አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የተለያዩ ሀገራት የኢኮኖሚ አሻጥር መፈፀምን በግልፅ ወንጀል አድርገው የደነገጉ ሲሆን /ለአብነት አውስትራሊያ እና ፊሊፒንስ/ አንዳንድ ሀገራት ደግሞ የኢኮኖሚ አሻጥርን በጥቅሉ ሳይሆን የኢኮኖሚ አሻጥር ለመፈፀም የሚረዱ ተግባራቶችን በመለየት ወንጀል ሲያደርጓቸው ይስተዋላል፡፡
ከሀገራችን አንፃር ህግ አውጪው ሁለተኛውን አማራጭ የተከተለ ይመስላል፡፡ የኢፌደሪ የወንጀል ህግ ርዕስ 4 ምእራፍ አንድ ከአንቀፅ 343 ጀምሮ በተከታዮቹ ድንጋጌዎች በመንግስት የኢኮኖሚ እና የገንዘብ ጥቅሞች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች የተዘረዘሩ ሲሆን የኢኮኖሚ አሻጥር ወንጀል ሆኖ አልተደነገገም፡፡ በልዩ ህጎችም የኢኮኖሚ አሻጥርን ወንጀል አድርጎ የደነገገ ልዩ ህግ የለም፡፡ ይህ ማለት ግን ተግባሩ የተፈቀደ ነው ማለት አይደለም ከወንጀል ህጉ ጀምሮ በተለያዩ ልዩ ህጎች ውስጥ የኢኮኖሚ አሻጥር ለመፈፀም ያስችላሉ የተባሉ ተግባራቶች ወንጀል ተደርገው ይገኛል ለአብነት፡- የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 913/2006 አንቀፅ 43/4/ በገበያ ላይ እጥረት ያለባቸውን መሰረታዊ ምርቶች ማከማቸት ወንጀል እንደሆነ ይደነግጋል፣ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 168/1/ ኮንትሮባንድ ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል፣ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 446 ተከታዮቹ እንዲሁም በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/200 መሰረት በውጪ ምንዛሪ መነገድ፣ ያለፈቃድ መያዝ እና መጠቀም ወንጀል ተደርጓል፡፡

ይህም በመሆኑ የኢኮኖሚ አሻጥር ያልተከለከለ ተግባር ነው ተብሎ ሊወሰድ የሚችል አይደለም፡፡

ሲጠቃለል ኢኮኖሚ ብቻውን የሚቆም ሳይሆን ከማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ነው፡፡ የኢኮኖሚ አሻጥር በግለሰቦች ላይ ከሚያመጣው ማህበራዊ ቀውስ አንስቶ በመንግስት ላይ የሚያስከትለው ፖለቲካዊ መናጋት እና አለመረጋጋት ከፍተኛ ነው ህጋዊ ነጋዴውም ነግዶ ለማትረፍ ጠንካራ የመግዛት አቅም ያለው ማህበረሰብ እና የተረጋጋ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ስርዓት የሰፈነባት ሀገር ይሻል፡፡ ስለሆነም መንግስት እንደመንግስት ጥብቅ የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ኢኮኖሚውን ሊጠበቅ እና አሻጥረኞችንም ለህግ ማቅረብ የግዴታዎቹ ሁሉ ዋነኛ አድርጎ ሊሰራበት ይገባል በሌላ በኩል ህዝቡ እና የንግድ ማህበረሰቡ እንደ-አንድ የድርጊቱ ሰለባ የኢኮኖሚ አሻር የሚፈፅሙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ባለመተባበር እና ፈፃሚዎቹ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንዲቻል ተገቢውን ጥቆማ ለህግ አካላት በመስጠት የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊወጣ ይገባል፡፡
Legal Advocate

Hagbes Private Limited Company

Addis Ababa
Full–time

Legal Advocate Job Description: Job Requirements: At least five(5) years of related preferable experience in labor, civil and criminal court litigation .
How To Apply:
Interested and qualified applicants can apply through until January 3,2022. Posted:12.28.2021 Deadline:01.03.2022 Job Category:Legal Employment:Full time Location:Addis Ababa, Addis Ababa
ጋብቻ በሚፈርስበት ወቅት የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ሥነ-ሥርዓት ከሰበር ውሳኔዎች ጋር ተገናዝቦ የቀረበ

በ፡ ሙሉቀን ሰይድ

በዚህ አጭር ጽሁፍ የጋራ ንብረት ክፍፍልን በተመለከተ አከራካሪ ከሆኑ ጉዳዩች መካከል የትኞቹ ንብረቶች የተጋቢዎቹ የጋራ ንብረት ይባላሉ፤ ተጋቢዎቹስ ምን ያህል ምጣኔ ድርሻ በንብረቶቹ ላይ ይኖራቸዋል፤ የጋር ንብረት ክፍፍል ጥያቄስ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ሊቀርብ ይገባዋል የሚሉ ነጥቦችን የፌዴራሉ የቤተሰብ ህግ እና ከተመረጡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ውሳኔ አንጻር ዳሰሳ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2018-procedures-of-partition-of-common-property-after-divorce
የንግድ ሥራ የመስራት መብት
----------------------------

1. መግቢያ
በኢትዮጵያ ዉስጥ ግለሰብ ነጋዴዎችም ሆኑ የንግድ ማኅበራት ማንኛዉንም የንግድ ሥራ ለማካሄድ ተመዝግበዉና የንግድ ሥራ ፈቃድ ወስደዉ መሆን እንዳለበት በህግ ተደንጓል (አዋጅ ቁጥር 980/2008 ዓ.ም ከነ ማሻሻያ አዋጁ 1150/2011 ዓ.ም)፡፡ በተጨማሪም የንግድ ስም ፣ የኢንቨስትመንት ፈቃድ እና ሌሎች የንግድ የንግድ ሥራ ለመስራት የሚያስፈልጉ ጉዳዮች ተሟልተዉ መሆን አለበት፡፡ ይህ አጭር ጽሁፍ የንግድ ሥራ የመስራት መብት በመያየዝ ዋና ዋና ሀሳቦችን ለማስጨበጥ የሚሞከርበት ሲሆን እነርሱም የንግድ ሥራ በጠቅላላዉ፤ የንግድ ሥራ ምንነት፣የንግድ ሥራ የመስራት መብት ከህገ መንግስቱ እና ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች አንፃር፣የንግድ ሥራን የመስራት ነፃነትና መብት እና መሰረታዊ የንግድ ሥነ-ምግባር መርሆች ላይ ይሆናሉ፡፡

2. የንግድ ሥራ በጠቅላላዉ
ግለሰብ ወይም ግለሰቦች በተናጠልም ሆነ በመደራጀት ኑሮን ለማሸነፍ፣ ሀብት ለማካበት፣ ለመበልጸግና ደስተኛ ሆኖ ለመኖር የተለያዩ የንግድ ድርጅቶችን በማቋቋም የንግድ ሥራ ይሰራሉ፡፡ ስኬታማ የሆነ የንግድ እንቅስቃሴ የንግድ ሥራ በመጀመሩ ብቻ ሳይሆን የተፈጠረዉ ስራ የሚገዛበትን፣ የሚመራበትን መሠረታዊ የሆኑ የንግድ መስፈርቶች / Elements / የንግድ ህግንና የንግድ ሥነ-ምግባርን ማወቅ ወይም መረዳት ሲቻል ነዉ፡፡ የንግድ ሥራ ከሀገሮች ዕድገት ጋር በእጅጉ የተሳሰረ ነዉ፡፡ የትስስሩ ሰንሰለት የሚጀምረዉ በግለሰብ ደረጃ ንግድን ከማካሄድ ሲሆን በተደራጀ መልክ እስከ ማስኬድ ድረስ ነዉ፡፡ ይህ አሁን ላሉት በግለሰብ ብቻ ሳይሆን በንግድ ማኅበራትና ኩባንያዎችን ለመስራትም መሠረት ነዉ፡፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲሱ የንግድ ህግ ዉስጥ በርከት ያሉ ስራዎችን በማቀፍና ካፒታል በማሰባሰብ በግለሰብ ደረጃም ሆነ በባለአክስዮኖች በሚመሰረቱ የንግድ ማኅበራት የወደደዉና የፈቀደዉን የንግድ ሥራ የመስራት መብት አለዉ፡፡ ማንኛዉም ሰዉ ግለሰብ ወይም ድርጅት (ማኅበር) በህግ ካልተከለከለ ወይም ተገቢ ያልሆነ የንግድ ዉድድር ሥራ በስተቀር የመረጠዉን ሕጋዊ የሆነዉን ማንኛዉንም የንግድ ሥራ የመስራት መብት አለዉ፡፡ አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ህግ አንቀጽ 22 ላይ በተገለፀዉ መሰረት ሀሳቡን ያጠናክረዋል፡፡

3. የንግድ ሥራ ምንነት
ንግድ ማለት ትርፍ ለማግኘት ሲባል የሚንቀሳቀሱም ሆነ የማይንቀሳቀሱ ነገሮችን አምርቶ ወይም ገዝቶ የመሸጥና የመለወጥ ሂደት ነዉ፡፡ የተለያዩ የቴክኒካል አገልገሎቶችን እና ሙያዊ አገልግሎቶችን ለአገልግሎት ፈላጊዎች የመስጠት ሂደትንም ይጨምራል፡፡ ይሁን እንጂ ማንኛዉም ግዥና ሽያጭ ንግድ አይደለም፡፡ የንግድ ስራ ተከናዉኗል ለማለት ሽያጭ እና ግዢዉ በቋሚነት እና በድግግሞሽ የሚከናወን መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ላይ ንግድ እና ነጋዴ ሚለዉን ማየቱ ተገቢ ነዉ፡፡ ንግድ ማለት የሰዉ ልጅ ፍላጎትና ምኞትን ለማሟላት፣የኑሮ ደረጃዉን ከፍ ለማድረግና ከንግድ እንቅስቀሴዉም ትርፍ ለማግኘት፣ ምርት ለማቅረብና አገልግሎት ለመስጠት የሚደረግ ማንኛዉም እንቅስቃሴ ነዉ፡፡ ከዚህ የምንረዳዉ የንግድ ሥራ ትርፍ ለማግኘት ሲባል የተለያዩ ምርቶችን ወይም ዕቃዎችን የመግዛትና የመሸጥ ወይም የተለያዩ የሙያ አገልግሎቶችን የመስጠት ሂደት መሆኑን ነዉ፡፡ በመሆኑም የንግድ ሥራ ማለት ነጋዴ የሚሰራዉ ማንኛዉንም ሥራ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 980/2008 ዓ.ም አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 3 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ለንግድ ዓላማ እየተዘጋጁ የሚሸጡ ማናቸዉም ዕቀዎችም ሆኑ ትርፍ ለማግኘት ሲባል ለአገልግሎት ፈላጊዎች የሚሰጡ ቴክኒካዊ (ሙያዊ) አገልግሎቶች በሕግና በንግድ ሥነ-ምግባር መግዛት አለባቸዉ፡፡ ለዚህም ዋናዉ ነጋዴዉ ነዉ፡፡ የንግድ ምዝገባና ሥራ ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ን ለማሻሻል ተደንግጎ በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1150/2011 ዓ.ም ነጋዴ ማለት ንግድን የሙያ ሥራዉ አድርጎ ተገቢ ጥቅም ለማግኘት በንግድ ህጉ እና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራ ፈቃድ መስጫ መደብ የተዘረዘሩትን ማንኛዉንም ስራዎች የሚሰራ የሚል ነዉ፡፡ በአዲሱ የኢትዮጵያ የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243 /2013 ዓ.ም አንቀጽ 5 ላይ የተዘረዘሩትን ሥራዎች የሚሰራ ወይም አገልግሎት የሚሰጥ የንግድ ሥራ ነዉ ተብሎ በሕግ የተደነገገዉን ሥራ የሚሰራ ማንኛዉም ሰዉ ነዉ ተብሎ ተተርጉሟል፡፡ በአደጉ ሀገራት ያሉት የንግድ መህበረሰቦች ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን የመሸጥ ሥራን እንደ መሠረታዊ የንግድ እንቀስቀሴአቸዉ ያደርጉታል፡፡ ለምሳሌ እ.ኤ.አ በ2001 ብቻ በአሜሪካ 10 ትሪሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ያላቸዉ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ተሸጠዋል፡፡ በሌሎች ያደጉና በማደግ ላይ በሚገኙ የዓለማችን አገራትም ዕቃዎችና አገልግሎቶች እንደዚሁ ይሸጣሉ፡፡

4. የንግድ ሥራ የመስራት መብት ከህገ መንግስቱ እና ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች አንፃር
ማንም ሰዉ ሥራ የመስራት፣ሥራዉን በነፃነት የመምረጥ፣በትክክለኛና በአመቺ የሥራ ሁኔታ ዉስጥ የመሥራትና ከሥራ አጥነት የመዳን መብት ያለዉ መሆኑን የሰብአዊ መብቶች ሁሉ አቀፍ መግለጫ (1948) አንቀጽ 23 (1) ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የኢኮኖሚ፣የማኅበራዊና የባሕላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን (1966) በክፍል ሶስት አንቀጽ 6 የመሥራት መብት ማንኛዉም ሰዉ በነፃ ፈቃዱ የመረጠዉን ወይም የተቀበለዉን ሥራ ሰርቶ ሕይወቱን ለመምራት እንዲችል ዕድል መስጠትን ይጨምራል በማለት አስፍሯል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 41 ላይ ግልጽ በሆነ በማያሻማ ሁኔታ የኢኮኖሚ የማኅበራዊና የባሕል መብቶች በሚለዉ ስር፡-
• ማንኛዉም ኢትጵያዊ በሀገሪቱ ዉስጥ በማንኛዉም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመሰማራትና ለመተዳደሪያዉ የመረጠዉን ስራ የመሥራት መብት አለዉ በሚል እና
• ሁሉም ኢትዮጵያዊ መተዳደሪያዉን ሥራዉንና ሙያዉን የመምረጥ መብት አለዉ በማለት ተደንግጎ ይገኛል፡፡
በመሆኑም የንግድ ሥራ እንደሌሎች ሥራዎች ሁሉ የንግድ ሥራ ለመስራት የፈለገ እና ለንግድ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በማሟላት ለሕግና ለሞራል የማይቃረኑ የንግድ ሥራዎች በመሰመራት የሚሰራ ሥራ መሆኑ በዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ህጎች መሰረት ያለዉ ነዉ፡፡
5. የንግድ ሥራን የመስራት ነፃነትና መብት
በህግ ተለይተዉ የተከለከሉ ነገሮች ወይም ተገቢ ያልሆነ የንግድ ዉድድርን የሚመለከቱ ክልከላዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ማንኛዉም ሰዉ ማንኛዉንም የንግድ ሥራ የመስራት ነፃነት እንዳለዉ በአዲሱ የኢትዮጵያ የንግድ ህግ አንቀጽ 21 ተደንግጎ የሚገኝ ሲሆን ይህ የተሰጠዉ ለሀገር ዉስጥ ነጋዴዎች ነዉ፡፡ በዉጭ ሀገር ስለተቋቋመ ወይም በዉጭ ሀገር ስለሚሰራ ማኅበርና ሀገር ዉስጥ ተመስርቶ በዉጭ ሀገር ስለሚቋቋም ቅርንጫፍ በአዲሱ ንግድ ሕግ አንቀጽ 579 ላይ የዉጭ ሀገር የግል ድርጅት፣ የንግድ ማኅበር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ድርጅት ኢትዮጵያ ዉስጥ ቅርንጫፍ ከፍቶ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዉስጥ የመሳተፍ መብት አላቸዉ፡፡ ሆኖም መጀመሪያ በንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወይም በሌላ አግባብ ያለዉ የባለስልጣን መስሪያቤት በሚያዘዉ የንግድ መዝገብ ዉስጥ መመዘገብ ያለበት መሆኑም ተገልጿል፡፡
6. መሰረታዊ የንግድ ሥነ-ምግባር መርሆች
መርህ / Principle / ማለት የሰዎች ድርጊቶችን የሚገዛ ሰዎች የተለያዩ የንግድም ሆነ ማንኛዉም ድርጊቶች በሚፈጽሙበት ጊዜ የሚመሩበትና ሚያከብሩት ደንብ ነዉ፡፡ ንግድ ሰፊና መሠረታዊ የወቅቱ የሰዉ ልጅ እንቅስቃሴ አካል፣ የኢኮኖሚ ዘርፍና የኅሊና ጉዳይም እየሆነ የመጣ እንቅስቃሴ በመሆኑ በንግድ ሥነ-ምግባር መገዛት አለበት፡፡ የንግድ ሥነ-ምግባር መርሆች የሚባሉት ፡-
1ኛ. ልዩነቶችን የማስወገድ መርህ፣
2ኛ. የደንበኖች ፍላጎትን የመጠበቅ መርህ፣
3ኛ. በንግድ እንቀስቃሴ ግልፅነትን የማበሰር መርህ፣
4ኛ. የምርቶች ደህንነትን የመጠበቅ መርህ
5ኛ. የአገልግሎት ደኅንነት መርህ፣
6ኛ. ሙስናን የማሰወገድ መርህ
7ኛ. የዉጭ ኢንቨስተሮችን የመሳብ መርህ
8ኛ. አገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት የማብሰር መርህ
9ኛ. የአከባቢ ደኅንነት የመጠበቅ መርህ
10ኛ. አግባቢነት ያለዉ ንግድ ዉድድርን የማብሰር መርህ የሚሉት ናቸዉ፡፡
በአጠቃላይ በህግ ያልተከለከሉና የተፈቀዱ የንግድ ሥራዎችን የሚሰራ ሰዉ ነጋዴ የሚባልና የነጋዴ መብቶች ያሉት ሲሆን ጎን ለጎን ደግሞ የነጋዴ ግዴታዎችንም ማክበር ይኖርበታል፡፡ ንግድ ሶስት ሰዎችን በቤተሰብነት አቅፎ ይዟል፡፡ አነዚህም የንግዱ ማኅበረሰብ፣ የንግዱ ተጠቃሚ ማኅበረሰብና መንግስት ናቸዉ፡፡ ስለዚህ የንግዱ ማኅበረሰብ (ነጋዴዎች) ንግዳቸዉን ለማካሄድና ስኬታማ መሆን የሚችሉት የደንብኞችንና የመንግስት ፍላጎትና ጥቅምን ማክበር ሲችሉ ነዉ፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
Senior Legal Officer

African Union

Addis Ababa
Full–time

[ad_1] Position description The Senior Legal Officer reports to the Deputy Director, Africa CDC and technically to the African Union Office of Legal Council (AU-OLC). Working in close collaboration with the AU-OLC, the incumbent shall provide legal advisory services to staff of the Africa CDC Secretariat, Regional Collaborating Centres (RCC) and National Public Health Institutes (NPHI) Main Functions • Provide technical support in the preparation and implementation of programmes developed out of Africa CDC’s strategic plan; • Ensure effective coordination and implementation at various levels; • Liaise with Member States, Regional Economic Communities (RECs), and other stakeholders on relevant matters; • Prepare and develop reports, budget and work programmes related to the functioning of the Office; • Provide technical support for the development of resource mobilization strategy with stakeholders coordination; • Manage and supervise employees under his/her supervision with regard to organization and performance evaluation; • Conduct complex analysis and generate accurate reports in a timely manner for Africa CDC’S and AU’s internal use; • Liaise with the various Departments/Units of the Commission for coordination and alignment purposes; • Participate in preparation of budgets for the Office in accordance with relevant frameworks. Support the promotion of the activities of the Africa CDC including preparing leaflets, guidelines and fact sheets as may be required; • Actively contribute in the development of strategies, policies, programmes and plans. Specific Responsibilities • Draft or assist in the drafting of legal texts and memoranda ensure that the interests of the Africa CDC are protected and ideals of the African Union are not compromised and offer advice on issues and disputes that may arise from their application; • Provide legal services to Africa CDC to ensure legality in decision-making and compliance with the AU rules and regulations; • Liaise with relevant Africa CDC divisions and assist in drafting and validating Legal frameworks; • Conduct legal research and proffer legal opinions on matters raised by Africa CDC; • Draft and review host agreements between the AU/Africa CDC and Regional Collaborating Centres; • Review and assist in drafting administrative contracts and agreements such as Memorandums of Understanding, Grant Agreements, Letters of Agreements, contracts of engagement of personnel, consultants and contracts awarded for the procurement of goods or services; • Participate in meetings of relevant legal nature on behalf of Africa CDC; • Advise on Legal Issues relating to conflict prevention, management and resolution; • Serve as focal point between Africa CDC and Office of the Legal Counsel; • Provide legal advice on the interpretation of legal texts relating to administrative and institutional matters; • Liaise with the Office of the Legal Counsel in negotiating Agreements where Africa CDC is a party; • Follow up agreements with partners as well as with the Office of the Legal Counsel; • Perform any other relevant functions as may be assigned by the Supervisor.
Qualifications • University Master’s Degree in Law with emphasis in the area of Global Health Law, Public Health Law, Public International Law, Administrative Law, Labor Law or equivalent with seven (7) years of relevant work experience out of which three (3) at a expert level in a legal position within an academic institution, a government or international organization; OR • University Bachelor Degree in Law with emphasis in the area of Public International Law, Administrative Law, Labor Law or equivalent with at least ten (10) years of relevant work experience out of which three (3) years of relevant work experience should be at a expert level in a legal position within an academic institution, a government or international organization..; • Relevant work experience refers to a progressively responsible experience in legal practice or related area, at least one of which should
be in an international setting. More specifically, the candidate should be experienced in the provision of legal advisory services in an organization dealing with multilateral issues, Ministries of Health/Departments of Justice/International Affairs or Cooperation of Member States, or such other relevant organizations and institutions; • Experience in providing legal advice and counsel to public health or related public sector programmes, of which 3 years at a specialist/expertise level. Required Skills Functional Skills • Knowledge of legal policies, practices and procedures and ability to apply them in an organizational setting; • Ability to identify issues, formulate opinions, make conclusions and recommendations in individual and team setting; • Demonstrable skills in issue identification, opinion formulation, and in documenting conclusions and recommendations; • Demonstrable legal writing skills and other writing skills to prepare responses for inquiries, reports, proposals, etc.; • Excellent organizational and time-management skills; • General knowledge of office administrative support procedures and processes; • Knowledge of interpersonal relationship practices to meet and deal with persons of diverse backgrounds; • Demonstrated ability with regard to computer skills, including excellent word-processing capabilities, proficiency with e-mail and internet applications and experience in using office software applications such as MS Excel, Power Point and Word; • Proficiency in one of the African Union working languages (Arabic, English, French, Portuguese or Spanish) is required. Knowledge of one or more of the other AU working languages would be an added advantage. Personal Abilities • Ability to work under pressure, stay on track and meet deadlines; • Analytical and problem solving abilities; • Proven ability to use clear, concise language in correspondence as well as including content fitting for the purpose and audiences when preparing written briefs and reports; • Adaptive, patient, resourceful, resilient and flexible; • Pro-active and solutions oriented. Application instructions Please be sure to indicate that you saw this position on ngotenders.net Apply Now To help us track our recruitment effort, please indicate in your email/cover letter where (ngotenders.net) you saw this job posting
African Union❗️
የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ/ ለፌዴራል ጠበቆች በሙሉ

በፌዴራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 መሰረት የጠበቆች ማህበር የተቋቋመ ሲሆን፣ ማህበሩን ስራ ከማስጀመር አንፃር የማህበሩን የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤ የሚጠራው ፍትሀ ሚኒስቴር መሆኑን በአዋጁ አንቀፅ 59 (1) ላይ ተመልክቷል፡፡

በዚሁ መሰረት ከፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር እና ከኢትዮጵያ ጠበቆች ማህበር የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች የተካተቱባቸው አብይ እና ንዑሳን ኮሚቴዎች ተዋቅረው የማህበሩን የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድና ማህበሩን ስራ ለማስጀመር የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን በዚሁ አግባብ የማህበሩ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባዔው ጥር 8 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ 24 ቀበሌ በሚገኘው ኮከብ አዳራሽ ይካሂዳል፡፡

በአዋጁ አንቀፅ 52(3) መሰረት ማኅበሩ ሁሉንም የፈዴራል ጥብቅና ፍቃድ የተሰጣቸውን ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች በአባልነት ያቀፈ በመሆኑ ማናቸውም የፌዴራል ጥብቅና ፈቃድ ያላችሁ ጠበቆችና የጥብቅና ድርጅቶች በጉባኤው ላይ እንድትሳተፉ ይህ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን፣ ጉባኤው የተሳታፊዎች ቁጥር ግምት ውስጥ ሳይገባ በጉባኤው ላይ በተገኙ አባላት የሚካሄድና የተለያዩ ውሳኔዎችን የሚያሳልፍ በመሆኑና ይህም ውሳኔ በሁሉም የፌዴራል ጥበቅና ፈቃድ ባላቸው የህግ ባለሙያዎችና የጥብቅና ድርጀቶች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን በመሆኑ፣ ይህንን ተገንዝባችሁ በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ እንድትሳተፉ ፍትህ ሚኒስቴር ጥሪውን ያቀርባል::
....በዚህ ጉባዔ ላይ የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ አባላት እንዲሁም የማህበሩ ፕሬዘዳንት እና ምክትል ፕሬዘዳንት የሚመረጡ ሲሆን ሌሎችም ክንውኖች የሚካሄዱ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር
#እቁብን_ከሕግ_አንፃር

በሀገራችን እቁብ በእጅጉ የተለመደ ባህላዊ የቁጠባ ዘዴ ነው።ይህ ባህላዊ የቁጠባ ዘዴ በየመንደሩ፣ በየአካባቢው የዳበረ መሆኑን በምሳሌያዊ አነጋገራችን ጭምር ሰውን ሰው ያሰኘው እቁብ ነው በሚል ዳብሮ እቁብ በመግባት እና በመቆጠብ የብርን መብረር መገደብ እንደሚቻል በማህበረሰባችን ዳብሮ እቁብ በቁጥር የተወሰኑ ሰዎች ስምምነት በማድረግና ለስምምነቱም ተገዢ በመሆን በቡድን ሆነው በተወሰነ ጊዜ የተወሰነ የገንዘብ መጠን በመሰብሰብ በየዙሩ የተሰበሰበውን ገንዘብ ስምምነት ያደረጉት ሰዎች በየተራ የሚወስዱበት ባህላዊ የቁጠባ ማህበር ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

ከባንክ ወይም ከሌሎች የቁጠባ ማህበራት የሚለይበት በብዙ ነገሮች ሲሆን በተደራጀ ተቋማት የሚካሄድ ባለመሆኑ፣ ዘመናዊና የተደራጀ አሰራርን የማይከተል፣ ወለድ የማይከፈልበት፣የሚመራበት ሕግ ወይም ተቆጣጣሪ አካል ወይም በህግ የታወቀ መብትና ግዴታዎችን መቀበል የሚያስችል ሕጋዊ ሰውነት የሌለው ማህበር ነው።

በሕጋችን እቁብን በሚመለከት የተቀመጠ የተለየ የህግ ማእቀፍና ድንጋጌ የለም። እቁብ ከሁለት በላይ የተሰበሰቡ ሰዎችን የሚይዝ ማህበር ቢሆንም እንደ ማህበር ተመዝግቦ እውቅና ሊያገኝ እንደማይችል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀፅ 3(3) (ለ) መሰረት አዋጁ በዕድር፣ ዕቁብና መሰል ባሕላዊ ስብስቦች ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን ተደንግጓል። በፍትሀ ብሔር ሕጉ የማህበራት ድንጋጌ መሰረትም መዝግቦ ለእቁብ እውቅና የሚሰጥ አካልም ስለሌለ እቁቦች ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ማህበራት ስላልሆኑ ሊከሱ ሊከሰሱ አይችሉም።

ነገር ግን እቁብተኞች የገቡት የውል ስምምነት አለ።የተወሰነውን ገንዘብ በየጊዜው በመክፈል በእጣ ወይም በስምምነነት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የተስማሙበትን ገንዘብ እንዲከፈላቸው ተስማምተዋል። ይህም በአባላቱ መካከል በተደረገው የውል ስምምነት መሰረት አባላቱ መዋጣት ያለባቸውን ግዴታ ማለትም የእቁብ ገንዘቡን የመክፈል እቁብ ወጥቶላቸው ገንዘብ የወሰዱ ከሆነም የወሰዱትን የእቁብ ገንዘብ ሙሉ እስኪመለስ ድረስ ገንዘቡን የመክፈል ግዴታ ያለባቸው ናቸው፡፡ይሄም ግዴታ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1678 እና 1731 (1) መሰረት በህጉ አግባብ የተቋቋሙ ውሎች ባቋቋሟቸው ሰዎች ላይ ህግ ናቸው በሚለው መሠረታዊ ከውል ህግ መሰረት ይመነጫል፡፡ በመሆኑም ግዴታዎች ይፈጠራሉ። የእቁብ ገንዘብ የበሉ ሰዎች የሚቀርባቸውን ክፍያ የመክፈል ግዴታ አለባቸው። ሰብሳቢው ከሌላው አባል በመሰረቱ የተለየ ግዴታ እና መብት የለውም መክንያቱም ሕጋዊ ሰውነት የሌለው ማህበር በመሆኑ ነው። ነገር ግን በዉላቸው ሰብሳቢው ከሌላው አባል የተለየ መብት እና ግዴታ እንዳለበት በውላቸው ካረጋገጡ ሰብሳቢውን ይሄንኑ ውል መሰረት በማድረግ መጠየቅ ይችላል።

ሌላው የእቁብተኞቹን ግዴታና መብቶች በፅሁፍ እንዲሆኑ የሚያስገድድ ሕግ ባይኖርም በፅሁፍ እንዲደረግ ይመከራል። የፅሁፉም ጥቅም በምን ያህል ጊዜ የእቁቡ ገንዘብ መከፈል እንዳለበት፣ ሳይከፈል ቢቀር ሀላፊነቱን ማን እንደሚወስድ፣ አባላት ከእቁቡ መውጣት ስለሚችሉበት ሁናቴ፣የከፈሉት ገንዘብ ተመላሽ መሆን አለመሆኑ ቀሪ ገንዘብ የመክፈል ግዴታን በተመለከተ አባላት ሊገደዱ የሚችሉት በግልፅ የሰጡትን ስምምነት መሰረት በማድረግ ወደፊት ለሚነሱ የህግ ክርክሮች እንደ ማስረጃ ያገለግላል።

በመጨረሻም የእቁብ ገንዘብ የበሉ ሰዎች ቀሪ ክፍያ ስለመክፈላቸው በፍታብሄር ህጋችን ከአንቀጽ 1920 ጀምሮ የተደነገጉትን አግባብነት ያላቸው የዋስትና ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የአንድነት አና የነጠላ ዋስትና በፅሁፍ፣ምስክሮች ባሉበት የገንዘቡ መጠን ተገልፆ ዋሶችን ማስፈረሙ በተለያየ ምክንያት እቁብ የበሉ ሰዎች ሲጠፉ ዋሱን ለመጠየቅ ስለሚረዳ በዚሁ አግባብ ማከናወን ይገባል።

ባጠቃላይ ወደፊት የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ የእቁብተኞቹን መብትና ግዴታ የሚደነግግ ዝርዝር የውል ስምምነት ቢኖራቸው ይሄም ስምምነት ሁሉም እቁብተኞች በፊርማቸው እንዲያረጋግጡት ስንል እንመክራለን።
መልካም ቀን።
በማስረሻ የሺጥላ
ጠበቃ HenokTayeLawoffice
https://t.me/lawsocieties
#በአዲስ_አበባ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጣለ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ጥሏል፡፡

ቢሮው በመዲናዋ በሞተር ብስክሌት ምክንያት የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችንና ህገ ወጥ ድርጊቶችን መከላከል የሚያስችል የሞተር ብስክሌት ፈቃድና ቁጥጥር መመሪያ በማውጣት ወደስራ መገባቱ አስታውሷል።

በአሁኑ ወቅት ውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በርካታ የዲያስፖራ አባላት ወደሀገራቸው እየገቡ ይገኛል፡፡

በተያያዘ ወቅቱ የበዓል ሰሞን እንደመሆኑ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ከቦታ ቦታ በብዛት እንቅስቃሴ እያደረጉ ሲሆን፥ ይህን ተከትሎ በከተማዋ የትራፊክ መጨናነቅ እና የዝርፊያ ምልክቶች እየታዩ ነው ሲል አሳውቋል።

ስለሆነ ከታህሳስ 22/2014 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ ቁጥጥር እንዲደረግ እና እርምጃ እንዲወሰድ ቢሮው ለሚመለከተው አካል የስራ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

AACATC
የዳይሬክተሮች እና የተቆጣጣሪ ቦርድ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት በአዲሱ የንግድ ሕግ

መግቢያ
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የንግድ ሕግ (አዋጅ ቁጥር 1243/ 2013) የንግድ ማኅበራት ማለት ሰዎች መዋጮ አዋጥተው በኅብረት በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በመሰማራት ከሚገኘው ትርፍ ተከፋይ ለመሆን በስምምነት የሚያቋቁሟቸዉ ማኅበራት እንደሆኑ ተደንግጓል፡፡ ሕጉ ሁለት የንግድ ማሕበራት በዳይሬክተሮች ቦርድ እንዲመሩ የፈቀደ ሲሆን እኒህም የአክሲዮን ማኅበር /Share Company/ እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር/ Praivate Limited Company/ ናቸው፡፡ የንግድ ማኅበር ዳይሬክተሮች ማኅበሩን ለማስተዳደር የሚያስችላቸዉ ሰፊ ሥልጣን አላቸዉ፡፡ ማኅበሩም ከዳይሬክተሮች ጥሩ አገልግሎት ማግኘት የሚችለዉ ዳይሬክተሮቹ በተናጠል ሲሰሩ ሳይሆን እዉቀታቸዉንና ጥረታቸዉን አንድ ላይ አስተባበረዉ ሲሰሩ ነዉ፡፡ በመሆኑም ዳይሬክተሮች ሥራቸዉን የሚያከናዉኑት እየተሰበሰቡ ወሳኔ በማሳለፍ ነዉ፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ትርጉም፣ የዳይሬክተሮችና የተቆጣጣሪ ቦርድ አወቃቀር፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሥልጣንና ግዴታ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት የሚሉትን እንመለከታለን፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ ትርጉም
የንግድ ማኅበራት የተፈጥሮ ሰዎች ባይሆኑም ሕጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ አካላት ናቸዉ፡፡ የንግድ ማኅበራት በራሳቸዉ ተግባሮችን ማከናወን ስለማይችሉ የማኅበሩን ሀሳብና ተግባር የሚያከናዉኑላቸዉ እና ንግዱን የሚመሩላቸዉ የተፈጥሮ ሰዎች ያስፈልጓቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች የማኅበሩ የአስተዳደር የዳይሬክተሮች ቦርድ ይባላሉ፡፡ ይህ የተቆጣጣሪ ቦርድንም ይጨምራል፡፡ የማኅበሩ ዳይሬክተሮች ለማኅበሩ ስኬት ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ማኅበሩ ጥሩ ካፒታልና ጥሩ ዓላማ ቢኖረዉም በጥሩ አስተዳደር ካልተመራ አጥጋቢ ዉጤት አያስገኝም፡፡

የዳይሬክተሮችና የተቆጣጣሪ ቦርድ አወቃቀር
አዲሱ የንግድ ሕግ የዳይሬክተሮች ቦርድን በተመለከተ በአንቀጽ 296 የደነገገው ቀድሞ ከነበረው ዘርዘር ያለ ሲሆን፣ ዋናዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ የአክሲዮን ማኅበር በባለ አክስዮኖች የሚመረጡ ቁጥራቸው ከሦስት እስከ አስራ ሦስት በሚደርሱ የዳይሬክተሮች ቦርድ የሚተዳደር መሆኑ (የዳይሬክተሮች ቦርድ አባለት የተፈጥሮ ሰዉ ወይም ሕጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ ድርጅቶች ሊሆኑ ይችላሉ)፣ከዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት መካከል ከ2/3ኛ በማኅበሩ የዕለት ተዕለት ሥራ አመራር ወስጥ የሥራ አስፈፃሚነት / Executive/ ሚና የሌላቸዉ መሆኑ፣ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርም በአስገዳጅነት ባይሆንም በፈቃዱ ከሦስት እስከ ሰባት የሚደርሱ አባላት ያሉት ቦርድ ሊኖረው እንደ ሚችል በሕጉ 513 ስር ተደንግጎ ይገኛል ፡፡ እንዲሁም በአንቀጽ 331 መሰረት የአክሲዮን ማኅበር በአስገዳጅነት ሳይሆን በፈቃዱ ቁጥራቸው ከከሦስት እስከ አምስት የሆነ ባለአክሲዮን የሆኑ ሰዎችን ብቻ የሚይዝ ተቆጣጣሪ ቦርድ ሊኖረው ይችላል፡፡ የዚህ ቦርድ ዓላማ ስሙ እንደሚያመለክተው በማኅበሩ ላይም ሆነ በሥራ አመራሩ ላይ ቁጥጥር ማድረግና እርምጃ እንዲወስድ ለማኅበሩ ጠቅላ ጉባዔ ማቅረብ ወይም የሚታረም ከሆነ ለቦርዱ ሀሳብ ማቅረብ ብቻ ነው፡፡ ከቀድሞው ሕግ በተለየ ቁጥራቸውን ከ1/3 ያልበለጡ ባለአክሲዮኖች ያልሆኑ ሰዎች የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ሆነው ሊመረጡ ይችላሉ፡፡ ይህም ማኅበሩ የልዩ ዕውቀት ባለቤት የሆኑ የማኅበሩ አባል ያልሆኑ ሰዎችን በሥራ አመራሩ ለማሳተፍ ያስችለዋል፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ ሥልጣንና ግዴታ
የንግድ ማኅበር ዳይሬክተሮች ማኅበሩን ወክለዉ የማስተዳደር፣ የመቆጣጠር እና የመምራት ስልጣን አላቸዉ፡፡ ይህንን ሥልጣናቸዉን በመጠቀም የንግድ ማኅበሩ እንዲያከናዉን የተፈቀደለትን ተግባር ይፈጽማሉ፡፡ ሥልጣናቸዉ መጠን እና ዝርዝር የሚገለጸዉ፡- በህግ፣ በማኅበሩ መመስረቻ ጽሁፍ እና በባለአክስዮኖች ጉባዔ በሚተላለፉ ዉሳኔዎች (ቃለ-ጉባዔዎች) ነዉ፡፡

በንግድ ሕግ አንቀጽ 315 መሠረት የዳይሬክተሮች ቦርድ በሕግ በማኅበሩ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም ጠቅላላ ጉባዔ የተሰጡትን ውሳኔዎች ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ ያለበት ሲሆን የማኅበሩን ፋይናስ በአግባቡ ማስተዳደር፣ ማኅበሩን ለአደጋ ተጋላጭ እንዳይሆን ተገቢውን አሠራር መዘርጋት፣ የማኅበሩ አስፈላጊ የሆኑ የሒሳብና ሌሎች ሰነዶች በአግባቡ ማስተዳደርና እንዲያዙ ማድረግ፣ የማኅበሩን ጠቅላላ ጉባዔ ማዘጋጀትና መጥራት ማኅበሩ 3/4 ካፒታሉን ሲያጣ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ መጥራት እና ማኅበሩ እዳውን የመክፈል አቅሙ ሲቀንስ መልሶ የማደራጀት ሥራ ወይም የኪሳራ ሥነ ሥርዓት እንዲጀምር የማድረግ ተግባርና ግዴታ አለባቸው፡፡ ለማኅበሩ ተገቢ ስትራቴጂካዊ የሆነ አመራር በመስጠት ኩባንያውን ውጤታማና አቅም ያለው ማድረግ የቦርዱ ዋና ኃላፊነት ነው፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ በማኅበሩ መመሥረቻ ጽሁፍና ሕግ መሠረት በአንድነት ሥራቸውን የሚያካሄዱና የማኅበሩ እንደራሴ ሆነው በማኅበሩ ስም የማኅበሩን ጉዳይ የመፈጸም መብት አለባቸው፡፡

