አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
LHR has organized a one and half days specialized capacity building training on the enforcement of socio-economic rights for practising lawyers at Azzeman Hotel, Addis Ababa.

Day-1
On the first day, the participants are discussing the legal nature and justifiability of Economic Social Cultural rights-ESC rights under international law and Ethiopian law as well as the model of adjudicator of ESC rights and experiences so far.

#socioeconomic #socioeconomicrights #socialjustices

#Ethiopia #HumanRight #HumanRightLawyers #LawyersforHumanRights #LHR
በሁለት ወር ተራዝሟል !

ብሔራዊ ባንክ ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ እንዲያሟሉ ተጨማሪ የሁለት ወር ጊዜ ሰጣቸው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፋይናንስ ውስጥ ያለውን ውንብድና ለመቆጣጠር ለባንኮች አዲስ የደንበኛ ማንነት እንዲያዘጋጁ ያስቀመጠውን የግዜ ገደብ ማራዘሙን ሰምተናል።

ምንጩ ያልታወቀና የህገወጥ ገንዘብ ለመከታተል ወይም በተጭበረበሩ ሰነዶች የሚገላበጠውን የገንዘብ ዝውውር ለማስቀረት ሁሉም ባንኮች ደንበኞቻቸው እነማን እንደሆኑ እንዲያጣሩ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ማውጣቱ ይታወሳል።

በዚሁ መሠረት ሁሉም የንግድ ባንኮች የደንበኞቻቸውን ማንነት እና ሙሉ መረጃ ጥንቅቅ አድርገው እንዲይዙ ብሔራዊ ባንክ ተጨማሪ የ2 ወር ቀነ ገደብ መስጠቱን ሰምተናል።

ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ ሰብስበውና አጣርተው ለማጠናቀቅ ብሔራዊ ባንክ የ ስድስት ወር ጊዜ ሰጥቷቸው ነበር።

የብሄራዊ ባንክ መመሪያ ደንበኞች ከሚሞሏቸው መረጃዎች ተጨማሪ ዝርዝር የደንበኛን መረጃ ጭምር እንዲጠየቁ ያስገድዳል።

ሁሉም የንግድ ባንኮች የውስጥ የደንበኛ መታወቂያ ካርድ እንዲያዘጋጁ ብሄራዊ ባንክ ማዘዙ ይታወሳል።

ሁሉም የንግድ ባንኮች ባንኮች መመሪያውን ለመተግበር ሲሞክሩ ቆይተዋል።

ሆኖም የተሰጠው ቀን ገደብ በመጠናቀቂያው ሰዓት ጥድፊያና ግርግር ታይቷል፡፡

በዚህም ምክንያት የብሔራዊ ባንክ ባንኮች የደንበኛቸውን መረጃ እንዲሰንዱ ተጨማሪ የሁለት ወር ግዜ መስጠቱን ሰምተናል። ShegerFM
የስንብት ክፍያ እና ካሳ እንደ ገቢ ይቆጠራሉ?

በሰ/መ/ቁ 61549 (አመልካች የኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን እና ተጠሪ ወ/ሮ ብርቄሣ አብራሂም ህዳር 6 ቀን 2004 ዓ.ም. ቅጽ 13) በተሰጠ የህግ ትርጉም ካሳና የስንብት ክፍያ የመክፈል ግዴታ የተጣለበት አሠሪ ክፍያውን ከመፈጸሙ በፊት የገቢ ግብር ቀንሶ ማስቀረት ይኖርበታል፡፡ ለአመልካች አቤቱታ መንስኤ የሆነው የሰበታ ሐዋሳ ወረዳ ፍ/ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር በነበራቸው የሥራ ክርክር እንዲከፈላቸው የተወሰነላቸው የስንብት ክፍያ፣ ካሳና ሌሎች ክፍያዎች ግብር ተቀናሽ ሳይደረግ አመልካች በደመወዛቸው በጥቅሉ አስቦ እንዲከፍላቸው ትዕዛዝ በመስጠቱ ሲሆን በትዕዛዙ ቅር በመሰኘት አመልካች ለዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበው ይግባኝ ተሰርዟል፡፡ በመቀጠል አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰ/ሰ/ችሎት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በመጨረሻ አመልካች ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/ሰ/ችሎት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ ትዕዛዙና ውሳኔዎቹ ተሽረዋል፡፡

አመልካች ለሰበር አቤቱታ መሰረት ያደረገው የገቢ ግብር አዋጅ ቁ. 286/94 እና የገቢ ግብር ደንብ ቁ. 78/1994 ሲሆን ችሎቱ የገቢ ግብር አዋጁን አንቀጽ 10 በመጥቀስ እንዳብራራው ማናቸውም ሰው በመቀጠር ከሚያገኘው ገቢ ግብር የመክፈል ኃላፊነት ያለበት ሲሆን ማናቸውም ቀጣሪም በሚከፍለው እያንዳንዱ ክፍያ ግብሩን የመቀነስና ለመንግስት ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ በተጨማሪም በገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 78/1994 አንቀጽ 13 ስር የገቢ ግብር እንደማይከፈልባቸው ከተዘረዘሩት ውስጥ የስንብት ክፍያ፣ካሳ እና ለተጠሪ ይከፈሉ የተባሉት ሌሎች ክፍያዎች ግብር እንደማይከፈልባቸው አልተደነገገም፡፡ ስለሆነም ተጠሪ ከተወሰኑላት ክፍያዎች ላይ የገቢ ግብር ተቀናሽ ሊደረግ ይገባል፡፡

ከካሳ እና ስንብት ክፍያ በተጨማሪ ሌሎች ከአሠሪና ሠራተኛ ህግ የሚመነጩ ክፍያዎችም የገቢ ግብር ይከፈልባቸዋል፡፡ በሰ/መ/ቁ 101040 /አመልካች ዳሽን ባንክ አክስዮን ማህበር እና ተጠሪ እነ አቶ ተፈሪ አሳልፈው ሚያዝያ 30 ቀን 2007 ዓ.ም. ቅጽ 18/ የሥራ ውል ሲቋረጥ በገንዘብ ተለውጦ በሚከፈለው የዓመት ፈቃድ ላይ እንዲሁም በሰ/መ/ቁ 65330 /አመልካች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ እነ አቶ ተክሌ ጋረደው (6 ሰዎች) ሰኔ 30 ቀን 2003 ዓ.ም. ቅጽ 11/ ለጡረታ ክፍያ የአገልግሎት ዘመን እና የዕድሜ መስፈርት የማያሟሉ የመንግስት ሠራተኞች ከሥራ ሲሰናበቱ ለመልሶ ማቋቋሚያ ድጋፍ እንዲውል በሚከፈላቸው ክፍያ ላይ የገቢ ግብር ተቀናሽ መደረግ እንዳለበት ተመልክቷል፡፡
#henoktayelawoffice


ሼር #Share @lawsocieties
🟩@lawsocieties
🟨@lawsocieties
🟥@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#የፌዴራል የጥብቅና ፈቃድ በፈተና ማውጣት ለምትፈልጉ #እንዳያልፋችሁ ከመጋቢት 05/2014 እስከ መጋቢት 16/2014 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል!!


ሼር #Share @lawsocieties
🟩@lawsocieties
🟨@lawsocieties
🟥@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
Happening right now...
LHR has organized a one and half days specialized capacity building training on the enforcement of socio-economic rights for practising lawyers at Azzeman Hotel, Addis Ababa.

Day-2
The participants continue to discuss in detail the protection of economic, social and cultural rights in the Ethiopian legal system. The protection of economic social cultural rights jurisprudence in Ethiopia and share their experiences on the topic. They also discuss the steps lawyers have to take to protect these groups of rights.


ሼር #Share @lawsocieties
🟩@lawsocieties
🟨@lawsocieties
🟥@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
🟢🟡🔴 ማስታወቂያ
የጥብቅና ፈቃድ ለማውጣት ለምትፈልጉ በሙሉ❗️❗️

የፌዴራል የጀመሪያ ደረዳ ፍ ቤት የጥብቅና ፈቃድ በፈተና ለማግኘ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮያዊ መመዝገብ የሚችል መሆኑን እንገልፃለን።

1. እውቅና ካለው _ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምርት ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ እና በህግ መያ ቢያንስ ሶስት (3) ዓመት ወይም በሕግ ዲኘሎማ የተመረቀና በሕግ ሙያ አምስት (5) ዓመት የሥራ ልምድ ያለው፣

2 ከኢትዮጵያ ውጪ ካለ ከፍተኛ የትምህርት ቋም በሕግ የመመሪያ ዲግሪ ያለውና በኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ ሙያ ለአምስት (5) ዓመት የሰራ፣

3. hሚሰራበት ተቋም የመልካም ስነ-ምግባር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ 4. በመጨረሻ ጊዜ ይሰራበት ክነበረበት ተቋም ተቋሙን ከለቀቀበት ጊዜ በፊት ባሉት 2 አመታት ዉስጥ በከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት ያልተቀጣ፣
5. የመመዝገቢያ 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/
6. የታደሰ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ

7. የትምህርትና "ሥራ ልምድ : ማስረጃ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ፣
8. ከግል መ/ቤት የሚቀርብ የሥራ ለምድ ግብር የከፈለበት ስለመሆኑ፣
9. በአማርኛ ያልተፃፉ ማንኛውም የሚቀርቡ ማረጃዎች በአማርኛ ተተርጉመው አንድ ላይ ማቅረብ፣
10.አዲሱ የትምህርት ፖሊስ በህግ ዲሎማ የተመረቀ ከሆነ የብቃት ማረጋገጫ ምዘና COC ተፈትኖ ያላፈበትን ውጤት ማቅረብ አለበት

ማሳሰቢያ፦

❖ የመመዝገቢያ ቀን መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ ም እስh መጋቢት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት፣
❖ የመመዝገቢያ ቦታ- ባንቢስ/ኡራኤል ቤተክርቲያን አካባቢ ፍትህ ሚኒስቴር ሕንፃ ጠበቆች አተዳደር ቢሮ 2ኛ ፎቅ
❖ የፈተና ኮድ የሚሰጥብት ቀን ከመጋቢት 15 እስከ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ጠበቆች አስተዳደር ቢሮ 2ኛ ፎት፣

* ፈተና የሚስጥበተ ቀንና ቦታ-መጋቢት 17 ቀን 2014 ዓ ም ከጥዋቱ 3.00 ሰአት ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን, ህንፃ አዳራሽ ውስጥ ይሆናል።

የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር

ሼር #Share @lawsocieties
🟩@lawsocieties
🟨@lawsocieties
🟥@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties