አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#የማስረጃ_ዓይነቶች_እና_ማስረጃ_ስለማያስፈልጋቸው_ፍሬ_ነገሮች
#መግቢያ

የአንድን ፍሬ-ነገር መኖር ወይም አለመኖር ማረጋገጥ የሚቻለው ማስረጃ በማቅረብ ነው፡፡
ማስረጃ በሰው ምስክሮች፣ በዘገባ፣ በሰነድ፣ ተጨባጭነት ባላቸዉ ሊታዩና ሊዳሰሱ በሚችሉ ነገሮች እና በኤግዚቢት መልክ ሊቀርብ ይቻላል፡፡ አቀራረቡም በሕግ በተደነገገው መሰረት ነው፡፡ በክርክር ሂደት ማስረጃ የማያስፈልጋቸው ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ይህ ከፍሬ ነገሩ የተለየ ባህሪ ወይም የሚያከራክር ነገር ባለመኖሩ ምክንያት ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ የማይሆንባቸዉ ሁኔታዎች ስላሉ ነዉ፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ ስለ ማስረጃ ዓይነቶችና ማስረጃ ስለማያስፈልጋቸው ጉዳዮች እንመለከታለን፡፡
1. #የማስረጃ_ዓይነቶች
ማስረጃ የአንድን ፍሬ ነገር መኖር ወይም አለመኖር ለማረጋገጥ ወይም ለማስተባበል ከሚቻልባቸው ዘዴዎች እና ማስረዳት ከሚፈለገው ፍሬ ነገር ወይም መደምደሚያ ጋር ማስረጃው የሚኖረውን ግንኙነትን መሠረት በማድረግ በተለያዩ መንገዶች ከፋፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
 ፍሬ ነገርን ለማስረዳት ከምንጠቀምበት ዘዴ አንጻር፤
ሀ. የሰው ማስረጃ
ሰዎች በአካል ፍርድ ቤት ቀርበዉ ለችሎት መረጃ የሚሰጡበት መንገድ ሲሆን ፍሬ ነገሩን ለፍርድ ቤቱ የሚገልፁት በንግግር ወይም በምልክት ነው፡፡ ይህም የምስክርነት ቃል ይባላል፡፡ የሰው ማስረጃዎች ቀጥተኛ ምስክር፣ የአከባቢ ምስክርና የባለሞያ ምስክር ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ለ. የሰነድ ማስረጃ
ይህ የማስረጃ ዓይነት በላዩ ላይ የተፃፈበት፣ የተሳለበት ወይም ማናቸዉም ዓይነት ምልክት የተደረገበት ሲሆን ለምሳሌ ውሎች፣ ቼኮች፣ ለፖሊስ ወይም ለፍርድ ቤት የተሰጠ የዕምነት ቃል የተመዘገበበት፣ በጽሁፍ የተገለፀ የላብራቶሪ ወይም የህክምና ምርመራ ውጤት የሰነድ ማስረጃዎች ናቸው፡፡
ሐ. ገላጭ ማስረጃ
ይህ የማስረጃ ዓይነት ፍርድ ቤት እንዲያየውና ግንዘቤ እንዲወስድበት የሚቀርብ ማስረጃ ነው፡፡ ለምሳሌ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረት ወይም ወንጀል ለመፈፀም አገልግሎት ላይ የዋለ መሣሪያ በማስረጃነት ሲቀርብ ገላጭ ማስረጃ ይባላል፡፡
 ማስረዳት ከተፈለገው ፍሬ ነገር አንጻር፤
 ቀጥተኛ የሆነ ማስረጃ
