የአስተዳደር ህግ እና ህገ መንግስታዊ መርሆዎች.....
የአስተዳደር ህግ እና የህገ መንግስት ትስስር እና ተዛምዶ
የህግ የበላይነት
የስልጣን ክፍፍል
የአስተዳደር ህግ እና የሰብዓዊ መብት አፈፃፀም
መሰረታዊ የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች
ተጠያቂነት ግልፅነት እና የህዝብ ተሳትፎ
የአስተዳደር ህግ እና ህገ መንግስታዊ መርሆዎች
የአስተዳደር ህግ እና የህገ መንግስት ትስስር እና ተዛምዶ
የአስተዳደር ህግ ጽንስቱ ሆነ ውልደቱ ከህገ መንግስት እንደመሆኑ ከዚህ የህግ ክፍል ጋር ብዙ ባህርያትን ይጋራል፡፡ ሁለቱም የመንግስትና የግለሰብ ግንኙነትን በሚመራው ‘የህዝብ አስተዳደር ህግ’ ተብሎ በሚጠራው የህግ ክፍል ውስጥ ይመደባሉ፡፡ አብዛኛዎቹ የአስተዳደር ህግ ጥያቄዎች በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የህገ መንግስታዊነት ጥያቄዎችን ያስነሳሉ፡፡ የአስተዳደር ህግን በጥልቀት ለመረዳት ከተፈለገ ሂደቱ መጀመር ያለበት ህገ መንግስትን በማጥናት ነው፡፡ በምሁራኑ አንደበት ይኸው እውነታ እንዲህ ይገለፃል፡፡
የአስተዳደር ህግ ከህገ መንግስታዊ መሰረቱ ተለይቶ በደንብ ሊታወቅ ሆነ ሊጠና አይችልም፡፡
የአስተዳደር ህግ በህገ መንግስት ማስፈጸሚያ መሳሪያነቱ የዝምድናቸውን ገጽታ በሚገባ ለማወቅ ይረዳናል፡፡ በዚህ የተግባሪነት ሚናው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት ላይ የተቀመጡትን የህገ መንግስታዊነትና የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች እንዲሁም የግለሰቦች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በተጨባጭ እንዲረጋገጡ በማድረግ ህገ መንግስቱን በማስፈጸም ረገድ እንደ አንድ መሳሪያ ያገለግላል፡፡
እ.ኤ.አ በ1959 ዓ.ም. የጀርመን የፌደራል አስተዳደር ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት እንደተናገሩት የአስተዳደር ህግ ‘ተጨባጭ ህገ መንግስት’ ማለትም በተግባር የሚታይ ህገ መንግስት ነው፡፡a የአንድ አገር ህገ መንግስት በዋነኛነት የዜጐችን ሰብአዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ፖለቲካዊ መብቶችና ነጻነቶች ይደነግጋል፡፡ የዜጐች መብት በሌላ ግለሰብ፣ ማህበር ወይም የንግድ ድርጅት ሊጣስ ይችላል፡፡ ትልቁ አደጋ ያለው ግን ከመንግስት በተለይም ከስራ አስፈፃሚው አካል በኩል ነው፡፡ መብቶች በሚገባ እንዲጠበቁ የመንግስት አስተዳደር ልኩ ተለይቶ በታወቀ የስልጣን ገደብ ውስጥ ሊከናወን ይገባል፡፡ ሆኖም ስልጣን ሁልጊዜ በህጉ መሰረት ግልጋሎት ላይ ይውላል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡ የግድ በአግባቡ ሊገራና ልጓም ሊበጅለት ይገባል፡፡
የአስተዳደር ህግ የስልጣን መቆጣጠሪያ መሳሪያ ነው፡፡ በዚህ ተግባሩ ውጤታማ የስልጣን ቁጥጥር የዜጐች ህገ መንግስታዊ መብትና ነፃነት እንዳይጣስ ዋስትና ይሰጣል፡፡ መንግስቱን በተግባር እንዲተረጐም የሚደርገውም በዚህ መንገድ ነው፤ ስልጣንን በመቆጣጠር የዜጐችን መብት በተጨባጭ ማቀዳጀት፡፡
ይህ ሚናውን በሌሎች ህገ መንግስታዊ መርሆዎች አንጻርም ጎልቶ ይታያል፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት በዋነኛነት ከሚደነግጋቸው የመንግስት አስተዳደር መርሆዎች መካከል ግልፅነት፣ ተጠያቂነትና የህዝብ ተሳትፎ ይገኙበታል፡፡b ግልጽነት እውን የሚሆነው የመንግስት ባለስልጣናትና የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ለዜጐች መረጃ የመስጠት ግዴታቸው ከነዝርዝር አፈፃፀሙ ጭምር በህግ ተደንግጐ ሲገኝ ነው፡፡ ተጠያቂነት፤ ጠያቂውና ተጠያቂው ተለይቶ የተጠያቂነት ስልቱ በዝርዝር ህግ ካልተቀመጠ በተግባር አይረጋገጥም፡፡ የህዝብ ተሳትፎ እንዲሁ የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች በሚሰጡት ውሳኔ በተለይም ደንብና መመሪያ ሲያወጡ በጉዳዩ ጥቅም ካላቸው ወገኖች ሀሳብና አስተያየት እንዲቀበሉ የሚያስገድድ የህግ ድንጋጌ ከሌለ የህዝብ ተሳትፎ በተጨባጭ አይታይም፡፡
ግልፅነትን፣ ተጠያቂነትንና የህዝብ ተሳትፎን በተግባር ለማረጋገጥ የሚወጡ ህጐች በአስተዳደር ህግ የሚካተቱ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ህጉ እነዚህ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች በተግባር እንዲረጋገጡ በማድረግ ህገ መንግስቱን ያስፈጽማል፡፡
በህገ መንግስትና በአስተዳደር ህግ መካከል ያለው የጠበቀ ግንኙነት ልዩነታቸው የላላ መሆኑን ያሳያል፡፡ ሊጠቀስ የሚችል ቀጭን ልዩነት ቢኖር የወሰን እና የህጎች የተፈጻሚነት ደረጃ (Hierarchy of Laws) ልዩነት ነው፡፡
ከወሰን አንፃር ህገ መንግስት አጠቃላዩን የመንግስት አወቃቀርና የሶስቱን የመንግስት አካላት ብሎም በፌደራልና በክልል መንግስታት ያለውን የስልጣን ክፍፍል ስለሚወስን በይዘቱ በጣም ሰፊ ነው፡፡ በአንፃሩ የአስተዳደር ህግ የአንደኛውን የመንግስት አካል ማለትም የስራ አስፈፃሚውን ስልጣን፣ ግዴታና ተግባር ብሎም የውሳኔዎቹን ህጋዊነት የሚመለከት ህግ ነው፡፡ በህግ አውጭው የሚወጣ ህግ እና ፍ/ቤቶች የሚሰጡት ውሳኔ ህገ መንግስታዊነት ከጥናት አድማሱ በላይ ነው፡፡ ስለሆነም ከወሰናቸው አንጻር ህገ መንግስት መስፋቱ የአስተዳደር ህግ መጥበቡ እንደ አንድ የልዩነት ነጥብ ተደርጐ ሊወሰድ ይችላል፡፡
ሁለተኛው ልዩነት የህጎች መሰላል (Hierarchy of Laws) ሲሆን በህጐች መካከል ያለውን የደረጃ ዝምድና ይመለከታል፡፡ ህገ መንግስት የአንድ አገር የበላይ ህግ እንደመሆኑ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና የአሰራር ልምዶች ዋጋ የላቸውም፡፡ የአስተዳደር ህግ በደረጃው ከህገ መንግስት ዝቅ ብሎ የሚገኝ እንደመሆኑ መቼም ቢሆን ከህገ መንግስቱ ጋር መጣጣም አለበት፡፡ ግጭት በተነሳ ጊዜ የበላይ የሆነው ህገ መንግስት ሁልጊዜ ተፈፃሚነት አለው፡፡
አብርሃም ዮሐንስ የህግ አማካሪና ጠበቃ
ይቀጥላል.........
#አለ_ህግ
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ
ይርጋ መነሻ ጊዜ
ይርጋ መቆጠር የሚጀምርበት ጊዜ
የይርጋ ቀን መቆጠር የሚጀምረው ግዴታውን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነው ወይም ውሉ የሚሰጠው መብት ከተሰራበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ የሥራ ውል የተቋረጠበትና የስንብት ደብዳቤ የተሰጠበት ቀን ከተለያየ ይርጋ መቆጠር የሚጀምረው ደብዳቤው ለሠራተኛው ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 94931 ቅጽ 16፣ ፍ/ብ/ህ/ቁ. 1846
በፍትሐ ብሔር ስነ-ስርዓት ህጉ የሚገኙት የጊዜ ገደቦች አቆጣጠር የሚመራው በፍትሐ ብሔር ህግ ባሉት የጊዜ አቆጣጠር ደንቦች ነው፡፡ ጉዳዩ በሌለበት ታይቶ ውሳኔ የተሰጠበት ወገን ውሳኔው እንዲነሳለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 78/1/ መሰረት በአንድ ወር ውስጥ የሚያቀርበው ጥያቄ የአንድ ወር ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ውሳኔ መሰጠቱን ከተረዳበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ ሆኖም የመጀመሪያው ቀን ለይርጋው ጊዜ መቆጠር መነሻ አይሆንም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 76601 ቅጽ 13፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 78/1/
በወራሾች መካከል ውርስ እንዲጣራ አቤቱታ መቅረብ ያለበት በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሲሆን ይህም ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው አንደኛው ወራሽ የውርሱን ንብረት በእጁ ካደረገበት እንጂ ስመ ሀብቱን በስሙ ካዞረበት ጊዜ ጀምሮ አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 52407 ቅጽ 11፣ ፍ/ህ/ቁ. 1000/1/
ከውርስ ሃብት ጋር በተያያዘ ወራሽ የሆነና አካለ መጠን ያልደረሰ ሰው ላይ የይርጋ ጊዜ ሊቆጠር የሚገባው አካለ መጠን ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 57114 ቅጽ 11
ይዞታን አስመልክቶ ከሚነሳ የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ ጋር በተያያዘ ተፈፃሚ የሚሆነው የይርጋ ጊዜ መቆጠር ያለበት አቤቱታ አቅራቢው የይዞታ መብቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ካገኘበት ቀን ጀምሮ እንጂ አቤቱታ የቀረበበት ድርጊት መፈፀም ከጀመረበት ዕለት አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 60392 ቅጽ 11፣ ፍ/ብ/ህ/ቁ. 1140፣ 1149፣ 1146/1/፣ 1144/2/

ብዙ ምሁራን በየፊናቸው በምርምርና ጥናት ባገኙት እውቀት ተመርኩዘው የህግ የበላይነት መርህ ምንነት፤ ይዘትና ፋይዳውን አስመልክቶ አያሌ ንድፈ ሀሳባዊ ትንታኔዎችን አቅርበዋል፡፡ በአገራችን ደግሞ አባቶችና እናቶች በልባቸው ከተጻፈው እውነትና ከልምድ ከቀዱት ቱባ እውቀት በመነሳት የህግ የበላይነትን ጽንስ ሀሳብ በአንድ አባባል እንዲህ ይገልጹታል፡፡
“በፍርድ ከሄደች በቅሎዬ ያለፍርድ የሄደች ዶሮዬ!”
የዚህ ተረትና ምሳሌ አንኳር መልዕክት ለጥቂት ሰዎች ብቻ የተገለጠ ሳይሆን በመላው ማህበረሰብ ዘልቆ የገባ ሀቅ ነው፡፡ እናም ይህን የህግ የበላይነት ፅንሰ ሓሳብን ጠንቅቆ ያወቀው ማህበረሰብ ህግ ሲጣስ፤ ፍትህ ሲጓደል፤ መብት ሲታፈን፤ ስርዓት አልበኝነት ሲነግስ፤ ማን አለብኝነትና በዘፈቀደኝነት ሲንሰራፋ፤ የግሉ የሆነችው ዶሮ ከህግ እና ከፍርድ ውጭ ሲቀማ ድምፁን አጉልቶ ይጮሀል፤ በህግ አምላክ! ይላል፡፡ የጮኸው የዶሮዋ ዋጋ አንገብግቦት አይደለም፡፡ የተወሰደችበት መንገድ እንጂ፡፡ በፍርድ ከሆነ፤ በህጉ መሰረት ከሆነ እንኳንስ ለዶሮ ለበቅሎም ቄብ አይሰጠውም፡፡
