የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር የስራ አመራር ኅዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የማህበሩ ፕሬዝደንት ያቀረቡት የሥራ መልቀቂያ ላይ ከመከረ በኋላ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል።
በጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀጽ 66 ንዑስ አንቀጽ 3 የማኅበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሬዝዳንቱ በማይኖሩበት ጊዜ ወይም ሥራቸውን ሊሠሩ በማይችሉበት ጊዜ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ፕሬዝዳንቱን ተክቶ ሥራውን ማከናወን እንዳለበት ይደነግጋል።
በዚሁ መሠረት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት የነበሩት ኃላፊነታቸውን በራሳቸው ፈቃድ የተዉ መሆኑን በጽሑፍ ስላሳወቁ የማህበሩ ም/ፕሬዝደንት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ፕሬዝደንቷን ተክተው እንዲሰሠሩ የሥራ አስፈጻሚው በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
የማህበሩ ም/ፕሬዝደንት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ከዛሬ ጀምሮ ለሚሰጡት አመራርና ለሚያከናውኗቸው ተግባራት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሙሉ ድጋፉን የሚሰጥ ሲሆን አቶ ቴዎድሮስ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ከፍ ባለ ትጋት እና ውጤታማ አመራር በመስጠት እንደሚወጡት በመተማመን መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ሥራ አስፈጻሚው ይመኛል!
ማህበሩ በቀጣይ እንቅስቃሴዎቹን በተመለከተ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም ለመላው አባላቱ እና ወደ ሦስተኛ አካላት የሚደርስ መሆኑን ያሳውቃል::
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ህዳር 14 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ

👍15❤1
መርህ እና የህግ የበላይነት
አንድ ጊዜ ልምምድ ለማድረግ ዘግይቼ ደርሸ ነበር እናም አሰልጣኙ ዙር እንድሮጥ አድርጎኛል። ወደ ስልጠናው የወሰደኝ አባቴ ነበር። አሰልጣኙም አባቴ ነበር።
One time was late to practice and coach made me run laps. My dad was the coach. And he drove me to practice.
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

👍3👏3😁2🤔1
Audio
👍3
#Ethiopia Road Authority(ERA)#🚩For Fresh & Exp
▪️25 Open Positions
▪️Qualification: Automotive Technology, Electro Mechanical Engineering, LLB law, Construction Law, Machine Operator, 8th, 10th, 12th & relateds.
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://bit.ly/3OG5huH
▪️Deadline: December 09/2022

👍4👎2
ሀ.👉የራስ ታክስ ስሌት የማሻሻያ ጥያቄ አቀራረብና አፈጻጸም መመሪያ ረቂቅ
ለ.👉የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ መመሪያ ረቂቅ
ሐ.👉የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት አሰጣጥ መመሪያ ረቂቅ
ረቂቁ የቀደሙትን መመሪያዎች ( መመሪያ 144/2011,142/2011 እና 139/2010 ( መመሪያ 128/2009 እና 55/2003 ጨምሮ ) እንደሚተኩ የሚጠበቅ ሲሆን, በገቢ ሚንስትር ከተፈረሙበት ጀምሮ ተፈፃሚ ናቸው::
_//_................
Hima _ Tax Solutions
Source: HIMA_Xpress_Tax

ተገዶ_የመያዝ_Habeas_corpus_ስረ_ነገር_ስልጣን.pdf
320.7 KB
የሰበር መዝ/ቁ. 230167፣ 230168፣ 230169 /ያልታተሙ/
በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 5(1)(ኘ) መሰረት ተገድዶ የመያዝን ህጋዊነት ለማረጋገጥ የሚቀርብን አቤቱታ / Habeas corpus/ ተቀብሎ የማየት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን ያለው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው እንጂ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አይደለም ።
#Click Ethiopian Laws

👍9
የማስረጃ ህግ ጽንሰ ሀሳቦች
= ማስረጃ ምንድነዉ ?
ማስረጃ በመመርመር ላይ ያለ ወይም አከራካሪ የሆነ ፍሬ ነገር ስለመኖር/ያለመኖሩ፣ እውነት /ሀሰት ስለመሆኑ ከሚረጋገጥባቸው ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ፍሬ ነገር ሲብራራ ደግሞ ሰዎች በስሜት ህዋሳቶቻቸው የሚረዱአቸው/የሚለዩአቸው ኩነቶች ወይም ክስተቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም ማስረጃ ማለት ሰዎች በስሜት ህዋሳቶቻቸው የሚረዱአቸው/የሚለዩአቸው ኩነቶች ወይም ክስተቶች ስለመኖር/ያለመኖሩ፣ እውነት /ሀሰት ስለመሆኑ ከሚረጋገጥባቸው ነገሮች አንዱ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ፡፡ ሰዎችም ብዙ ግዜ ወደ ፍርድ ቤት የሚመጡት የዚህን ፍሬ ነገር መኖር አለመኖር ወይም እዉነት/ሀሰት መሆን እንዲረጋገጥላቸዉ ስለሚፈልጉ ነዉ፡፡ የዳኞችም ስራ ይህ ፍሬ ነገር በማስረጃ መረጋገጡን ማጣራት ነዉ፡፡
= የማስረጃ አይነቶች
1. የቃል ማስረጃ፡- በምስክር አንደበት የሚነገር ወይም የሚሰማ
2. የሰነድ ማስረጃ፡-ወረቀት ላይ ሰፍሮ የሚገኝና የሚነበብ ወይም ሀሳብ የያዘ ነገር
3. የቁሳዊ/ገላጭ ማስረጃ፡-መጠኑን ፣ዓይነቱን…ወዘተ የሚያሳይ ነዉ፡፡ዳኞች በራሳቸው የስሜት ህዋሳት ተረድተው ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ የሚቀርብ ዳኞች በአካል የሚመለከቱትን፣ የሚሰሙትን…የሚያመለከት ነው፡፡
4. የሳይንሳዊ ማስረጃ፡-የህክምና ሳይንስን ጨምሮ በሌሎች ሳይንሳዊ ዘዴዎች የተሰበሰበን፣ የተገኘን፣ የታወቀን፣ የተረጋገጠን… ፍሬ ነገር የሚመለከት
5. የኤሌክትሮኒክስ ማስረጃ፡-በኮምፒውተር፣ በኢንተርኔት ወይም ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ውስጥ የሚገኝ የማይጨበጥ/የማይዳሰስ መረጃ ናቸዉ።
= በማስረጃ የሚረጋገጥ እና የማይረጋገጥ ፍሬ ነገር ምን ማለት ነዉ?
የሚረጋገጡ ፍሬ ነገሮች
1. ከመሰረታዊ ህግ በመነጨ በጭብጥ የሚያዙ
2. ከማስረጃ ህግ በመነጨ በጭብጥ የሚያዙ ተቀጽላ ወይም ተጓዳኝ ፍሬ ነገሮች፤
3. በጭብጥ ለተያዙ ፍሬ ነገሮች አግባብነት ያላቸው ፍሬ ነገሮች ናቸዉ፡፡
እነዚህንም ፍሬ ነገሮች
በፍሬ ነገር ማረጋገጫ ዓይነቶች-
• በፍርድ ቤት ፊት የሚሰጥ የእምነት ቃል (Formal Admission)፣
• የዳኞች ግንዛቤ መዉሰድ/መያዝ (Judicial Notice)፣
• የህግ ግምት (Presumption)፣
• የመኃላ ቃል (Oath)፣
• ማስረጃ (Evidence) ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
= የማይረጋገጡ ፍሬ ነገሮች
- በፍ/ቤት ፊት በተከራካሪ ወገን የታመኑ (Formally Admitted Facts)
- በዳኞች ግንዛቤ የሚያዝባቸው (Facts which judges take Judicial Notice)
- በህግ ግምት የሚወሰድባቸው (Presumed Facts) ሆነው ከተገኙ ነው፡፡
ስለዚህ እነዚህን ፍሬ ነገሮች ተጨማሪ ማስረጃ ማቅረብ ሳያስፈልግ በነዚህ በቀረቡት ሁኔታዎች ብቻ ማስረዳት ይቻላል፡፡
= አግባብነት ወይም አስፈላጊነት እና ተቀባይነት ያለዉ ማስረጃ ምንነት
አግባብነት፡- አግባብነት ሲባል አንድ ፍሬ ነገር ወይም ማስረጃ ከሌላ ፍሬ ነገር ወይም ማስረጃ ጋር ያለውን ተዛመዶ ወይም ትስስር የሚገልጽ ቃል ነው፡፡ ይህም ማለት በተከራካሪ ወገን የሚቀርብ ማንኛዉም ማስረጃ ሳይሆን በግራቀኝ ለቀረበዉ ክርክር ተገቢነት ኖሮት ሊያስረዳ የሚችል ማለት ነዉ፡፡
ተቀባይነት፡- ሲባል አንድ ማስረጃ ለፍርድ ቤት ሲቀርብ ችሎቱ ይቀበለዋል ወይስ አይቀበለዉም የሚለዉን የሚያሳይ ነዉ፡፡ ችሎትም ማስረጃዉን ሊቀበለዉ ወይም ማስረጃዉን ሊተወዉ የሚችለዉ ደስ ስላለዉ ወይም ስላላለዉ ሳይሆን ማስረጃዉ በህጋዊ ሁኔታ መምጣት አለመምጣት ማጣራት እንዳለበት የሚያሳይ ሃሳብ ነዉ፡፡
= ማስረጃ ለማቅረብ ማን ይገደዳል ወይም የማን ሸክም ይሆናል?
ማስረጃ ለማቅረብ ማን ይገደዳል ሲባል መጀመሪያ ማስረጃ ማን ማቅረብ አለበት የሚለዉን ሃሳብ የሚያንጸባርቅ ነዉ፡፡ይህም ከሁለቱ ወገኖች አቤቱታ ይዘትና በህግ ተለይቶ ከተቀመጠው አንጻር ታይቶ የሚለይ ነው፡፡ በመሆኑም አንድ ነገር እንዳለ የሚከራከር ወገን ይህ ፍሬ ነገር ስለመኖሩ ቀድሞ የማስረዳት ወይም ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ፍሬነገሩም እንዳለ ተከራካሪዉ ካስረዳ ይህን ማስረጃ በማቅረብ መቀልበስ ወይም መቃወም ያለበት የሌላኛዉ ወገን ድርሻ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡ይህም የማስረዳት ሸክም ዞረ ይባላል፡፡
= የማስረጃ አቀራረብ መንገዶች
በመሰረቱ ማስረጃ ለፍርድ ቤት መቅረብ ያለበት ከአቤቱታ ወይም ከመልስ ጋር ነዉ፡፡ ነገር ግን አንድ አንድ ማስረጃዎች በምንፈልገዉ ሰሀት እና በምንጠይቀዉ ሰአት ላናገኛቸዉ እንችላለን፡፡ እነዚህንም ማስረጃዎች በወንጀልም ይሁን በፍትሐብሔር ክርክሮች እንድናቀርብ የምንጠይቅባቸዉ አግባቦች አሉ፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለዉ በማስረጃ ዝርዝራችን ላይ በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንዲቀርቡ በመጠየቅ፣ክስ ከመሰማቱ በፊት በችሎት በማቅረብ፣ እንዲሁም ክርክሩ እየተካሄደ ባለበት ግዜ በበቂ ምክንያት ሳይቀርቡ የቀሩ ማስረጃዎች ለችሎቱ በማቅረብ ነዉ፡፡
ዉበአለም መስፍን የቦ/ክ/ከ/ፍ/ጽ/ቤት/የህ/ስ/ም/መ ዳይሬክቶሬት ዐ/ህግ
ምንጭ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት

👍5😁2
Characterization
ካልታተሙት የሰበር ውሳኔዎች መካከል በምርጥነት ከሚፈረጁት አንዱ ሰ/መ/ቁ 197753 ነው።
በዚህ መዝገብ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሲሰጡ መርሳት የሌለባቸውን መሰረታዊ ቁምነገር ያስጨብጣል። በችሎቱ የተነሳው ነጥብ ተፈጻሚውን ህግ አስቀድሞ መለየት ይመለከታል።
ተፈጻሚውን ህግ ለመለየት በመጀመሪያ ጉዳዩ በምን የህግ ክፍል ስር እንደሚወድቅ መመደብ characterization ያስፈልጋል። characterization በተለይ በ conflict of laws ክርክሩ በየትኛው አገር ህግ እንደሚገዛ ለመለት ወሳኝ ሂደት / stage of the procedure to resolve a lawsuit that involves foreign law/ ነው። አንድ ፍርድ ቤቱ ለክርክሩ ተፈጻሚነት ያለው ህግ የቻይና አሊያም የፈረንሳይ ወይም የኢትዮጵያ መሆኑን ለመወሰን በቅድሚያ የጉዳዩ ዓይነት የቤተሰብ፡ የውርስ፡ የውል፡ ከውል ውጭ ሀላፊነት ስር እንደሚወድቅ መወሰን አለበት። አንዳንድ ጊዜ በአንዱ የህግ ክፍል ስር እንዲሁ ንዑስ የህግ መደቡን መለየት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ጉዳዩ የቤተሰብ ህግ ስር የሚመደብ ቢሆንም ጋብቻ፡ እንደ ባልና ሚስት፡ ጉዲፈቻ ወዘተ ስር የሚወድቅ መሆኑ ካልተፈረጀ በስተቀር ተፈጻሚውን አገር ህግ ለመለየት የሚያስችሉትን conflict of laws ደንቦች ማወቅ ያስቸግራል።
ሁለተኛው characterization አስፈላጊ የሚሆንበት ሁኔታ በአንድ ክስ ላይ የተነሳ/ሱ/ መቃወሚያ/ዎች/ ለመወሰን ነው። አንድ ፍርድ ቤት የይርጋ ደንቦችን ተፈጻሚ ለማድረግ ጉዳዩ በየትኛው የህግ ክፍል ስር እንደሚወድቅ መወሰን ይኖርበታል። በተለይ በፍ/ህ/ቁ የተመለከተውን የይርጋ ደንብ ተፈጻሚ ለማድረግ ፍርድ ቤቱ በልዩ ህግ ላይ የተመለከተ ይርጋ አለመኖሩን ማረጋገጥ ይኖርበታል። “በልዩ ህግ ላይ ይርጋ የለም” ለማለት ጉዳዩ በየትኛው ልዩ ህግ ስር እንደሚመደብ መወሰን ይኖርበታል። ይህን ሳያደርግ የፍ/ህ/ቁ 1845 ተፈጻሚ ሊያደርግ አይችልም።
የሰበር ችሎት ከላይ በተጠቀሰው ሰ/መ/ቁ 197753 ላይ ተፈጻሚውን ህግ መለየትን አስመልክቶ የሰጠው ትርጉም የስር ፍርድ ቤቶች አቅጣጫ የሚያስቀምጥ መመሪያ ተደርጎ መወሰድ ይኖርበታል።
ተፈጻሚውን ህግ አስቀድሞ መለየት የአንድ ፍርድ ቤት ዓይነተኛ ተግባርና ግዴታ ስለመሆኑ ችሎቱ በግልጽ አብራርቶ የሰጠው የህግ ትርጉም እንደሚከተለው ይነበባል።
የፍትሐብሔር ጉዳይ የቀረበለት ፍርድ ቤት በቀዳሚነት እንዲያከናውን ከሚጠበቁበት ተግባራት ውስጥ አንዱ እና መሠረታዊዉ ለቀረበለት ጉዲይ ተፈፃሚነት ያለዉ የህግ ክፍል የመለየት ተግባር (identification of applicable law) ነው፡፡ አስቀድሞ ይህን ማድረግ የቀረበው ክስ የክስ ምክንያት ያለው መሆን አለመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ያለው መሆን አለመሆኑን እና ሌሎች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ካሉ አስቀድሞ በመለየት መርምሮ ተገቢዉን ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችለዉ ሲሆን፣ ጉዳዩ ወደ ሙሉ የክርክር ሂደትት (full scale trial) የሚገባ ከሆነም በጉዳዩ ላይ ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችለዉን ጭብጥ ይዞ ክርክሩን በመምራት ለጉዳዩ ተፈፃሚነት ያለዉን ድንጋጌ በአግባቡ ለይቶ ፍትሐዊ ውሳኔ ለመስጠት ያስችላል።
By Abrham Yohannes