ማስረጃ ቀጥተኛ ነዉ የሚባለው አንድን በጭብጥነት የተያዘ ፍሬ ነገር ወይም የተወሰደን መደምደሚያ ትክክለኛነት በቀጥታ ለማረጋገጥ ወይም ለማስተባበል የሚቀርብ ሲሆን ነዉ፡፡ ከዚህ አንፃር ምስክር ቀርቦ በጭብጥ የተያዘው ፍሬነገር መኖሩን ወይም አለመኖሩን ራሱ በስሜት ህዋሳቱ አማካኝነት በማየት፣ በማሽተት፣ በመቅመስ፣ በመስማት ወይም በመዳሰስ ያወቀ መሆኑን የሚመሰክር ሲሆን ቀጥተኛ ማስረጃ ይባላል፡፡ በሰነድ ማስረጃ በኩልም በማስረጃነት የቀረበው ሰነድ በጭብጥ የተያዘዉ ፍሬ ነገር መኖርን ወይም የተደረሰበት መደምደሚያ ትክክለኛ መሆኑን ሰነዱ ራሱ በቀጥታ ያረጋግጣል ወይም ያስተባብላል በሚል የቀረበ ከሆነ ቀጥተኛ ማስረጃ ይባላል፡፡ ለምሳሌ በቂ ስንቅ ሳይኖረው ቼክ ፈርሞ ሰጥቷል በሚል ገንዘብ እንዲከፍል በተከሳሽ ላይ ለቀረበ ክስ ከሳሽ ቼኩን በማስረጃነት ያቀረበ ቢሆን ተከሳሹ ስለመፈረም አለመፈረሙ እና ስለ ገንዘቡ ልክ ቼኩ በቀጥታ የሚናገር ስለሆነ ቀጥተኛ ማስረጃ ይባላል፡፡
 ቀጥተኛ ያልሆነ ማስረጃ
ማስረጃ ቀጥተኛ ያልሆነ ነዉ የሚባለው ከሁለት ሁኔታዎች አንፃር ነዉ፡- አንደኛዉ ማስረጃ ያስረዳል የተባለዉን ፍሬ ነገር ምንጭ ማስረጃዉ ራሱ በቀጥታ ያወቀዉ ሳይሆን ከሌላ ያገኘዉ ወይም የተረዳዉ ሲሆን ነዉ፡፡ ምስክር ሌላ ሰዉ የገለፀለት መሆኑን ጠቅሶ የሚመሰክር ሲሆን ቀጥተኛ ሳይሆን የስሚ ስሚ ማስረጃ (Hearsay Evidence) ይባላል፡፡ የስሚስሚ ማስረጃን ቀጥተኛ ያልሆነ የሚያሰኘዉ ማስረጃዉ ፍሬ ነገሩን የሚገልፀዉ ራሱ በቀጥታ እንዳወቀ ሳይሆን ከሌላ ሰዉ የሰማዉ ወይም ከሰነድ ያነበበዉ በመሆኑ ነዉ፡፡ በሰነድ ማስረጃም በኩል የስሚ ስሚ የሚያሰኘዉ ማስረጃ ሆኖ የቀረበዉ ሰነድ ላይ የተገለፀዉ ፍሬ ነገር አዉቃለሁ በሚል በሌላ ሰዉ የተዘጋጀ ሲሆን ነዉ፡፡
ሁለተኛዉ ቀጥተኛ ያልሆነ ማስረጃ ነዉ የሚባልበት ሁኔታ የሚያጋጥመዉ አካባቢያዊ ማስረጃ (Circumstantial Evidence) የቀረበ እንደሆነ ነዉ፡፡ አካባቢያዊ ማስረጃ በጭብጥ ስለተያዘዉ ፍሬ ነገር መኖር አለመኖር በቀጥታ አይነግረንም፡፡ ይልቁንም የተወሰኑ ፍሬ ነገሮችን መኖር ወይም አለመኖር በማረጋገጥ ከዚህ ተነስተን በጭብጥ የተያዘዉን ፍሬ ነገር በተመለከተ አንድ ዓይነት መደምደሚያ ላይ እንድንደርስ የሚያደርግ ነዉ፡፡
የማስረጃዉ ቀጥተኛ ወይም አካባቢያዊ መሆን አለመሆኑን መለየት በማስረጃ ምዘና ጊዜ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ፡፡
1. ማስረጃ ስለማያስፈልጋቸዉ ፍሬ ነገሮች
ከፍሬ ነገሮቹ የተለየ ባህሪ ወይም የሚያከራክር ነገር ባለመኖሩ ምክንያት ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ የማይሆንባቸዉ ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነሱም፡-
ሀ. ፍርድ ቤት ግንዛቤ ሊወስድባቸዉ የሚችሉ ወይም የሚገቡ ፍሬ ነገሮች፣ ለምሳሌ በአዋጅ ቁጥር 3/1987 መሠረት በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ላይ የወጡ ነገሮችን ፍርድ ቤቶች ሊቀበሏቸዉ እንደሚገባ ተደንግጓል፡፡ በነጋሪት ጋዜጣ ላይ የተገለፀ ፍሬ ነገር ለማረጋገጥ ሌላ ማስረጃ መቀበል አያስፈልግም፡፡ ጋዜጣዉን በመመልከት ብቻ ግንዛቤ ሊወሰድበት ይገባል፡፡
ለ. በፍርድ ቤት በሚደረግ የክርክር ሂደት በተከራካሪ ወገን የታመኑ ፍሬ ነገሮች፣
ሐ. ጠቅላላ እዉነታዎች (Universal Truth)፣
መ. የሕግ ግምቶች (Presumptions) ናቸዉ፡፡ ለምሳሌ በጋብቻ ውስጥ የተፀነሰ (የተወለደ) ልጅ አባቱ ባልየው እንደሆነ ህጉ ግምት ይወስዳል፡፡
በአጠቃላይ ግራ ቀኝ ተከራካሪ ወገኖች ያስረዱልናል የሚሏቸዉን ማስረጃዎች ወይም ማስረጃ ባይቀርብባቸዉም በሕግ መሠረት የሚወሰኑትን ለይቶ ለማቅረብ የማስረጃ ዓይነቶችን እና ማሰረጃ የማያስፈለጋቸዉን ፍሬነገሮች ማወቁ ተገቢ ነዉ፡፡
https://t.me/lawsocieties
ምንጭ፡- FDRE Ministry of Justice/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር (13/01/2015 E.C)
Corporate Legal – Legal Advisor
Bank of Abyssinia
Addis Ababa
Full–time
Job Requirement • Education: LLB Degree in Law. • Experience: Minimum of 6 years banking experience, of which 3 years in the area of Law.
How to Apply
• Only short-listed candidates will be contacted. • Applicants should attach their educational credentials & updated work experience in PDF format Interested applicants who meet the above criteria are invited to apply within 5 consecutive days from the date of this advertisement using https://vacancy.bankofabyssinia.com Note:- In person or postal application is not accepted.
Vacancy at Ethiopian Human Rights Commission (EHRC)

🔰 Position: Senior Human Rights Officer Research, Campaign & Advocacy

SALARY RANGE: Gross monthly salary of ETB 22,014.00 – ETB 26,219.00 plus ETB 6,000.00 Housing allowance and ETB 1,500.00 Transport allowance

MA in Human Rights Law, LL.M in Human Rights, LLM in International Law, LLM in Law (Public Law relevant to Human Rights). Candidates with Bachelor of Laws (LL.B) with 4 years of relevant experience

📌 Deadline: 12 October 2022

📌ሰለ ሰራው ሙሉ መረጃ ለማየት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ👇👇
👉 Read Detail:- https://bit.ly/3SIc748
በወንጀል ጉዳዮች የእርቅ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2012

በእርቅ ማለቅ የሚችሉ ወንጀሎችን የወንጀል ምርመራ ከመጣራቱ በፊትም ሆነ ምርመራ ከተጣራ በኋላ ወይም ክስ ክተመሰረተ በኋላ ጉዳዩን በእርቅ መጨረሱ ወጪ ቆጣቢ፣ አስተማሪ፡ ማህበራዊ ግንኙነት ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል የሚያግዝ በመሆኑ፣

በእርቅ የሚያልቁ ጉዳዮችን በተመለከተ ወጥ አሰራር እንዲኖር፣ በእርቅ አፈፃፀም ሂደት ባለሙያዎቸ ሊከተሉት የሚገባቸዉን ስነ-ስርዓት ማስቀመጥ እና ግልፅነት ያለዉ አሰራር መዘርጋት በማስፈለጉ፣

በቀድሞዉ ፍትህ ሚኒስቴር ሲሰራበት የነበረዉ “በወንጀል ጉዳዮች የእርቅ አሰራር መመሪያ ቁጥር 14/2007 ከፌደራል ጠቅላይ ዐ/ህግ አኳያ መቃኘት እና ማሻሻል በማስፈልጉ፤ የፌዴራል ጠቅላይ ዐ/ህግ በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀፅ 21(2) መሰረት ይህንን መመሪያ አዉጥቷል፡፡
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ስር በሚገኙት የፍትሕ ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና ሌሎች 2 የወንጀል ተሳታፊዎች ላይ ክስ ተመሰረተ

ዐቃቤ ሕግ ከሙስና ወንጀል ምርመራ ጋር በተያያዘ 1ኛ ተከሳሽ አቶ ፈይሳ ሾርኬ ሳፋዎ በፍትሕ ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ 2ኛ ተከሳሽ አቶ አለማየሁ ታደሰ ከበደ በፍትሕ ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዐቃቤ ሕግ እንዲሁም 3ኛ ተከሳሻ አቶ ፍሬው በቀለ ታየ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የታገደውን እግድ እናስነሳልሃለን፤ በዋስም እንድትወጣ እና የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች እንዳይቀርቡ በማድረግ ክሱ እንዲቋረጥ እናደርጋለን በማለት ገንዘብ ጠይቀዋል፤ ተቀብለዋል በሚል የሙስና ወንጀል ክስ መስርቷል፡፡

የዐቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው ተከሳሾች በጥቅም በመመሳጠር የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘትና ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ የግል ተበዳይ አቶ አረጋይ ግርማይ በድሬደዋ ከተማ ቀበሌ 03 የሚገኝ ኤም. ኤ ሆቴል ኃ/የተ/የግ/ማ የተባለ ድርጅቱን ለ2ኛ የዐቃቤ ህግ ምስክር ለመሸጥ ፈልጎ ሆቴሉ ከሙስና ወንጀል ምርመራ ጋር በተያያዘ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የታገደ በመሆኑ ምክንያት እግዱ እንዲነሳ እናደርጋለን በማለት የግል ተበዳይ ገንዘብ እንዲከፍል ጠይቀዉት፣ የግል ተበዳይ በበኩሉ እግዱ በሌላ ክርክር በፍርድ ቤት የተነሳ በመሆኑ ለመክፈል ፈቃደኛ ሳይሆን የቀረ በመሆኑ፣ ተከሳሾች በጥቅም በመመሳጠር የተጠየቀዉን ገንዘብ እንዲከፍል በማስገደድና በማሳመን በአጠቃላይ የግል ተበዳይ በ3ኛ ተከሳሽ በኩል 7,800,000 ብር እንዲከፍል በማድረግ ብር በመቀበላቸው ሶስቱም ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተከፋይ በመሆን በፈፀሙት በስልጣን አላግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

በዚሁ የክስ መዝገብ በ1ኛ ተከሳሽ ተከሳሽ ላይ በቀረበ 2ኛ ክስ ተከሳሽ የተቀበለው ገንዘብ በወንጀል የተገኘ መሆኑን እያወቀ ገንዘቡን በራሱ ስም ቢቀበልና ገቢ ቢደርግ ወንጀሉ ሊደረስበትና የህግ ተጠያቂነት እንደሚመጣበት በማሰብ በወንጀል ድርጊት ያገኘውን ገንዘብ ህገወጥ ምንጩን፣ ዝውውሩን ወይም የባለቤትነት መብቱን የደበቀ ወይም እንዳይታወቅ ያደረገ በመሆኑ በፈፀመው በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል፡፡
ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ተከሳሽ ቀርቦ ያቀረበውን የዋስትና ጥያቄ እና የዐቃቤ ሕግን ተቃውሞ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒሰቴር የሙስና ወንጀልን ከመከላከል አንጻረ በተቋም ደረጃ ከውስጥ በመጀመር በሰራተኞች ላይ የሚስተዋልን የስነ-ምግባር ጉድለት ለመለየት የሚያስችል ጥናት ከማጥናት ጀምሮ በተለያዩ ደረጃዎች የሙስና ወንጀል ተሳትፎ ስለማድረጋቸው ጥቆማ በቀረበባቸው ዐቃቤያነ ሕግ እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኛ ላይ ተገቢውን የወንጀል ምርመራ እና ከሶ የማስቀጣት ስራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ይህንኑ እርምጃ በተለያዩ ተቋማት የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ላይም ሲወስድ እንደነበረም ይታወሳል፡፡
ይህ እርምጃም የሙስና ወንጀል መከላከል ሥራ አካል ሲሆን ማህበረሰቡም በፍትሕ ሚኒስቴርም ሆነ በሌሎች የመንግስት ተቋማት የሙስና ወንጀል ተግባራት መፈጸማቸዉን ያወቀ እንደሆነ ለፖሊስ ተቋማት ወይም ለፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ጥቆማ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተቋማቱ ጥቆማውን በሚስጥር በመያዝ ተገቢውን የማጣራት ስራ ሰርተው ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
ሳፋሪኮም በአዲስ አበባ የቴሌኮም አገልግሎት በይፋ አስጀመረ
****
👇👇👇👇👇👇👇👇
(ኢ ፕ ድ )

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የቴሌኮም አገልግሎቱን በይፋ አሰጀምሯል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሳኡሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፣  ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የቴሌኮም ኩባንያ በርካታ ቅድመ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ሳፋሪኮም ትልቅ ሚና ይኖረዋል ያሉት ስራ አስፈጻሚው፣ ከባለድርሻ አካላትና ከክልሎች ጋር በጋራ በመስራት በሁሉም ቦታ ተደራሽ ለመሆን እንሰራለን ብለዋል።

ሳፋሪኮም ለደረሰበት ደረጃ የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮ ቴሌኮም እገዛ ትልቅ መሆኑን በመግልጽ አመስግነዋል። 

ኩባንያው ባለፉት ሳምንታት በድሬዳዋ፣ በባህርዳር፣ በአወዳይ፣ ጎንደር ፣ሞጆ፣ ሐረር፣ አዳማ፣ ሀረር፣ ቢሾፍቱና ደብረ ብርሃን የኔትዎርክ ሙከራ አገልግሎቱን መጀመሩ ይታወሳል።

በሞገስ ፀጋዬ
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን
https://t.me/lawsocieties
የጋብቻ ውል (አጫጭር የምልከታ ነጥቦች)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የጋብቻ ውል(Contract of marriage ) ማለት ምን ማለት ነው? ከጋብቻ ምስክር ወረቀት(Certificate of marriage) በምን ይለያል?
ጋብቻ የሁሉም መሠረት እንደመሆኑ በኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕገ መንግሥት(constitution) እና ሌሎች ህጎች ሳይቀር ጥበቃ የተሰጠው ትልቅ ማኅበራዊ ተቋም(institution) ነው፡፡ የጋብቻ ውል(contract of marriage) ማለት ከጠቅላላው ውል ሕግ(Law of contract) ተነስተን ትርጉም የምንሰጠው አይደለም፡፡ ጋብቻ የሚፈጸመው መሃል ላይ የተለያዩ አጋጣሚዎች እንደተጠበቁ ሆነው እስከ ዕለተ ሞት ድረስ በአንድ ጣራ ስር አብሮ ለመኖር ነው፡፡ በዚሁ መሠረት የጋብቻ ውል የሚባለውም ተጋቢዎች ጋብቻቸውን በፈጸሙበት ዕለት ወይም ቀደም ብለው ጋብቻቸው እና አጠቃላይ ጋብቻቸው የሚያስከትለውን ውጤት ወስነው የሚያልፉበት ትልቅ ሰነድ ነው፡፡ በተሻሻለው የፌዴራል መንግስት የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 42 (1) ላይ የተመለከተውም ይሄንኑ ነው፡፡

