አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Names of books that brought to Exam hall

2021/2022 ACADEMIC YEAR


PART I: PRIVATE LAWS

THIS IS A CLOSED BOOK EXAM EXCEPT PERTINENT ETHIOPIAN LAWS.

Part Ii: public Laws

Laws that can be brought to the exam room are
The UN Charter,
The Vienna Convention on the Law of Treaties,
The FDRE Constitution,
The Criminal Code,
The Income Tax Proclamation,
The VAT Proclamation,
The Environmental Pollution Control Proclamation, And
The EIA Proclamation.

Part III: Procedural Laws

A closed book exam for all materials except clean copies of
the Civil Procedure Code,
the Criminal Procedure Code
the Criminal Code,
the Federal Courts Establishment Proclamation, and
Corruption Crime Proclamations (substantive and procedural)
Which cannot be lent to nor borrowed from other students.

Part IV: Miscellaneous Law Courses

It is a closed book examination.

Via @Lawsocieties Ale_Hig አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties
አንድ የመንግሥት ሠራተኛን በኃላፊ በተፃፈ ደብዳቤ ብቻ ከሥራ ማሰናበት ሕገ መንግሥታዊ ነውን?

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 37(1) መሰረት ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት ሕገ መንግሥታዊ መብት ያለው ስለመሆኑ ተደንግጓል። በተጨማሪም በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 42 ስር ለሠራተኞች የተደነገጉ በርካታ መብቶች አሉ። በተለይም ከዚህ የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ አርዕስት መረዳት አንደሚቻለው ሠራተኞች በሕገ መንግሥቱ የተጠበቀላቸው የሥራ ዋስትና መብት ያላቸው መሆኑን መረዳት ይቻላል። በሕገ መንግሥቱ ለሠራተኞች የተጠበቀው የሥራ ዋስትና መብት ከሚከበርበት መንገድ ውስጥ አንዱ ሠራተኞች በሕግ አግባብ ከተቀመጠው ሂደት እና አሠራር ውጪ ከሥራቸው መባረር የሌለባቸው መሆኑ ነው። ሠራተኞች በሥራ ቦታ ለሚያጠፉት ጥፋት በሕግ አግባብ በተቀመጠው የዲስፕሊን ሂደት የመዳኘት መብት አላቸው። ይህ መብት ከላይ በተጠቀሰው የሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 37(1) መሰረት የሚተገበር ነው።
በዚህ ድንጋጌ መሰረት በተለይም የመንግሥት ሠራተኞች በዲስፕሊን ጥፋት ከሥራ የሚሰናበቱት ጉዳያቸውን ለማየት እና ፍርድ ወይም ውሳኔ ለመስጠት በሕግ ስልጣን ባለው አካል ብቻ ነው። በሕግ በግልፅ ከተደነገገው አግባብ ውጪ አንድ የመንግሥት ሠራተኛ ተገቢውን ክርክር ሳያደርግ፤ ያለውን ማስረጃ በማቅረብ እራሱን ሳይከላከል አንዲሁም ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ላለው አካል ይግባኝ አቅርቦ ሳይከራካር ከሥራ ሊሰናበት አይችልም።.......ይቀጥላል 👇👇👇👇👇
የቀጠለ.......👆👆👆👆👆👆👆👆👆
አንድ ሠራተኛ ጥፋት ሲያጠፋ ተገቢው ክስ ቀርቦበት በቀረበበት ክስ ላይ ሠራተኛው መልስ ሰጥቶ የመከራከር፣ ማስረጃ የማቅረብ እና የመከላከል መብቱ ሊከበርለት ይገባል።
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 9(1) መሰረት ማንኛውም ሕግ፣ ልማዳዊ አሠራር፣ አንዲሁም የመንግሥት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ሕገ መንግሥቱን የሚቃረን ሆኖ ሲገኝ ተፈፃሚነት አንዳይኖረው በሕገ መንግሥት ትርጉም ስርዓት ውድቅ ይደረጋል።
የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 84 እና 9(1) ጣምራ ንባብ መሰረት ማንቸውንም ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን የማጣራት ስልጣን አለው። በሚያደርገው ማጣራትም ማናቸውንም ሕግ፣ ልማዳዊ አሠራር፣ የባለስልጣን ወይም የመንግሥት አካል ውሳኔ የሕገ መንግሥቱን ድንጋጌ የሚጥስ ሆኖ ከተገኘ ተፈፃሚነት እንዳይኖረው የውሳኔ ሃሳቡን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀርባል። ምክር ቤቱም የጉባዔውን የውሳኔ ሃሳብ ተቀብሎ ካፀደቀው ውሳኔው የመጨረሻ ይሆናል።
በዚሁ መሰረት ቀጥለን የምናየው ጉዳይ አስፈፃሚ የመንግሥት አካል የሆነው የአዲስ አበባ ከተማ የክ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት የአንድን መምህር የዲስፕሊን ጉዳይ አስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ ኢ-ሕገ መንግሥታዊነትን ነው።
አመልካች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኝ የአንድ ትምህርት ቤት መምህር ናቸው። እኝህ በአዲስ አበባ ከተማ በመምህርነት የሚያገለግሉ አመልካች በትምህርት ቤቱ ያሉ መምህራንን በማስተባበር የሥራ ማቆም አድማ አንዲደረግ አድርገዋል እንዲሁም የመማር ማስተማሩን ሥራ አስተጓጉለዋል በሚል በክ/ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ ደብዳቤ ከሥራ እንዲሰናበቱ ተደርጓል። አመልካች ይህን የክ/ከተማውን ፅ/ቤት ውሳኔ ለማሻር የይግባኝ ቅሬታ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት ሬጅስትራር ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን አልተቀበላቸውም። ቀጥሎም አመልካች አቤቱታቸውን ለሌሎች የተለያዩ የመንግሥት አካላት ቢያቀርቡም የሚቀበላቸው እና መፍትሄ የሚሰጣቸው አካል አላገኙም።
በመጨረሻም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን ለማጣራት ስልጣን ለተሰጠው የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በአስተዳደር አካሉ ውሳኔ ላይ የሕገ መንግሥት ትርጉም አንዲሰጣቸው አመልክተዋል።
ጉባዔውም ጉዳዩን ለማጣራት ያመች ዘንድ አመልካች በወቅቱ ለአዲስ አበባ ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት ሬጅስትራር የይግባኝ ማመልካቻ ማቅረብ አለማቅረባቸውን እና አንድ ጉዳይ በዲስፕሊን ኮሚቴ ሳይታይ በሥራ ኃላፊ ደብዳቤ ብቻ የተሰናበተ ከሆነ ለሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ እና መዝገብ ማስከፍት ይችላል ወይ የሚለውን አጣርቷል። ፍርድ ቤቱ በሰጠው ምላሽ በወቅቱ የነበረው ሬጅስትራር የለቀቀ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ምላሽ መስጠት የማይቻል መሆኑን ጠቅሷል። በሌላ በኩል አንድ ጉዳይ በዲስፕሊን ኮሚቴ ሳይታይ በሥራ ኃላፊ በተፃፈ ደብዳቤ ከሥራ ቢሰናበት በዚሁ ደብዳቤ መነሻነት የይግባኝ መዝገብ መክፈት የሚቻል መሆኑን በመግለፅ መልስ ሰጥቷል።
አመልካች የስንብት ደብዳቤ በተሰጣቸው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የይግባኝ ማመልከቻ ለአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት አቅርበው የነበረ መሆኑን ለጉባዔው ካቀረቡት ማስረጃ መረዳት ይቻላል። በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት የአመልካችን ጉዳይ ተቀብሎ ማስተናገድ ሲገባው “አንቀበልም’’ ማለቱ አመልካች በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 37(1) የተረጋገጠላቸውን ፍትህ የማግኘት መብታቸው መጣሱን ያረጋግጣል።
የአመልካች ዓይነት የይግባኝ አቤቱታን የመቀበል፣ የመመርመር እና ፍርድ ወይም ውሳኔ የመስጠት ሕጋዊ ግዴታ የተጣለው በአዲስ አበባ ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት ላይ ነው። ነገር ግን ፍርድ ቤቱ በሕግ በተሰጠው የዳኝነት ስልጣን መሰረት የአመልካችን አቤቱታ በመቀበል ተገቢውን ማጣራት እና ክርክር በማድረግ ውሳኔ ወይም ፍርድ መስጠት ነበረበት። የአዲስ አበባ ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት ይህን ኃላፊነቱን ባለመወጣት እና የአመልካችን አቤቱታ ተቀብለው ባለማስተናገዳቸው አመልካች ማግኘት የነበረባቸውን ፍትህ ሊያገኙ አልቻሉም።
ጉባዔው ጉዳዩን ካጣራ በኋላ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት የአመልካችን ጉዳይ ተቀብሎ ማስተናገድ ሲገባው አንቀበልም ማለቱ በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 37(1) ስር የተደነገገውን ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብቱን የሚጥስ ነው በማለት፣ አመልካች በፅ/ቤቱ ኃላፊ ደብዳቤ ብቻ የተላለፈባቸው የሥራ ስንብት ውሳኔ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ነው በማለት የሕገ መንግሥት ትርጉም እንደሚያስፈልገው የውሳኔ ሃሳቡን አሳልፏል።
ስለሆነም አመልካች ጉዳያቸውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት የማቅረብ መብት አላቸው በማለት ጉባዔው የውሳኔ ሃሳቡን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተላልፏል። ምክር ቤቱም የአጣሪ ጉባዔውን የውሳኔ ሃሳብ በመቀበል በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጥቷል።
በያደታ ግዛው
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#የአላባ ጥቅም ውል

የአላባ መብት ማለት የሚጠቀሙበትን ነገር ከመጠበቅ ግዴታ ጋር ከዚሁ ነገር ላይ በሚገኙት ነገሮች (ፍሬዎች) ወይም መብቶች ለመጠቀምና ለመገልገል የሚሰጥ መብት ነው፡፡

ይህም መብት የሚንቀሳቀሱና በማንቀሳቀሱ ንብረቶች መብቶች ወይም በአንድ ጠቅላላ ንብረት ላይ ሊሆን የሚችል ነው:: በማለት በፍትሐ ብሔር ህግ አንቀጽ 1309 (1) እና (2) ላይ ተቀምጧል፡፡

በመሆኑም ተገልጋዮች የአላባ ጥቅም ውልን ለመዋዋል ወደመስሪያ ቤታችን ሲመጡ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡

. በህግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣

. ተዋዋይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጫ ሰነድ፣

. የንብረት ባለቤትነት ማስረጃ፣

. በማንኛውም መልኩ ንብረቱ ከእዳና እገዳ ነጻ መሆኑን ማረጋገጥ፣

የአላባ ውሉ የሚደረገው በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ከሆነ የሁለት ምስክሮቻዉና የታደሰ መታወቂያ፣

. የአላባ ሰጪ እና ተቀባይ የታደሰ መታወቂያ፣

. የአላባ ሰጪው ያገባ ወይም ያላገባ ከሆነ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት /ውክልና፣

. የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ የንግድ ዋና ምዝገባ እና እንደአስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባኤ፡፡
via DARA
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ በግል ስልካቸው ላይ ከተከሳሽ ቤተሰብ በተላከላቸው መልክት ምክንያት እራሳቸውን ከዳኝነት አነሱ።

ዳኛው በፌደራል የዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁ.1233/2013 መሰረት ነጻና ገለልተኝነታቸውን ለማረጋገጥ ሲሉ ነው ከሚመለከቱት መዝገብ ዳኝነታቸውን በራሳቸው ፍቃድ ያነሱት።

ለፍርድ ከተቀጠረ የሙስና ወንጀል መዝገብ እራሳቸውን ከዳኝነት ያነሱት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የ1ኛ ሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ ናቸው።

የችሎቱ ዳኛ ከሁለት ወር በፊት በሙስና ወንጀል ክስ የቀረበባቸውን የቀድሞ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች 1ኛ ተከሳሽ አዱኛ ነጋሳ ፣ 2ኛ ተከሳሽ አክሊሉ ዘሪሁንን ፣ 3ኛ ረቂቅ ዜናዊ ፣ 4ኛ ተከሳሽ ረቡማ በለጠ እንዲሁም ከዚህ በፊት በዋስ ወጥተው በውጪ ጉዳያቸውን የሚከታተሉት 5 ኛ ተከሳሽ ቶፊቅ ሙላት ፣ 6ኛ ተከሳሽ የከፍተኛው ፍ/ቤት ሬጅስትራር ስሜነህ አለሙና እና 7ኛ ቸከሳሽ የቦሌ
ክ/ከ ወረዳ 6 የኗሪዎች መረጃና ማስረጃ አገልግሎት ባለሙያ ከድር ዱንዲን መዝገብ ሲመለከቱ መቆየታቸው ይታወሳል።

ተከሳሾቹ በህዳር 28 ቀን 2014 ዓ/ም በዓቃቤ ህግ በቀረበባቸው ክስ ላይ የአቶ ዳዊት ገ/እግዛብሔር የሆነ በስራ ግንኙነት ሳይከፈል የቀረ የ276 ሚሊዮን ብር እና 9 ከመቶ ወለድ ክፍያ ብር በጥቅም በመመሳጠር በጥቅምት 10 ቀን በ2009 ዓ/ም ቱፋ ጣፋ በሚባል በሀሰተኛ ስም በተከፈተ መዝገብ አንደኛ ተከሳሽ በሚመለከቱት 11ኛ የአፈጻጻም ችሎት ክርክር ሳይደረግ ያልተገባ ውሳኔ በመስጠት ከ4ኛ ተከሳሽ ረቡማ በለጠ የ3ሚሊዮን ብር ጉቦ እና የ2 ሚሊዮን ብር ቼክ በመቀበል በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የሚገኝ የዳዊት ገ/እግዛብሔር ሒሳብ የነበረ 276 ሚሊዮን ብር ወደ ቡና ባንክ ገቢ እንዲሆን ያልተገባ ትዛዝ ሰጥተዋል ተብለው በዓቃቤ ህግ በየተሳትፎ ደረጃ ተጠቅሶ በሙስና ክስ መከሰሳቸው ይታወሳል።

ተከሳሾቹ ክሱ ከደረሳቸው በኋላ ክሱን አለመፈጸማቸውን ገልጸው የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ለችሎቱ አስመዝግበዋል።

ከሳሽ ዓቃቤ ህግም የሰው ምስክር ችሎት አቅርቦ በየደረጃው አሰምቷል።

የችሎቱ ዳኞች የተሰማውን የምስክር ቃል ተገልብጦ መርምረው ፍርድ ለመስጠት ለዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተው ነበር።