በህዝብ አስተዳደር፤ ፖለቲካ ሳይንስ፤ ህግ እና በሌሎችም የጥናት መስኮች የሚገኙ ምሁራን ስለ የህግ የበላይነት ምንነትና ይዘት ያላቸው ግንዛቤና አስተሳሰብ የተራራቀ ከመሆኑ የተነሳ ጽንሰ ሀሳቡ አሁንም ድረስ ቁርጥ ያለ ትርጓሜ አልተገኘለትም፡፡ አንድ የመስኩ ምሁር ይህንን ሀሳብ በማጠናከር እንዳብራራው፤
‘[T]he rule of law’, like ‘democracy’, has no single meaning: it is not a legal rule, but a moral principle, which means different things to different people according to their particular moral positions.a
በዚህ የተነሳ በተለያዩ አገራት የፖለቲካና የህገ መንግስት ስርዓት ውስጥ ይዘቱና አፈጻጸሙ የተለያየ አንዳንዴ የማይጣጣም መልክ በመያዙ መሰረታዊ እሳቤው ወጥነት ርቆታል፡፡
ለምሳሌ በእንግሊዝ አንደኛውና የህግ የበላይነት መገለጫ በመንግስትና በግለሰብ መካከል የሚነሱ ክርክሮች በመደበኛ ፍ/ቤቶች ብቻ መዳኘታቸው ነው፡፡ ያ ማለት በእንግሊዛዊ አይን ፈረንሳይ ውስጥ የህግ የበላይነት የለም እንደ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በፈረንሳይ በግለሰብና በመንግስት መካከል የሚነሱ ክርክሮች ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ የሚዳኙት ከመደበኛ ፍ/ቤት ትይዩ ራሱን ችሎ በተቋቋመ የአስተዳደር ፍ/ቤት ስርዓት አማካይነት ነው፡፡ በእንግሊዝ ሌላኛው የህግ የበላይነት ትርጉም የግለሰቦች መብትና ነፃነት መደበኛ ፍ/ቤቶች በቀረቡላቸው ተጨባጭ ጉዳዮች የሚሰጡት ውሳኔ ውጤት ነው የሚል ይዘት አለው፡፡ ይህ አስተሳሰብ በእንግሊዝ እውነት ቢሆንም የኛን አገር ጨምሮ የተጻፈ ህገ መንግስት ባላቸው እንደ አሜሪካ ባሉ አገራት የዜጐች መብቶችና ነፃነቶች በህገ መንግስቱ ላይ በጽሑፍ ይዘረዘራል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በሊብራል ዲሞክራሲ ስርዓት ውስጥ የህግ የበላይነት ማለት በህጉ መሰረት ከመግዛትና ከማስተዳደር ባለፈ የህጉ ይዘት (ለምሳሌ ፍትሐዊነቱ፤ የዜጐችን መብት ማክበሩ፣ ህጉ የወጣው ህዝብ ወዶና ፈቅዶ በመረጣቸው ተወካዮች መሆኑ ወዘተ…) ብሎም የገለልተኛና ነፃ ፍ/ቤቶች፤ የዲሞክራዊ ተቋማት፤ ነፃ ፕሬስ ወዘተ… መኖር ሁሉም በህግ የበላይነት ጽንስ ሀሳብ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ የሊብራል ዲሞክራሲ ጠበል አልተጠመቁም በሚባልላቸው መንግስታት (ለምሳሌ በቻይና) ጽንሰ ሀሳቡ ስልጣን ያለው አካል በሚያወጣቸው ህጐች መሰረት መግዛትና ማስተዳደር ላይ ብቻ የተገደበ ነው፡፡
የህግ የበላይነት መርህ የአስተዳደር ህግ (በተለይ በእንግሊዝ) የተተከለበት መሰረት ነው፡፡ በዚህ መርህ መሰረት ስራ አስፈፃሚው፣ የአስተዳደር መ/ቤቶች እና የአስተዳደር ጉባዔዎች የሚሰጡት ውሳኔ በህጉ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡ በመንግስት አስተዳደር ውስጥ ህጋዊነት የሚሰፍነው ስልጣን የተሰጠው ማናቸውም የመንግስት አካል የሚወስዳቸው እርምጃዎች፣ የሚፈጽማቸው ድርቶች፣ የሚሰጣቸው ውሳኔዎች እና የሚያወጣቸው ደንብና መመሪያዎች በህግ ጥላ ስር መሆናቸው ሲረጋገጥ ነው፡፡
የመንግስት ባለስልጣናት የሚሰጡት ውሳኔ በህግ ከተቀመጠው የስልጣን ክልል በላይ ከሆነ ውሳኔው የህግ የበላይነት መርህን እንደሚጥስ ጥርጥር የለውም፡፡ ህጋዊነት መከበሩን ማረጋገጥ ማለት አስተዳደራዊ ድርጊት፣ ውሳኔ፣ እርምጃ፣ ደንብና መመሪያ በህግ በተቀመጠው የስልጣን ገደብ ውስጥ መሆኑን አሊያም አለመሆኑን ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የመደበኛ የፍርድ ቤቶች ተግባር ነው፡፡ ይህንን ተግባር በሚያሳንስ መልኩ በፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ላይ በህግ አውጭው የሚደረግ ገደብ በውጤቱ የህግ የበላይነት መርህን ይሸረሽራል፡፡ ገደቡ በህግ የበላይነት መርህ ላይ ከሚፈጥረው አደጋ በተጨማሪ የዜጎችን ፍትህ የማግኘት መብት ያጣብባል፡፡ በተለይም ይህ መብት ህገ-መንግስታዊ እውቅና የተሰጠው ከሆነ የፍርድ ቤቶችን ስልጣን መገደብ ዞሮ ዞሮ የዜጎችን ህገ-መንገስታዊ መብት መገደብ ነው፡፡
የህግ የበላይነት መርህ የአስተዳደር ህግ መሰረት ብቻ ሳይሆን ገደብ ጭምር እንደሆነ ማውሳት ያስፈልጋል፡፡ የውሳኔን ህጋዊነት ማረጋገጥ በይዘቱ ላይ መቆጠብን ያስከትላል፡፡ ፍ/ቤቶች የህግ የበላይነት በማስከበር ሚናቸው የአስተዳደራዊ ውሳኔዎች ይዘት እንዳያጣሩ ወይም በፖሊሲ ጥያቄዎች ጣልቃ እንዳይገቡ ይገድባቸዋል፡፡
አብርሃም ዮሐንስ የህግ አማካሪና ጠበቃ
ይቀጥላል.....................

የህፃናት መብት
ሕፃናት እንደ ማንኛውም ተፈጥሮአዊ ሰው መብት ያላቸው ሲሆን በሥነ-አዕምሮአዊ፣ ሥነ-ልቦናዊ፣ ማኅበራዊ ግንኙነት እንዲሁም አካላዊ ሁኔታ ምክንያት ተጨማሪ ጥበቃ እንደሚያስፈልጋቸው በዓለም አቀፍና ብሔራዊ ህግ ማዕቀፎች ተደንግጓል፡፡ በዚህ የንቃተ ህግ ፅሁፍ በአጠቃላይ መሰረትዊ የህፃናት መብቶች እና ህፃናትን በተመለከተ የተደነገጉ መርሆችን ለመዳሰስ ተሞክሯ፡፡
1. የህፃን ትርጉም
ለሕፃንነት የሕግ ትርጓሜ መስጠትን አስፈላጊ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል ዋነኛው የመብትና ግዴታ ወሰን (scope of rights and duties) ለማወቅ ስለሚያስችል ነው፡፡ እንዲሁም ሕፃናት ለአደጋ ተጋላጭ ከመሆናቸው አኳያ ልዩ ጥበቃ (special protection due to vulnerability) ስለሚያስፈልጋቸው ህፃናትን በመለየት ይህን ጥበቃ ለማድረግ ነው፡፡
ህፃን ማን ነው ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ አገራት ሕጎች የተለያየ ትርጓሜ ሰጥተዋል፡፡ ምንም እንኳ አንድ ወጥ የሆነ የሕፃን ትርጓሜ ባይኖርም ሕፃን የሚለው ቃል ብዙ አገራት ዕድሜን ግምት ውስጥ ያስገባ ትርጉም ይጠቀማሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር በአንዳንድ አገሮች ሕፃን ለሚለው ትርጓሜ ለመስጠት ማኅበራዊ አረዳድን (social construction of age) ግምት ውስጥ የሚያስገቡ ሲሆን ለምሳሌ በጉርምስና ወቅት የሚታዩ አካላዊ ለውጦች እና የድምፅ መጎርነን ከግምት ውስጥ ያስገባሉ፡፡
በዓለም አቀፍ የሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀፅ 1 የተመለከተው ዕድሜን መሠረት ያደረገ ትርጉም ሲሆን “ሕፃን ማለት ማንኛውም ዕድሜው ከአሥራ ስምንት ዓመት በታች የሆነ የተፈጥሮ ሰው” እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ሆኖም በምን ጉዳይና ምን ቅድመ ሁኔታዎች ሲሟሉ ዝቅ ማድረግ ወይም 18 ዓመት ሳይሞላ ለአካለ መጠን መድረስ እንደሚቻል ባያስቀምጥም አገራት በሚያወጡት ሕግ መሠረት ከአሥራ ስምንት ዓመት በታች መውረድ የሚቻልበት አጋጣሚም እንዳለ በኮንቬንሽኑ ተገልጧል፡፡ በዚሁ መሰረት ለምሳሌ በኢትዮጵያ ለጋብቻ ሊባል ማለትም ከባድ ምክንያት ሲያጋጥም ተጋቢዎቹ ወይም ከተጋቢዎቹ የአንዳቸው ወላጆች ወይም አሳዳሪ በሚያቀርቡት ጥያቄ መሰረት ፍትህ ሚኒስትሩ ከመደበኛ የጋብቻ እድሜ (18 ዓመት) ከሁለት አመት ያልበለጠ ጊዜ በመቀነስ እንዲጋቡ ሊፈቅድ ይችላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሕፃኑ ከሞግዚት አስተዳደር ነፃ እንደወጣ (emancipated) ይቆጠራል፡፡ ይህ የዕድሜ ጣራ መድረሻ (አሥራ ስምንት ዓመት) ከየት እንደሚጀምር በግለፅ የተደነገገ ነገር ባይኖርም በኮንቬንሽኑ መግቢያ ላይ እንደተገለፀው ከመወለድ በፊትም ማለትም በጽንስ ወቅትም ጥበቃ እንዳለ ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የአፍሪካ የሕፃናት መብቶች እና ደህንነት ቻርተር አንቀፅ 2 ሕፃን ለሚለው ትርጓሜ ሲሰጥ “ሕፃን ማለት ማንኛውም ዕድሜው ከአሥራ ስምንት ዓመት በታች የሆነ የተፈጥሮ ሰው ነው” በማለት ደንግጓል፡፡
በኢትዮጵያ ለሕፃን ያለውን ትርጉም ስንመለከት ሀገሪቱ ፌደራላዊ ስርዓት የምትከተል በመሆኑ እና የ1987 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራስያዊ ሪፐብሉክ ሕገ መንግሥት የፌደራል እና የክልል መንግሥታት የየራሳቸውን የቤተሰብ ሕግ እንዲያወጡ ስለሚፈቅድ የተለያየ የሕፃን ትርጓሜ ሊኖር የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ በፌደራል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 215 መሠረት አካለ መጠን ያልደረሰ ሰው ማለት ጾታ ሳይለይ ዕድሜው አሥራ ስምንት ዓመት ያልሞላው ልጅ ነው፡፡
2. የህፃናት መብት መርሆዎች
ዓለም አቀፍ እና አገር አቀፍ ሕጎች የሕፃናት መብቶችን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል በማሰብ የተለያዩ መርሆዎችን አውጥተዋል፡፡ እነዚህ መርሆዎች የሕፃናት መብቶች ለማስከበር እና ማስተግበር ከፍተኛ አስተዋፅዖ አላቸው፡፡ ከእነዚህ መርሆዎች ዋነኛው የሆነው ለሕፃናት ጥቅምና ደህንነት ቅድሚያ መስጠት (Best interest of the child) የሚለው መርህ ነው፡፡ በዚህ ረገድ እ.ኤ.አ በ1959 የወጣው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሕፃናት መብቶች መግለጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕፃናት ጥቅም እና ደህንነት ቅድሚያ መስጠት የሚለውን መርህ አካቶ የወጣ ዓለም አቀፍ ሰነድ ነው፡፡ በመሆኑም ሕፃናት ነክ ውሳኔዎች ሲወሰኑ (ለምሳሌ ወላጆቻቸው የሚለያዩ ከሆነ ከማን ጋር መኖር እንዳለባቸው ሲወሰን) ውሳኔ ሰጭ አካላት ለሕፃናት ጥቅምና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት የሕግ ግዴታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተያያዘ ሁኔታ የኮንቬንሽኑ አራት ዋና ዋና መርሆዎች በሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን ውስጥ የተዘረዘሩትን ሌሎች መብቶች ለማስፈፀም እና ለመተርጎም የሚያገለግሉ ናቸው ፡፡
እነርሱም፣
• የእኩልነት መብት (The Non-discrimination clause) የኮንቬንሽኑ አንቀፅ 2
• ለህፃናት ጥቅምና ደህንነት ቅድሚያ መስጠት (The Best Interest of the Child) የኮንቬንሽኑ አንቀፅ 3)
• የመሳተፍ መብት (The Right to participation) ኮንቬንሽኑ አንቀፅ 12፣
• በሕይወት የመኖር እና የመልካም አስተዳደግ መብት (The Right to life, survival and development) የኮንቬንሽኑ አንቀፅ 6፣ ናቸው፡፡
3. መሰረታዊ የህፃናት መብቶች በኢትዮጵያ
የሀገራችን ህገ መንግስት ለህፃንነት ትርጉም ያልሰጠ ወይም የእድሜ ገደብ ያላስቀመጠ ቢሆንም የህፃናትን መብት ዝርዝር በአንቀፅ 36 ስር ደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት ማንኛውም ህፃን የሚከተሉት መብቶች አሉት፡-
1. በህይወት የመኖር መብት፣
2. ስምና ዜግነት የማግኘት መብት፣
3. ወላጆቹን ወይም በህግ የማሳደግ መብት ያላቸውን ሰዎች የማወቅና የእነሱንም እንክብካቤ የማግኘት መብት፣
4. ጉልበት ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፣ በትምህርት፣ በጤናውና በደህንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ስራዎች እንዲሰራ ያለመገደድ ወይም ከመስራት የመጠበቅ፣
5. በትምህርት ቤቶች ወይም በሕፃናት ማሳደጊያ ተቋሞች ውስጥ በአካሉ ከሚፈፀም ወይም ከጭካኔና ኢ-ሰብዓዊ ከሆነ ቅጣት ነፃ የመሆን መብት ናቸው፡፡