❤3
አለአግባብ መበልጸግ በኢትዮጵያ ህግ
=============================⤵️
ያለአግባብ መበልፀግ ህግ የውል፣ የንብረት እና ከውል ውጭ ያለ ሃላፊነት ህግ ክፍል በተጨማሪ የፍታብሔር ግንኙነትን የሚገዛ የህግ ክፍል ነው፡፡ ይህ የህግ ክፍል የውል፣ የንብረት እና ከውል ውጪ ያለ ሃላፊነት ህጎች የማይገዙትን የሰው ግንኝኑነት ክፍተት ለመሙላት በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ህግ ሲሆን ከዚህ ባሻገር ይህ የህግ ክፍል የሰዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ከመግዛት አኳያ ሰፊ ድርሻ ያለው ነው፡፡
ያለአግባብ መልፀግ ህግ በመሰረታዊነት የሚመነጨው ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው ኪሳራ ወይም ጉዳት ምክንያት መበልፀግ የለበትም ከሚለው መርህ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛው ሰው በሌላ ሰው ጉዳት ወይም ኪሳራ ምክንያት ያለአግባብ የበለፀገ እንደሆነ ጉዳት ወይም ኪሳራ ለደረሰበት ሰው ካሳ የመክፈል ግዴታ እንደሚኖርበት ይህ የህግ ክፍል ያስገድዳል፡፡
አጠቃላይ መርሆዎች
የዚህ ህግ ዋንኛ አላማ ሰዎች በገንዘባቸው፣ በንብረታቸው እና በጉልበታቸው ላይ ሚኖራቸውን ህጋዊ መብት መጠበቅ ነው፡፡
ይቀጥላል..... 👇👇👇👇👇👇

👍5