ሆኖም ሰብሳቢ ዳኛው የግል ስልካቸው ላይ በሚያውቋቸው የ4ኛ ተከሳሽ ዘመድ ረቡማ ለተባለ ለ4ኛ ተከሳሽ ድጋፍ እንዲያደርጉ መልክት መላኩንና ቤተሰብ ላይ ጫና እንደተደረገባቸው በችሎት ይፋ አድርገዋል።

ዳኞች የዳኝነት ስራቸውን ከማንኛውም ውስጣዊና ውጪያዊ ተፅኖ ነጻ ሆነው በገለልተኝነትና በተጠያቂነት መንፈስ ማከናወን ያለባቸው መሆኑ መደንገጉን ሰብሳቢ ዳኛው ጠቅሰዋል።

በዚህ በፌደራል የዳኞች አስተዳደር አዋጅ ቁ. 1233/2013 ድንጋጌ መሰረት በግል ስልኬ የተላከው መልክት ነጻ ሆኜ ትክክለኛ ፍትህ መስጠት ስለማያስችለኝ እራሴን ከመዝገቡ አስቻለው ሲሉ ከመዝገቡ ዳኝነት መነሳታቸውን በችሎት ይፋ አድርገዋል።

15/10/2014

ሕግ አገልግሎት/Legal Service እንደዘገበዉ
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀል፣ የሕግ ማዕቀፋ እና አተገባበሩ

ይህ ጽሑፍ ከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀል በኢትዮጵያ ያስዳስሰናል።

ጸሐፊው፦ ገብረእግዚአብሔር ወልደገብርኤል

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2031-fraudulent-misrepresentation-under-corruption-laws-in-ethiopia
በፍርድ ቤት 'የራስ አነሳሽነት' የሚሰጥ ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ እና የመሰማት መብት
#አብርሃም ዮሐንስ

በወንጀል ጉዳይ በተለይ ደሞ በፍትሐብሔር ክርክር ወቅት ፍርድ ቤት በራሱ አነሳሽነት ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ የመስጠት ሰፊ ስልጣን አለው። ጥቂት ምሳሌ መጥቀስ ቢያስፈልግ አቤቱታ እንዲሻሻል: ተጨማሪ ማስረጃ እንዲቀርብ ትዕዛዝ መስጠት፤ የስረ-ነገር ስልጣኑ ላይ ብይን መስጠት እንዲሁም የመብት መቅረት በጊዜ ገደብ ሲወሰን በመብቱ አለመኖር ላይ ውሳኔ መስጠት /ለምሳሌ አሰሪው የሚከራከርበት የስንብት ምክንያት ድርጊቱ መፈፀሙን አሰሪው ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ ሲታሰብ አንድ ወር ካለፈው/ የአሰሪው የማሰናበት መብት ቀሪ ይሆናል። ይህ ከይርጋ የተለየ እንደመሆኑ በፍርድ ቤቱ በራሱ ሊነሳ ይችላል። ከጊዜ ገደብ ጋር በተያያዘ የሰ/መ/ቁ 17361 ቅፅ 10 ይመለከቷል/

የራስ አነሳሸነት ለፍርድ ቤቱ አስገዳጅ ነው ወይስ 'የእንደፈቀደ' /discretionary/ ስልጣን የሚለው ጥያቄ መሰረታዊና አከራካሪ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሌላ ይበልጥ መሰረታዊ ጉዳይ ጥያቄ ሆኖ ሲነሳ አይታይም።

በራስ አነሳሽነት የሚሰጥ ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ መሰረታዊና እና ህገ-መንግስታዊ ከሆነው የመሰማት መብት አንጻር አሉታዊ እንደምታው በሚገባ አልተፈተሸም።

በምሳሌነት የስረ-ነገር ስልጣንን እንመልከት።
በተግባር እንደሚታየው ብሎም በስነ-ስርዓት ህጉ እና በሰበር ትርጉም ጭምር ድጋፍ ያገኘው አቋም አንድ ፍርድ ቤት የሰረ-ስልጣን ከሌለው በተከራካሪ ወገኖች ባይነሳም በራሱ አነሳሽነት መዝገቡን መዝጋት ይኖርበታል።
ግን በራስ አነሳሽነት ሲባል ምን ማለት ነው? በራስ አነሳሽነት የሚያስገነዝበው ፍርድ ቤቱ ነጥቡን መጀመሪያ በክርክር ወቅት ማንሳት አለበት ማለት ነው። የሚያነሳው ደግሞ ለተከራካሪ ወገኖች ነው። በዚሁ መሰረት ተከራካሪ ወገኖች በተነሳው ነጥብ ላይ ያላቸውን የህግ ክርክር ብሎም ማስረጃ ማቅረብ ወይም ማሰማት አስፈላጊ ከሆነ ማስረጃቸውን ሊያሰሙ ይገባል። የመሰማት መብት በግራ ቀኙ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ፍርድ የሚያነሳውንም ነጥብ ይጨምራል።

በራስ አነሳሽነት ማለት ተከራካሪ ወገኖች ሳያውቁትና ሳይሰሙ በድንገት እና በድብቅ የሚሰጥ ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ ማለት አይደለም። ፍርድ ቤት የስረ-ነገር ስልጣኑን የሚወስነው በግምት ሳይሆን በተረጋገጡ አግባብነት ያላቸው ፍሬ ነገሮችና በህጉ ትርጓሜ ላይ በመመስረት ነው። በፍሬ ነገር /ማስረጃ/ እና የህግ ትርጉም በሚመለከት ጉዳይ ተከራካሪ ወገኖች የመሰማት መብት አላቸው።

ነገሩን እንደሚከተለው እንመልከተው።
የስረ-ነገር ስልጣን መቃወሚያ በተከራካሪ ከተነሳ ተቃራኒው ወገን የመሰማት መብት ካለው ፍርድ ቤት ስላነሳው ብቻ ይህን መብቱን የሚያጣበት አንዳችም የህግ መሰረት የለም።
በተጨማሪም ተካራካሪዎችን ያላሳተፈ 'የራስ አነሳሽነት' ለስህተት የመጋለጡ ዕድል በጣም ሰፊ ነው።

እንበልና በመኪና አደጋ የተነሳ ከውል ውጭ ሀላፊነት ክስ ሲቀርብ ተከሳሽ በመልሱ ላይ የጠቀሰው አድራሻ ተከራካሪዎች የተለያየ ክልል ነዋሪዎች መሆናቸውን ይጠቁማል። ሆኖም ተከሳሽ የጠቀሰው ቤተሰቡ የሚኖርበትን አድራሻ እንጂ መደበኛ የንግድ ስራውን የሚያከናውነውና አብዛኛውን ጊዜ የሚኖረው አደጋው በደረሰበት ክልል ነው። ተከሳሽ የስረ-ነገር ስልጣን አላነሳም። ከሳሽም በዚህ ነጥብ ላይ ማስተባበያ አላቀርበም። ካሁን አሁን ፍርድ ቤት በራሱ አነሳሽነት የስረ-ነገር ስልጣኑን በዚህ ላይ ተመስርቶ ብይን ሊሰጥ ይችላል በሚል ስሌት ማስተባበያ እንዲያቀርብም አይጠበቅበትም። ፍርድ ቤት በራሱ የሚያነሳቸው ነጥቦች በርካታ እንደመሆናቸው የትኛውም የህግ ባለሞያ ሁሉንም ከወዲሁ ሊያውቃቸው ሆነ ሊገምታቸው አይችልም።

ፍርድ ቤት በራስ አነሳሽነት የስረ-ነገር ስልጣኑን የመወሰን ሀሳብ ካለው ማድረግ ያለበት ተከራካሪ ወገኖች የተለያየ ክልል ነዋሪዎች መሆናቸውን እንደ ምክንያት ይዞ በራሱ ጊዜ መዝገቡ መዝጋት አይደለም። መጀመሪያ ከስልጣን ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤቱ የስረ-ነገር ስልጣኑን ለመወሰን የተከራካሪ ወገኖች አድራሻ መጣራት እንዳለበት ለተከራካሪ ወገኖች በመንገር በዚህ ረገድ የህግ ክርክር ካላቸው በተጨማሪም ክርከራቸውን የሚደግፍ ማስረጃ ካላቸው እንዲያቀርቡ ዕድል መስጠት አለበት። ይህ ሲሆን ነው ተከሳሽ የንግድ ስራውና አብዛኛውን ጊዜ የሚኖረው አደጋው በደረሰበት ክልል መሆኑን ከሳሽ ማስተባበያ ማቅረብ የሚችለው። በተጨማሪም አንድ ሰው የንግድ እና የቤተሰብ መኖሪያ ስፍራው የተለያየ ከሆነ ለስረ-ነገር ስልጣን አወሳሰን የየትኛው ክልል ነዋሪ ነው? የሚለው የህግ ጭብጥ ግራ ቀኙ ሊከራከሩበት ይገባል።

በአጠቃላይ 'በራስ አነሳሽነት' ማለት ፍርድ ቤት በራሱ ጊዜ የሚያነሳው ሆኖም ባነሳው ነጥብ ላይ ግራ ቀኙ የመሰማት መብታቸው ተጠብቆ ከተከራከሩ በኋላ የሚሰጥ ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ ማለት እንጂ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ሳያውቁት ፍሬ ነገሩን በራሱ ገምቶ፣ የህጉን ትርጉም ለብቻው አውጥቶ አውርዶ መጨረሻ ላይ ድንገት የሚሰጠው ብይን/ትዕዛዝ/ውሳኔ ማለት አይደለም።
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ሰላም እንዴት ናችሁ፤

እኔ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ስፖንሰርነት የስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ከሚማሩ ሐኪሞች አንዱ ነኝ። በተለይም ካለፈው አመት ጀምሮ ከሌሎች መሰል ዩኒቨርሲቲዎች፣ ብሎም በጤና ሚኒስቴር ስፓንሰር ከሚማሩት ጓደኞቻችን ከ 2-3 ሺህ ብር ያነሰ ገንዘብ እየተከፈለን ለመማር ቀርቶ ለመኖር ተቸግረናል። በተደጋጋሚ ስንጠይቅ ይህን የኦዲት ግኝት ያሉትን እንደ ምክንያት ያቀርባሉ።
ያልተደነገገ ከሆነ ምንም ያክል ሊደረግ የሚገባው መሆኑን ብናምንም ለምን አልሰጡንም አንልም። ሌላ አንድም ዩኒቨርሲቲ ላይ አለመገኘቱ ፣ ዲላ ራሱ ለ 10 አመታት ስፖንሰር ሲያደርግ ያልተገኛ መሆኑ ግን ጥርጣሬን ፈጥሮብናል።

በሕጉ ዘርፍ አቅሙም እውቀቱም ስለሌለን ብታግዙን ብዬ ይህን ፅፊያለሁ።

ብሶቴን ከመዘርዘር የቻልኩትን ተቆጥቢያለሁ።

ለምላሻችሁ አመሰግናለሁ።
#fias777 አዲሱ የማጭበርበሪያ ዘዴ ልክ እንደ ቲያንስ ከ3 ሚሊዮን በላይ አባል ያለው ግማሹ :- መሬት ሽጦ ፣ባጃጁን ሽጦ፣ ከደሞዙ ቆጥቦ እቁብ እየጣለ አጠራቅሞ አተርፋለው ብሎ ተስፋ የደረገው website ከጥቅም ውጪ ሆኗል።
ከዚህ በፊት በኢትዮቼክ ተናግረው ነበር ህዝቤ ግን ብትነግረው ስላማይሰማ ይኸው ገንዘባቸውን ይዞ የውሀ ሽታዎች ሆነ ብለዋል።
ባለቤቶቹ የማይታወቁ ሲሆን መንግስትም ተጠንቀቁ ሲል ነበር ።
ይሄ ህዝብ ግን መቼ ነው የሚባንነው 😎😎
ከዘመኑ የረቀቀ ዘመናዊ ውንብድና እና ዘረፋ.... ተጠቀቁ።
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የኢትዮጵያ ብር እና የውጭ ሀገር ገንዘብን ይዞ መገኘት/ማዘዋወር ያለው የሕግ ተጠያቂነት

በ:-ገመቺስ ደምሴ

ሀገራችን የኢኮኖሚዋ መሠረት ሆኖ የሚያገለግልና ውስን የሀገር ሀብት በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ ለማዋል አስፈላጊ የሆኑ የቁጥጥር እርምጃዎችን ለመውሰድ ገንዘብ የሚያዝበትና የሚተዳደርበትን አግባብ በተመለከተ የተለያዩ ሕጎች ተደንግገው እናገኛለን፡፡ ይህንን ዓላማ ለማሳካት አስተዳደራዊና የወንጀል ተጠያቂነትን እንደማስፈፀሚያ መሳሪያ አድርጋ በተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች ውስጥ አካታ እየተገበረች በመሆኑ በቀጥታ ከወንጀል ጋር ያለውን ቁርኝት ጽሑፉ ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡

ጽሑፉ በቅድሚያ አጠቃላይ መንደርደሪያ ሀሳቦችን ለማንሳት የሚሞክር ሲሆን የገንዘብ ትርጉምን፣ የውጭ ምንዛሬ ምንነትንና ሊታዩ የሚገባቸውን የሕግ ማዕቀፎችን መነሻ አድርጎ ያትታል፡፡ በመቀጠልም የኢትዮጵያ እና የውጭ ሀገር ገንዘብን በጥሬ ገንዘብ ለመያዝና ለማዘዋወር የሚፈቀድባቸው አግባቦች ከተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች አንፃር ለማንሳት ይሞክሯል፡፡

የተለየ ትኩረትም ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ ሊታዩ የሚገቡ ነጥቦችን አንስቶ የሚሞግትና የሚያስገነዝብ አፃፃፍን ተከትሏል፡፡ ጽሑፉ በሕግ ከተቀመጠው አግባብ ውጭ ገንዘብ መያዝና ማስተላለፍ የሚያስከትለውን የወንጀል ተጠያቂነትን አጉልቶ በማንሳት የሚስተዋሉ የአረዳድና የአተረጓጎም ክፍተቶችን ሽፋን ሰጥቶ ካነሳ በኋላ ሊያዝ የሚገባውን ተገቢ አረዳድና አተረጓጎማቸውን አንስቶ ይሞግታል፡፡ በመጨረሻም ጽሑፉ ማጠቃለያ ሃሳቦችን ጨምቆ ለማስቀመጥ ሞክሯል፡፡

Enjoy reading!