የቦርድ አባላት ለማኅበሩ የመታመን ግዴታ (Duty of Loyalty) ያለባቸው ሲሆን ማኅበሩን የበለጠ ስኬታማ ያደርጋል ብለው ያመኑበትን በቅን ልቦና መተግበር አለባቸው፡፡ ይህንን ተግባራዊ ሲያደርጉም የመላው ባለአክሲዮኖችን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩና የማኅበሩን የረዥም ጊዜ ጥቅም፣ የሠራተኞች ጥቅም፣ የባለገንዘቦችን ጥቅም፣ ሥራውን በማኅበረሰቡና በአካባቢው ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ ግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለባቸው በንግድ ሕጉ አንቀጽ 316 ሥር ተመልክቷል፡፡ ይህ ድንጋጌ በርካታ ግዴታዎችን የያዘና የቦርድ ዳይሬክተሮች ኃላፊነት ምን ያህል የከበደ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል የሆነ ሰው ኃላፊነቱ በሚወጣበት ጊዜ በነፃነትና በመሰለው (Independent Judgment) መንገድ መወሰን አለበት፡፡ የመወሰን ነፃነቱን ግን አስቀድሞ በመመሥረቻ ጽሑፍ ወይም ከኩባያው ጋር በተገባ ስምምነት የተወሰነ ከሆነ ግን ገደቡ የተጠበቀ አንደሆነ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 317 (2) ተመልክቷል፡፡ ዳይሬክተሩ በነፃነትና ይወሰናል ማለት ግን የማኅበሩን መመሥረቻ ጽሑፍ፣ የጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ ወይም ሕግ በመጣስ ይወስናል ማለት አይደለም፡፡ በነፃነትና በመሰለው የሚወሰነው በሕጉ ወይም በማኅበሩ ሕገ ደንብ ማዕቀፍ ሆኖ ፍቅደ ሥልጣኑን (Discretion) በሚጠቀምበት ጊዜ ነው፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል የሆነ ሰው ሌላው ግዴታ ኃላፊነቱን በጥንቃቄ በብልህነትና በትጋት (Duty to Exercise Reasonable Skill, Care and Diligence) መወጣት እንደሆነ በንግድ ሕጉ በአንቀጽ 318 ላይ ተመልክቷል፡፡ ጥንቃቄ፣ ትጋት ወይም ብልህነት እንዴት ይለካል የሚለው አከራካሪ ቢሆንም የንግድ ሕግ፣ ኃላፊነቱ በምክንያታዊ ደረጃ ትጉህ የሆነ የቦርድ አባል ሊኖረው ከሚገባው ጠቅላላ ዕውቀት ብልኃትና ጥንቃቄ አንፃር የሚለካ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ይህም አንፃራዊ (Subjective Standard) መለኪያ ነው፡፡
ሌላው በቦርድ አባላት ላይ የተጣለው ግዴታ የጥቅም ግጭትን የማራቅ (Duty to Avoid Conflict of Interest) ነው፡፡ ማኅበሩ ሊጠቀምባቸው ቢችልም ባይችልም ዳይሬክተሩ የማኅበሩን ንብረት፣መረጃ ወይም የንግድ ዕድል ለግል ጥቅሙ እና ለሌላ ሰው ማዋል እንደማይችል በአንቀጽ 320 (1) (2) ሥር ተደንግጓል፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ ወይም የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ግን ክልከላውን በማንሳት ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል፡፡ በቦርድ አባሉና በማኅበሩ መካከል የጥቅም ግጭት ሊፈጥር የሚችል ሁኔታ ካለ ወይም ሊደረግ የታሰበው ወይም የተደረገ ውል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የቦርድ አባሉን ጥቅም ጋር የሚገናኝ ከሆነ ሁኔታውን በዝርዝር ለተቀሩት ዳይሬክተሮች በተሟላ መልኩ ሊገለጽላቸው ይገባል፡፡
በማኅበሩና ከማኅበሩ ጋር ቅርበት ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ ስምምነት በቅድሚያ በቦርዱ መፈቀድ እንዳለበት የጥቅም ግጭት ያለበት የቦርድ አባልም ድምፅ መስጠት እንደማይችል በአንቀጽ 306 ሥር ተመልክቷል፡፡

ዳይሬክተሮችን የሚመለከት ብድር ወይም ዋስትና በቅድሚያ በጠቅላላ ጉባዔ መፈቀድ ይገባዋል፡፡ ዳይሬክተሮችን ይህንን የማክበር ግዴታ አለባቸው፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በጠቅላላ ጉባዔ ካልተፈቀደላቸው በስተቀር በራሳቸው ወይም በሦስተኛ ወገኖች ስም ከማኅበሩ ጋር መወዳደር ወይም ተወዳዳሪ የሆኑ የንግድ ማኅበራት ውስጥ አባል መሆን እንደማይችሉ በንግድ ሕግ ቁጥር 319 ሥር ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል የሆነ ሰው ያለ ቦርዱ ፈቃድ ከሦስተኛ ወገን ስጦታም ሆነ ሌላ ዓይነት ጥቅም መቀበል እንደማይችል በንግድ ሕግ ቁጥር 322 ላይ ተደንግጓል፡፡ ዳይሬክተሮች ማኅበሩን በሥራው ውጤታማ እንዲሆን ማድረግ እንዳለባቸውና ዕዳውን መክፈል እንደማይችሉ እያወቁ ሥራውን መቀጠል (Reckless Trading) እንደሌለባቸው በንግድ ሕጉ ተመልክቷል፡፡

በማኅበሩ መመስረቻ ጽሁፍ እና ቃለ ጉባዔ ለዳይሬክተሮች የሚሰጠዉ የተግባር ግዴታ እንዳለ ሆኖ በህግ ከተሰጣቸዉ ግዴታዎች መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ፡፡

1. የዳይሬክተሮች ቦርድ በሕግ ፣ በማኅበሩ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም በባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ዉሳኔ የሚሰጥ ሥልጣን ይኖረዋል፡፡
2. የማኅበሩ መመስረቻ ጽሁፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በአንድነት ሥራቸዉን የሚያካሂዱና ለማኅበሩ እንደራሴ መሆናቸዉን ወይም ከእነርሱ ዉስጥ አንዱ ለዚህ ተግባር በተለይ ስልጣን ያለዉ መሆኑን መለየት አለበት፡፡
3. ለማኅበሩ እንደራሴ እንዲሆኑ የተፈቀደላቸዉ ዳይሬክተሮች በማኅበሩ ስም የማኅበሩን ጉዳይ ለመፈጸም አስፈላጊ የሆኑትን ሥራዎች ሁሉ በእንደራሴነት የመሰራት መብት አላቸዉ በማለት አዲሱ የንግድ ሕግ በአንቀጽ 324 ላይ አስፍሯል፡፡
የአክስዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ እነዚህ የተሰጡትን ሥልጣኖች መሰረት በማድረግ ዉሳኔዎችን የሚያስተላልፈዉ በቦርድ ስብሰባዎች ነዉ፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት
የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የአክስዮን አባል ቢሆኑም ባይሆኑም በአስተዳዳሪነት ሥራቸዉ ለሚያደርሱት ጥፋት ኃላፊነትና ተጠያቂነት ያለባቸዉ ሲሆን እነዚህም የፍትሐብሔር ኃላፊነት እና የወንጀል ተጠያቂነት ናቸዉ፡፡ የወንጀል ተጠያቂነት ማለትም በወንጀል ተከሶ የገንዘብ ቅጣትና እስር ሊወሰንባቸዉ ይችላል፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ ፍትሐብሔራዊ ኃላፊነት
የዳይሬክተሮች ቦርድ በሕግና በማኅበሩ መመሥረቻ ጽሁፍ ውስጥ የተመለከቱ ተግባርና ኃላፊነታቸውን ካልተወጡ ወይም ከጣሱ በኃላፊነት ይጠየቃሉ፡፡

ለማኅበሩ ያለባቸዉ ኃላፈነት
የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በህግ፣በማኅበሩ መመስረቻ ጽሁፍ እንዲሁም በጠቅላላ ጉባዔ ዉሳኔዎች የተሰጠቸዉን የአስተዳደር የሥልጣን ወሰን ሳያልፉ ተግባሮቻቸዉን በጥንቃቄ መፈጸም አለባቸዉ፡፡በቅን ልቦና( ህሊና) እና በጥንቃቄ ባለመስራታቸዉ በማኅበሩ ላይ ጉዳት እንዲደርስ ካደረጉ ለደረሰዉ ጉዳት ማኅበሩን ለመካስ በአንድነት ኃላፊዎች ይሆናሉ፡፡ ይህም በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 325 ተድግጎ ይገኛል፡፡ የቦርድ አካላት በተገቢው ጥንቃቄና ትጋት ስለማስረዳታቸው የማስረዳት ሸክም አለባቸው፡፡ ማኅበሩ በዳይሬክተሮች ላይ ክስ ማቅረብ የሚችለው ግን የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ሲወሰን ብቻ ነው፡፡ የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ወስኖ ማኅበሩ ክስ ያልመሠረተ እንደሆነ የማኅበሩን ካፒታል አሥር በመቶ የያዙ ባለአክሲዮኖች በማኅበሩ ስም በዳይሬክሮች ላይ ክስ የማቅረብ መብት አላቸው፡፡ ማኅበሩ በዳይሬክተሮች ላይ የሚያቀርበዉን ክስ ለመተዉ ወይም በግልግል ለመጨረስ ይችላል፡፡ ሆኖም ክሱን ለመተዉና በግልግል ለመጨረስ የሚቻለዉ ከማኅበሩ ዋና ገንዘብ ቢያንስ አሥር በመቶ ድርሻ ያላቸዉ ባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔዉ ክስ ለመተዉ ወይም በግልግል ለመጨረስ የሰጠዉን ዉሳኔ ያልተቃወሙት እንደሆነ ነዉ በማለት በሕጉ አንቀጽ 328 ተደንግጓል፡፡

ለባለአክስዮኖች ያለባቸዉ ኃላፊነት
የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በፈጸሙት ጥፋት የተነሳ በአንድ /በተወሰኑ ባለአክስዮኖች ላይ በቀጥታ ጉዳት ካደረሱ ጉዳቱን ለደረሰበት (ለደረሰባቸዉ) ባለአክስዮኖች ተጠያቂነት ይኖርባቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ የንግድ ህግ ይህ መብት ለባለአክስዮኖች የተሰጠዉ በቁጥር 355 ነዉ፡፡ ከማኅበሩ ዋና ገንዘብ ቢያንስ አሥር በመቶ ድርሻ ባላቸዉ ባለአክሲዮኖች ጥያቄ በሚደረግ ምርመራ የሚደረግ ነዉ፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥፋት ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ባለአክስዮን በዳይሬክተሮች ላይ በቀጥታ ክስ ለማቅረብ በጠቅላላ ጉባዔ ካልተፈቀደለት በአማራጩ የንግድ ማኅበሩን የመክሰስ መብት ይኖረዋል፡፡

ከማኅበሩ ላይ ገንዘብ ለሚጠይቁ ሰዎች (ሦስተኛ ወገኖች) ያለባቸዉ ኃላፊነት
ከማኅበሩ ላይ ገንዘብ ለሚጠይቁ ሰዎች የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ተጠያቂነት ያለባቸዉ ሲሆን ዳይሬክተሮች የማኅበሩ ገንዘብ በሙሉ አንዲጠበቅ የማድረግ ግዴታቸዉን በጥንቃቄ መወጣት አለባቸዉ፡፡ ይህንን አስተዳደራዊ ጥንቃቄ በሚገባ ባለማድረጋቸዉ የተነሳ ከማኅበሩ ላይ ገንዘብ ለሚጠይቁ ሰዎች ከማኅበሩ ላይ የሚጠይቁትን ገንዘብ ሳያገኙ ቢቀሩ (ለምሳሌ በማኅበሩ አንቀጾች እንዲቀመጥ የታዘዘዉን መጠባበቂያ ገንዘብ በአግባቡ እንዲቀመጥ ሳያደርጉ ቢቀሩ) ከማኅበሩ ላይ ገንዘብ ለሚጠይቁ ሰዎች በኃላፊነት ተጠያቂዎች ይሆናሉ፡፡

ሦስተኛ ወገኖች ከማኅበሩ የሚጠይቁትን ገንዘብ ከማኅበሩ ንብረት ላይ ነዉ የሚወስዱት ፡፡ ነገርግን የማኅበሩ ንብረት የማኅበሩን ዕዳ ለመሸፈን ካልበቃ እና ላለመብቃቱ የዳይሬክተሮች ጥፋት ካለበት ገንዘብ ጠያቂዉ በዳይሬክተሮች አባላት ላይ በግል ክስ የማቅረብ መብት አላቸዉ፡፡ ዳይሬክተሮችን በግል ከሚያስጠይቁ ጉዳዮች መካከል ለማኅበሩ ጉዳይ በራሳቸዉ ስም ተዋዉሎ መገኘት፣ማኅበሩ ከሰጣቸዉ ሥልጣን ዉጪ በማኅበሩ ስም ቢሆንም ተግባሮችን ፈጽሞ መገኘት እና ለ 3ኛ ወገኖች የተሳሳተ ወይም የተጭበረበረ መግለጫ (ማስረጃ) መስጠት የመሳሰሉት ይገኙባቸዋል፡፡ ማኅበሩ በዳይሬክተሮች ላይ የሚያቀርበዉን ክስ ለመተዉ ቢወስን ከማኅበሩ ላይ ገንዘብ ለሚጠይቁ ሰዎች በዳይሬክተሮች ላይ ክስ ለማቅረብ ያላቸዉን መብት አያስቀርም፡፡( አዲሱ የንግድ ሕግ 329 ይመለከቷል)፡፡
የዳይሬክቶች ቦርድ አባላት የወንጀል ተጠያቂነት
የንግድ ማኅበር ዳይሬክተሮች የተሰጣቸዉን ኃላፊነት በአግባቡ ሳይወጡ ሲቀሩ ወይም የማኅበሩን ጥቅም በሚፃረር እና በሚጎዳ ሁኔታ ቢሰሩ ከሚኖርባቸዉ ፍትሐብሔራዊ ኃላፊነት በተጨማሪ የወንጀል ተጠያቂነት ይኖርባቸዋል፡፡ ሥራዉን እንዲመራ በሕግ ወይም በዉል ግዴታ የተቀበለ ሰዉ (የንግድ ማኅበር አስተዳዳሪ) በተሰጠዉ ኃላፊነት ያለአግባብ በመገልገል ወይም የተጣለበትን ግዴታ ባለመፈጸም በሚጠብቀዉ (በሚያስተዳድረዉ) የንብረት ጥቅም ላይ ወይም በድርጅት አገልግሎት ላይ አስቦ ጉዳት ካደረሰ እንደነገሩ ክብደት በቀላል እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ እንደሚቀጣ በኢፊዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 702 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ አስተዳዳሪዉ ጥፋቱን የፈፀመዉ በቸልተኝነት የተፈፀመ ከሆነ በመቀጮ ወይም ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ይቀጣል፡፡ አስተዳዳሪዉ ጥፋቱን የፈፀመዉ የንብረት ጥቅም ለራሱ ወይም ለሌላ ሰዉ ለማስገኘት አስቦ ከሆነ ደግሞ ቅጣቱ ከአንድ ዓመት ያላነሰ ቀላል እስራት ሆኖ ከብር ከብር ሰላሳ ሺህ የማይበልጥ መቀጮ በተጨማሪ ይወሰንበታል፡፡ እንደሁኔታዉ የቅጣቱ መጠን ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል በወንጀል ሕግ በዝርዝር ተገልጧል፡፡ ጥፋቱ ከወንጀል ሕጉ በተጨማሪ ከነገሩ ጋር አግባብነት ባላቸዉ ሌሎች አዋጆችም ሊታይ ይችላል፡፡

በማኅበሩ ውስጥ የማታለል ድርጊት ተፈጽሞ ከሆነ የተወሰኑ ባለአክሲዮኖችን መብት የሚጎዳ ድርጊት ተፈጽሞ ከሆነ ሕገወጥ የሆነ ወይም የማታለል ድርጊት ያለበት አሠራር በማኅበሩ ውስጥ ያለ እንደሆነ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞ ከሆነ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ወይም ሌላ ሥልጣን ያለው አካል ምርመራ ሊያደርግና የአስተዳደር ወይም የወንጀል ክስ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግም በሕግ ወይም በውል ሥራ እንዲመራ ኃላፊነት የተሰጠው ሰው ኃላፊነቱን ሳይወጣ ጉዳት ያደረሰ መሆኑ ከተረጋገጠ እስከ አሥር ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና እስከ 50,000 ብር በሚደርስ መቀጫ ሊቀጣ ይችላል፡፡
በአጠቃላይ አዲሱ የንግድ ሕግ ውስጥ ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት በእጅጉ የገዘፈና ኃላፊነቱም የግል ሀብትና ንብረት ድረስ የሚመጣ፣ ለእስራት የሚዳርግ ስለሆነ ኃላፊነቱን የሚወስዱ ሰዎች ዝርዝር ጉዳዩን አውቀው ወደ ሥራው እንዲገቡ እናስገነዝባለን፡፡
የፌዴራል_የፍትህ_እና_ሕግ_ኢንስቲትዩት_የቅድመ_ሥራ_ሠልጣኞች_የኪስ_ገንዘብ_አከፋፈል_እና_የጥቅማጥቅም.pdf
195 KB
የፌዴራል የፍትህ እና ሕግ ኢንስቲትዩት የቅድመ-ሥራ ሠልጣኞች የኪስ ገንዘብ አከፋፈል እና የጥቅማጥቅም አሰጣጥ መመሪያ
ከባንክ በሳምንት ከ5 ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ ተነሳ!

ብሔራዊ ባንክ በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ ማንሳቱን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ መነሳቱን ይፋ አድርጓል። ብሔራዊ ባንክ ካለፈው ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ የባንኮች ደንበኞች በሳምንት ከአምስት በላይ የባንክ ዝውውሮችን እንዳያደርጉ የሚያዝ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል።

ይህም መመሪያ መደበኛ ባልሆነው የልውውጥ ገበያ ውስጥ ያሉ ተጫዋቾችን ተስፋ ለማስቆረጥ ያወጣው ደንብ መሆኑን አስታውቆ ነበር። ይሁን እንጂ ካሳለፍነው ሳምንት ታህሳስ 27 ቀን 2014 ጀምሮ ይህ መመሪያ መነሳቱን በብሔራዊ ባንክ የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው፣ መግለፃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

“የዝውውር ገደቡ አሁን ሙሉ በሙሉ በመመርያ ተነስቷል” ያሉት ፍሬዘር፣ ነገር ግን ባሳለፍነው ዓመት የወጣው የገንዘብ ወጪ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ገደቦችም አሁንም ድረስ ተፈፃሚ ሆነው ይቀጥላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

መረጃ
ጋብቻ በሚፈርስበት ወቅት የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ሥነ-ሥርዓት ከሰበር ውሳኔዎች ጋር ተገናዝቦ የቀረበ

በ፡ ሙሉቀን ሰይድ

በዚህ አጭር ጽሁፍ የጋራ ንብረት ክፍፍልን በተመለከተ አከራካሪ ከሆኑ ጉዳዩች መካከል የትኞቹ ንብረቶች የተጋቢዎቹ የጋራ ንብረት ይባላሉ፤ ተጋቢዎቹስ ምን ያህል ምጣኔ ድርሻ በንብረቶቹ ላይ ይኖራቸዋል፤ የጋር ንብረት ክፍፍል ጥያቄስ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ሊቀርብ ይገባዋል የሚሉ ነጥቦችን የፌዴራሉ የቤተሰብ ህግ እና ከተመረጡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ውሳኔ አንጻር ዳሰሳ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2018-procedures-of-partition-of-common-property-after-divorce
ስለ ኑዛዜ ከውርስ ሕግና ከሰበር ውሳኔዎች ጋር ተገናዝቦ የቀረበ
በ፦ ሙሉቀን ሰይድ ሀሰን

የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ ኑዛዜ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሰጠው ትርጉም ባይኖርም አንድ ኑዛዜ ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች ምን ምን እንደሆኑ በዝርዝር የሚያስቀምጡ የሕግ ድንጋጌዎችን ከፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 857 እስከ 908 ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡

በዚህ ጽሁፍ ኑዛዜ በምን አግባብ ቢደረግ በሕግ ዘንድ ውጤት ይኖረዋል፤ በውርስ ሕጋችን ላይ የተቀመጡት የኑዛዜ አደራረግ ስርዓቶች አስገዳጅነታቸው እስከምን ድርስ እንደሆነና ኑዛዜ በፍርድ ቤት ቢጸድቅ ሊያስገኝ የሚችለው ውጤትና ባለመጽደቁ የሚያመጣው ተጽእኖ ምን እንደሆነ ከውርስ ሕግ እና አስገጋጅ ከሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ውሳኔዎች አንጻር በአጭሩ ዳሰሳ ለማድርግ ተሞክሯል፡፡
መልካም ንባብ!

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2003-wills-presented-with-succession-laws-and-cassation-decisions
ስለጉዳዩ በዝርዝር የሚጠየቁትን ትተን የሚከተሉትን አሰልቺ ጥያቄዎች ለመመለስ መዘጋጀት አለብዎት፦

ክሱ ለምን እዚህኛው ፍርድ ቤት ሆነ? ለምን የዳኝነት ይከፈላል? ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማየት እንደጠበቃ ገንዘብ ይቀባለል? አይቀንስም? ይህንን ክፍያ በኋላ ፍርድ ቤቱ ይመልስልኛል? ስንት ዳኞችና ናቸው ጉዳዩን የሚያዩት? በስንት ጊዜ ውሳኔ ይሰጣሉ? ውሳኔ የሚሰጥበት ቁርጥ ያለ ጊዜ ልትነግረን ትችላለህ? ከዳኞችም ሱፍ ለምን አይለብሱም? ለምን ዳኛው ቢሮ ውስጥ ጠራህ/አስተናገደህ? ፍርድ ቤቶች ሽንት ቤት የላቸውም? ፍርድ ቤቱ የቀጠረን ሰዓት ለምን አያከብርም? ለምርመራ ምን ማለት ነው? አሁንም ቀጠሮ? ቃል ክርክር ምን ማለት ነው? አዲስ ማስረጃ ማስገባት አይቻለም? ለምን ዳኛው ጋር ሔደን በዝርዝር ጉዳዩን እንዲረዳ አናደርገውም? ጉዳዩን የሚያየው አንድ ዳኛ ብቻ ነው? ለምን ሌሎች ዳኞች አላዩትም? ችሎት ጸሐፊ ምንድነው? ሬጂስትራርስ? አቤቱታ ምንድነው? የአቤቱታ ቀን ለምን ሁሉ ጊዜ አይሆንም? ጠበቆች ለምን ፕሮቶኮል አይጠብቁም? ጠበቆችም እንደባለጉዳይ ነው ሚታዩት? ጠበቃዬ እስከሆንክ ለምን ይህንንም ጉዳይ አታማክረኝም? ከተከራካሪ ወገን ጠበቃ ጋር ለምን ትነጋገራለህ? ጉዳዩን ለምን በዝርዝር ለፍርድ ቤቱ አልተናገርክም? ሌላኛው ጠበቃ ሁለቴ ተናግሮ አንተ አንድ ጊዜ ብቻ ለምን ተናገርክ? ስልክህን ለምን አታነሳም? በፈለኩህ ጊዜ ላገኝህ አልቻልኩም፥ ምን ይሻላል? ………. ወዘተ

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2019-four-types-of-clients-group-one