ከደረሰኝ ጋር የተገናኙ ወንጀሎች እና ቅጣታቸው።።።።።።።።።።።።።።።።
#አለ_ህግ #Ale_Hig
I. ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ ያለደረሰኝ ግብይት ያከናወነ እንደሆነ ከብር 25ሺ (ሃያ አምስት ሺ ብር) እስከ ብር 50ሺ (ሃምሳ ሺ ብር) የገንዘብ መቀጫ እና ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
II. በአንድ ግብይት በተሰጡ ተመሳሳይ የደረሰኝ ኮፒዎች ላይ የተለያዩ ዋጋዎችን በመመዝገብ የሽያጭ ዋጋን ያሳነሰ ማንኛውም ሰው ብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እና ከአምስት ዓመት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
III. የሽያጩ ትክክለኛ ዋጋ ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ ከሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (||) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኞቹ ላይ ከተመለከቱት ከፍተኛው የገንዘብ መጠን እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት የሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
IV. ግብይት ሳይፈጸም ደረሰኝ የሰጠ ወይም የተቀበለ ሰው ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
V. በዚህ ተራ ቁጥር (IV) የተመለከተው ደረሰኝ ከብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ የገንዘብ መጠን የያዘ እንደሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (|) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኙ ከተገለጸው የገንዘብ መጠን ጋር እኩል በሆነ የገንዘብ ቅጣት እና ከአስር ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት የሚደረስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
VI. ባለሥልጣኑ ሳይፈቅድለት የታክስ ደረሰኝ ያተመ ሰው ከብር 300ሺ (ሦስት መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 500ሺ (አምስት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሁለት ዓመት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
VII. በዚህ ተራ ቁጥር (VI) መሠረት ጥፋተኛ የተባለ ሰው ወንጀሉን ለሁለተኛ ጊዜ ፈጽሞ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ የህትመት መሣሪያው እና የማተሚያ ድርጅቱ ይወረሳል፣ የንግድ ፈቃዱም ይሰረዛል፡፡

የቤተሰብ ውክልና #አለ_ህግ #Ale_Hig
የቤተሰብ ውክልና ፡- መሰረቱ የፍትሃብሔር ህግ አንቀጽ 2203 እና /ወይም 2205 ድንጋጌዎች ሆኖ በፍትሃብሄር ስነ-ስርዓት ህግ አንቀጽ 58 መሰረት ለቅርብ ዘመድ ማለትም ባለቤት፣ወንድም፣እህት፣ልጅ፣አባት፣አያት፣ እናት ለሆኑ ሰዎች የሚሰጥ የውክልና ዓይነት ነው፡፡
ውስን ውክልና
ውስን ውክልና፡- ተወካይ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ንብረቱን በስም እና ዝርዝር መረጃውን በመጥቀስ የውክልና ስልጣን የሚሰጥበት ነው ፡፡
ሙሉ ውክልና
ሙሉ ውክልና፡- ተወካይ አጠቃላይ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረቱን በሚመለከት ዝርዝር መረጃ መስጠት ሳያስፈልገው በጥቅሉ ውክልና የሚሰጥበት ነው፡፡
#አለ_ህግ @Lawsocieties

አዲሱ-የንግድ-ሕግ 55932.pdf
3.4 MB
Share 'አዲሱ-የንግድ-ሕግ 55932.pdf'
አለሕግAleHig ️
በህግ አምላክ ምን ማለት ነው❗️❓ ቀድሞ በጥሩ ማብራሪያ የመለሰ ሽልማት አለው። #አለ_ህግ #Ale_Hig
በህግ አምላክ ❗️❓
ቃሉ ከብዙ ዓመታት በፊት ጀምሮ በእኛ አገር ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አገራት ላይ መሰረት ያለው ነው።መነሻውም ሰወች ሕጉን ብቻ ሳይሆን ሕግ ያወጣውን አካል ምላሽ እንዲመለከቱና ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሚያሳስብ ነው።ሰወች ህገ ወጥ ድርጊት ሲፈፅሙ ለድርጊታቸው ህገወጥነት ምላሽ የሚሰጥ አካል እንዳለ በዚሁ ቃል ያስታውሳሉ።እንዲያውም አንዳንዴ ሕጉን ያወጡ ንጉሶች ስም እየተጠራ በእነሱ አምላክ ስም ድርጊት ፈፃሚው ድርጊቱን እንዲያቆም ይጠየቅ እንደነበር ይነገራል። ይሄንን የሰማ ህገ ወጥ አካል ድርጊቱን የሚያቆመው ከድርጊቱ በሁዋላ የሚመጣበትን ምላሽ በቃሉ ውስጥ ስለሚመለከት ነው።
ሌላኛው ደግሞ ሕግን የሚሰጥ ፈጣሪ እንደሆነ ሰወች ያምናሉ።ይሄም እምነታቸው ሕግን እንዲከተሉ ምክንያት ይሆናቸዋል።በዚህ እይታ ደግሞ በሕግ አምላክ የሚለው ቃል ሰወች ፈጣሪን ፈርተው ከድርጊታቸው እጃቸውን እንዲመልሱ ምክንያት ይሆናቸዋል።በአጠቃላይ የቃሉ አንድምታ ይሄንን ይመስላል።
One Love:

👉በህግ አምላክ ማለት:-
አገሬው ስለ ሕግ ሃያልነት ሲናገር "በሕግ አምላክ ሲባል እንኳን ሰው ወራጅ ውሃ ይቆማል" ይል ነበር፡፡ ሕግ ተፈጥሮንም እስከማቆም ሃይል እንዳለው አድርጎ ለመግለፅ ምን ዓይነት በሕግ የፀና እምነት ቢኖር ነበር ያስብላል፡፡ በሕግና ፍትሕ ላይ እምነት ያለው ሕዝብ ያለማንም አስገዳጅነት ለሕግ ተገዢ ነው፡፡ ክስተቶችንም ተከትሎ ለሕግ ያለውንም እምነት በተለያዬ መንገድ ይገልፃል፡፡ ግጭቶችን በጉልበት ከመፍታት በሕግ መፍታት ተመራጭ እንደሆነም ያምናል፡፡ በጉልበቱ አዳሪ ሲገጥመው ሰይፍን በሰይፍ ከመመለስ በሕግ አምላክ ቢል ይመርጣል፡፡ ከማትረባ ጉልበት በሕግ አምላክ ይሻላል የሚለውም ለዚህ ይመስላል፡፡ ስለዚህ የሕግ መከበር ሕበረተሰቡ ስለሕግና ፍትሕ ባለው አመለካከት ይወሰናል ማለት ነው፡፡ ሕግ በሕበረተሰቡ ውስጥ በሚፈለገው ደረጃ ለውጥ እንዲያመጣ ከተፈለገ እያንዳንዱ ሰው ስለሕግ ያለው አመለካከት አብሮ መመለወጥና ማደግ ይኖርበታል፡፡ ሕበረተሰቡ ለሕግና ፍትሕ ያለው አመለካከት ሁለት ነገሮችን ይገልፅልናል፡፡ በአንድ በኩል ሕብረተሰቡ ስለሕግ ያለውን እምነት ሲገልፅልን በሌላ በኩል ደግሞ የሕግ መከበር ያለበትን ደረጃ ያሳየናል፡፡
👉ዘመናዊ የፍትሕ ሥርዓት ሳይዋቀር በፊት አገሬው ስለሕግ የበላይነት የፀና እምነት ነበረው ማለት እንችላለን፡፡ አስገዳጅ ነገር ሳይኖር በአገር ደንብ ብቻ መንገድ ላይ ባላጋራውን ሲያገኘው በሕግ አምላክ ብሎ ተላላፊው መንገደኛ ጉዳዩን እንዲመለከትለት ያደርግ ነበር፡፡ ተላላፊው መንገደኛም ዳኝነቱን ተቀብሎ የግራ ቀኙን ጉዳይ ሰምቶ ይፈርዳል፡፡ ውሳኔው ከተስማማቸው ይፈጽማሉ ካልተስማቸው በአካባቢው ወዳለው ጭቃ ሹም ተያይዞ መሄድ ነው፡፡ ይህን ተላላፊ መንገደኛ ዳኛ የሕግ ሙሁር አበራ ጀንበሬ የመንገድ ዳሩ ፍርድ ቤት(የመንገድ ዳር ዳኛ) በማለት ሲገልፁት ከሳቴ ብርሃን የአማርኛ መዝገበ ቃላት ደግሞ "ዳኛ የውሃ ወራጅ ዳኛ" በማለት ይገልፀዋል፡፡ ስያሜው ምንም ይሁን ተላላፊውን መንገደኛ ዳኛ፣ ባላጋራዎችን ተከራካሪ አድርጎ ሲያቆማቸው የነበረው ያገር ደንብና ልማድ፣ፈቃደኝነትና ለሕግና ፍትሕ የፀና እምነት መኖር እንጅ ሌላ አስገዳጅ ሃይል አልነበረም፡፡
👉በአጠቃላይ በህግ አምላክ ማለት ለህግ ተገዢ ሁን ወይም ለህግ ብለክ ድርጊትህን አቁም ወይም ተዉ እንደማለት ነዉ፡፡
Am the one☝️:

አዲሱ_የሒሳብ_መዝገብ_አያያዝ_መመሪያ.pdf
1.1 MB
#እንድታውቁት #አለ_ህግ #Ale_Hig
የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦዲት የቅሬታ ምንጭ ሆኖ የቆየው
" የሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 152/2011 " ን በአዲስ መመሪያ እንዲተካ ማድረጉን አሳውቋል።
መመሪያውን ማሻሻል ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት የታክስ አስተዳደሩን ቀልጣፋ ለማድረግ እና ግልጽነት የጎደላቸውን አሰራሮች ግልጽ ለማድረግ ነው ብሏል ሚኒስቴሩ።
አዲሱ መመሪያ ቁጥር 176/2014 በሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 152/2011 ላይ የነበረውን አሰራር ያሻሽላል ተብሏል።
አዲሱ ወይም የተሻሻለው የሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 176/2014 ከላይ በPDF ተያይዟል።
tikvah ethiopia

የፌዴራል ጠበቆች ምዝገባ - መራዘሙን ስለማሳወቅ
#አለ_ህግ #Ale_Hig
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር በአባልነት ላቀፋቸው ጠበቆች አስፈላጊውን አገልግሎት በመስጠት ኃላፊነት እና ግዴታውን ለመወጣት ይችል ዘንድ እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ
1. በድህረ-ገጽ በኦንላይን በዚህ አድራሻ http://t.ly/RzWs ወይም
2. በፍትሕ ሚኒስቴር ዋና መ/ቤት ወይም በአራዳ ምድብ ችሎት በሚገኘው የማኀበሩ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት
እንድትመዘገቡ መጠየቁ ይታወሳል።
በዚህ መሠረት በርካታ ጠበቆች በኦንላይን እና በአካል በመገኘት ምዝገባቸውን አከናውነዋል።
ምዝገባው እንዲከናወን የታሰበበት ጊዜ የበዓል ቀናት የተበራከቱበት መሆኑን በመገንዘብ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ለመመዝገብ ያልቻሉ ጠበቆች ምዝገባውን እንዲያከናውኑ ተጨማሪ ቀን መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ማኅበሩ አምኗል።
በዚህ መሠረት ያልተመዘገባችሁ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች በሙሉ የምዝገባ ጊዜው
ከሰኞ ከግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን አውቃችሁ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ ማኅበሩ ያሳስባል።
በኦንላይን ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ http://t.ly/RzWs
በአካል ተገኝተው ለመመዝገብ፦
1. የጥብቅና ደብተርዎን መያዝዎን አይዘንጉ፤
2. የጥብቅና ደብተርዎን የፊት ገጽ እና ፈቃድዎ የታደሰበትን የሚያሳየውን ክፍል ኮፒ አድርገው መያዝዎን አይዘንጉ
3. ለማኅበሩ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ስሊፕ መያዝዎን አይዘንጉ፤
4. የግብር መለያ ቁጥር መያዝዎን አይርሱ፤
የኢትዮጵያ የፌዴራል ጠበቆች ማኅበር

#1-ደሀ ደንብ
• ዳኝነት ሳይከፈል፣ በነፃ መዝገብ ማስከፈት
ክስ ለማቅረብ የፈለገ ወገን ከፍርዱ ለሚያገኘው የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችል የገንዘብ አቅም የሌለው ከሆነ ክሱን ያለዳኝነት ገንዘብ በደሀ ደንብ መሠረት የማቅረብ መብት እንዳለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 215 ተደንግጓል፡፡ ክሱን የሚያቀርበው ወገን ድሀ በመሆኑ ምክንያት የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍል ክሱን አቅርቦ እንዲያሰማ ሊፈቅድለት ይገባል? የሚለው ጉዳይ ሊለይ የሚችልበት ዝርዝር አፈፃፀም ደንቡም ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 እና ተከታዩ ድንጋጌዎች ተመልክቷል፡፡ እነዚህ ደንቦች ተፈፃሚነታቸው ክስ ለማቅረብ በፈለገ የተፈጥሮ ሰውም ሆነ በሕግ ሰውነት ያላቸው ወገኖችም ጭምር ነው፡፡
በዚህም መሠረት ድሀ ነኝ፤ መብቴን ለማስከበር ያለኝ ፍላጐቴ በዳኝነት ገንዘብ እንቅፋት ምክንያት ሊሰናከል አይገባም፡፡ ስለሆነም በድሀ ደንብ መሠረት ክሱን በነፃ እንዳሰማ ይፈቀድልኝ የሚል ማናቸውም ከሳሽ ድሀ መሆኑን ሊያመለክት የሚችል የሚገኝበትን የገንዘብ አቋም ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡ ይህም ከሳሹ የሚገኝበት የገንዘብ አቋም ከተረጋገጠ በኋላ ለክሱ ሊከፈል የሚገባው የዳኝነት ገንዘብ መጠን ከሳሹ ከሚገኝበት የገንዘብ አቋም አኳያ ተገናዝቦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 መሠረት ድሀ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ሊለይ ይገባል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 79555 ቅጽ 14፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215፣ 467
አንድ ሰው በፍርድ ሊያልቅ የሚገባው ጉዳይን ፍርድ ቤት ይዞ ሲቀርብ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ መክፈል ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 215፣ ከ467 እስከ 479 ድረስ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ያሳያሉ፡፡ የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የማይችል ሰው ክስ ለማቅረብ የሚችልበት አግባብ ስለመኖሩም ተጠቃሽ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ፡፡ አንድ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለመክፈል የማይችል ሰው በደሃ ደንብ ክስ ለማቅረብ የሚችል ሲሆን ለመክፈል አቅም እያለው ክስ ያቀረበ መሆኑ ከተረጋገጠ ግን መዝገቡ እንደሚዘጋ፣ የተዘጋ መዝገብ ደግሞ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ /ገንዘቡን/ ለመክፈል ዝግጁ እስከሆነ ድረስ የሚንቀሳቀስለት መሆኑን የሥነ ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች መንፈስና ይዘት ያስገነዝባሉ።
ሰ/መ/ቁ. 52942 ቅጽ 12፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215፣ 467-479 ....ይቀጥላል --- source ፦Amharic Legal Glossary Abrham Yohanes

የፌደራል የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩት ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ያዘጋጀው 6ኛው ዙር የኢትዮጵያ የህግ ትምህርት ቤቶች ምስለ ችሎት ውድድር በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀመረ (ሚያዝያ 28/2014 ዓ ም)
የውድድር ኮሚቴው ባወጣው መርሃ-ግብር መሠረት በወንጀል ህግ(Transitional Criminal Justice) ላይ የሚያተኩር መነሻ የክርክር ጭብጥ ተዘጋጅቶ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለሚገኙ የህግ ት/ቤቶች ከተላከ በኋላ የጽሁፍ ክርክሩን ያለፉ12 ዩኒቨርሲቲዎች የቃል ክርክራቸዉን በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ተከታታይ 3 ቀናት ውድድራቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።
ዝርዝር መረጃውን የውድድሩ ማጠናቀቂያ ዕለት የምናቀርብ ይሆናል።
√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√
ዘገባው: የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው !