አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ተጠሪዎች እየሞገቱ ያሉት የመሰረዙን ሕጋዊነት ነው፡፡ የተጠሪዎች ሙግት
በአብላጫው ድምፅ ሰሚ አላገኘም፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር
ካርታው ከደንብ ውጭ ለአመልካች እንደተሰጠ ስላላስረዳ ድርጊቱ ሕገ ወጥ
ወይም ከሥልጣን በላይ ነው፡፡ በቤቱ ላይ በሕጉ መሠረት ባለቤት እንደሆነ
ስላላስረዳም ‘ከመሬት ተነስቶ በሌላ ሰው መብት ባለቤትነት ሊኖረው
አይችልም፡፡ ይህን ሀሳብ በአነስተኛ ድምፅ አስተያየት ስንቋጨው፤
አመልካች እንኳንስ መብት ሊኖረው ቀድሞውኑ በተቃውሞ ወደ ክርክር
ውስጥ እንዲገባ ሊፈቀድለት አይገባም ነበር፡፡
በሌላ ተመሳሳይ መዝገብ እንዲሁ ፍርድ ያረፈበት የባለቤትነት መብት
አስተዳደሩ ስላመከነው መና ሆነ ቀርቷል፡፡ በሰ/መ/ቁ. 22719[1] ተጠሪ
በሁለት የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር /ካርታ/ የተመዘገቡ ሶስት የቤት
ቁጥር የተሰጣቸው ቤቶች የራሳቸው መሆናቸው ተረጋግጦ በፍርድ ቤት ውሳኔ
አርፎባቸው በአፈጻጸም መዝገብ ቤቶቹን ተረክበዋል፡፡ የፍርድ ሂደቱ
እንደተጠናቀቀ አመልካች የቤት ማረጋገጫ ደብተሮቹን በመሰረዙ ተጠሪ ክስ
አቀረቡ፡፡ በሰበር ችሎት በነበረው ክርክር ችሎቱ ተጠሪ መብታቸውን በፍርድ
ቤት አስከብረውና አረጋግጠው የተፈጸመባቸው ዓይን ያወጣ ህገ ወጥ ተግባር
ከማረምና የህግ የበላይነትን ከማስከበር ይልቅ ክስ የማቅረብ መብታቸውን
ነፍጓቸዋል፡፡ ችሎቱ ለማመዛን እንደሞከረው፡
አመልካች የተጠሪን የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነዶች ከሰረዘ ተጠሪ አስቀድሞ
በተጠቀሱት ቤቶች ላይ ባለመብት መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን
በእጁ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ይህ መሠረታዊ ማረጋገጫ ሰነድ ወይም
ማስረጃ ሳይኖረው ፍ/ቤት ሰነድ እንዲሰጠው እንዲወሰንለት መጠየቅ
አይቻልም፡፡
በአጭር አነጋገር ቤቱን በአስተዳደሩ ህገ ወጥ ተግባር የተነጠቀ ሰው ቤቱ
እንዲመለስለት የመጠየቅ መብት እንኳን የለውም፡፡
የሰበር ችሎት ዘግይቶም ቢሆን የሰ/መ/ቁ 17712 እና 22719 ውሳኔ ካገኙ
ከሰባትና አምስት ዓመታት በኋላ ፍጹማዊ በሆነውና ፍጹማዊነቱንም ችሎቱ
ይሁንታ በሰጠው የአስተዳደሩ ካርታ የማምከን ስልጣን ላይ ገደብ ለማበጀት
ተገዷል፡፡ በሰ/መ/ቁ. 42501[2] ፍርድ ባረፈበት ጉዳይ ካርታ ማምከን ህገ
ወጥነቱን ጠንከር ባሉ ቃላት እንደሚከተለው ገስጾታል፡፡
አንድ የአስተዳደር አካል በፍርድ ቤት ክርክር መረታቱን ከተረዳ በኃላ በሕጉ
የተሰጠውን ስልጣን መነሻ በማድረግ ለፍርዱ መሰጠት መሠረት የሆነውን
ማስረጃ ዋጋ በማሣጣቱ ምክንያት የፍርድ አፈፃፀም ዋጋ እንዲያጣ የማድረግ
ውጤት በኢ.ፊ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 78/1/ እና 79/1/ እና /4/
ስር የተረጋገጠውንና የተከበረውን የነፃ ፍርድ ቤት መኖርንና የዳኝነት ስልጣን
ትርጉም አልባ የሚያደርገው ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 42501 ቅጽ 15፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 37፣ 38፣
79፣ ፍ/ህ/ቁ. 1195፣ 1196፣ 1198
አስተዳደራዊ ተቋማት በሕግ ተለይቶ በተሰጣቸው ጉዳይ የመወሰን ሥልጣን
እንዳላቸው የታወቀ ነው፡፡ ይሁንና ለአንድ ባለ ጉዳይ የተሰጠው ካርታ
የተሰጠበት እና የተሻረበት አግባብ በሕግ አግባብ መሆን ያለመሆኑን አጣርቶ
የመወሰን ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ነው፡፡ በዚህ ረገድ አንድ ፍርድ ቤት
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታን የመሰረዝ ሥልጣን የአስተዳደር ክፍል ነው፣
ፍርድ ቤት ጉዳዩን አይቶ የመወሰን ሥልጣን የለውም በማለት የሚደርስበት
ድምዳሜ የጉዳዩን የክርክር ባህሪ እና ይዘት ያላገናዘበ ነው፡፡ ፍርድ ቤቶች
በአስተዳደር ክፍል የተሰጠው ካርታ የተሰጠበት ወይም የተሻረበት ሥርዓት እና
አስተዳደራዊ ውሳኔው ሕግና መመሪያ ያገናዘበ መሆን ያለመሆኑን በማጣራት
ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን እንዳላቸው ከፍ/ህ/ቁ. 1196 እና በህገ
መንግስቱ ስለ ንብረት መብት ከአደረገው ድንጋጌና በፍርድ የሚያልቁ
ጉዳዮችን በተመለከተ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 37 ከተመለከቱት ድንጋጌዎች
ይዘት የምንረዳው ጉዳይ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ 99071 ቅጽ 18፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 37፣ ፍ/ህ/ቁ. 1196
ከቴምብር ቀረጥ ነፃ የመሆን መብት /Stamp Duty Exemption/
-------------------------------------

1. የቴምብር ቀረጥ ምንነት እና ዓላማዉ
መንግስት ገቢ ከሚሰበስብባቸዉ ምንጮች መካከል የቴምብር ቀረጥ አንዱ ነዉ፡፡ የቴምብር ቀረጥ ቀጥተኛ ያልሆነ ታክስ ሲሆን የሚሰበሰበዉም በተወሰኑ ሰነዶች ላይ እንዲለጠፍ ወይም እንዲከፈል በማድረግ ነዉ፡፡ በሀገራችን ኢትጵያ የቴምብር ቀረጥ የተጣለዉ ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ በወጡ የቴምብር ቀረጥ አዋጅና ደንብ (አዋጅ ቁጥር 334/1979 ዓም እና በቴምብር ቀረጥ ደንብ ቁጥር 221/ 1951 ዓ.ም) ሲሆን አሁን በሥራ ላይ ያለዉ የቴምብር ቀረጥ አከፋፈል አዋጅ 110/1990 ዓ.ም ነዉ፡፡ የቴምብር ቀረጥ የመንግስት አንዱ የገቢ ምንጭ ከመሆኑ ባሻገር በሰነዶች ላይ የተለያዩ የስራ ዘርፎችን የኪነ-ጥበብ ዕድገትን፣ የፋይናንስ ተቋሞችን እንቅስቃሴ እና የካፒታል ንብረት ዝዉዉርን ለማገዝ የሚያስችል እና የቴምብር ቀረጥ የሚከፈልባቸዉን ሰነዶችና ከቴምብር ቀረጥ ነፃ ስለመሆን የሚለዉን ለይቶ የማሳወቅ እና ሌሎች አለማወችን ያገናዘበ ነዉ፡፡

የቴምብር ቀረጥ የሚከፈልባቸዉ እና የማይከፈልባቸዉ ግብይቶች
የቴምብር ቀረጥ በሰነዶች ላይ የሚጣል ታክስ ቢሆንም ሁሉም ሰነዶች ላይ የሚጣል አይደለም፡፡ አዋጁ በአንቀጽ 3 የተለያዩ ሰነዶችን በመዘርዘር የሚከፈልበትን ጊዜ፣ሁኔታና መጠን በግልጽ አመልክቷል፡፡ የቀረጥ ቴምብር የሚከፈለዉ የመንኛዉም ንግድ ማኅበር፣የኅብረት ሥራ ማኅበር ወይም የማኝኛዉም ዓይነት ማኅበር መመሥረቻና መተዳደሪያ ደንብ፤የግልግል ሰነድ፤ ማገቻ፤ የዕቃ ማከማቻ ማረጋገጫ ሰነድ፤ ዉል ስምምነትና የእነዚህ መግለጫ፤የመያዣ ሰነዶች፤የኅብረት ስምምነት፤ የሥራ (ቅጥር) ዉል፤የኪራይ፣የተከራይ አከራይና መሰል መብት የማስተላለፊያ ሰነዶች፤ ማረጋገጫ፣ የዉክልና ሥልጣን እና የንብረት ባለቤትነትን ማስመዝገቢያ ሰነድ ላይ ነዉ፡፡ ከእነዚህ ሰነዶች ዉጭ ባሉ ሰነዶች ላይ የቴምብር ቀረጥ አይከፈልም፡፡ የአዋጁ ዝርዝር ምሉዕ / Exhaustive / በመሆኑ በማመሳሰል / Analogy / ሌሎች ያልተጠቀሱ ( ያልተዘረዘሩ) ሰነዶች ላይ የቴምብር ቀረጥ እንዲለጠፍ ወይም እንዲከፈል መጠየቅ የሚቻል አይደለም፡፡

2. ከቀረጥ ነፃ ስለ መሆን
የቴምብር ቀረጥ አዋጁ ከቀረጥ ነፃ የመሆን መብትን በአንቀጽ 11 ደንግጓል፡፡ ድንጋጌዉ ከቴምብር ቀረጥ ነፃ የሆኑትን ( የቴምብር ነፃ መብት ተጠቃሚዎችን) የዘረዘረ ሲሆን የአትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሰት የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 57/1989 ዓ.ም ተፈፃሚ የሚሆንባቸዉ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች፣የአስመጭነት የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ ነጋዴዎች ለሽያጭ የሚያስመጡት ንብረት በአስመጭዎቹ ስም በሚመዘገቡበት ጊዜ፣ በዓለም አቀፍ ስምምነቶች ተጠቃሚ የሆኑ፣ ተመሳሳይ መብት የሚሰጡ ኤምባሴዎችና የአክስዮን ድርሻ የምስክር ወረቀት ሲመዘገብ ከቴምብር ቀረጥ ነፃ የመሆን መብት ይኖራቸዋል፡፡ ባንኮች ለ3ኛ ወገን በሚሰጧቸዉ ቦነዶች / Bid Bond, Performance Bond / ላይ የቴምብር ቀረጥ አይከፍሉም፡፡በተጨማሪም ኢንበስተሮች (ባለሀብቶች) ከኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ ከባንኮች ብድር ሲወስዱ ከቀረጥ ቴምብር ነፃ እንዲሆኑ ተፈቅዷል፡፡

ይህ የሆነዉም ኢነቨስትምንትን ለማበረታት ሲባል ነዉ፡፡ እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 867/07 አንቀጽ 4 መሠረት ከሚወጡት የመንግስት የዕዳ ሰነዶች ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ወይም ሰነዶች ላይ የቴምብር ቀረጥ አይከፈልባቸዉም፡፡ ሌሎችን ደግሞ የገንዘብ ሚኒሰቴር በቂ ምክንያት ሲቀርብለት ከቴምብር ቀረጥ ነፃ ሊያደርግ እንደሚችል ገልጿል፡፡ ይህን ለማስፈፀም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 7/1988 ዓ.ም እና በፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር በቁጥር 01/1/9/11/33/3 በቀን 24/02/ 1997 የወጣዉን መመሪያ ይመለከቷል፡፡ የኢንቨስትመንት ኤጀንሲ በቁጥር ኢዲክ9/ኢጠ/1/662 በቀን 22/03/1999 ዓ.ም ማብራሪያ ይህንኑ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡

3. ከቴምብር ነፃ ማበረታቻ ከሌሎች ማበረታቻዎች በምን ይለያል
ከቀረጥ ቴምብር ነፃ መሆን ማበረታቻ ከሌሎች ማበረታቻዎች በተለይም ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ እና ከገቢ ግብር ማበረታቻ የሚለየዉ በመመሪያ የተሰጠ መብት በመኖሩ፣ የቴምብር ቀረጡ የሚከፈልበት ጊዜና ሁኔታ የተገለጸ በመሆኑ እና ዝርዝር የመብቱ አጠቃቀም መብቱ የሚጀምርበትና የሚጠናቀቅበት ጊዜ ግን በግልጽ ባለመመልከቱ ነዉ፡፡

4. የቴምብር ቀረጥ አለመከፈል የሚያስከትለዉ ዉጤት
ይህ ጉዳይ በአዋጁ አንቀጽ 10 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ የቴምብር ቀረጥ በአዋጁ አንቀጽ 12 በተጠቀሰዉ መሠረት በወንጀል ከማስቀጣቱ በተጨማሪ የሚከተሉት ዉጤቶች አሉት፡-
 ማንኛዉም ሰነድ በቴምብር አዋጁ መሰረት ትክክለኛ የተምብር ቀረጥ ካልተከፈለበት በስተቀር በዉል ወይም በሕግ ማስረጃ የመቀበል ሥልጣን ባለዉ ሰዉ ወይም የመንግስት መስሪያቤት ዘንድ በማስረጃነት ተቀባይነት አይኖረዉም፣ ምልክት አይደረግበትም ወይም ማረጋገጫ አይሰጥበትም፡፡
 በአዋጁ መሠረት በመረጃነት ያላገኙ ሰነዶች ሊከፈልባቸዉ የሚገባዉ ቀረጥ በሁለት እጥፍ ተከፍሎባቸዉ በመረጃነት ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ የሚከፈለዉ ቀረጥ ከ ፲ ብር ( አስር ብር) ማነስ የለበትም፡፡
 ዉጤቱ በወንጀል ፍርድ ቤት በሚታይ ክርክር በማስረጃነት የሚቀርቡ ሰነዶችን አይመለከትም፡፡
በአጠቃላይ የቴምብር ቀረጥ አዋጅ 110/1990 ዓ.ም መሠረት ቢሆንም በአንዳንድ ጉዳዮች በተለይም ይግባኝን በተመለከተ በቴምብር ቀረጥ መሻሻያ አዋጅ ቁጥር 612/2001 ዓ.ም ማሻሻያ የተደረገበት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ሌላዉ ጉዳይ በቴምብር ሕጉ አና አተገባበሩ ላይ የተወሰነ ክፍተት የሚታይበት በመሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጣና መሰጠት ቢቻል ለዉጥ ይመጣል የሚል ነዉ፡፡
Great call from Pm Abiy Ahmed 🇪🇹💚💛❤️

Yes , we Africans ask for a permanent seat and voice at UNSC ASAP .

Wake up Africa 🌎💪🏻
#PanAfricanismPrevails
#BBCfakenews
#WeStandTogether
#PermanentseatforAfricaUNSC
#AfricanUnite
የቱ ነው ልክ ?
ዳኛው የተለመደ ተግባራቸውን ለማከናወን ተቀምጠዋል ፤ ከእርሳቸው አጠገብ በስተቀኝ በኩል ችሎት ጸሐፊያቸው አለ። ከፊት ለፊታቸው ደግሞ ሁለት ሰዎች ቆመዋል፤ ከሳሽና ተከሳሽ ። ዳኛው ቅድሚያ ለከሳሽ እድል በመስጠት ጉዳዩን እንዲያስረዳ ጋበዙት ።ከሳሽም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው ክሱን በዝርዝር አቀረበ ። ዳኛውም " ይገርማል ያልከው ሁሉ ልክ ነው " አሉና
በቀጣይ መልስ እንዲሰጥበት ተከሳሽን ጋበዙት። ተከሳሽም የተከሰሰው ያለአግባብ መሆኑን በመጥቀስ ክሱን አስተባብሎ በመናገር ጉዳዩን አስረዳ ። አሁንም ዳኛው በመገረም " ይገርማል፤ እጅግ በጣም ይገርማል ልክ ነህ ወዳጄ ፤ ያልከው ነገር ሁሉ ልክ ነው " አሉት ። ይኼኔ ዳኛው ግራቀኙን (ከሳሽንና ተከሳሽን ) ልክ ናችሁ በማለታቸው ግራ የተጋባው ችሎት ጸሓፊያቸው በድንገት ብድግ ይልና " ክቡር ዳኛ እንዴት ነው ነገሩ ? ከሳሽ የተናገረውም ልክ ከሆነ ተከሳሽ የተናገረውም ልክ ከሆነ ጥፋተኛ ማን ሊሆን ነው ? እንዴትስ ሆኖ ነው አንዱ ተበደልኩ ሌላው አልበደልኩም እያለ ሁለቱም ልክ የሚሆኑት ? እኔ ይኼ ነገር አልገባኝም " አለ። ዳኛው ወደ ጸሓፊያቸው እያዩ " ይገርማል አንተም ልክ ነህ " አሉት ይባላል።
ሸንበቆ " አቋምህ ምንድን ነው ?" ተብሎ ሲጠየቅ " ንፋስን ጠይቁት " አለ ይባላል ። እንደ ሸንበቆ አቋማቸው በሚነፍሰው ጊዜያዊ ነፋስ ላይ ብቻ የሚወሰንባቸው ብዙ ሰዎች አሉ ።በራሳቸው ልብ የማያስቡ ፣ በራሳቸው ህሊና የማይበይኑ ፤ ሁሉን እንደየስሜቱና እንደየፈቃዱ የሚዳኙ ፣ ከሁሉ ጋር መስሎና ተመሳስሎ ሕሊናን ሽጦ መኖር የለመዱ በርካቶች አሉ።
እንዲህ ያሉት ናቸው ዛሬ ፍትህ ሲጠፋ ፍርድ ሲጓደል ድሀ ሲበደል ሕዝብ በሌቦች ሲበዘበዝ እያዩ በተሰጣቸው የማስተዳደር ስልጣን ተጠቅመው ማስከበር እየቻሉ ሁሉን ሳያስቀይሙ ለመኖርና የግል ጥቅማቸውን ብቻ ለማስከበር ሲሉ እናንተም እነሱም ያነሳችሁት ጥያቄና ሐሳብ ትክክል ነው ሁለታችሁም ትክክል ናችሁ ተስማሙ እያሉ ብርሃንን ከጨለማ ጋር ሊደምሩ የሚተጉት።
እውነትን እንድፈር እውነትን ተናግረናት ከመሸብን እንደር።
እውነተኛ መሆን ማለት እውነትን በሚጠሉ ሰዎች መገፋት መጠላት ብሎም መሞት ነው።
በስዩም ይዘንጋው
Internship (Law)

Ethiopian Women Lawyers Ass...

Addis Ababa

About EWLA: The Ethiopian Women Lawyers Association (EWLA) is a not-for-profit Civil Society Organization (CSO) founded by Ethiopian women lawyers. It began its work in 1996 after being registered in 1995. It was re-registered as a charitable organization by the Charities and Societies Agency in 2010 as per the Charities and Societies Proclamation No.1113/2019. Its vision is to see a country where women are equal to men. It also has the mission of promoting the economic, political, social, and legal rights of women and, to that end, assisting them to secure full protection of their rights under the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia and other international human rights conventions. Since its establishment, EWLA has been working to achieve this vision and mission. EWLA has eight branch offices in Adama (Oromia Regional State), Bahir Dar (Amhara Regional State), Hawassa (SNNPRS), Asossa (Benishangul Gumuz Regional State), Gambella (Gambella Regional State), Dire Dawa City Administration, Jigjiga (Somali Regional State) and Semera (Afar Regional State). The Association has 54 volunteer committees that work at the zonal and woreda levels. The core program areas of EWLA include: Free Legal Aid Service, Public Education and Capacity Building, Research and Advocacy. Duties and Responsibilities: Assist and support project team members in completing the project Provide technical and logistic support including the scheduling of activities implementation, monitoring and evaluation and reporting Facilitate trainings, workshops and events Perform any other duties as required by the program manager and program coordinator Prepare and submit activity plan and implementation reports And other responsibilities as per the job description of the organization Location/Place of work: Addis Ababa, Head Office of Ethiopian Woman Lawyers Association located at Kirkos Sub-city, around Africa Union behind St. Michael Church Duration: 6 months with possibility of Extension Number required: 2 Educational Requirements: Law back ground Applicants are expected to fulfill the next criteria. Graduate from Faculty of Law and Accounting & Finance of a recognized university Passionate to serve women seeking legal aid service Possible exposure to project coordination experience will be a plus Female applicants encouraged for the position Required Experience: Entry Level (Fresh Graduate
2 Interns (Law)


Ethiopian Women Lawyers Association(EWLA)

JOB DETAILS: Duties and Responsibilities: • Assist and support project team members in completing the project • Provide technical and logistic support including the scheduling of activities implementation, monitoring and evaluation and reporting • Facilitate trainings, workshops and events • Perform any other duties as required by the program manager and program coordinator • Prepare and submit activity plan and implementation reports • And other responsibilities as per the job description of the organization • Location/Place of work: Addis Ababa, Head Office of Ethiopian Woman Lawyers Association located at Kirkos Sub-city, around Africa Union behind St. Michael Church Job Requirements • Law back ground Applicants are expected to fulfill the next criteria. • Graduate from Faculty of Law and Accounting & Finance of a recognized university • Passionate to serve women seeking legal aid service • Possible exposure to project coordination experience will be a plus • Female applicants encouraged for the position Job Experience: No Requirements Work Hours: 8 Level of Education: Bachelor Degree
አዲስ ፓስፖርት ማውጣት እንዲሁም ነባር ለማደስ ለምትፈልጉ በአካል መምጣት ሳይጠበቅባችሁ online እናመለክታለን ቀጠሮ እናሰጣለን።
https://t.me/casemanagers
https://t.me/casemanagers
https://t.me/casemanagers
New vacancy❗️👇👇👇
Internal/External

Reference No:  REC/ 105 /21
Job title:  Legal Advisor
Location:  Addis Ababa with travels to the field sites
Reports to:Systems Director
Closing date: December 19, 2021

About GOAL
GOAL is an Irish international humanitarian organization founded in 1977 and currently operational in 13 countries[1]; in both protracted crisis

and long-term development contexts. GOAL has four programmatic foci: people survive crisis; people have resilient health; people have food and nutrition security; and people have sustainable livelihoods.

