህግ #ale_hig #ህግ #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
በዋና ጥያቄ ላይ ያልተነሳ
ምስክር መስቀለኛ ጥያቄ በሚጠየቅበት ወቅት በጣም የተለመደው መቃወሚያ በዋና ጥያቄ አልተነሳም የሚል ሲሆን ፍርድ ቤቶች በደፈናው ይቀበሉታል፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱም የስነ ስርዓት ህጎች ለጥያቄ መለኪያ የሚያስቀምጡት አግባብነት /relevance/ እንጂ ጥያቄው በዋና ጥያቄ መነሳት አለመነሳቱ አይደለም፡፡

#ምሳሌ
ምስክሩ በዋና ጥያቄ ወቅት "መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ጠዋት 3 ሰዓት አካባቢ መኖሪያ ቤቴ አካባቢ ተከሳሽ ተበዳዩን ሲመታው አይቻለው" በማለት ምስክርነት ሰጠ። በቀጣይ የቀረበለት መስቀለኛ ጥያቄ እና የሰጠው መልስ ይህንን ይመስላል።

ጥ---ልጅ አለህ?
መ--አዎ
ጥ--ስንት ልጅ?
መ--አንድ
ጥ--ወንድ ወይስ ሴት?
መ--ሴት
ጥ--መቼ ነው የተወለደችው?
መ--መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ.ም.
ጥ--ጥሩ፤ መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ብለሀል። ጠዋት ነው ወይስ ሌሊት?
መ--ጠዋት። 1 ሰዓት አካባቢ ወደ ሆስፒታል ወስድኳት። 5 ሰዓት አካባቢ ተገላገለች።
ጥ--ባለቤትህን ሆስፒታል ከወስድክበት ጊዜ ጀምሮ እስክትወልድ ድረስ አብረሃት ነበርክ?
መ--አዎ። ከዛ በኋላም እስከ 7 ሰዓት ድረስ አብሬያት ነበርኩኝ።

ቀጣዩ ጥያቄ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም። ተከሳሽ ተበዳይን ሲመታው አየሁኝ ያለበት ቀንና ሰዓት ሆስፒታል ነበርኩኝ ካለበት ቀንና ሰዓት ጋር ተመሳሳይ ነው። ሆኖም እዚህ ላይ ለመድረስ እስካሁን የተጠየቁት ጥያቄዎች በዋና ጥያቄ ያልተነሱ ናቸው።
ስለሆነም በመስቀለኛ ጥያቄ ወቅት የጠያቂው ግዴታ የጥያቄውን አግባብነት ማስረዳት ብቻ ነው። ይህንን ሲያደርግ ከተቃራኒው ተከራካሪ ጋር ወደ ዳኛው ተጠግቶ አግባብነቱን ማስመዝገብ አለበት።
ምስክሩ እየሰማ የሚናገር ከሆነ ግን ምስክሩ እንዲነቃና ቀድሞ ለመልሱ እንዲዘጋጅበት /ምናልባትም ሐሰተኛ ምስክርነት እንዲሰጥ/ ያደርገዋል።
በአብርሐም ዩሐንስ
ኢትዮ-ሕግ🇪🇹👇
#ethiolawtips
#አለ_ህግ #ale_hig #lawsocieties #ህግ
https://t.me/lawsocieties
ውል መሰረዝ፤
ማፍረስ እና በስምምነት ማቋረጥ
ውል መሰረዝ

ከተዋዋይ ወገኖች መካከል አንደኛው እንደ ውሉ ባለመፈጸሙና የውሉን ግዴታ በመጣሱ በተዋዋዩ ወይም በፍርድ ቤት ውሉን ወይም በውሉ የተቋቋሙትን ግዴታዎች ቀሪ ማድረግ
ውል የሚሰረዘው ከመሠረቱ ግድፈት ስላለው አይደለም፡፡ ይልቁንም የውል መሠረዝ ምክንያት ከተዋዋይ ወገኖች የውል ግዴታን ከመፈፀምና ካለመፈፀም ጋር ተያይዞ የሚከሠት ነው፡፡ የውል መሠረዝ ሥርዓትም የራሱ የሆነ አካሄድ አለው፡፡ ይኸውም ውሉን የመሠረዝ ፍላጐት ያለውን ወገን የውሉ ግዴታ ባለመፈፀሙ የተነሳ ከህግ ወይም ከውሉ ከራሱ ባገኘው መብት ተጠቅሞ ውሉን ሊሰርዝ ይችላል፡፡ ይህ መብት ተግባራዊ የሚሆንበት አጋጣሚም ግዴታው ባለመፈፀሙ የተነሳ የደረሰውን ጉዳት ከማረጋገጥ ጋር ተያይዞ የሚታይ እንጂ ጥያቄ አቅራቢው ሁል ጊዜ ተቀባይነት የሚያገኝበት አይደለም፡፡ በመሆኑም የውል ይሰረዝልኝና ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎች በህጉ አግባብ የሚስተናገዱ ስለመሆኑ የፍ/ህ/ቁ. 1784 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ፡፡
ሰ/መ/ቁ. 32299 ቅጽ 8
ውል በተናጠል መሰረዝ
አንደኛው ተዋዋይ ወገን የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌን መሠረት በማድረግ ውልን በተናጠል ለመሠረዝ የሚችለው ከሚከተለት ሶስት ሁኔታዎች አንደኛው የተሟላ መሆኑን ለማስረዳት ሲችል ነው፡፡
• የመጀመሪያው ባለዕዳው በውሉ ላይ በተመለከተው መሠረት የውሉን ግዴታ የሚፈፅምበት ቁርጠኛ ጊዜ በውሉ ላይ በግልፅ ተመልክቶ እንደሆነና በውሉ ላይ የተገለፀው ቁርጥ የሆነ የውል መፈፀሚያ ጊዜ ያለፈ እንደሆነ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ አንደኛው ተዋዋይ ወገን በተናጠል ውሉን ለመሰረዝ የሚችል መሆኑን የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 እና የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1775(ለ) ድንጋጌዎች በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
• ሁለተኛው ምክንያት ባለዕዳው ውሉን ያልፈፀመበትን ምክንያትና ሌሎች የአካባቢ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ዳኞች ባለዕዳው ውሉን የሚፈፅምበት የችሮታ ጊዜ ከሰጡት በኋላ ባለእዳው በዳኛ ውሣኔ በተሰጠው የችሮታ ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ሳይፈጽም የቀረ እንደሆነ መሆኑን ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1770 ድንጋጌዎች ለመረዳት ይቻላል፡፡
ሶስተኛው ባለገንዘቡ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 በተደነገገው መሠረት ሌላኛው ተዋዋይ (ባለዕዳው) በውል የገባውን ግዴታ የሚፈፅምበትን ጊዜ በመግለፅ ማስጠንቀቂያ የሰጠ ሲሆንና በማስጠንቀቂያው በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሳይፈፅም ሲቀር መሆኑን ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል፡፡ አንደኛው ተዋዋይ ወገን ሌላኛው ተዋዋይ ወገን በውሉ መሠረት እንዲፈፅም ለመጠየቅና ማስጠንቀቂያ ለመስጠት የሚችለው በመጀመሪያ እሱ የበኩሉን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም የተዘጋጀ ሲሆን እንደሆነ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1857 በግልፅ ይደነግጋል፡፡
ስለሆነም ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ መሠረታዊ ዓላማና ግብ እንደዚሁም የድንጋጌውን የተፈፃሚነት ወሰን ለመረዳት የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771 ንዑስ አንቀጽ 1 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1757 ድንጋጌዎች ጋር በማጣመር መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አንፃር ስንመዝነው አንደኛው ተዋዋይ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771 ንዑስ አንቀጽ 1 ሌላኛው ተዋዋይ ውሉን እንዲፈፅምለት ለመጠየቅ፤ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 ድንጋጌዎች መሠረት የውል መፈፀሚያ ጊዜ ግልፅ ማስጠንቀቂያ በመስጠትና በፍትሐብሔር ቁጥር 1787 በተደነገገው መሠረት ውሉን በተናጠል ለመሠረዝ በመጀመሪያ በእሱ በኩል በውል የተጣለበትን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑ በማስረጃ ለማረጋገጥ የቻለ መሆን እንዳለበት የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1757 እና የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌዎችን ይዘትና መሠረታዊ ግብ በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
ሕግ አውጭው በውል ለገባው ግዴታ ተገዥ በመሆን በእሱ በኩል ያለውን ግዴታ ያልፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ለማረጋገጥ ያልቻለ አንድ ተዋዋይ ወገን ሌላኛውን ተዋዋይ ወገን ቀድሞ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን በተናጠል እንዲሰርዝ በማሰብ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌን አውጇል ተብሎ አይገመትም፡፡ አንድ ተዋዋይ የውሉን መፈፀሚያ የጊዜ ገደብ በመግለጽ ለሌላኛው ወገን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውል በተናጠል ለመሰረዝ የሚችለው በመጀመሪያ እሱ በውሉ የገባውን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 57280 ቅጽ 13፣ ፍ/ህ/ቁ. 1770፣ 1771፣ 1774፣ 1757፣ 1787
ውል ማፍረስ
በህጉ የተቀመጡት የውል አመሰራረት መስፈርቶችን ያለሟላና ግድፈት ያለበት በመሆኑ የተነሳ የውሉ ወይም በውሉ የተቋቋሙትን ግዴታዎች መቅረት
ውል ማፍረስና ውል መሠረዝ በውል የተቋቋሙት ግዴታዎች ከሚቀሩባቸው መንገዶች ውስጥ የሚካተቱ ቢሆንም ምክንያታቸውና ውጤታቸው የተለያዩ ነው፡፡ የውል ማፍረስ ከውል አመሠራረት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሲሆን ሲሆነ
ውሉ ከአመሰራረቱ በህጉ የተመለከቱትን ሁኔታዎች ባለማሟላቱ ግድፈት ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በሌላ በኩል የውል መሰረዝ ጉዳይ ከውል አመሰራረት ችግር የሚነሳ ሳይሆን ከተዋዋይ ወገኖች የውል ግዴታውን ካለመወጣት የሚመነጭ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 32299 ቅጽ 8
ውል በስምምነት ማቋረጥ /ቀሪ ማድረግ/
ተዋዋይ ወገኖች በውል አቋቁመውት የነበረውን ግዴታ በፍታሐብሔር ሕግ ቁጥር 1819 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት በስምምነት ቀሪ ሲያደርጉ የተለየ ፎርም መከተል እንዳለባቸው የሚደነግግ አስገዳጅ ድንጋጌ የለም፡፡ የውለታ በተዋዋዮች ስምምነት መቋረጥ (terminate) መደረግ ከውል መፍረስ ወይም ከውል መሠረዝ የተለየ ባህሪና ውጤት ያለው መሆኑን አግባብነት ያላቸውን የፍታብሔር ድንጋጌዎች ይዘት በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡ እንደዚሁም ውል በስምምነት ቀሪ ማድረግ (termination of contract) ውልን ከማሻሻል (ውል ከመለወጥ) (variation of contract) እና ውል ከመተካት (Novation of contract) የተለየ ባህሪ፣ ይዘትና ውጤት ያለው መሆኑን፣ የፍታሐብሔር ሕግ ቁጥር 1819 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን፣ የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1722 እና የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1826 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን ይዘት በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
የውሉ በተዋዋዮቹ ፈቃድና ስምምነት መቋረጥ (ቀሪ) መሆን የተዋዋይ ወገኖች የወደፊት የውል የመፈፀም ግዴታ የሚያስቀር መሆኑን የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1819 ንዑስ አንቀጽ 2 ይደነግጋል፡፡ እንደዚሁም የውሉ መቋረጥ /ቀሪ/ መሆን ያለፈውን ሁኔታ የማይነካ መሆኑን የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1819 ንዑስ አንቀጽ 3 ይደነግጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የውል ቀሪ መሆን (termination of contract) ተዋዋዮቹ በውል አቋቋመውት የነበረውን መብትና ግዴታ ቀሪ የማድረግ ውጤት የሚኖረው መሆኑን ከፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1807 /ለ/ ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 63063 ቅጽ 14፣ ፍ/ህ/ቁ. 1682-84፣ 1722
በአብላጫ ድምፅ የተሰጠ
#ethiolawtips
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የ737 ማክስ አደጋ ሰለባ ዘመዶች ፍርድ ቤት ቃላቸውን ሊሰጡ ነው
አውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ኩባንያ እንዲከሰስ የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ፍርድ ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት፣ በሁለቱ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ በደረሰው አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ዘመዶች በመጪው ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን እንደሚሰጡ ከፍርድ ቤታ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
ኢትዮጵያ የሚበላ ምግብ ዋጋ ውድ ከሆነባቸው የአፍሪካ ሃገራት ከቀዳሚዎቹ ተርታ ነች ተባለ

ከአለም 8ተኛ ደረጃ ላይ መሆኗን ሰምተናል፡፡

ከዚምባቡዌ ቀጥላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያለባት ሃገር እንደሆነች በጥናት ተረጋግጧል፡፡

የኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በዋጋ ግሸበት ምክንያቶችና መፍትሄ ላይ ያደረገውን ጥናት ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል ይፋ አድርጓል፡፡

አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ 49.1 በመቶ ነው የተባለ ሲሆን የምግብ የዋጋ ንረት ከፍተኛውን ድርሻ ይዟል፡፡

ይህም ከክልል ክልል የተለያየ መሆኑ በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡

በአማራና ደቡብ ክልል ያለው የዋጋ ግሽበት ከሃገራዊ ምጣኔው ከፍ ያለ ነው ተብሏል፡፡

በተለይ ለምግብ የዋጋ ንረቱ የምርት መጠን ከፍላጎት ጋር አለመመጣጠን አንዱ ምክንያት ነው ብለዋል ጥናቱን ያቀረቡት ዶ/ር ታደሰ ኩማ፡፡

ገበሬው ከሚያመርተው ምርት ከራሱ ፍጆታ ተርፎት ለገበያ የሚያቀርበው በአማካይ ከ20 በመቶ አይበልጥም ተብሏል፡፡

ከሚመረተው በቆሎ 85 በመቶው ገበሬው ለእለት ፍጆታው ያውለዋል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል ከሚመረተው ጤፍ ለገበያ ቀርቦ ከተማው የሚሸምተው 30 በመቶውን ብቻ ነው ተብሏል፡፡

ይህም ምርታማነት ጨምሯል ቢባልም አብዛኛው አነስተኛ አምራች ገበሬ በመሆኑ የሚያመርተው እህል እምብዛም ከራሱ የሚያልፍ በመሆኑ ዋጋ እንዲንር ምክንያት መሆኑን ሰምተናል፡፡

ማምረት እንደተቻለ ከውጭ ማስመጣት ደግሞ ሌላው ምክንያት ሆኖ ቀርቧል፡፡

ኢትዮጵያ ከ97 በመቶ በላይ የዘይት ፍላጎቷን ከውጭ ገዝታ እንደምታመጣም በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡

ከፍላጎትና አቅርቦት አለመመጣጠን ባሻገር እሴት የማይጨምሩ ደላሎች በገበያ ሰንሰለቱ በብዛት መሳተፍ ፣ መንግስትም ተገቢውን ቁጥጥርና የእርምት እርምጃ አለመውሰድ የዋጋ ንረቱን አባብሶታል ይላል ጥናቱ፡፡

በዚህም ምክንያት ምርት አምራቹ ከሚሸጥበት 58 በመቶ ዋጋው ከፍ ብሎ ሸማቹ ጋር እንዲደርስ አድርጓል ተብሏል፡፡

ይህን ሁኔታ ለመቀየር መንግስት የፖሊሲ ለውጥ እንዲያደርግ ጥናቱ መክሯል፡፡

ገበያውን ማዘመን፣ የገበያውን ምርታማነት ለመጨመር ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የተቋማት አደረጃጀትና አሰራርን በመፈተሽ ተገቢውን እና መልክ ያጣውን የገበያ ሥርዓት ማስተካልም የመንግስት የቤት ስራ ነው ተብሏል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
#Ethiopia #ShegerWerewoch
#አለ_ህግ #ale_hig #lawsocieties #law
https://t.me/lawsocieties