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2032-money-holding-limit-in-ethiopian-law
የፍርድ ቤቶች የጉዳይ መጓተት እና የተገልጋዩ ግንዛቤ
👆👆👆👆👆👆👆
ለፍርድ ቤቶች ትልቅ ፈተና እየሆነ የመጣዉ ከታች በአሚኮ እንደተዘገበዉ
የጉዳይ መጓተት የሚል ነዉ።
ባለጉዳዮች ለምን ብዙ ጊዜ እንቀጠራለን ሲሉ ይደመጣል።
አንድ መደበኛ ክርክር ሁሉም ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነዉ ቢሳካ

1ኛ / አቤቱታ ለማስገባት
2ኛ / መልስ ለመቀበል
3ኛ /ለክርክር
4ኛ /ለምስክር
5ኛ /ለዉሳኔ
6ኛ / የአፈጻጸም አቤቱታ ለማስገባት
7ኛ /ተከሳሽ ፈጽሞ ሲቀርብ ለመጠባበቅ እና በእለቱ ቢፈጸም እንኳ 7 ጊዜ
ይመላለሳሉ።

ይህን ስነ ስርዓት ደግሞ ዳኛዉ ሊቀይረዉ የማይችል አስቀድሞ
የተጻፈ እና ዳኛዉ ሊተገብረዉ እንጅ ሊቀይረዉ የማይገባ ስነ ስርዓት ነዉ።ለባለ
ጉዳዩ እንዲህ ቢሆንለት እና ፈጣን አገልግሎት አገኘህ? ተብሎ ቢጠየቅ!
በፋጹም ነዉ የሚሉት። ምክንያቱም በመጀመሪያዉ ቀጠሮ ተከሳሽ መልሱን
አስገብቶ ክርክር ተደርጎ ለምስክር እንዲጠራና፤ምስክር በተሰማ ጊዜ ዉሳኔ
እንዲወሰን ይፈልጋሉ። ይህ ደግሞ ሊሆን የማይችል እና ስነ ስርዓታዊ የሆነ
አካሄድ አይደለም።
ከዚህ አልፎ ደግሞ ከላይ ከተጠቀሱት የቀጠሮ ቀናት በላይ በእጥፍ ሊመላለሡ
የሚችሉበት አጋጣሚ አለ።
ለምሳሌ
=ተከሳሽ በመልስ ጊዜ ባይቀርብና ከሳሽ መጥሪያ ማድረሱን መተማመኛ
ባያቀርብ
=መልስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ቢያቀርብ በመቃወሚያዉ ላይ
ክርክር ቢደረግ
=በመቃወሚያዉ ላይ ምስክር መስማት ቢያስፈልግ
=በመቃወሚያዉ ላይ ብይን ለመስጠት
=ጉዳዩ በመቃወሚያዉ የማይዘጋ ሆኖ ወደ ፍሬ ነገር ቢገባ
=በፍሬ ነገር ላይ ክርክር ማድረግ
=ቀጥሎ ምስክር መስማት
=ምስክሮች በተቀጠሩበት ቀን ባይቀርቡ ወይም ባይሟሉ ተገደዉ እንዲቀርቡ
ለማዘዝ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥ
=የተለያዩ ጽ/ቤቶች ማስረጃ ባይልኩ ተገደዉ እንዲያቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ
ሲሰጥ
=ከክርክር ወይም ከምስክር ደርሶ የጣልቃ ገብ አቤቱታ ቢመጣ እና በዚሁ
ምክንያት እንደገና" ሀ" ብሎ ቢጀመር እስከ 16_20 ጊዜ በላይ ቀጠሮ ሊሰጥ
ይችላል።
=ከዚያም አልፎ በይግባኝ እሰከ ፌ /ሰበር ደርሶ ሲመለስ ዓመታት ሊፈጅ
ይችላል። ይህ ደግሞ በህጉ እና ፍርድ ቤቱ ሊቆጣጠራቸዉ በማይችሉ ጉዳዮች
የሚመጣ ችግር ነዉ። በማህበረሰባችን ቀን በቀን ወይይት ስናደርግ ይህን
የመረዳት ችግር አስተዉያለሁ።
ሌሎች ጉዳዮች
##########
ወደ ፍርድ ቤት የሚመጣዉ ባለጉዳይ እጅግ በጣም ብዙ በመሆኑ በተቀጠረዉ
አግባብ ለመስራት እጅግ አስቸጋሪ የሚሆንበት ጊዜ አለ።
# ዳኛዉ ሰዉ ነዉና ይታመማል፣ስብሰባ ይሄዳል ወዘተ ማህበራዊ ችግሮች
ያጋጥሙታል። ስለዚህ ተለዋጭ ቀጠሮዎች ይሰጣሉ
።።።።።
ስንፍና
*
አንዳንድ ዳኞች በዘፈቀደ የሚቀጥሩ ይኖራሉ፤ይህን እየለዩ ማረም ይጠይቃል።
ነገር ግን ሚዲያዎችም ሆነ ባለ ጉዳዮች ከላይ የተጠቀሱትን ልብ ሊሉ ይገባል
እላለሁ።
መንግስትም ለፍርድ ቤቶች በቂ አቅርቦት እና ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም
አማራጭ የግጭት መፍቻ አሰራሮችንና ተቋማትን በማቋቋም ችግሩ ማቃለል ይችላል።
ላስታ ወረዳ ፍርድ ቤት
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
በአሜሪካ ጽንስ የማቋረጥ ሕገ መንግሥታዊ መብት ተሻረ

የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍ/ቤት የጽንስ ማቋረጥን ጉዳይ ለየግዛቶቹ ሰጥቷል። ጽንስ የማቋረጥ ውሳኔን ከወሰነ በኋላ በርካቶች ድጋፍም ተቃውሞም እያሰሙ ነው።
https://am.al-ain.com/article/us-supreme-court-removed-american-women-s-constitutional-right-to-abortion
የእጅ ከፍንጅ ወንጀል በኢትዮጵያ ሕግ

👇👇👇👇👇👇👇👇
መግቢያ

ወንጀል የሰዉ ልጆች በህይወት ዘመናቸዉ ከሚያጋጥሟቸዉ ችግሮች መካከል አንዱ ነዉ::
ከብዙዎቹ ወንጀሎች መካከል አንዱ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ነዉ፡፡ ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረ ሰዉ በህግ አግባብ በፖሊስ የሚያዝ ሲሆን የሚያዘዉም በዋናነት በመያዣ በልዩ ሁኔታ ግን ያለመያዣ ነዉ፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርአት ህጉ መሠረት ፖሊስ ተጠርጣሪን ያለፍርድ ቤት መያዣ ትእዛዝ ሊይዝ እንደሚችል የሚያመለክቱት ድንጋጌዎች አንቀፅ 19፣20፣50 እና 51 ናቸው፡፡ ያለመያዣ ትእዛዝ መያዝ በፖሊስ ወይም በማንኛውም ሰው ሊፈፀም እንደሚችል የሥነ ሥርዓት ህጉ ያስቀምጣል፡፡
በዚህ መሠረት የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች ተፈፅመው ሲገኙ ፖሊስ ወይም ማንኛውም ሰው ተጠርጣሪውን መያዝ ይችላል፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ምንነትና በምርመራ ጊዜ ያለው ውጤት፣ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል በክስ ሂደት እና በፍርድ ሂደት ያላቸዉ እንድምታ የሚሉትን እንመለከታለን፡፡.....።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇ይቀጥላል
👆👆👆👆👆👆👆👆👆የቀጠለ

የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ምንነትና በምርመራ ጊዜ ያለው ውጤት

የእጅ ከፍንጅ ወንጀል የሚለው ቃል ትርጉም በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል የተዘጋጀዉ አማርኛ መዝገበ ቃላት አንድ ሰው ወንጀል በመፈፀም ላይ እንዳለ የመያዝ ሁኔታ ነዉ በማለት አስፍሮ ይገኛል፡፡ In flagrante delicto is a latin phrase defined as someone being caught during the act of crime...አንድ ሰው የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም ከተያዘ እጅ ከፍንጀ ወንጀል መሆኑን ይገልፃል፡ Black law dictionary እጅ ከፍንጅ ወንጀል ሲገልጽ፣Flagrant crimen-in Roman law a fresh or recent crime. This term designated the very act of its commission or while it was of recent occurrence. Flagrant delit –in French law a crime which is in actual process of perpetorration which has just been committed. ከነዚህ ሁለት ትርጉሞች የምንረዳዉ እጅ ከፍንጅ ወንጀል ማለት ወንጀሉ እየተፈጸመ ያለ ወይም እንደ ተፈጸመ ወዲያዉኑ ከሆነ ወይም ከተፈጸመበት ቅርብ ጊዜ እንደሆነ ይገልጻል:: በታይዋን ህግ መሰረት እጅ ከፍንጅ የሚባለዉ ወንጀሉን ሲፈጽም ከተያዘ ወይም እንደፈጸመ ወዲያዉኑ ከተያዘ በሚል ያስቀምጣል:: ከዚህም በተጨማሪ አንድ ሰዉ ከተሰረቀ ንብረት ጋር ከተገኘ ወይም ወንጀል ለመፈጸም ከሚያግዝ መሳርያ ጋር ከተያዘ ወይም ወንጀሉን ስለመፈጸሙ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ጋር ከተያዘ እጅ ከፍንጅ ወንጀል መሆኑን ይገልጻል::

የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ከተፈፀመ ከላይ ከተገለፁት የወንጀል አፈፃፀሞች በአንዱ ዓይነት ወንጀል ተፈፅሟል ማለት ነው:: የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች ከተፈፀሙ የወንጀል ምርመራ ይጀመራል:: በመቀጠልም ክስ እና ክርክር ይቀጥላል በመጨረሻ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡ ከዚህ በመቀጠል የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች አፈፃፀም በምርመራ ጊዜ፣ በክስ፣ በክርክር እና ውሳኔ ጊዜ ያለውን ሁኔታ ይገልፃል፡፡

አንድ ወንጀል በተፈፀመ ጊዜ ወንጀል አድራጊውን ለማወቅና ለፍርድ ለማቅረብ ምርመራ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ምርመራውም የሚጀመረው አግባብ ላለው አካል ይህ ድርጊት ሲገለፅ ነው፡፡ የወንጀል ምርመራ በሦስት መንገድ ሊጀመር ይችላል፡፡ አንደኛዉ ለሚመለከታው የፖሊስ አካል የሚቀርበው ጥቆማ ወንጀሉ በክስ (accusation) ከሆነ በማንኛው ሰው አማካይነት ሊሆን ይችላል:: ሁለተኛው መንገድ ደግሞ የግል ባህሪ ባላቸዉ ወንጀሎች ጉዳይ በግል ተበዳይ አቤቱታ ብቻ የወንጀል ምርመራ ይጀምራል፡፡ ሦስተኛዉ ፖሊስ በራሱ አነሳሽነት የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን ሲጠራጠር የሚጀምረዉ የምርመራ አይነት ነዉ:: የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች በምን ሁኔታ ምርመራ እንደሚጀመር ከመግለፅ አስቀድመን የእጅ ከፍንጅ ወንጀል በተመለከተ በ1954 ዓ.ም የወጣውን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ህግ የሰጠው ትርጉም ማየት አስፈላጊ ነው፡፡

በሥነ-ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 19(1) እና (2) መሰረት እጅ ከፍንጅ የሚባሉ ወንጀሎች
1. ወንጀል አድራጊው ወንጀሉን ሲሰራ የተያዘ ሲሆን ወይም ለመስራት ሲሞከር ወይም የወንጀሉን ስራ እንደፈፅመ ወዲያውኑ የተያዘ ሲሆን ነዉ፡፡
2. ወንጀል አድራጊው የወንጀሉን ስራ ከፈፀመ በኃላ ወዲያውኑ ሲሸሽ ምስክሮቹ ወይም ህዝቡ የተከታተሉት ወይም የህዝብ ጩኸትና እሪታ የተሰማ እንደሆነ ወንጀሉን እንደ እጅ ከፍንጅ መሰል ነዉ::

ስለሆነም በህጉ መሰረት አንድ ተጠርጣሪ አንድ ወንጀል ለመስራት ሲሞክር፣ ሲሰራ ወይም ከፈፀመ በኋላ በቦታው መያዙ እጅ ከፍንጅ መሆኑ ይገለፃል:: በህጉ ቁጥር 20 መሰረት ተመሳሳይ ሁኔታ ሲገለፅ አንድ ወንጀል የእጅ ከፍንጅ ተብሎ በቁጥር 19 መሰረት ሊጠቀስ የሚቻለው ወንጀሉ በተሰራበት ቦታ ወዲያውኑ ፖሊስ የተጠራ እንዲሆነ በተጨማሪ ወንጀሉ ሲሰራ ወይም እንደተፈፀመ ወንጀሉ ከተሰራበት ቦታ ላይ የድረሱልኝ እሪታ የተሰማ እንደሆነ ነው እንደ እጅ ከፍንጅ የሚቆጠረው:: ተጠርጣሪዉ ሲሸሽ በመከታተል የሕዝብ ጩኸት ከተሰማ፣ ወደ ቦታው ፖሊስ ወዲያውኑ ከተጠራ ወይም ተጠርጣሪውን ባይከታተሉውም በወንጀሉ ቦታ የይድረሱልኝ እሪታ የተሰማ እንደሆነ በተመሳሳይ ሀኔታ እንደ እጅ ከፍንጅ ወንጀል ይቆጠራል:: የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች አፈፃፀም ሆነ የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች መሰል ወይም ተመሳሳይ ሁኔታ አፈፃፀሞች በሕጉ ያለው ውጤት አንድ አይነት ነው:: ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ የወንጀል ምርመራ የሚጀምረው በግል ተበዳይ አቤቱታ ወይም በማናቸውም ሰው ጥቆማ ወይም ፖሊስ በራሱ በደረሰዉ ሁኔታ ቢሆንም የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ከተፈፀመ በዚህ ክፍል በተጠቀሰው ሕግ ቁጥር 21 መሰረት በቁጥር 19 እና 20 በተዘረዘሩት ወንጀሎች ማለትም እጅ ከፍንጅ እና እጅ ከፍንጅ መሰል ወይም ተመሳሳይ ወንጀሎች መሰረት ወንጀሉ የክስ አቤቱታ ሳይቀርብ ክስ ሊቀርብበት የማይችል ካልሆነ በቀር ክስ ወይም የክስ አቤታቱ እንዲቀርብበት አስፈላጊ ሳይሆን ክስ ማቅረብ ይቻላል:: እንደዚህ ያለው ሁኔታ በሚያጋጥምበት ጊዜ ፍርድ ቤት የሚሰጠው የመያዝ ትዕዛዝ ሳይኖር በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ- ሥርዓት ቁጥር 49 እና በተከታዩቹ ቁጥሮች መሰረት ወንጀለኛውን ለመያዝ ይቻላል:: በመሆኑም የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች በተፈፀሙ ጊዜ የግል አቤቱታ የማያስፈልጋቸዉ ከሆነ ምርመራ እና ተጠሪጣርን መያዝ በአንድ ላይ ይጀምራል:: ስለዚህም በግል አቤቱታ የሚቀርቡ ጉዳዩች በተበዳይ ፍላጎት ካልሆነ በስተቀር ወንጀለኛ ሊያዝ አይችልም:: ምክንያቱም ተበዳይ ጉዳዩ እንዲገለጽ ላይፈልግ ስለሚችል፣ ለኀብረተሰቡም ብዙ ጉዳት የሚያደርስ ባለመሆኑ ወንጀሉ በተፈፀመ ቦታ ወንጀለኛ መያዝ አስፈላጊ ባለመሆኑ ነው፡፡

