አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
October 17, 2022
October 17, 2022
October 19, 2022
ክስ መመስረቻ ጊዜ
---------_-__🛑
በሕገመንግሥቱ መሠረት ሰውን ከ48 ሰዓት በላይ ለ1 ሰዓትም እንኳን ማቆየት አይቻልም። በዚህ መሠረት በወንጀል ተጠርጥሮ ምርመራ እስኪጣራ በእስር የሚገኝን ሰው፣ ምርመራው ካለቀ በኋላ ክስ እስኪመሠረት ድረስ በእስር ለማቆየት የተፈለገ እንደሆነ ፍርድ ቤትን ማስፈቀድ ግድ ይላል። ምክንያቱም ከ48 ሰዓት በላይ አልፎም ለቀናት በእስር የነበረውን ሰው ክስ እስከሚመሠረትበት ድረስ በሚል ለተጨማሪ ጊዜ ማቆየት የተፈለገ እንደሆነ ፍርድ ቤት ሳይፈቅድ ማቆየት ጨርሶ ስለማይቻል ነው። የወመሕሥሥቁ 109 ዐቃቤ ሕግን በ15 ቀን ውስጥ ክስ እንዲያዘጋጅ ከሚያስገድድ ውጪ ክሱ እስከሚመሠረት ድረስ ግን ተጠርጣሪው በእስር እንዲቆይ አያዝዝም። ስለዚህ ተከሣሹን በእስር ማቆየት ከተፈለገ ፍርድ ቤትን ማስፈቀድ የግድ ነው።

በተጨማሪም ሕጉ ለዐቃቤ ሕግ የሚሰጠው የ15 ቀን ጊዜ ገደብ ጣሪያው ነው እንጂ ለእያንዳንዱ ጉዳይ እስከ 15 ቀን መቆየት ይችላል ማለት አይደለም ። ስለዚህ ጉዳዩ ግልጽና ብዛት የሌለው ወይም ውስብስብ ካልሆነ ዐቃቤ ሕግ ከ15 ቀንም ቀደም ብሎ ክስ መመሥረት ወይም መወሰን ይጠበቅበታል ማለት ነው። ስለዚህ ፍርድ ቤት ስንት ቀን እንደሚበቃው ጭምር ይወስናል፤ ከተጠየቀው 15 ቀን ውስጥ የሚበቃውን ያህል ብቻ በመፍቀድ ተከሳሹ በሕገመንግስቱ አንቀጽ 37 መሠረት የተፋጠነ ፍትሕ እንዲያገኝ ያደርጋል ማለት ነው።
በጠበቃ ታምራት ኪዳነማርያም
https://t.me/lawsocieties
October 19, 2022
October 19, 2022
October 19, 2022
እሁድ እሁድ ሁሌ ማታ ማታ በሳምንት አንድ ቀን የህግ ባለሙያዎች የሚመሩት የውይይት ጊዜ ስንት ስዓት ይመቸወታል?
Anonymous Poll
27%
2:00 ስዓት
41%
3:00 ስዓት
12%
3:30 ስዓት
20%
4:00 ስዓት
October 19, 2022
October 19, 2022
October 19, 2022
አዲሱ_የሒሳብ_መዝገብ_አያያዝ_መመሪያ_ቁጥር_176_2014.pdf
7.1 MB
October 20, 2022
October 20, 2022
"ይህን ያውቆ ኖሯል" አምዳችን ከመድሀኒት ትዕዛዝ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የወንጀል ድርጊቶች እና ቅጣታቸውን የሚመለከት ነው።

በዚሁም መሰረት የናርኮቲክ ወይም ሳይኮትሮፒክ መድሃኒቶችን ለህገወጥ አላማ ለማዋል በማሰብ የሕክምና ባለሙያን በማጭበርበር የመድሃኒት ማዘዣ እንዲሰጠው ያደረገ ወይም በህጋዊም ሆነ በህገወጥ በሆነ መንገድ ያገኘውን የመድሃኒት ማዘዣ ላልተፈቀደለት ሦስተኛ ወገን ያስተላለፈ ሰው፤ ወይም የናርኮቲክ ወይም ሳይኮትሮፒክ ነገሮች ማዘዣ አስቦ በህገወጥ መንገድ የፃፈ የሕክምና ባለሙያ እስከ አምስት ዓመት ሊደርስ በሚችል ጽኑ እስራት እና በገንዘብ መቀጮ ይቀጣል።
መልካም ቀን!
#Share #𝚊𝚕𝚎𝚑𝚒𝚐
https://t.me/lawsocieties
October 20, 2022
በተንቀሳቃሽ ስልኮቻችን አማካኝነት የሚፈጸሙ የማጭበርበር ተግባሮች

በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት የሚፈጸሙ የማጭበርበ ተግባራት በስልኮቻችን አማካኝነት በተጠቃሚዉ ላይ የሚቃጣ የጥቃት አይነት ነው፡፡

የጥቃቱ መነሻም የምንጠቀምባቸዉ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ከሲም ካርድ ጋር ግንኙነት በሚፈጥርበት ጊዜ እንዲሁም ከበይነመረብ ጋር በሚገናኝበት ወቅት የሚፈጸሙ የማጭበርበር አይነቶች ናቸዉ።

በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት ከሚፈጸሙ የማጭበርበሪያ መንገዶች መካከል የሚከተሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ ፦

👉 በስልኮቻችን ላይ ያልተሳኩ ጥሪዎችን በማድረግ( (Missed call) የሚፈጸም ማጭበርበር

ይህ አይነት የማጭበርበር ወንጀል መልሰዉ የይደዉሉልኝ ጥሪ በማስመሰል እና ተጠቃሚዎች መልሰው እንዲደዉሉላቸው በማድረግ ያላቸዉን ሂሳብ በሰከንድ የመዉሰድ ስልት ነዉ።

👉 በአላስፈላጊ መልክቶችን በማጥለቅለቅ የሚፈጸም ማጭበርበር ፦ ይህ ደግም በጣም ብዙ መልክቶችን በመላክ የሚመጣ የማጭበርበር ስልት ሲሆን ከመልክቶችም መካከል እንደ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፣ ሎተሪ ደርሷችኋል፣ ስኮላርሽፕ እና የመሳሰሉትን መልክቶች በመላክ ደንበኞች መልሰው እንዲልኩ፣ እንዲደዉሉ በማድረግ ሚስጥራዊ መረጃን መመንተፍ፣ ሂሳብን መዉሰድ እና ሌሎችን ድርጊቶች በማድረግ የሚፈጸም የማጭበርበር ወንጀል ነዉ።

👉 በቀጥታ በመደወል / direct call /፦ በቀጥታ በመደወል ከትክክለኛ ሰዉ ወይም ከትክክለኛ ድርጅት እንደተደወለ በማስመሰል የተለያዩ መረጃዎችን/ፋይሎችን/ዶክመንቶችን መስረቅ፣ማንነታችን የማጣራት፣ የተለያዩ ሚስጢራዊ ኮዶችን፣ አካዉንቶችን፣ የይለፍ ቃሎችን የመመንተፍ እንዲሁም በዚህ አካዉንት ብር መላክ አለብዎ ምክንያቱም ስኮላር ደርሶዎታል ፣ ሎተሪ ደርሶዎታል እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች በመጠቀም የሚፈጸም የማጭበርበር ስልት ነው፡፡
Source: INSA
#Share ላልሰማ ያሰሙ #ሼር
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
October 21, 2022
በንግድ_ችሎቶች_የሚታዩ_ጉዳዮች_ዓይነት.pdf
1 MB
October 21, 2022
በንግድ_ችሎቶች_የሚታዩ_ጉዳዮች_ዓይነት.pdf
1 MB
October 21, 2022
October 21, 2022