Globally, GOAL’s systems approach guides our partnerships to create shared value and promote inclusive growth by linking communities, government, business, and civil society. These initiatives blend social and economic objectives, strengthening the bottom line whilst contributing to social, economic, and environmental outcomes for society. Partnering with the permanent players i.e., government, community & civil society and the private sector is key to improving the systems in which the people we work for live. GOAL works with corporate players to leverage; technology and skills, financial and business development service; and Micro, Small & Medium Enterprises (MSMEs) to increase access to goods and services and economic opportunities for poor people.

GENERAL DESCRIPTION OF THE ROLE

The Legal Advisor is responsible for providing accurate and timely legal advice to the organisation and its management on a variety of legal matters including but not limited to, Labour and Employment, Tax directives and government related guidelines, Immigration, Finance, Supplies, Service & Works contracts, and general operations. Responsibilities include conducting legal analysis and researching and evaluating different risk factors and offering proactive advice on possible legal issues. S/he must also know how to apply the law to the organisation’s circumstances. The Legal Advisor will maintain the country knowledge of laws and provide clarification on legal language and advise the organisation and its management accordingly. The Legal Advisor will regularly monitor and ensure the organisation’s compliance with local laws. In addition, this role will be responsible for handling the organisation’s legal responsibilities, organizing court order responses, preparing and review of contracts and documentation as well as providing a variety of legal support. The Legal Advisor will be delegated by the Country Director to legally represent on behalf of the organisation and expect to perform his/her duty with integrity complying with the rules and regulation of the country and organisation code of conduct policy.

KEY AREAS OF ACCOUNTABILITY/DUTIES:

·         Keeping up with current changes on all relevant areas of laws and contributing to the enhancement of the knowledge base of the organisation’s legal function

·         To conduct legal analysis and research on various legal matters of the organisation

·         To provide advice on different legal issues and assist in drafting legal opinions, memoranda, and other briefing documents

·         To be actively involved in preparing and drafting of different acts and legal submissions and draft the authoritative legal opinions as well

·         To conduct legal research by utilizing various resources and selecting the relevant material to analyze the legal information

·         To assist in reviewing the legal material and any other relevant documents and to identify the most important issues that need to be sorted out on a priority basis

·         To draw up formalities regarding the settlement of disputes and monitor the implementation of the legal clauses

·         Provide monthly legal reports and status to the Country Director and Systems Director
·         Give accurate and timely counsel to the organisation and management in a variety of legal topics not limited to, Labour Laws, Tax regulation, Data Protection, Employment, Immigration, Finance, Supplies, Service & Works contracts, and overall organisation’s operation

·         Research and evaluate different risk factors regarding business decisions and operations and apply effective risk management techniques and offer proactive advice on possible legal issues

·         Maintain current knowledge of alterations in legislation

Serve as liaison between the organisation and external attorneys.

Document and maintain legal files and issues.

High quality advice to the organisation and management on major legal issues and problems

·         S/he is responsible for formulating the best possible legal solution after analyzing the legal problem in depth.

·         S/he should be able to provide the much-needed legal assistance while dealing with legal tasks, litigations, contracts, dispute resolution and guide the organisation on taking an appropriate decision.

·         S/he should be skilled enough to come out with a desired outcome from the organisation’s point of view.

·         He/she should be able to take correct decisions and provide the necessary professional support.

·         S/he should advice whether all the court proceedings of the organisation are in compliance with the requirements of the legislation.

·         S/he will supervise, analyze and research the implication of laws, legislation, etc., that may affect the organisation business.

·         S/he advises the organisation to minimize legal exposure and liability

·         Collaborate with management to devise efficient defense strategies

·         Specify internal governance policies and regularly monitor compliance

·         Deal with complex matters with multiple stakeholders and forces

·         Support HR department in the preparation of disciplinary hearing documents.

·         Support in conducting investigations and prepare witnesses in advance of a disciplinary hearing.

Departments Support:

·         S/he will support in the review of supplier, contract of employment, donor and partners agreement reviews refencing to the relevant country laws

·         Provide clarification on legal language or specifications to the organisation and its management

·         Draft and solidify agreements, contracts, and other legal documents to ensure the organisation’s full legal rights

Work collaboratively with departments/sectoral heads to ensure compliance

Safeguarding:

To foster an inclusive working environment which is non-threatening and safe for all. An environment that addresses safeguarding adequately in its processes and where the barriers to raise and discuss concerns about safeguarding issues are identified and where possible mitigated.

Work Schedule:

The job of Legal Advisor is full time job and requires him/her to work in accordance to the organisation working and may be required to work after working hours

Values & Behaviors:

Strong commitment to upholding and promoting GOAL’s values; Respect, Integrity, Courage, Partnership and Humanitarianism.

Other duties:

Support in the review of HR handbook

Take lead in training staff on data protection policy

Network with GOAL Global Legal/Data Protection/HR departments to keep informed of disciplinary and employment contractual matters (related to HR)

Any other task assigned by the line manager.

COMMITMENTS:

GOAL’s recruitment procedure is fair and transparent which is also in line with the organization’s commitment to its integrity, honesty and culture. GOAL is committed to ensure that, its performance complies with the terms and conditions of relevant agreements, applicable laws & regulations.
Hence, pre-employment background checks will be conducted, and employees are required to read, understand, sign and implement different polices including safeguarding and child protection policy, Protection from Sexual Exploitation and abuse policy, sexual harassment policy, code of conducts and any other policy, rules and regulation of the organization. 

Job Requirements:

JOIN US

Do you want to join an exciting organization that brings high level impact to the community and add value to your professional advancement?  Then join us if you have:

·          Bachelor's/Master’s degree in law-related field

·         7 years’ experience as a Legal Counsel /lawyer and able to attend to routine administrative labour law among other related litigation tasks

·         Must be prepared to make ethical and moral decisions

·         Previous working experience as a Legal Counsel/ lawyer   in business/INGO sector

·         In-depth knowledge of administrative law and procedures

·         Good organisational, prioritization and time-management skills

·         Arbitration and mediation skills

·         Exemplary writing and editing skills, with proficiency in Microsoft Office: - Word, PowerPoint, Excel, Outlook etc.

·         Excellent communication, presentation, and interpersonal skills and analytical skills in both written and spoken; English, Amharic, and Afaan Oromo

·         Working well under pressure

·         Attention to detail

·         Ability to use your initiative.

·         Discretion in handling confidential matters and proactive approach to problem solving.

·         Excellent judgment and ability to anticipate legal issues or risks

·         High degree of professional ethics, integrity, and responsibility

Note: This description is not an exhaustive list of the skill, effort, duties and responsibilities associated with the position.

REMUNERATION and BENEFITS:

GOAL will pay a competitive basic salary based on the salary grading with addition benefits.

A chance to develop tangible experience.

Being part of a team who continue to make a real difference to the lives of the most vulnerable people.   

How To Apply:

APPLICATION PROCEEDURE:

Interested and qualified applicants need to submit ONLY once their non - returnable application with CV for one vacancy. The vacancy reference number along with the title & Duty station need to be written in the application letter and/or subject of the email. Applicants can apply using the following option.

Applicants can directly apply online usingwww.ethiojobs.net  orgoaljobs@et.goal.ie

GOAL strongly encourages female candidates to apply!

Only short-listed candidates will be contacted for an interview and exam.

Shortlisted candidates will need to submit other supporting documents upon request at later stage.

GOAL is not able to contribute towards any costs incurred by candidates during the recruitment process

Posted: 12.09.2021

Deadline: 12.19.2021

Job Category:
Human Resource and Recruitment, Legal, Management
Employment:

Location: GOAL Ethiopia

http://www.goal.ie/Ethiopia/159
የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ
Federal Document Authentication And Registration Agency


ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት

ቅርንጫፍ 1-ላንቻ
ቅርንጫፍ 2-መሳለሚያ
ቅርንጫፍ 3-መገናኛ
ቅርንጫፍ 4-ስድስት ኪሎ
ቅርንጫፍ 5-ጉለሌ
ቅርንጫፍ 6-አየር ጤና
ቅርንጫፍ 7-ቃሊቲ ቅርንጫፍ 8-ካሳንቺስ
ቅርንጫፍ 9-ንፋስ ስልክ ላፍቶ
ቅርንጫፍ 10-ልደታ
ቅርንጫፍ 11-ሲኤምሲ
ቅርንጫፍ 12-ቦሌ
ቅርንጫፍ 13-ጎጃም በረንዳ (መርካቶ)
ቅርንጫፍ 14 – ጀሞ

ተራ በመጠበቅ እና በወረፋ ጊዜዎን እንዳያጠፉ ቤትዎ እና ስራ ቦታዎ ሁነው
online ማንኛውም አይነት ጉዳይ እንሞላለን print አድርገው ብቻ የሚገለገሉበት ሲስተም ላይ አስገብተን በሚመችዎት መንገድ እንልክልዎታለን።
በቴሌግራም ብቻ ጉዳዮን ይጨርሳሉ።
https://t.me/GudayAsfetsami
@GudayAsfetsami
@GudayAsfetsami
በአዲሱ የንግድ ሕግ የተካተቱ አዳዲስ ጉዳዮች

1. መግቢያ
በሥራ ላይ የነበረዉ የንግድ ሕግ (1952 ዓ.ም) አገሪቷ ከደረሰችበት የንግድ እንቅስቃሴና ዘርፉ ከሚፈለገዉ ዕድገት አንፃር ብዙ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑ እና የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ የንግድ ሕጉን መፈተሽ እና ማሻሻያዎችን ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ አዲሱ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2014 ሆኖ ታትሞ ሥራ ላይ እንዲዉል ተደርጓል፡፡ አዲሱ የንግድ ሕግ ከዚህ በፊት ከነበረው አንጻር በርካታ ለውጦች ተደርገዉበታል። የሕጉ መውጣት የኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴን በአወንታዊ መንገድ ለመቀየር ከፍተኛ አስተዋጾ አለዉ። በዚህ አጭር ጽሁፍ የንግድ ሕጉን ዓላማዎች፣የንግድ ሕጉን ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት፣የንግድ ሕጉ ማሻሻል ያለዉ ጠቀሜታ እና አዳዲስ የተካተቱ ጉዳዮች የምንመለከት ይሆናል፡፡

2. የንግድ ሕግ ዓላማዎች
አንድ ግለሰብ ነጋዴ ወይም የንግድ ማኅበር በዕለት ተዕለት የንግድ እንቅስቃሴው ከተለያዩ አካላት ጋር የውል እና ከውል ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን ይፈጥራል።

ለምሳሌ፦ አንድ የንግድ ድርጅት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች ከሚያቀርቡ ድርጅቶች፣ ምርቶቹን እና አገልግሎቶቹን ከሚገዙት ደንበኞች ወይም ሸማቾች፣ ለድርጅቱ ብድር ከሰጡ ወይም በሌላ ምክንያት ከድርጅቱ ገንዘብ የመጠየቅ መብት ካላቸው ሰዎች፣ ከንግድ ተወዳዳሪዎቹ፣ ከተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ከድርጅቱ ሠራተኞችና ሥራ አመራሮች ጋር ግንኙነት ይኖረዋል፤ ድርጅቱ ከባለሀብቶቹ የተለየ የራሱ የሕግ ሰውነት ያለው የንግድ ማኅበር ሲሆን ደግሞ ከማኅበርተኞቹ ጭምር ግንኙነት ይኖረዋል። ከላይ ከተገለጹት የንግድ ድርጅት ከሚፈጥራቸው ዘርፈ ብዙ ግንኙነት አኳያ የንግድ ሕጎች ሁለት ዋና ዋና ዓላማዎች አሏቸው፦ አንደኛው ዓላማ አንድ የንግድ ድርጅት ከላይ በተመለከትናቸው ውስብስብ ግንኙነቶች ውስጥ ተንቀሳቅሶ ሀብት እንዲያፈራ እና አትራፊ እንዲሆን የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ማበጀት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከላይ ለተጠቀሱት ከአንድ የንግድ ድርጅት ጋር የተለያዩ ግንኙነቶች ለሚፈጥሩት አካላት መብቶች እና ቅቡልነት ያላቸው ፍላጎቶች ተገቢውን የሕግ ጥበቃ ማድረግ ነው። የንግድ ሕግ መድብል (ኮድ) እነዚህን ሁለት አንኳር ዓላማዎች ይጋራል። ይህ ሲባል ግን የንግድ ሕግ መድብል (ኮድ) ሁሉንም ከላይ የተመለከትናቸውን ግንኙነቶች አሟልቶ ይገዛል ማለት አይደለም።

3. የንግድ ሕጉን ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት እና ጠቀሜታ
የንግድ ህጉ አሁን ያለውን ዘመናዊውን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሊመልስ በሚችል መልኩ ካልተቀረፀ ወይም ካልተዘጋጀ በሀገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና የሚኖረው በመሆኑ የንግድ ህግ ዘመናዊ መሆን ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም አሁን የሚመጡ አዳዲስ ዕድገቶችን ታሳቢ ተደርጎ መረቀቅ እና በተጨባጭ ያንን ሊመልስ በሚችል መልኩ መሰራት አለበት፡፡ የእኛ ሀገር የንግድ ህግ ከብዙ ዓመታት በፊት የተዘጋጀ በመሆኑ አሁን ያለውን አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በንግድ ሂደት የሚፈጠሩ ችግሮች ሊመልስ የማይችልባቸው ምክንያቶች አሉ፡፡ ከነዛ መካከል አንዱ በንግድ ህጉ የተካተቱ በርካታ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ባለመሆናቸው፣የሚፈፀሙትም ቢሆን አሁን ካለው አጠቃላይ የንግድ እና ኢኮኖሚ እንቅሳሴ ጋር የማይሄዱ በመሆናቸው፣ በተለይም በሀገራችን ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ያለው ከማህበራት ጋር ተያይዞ የሚታዩ ክፍተቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም የነበረው የንግድ ህግ ሊመልሳቸው የሚገቡ ጥያቄዎችን መመለስ ባለመቻሉ የመጣ ችግር ነው፡፡ በመሆኑም ክፍተቶቹን በመፈተሽ አሁን ካለው እና ዘመኑ ከሚጠይቀው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ ዘመናዊ የንግድ ህግ ማደራጀት በማስፈለጉ የንግድ ህጉ እንደገና እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

በዚህ ሕግ መሰረት የትኛውም እንቅስቃሴ ከኢኮኖሚ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ለምሳሌ የንግድ ማህበራት የሚቆጣጠራቸው ሕጉ ነው፡፡ የንግድ ምዝገባ ለማድረግም መነሻ ህጋቸው ይህ ህግ ነው፡፡ የዚህ ሕግ ዘመናዊ ሆኖ መደራጀቱ ለነጋዴው፣ ለንግድ ማህበራት፣ ለ3ኛ ወገኖች እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን ዘመናዊ በሆነ መንገድ መደራጀታቸው ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዘመኑ የሚጠይቀው ሕግ ተደንግጎ የወጣ፣ አሁን ካለው የስራ እንቅስቃሴ ጋር አብሮ የሚሄድ እና ለነጋዴው ግልፅ የሆነ የንግድ ሕግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ለልማታዊ ባለሀብቶች የሚያመች ሁኔታ በመፍጠር ረገድ በርካታ ጠቀሜታዎች ያሉት በመሆኑ በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

4. አዳዲስ የተካተቱ ጉዳዮች
ነባሩ የንግድ ህግ ጥራዝ በስድስት መጽሀፍት የተደራጀ ሲሆን፣ በአንደኛ መጽሀፍ ስለንግድ ስራና ነጋዴዎች፣ በሁለተኛ መጽሁፍ ስለንግድ ማኅበራት፣በሶስተኛ መጽሀፍ ስለኢንሹራንስና የማጓጓዣ አገልግሎት፣በአራተኛ መጽሀፍ ስለባንክና ተላላፊ ሰነዶች (የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች)፣በአምስተኛ መጽሀፉ ስለኪሳራ ህግ ፣ በስድስተኛ መጽሀፍ መሸጋገሪያ ድንጋጌዎች ሆኖ ዝርዝር ጉዳዮችን አካትቶ የተሰነደ ነው። በተደረገዉ ጥናት መጽሐፍት 3 እና 4 የንግድ ሕግ አካል ሳይሆኑ ራሳቸዉን ችለዉ የፋይናንስ አገልግሎት መድብል / Code / እንዲሆኑ እና መጽሀፍ አንድ፣ሁለት እና አምስት የንግድ ሕግ ተብሎ እንዲሻሻል ተደርጎ በአዲሱ የንግድ ሕግ ወጥቷል፡፡ በአዲሱ አዋጅ ያልተካተቱት የባንክ፣ የኢንሹራንስና፣ የማጓጓዣ ዘርፎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በቀድሞው አሠራር መሠረት የሚቀጥሉ ሲሆን አዲሱ የንግድ ሕግ በርካታ ማሻሻያዎችን እና አዳዲስ አሰራሮችን የያዘ ሆኖ ወጥቷል። ከእነዚህ ጥቂቶቹን እንመልከት።

 አንድ ግለሰብ ለብቻው ኩባንያ መክፈት እንዲችል ተፈቅዷል
አዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 534 እንደሚያሳየዉ አንድ ግለሰብ ብቻውን ኩባንያን መመስረት እንዲችል ተፈቅዷል። ይህም ሰዎች በቀላሉ ወደ ሥራ እንዲገቡ ያግዛቸዋል ።
 የንግድ ትርጓሜን መቀየር
በተሻረው ሕግ የተዘረዘሩት የንግድ አይነቶች 21 ብቻ ናቸው። ከነዚህ ውጪ ያሉት ንግድ አይደሉም ተብለው እንደሚገመቱ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። አሁን ግን በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 5 መሰረት የንግድ አይነቶችን ወደ 37 አድገዋል። በዚሁ ሕግ የንግድ ትርጉም ክፍት ነው። በግልፅ ካልተከለከለ በስተቀር ያተርፋል ብሎ እንደሙያ የያዘውን ሥራ አስመዝገቦ መቀጠል ይችላል። ይህ መሆኑ ደግሞ አዳዲስ የንግድ አይነቶችንና የፈጠራ ሐሳቦችን ያበርታታል ።
 ኃላፊነታቸው የተወሰነ የሙያ ሽርክና ማኅበራት (አንቀፅ 221)
በአዲሱ የንግድ ህግ ውስጥ ከተካተቱ ጉልህ ለውጦች መካከል አንዱ የሆነው ይህ አዲስ የሽርክና ማህበር አይነት፣ ሰዎች በተለይም የሙያ ስራዎችን ለመስራት በሙያ ከሚመስሏቸው ሌሎች ሰዎችና ለሙያው ደጋፊ የሆነ አገልግሎት ሊሰጡ ከሚችሉ አጋሮቻቸው ጋር ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሆነው የሚያቋቁሙት፣ ኃላፊነቱም በሽርክና ማኅበሩ ሃብት ላይ ብቻ የተወሰነ የንግድ ማኅበር ነው በሚል በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 221 ላይ ተደንግጓል። ከቀደመው ሕግ በተቃራኒው አዲስ የጸደቀው አዋጅ ግለሰቦች በሙያቸው ተደራጅተው እንዲሠሩ በግልጽ ድንጋጌ አስቀምጧል። እያንዳንዱ ሙያ የሚጠይቀውን ሥነ ምግባር ይዘው ደንበኞቻቸውን የሚያስተናግዱ የሽርክና የሙያ ማኅበራት እንዲስፋፉ ያስችላል።

https://t.me/lawsocieties
በሌላ በኩል የቀድሞው ሕግ የአክስዮን ማኅበራት የዳይሬክተሮች የቦርድ አባላት ሁሉም የአክሲዮን ባለድርሻ እንዲሆኑ ግዴታ የጣለ ነበር። ነገር ግን በአዲሱ ሕግ ባለድርሻ መሆን ሳይጠበቅባቸው፤ ባለ ድርሻ ያልሆኑ ሰዎች በሙያቸው እስከ አንድ ሦስተኛ ድረስ የሚሆነውን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ቦታን እንዲይዙ ይፈቃዳል። ይህ አይነቱ የሽርክና ማኅበር የህግ አገልግሎትን፣ የሂሳብ መዝጋትና ኦዲት ወይም ሌላ አይነት ቴክኒካዊ እውቀትን በሚጠይቁና የሙያ ፈቃድ ቁጥጥር በሚደረግባቸው የስራ ዘርፎች ላይ በቅንጅት መስራት ለሚሹ ሙያተኞች አይነተኛ ምርጫ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም።
 የሆልዲንግ ካምፓኒ ስለ መፈቀዱ
በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 5 ስር በተመለከቱት ሥራዎች ላይ በመሰማራት በቀጥታ ራሱ ምርትና አገልግሎት ባያቀርብም በዚህ ተግባር በተሰማሩ ሌሎች የንግድ ማኅበራት ዉስጥ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ድርሻ የሚይዝ ኩባንያ ወይም ሆልዲንግ ካምፓኒ እንደ ነጋዴ እንደሚቆጥር አዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 9 ያመለክታል፡፡ በተጨማሪም ሆልዲንግ ካምፓኒ በቀጥታ ምርትና አገልግሎት ማቅረብ ይችላል፡፡

 ተራ የሽርክና ማህበርን የሚመለከተው የህጉ ክፍል ስለመቅረቱ፦
ነባሩ የንግድ ህግ ስለንግድ ተቋማት በሚዘረዝርበት ሁለተኛ መጽሀፉ ተራ የሽርክና ማህበርን ሰፊ ሽፋን የሰጠው ሲሆን በትንታኔው ግን ይህ አይነቱ ማኅበር በንግድ ስራ ውስጥ መሳተፍ እንደማይችል በግልፅ አስቀምጧል። እንግዲህ የንግድ ስራ ውስጥ መሳተፍ አይችልም የተባለ የሰዎች ስብስብ፣ በንግድ ህግ ጥራዝ ውስጥ እንደ ንግድ ተቋም መቀመጡ የህግ አመክንዮ የማይገኝለት በመሆኑ ውሳኔው ትክክለኛነቱ አያጠያይቅም።

 አክስዮን ማኅበርን በሚመለከተው የህጉ ክፍል አክሲዮኑ ለህዝብ ክፍት ስለሚሆን ማሕበር ሰፊ ሽፋን ስለመሰጠቱ፦
ኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ከሚሰራባቸው የንግድ ተቋማት አይነቶች ውስጥ ዋናውን ስፍራ የሚወስደው አክስዮን ማኅበር መሆኑ ይታወቃል። የባንክ እና የኢንሹራንስ ስራን የመሳሰሉ የፋይናንስ አገልግሎት ስራዎችን ለመስራት የተፈቀደለት ብቸኛው የንግድ ተቋም ፎርም አክስዮን ማኅበር ነው። በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 248 ላይ እንደተመለከተዉ የአክስዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት በሆነ የአክስዮን ሽያጭ የሚመሰረትበትን ሁኔታ አስቀምጧል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም ይህን መሰሉን ማህበር ለማቋቋም በሚሰሩት አደራጆች መብትና ግዴታ እንዲሁም ሀላፊነት ዙሪያ የተብራሩ ድንጋጌዎችን አካቷል፡፡

 በንግድ ድርጅቶች መካከል የሚፈጠርን ዝምድና (Affiliation) ለማስተዳደርና ለመቆጣጠር የሚሆን የህግ ክፍል ስለመካተቱ
የንግድ ማኅበራትን በሚመለከተው መጽሀፍ ሁለት ውስጥ በርዕስ ዘጠኝ በመጀመሪያው ምዕራፍ የተካተተው የኩባንያዎች መዛመድ ጽንሰ-ሀሳብ ሰፋ ያለ ዳሰሳና ጥናት የሚጠይቅ ጉዳይ ቢሆንም በዚህ የንግድ ህግ መካተቱ ምን አይነት ለውጦች ሊያስከትል እንደሚችል ልናነሳ ይገባል። አንድ ኩባንያ የሌላኛውን ኩባንያ አክስዮን የገዛ ከሆነ፣ ወይም እርስ በእርስ አክስዮኖች የተገዛዙ ከሆነ፣ ወይም በኩባንያዎቹ መካከል የሆልዲንግና ሰብሲዲየሪ (ተቀጽላ) ግንኙነት ካለ ወይም የአንድ ቡድን ኩባንያ (Group Company) አባላት ከሆኑ የተዛመዱ (Affiliated) ኩባንያዎች ይባላሉ። አዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 550 የኩባንያዎችን ዝምድና በመተንተን ሂደትም አንድን ኩባንያ የሆልዲንግ ኩባንያ አቋም የሚያሰጡት ሁኔታዎችና የአክሲዮንና የድምጽ መብቶች መጠን፣ ሆልዲንግ ኩባንያ በተቀጥላ (Subsidiary) ላይ ስለሚኖረው ልዩ ልዩ መብትና ስልጣን እንዲሁም ሆልዲንግ ኩባንያ ከዘጠና በመቶ በላይ የድምጽ መብት በሚኖረው ጊዜ ሌሎች የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ስለሚኖራቸው አማራጭ እና በተቀጥላ ኩባንያ ውስጥ ስላሉት የስራ አመራር አባላት ተጠያቂነት በዝርዝር ያስቀምጣል።

 የኪሳራ ህግን በሚመለከተው መጽሀፍ ውስጥ ዕዳን እንደገና ስለማደራጀት የሚመለከት ተጨማሪ ጽንሰ-ሀሳብ ስለመካተቱ፦
ማንኛውም ነጋዴ ይብዛም ይነስም በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ሲሰማራና ገንዘብና ጊዜውን ሲመድብ ይሳካልኛል የሚል ብርቱ እምነት ቢኖረውም ቅሉ፣ ጥቂት የማይባሉ ነጋዴዎች ግን እንዳሰቡት ሳይሳካላቸው ይቀርና ወደኪሳራ ያመራሉ። ነባሩ የኪሳራ ህግ፣ አንድ ነጋዴ ያሉበትን ዕዳዎች መክፈል ማቋረጡን እንደዋና ምክንያት በመያዝ፣ የአበዳሪዎችንና ሌሎች መብት ጠያቂዎችን ጥቅም ለማስከበር ሲባል የመክሰር ውሳኔ ሊተላለፍ እንደሚችል ያትታል። አዲሱ የንግድ ህግ በዚህ ረገድ አዲስና እጅግ ጠቃሚ የሚባል ዕዳን እንደገና ስለማደራጀት የሚገልፅ ክፍል በመክሰር ሂደት ውስጥ እንዲካተት አድርጓል። ለማሻሻያው ዋና መነሻ የሚሆነው የህጉ አላማ በጊዜያዊ የገንዘብ ችግር ምክንያት ዕዳ መክፈል ያቋረጡ ወይም ለማቋረጥ የተቃረቡ ነጋዴዎች እንደገና ተደራጅተው እንዲያገግሙ እድል መስጠት ነው። እዳን እንደገና ማደራጀት የሚባለው ባለዕዳው ያለበትን የዕዳ መጠን፣ አይነት እና የአከፋፈል ሁኔታዎች በሌላ የዕዳ ወይም የመብት አይነት፣ መጠንና የአከፋፈል ሁኔታዎች በፍርድ ሲለወጡ ነው። እዚህ ላይ ሳይጠቀስ መታለፍ የሌለበት ጉዳይ ዕዳን እንደገና የማደራጀት ተግባር የመክሰር ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ወይም ከተሰጠ በኋላ ሊከናወን የሚችል ሲሆን በዋነኝነትም የገንዘብ መብት ጠያቂዎች ፍላጎትና የፍርድ ቤት ውሳኔ እንደቅድመሁኔታ የሚጠቀሱ ተግባራት ናቸው።

በአጠቃላይ አዲሱ የንግድ ህግ በይዘትም ሆነ በቅርፅ መሰረታዊ የሚባሉ ለውጦችን የያዘ ሰነድ ሲሆን አንዳንድ ማሻሻያዎቹ የሌሎች ሀገራት የንግድ ህግጋትን መነሻ ተጨማሪ ጽንሰ ሀሳቦችን ያካተተ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በተጨማሪም ከተሻረው ሕግ በተቃራኒ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የሚከስሩ የንግድ ሰዎች ነጻ የሚሆኑበትን መንገድ አመቻችቷል፡፡ እነዚህን ጨምሮ ለንግድ እንቅስቃሴው የማይመቹ ሕጎችን ያሻሻለው የአዲሱ አዋጅ መውጣት በሀገር ውስጥ ያለውን የንግድ እንቅሰቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ያሳልጣል።

ፍትህ ሚኒስቴር
https://t.me/lawsocieties
Legal Officer job at Center for African Leadership Studies (CALS) & xHub Addis
Legal Officer
Center for African Leadersh...

Addis Ababa
Full–time
JOB DETAILS:
Job Brief responsible for monitoring all legal affairs within CALS and xHub Addis. The Legal Officer handles both internal and external legal concerns and is tasked with doing everything in their power to keep their organization out of legal trouble.
Summary
Date Posted: Friday, December 10, 2021 , Base Salary: Not Disclosed

JOB DETAILS:
Job Brief responsible for monitoring all legal affairs within CALS and xHub Addis. The Legal Officer handles both internal and external legal concerns and is tasked with doing everything in their power to keep their organization out of legal trouble

Job Requirements
• Bachelor of Laws (LL.B.) or Master of Laws (LL.M.)
• 3 - 5 years of experience in a law firm or multinational organization (private sector or NGO).

Work Hours: 8

Experience in Months: 36

Level of Education: Bachelor Degree

Job application procedure
Attach the following documents in one folder to the mentioned email
Tempo of degree
Well detailed Resume and cover letter
With the subject line "Legal Officer Dec 2021" email your application to ephratag.xhubaddis@gmail.com 

Job Brief responsible for monitoring all legal affairs within CALS and xHub Addis. The Legal Officer handles both internal and external legal concerns and is tasked with doing everything in their power to keep their organization out of legal trouble. Duties and Responsibilities In order to ensure that the best legal action is taken for the organization, Legal Officers perform a variety of important tasks; Provide Legal Advice- Using oral or written platforms, Legal Officer will be expected to brief a team of staff members on legal issues, potential liabilities, and possible courses of action. This involves translating complicated legal jargon (gibberish) into a language that everyone can understand, as well as taking all possible legal problems into consideration before making any recommendations. All recommendations which the Legal Officer makes must be in complete compliance with the law, and must also strive to minimize risk for their organization. Process Documents- Any sort of legal work involves a great deal of paperwork. Legal Officers will frequently need to write and review settlement documents, contracts, agreements, stock certificates, and more. This task makes up a significant portion of the day-to-day work of Legal Officers and requires both focus and precision. Perform Research- Since laws and regulations are always changing and being modified, it’s up to the Legal Officer to continuously research legal resources such as articles, codes, statutes, judicial decisions, and more. Doing so will allow the Legal Officer to stay up to date on all current laws and make well-educated legal recommendations. Identify Risks- Ideally, legal issues should be gripped in the bud before they even begin. This is why it’s essential for Legal Officers to regularly analyze the actions and decisions of the company in order to identify problem areas, suggest alternative courses of action and mitigate risk as much as possible. Review and provide legal advice on MOUs, Contracts, and tender documents. Liaise with relevant departments to ensure that where legal risks have been identified, appropriate courses of action have been taken. Provide legal protection and risk management advice to management especially on contract management.

https://t.me/lawsocieties
ማስታወቂያ
ጉዳይ አስፈፃሚዎችን ከሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማዎች እና ክልል ከተሞች መመዝገብ እንፈልጋለን።