የጋብቻ ውል ጥቅም ምንድን ነው?
ምናልባት ተጋቢዎች ትኩስ ፍቅር ላይ ሆነው ወደፊት ጸብ ሊኖር እንደሚችል አይገመቱም፡፡ ፍቅር እንዳለ ጸብም አለ፡፡ እነዚህ የማይነጣጠሉ ክስተቶች ናቸው፡፡ ከዚህ በመነሣት ተጋቢዎች ንብረታቸውን በሚመለከት (የግሉን በግል፣የጋራውን በጋራ) አድርገው የሚወስኑት በዚሁ የጋብቻ ውል ስለሆነ አለመግባባት ተከስቶ የንብረት ይገባኛል ጥያቄ እና ሙግት በሚነሣበት ወቅት ማስረጃነቱ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ አንዳንድ የፍርድ ቤት ጉዳዮችን ስንመለከት ይህን ባለማድረግ የሚከሰቱ ጉዳዮችም ያጋጥማሉ፡፡ ተጋቢዎች ከጋብቻ በፊት የንብረታቸውን ሁኔታ ወስነው ካላለፉ ለወደፊት ለትዳራቸው አለመስማማት እና ለፍቺ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል በመገንዘብ ቀድመው ሊያስቡበት የሚገባ ትልቅ ጉዳይ ነው፡፡
በፍርድ ቤቶች የሚታየው ክርክርም ቢሆን ባልና ሚስት የንብረታቸውን ጉዳይ የግል ንብረቶችን በግል፣የጋራውን ደግሞ በጋራ በየፈርጁ ለይተው ባለማስቀመጣቸው ምክንያት የንብረት ባለቤትነት የሚያሣጣ ባይሆንም ንብረት ያላፈራው ሰው ተጋሪ ሲሆን የምንመለከትበት ሁኔታ ያጋጥማል፡፡

በጋብቻ ውል የንብረታቸውን ጉዳይ ሳይወስኑ የተቀመጡ ተጋቢዎች ዕጣ ፈንታ ምንድንነው?
ተጋቢዎች ቢዘገይ በጋብቻቸው ዕለት ወይም ደግሞ ቀድም ብለው የንብረታቸውን ጉዳይ ወስነው ካላለፉ በትዳር ውስጥ ሆነው የንብረት ማግለል ውል ማድረግ ይችላሉ፡፡ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 73 መሠረት ውላቸውን ፍርድ ቤት አቅርበው ሊያጸድቁ ይገባል፡፡ በትዳር ውስጥ የሚደረጉ ውሎችን ፍርድ ቤት ሊያጸድቃቸው ይገባል፡፡ (ንብረት ማግለል፣ስጦታ፣ሽያጭ፣………) ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ተጋቢዎች በመካከላቸው የሚያደርጓቸውን ውሎች ውልና ማስረጃ በመውሰድ ተመዝግቦ እንዲረጋገጥላቸው ሲጠይቁ ይስተዋላል፡፡ ውልና ማስረጃም የዚህን ዓይነት የውል ስምምነት የመዘገበበት ሁኔታ ተስተውሏል፡፡ በዚህ ላይ ማረጋገጥ እና ማፅደቅ (authentication and ratification) የሚሉትን ነጥቦች መለየት ያስፈልጋል፡፡