በህጉ አንቀጽ 49 በተገለፀው መሰረት ማንም ሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሊያዝ ወይም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ለማድረግ አይቻልም:: ሆኖም በህጉ አንቀጽ 50 በተገለፀው መሰረት ማንኛውም ሰው ወይም የፖሊስ ሰራዊት ባልደረባ በቁጥር 19 እና 20 በተመለከተው መሰረት ከሦስት ወር በማያንስ በቀላል እስራት ቅጣት የሚያስቀጣ የእጅ ከፍንጅ ወይም መሰል ወንጀል የፈፀመ እንደሆነ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወንጀል ሰሪውን ለመያዝ እንደሚቻል ገልጿል:: በመሆኑም በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ወንጀል ህግ ውስጥ በግልፅ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስቀጡ ወንጀሎች ተብለዉ የተጠቀሱ ለምሳሌ የእጅ እልፊት፣ ስድብ የመሳሰሉት እና በዚሁ በተጠቀሰው የወንጀል ህግ የወንጀል ቅጣት ከሦስት ወር በታች የሚያስቀጡ ከሆነ እጅ ከፍንጅ የተሰራ ወንጀል ቢሆንም ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዥ ወይም በሥነ ሥርዓት ህጉ 51 መሰረት በተሰጠው ስልጣን ካልሆነ ተጠሪጣሪን መያዝ አይቻልም፡፡ ሌላ በዚህ ክፍል ሊጠቀስ የሚገባው በህጉ መሰረት ከተጠቀሱት በግል አቤቱታ የማይቀርብና ከሦስት ወር በላይ የሚያስቀጣ ወንጀል ከሆነ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ወይም መሰል ወይም ተመሳሳይ ሁኔታ የፈፀመን ሰው ማንም ሰው በመያዝ ወደ አቅራቢያዉ ወደ አለው ፖሊስ ጣቢያ ማስረከብ ይቻላል:: በሌላ ሁኔታ ከፖሊስ ዉጭ በህግ የተጠረጠረን ሰዉ መያዝ አይቻልም፡፡
👇👇👇👇👇 ይቀጥላል
...... 👆👆👆👆👆👆👆👆የቀጠለ
በሌላ በኩል በሌሎች ህጎች የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች ሰርተው በህጉ በተለየ ሁኔታ የተቀመጠ ነገር ካልተሟላ በስተቀር ተጠርጣሪን መያዝ የማይቻልበት ሁኔታ አለ፡፡ ለምሳሌ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 54(6) እንደሚገልፀው ማንኛውም የሕዝብ ተወካዩች ምክር ቤት አባል ከባድ ወንጀል ሲፈፀም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም:: በወንጀልም አይከሰስም፡፡ በዚሁ ህግ አንቀጽ 63(2) መሰረት ማንኛውም የፌዴሪሽኑ ምክር ቤት አባል ከባድ ወንጀል ሲፈፅም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም:: በወንጀልም አይከሰስም፡፡ በእነዚህ ህግ መሰረት የየምክር ቤት ፈቃድ ተጠይቆ ዉሳኔ ሲሰጥ መያዣ ትዕዛዝ ማወጣት እና ማስረጃ በቂ ከሆነ ክስ መመስረት ብዙም ችግር የለም:: የወንጀል ደረጃ በተመለከተ ከባድ ወንጀል ነው ለማለት ምን መስፈርት መጠቀም አለብን የሚለው አከራካሪ ነው፡፡ የወንጀል ሕግ ስለወንጀል ደረጃዎች በግልፅ የሚናገረው ነገር የለም:: ሆኖም የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 106(1) ላይ ቀላል እስራት፣ ከባድነቱ መካከለኛ የሆነ ወንጀልን ባደረገና ጥፋተኛውም ለኅብረተሰቡ እጅግ አደገኛ መስሎ ባልታየ ጊዜ የሚወሰን የነፃነት ማሰጣት ቅጣት ነው:: በአንቀጽ 108(1) በተጠቀሰዉ መሰረት፣ የፅኑ እስራት ቅጣት የሚወሰነዉ ከባድ ወንጀል ባደረጉና በተለይም ለኅብረተሰቡ አደገኛ በሆኑ ወንጀለኞች ላይ ነው:: ከእነዚህ ከሁለት አንቀፆች የምንረዳው በወንጀል ሕግ ውስጥ በቀላል እስራት የሚያስቀጡት ወንጀሎች መካከለኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጡ የወንጀል አይነት ሲሆን በፅኑ እስራት የሚያስቀጡት ወንጀሎች በከባድ ደረጃ የሚቀመጡ የወንጀል አይነት ናቸው ማለት ነው:: በሌላ በኩል በአንቀጽ 103(1) ላይ እንደተገለፀው ከባድትነት የሌላቸውና በገንዘብ መቀጮ ወይም በግዴታ ስራ የሚያስቀጡ፣ ቀላል ደረጃ ያላቸዉ የወንጀል አይነቶች እንደ ቀላል ደረጃ ያላቸዉ የወንጀል አይነቶች እንደሆኑ መረዳት ይቻላል:: በመሆኑ በገንዘብ ወይም በግዴታ ስራ እንዲሰራ የሚደነግግ የወንጀል አይነት የፈፀመ ቀላል ደረጃ አይነት ወንጀል እንዲሁም በቀላል እና በፅኑ እስራት የሚያስቀጡ ወንጀሎች እንደ ቅደም ተከተላቸዉ በመካከለኛ እና በከባድ ደረጃ የሚቀመጡ ናቸው::

በመርህ ደረጃ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህጉ ቁጥር 32 በተጠቀሰው መሰረት ማንኛውም መርማሪ ፖሊስ ወይም የፖሊስ ሰራዊት ባልደረባ በፍርድ ቤት የተሰጠ የብርበራ ማዘዣ ካልያዘ በቀር መበርበር አይችልም:: ነገር ግን በልዬ ሁኔታ ያለብርበራ ማዘዣ መበርበር የሚፈቅድለት ፤ ወንጀለኛውን እጅ ከፍንጅ ሲከታተሉትና እቤት ውስጥ ሲገባ ወይም ወንጀል የሰራበትን ነገር እቤት ውስጥ ያስቀመጠ ሲሆን ነው፡፡ በተከሰሰበት ወንጀል ወይም ወንጀል ሰርቷል ተብሎ በተጠረጠረበት ነገር ማስረጃ የሚሆን በሰውነቱ ደብቋል የሚያሰኝ በቂ ምክንያት ካለ የተያዘውን ሰው መፈተሽ ይቻላል፡፡ እጅ ከፍንጅ ወይም መሰል ወንጀል እንደተፈፀመ በመከታተል ሰውነቱንም ሆነ ንብረቱ የተቀመጠበትን ቦታ መበርበር ይቻላል፡፡