በተጨማሪም በህገ መንግስቱ እንደተደነገገው ህፃናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወሰዱበት ጊዜ በመንግስታዊ ወይም በግል በጎ አድራጎት ተቋሞች፣ በፍርድ ቤቶች፣ በአስተዳደር ባለስልጣኖች ወይም በህግ አውጪ አካላት የህፃናት ደህንነት በቀደምትነት መታሰብ አለበት፡፡ ወጣት አጥፊዎች በማረሚያ ወይም በመቋቋሚያ ተቋሞች የሚገኙ በመንግስት እርዳታ የሚያድጉ ወጣቶች በመንግስት ወይም በግል እጓለ ማውታን ተቋሞች (የህፃናት ማሳደጊያዎች) ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ከአዋቂዎች ተለይተው መያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ከጋብቻ ውጪ የተወለዱ ሕፃናት በጋብቻ ከተወላዱ ሕፃናት ጋር እኩል መብት አላቸው፡፡ እንዲሀም መንግስት ለእጓለ ማውታን ልዩ ጥበቃ እንደሚያደርግላቸው እና በጉዲፈቻ የሚያድጉበት ሥርዓት የሚያመቻቹና የሚያስፋፉ፣ ደህንነታቸውንና ትምህርታቸውን የሚያራምዱ ተቋሞች እንዲመሰረቱ እንደሚያበረታታ ይደነግጋል፡፡

በአጠቃላይ ህፃናት የሚከተሉት አለም አቀፍ መሰረታዊ መብች ሊጠበቁላቸው ይገባል፡፡
• የእኩልነት መብት:- በጾታ፣ በዘር፣ በጎሳ፣ በቋንቋ፣ በኢኮኖሚ አቋም፣ በብሔር ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት ወይም አድሎአዊ በሆነ በማንኛውም ሁኔታ ላይ በመመርኮዝ ልዩነቶች ሊደረጉ አይገባም፡፡
• መብላት እና መጠለያ የማግኘት መብት:- ሁሉም ልጆች ለትክክለኛው እድገታቸው አስፈላጊ የሆነውን ምግብ የማግኘት እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በሚኖሩበት ቤት የማግኘትና የመደሰት መብት አላቸው ፡፡
• የትምህርት መብቶች:- ሁሉም ልጆች ችሎታቸውን ለማዳበር እና የራሳቸውን የወደፊት ዕድል ለመፍጠር ትምህርት የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ምክንያቱም ለትክክለኛው ሥነ-ልቦናዊ፣ ስሜታዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገታቸው አስፈላጊ ነው፡፡
• የጤንነት መብት:- ልጆች ጤንነታቸውን ለመንከባከብ እና ለማቆየት እንዲሁም በሽታን ለመከላከል አስፈላጊ የሕክምና ክትትል እና እንክብካቤ ማግኘት አለባቸው፡፡ ወደ ጤናማ አዋቂዎች እንዲያድጉ ጥሩ ፈውስ የማግኘት መብት አላቸው፡፡
• በሕይወት የመኖር መብት፡- ሕፃናት ህይወታቸውን አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ ነገሮች የመጠበቅ እና የመትረፍ (right of protection and survival) መብት አላቸው፡፡ እንዲሁም በቂ የኑሮ ደረጃ (adequate standard of living) የማግኘት መብት አላቸው፡፡
በአጠቃላይ ህፃናት በተለይ በእድሜያቸው ምክንያት ለተለያዩ አደጋዎች የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ስለሆነ መንግስት በሂደት (progressively) የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በፈቀደ መጠን የህፃናትን ደህንነት ለማስጠበቅ የህፃናትን መብት ለማክበር፣ ለመጠበቅ እና ለማሟላት ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
በንቃተ ሕግ፣ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት
#አለ_ህግ
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
• የእኩልነት መብት:- በጾታ፣ በዘር፣ በጎሳ፣ በቋንቋ፣ በኢኮኖሚ አቋም፣ በብሔር ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት ወይም አድሎአዊ በሆነ በማንኛውም ሁኔታ ላይ በመመርኮዝ ልዩነቶች ሊደረጉ አይገባም፡፡
• መብላት እና መጠለያ የማግኘት መብት:- ሁሉም ልጆች ለትክክለኛው እድገታቸው አስፈላጊ የሆነውን ምግብ የማግኘት እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በሚኖሩበት ቤት የማግኘትና የመደሰት መብት አላቸው ፡፡
• የትምህርት መብቶች:- ሁሉም ልጆች ችሎታቸውን ለማዳበር እና የራሳቸውን የወደፊት ዕድል ለመፍጠር ትምህርት የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ምክንያቱም ለትክክለኛው ሥነ-ልቦናዊ፣ ስሜታዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገታቸው አስፈላጊ ነው፡፡
• የጤንነት መብት:- ልጆች ጤንነታቸውን ለመንከባከብ እና ለማቆየት እንዲሁም በሽታን ለመከላከል አስፈላጊ የሕክምና ክትትል እና እንክብካቤ ማግኘት አለባቸው፡፡ ወደ ጤናማ አዋቂዎች እንዲያድጉ ጥሩ ፈውስ የማግኘት መብት አላቸው፡፡
• በሕይወት የመኖር መብት፡- ሕፃናት ህይወታቸውን አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ ነገሮች የመጠበቅ እና የመትረፍ (right of protection and survival) መብት አላቸው፡፡ እንዲሁም በቂ የኑሮ ደረጃ (adequate standard of living) የማግኘት መብት አላቸው፡፡
በአጠቃላይ ህፃናት በተለይ በእድሜያቸው ምክንያት ለተለያዩ አደጋዎች የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ስለሆነ መንግስት በሂደት (progressively) የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በፈቀደ መጠን የህፃናትን ደህንነት ለማስጠበቅ የህፃናትን መብት ለማክበር፣ ለመጠበቅ እና ለማሟላት ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
በንቃተ ሕግ፣ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት
#አለ_ህግ
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
#አለ_ህግ
#አለ_ችሎት
#አለ_ስራ
#አለ_ዜና
#አለ_ትምህረት
#አለ_ልዩ ልዩ
......................
የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ክሶች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች 🔴ሁሉም ሕጎች በአንድ🔴 All in one, for All.
አለ_ህግ፣ መሰረታዊ የህግ መረጃ እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው።
contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.com
@lawsocieties

Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
trade 42.docx
43.2 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
trade.pdf
272.5 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
trade 42.docx
43.2 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
trade 4.pptx
118 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
Trade remedies.pptx
73.9 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
trade.pdf
272.5 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
trade 42.docx
43.2 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
trade 4.pptx
118 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
Trade remedies.pptx
73.9 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️
Law Of Traders & Bisness Organizations.pptx
408.1 KB