This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አሳትፉን
#ህጉ_የኔም_ነው_ይመለከተኛል
ኤቲኤሞች ለአካል ጉዳተኞችተደራሽ ናቸው ?
በአዲስ አበባ ውስጥ የምናገኛቸው አብዛኛዎቹ ኤቲኤምዎች ለአካል ጉዳተኞች ሙሉ በሙሉ ተደራሽ አለመሆናቸውን ሲቪል ሶሳይቲ ሪሶርስ ሴንተር ከCSSP2 ጋር በመተባበር አዘጋጅቶ በላከልን መልዕክት አሳይቷል።
ይህ ሁኔታ እንዲስተካከልና ሁሉም አካል ጉዳተኞች የህዝብ አገልግሎት የማግኘት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው እንዲከበር ጠይቋል።
@tikvahethiopia

#ህጉ ምን ይላል?
#የዉል ስምምነት የሚጸናባቸዉ ነጥቦች
በእዉቁ የህግ መዝገበ ቃላት ብላክስ ሎዉ ላይ “ዉል ማለት በሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በመካከላቸዉ አንድን ድርጊት ለማድረግ ወይንም ላለማድርግ በመስማማት ግዴታ የሚፈጥሩበት መንገድ ነዉ” ሲል ትርጉም ይሰጠዋል፡፡ እንዲሁም በፍትሐ ብሔር ህጋችን አንቀፅ 1675 ላይ “ዉል ማለት ንብረታቸዉን የሚመለከቱ ግዴታዎችን ለማቋቋም ወይም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ባላቸዉ ተወዳዳሪ ግንኙነት በሁለት ወይም በብዙ ሰዎች መሀል የሚደረግ ስምምነት ነዉ” በማለት ትርጉም ሰጥቶታል፡፡
የዉል ስምምነት ከሌሎች ስምምነቶች የሚለየዉ ለአፈፀሙ ከበስተጀርባዉ የሕግ ድጋፍ ያለዉ ስምምነት መሆኑ ነዉ፡፡ ይህም ማለት ተዋዋይ ወገኖች የተስማሙበትን ነገር እንደ ስምምነታቸዉ ባይፈፅሙ ያልፈፀሙትን ነገር በህግ ተገደዉ እንዲፈፅሙ ይደረጋሉ፡፡ ይህም የሚያሳየን ዉል በተስማሚዎቹ አካላት መካከል እንደ ህግ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን ነዉ፡፡

ድፍንፍን ለማድረግ የተሞከረው ሹም ሽረት #ከህግ አንፃር፣
ስለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት “ መልቀቂያ እና ሹመት ” ህገ መንግስቱ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት በፌደራል መንግስት ጠቅላይ ሚኒሰቴር አቅራቢነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማሉ።
የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ
አላማ- በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሚሾሙ ዳኞች ግልጽ፣ ገለልተኛና ተአማኒ በሆነ አሰራር የሚሾሙበትን ሥርዓት በመዘርጋት ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በብቃት፣ በሙሉ ነጻነት፣ ገለልተኝነትና ተጠያቂነት የሚያከናውኑበትን አሰራር ማረጋገጥ፤
"የፌደራል ዳኞች" ማለት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሾሙ ዳኞች ሲሆኑ ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ይጨምራል ።
የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ የዳኞች የሥራ ስንብት/ መልቀቅን በተመለከተ
ከዳኝነት ሥራ ለመልቀቅ ጥያቄ ሲያቀርብ የሁለት ወር / እንጊሊዝኛው 3 ወር ይላል / ቅድሚያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፤
በተጨማሪም
የፌደራል ጠቅላይ ፕሬዚዳንት ወይም ምክትል ፕሬዚዳንት ስለቀረበበት ከስራ የሚሰናበቱት ጉዳይ በጉባዔው ታይቶ ውሳኔ ሲያገኝ እና ጥያቄው በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት ለህዝብ ተወካዮች ቀርቦ ምክርቤቱ ውሳኔውን በአብላጫ ድምጽ ሲያጸድቀው ነው ፡፡
የፌደራል ጠቅል ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምከትል የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አባሎች እንደመሆናቸው ሥራቸውን ስለሚለቁበት ሁኔታ አንቀጽ 19 ላይ ዝርዘር ድንጋጌዎችን ያስቀምጣል
የጉባዔው አባሎች ሥራቸውን ስለሚለቁበት ሁኔታ
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮(፩ ) ሀ፣ ለ፣ሐ፣መ፤ ሠ እና ሰ ከተመለከቱት በስተቀር ማንኛዋም የጉባኤ አባል፤
ሀ) ከደንብ መተላለፍ ውጭ በሆነ ወንጀል ተከሶ ሲፈረድበት፣
ለ)በጤና ችግር ምክንያት ስራውን በአግባቡ ማከናወን ሲሳነው፤
ሐ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም በክልል ምክር ቤት አባልነት ሲመረጥ ወይም በሹመት፤ ወይም በዝውውር በፌደራል ወይም በክልል መንግስት ሥራ አስፈጻሚ ቦታ ሲመደብ፤
መ) ይህን አዋጅ ወይም የጉባዔውን የውስጥ የአሰራር ሥነ ሥርዓት ባለማክበሩ ጉዳዩ ለጉባኤው ቀርቦ ለአባልነት ተገቢ አለመሆኑ ከጉባኤው ጠቅላላ አባላት በሁለት ሶስተኛ ድምጽ ሲወሰን፤
ሠ) በሌላ ማናቸውም ምክንያት በጉባኤው ላለዉ ከፍተኛ ኃላፊነት አባል ሆኖ ለመቀጠል የማይችል ሲሆን እና በጉባኤዉ ሲወሰን፤ ከጉባዔው አባልነት ይሰናበታል ፡፡
፪/ ማንኛውም የጉባኤው አባል ከጉባኤው ጽሕፈት ቤቱ በኩል ከአንድ ወር አስቀድሞ ለጉባዔው በጽሁፍ ማቅረብ አለበት፡፡
ተሿሚዎችን በተመለከተ
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ለመሾም - የሚያበቁ ተጨማሪ ሁኔታዎች
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ለመሾም ከዚህ በላይ በአንቀጽ ፳፪ ከተደነገገው በተጨማሪ የሚከተሉት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
፩/ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳኝነት ቢያንስ አስር ዓመት ወይም በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኝነት ቢያንስ አስር ዓመት ያገለገለ እና በሥራዉ ዘመን መልካም ሥነ-ምግባርን ፣ታታሪነትን ፣ ብቃትን እና ቅንነትን ያሳየ፤ ይህም በዳኞች ምልመላ ኮሚቴ ከተረጋገጠ፤ ወይም
፪/ በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ፩ የተደነገገው ቢኖርም በዳኝነት ሙያ ከተጠቀሰው የአገልግሎት ጊዜ ሁለት ሶስተኛውን ያገለገለ በዳኝነት ሥራዉ ላይ በቆየችበት ጊዜ መልካም ሥነ-ምግባሩ፣ ታታሪነቱ እና የላቀ ሞያዊ ብቃቱ የተመሰከረለት ሰው የጉባዔውን ሁለት ሦስተኛ የድምፅ ድጋፍ ካገኘ በልዩ ሁኔታ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት ዕጩ ሆኖ ሊቀርብ ልትቀርብ ይችላል፡፡
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ እና ፪ የተደነገገው ቢኖርም በማንኛውም የህግ ሙያ ቢያንስ ፳ ዓመት ያገለገለ በሥራው ላይ በቆየችበት ጊዜ መልካም ሥነ-ምግባሩ፣ ታታሪነቱ እና የላቀ ሞያዊ ብቃቱ የተመሰከረለት ሰው የጉባዔውን ሁለት ሦስተኛ የድምፅ ድጋፍ ካገኘ በልዩ ሁኔታ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት ዕጩ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል።
ህገመንግስቱ እና የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ከላይ በተዘረዘረው መልኩ ሰንበትና ሹመቱ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለመት መንገድ መሆን እንዳለበት በግልጽ ቢደነግጉም ፣ ከአንዳንድ የፓርላማ አባላትም የምክር ቤት አባላት አዲስ የተሸሙት ግለሰቦች ማንነት በተገቢው ሁኔታ ለመገምገም ቀድሞ ስለግለሰቦቹ አለመነገሩን እንዲሁም ከዚህ ቀደም የነበሩት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት በምን ምክንያት እንደለቀቁ አለመብራራቱ ጥያቄ አንስተው የነበር ቢሆንም መልቀቂያውና ሹመቱ መጽደቁ አልቀረም፡፡
#Daniel_Fikadu /ዳንኤል ፍቃዱ
(ጠበቃና የህግ አማካሪ)/
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Law_Societies
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/