ከዚህ በታች ባለው ቦት ይመዝገቡ❗️
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@Casemanager_bot
ይመዝገቡ🔷
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
https://t.me/GudayAsfetsami
የውክልና ስልጣን፣ አይነት እና አተገባበሩ
--------------****---------------
1. የውክልና ምንነት እና ፋይዳው
የሀገራችን የፍታብሔር ህግ አንቀጽ 2199 እንደሚደነግገው ወክልና ወካይ የተባለው ሰው ተወካይ ለተባለው ሰው እንደርሱ በመሆን አንድ ወይም ብዙ ህጋዊ ስራዎችን በእርሱ ስም እንዲያከናውን የሚሰጥ ስልጣን ነው፡፡ ተወካይ በውክልና የተሰጠውን ተግባር ሲያከናውን ሊመራባቸው የሚገባው መርሆች በህጉ የተቀመጡ ሲሆን እነዚህም፡- ተወካይ የሚያከናውነውን ተግባራት በወከለው ሰው ስም መሆን እንዳለበት፣ ተወካይ ወካይ በሰጠው የስልጣን ወሰን ውስጥ ብቻ ተግባሩን ማከናወን እንዳለበት፣ ተወካይ ወካዩ ከሰጠው ስልጣን ውጪ በመውጣት ለሚያከናውነው ተግበር ወካይ የማይጠየቅ መሆኑ (ስልጣን ባይሰጠውም ተግባሩን ካላፀደቀለት) የተቀመጡ መርሆች ናቸው፡፡
ውክልና የተለያዩ ጥቅሞች አሉት፡፡ ከነዚህ ጥቅሞች መካከል ወካይ በጊዜ እና በቦታ ሳይገደብ በአንድ ጊዜ የተለያዩ ተግባራትን እንዲያከናውን፣ የእውቀት እና ልምድ ማነስ ሳያግደው የተለየ እውቀት እና ልምድ በሚያስፈልገው ስራ ላይ በወኪሉ በኩል መከናወን መቻል፣ በህግ መሰረት ህጋዊ ሰውነት ያገኙ ተቋማት ምንም እንኳን የህጋዊ ሰውነት ቢኖራቸው እንደ ተፈጥሮዊ ሰው የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የማይችሉ በመሆኑ በውክልና ስልጣን በተሰጠው ተፈጥሮዊ ሰው ተግባራቸውን በውክልና ማከናወን እንዲችሉ ማድረጉ፣ እድሜቸው ለአቅመ አዳም ያልደረሱ እና ችሎታ ያጡ ሰዎች ህግ በሚስጣቸው ተወካዮች ጥቅማቸውን እንዲያስከብሩ ማስስቻል እንደ ውክልና ጥቅሞች ይጠቀሳሉ፡፡
2. የውክልና የስልጣን ምንጭ
ሶስት አይነት የውክልና ስልጣን ምንጮች ያሉ ሲሆን እነዚህም እንደሚከተለው ተብራርተዋል፡፡
2.1. በህግ የሚገኝ የውክልና ስልጣን
ይህ አይነቱ የውክልና ስልጣን የሚመነጨው ወካይ ለተወካይ ውክልናውን በእርሱ ፍላጎት እና ፍቃድ የሚሰጠው ሳይሆን የወካዩ ፍቃድ እና ፍላጎት በህግ ድንጋጌ መሰረት የሚገኝ የውክልና ስልጣን ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ተወካይ በህግ የሚሾምለት ሰው በተለያዩ ምክኒያቶች ጥቅማቸውን ማስከበር የማይችሉ እንደ ህጻና፣፤ በእድሜ ወይም በህመም ምክንያት የመወሰን ችሎታቸውን ያጡ ሰዎች ወይም ህጋዊ ሰውነት ያለቸው ድርጅቶች ሲሆኑ ህግ የነዚህን ግለሰቦች እና ህጋዊ ድርጅቶች መብት እና ጥቅሞች ሊያስከብሩ ይችላሉ በማለት የሚገምታቸውን ሰዎች እና የድርጅት ሥራ አስኪያጆች የውክልና ስልጣን ይሰጣቸዋል፡፡ በተለይ ጥቅማቸውን ለማስከበር የማይችሉ እንደ ህጻናት፣ በእድሜ ወይም በህመም ምክንያት የመወሰን ችሎታቸውን ያጡ ሰዎች የቅርብ ዘመዶች፣ በተወላጆች ወይም በትዳር አጋሮቻቸው የሚወከሉ ይሆናል፡፡
2.2. በውል የሚገኝ ውክልና
ይህ የውክልና አይነት በብዛት ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ወካይ ለተወካይ እርሱን የሚመለከቱ አንድ እና ከዛም በላይ የሆኑ ተግባራትን እንዲያከናውንለት በስምምነት የሚሰጠው የውክልና አይነት ነው፡፡ ይህ ውክልና ልዩ ውክልና ሲሆን ወካይ ለተወካይ በቀል፣ በጽሑፍ ወይም በዝምታ ሊሰጠው ይችላል፡፡ ይህ ውክልና በወካይ እና ተወካይ ስምምነት ላይ የሚመሰረት ነው፡፡
2.3. በፍርድ ቤት ውሳኔ የሚገኝ የውክልና ስልጣን
ይህ የውክልና ስልጣን በፍ/ሕ/ህጉ አንቀጽ 2253 እስከ 2255 መሰረት በፍ/ቤት የሚሰጥ ሲሆን አንድ የተወሰነ ስራን ወይም የተመደቡ ስራዎችን በሌላ ሰው ስም ሆኖ እንዲያከናውን ዳኞች ጠባቂ ባለአደራ ለተባለው ሰው ውክልና የሚሰጡበት የውክልና ስልጣን አይነት ነው፡፡ ይህም የሚሆነው እንደራሴ ይደረግለት የተባለው ሰው በአካባቢው የሌለ ወይም በህመም ወይም በሌላ ምክንያት ወኪል ማግኘት የማይችል ከሆነ እንደራሴ እንዲደረግበት ለሚያስፈልገው ሰው ባል ወይም ሚስት የሆኑ ወይም ዘመዶች ብቻ ወኪል እንዲሾምለት ለፍ/ቤት ማመልከት የሚችሉ ሆኖ በዳኞች የተሾመውም ወኪል አስቸኳይ የሆኑ ጉዳዮችን እንዲያከናውን ብቻ የሚፈቀድለት ይሆናል፡፡
3. ውክልና ሊያሟላ የሚገባው መስፈርቶች
ውክልና ከልዩ የውል ህጎች ውስጥ አንዱ ስለሆነ አንድ ህጋዊ ውል ሊያሟላ የሚገባውን በፍታብሔር ህጉ አንቀጽ 1678 ስር የተቀመጡትን መስፈርቶች ሊያሟላ ይገባል፡፡ ይህም አንድ ውል የፀና እንዲሆን ውል ለመዋዋል ችሎታ ባለው ሰው መሆን እንዳለበት፣ ጉድለት የሌለው ስምምነት መኖር፣ የሚቻል እና ህጋዊ የሆነ ጉዳይ፣ የውል ፎርም በህግ የታዘዘ ከሆነ ህጉ እንደሚያዘው ልዩ ፎርም መሆን አለበት፡፡
የፍታብሔር ህጉ አንቀጽ 2200 ወካይ ለተወካይ የውከልና ስልጣኑን በቃል ወይም በዝምታ ሊሰጥ የሚችል ሲሆን ነገር ግን ህጉ የውከልና ስልጣኑ በተለየ ፎርም መሰጠት አለበት በማለት የሚያዝ ከሆነ ይህን ማሟላት ይኖርበታል በማለት አስቀጧል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም የውክልና ውል አንድ ውል ሊያሟላ የሚገባውን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ የተሰጠው የውክልና ውል ፈራሽ ይሆናል፡፡
ነገር ግን የውክልና ውሉ በሚፈርስበት ጊዜ ተወካይ ከ3ኛ ወገን ጋር ያደረገው ውል እጣ ፋንታ ምን ሊሆን ይችላል በሚለው ጥያቄ ላይ በህጉ በግልፅ ያልተቀመጠ የፍ/ህግ አንቀጽ 1816 ላይ በተቀመጠው መሰረት በቅን ልቦና የተንቀሳቀሰውን 3ኛ ወገን ጥቅም ሊጎዱ የሚችሉ በሚሆንበት ጊዜ ውሉ ፈራሽ የማይሆን መሆኑ በዚህ ሁኔታ ጥቅም ላይ እንደሚውል የሚነሳ ሲሆን በወካይ እና በተወካይ መካከል ያለው ግንኙነት ተወካይ የውክልና ስልጣን ውል መሰረት ከ3ኛ ወገን ጋር ከሚያደርገው ግንኙነት ተለይቶ መታየት ስላለበት የውክልናው ውል ቀሪ እና ፈራሽ መሆን ተወካይ እና 3ኛ ወገን ያደርጉትን ውል ቀሪ ሊያደርገው አይገባም የሚል ክርክርም ይነሳል፡፡
4. የውክልና አይነቶች
ሁለት የውክልና አይነቶች ያሉ ሲሆን እንደሚከተለው ተብራርተዋል፡፡
4.1. ጠቅላላ ውከልና
ይህ የውክልና አይነት በጠቅላላ አነጋገር የሚደረግ የውክልና አይነት ሲሆን ይህም ተወካይ የአስተዳደር ስራዎችን ብቻ ለመስራት የሚያስችለው ነው፡፡ በፍታብሔር ህጉ አንቀጽ 2204 መሰረት የአስተዳደር ስራዎች የሚባሉት፡- የወካዩን ሀብት ማስቀመጥ/መጠበቅ፣ ከ3 አመት ለማያልፍ ዘመን ማከራየት፣ በብድር የተሰጠውን ሀብት የመሰብሰብ፣ ከሀብቱ የሚገኘውን ገቢ ተቀብሎ የማስቀመጥ፣ ለተከፈለ እዳ ደረሰኝ የመስጠት፣ ሰብሎችን መሸጥ፣ ለሽያጭ የተመደቡ የንግድ እቃዎችን ወይም ይበላሻሉ ተብለው የሚታሰቡ ነገሮችን መሸጥ ናቸው፡፡
4.2. ልዩ ውክልና
ይህ ውክልና ወካይ ለተወካይ ከአስተዳደር ስራዎች ወጪ የተለየ ተግባር እንዲፈጽምለት በመግለጽ የሚሰጠው የውክልና አይነት ሲሆን ልዩ ውክልና የተሰጠው ሰው የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መሸጥ፣ አስይዞ መበደር፣ በካፒታሎች ላይ እንቬስት የማድረግ አክሲዮኖችን የመግዛት የመሸጥ በመሃበር የመግባት፣ ስጣታን ማድረግ፣ በአንዳንድ ጉዳይ ፍ/ቤት ቀርቦ መከራከር እና የመሳሰሉ ተግባራትን ለመፈጸም የሚያስችለው የውከልና አይነት ነው፡፡
5. የወካይ እና የተወካይ ግዴታዎች
5.1. የተወካይ ግዴታዎች
ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ማሳየት- ተወካይ ለወካዩ ፍጹም ታማኝ እና ግልጽ መሆን ያለበት ሲሆን ወካዩ ውክልናውን ለማስቀረት ወይም የውክልና ቃሉን ለመቀየር የሚያስችሉ ነገሮች በሚከሰቱበት ወቅት ለወካዩ የማሳወቅ ሀላፊነት አለበት፡፡ እንዲሁም ስራውን በሚያከናውንበት ወቅት የወካዩን ጥቅም ለማስከበር መንቀሳቀስ ያለበት ሲሆን ያለ ወካዩ ፍቃድ እና እውቅና ምንም ጥቅም መውሳድ የለበትም፡፡ በተጨማሪም ተወካይ በውክልናው ምክንያት ያገኛቸውን መረጃዎች ወካዩን በሚጎዳ መልኩ
ሊጠቀምባቸው አይገበም፡፡
የውክልናው ሒሳብ አያያዝ- ተወካይ የሚያደረጋቸውን የገንዘብ እንቅሳቃሴዎችን ገቢ እና ትርፎችን፣ ወጪ እና ኪሳራዎችን የመመዝገብ እና ለወካዩ የማሳወቅና ገቢ የማድረግ ሀላፊነት ያለበት ሲሆን ተወካይ ለወካዩ ሊሰጠው የሚገባውን ገንዘብ ለራሱ አውሎት እንደሆነ ከወሰደበት ቀን ጀምሮ አንድም ማስጠንቀቂያ ሳያስፈልገው ከነወለዱ እንዲከፍል የሚደረግ ይሆናል፡፡
አስፈላጊ ትጋት ማሳየት- ተወካዩ የተሰጠውን ሀላፊነት በከፍተኛ ትጋት እና ጥንቃቄ የማከናወን ሀላፊነት ያለበት ሲሆን ይህን ባለመድረጉ በወካይ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
የሒሳብ ማቅረብ ግዴታ- ተወካይ ወካዩ በጠየቀው ጊዜ የስራውን አካሄድ መግለጫና ሒሳብ በየጊዜው የማቅረብ ግዴታ እና የተሰጠውን ውክልና በአግባቡ መፈጸሙን በየጊዜው ለወካዩ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡
የተወከለበትን ሥራ በእራሱ የመፈጸም ሀላፊነት- ተወካይ የተወከለበትን የስራ ተግባር እራሱ የመፈጸም ሀላፊነት አለበት፣ ነገር ግን በእርሱ ፋንታ ሌላ ሰው ወክሎ ማሰራት የሚችለው፡- የወከለው ሰው ሲፈቀደለት፣ በልማዳዊ ደንብ እና አሰራር መሰረት ሌላ ሰው ተክቶ ማሰራቱ ተወካዩ እራሱ እንደሰራው የሚያስቆጥር እንደሆነ፣ ተወካዩ ጊዜ የማይሰጥ ድንገተኛ መሰናክል የገጠመው እንደሆነ እና በወቅቱ ለወካዩ ለማሳወቅ በቂ ጊዜ የሌለው እና የወካዩን ጥቅም ለማስከበር የስራው ሁኔታ የሚያስገድደው እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
ከዚህ ውጪ ተወካይ በራሱ ፍቃድ ወክሎ የሚያሰራው ሰው በሚያከናውነው ተግባር ለሚደርሰው ጉዳት ተወካይ እራሱ እንደፈጸመው ተቆጥሮ ሙሉ ሀላፊነቱን የሚወስድ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከላይ በተገለጹት ሁኔታ ሌላ ሰው ወክሎ ተወካዩ በስራው ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ተወካዩ የሚጠየቀው የወከለውን ሰው ሲመርጥ መድረግ የሚገባውን ጥንቃቄ ባለማድረጉ እና ለተተኪው ተገቢውን የስራ መመሪያ እና ትዕዛዝ ሲሰጥ ለሚፈጽመው ስህተት እና ጉድለት ይሆናል፡፡
5.2. የወካይ ግዴታዎች
የድካም ዋጋ መክፈል- ወካዩ በውላቸው ላይ የተመለከተውን የድካም ዋጋ ለተወካይ የመክፈል ሀላፊነት ያለበት ሲሆን በውላቸው ላይ ይህ ያልተካተተ እንደሆነ የስራ ዋጋ በተለምዶ አሰራር ለሞያው ሊከፈለው የሚገባ በቦታው የዋጋ ልክ መስታወቂያ ታሪፍ እና ልማዳዊ ህግ መሰረት ታስቦ ለተወካይ የሚከፈለው ይሆናል፡፡
ተቀዳሚ ተከፋይ እና ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ- ለተወካይ ስለ ውክልናው ሥራ ማስኬጃ እና ማከናወኛ የሚሆን ተቀዳሚ ተከፋይ ወጪ ሊሰጠው የሚገባ ሲሆን ተወካይ ለተወከለበት ሥራ ሲል ላወጣው ወጪ ወጪው ከወጣበት ቀን ከሚታሰብ ወለድ ጋር ተስቦ ሊከፈለው ይገባል፡፡
ግዴታ እና ኪሳራ- ተወካይ ለወካዩ የስራ ጥቅም እና ውጤት ሲል የገባውን የውል ግዴታዎች ውስጥ ነጻ ሊያወጣው እና ተወካይ የተወከለበትን ስራ በሚያከናውንበት ወቅት የራሱ ጥፋት ከሌለበት ለሚደርስበት አደጋ ኪሳራውን ሊከፍለው ይገባል፡፡
በአጠቃላይ ወካይ የስራው ጉዳይ ተገቢውን ውጤት አላስገኘም በማለት ለተወካይ ሊከፍለው የሚገባውን ገንዘብ መከልከል የማይችል ሲሆን ተወካይ በስራው ወቅት ላደረሰው ጥፋት ልክ ሊከፍለው ከሚገባው ገንዘብ ጋር ማቻቻል ይችላል፡፡ ተወካይም በበኩሉ ወካይ ሊከፍለው የሚገባውን ገንዘብ ያልከፈለው እንደሆነ በስራ ምክንያት እጁ የገባውን አቃ ሊከፈለው የሚገባውን መጠን ልክ የሚያወጣ እቃ በመያዣነት ሊይዝ ይችላል፡፡
6. ስለውክልና መቅረት
6.1. ውክልናን በመሻር
ወካይ አስፈላጊ መስሎ ከታየው የሰጠውን የውክልና ስልጣን የመሻር እና ተወካይ የውክልና ውል እንዲመልስለት ሊያስገድደው ይችላል፡፡ ነገር ግን ተወካይ የተሰጠውን የውክልና ውል ለመመለስ ፍቃደኛ በማይሆንበት ወቅት ወካዩ በምን አይነት ሁኔታ ሊያስገድደው እንደሚችል ህጉ በግልጽ አልተቀመጠም፡፡ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወካይ ተወካይ በእርሱ እና በ3ኛ ወገኖች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሰጠውን ውክልና በማንሳት ለሚመለከታቸው አካላት እና በውክልናው ምክንያት ሊጎዱ የሚችሉ ወገኖችን ስለውክልናው መሻር ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም የውክልና ውሉን ተወካይ እንዲመልስለት በፍርድ ቤት ለመጠየቅ ይችላል፡፡
የተሰጠው የውክልና ጊዜ ከማለቁ በፊት የውክልናው መሻር በተወካይ ላይ ኪሳራ አድርሶበት እንደሆነ ወካይ ተወካይ ላይ በውሉ መሻር ምክንያት ለደረሰበት ኪሳራ ካሳ የመክፈል ሀላፊነት አለበት፡፡ ብዙ ወካዮች ለጋራ ጉዳያቸው የወከሉትን ተወካይ በቂ የሆነ ምክንያት ከሌለ በቀር ወካዮቹ በሙሉ ሳይስማሙበት አንዱ ወካይ ብቻውን ተወካዩን ሊሽረው አይችልም ፡፡
6.2. ወኪሉ የውክልና ስልጣኑን ሲተው
ተወካዩ የውክልናውን ሥራ እንደሚተው ለወካዩ አስታውቆ ወክልናውን መተው የሚችል ሲሆን የውክልናውን ሥራ መተው በወካዩ ላይ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ ተወካይ ለደረሰው ኪሳራ ካሳ የመክፈል ሀላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም ተወካይ የውክልናውን ስራ መቀጠሉ በእርሱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ኪሳራ የሚያስከትልበት መሆኑ ከታወቀ እና ሥራውንም ለመቀጠል በፍጹም የማያስችል ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠ ማንኛውንም የጉዳት ኪሳራ እንዲከፍል አይገደድም፡፡
6.3. ውክልና ቀሪ የሚሆንባቸው ሌሎች ምክንያቶች
የወካዩ ወይም የተወካዩ መሞት፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ በስፍራው ያለመኖር የተረጋገጠ እንደሆነ፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ ለመስራት ችሎታ ማጣት፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ ኪሳራ ደርሶበት በንግድ ኪሳራ ላይ መውደቁእና የተረጋገጠበት እንደሆነ ውክልና ቀሪ ይሆናል፡፡
ብዙ ተወካዮች አንድ አይነት ጉዳይ እንዲያከናውኑ ተወክለው እንደሆነ ከመካከላቸው አንዱ የውክልና ስራውን ከተጠቀሱት ምክንያቶች በአንዱ መቀጠል ያልቻለ እንደሆነ እና የውክልና ስራውን ካቋረጠ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የአንዱ መቋረጥ የሌሎችንም ተወካዮች የውክልና ስልጣን የሚያቋርጥ ይሆናል፡፡
Source:- FDRE Attorney General
ክፍል ፫

ጋብቻ በንብረት በኩል ስለሚኖረው ውጤት

አንቀጽ ፶፯ የባልና ሚስት የግል ሀብት (፩) ያለግብይት የተገኙ ንብረቶች

ባልና ሚስት ጋብቻቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜ በየግል የነበሯቸው ንብረቶች ወይም ከጋብቻ በኋላ በውርስ ወይም በስጦታ በየግላቸው ያገኙዋቸው ንብረቶች የግል ንብረቶቻቸው ሆነው ይቀራሉ፡፡

አንቀጽ ፶፰ (፪) በግብይት የተገኙ ንብረቶች

፩. ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ አንዱ የግል ሀብቱ በሆነ ንብረት ለውጥ ያገኘው ወይም በግል ገንዘቡ የገዛቸው ወይም የግል ንብረቱን ሸጦ የሚያገኘው ገንዘብ የግል ሀብቱ ይሆናል፡፡

፪. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተመለከተው ድንጋጌ ተፈፃሚ የሚሆነው በግብይት የተገኘው ንብረት የግል ይባልልኝ ብሎ አንደኛው ወገን ጥያቄ ሲያቀርብ እና ፍርድ ቤት ሲያፀድቀው ብቻ ነው፡፡

አንቀጽ ፶፱ የግል ሀብትን ስለማስተዳደር (፩) መሠረቱ

፩. እያንዳንዱ ተጋቢ የግል ሀብቱን ራሱ ለማስተዳደርና ገቢውንም ለመቀበል ይችላል፡፡

፪. እያንዳንዱ ተጋቢ የግል ሀብቱን ራሱ ሊያዝበት ነፃነት አለው፡፡

አንቀጽ ፷ (፪) የግል ሀብት አስተዳደርን በጋብቻ ውል ስለመወሰን

፩. ባልና ሚስት አንደኛው የሌላውን ተጋቢ የግል ሀብት በሙሉ ወይም በከፊል እንዲያስተዳድርለት እና እንደአስፈላጊነቱ እንዲያዝበት በጋብቻ ውላቸው ሊወስኑ ይችላሉ፡፡

፪. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) በተመለከተው አኳኋን ንብረት የማስተዳደር ሥልጣን የተሰጠው ተጋቢ በሌላኛው ተጋቢ ሲጠየቅ ስለንብረቱ አስተዳደር ዓመታዊ የሂሳብ መግለጫ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ ፷፩ (፫) ስለውክልና ሥልጣን

ከተጋቢዎች አንዱ የግል ሀብቱን በሙሉ ወይም በከፊል እንዲያስተዳድርለት ለሌላኛው ተጋቢ ውክልና መስጠት ይችላል፡፡

አንቀጽ ፷፪ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት

፩. ባልና ሚስት ከግል ጥረታቸውና ከግል ወይም ከጋራ ንብረታቸው የሚያገኟቸው ገቢዎች ሁሉ የጋራ ሀብቶቻቸው ይሆናሉ፡፡

፪. በዚህ ሕግ በአንቀጽ ፶፰ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት የአንደኛው ተጋቢ የግል ሀብት ነው ካልተባለ በስተቀር፣ ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ በግብይት የሚያገኙት ንብረት ሁሉ የጋራ ሀብታቸው ይሆናል፡፡

፫. በስጦታው ውል ወይም በኑዛዜው ቃል በሌላ አኳኋን ካልተመለከተ በስተቀር፣ በስጦታ ወይም በኑዛዜ ለተጋቢዎቹ የተሰጧቸው ንብረቶች ሁሉ የጋራ ሀብቶቻቸው ይሆናሉ፡፡

አንቀጽ ፷፫ የሕግ ግምት

፩. አንደኛው ተጋቢ የግል ሀብቱ መሆኑን ካላስረዳ በስተቀር ማንኛውም ንብረት በአንደኛው ተጋቢ ስም ብቻ የተመዘገበ ቢሆንም እንኳን የጋራ ሀብት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡

፪. የግል ንብረት መሆኑን ሦስተኛ ወገኖች የሚያውቁት ወይም ሊያውቁት የሚገባ ካልሆነ በስተቀር፣ ባልና ሚስቱ ወይም ከሁለቱ አንዱ ይኸው ንብረት የግል ነው በማለት በሦስተኛ ወገን ላይ መቃወሚያ አድርገው ሊያቀርቡት አይችሉም፡፡

አንቀጽ ፷፬ ስለባልና ሚስት ገቢ (፩) መደበኛ የገቢ አስተዳደር

፩. ባልና ሚስት እያንዳንዳቸው ገቢያቸውን በየራሳቸው ይቀበላሉ፡፡

፪. ባልና ሚስት በየግላቸው የሚያገኙትን ገቢ የግል ወይም የጋራ የባንክ ሂሳብ በመክፈት ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡

፫. ከባልና ከሚስት አንደኛው ሲጠይቅ፣ ሌላኛው ተጋቢ ያገኘውን የገቢ መጠን የማስታወቅ ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ ፷፭ (፪) ልዩ ሁኔታ

፩. ከባልና ከሚስት አንዱ፣ ገቢውን ሌላኛው ተጋቢ እንዲቀበልለት ሥልጣን ለመስጠት ሙሉ ነፃነት አለው፡፡

፪. ከባልና ከሚስት በአንደኛው ጠያቂነት የአንደኛውን ገቢ ሌላኛው ተጋቢ እንዲቀበልና ለመቀበሉም ደረሰኝ እንዲሰጥ ፍርድ ቤት ሊወስን ይችላል፡፡

፫. በሌላ ሕግ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር፣ ከባልና ከሚስት የአንደኛው ገቢ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲከበር በፍርድ ቤት ሊታዘዝ ይችላል፡፡

አንቀጽ ፷፮ የጋራ ሀብትን ስለማስተዳደር

፩. ከባልና ከሚስት አንዱ፣ የጋራ ሀብታቸውን በሙሉ ወይም በከፊል እንዲያስተዳድር ግልጽ ስምምነት ከሌለ በስተቀር ባልና ሚስቱ የጋራ ሀብታቸውን በጋራ ያስተዳድራሉ፡፡

፪. ከባልና ከሚስት አንዱ ችሎታ የለውም ተብሎ ሲወሰን ወይም ንብረት የማስተዳደር መብቱን ሲገፈፍ ወይም በሌላ ማናቸውም ምክንያት የጋራ ሀብታቸውን ለማስተዳደር የማይችል ሆኖ ሲገኝ ሌላኛው ተጋቢ የጋራ ሀብቱን የማስተዳደሩን ተግባር ያከናውናል፡፡

አንቀጽ ፷፯ የማስታወቅ ግዴታ
ከተጋቢዎች አንዱ ብቻ የጋራ ሀብታቸውን በሚያስተዳድርበት ጊዜ የሀብቱን አስተዳደር በተመለከተ ለሌላኛው ተጋቢ መረጃ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ ፷፰ (፩) የተጋቢዎች ስምምነት አስፈላጊ ስለመሆኑ
በሌላ ሕግ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር፣ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ የተጋቢዎቹ ስምምነት አስፈላጊ ነው፤
ሀ) የጋራ የሆነውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ፣ ለመለወጥ፣ ለማከራየት በመያዣ ወይም በዋስትና ለመስጠት ወይም በሌላ በማናቸውም ሁኔታ በዚሁ ንብረት ላይ ሌሎች ሰዎች መብት እንዲያገኙ ለማድረግ፤

ለ) ዋጋቸው ከብር ፭፻ (አምስት መቶ) በላይ የሆኑ የሚንቀሳቀሱ የጋራ ንብረቶችን ወይም የገንዘብ ሰነዶችን፣ ለመሸጥ፣ ለመለወጥ በመያዣ ወይም በዋስትና ለመስጠት ወይም በሌላ በማናቸውም ሁኔታ ለማስተላለፍ፤

ሐ) ከብር ፻ (አንድ መቶ) በላይ ዋጋ ያለውን የጋራ ንብረት ወይም ገንዘብ ለሌላ ሰው በስጦታ ለማስተላለፍ፤

መ) ከብር ፭፻ (አምስት መቶ) በላይ ለመበደር ወይም ለማበደር ወይም ለሌላ ሰው ዋስ ለመሆን፡፡

አንቀጽ ፷ (፪) የስምምነት አለመኖር ስለሚያስከትለው ውጤት

፩. አንደኛው ተጋቢ ከዚህ በላይ የተመለከተውን ድንጋጌ ባለማክበር የውል ግዴታ ገብቶ የተገኘ እንደሆነ፣ ሌላኛው ተጋቢ ለፍርድ ቤት በሚያቀርበው ጥያቄ ግዴታው ሊፈርስ ይችላል፡፡

፪. ግዴታው እንዲፈርስ የሚቀርበው ጥያቄ ጠያቂው ወገን ግዴታው መገባቱን ከአወቀበት ቀን ጀምሮ ከስድስት ወር በኋላ ወይም በሌላ በማናቸውም ሁኔታ ግዴታው ከተገባ ከሁለት ዓመት በኋላ ሊቀርብ አይችልም፡፡

አንቀጽ ፸ የባልና ሚስት ዕዳ

፩. ከባል ወይም ከሚስት በግል የሚጠየቅ ዕዳ፣ ከባለዕዳው ተጋቢ የግል ሀብት፣ የግል ሀብቱ ዕዳውን ለመሸፈን በቂ በማይሆንበት ጊዜ ከጋራ ሀብታቸው ይከፈላል፡፡

፪. ዕዳው የመጣው ለትዳራቸው ጥቅም ከሆነ ከጋራ ሀብታቸው የጋራ ሀብታቸው፣ ዕዳውን ለመሸፈን በቂ በማይሆንበት ጊዜ ከባል ወይም ከሚስት የግል ሀብት ይከፈላል፡፡

አንቀጽ ፸፩ ለትዳር ጥቅም እንደተደረገ የሚቆጠር ዕዳ
የሚከተሉት ዕዳዎች ለትዳር ጥቅም እንደተደረጉ የሚቆጠሩ ናቸው፡፡

ሀ) ለባልና ለሚስት እንዲሁም ለልጆቻቸው የዕለት ኑሮ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለማሟላት የተገቡ ዕዳዎች፤

ለ) ባል ወይም ሚስት ቀለብ ለመስጠት ያለባቸውን ግዴታ ለመወጣት የተደረጉ ወጪዎች፤

ሐ) ከባልና ከሚስት በአንደኛው ወይም በዕዳ ጠያቂው አለመልካችነት ለትዳር ጥቅም ስለመሆኑ ፍርድ ቤት የተቀበለው ሌላ ዕዳ፡፡
አንቀጽ ፸፪ የትዳር ወጪዎችን ስለመሸፈን
ተጋቢዎች የትዳራቸውን ወጪ ለመሸፈን እያንዳንዳቸው እንደየአቅማቸውና ችሎታቸው አስተዋጽኦ ማድረግ አለባቸው፡፡
አንቀጽ ፸፫ በተጋቢዎች መካከል ስለሚደረጉ ውሎች
ባልና ሚስቱ ተጋብተው በሚኖሩበት ጊዜ በመካከላቸው የሚያደርጓቸው ውሎች፣ ፍርድ ቤት ካላፀደቃቸው በስተቀር ውጤት አይኖራቸውም፡፡