ከጋብቻ የምስክር ወረቀት ጋር ልዩነቱ ምንድን ነው?
የጋብቻ ምስክር ወረቀት(certificate of marriage) ምን ማለት እንደሆነ ከመግለጻችን በፊት በሀገራችን ያሉትን የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቶችን ማየት ያስፈልጋል፡፡ በሀገራችን ሦስት ዓይነዋና ዋና የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቶች አሉ (በባህል(Custom) ፣ በሃይማኖት(religion) እና በክብር መዝገብ ፊት(Civil status) የሚፈጸሙ የጋብቻ አፈጻጻም ሥርዓቶች ናቸው)፡፡ ጋብቻው የተፈጸመው በየትኛውም የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓት ቢሆንም ጋብቻን በሚመዘግበው አካል ፊት ቀርቦ መመዝገብ አለበት፡፡ ይህ ነው የጋብቻ ምስክር ወረቀት የሚባለው፡፡ የጋብቻ ምስክር ወረቀት ተጋቢዎች ባልና ሚስት መሆናቸውን የሚያሣይ ሰርቲፊኬት ነው፡፡ ይህም በተሻሻለው የፌዴራል መንግሥቱ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 28/3/ ላይ ተመልክቷል፡፡
አንዳንድ ተጋቢዎች የባልና ሚስት ማስረጃ በሚጠይቁ ግልጋሎት ላይ በሃይማኖት ተቋም የተሰጣቸውን የጋብቻ ምስክር ወረቀት ሲያቀርቡ ይስተዋላሉ፡፡ ምሳሌ፡ ውልና ማስረጃ ላይ ይህን መታዘብ ይቻላል፡፡ ይህ በሃይማኖት ተቋም የሚሰጥ የጋብቻ ምስክር ወረቀት ተጋቢዎች በሃይማኖታቸው መሠረት(ከሦስቱ የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓት በአንደኛው) ጋብቻ የፈጸሙ መሆኑን የሚያሣይ ነው እንጂ በሕጉ የተቀመጠው የጋብቻ ምስክር ወረቀት(certificate of marriage ) አይደለም፡፡
Source: Document Registration and Authentication Office

https://t.me/lawsocieties
#ዉሳኔ ካገኙ ጉዳዮች/ኬዞች መካከል

ሰላማዊት (ስሟ የተቀየረ) በአሶሳ ከተማ የሚገኝ ሟች እናቷ ትተውት ያለፉትና ከሌሎች 2ት ግለሰቦች ጋር የምትጋራዉ የውርስ ሃብት ነበራት፡፡ የውርስ ሃብቱ በግምት 2500 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ያረፈና ሶስት መኝታ ቤት ፣ አንድ መታጠቢያ/ሻወር ቤት እና አምስት ክፍል ሰርቪስ ቤቶች ያሉት አንድ ቪላ/መኖሪያ ቤት እምዲሁም በግምት 100 ካ.ሜ ላይ ያረፈ ሁለት የድርጅት ቤቶች ይገኙበታል፡፡ ይህ የሰላማዊትና የሌሎች 2 ግለሰቦች የጋር ውርስ የነበረዉን ንብረት ሰላማዊት እና 2ቱ ግለሰቦች ሟች ከሞቱ በኋላም በጋራ ሲጠቀሙበት ነበር፡፡ ነገር ግን 2ቱ ግለሰቦች ሴራ በመጠንሰስ የሰላማዊትን የወራሽነት መብት ይጥሳሉ፡፡ እነኝህ ከሰላማዊት ጋር የሚጋሩ ሁለት ወራሾች የሰላማዊትን አለመማር እና በእነርሱ ላይ ያላትን ዕምነት ተጠቅመው ነበር ከውርስ ባለመብትነቷ በማታውቀው ሁኔታ እንድትገለል ያደረጓት፡፡
ይህን ጊዜ ነበር ሰላማዊት ጉዳዩን ወደ ኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር አሶሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ይዛ በመቅረብ የህግ ድጋፍ እንዲደረግላት የጠየቀችው፡፡ የማህበሩ አሶሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትም ጠበቃ በመመደብ ጉዳዩ ውሳኔ እስካገኘበት ድረስ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በመጨረሻም ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የውርስ ሃብት ከሆነው የመኖሪያ ቤት ውስጥ ድርሻዋ ከ2ቱ ግለሰቦች/ተከሳሾች እኩል ተሰልቶ እንዲሰጣት እንዲሁም ከንግድ ድርጅቶቹ በኪራይ ከሚገኘዉ ገቢ ዉስጥ ብር 925,800 (ዘጠኝ መቶ ሃያ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ብር) 2ቱ ግለሰቦች/ተከሳሾች ለሰላማዊት እንዲከፍሏት ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
ኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር
https://t.me/lawsocieties
#Humanitarian #intervention
Humanitarian intervention is a right to use force ‘exceptionally, to avert overwhelming humanitarian catastrophe’. It envisaged the use of massive military force in a foreign State for the protection of the citizens of that State.
Opinion on the legality of that intervention was divided. Some pointed out that there is no hint of any right of humanitarian intervention in the UN Charter, and urged caution in slackening the constraints upon the unilateral use of force in international relations.
Others took the view that if the UN was unable to act in the face of outrages such as the 1995 Srebrenica Massacre and the continuing ‘ethnic cleansing’ in the Balkans, there may come a point where moral imperatives eclipse the lack of any legal foundation for unilateral intervention.
A point at which neighboring States can no longer sit by and watch the calculated slaughter of thousands of civilians, but must act in the name of elementary imperatives of humanity........👇👇👇👇👇👇
አለሕግAleHig ️
#Humanitarian #intervention Humanitarian intervention is a right to use force ‘exceptionally, to avert overwhelming humanitarian catastrophe’. It envisaged the use of massive military force in a foreign State for the protection of the citizens of that State.…
Continued...... 👆👆👆👆👆
The UK claimed to be acting on the basis of this right when it used military force in Kosovo in 1999. No such right was clearly established by State practice. States could give non-discriminatory humanitarian relief, dropping blankets and food parcels to those in need. States had also often acted to protect and rescue their own nationals abroad. But the very limited nature of the threat or use of force in those contexts is better viewed as being primarily a (defensible) infringement on the duty of non-intervention in the internal affairs of other States.
NATO States took the view that where there is an imminent humanitarian catastrophe which can be averted by the use of force and only by the use of force, and where there has been a prior determination by the Security Council of a grave crisis threatening international peace and security and an articulation by the Council of policies for the resolution of the crisis, States acting collectively through a body such as NATO are justified in intervening with the use of force even in the absence of Security Council authorization.
An argument might be made out for the view that the law should leave matters as they are, and tolerate but not condone interventions of this kind, leaving them resting on a moral rather than a legal justification.
#Global study and international Relations classical lecture
Enjoy Ethiopian 🇪🇹 coffee with butter!
https://t.me/lawsocieties
War Crime
War crime is grave breaches of the Geneva Conventions of and other serious violations of the laws and customs applicable in armed conflicts.
A war crime constitutes egregious violations of IHL & trigger individual responsibility.
States are obliged ‘to respect and ensure respect’ for the Geneva Conventions, and the inculcation of their principles is (or at least should be) a basic part of the training of all members of the armed forces.
Breaches of the laws of war are serious offences, punishable by law.
Many options exist for the prosecution of war and other international crimes: national courts, foreign courts, ad hoc tribunals, & the International Criminal Court (ICC).
International Criminal Court (ICC)
The ICC is an international tribunal established by the 1998 Rome Statute and began functioning on 1 July 2002 that sits in The Hague in the Netherlands.
The ICC has the jurisdiction to prosecute individuals for the international crimes of genocide, crimes against humanity, and war crimes.
The ICC is intended to complement existing national judicial systems and it may therefore only exercise its jurisdiction when national courts are unwilling or unable to prosecute criminals or when the UN Security Council or individual states refer investigations to the Court.
The ICC was designed to supplement rather than replace national jurisdiction over war crimes.
https://t.me/lawsocieties