የእጅ ከፍንጅ ወንጀል በክስ ሂደት ያለዉ እንድምታ
የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ በ109(1) በተገለፀው መሰረት ዐቃቤ ሕግ የፖሊስ ምርመራ መዝገብ በደረሰው በአስራ አምስት ቀን ጊዜ ውስጥ ውሳኔ መስጠት እንዳለበት ይገለፃል፡፡ ዐቃቤ ህግ ምርመራውን በቅርበት የሚከታተል በመሆኑ በሰዓታት ወይም በቀናት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል:: የኢ.ፌዲ.ሪ የወንጀል ፍትህ ፖሊሲ መሰረት በማንኛውም የወንጀል ክስ ጉዳይ የተሟላ ማስረጃ እስከቀረበ ድረስ ማንኛዉም የወንጀል ክርክር በተቀላጠፈ ሥነ ሥርዓት ሊመራ ይችላል:: ምክንያቱም ሲገለፅ ማስረጃዎች ክሱን የማስረዳት ብቃታቸዉ ሳይቀንሱ በትኩሱ እንዲቀርቡ ለማድረግ፣ ከኤግዚቪይት ጋር ተያይዘው ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት እና የተጎጂ እና የተጠርጣሪ መብቶችን በአግባቡ ለማክበር በጊዜ ፍትህ ለመስጠት የሚስችል ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ነው፡፡ አሁን በተግባር የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች ችሎት እና መደበኛ ችሎቶች አሉ:: የእጅ ከፍንጅ የሚቀርቡ ጉዳዩች በፖሊሲ በግልፅ የመወሰን ስልጣን የዐቃቤ ሕግ እንደሆነ ይገለፃል፡፡ በዐቃቤ ሕግ በማስረጃ ይዘታቸዉ ውስብስብነት የሌላቸዉ የእጅ ከፍንጅ እና ለሌሎች ወንጀሎች በፈጣን ሥርዓት ማስከሄድ የተፈጣነ ፍትህ እንዲሰጥ ያደርጋል:: ይህንም ሲወስኑ የወንጀሉን አጠቃላይ ባሕሪይ የማስረጃዎችን ይዘትና ብቃት እንዲሁም የተጠርጣሪውንና የተጎጂውን ፍላጎት ግምት ዉስጥ ማስገባት ያስፈልጋል::

እጅ ከፍንጅ ወንጀሎች በፍርድ ሂደት ያለዉ እንድምታ
ዐቃቤ ሕግ ወደ እጅ ከፍንጅ ችሎት እንዲቀርብ አንድ ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ሲመራ በፍርድ ቤት እጅ ከፍንጅ ችሎት የሚከፈት መዝገብ በዕለቱ ወደ ችሎት ሄዶ ጉዳዩ ይታያል:: ነገር ግን በሌሎች መደበኛ ችሎቶች ቀጠሮ ተሰጥቶ ከዛም በኋላ በቀጠሮ ቀን ችሎት ይቀርባል:: እጅ ከፍንጅ ችሎት ከሌላው የሚለየው በዕለቱ ስራ መቀጠሉ ነው:: በላይ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ እጅ ከፍንጅ ችሎት የሚቀርቡት እጅ ከፍንጅ የተያዙት ተጠርጣሪዎች ብቻ ሳይሆን ማንኛውም የተሟላ ማስረጃ እና ተከሳሽ ያለበት መዝገብ እዚህ ችሎት ይቀርባል:: ሌላው ከመደበኛ ችሎት የሚለየው የተፋጠነ ስርዓት ከመሆኑ አኳያ ብዙ ጊዜ የዋስትና መብት እንደ አንድ ችግር ይታያል:: የዐቃቤ ህግ ምስክር ተሰምቶ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ መከላከያ ማስረጃ የለኝም ካለ ፍርድ ቤት ውሳኔ ወዲያዉኑ መስጠት ካልቻለ አንዳንድ ችሎት እንደሚያደርጉ ተከሳሽ በዋስ መለቀቅ አግባብ አይሆንም:: ምክንያቱም ውሳኔ መስጠት ብቻ የሚቀር በመሆኑ:: ከዚህ ውጭ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ችሎት ከሌሎች መደበኛ ችሎት ጋር አንድ አይነት ነዉ::
በአጠቃላይ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል በህግ የተደነገገ፣ ማሰረጀዉ የቅርብ የሆነ እና የወንጀል ምርመራዉ፣ የክስና የፍርድ ሂደቱ የተፋጠነ በመሆኑ በተሻለ ሆኔታ ፍትህን ለመስጠት የሚያስችል ነዉ፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 205827 ህዳር 27ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ አላማውን በማያሳካ መንገድ ተርጉሞታል በማለት አስገዳጅ ውሳኔ ሰጠ ።

ጉዳዩ የተነሳው ያረጋል ተገኘ የተባለ ተከሳሽ መስከረም 11/2012 ዓ/ም በአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ 1 ቱርክ ሽጉጥ ከመሰል 31 ጥይቶች ጋር ይዞ በመገኘቱ ዐቃቤ ህግ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 4(1) እና 22(2) ላይ የተመለከተውን ተላልፎ ጦር መሳሪያ ይዞ ተገኝቷል በሚል ክስ መስርቶበት የአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ፍ/ቤት ተከሳሸን ባመነው መሰረት ጥፍተኛ በማለት 2ወር ቀላል እስራትና 600ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ስለወሰነና ውሳኔ የአዊ/ብ/ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ስላጸናው በተከሳሽ ይግባኝ ጠያቂነት የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2) ላይ የተመለከተውን የጊዜ ገደብ በመጥቀስ ተቆጣጣሪ ተቋሙ የጊዜ ገደብ አውጥቶ ምዝገባ ባልጀመረበት ሁኔታ ተከሳሽን ጥፋተኛ ብሎ መቅጣት ህጋዊ መሰረት የለውም በማለት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ በመሻሩ የአብክመ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ለፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ በማቅረቡ ነው ።
ይግባኝ የቀረበለት የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም ፦
1ኛ የአዋጁ አንቀጽ 23(2) ጊዜ ሰሌዳ ያስቀመጠ ቢሆንም ቅሉ በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ ሆኖ ማነኛውም ግለሰብ ጦር መሳሪያ ይዞ ቢገኝ ከተጠያቂነት እንደሚድን አያስቀምጥም ።
2ኛ የአዋጁ መሰረታዊ አላማ የጦር መሳሪያን ወደ ህጋዊ ስርዓት አስገብቶ መቆጣጠር እንጅ በዚህ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ማንኛውም ግለሰብ የጦር መሳሪያ ይዞ ለመገኘት ፈቃድ የሚሰጥ አይደለም ፤ የጊዜ ገደቡ የሚያገለግለው ጦር መሳሪያው በምዝገባ ሂደት ላይ እያለ ችግር እንዳያጋጥም እንጅ የአንድ አመት የመያዝ ፈቃድ የሚሰጥ ተደርጎ መተርጎም የለበትም ፤
ስለሆነም የጊዜ ገደብ መቀመጡ እስከ አንድ አመት ያለማንም ጠያቂነት የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመፍቀድ ታስቦ የተደነገገ አድርጎ መተርጎም የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የወጣውን አዋጅ አላማ የሚያሳካ ካልመሆኑም በተጨማሪ ተከሳሹ በሰጠው የእምነት ቃል መሰረት ጦር መሳሪያውን የያዘው ነባሩ አዋጅ በስራ ላይ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑ ያልተካደ በሆነበት ሁኔታ ተከሳሽን ከተጠያቂነት ነጻ ማድረግ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ አላማ ባልተገባ መንገድ በመተርጎም መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸም ነው በማለት የወረዳውንና የከፍተኛውን ፍ/ቤቶች ውሳኔ አጽንቶ የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሽሮታል ።
Please share it ( እባክዎ ያጋሩት)
በ ተስፍሽ ዐቢሲኒያ
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties