አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
share 👍 @lawsocieties
ጉዳይ አስ/ፈፃሚ ለመቀላቀል እና
ለጉዳይ አስ/ፈፃሚ መልዕክት ለመላክ ይጫኑት -👇👇👇👇👇👇👇👇👇
መልዕክት ለመላክ ይጫኑት 👇👇👇
Junior Legal Advisor (Intern)

Hailu Tessema Legal Consultancy Services

Position: Junior Legal Advisor (Intern)

Job Time: Full-Time

Job Type: Internship

Place of Work: Addis Ababa, Ethiopia

Application Deadline: Oct, 5/2021 (6 days left)

We are looking for a passionate Law graduate in the Junior Legal Advisory Internship position. This job is for you if you want to gain deep practical experience in the legal environment, working with a renowned lawyer in Addis Ababa with over 30+ years of experience. This job requires you to perform different legal tasks under the supervision of a Senior Legal Advisor. We accept passionate, dedicated recent law graduates with zero years of experience.

Professionalism, politeness and quick communication is a NECESSITY for this job!

Requirement:

Proficiency in Amharic and English. Other languages are a plus.

Attention to detail

Experience in using Microsoft Word and other related applications

Excellent time management skills

Solid organizational skills

Computer typing skills both Amharic and English

Educational level:

Degree in Law from any university

Responsibilities:

Preparing legal reply for accusations made against clients

Preparing case documents for new clients

Gathering evidences for cases

Analyzing court documents and advising Senior Legal Advisor or clients

Preparing customer documents and keeping online records

Typing hand written case documents using computer Word applications

Length of internship - 6 months

Location of work - Addis Ababa, around Kazanchis Urael Church

Salary: Unpaid

If you are hard working and fit for the position, you will be provided with an employement contract upon the end of the internship period.

How to apply

If you are interested and believe you have the necessary requirements for this position, write a short paragraph (250 words max.) explaining why we should hire you for this position and send your personalized resume quoting "Internship Application for Junior Legal Advisory Position" on the email subject to HailuTessemaLegalServices@gmail.com

If you do not hear from us, it means you were not chosen for the role. Thank you for your interest.
https://t.me/EthiopiaLawyer
Legal Aid

Debub Global Bank S.C

Addis Ababa

Full–time

Job Title: Legal Aid Company: Debub Global Bank Location: Addis Ababa Salary: Attractive Deadline: October 2, 2021 Job Requirement
• Education (Minimum): College Diploma in Law.
• Experience: 2 years of relevant experience Place of work: Addis Ababa
How to Apply
• Application Dead line: 5 working days (Sept. 28-Oct 2, 2021) starting from the date of announcement on the newspaper
• Interested applicants should submit their non-returnable applications along with CV and photocopies of other relevant documents through post office only.
• Debub Global Bank S.C
• Human Resources Management Dep’t
• P.O. Box 100743 • Addis Ababa

https://t.me/EthiopiaLawyer
Intermediate Attorney


Addis Credit and Saving Institution S.C/ADCSI/

Addis Ababa

Job Description - Number of job position: 3 - Salary:- 17,665.00 - Place of work:- A.A Akaki Kality, Kolfe, Neface selk Area office Job Requirements - LLB degree/ diploma (Level IV) IN law. - 4/6 years of relevant experience and basic computer
How to Apply
N.B - Employment condition for all job positions:- permanent - Other benefits for all job positions:- as per the institutions benefit package designed - Qualified applicants should present their application with none returnable copy of cv, educations certificaties supported by student copies, written experience from respective institutions or offices, and origienal certificate document of each for registration. - Direct job Experience is preferable and considerable. - All applicants Registration date According to Alpabeatical order A up to E= Tuesday, F up to J-= Wensday, K up to 0 = Tursday, P up to T = Friday, U up to Z = Monday - Addis Credit and saving institutions Head quarter located at churchill road 1st floor office number 111 - For more information, call 0111-26-26-88, 0111-11-15-12
https://t.me/EthiopiaLawyer
Legal Assistant

Dagnachew and Mahlet Law Office (DMLO)
Addis Ababa
Full–time
The ideal candidate will ensure smooth running of the office and effective case management by providing legal services under the supervision of an attorney. This individual will communicate frequently with the clients in order to serve them adequately. Additionally, this candidate will conduct necessary case research to aid the legal proceedings. Responsibilities
• Provide administrative support to lawyer • Handle communication with clients
• Locate and develop case relevant information Qualifications
• Bachelor's degree in Law
• Familiarity with law, legal procedures, and protocols
Apply on LinkedIn

https://et.linkedin.com/jobs/view/legal-assistant-at-dagnachew-and-mahlet-law-office-dmlo-2737174269?refId=mBLbeIPcN9aLXwVHiOgvaQ%3D%3D&trackingId=5tvqFMprBreQ%2BCK2CSgtsw%3D%3D&position=5&pageNum=0&trk=public_jobs_jserp-result_search-card&utm_campaign=google_jobs_apply&utm_source=google_jobs_apply&utm_medium=organic

https://t.me/EthiopiaLawyer
Sr. legal contract administration officer

Biftu Adugna Business S.C

Addis Ababa
Full–time

Job Description
- Salary:- is according to company scale Terms of employment for all position is contractual based Job Requirements
- First Degree in Law
- Ability to communicates effectively, and promotes a team approach.
- Excellent verbal and written communication skills in English, Afan Oromo and Amharic
- 4 years related work experience

How to Apply

- Interested applicant can submitted CV within non-returnable copy of education and work experience credentials to Human resource department per personal

Location:-
Head office in front of Addis Ababa university school of commerce Biftu Building 7th floor
https://t.me/lawsocieties
🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝ሰላም ጤና ይስጥልኝ የተከበራችሁ ክብራት እና ክብሯን የ ALE CHANNEL ቤተሰቦች በሙሉ በያላችሁበ:🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝

👏👏በመጀመሪያ እንኳን ደስ አላችሁ EXIT EXAMን ላለፋችሁት በሙሉ

😒😏😞😔አጋጣሚ ሁኖ fAIL የደረጋችሁ ደግሞ ፅናቱን ይስጣችሁ ይስጠን

✳️✳️እኔ በወ/ዩ የ5ኛ አመት የሕግ ተማሪ ስሆን #EXIT #EXAMን ስንፈተን #17 መደበኛ ተማሪዎች 1 አንዲት ሴት እና 16 ወንዶች መለያ ቁጥር /CODE አልተሰጠንም ነበር

❇️በመሆኑም 17ታችንም ስማችን በፈተናው ወረቀት መጀመሪያ ገፅ ላይ ብቻ ስማችንን እና የመፈተኛ ጣቢያውን ብቻ እንድንፅፍ ተነገረን: እኛም በወቅቱ ቱክረታችን ፈተናው ላይ ስለሆነ ነገሩን እንዲህ የተጋነነ ስህተት ይኖረዋል ብለን ስላላሠብን ፈተናውን እንደጨረስን በወቅቱ የፈተናው አስተባባሪ የሆኑትን #አደራ #አደራ #አደራ በማለት ግቢውን ለቀን መውጣት ግድ ስለነበረብን ሁላችንም በየፊናችን በመሄድ ተለያየን፡🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲🥲

🅾ነገር ግን አሁን ላይ እንዳያችሁት /እንደሰማችሁት እጂግ በጣም በሚባል ደረጃ #TECHNICAL #ስህተት በተሞላበት ሁኔታ የ 17ታችንም ተማሪዎች ውጤት ውሃ በልቶታል

👉 የሚገርመው ነገር ቢኖር የመፈተኛ ጣቢያችንንም በተሳሳተ መልኩ ሰፍሯል ፡
😢😞😒😒😒😒😒😒😒😒😒
እኔ በበኩሌ ቤተሰቦቼም ጭምር በጣም በጣም በሚባል ደረጃ አዝነናል ሌሎቹም እንደዚያው ፡ ዳግም ይህ አይነት ስህተት እንዳይፈጠር ሁላችንም የየበኩላችንን አስተዋፅኦ እናድርግ ፡

➡️ በተወሰኑ ሰዎች ስህተት የብዙዎቾን ህይዎት አደጋ ላይ ከመጣል ጥንቃቄ የተሞላበት ሥራን ብንሰራ ጥሩ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡


▶️አሁንም ይህ ስህተት እንደገና ታይቶ እኛም ከጭንቀት ብንዎጣና ቤተስቦቻችን ደስብሏቸው #እንዳስመረቁን በፍሬችን /በውጤታችን እንዲደሰቱ ብታደርጉልን መልካም ነው ፡፡

↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️ይህን በመፃፌ እባካችሁ ቅር እንዳይሰኛችሁ በእኔ እና በእነሱ ቦታ ሆናችሁ ብታስቡት ቅር አይላችሁም፡፡



🔵ስለሆነም የሚመለከታችሁ ሁሉ ቅሬታችንን ብታዩልን እና መፍትሔ ብናገኝ?


ሰላም ለ እናት ሀገራችን እትዮጵያ

ቱክረት ለ 17ቶቹ የወሎ ዩኒቨርስቲ የሕግ ተማሪዎች በዩሉበት!!!!

2014 ዓ.ም
አህመድ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ
ስለ ስጦታ የፍትሐብሔር ህግ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

👉 የስጦታ ምንነት

በአጭሩ ለማስቀመጥ ስጦታ ማለት ሰጪው ተቀባይ ለተባለ ሌላ ሰው ከንብረቶቹ አንዱን ያለ ዋጋ የሚለቅበት ወይም ግዴታ የሚገባበት ውል ነው።
በመሆኑም ስጦታ በራሱ ውል ነው ማለት ነው።

👉የስጦታ ልዩ ባህሪያት*

በመርህ ደረጃ ስጦት ግላዊ ተግባር ነው ይህም ማለት ስጪው እራሱ የሚያድረገው ተግባር ነው ማለት ነው። ስጦታ የሚደረገው በወኪሉ ሲሆን ደግሞ የሚሰጠው ንብረት አይነት እና ለማን እንደሚሰጥ በግልጽ ሊመለከት ይገባል። ስጦታ የሚደረገው የሰጪው ንብረት በሆነው ለይ ብቻ ነው።ስጦታ አድርጋለሁ ብሎ የተስፋ ቃል መስጠት በህጉ መሠረት ግዴታን አያስከትልም ከዚህም በተጨማሪ ስጦታ ተቀባዩ ስጦታውን እቀበላለሁ በሚል ሀሳቡን
መግለፅ ይኖርበታል።ስጦታ እንዲቀነስ ወይም እንዲሻር የሚቀርበው ጥያቄ ስጦታው ከተደረገበት ቀን አንስቶ እስከ ሁለት አመት ለዳኞች ካልቀረበ በቀር ዋጋ አይኖረውም።

👉የስጦታ ሥርዓት ፍፎርም*

ስጦታ በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ ወይም በሚይንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ ሊደረግ ይችላል።

*1)በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ *

በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በፍትሐብሔር ህግ አንቀጽ 881 ላይ በተደነገገው መሠረት በግልጽ ኑዛዜ ሥርዓት ፎርም መሠረት የሚፈጸም መሆኑን ህጉ ያስረዳል።በሌላ በኩል በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ለይ የሚደረገው ስጦታ በፍ/ህግ አንቀጽ 1723 መሠረት በጽሁፍ ሆኖ በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መሆን አለበት።

*2) በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ለይ የሚደረግ ስጦታ*

በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በሁለት አይነት መልኩ ሊደረግ ይችላል ይህም እጅ በእጅ በሚደረግ ማስተላለፍ ብቻ ወይም ለማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ በሚደረገው ፎርም ሊሰጥ ይችላሉ።

👉 ስጦታ እንደማድረግ የማይቆጠርባቸው ሁኔታዎች ያሉ ሲሆን እነኚህም ሁኔታዎች።

1)ያለ ዋጋ የሚደረግ የአገልግሎት ሥራ ወይም የራሱን እቃ ያለ ዋጋ ዝግጁ ማድረግ ስጦታ አይባልም የፍ/ህግ አንቀጽ 2430።

2)መንፈሳዊ ተግባርን ለመፈጸም የሚደረገው የገንዘብ መክፈል ስራ ስጦታ አይባልም የፍ/ህ አንቀጽ 2432።

3) አንድ ሰው ለሰጪው ወይም ለቤተሰቡ አገልግሎት በልማድ መሠረት ያደረገው የሥራ ዋጋ መክፈል ስጦታ አይባልም የፍ/ህ አንቀጽ 2433።

4)ወራሽነትን አልፈልግም ብሎ መተው ወይም ኑዛዜ የተደረገለትን ስጦታ አልቀበልም ማለት ስጦታ ነው ተብሎ አይቆጠርም የፍ/ህግ 2431።

👉ስጦታ ፈራሽ የሚሆንባቸው ምክንያቶች*

በሚንቀሳቀስ ወይም በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ለይ የተደረገው ስጦታ በህጉ በተጠቀሱት በተለያየ ምክንያቶ ፈራሽ ሊሆን የሚችሉባቸው ምክንያቶች ያሉ ሲሆን እነኚህም:-

1ኛ የሰጪው አዕምሮ ትክክል አለመሆን

ሰጪው ስጦታውን በሚያድርግበት ወቅት በአዕምሮ መታወክ(ህመም ምክንያት) በፍርድ የተከለከለ ሲሆን ያደረገው ስጦታ ፈራሽ ሊሆን ይችላል ።የፍ/ህ አንቀጽ 2437

2ኛ ግብረ ገብነት የሌለው ወይም ህገ ወጥ ምክንያት ያለበት ስጦታ ፈራሽ ነው። የፍ/ህ አንቀጽ 2438

3)በመንፈስ መጫን ምክንያት የተደረገውን ስጦታ ዳኞች ለመቀነስ ወይም ለመሻር ይችላሉ።የፍ/ህ አንቀጽ 2439

4ኛ በ ፍ/ህ አንቀጽ 2442 ሥር በሚፈቅደው መሠረት ስጦታው የተደረገው በስህተት ወይም በተንኮል የሆነ እንደሆነ ፈራሽ ይሆናል።

5 ስጦታ የተደረገው ክርክር ያለበት ሀብት ላይ ሲሆን ስጦታው ፈራሽ ይሆናል።የፍ/ህ አንቀጽ 2452
👇👇👇
ኢትዮ ህግ

🟢 @lawsocieties
🟡 @lawsocieties
🔴 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
በፍታብሄር ጉዳይ በፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዲቀርብ ስለሚታዘዝ ተጨማሪ ማስረጃ
በዳንኤል ፍቃዱ / ጠበቃ እና የህግ አማካሪ/
ማስረጃ ማለት ማንኛውም የቀረበ አከራካሪ ጉዳይ እወነተኝነቱ የሚረጋገጥበት ወይም ውድቅ የሚደረግበት ዘዴ ነው፡፡ ይኸውም የተከሰሱትን ሰዎችቃል፣ የእምነት ቃል ፣ የፍርድ ቤት መዝገብ ፣ ማስረታወቂያ ፣ እንደተረጋገጠ በህግ የሚቆጠር /ፕሪዘምፐሽን/ ፣ የፍርድ ቤት ወይም እሱ ባቋቋመው ኮሚሲዮን በአይን የታየውን እና የተጎበኘውን ሁሉ ይጨምራል፡፡
ከታች ለማብራራት የምሞክራቸው የፍታብሄር ስነስርአት ህግ ድንጋጌዎች ባብዛኛው በተከራካሪ ወገኖችም ሆነ በዳኞች ዘንድ ቀላል የሚመስሉ ግን በተደጋጋሚ እሚዘወተሩ እና ከፍተኛ የሆነ ጉዳትን በተከራካሪ ወገኖችም ላይ ሆነ ክርክሩን ተመልክተው ውሳኔ በሚያስተላልፉ ዳኞች ላይ የሚያስከትሉ ናቸው፡፡
በመሰረቱ ማስረጃ ለፍርድ ቤት መቅረብ ያለበት ከአቤቱታ ጋር ተያዞ ነው፡፡ሆኖም ማስረጃው በሌላ ሰው፣ መ/ቤት፣ድርጅት፣…ወዘተ እጅ የሚገኝ ግዙፍ ወይም የማይንቀሳቀስ ወይም ለማስገልበጥ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን የማይችል ከሆነ የህንኑ ጠቅሶ ለፍርድ ቤት በወቅቱ በጽሁፍ ማመልከት ይኖርበታል፡፡
ነገሬን በምሳሌ ለማስደገፍ ያክል አንድ ራሴ እሰከ ፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከራከርኩበትን እና ውሳኔ ያገኘ መዝገብ ላንሳ፡፡ በጉዳ ላይ ታች ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበረው የኔ ደንበኛ ሲሆን ተከሳሹ በጠበቃቸው በኩል ባቀረቡት የፅሁፍ ምላሽ ካቀረባቸው የማስረጃ ዝርዝሮች መሃከል የተወሰኑትን በደፈናው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 145 መሰረት በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ይቅረብልኝ በማለት ዘርዝሮ አስቀምጧል፡፡ሆኖም ፍርድ ቤቱ በክርክሩ ሂደት የተወሰኑ ቦታዎች ላይ እነዚህ ማስረጃዎችን የተከሳሽ ጠበቃ ለማንሳት ቢሞከሩም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 145/2/ እና 137/1/ሀ/ እና /3/ መሰረት ተከሳሹ‹‹ እነዚህ ማስረጃዎች እንዲቀርቡለት የሚፈልግበትን ምክንት በፅሁፍ ገልጾ ማስረዳት ሲገባው ባለማስረዳቱ እንዲሁም በመጀመሪያው ቀጠሮ ማቅረብ ስላልቻለ የነዚህ ማስረጃዎች መቅረብም ሆነ በክርክር ላይ መነሳት ተገቢ አለመሆኑን›› ጠቅሰን የተከራከርነውን ተቀብሎ ተከሳሽ እነዚህ ማስረጃዎች ላይ ያለውን መብት አልፎ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን፡፡
በይግባኝ ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤት በበኩሉ ውሳኔውን በመሻር ማስረጃዎቹ በመጠቀሳቸው እና ለጉዳዩ ተገቢነት ያላቸው በመሆናቸው ሊመረመሩ እንደሚገቡ ትእዛዝ ሰጠ፡፡
በጉዳዩ ላይ የመወሰን ስልጣኑን ለናንተ ውይይት ልተወው እና አንዳንድ የሰበር መዝገቦችን ፣ ህጉን እና አንዳንድ ሃሳቦችን እንደሚከተለው ላንሳ፤
1.ክሱ እና መልሱ ሲቀርብ ማስረጃዎቹን ማቅረብ ያልተቻሉ እና ፍ/ቤቱ እንዲያቀርብላቸው የሚፈልጉትን ማስረጃ በመጀመሪያው ቀጠሮ ማቅረብ አለባቸው ፡፡ በመጀመሪያው ቀጠሮ ማቅረብ ካልቻሉ ሌላ ጊዜ ማቅረብ አይችሉም፡፡(የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.137/1/ሀ/ እና /3/)
2. የሰ.መ.ቁ. 85468 - በፍርድ ቤት እገዛ ማስረጃ የሚቀርበው ተከራካሪ ወገን አጠቃሎ ማቅረብ የማይችለው መሆኑ በቅድሚ ሲረጋገጥ ነው፡፡ በተጨማሪም ማስረጃው ማስረጃው ለጉዳዩ ያለውን አግባብነት በመመልከት ተገቢውን ትዕዛዝ መስጠት ይችላል፡፡ማስረጃው እንዲቀርብለት የጠየቀ ተከራካሪ ወገን ደግሞ እንዲቀርብለት የጠየቀው ማስረጃ ለጭብጡ ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳለው በፅሁፍ ገልፆ ማስረዳት ይጠበቅበታል፡፡(145(2)) ተከራካሪ ወገን ደግሞ ማስረጃውን ለማቅረብ ባለጉዳዩ እንደማይችል ባልተረጋገጠበት እና ማስረጃውም በህጉ አግባብ ዋጋ የሚሰጠው ወይም አግባብነት ከሌለው ፍርድ ቤቶች የግድ እንዲያስቀርቡት አይገደዱም፡፡(የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 138 እና 145/3/)
3. የሰ.መ.ቁ. 52546 - የተቆጠረ ማስረጃ ተገቢነት የሌለው መሆመሆኑን ፍርድ ቤት ውድቅ የሚያደርገው መክንያቱን በመግለፅ እና በግልፅ በፅሁፍ በማስፈር እንጂ በደፈናው አይደለም፡፡(የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 138 )
4.ከሰነድ ማስረጃዎች ውጪ ያሉ ቁሳዊ ማስረጃዎችን በተመለከተም የማስረጃ አቀራረብ ስረአቱ (145ን ጨምሮ) የሚገዛበት ስረአት ተመሳሳ ነው፡፡ (የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 138 )( those two types of evidences together called a real proof)
5.የማስረጃ ህጉ ረቂቅ በክፍል 4 ላይ በማስረጃ አቀራረብ በሚሰጥ ውሳኔ ላይ ስለሚቀርብ ይግባኝ በሚል ርእስ ስር የሚከተለው ተቀምጦ እናገኛለን፡፡
ቁ.99 የማስረጃ መቀበል ወይም አለመቀበል
1.ፍርድ ቤት በተሰጠው ስልጣን መሰረት ማስረጃ ስለማቅረብ እና ወይም ተጨማሪ ማስረጃ ስለማቅረብ እና ስለአቀራረብ ሁኔታ መጠን ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ ለይግባኝ አቀራረብ ይረዳ ዘንድ በህጉ መሰረት ውሳኔውን ከነምክንያቱ በጽሁፍ ያደርጋል፡፡
ማጠቃለያ
የማስረጃ እና የስነስርአት ህግ /አንድ ላይ Adjective laws የሏቸዋል/ አላማቸው ጉዳዮች ባጭር ጊዜ፣ በአነስተኛ ወጪ ፍትሃዊ ውሳኔ እንዲያገኙ ማድረግ ነው፡፡ አነዚህን አላማዎች ከግምት ውሰጥ በማስገባት ህግ አውጪው በፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዲቀርብ ስለሚታዘዝ ተጨማሪ ማስረጃዎችን በተመለከተ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ሊፈልገላቸው ይገባል እላለሁ፡፡ሰበር የሚያደርገው ጥረት እሚደነቅ ቢሆንም እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ ውሳኔዎችን በጉዳዩ ላይ መወሰኑ የጭብጡን አደናጋሪነት ያሰፋዋል፡፡ ፡፡ ለጠጨማሪ ንባብ እነዚህን ብታዩ፡-
. የማስረጃ ህግ ረቂቅ
. ሮበርት አለን ሴድለር የኢትዮጵያ የፍታብሄር ስነ-ስርአት
. የሰበር መዝገቦች 43843፣ 37105፣ 22603፣ 36979፣ 52546፣
.የፍታበሄር ስነስርአት ህጉ አንቀጾች 6፣91፣136፣137፣234፣249-261፣264፣327፣345
🟢 @lawsocieties
🟡 @lawsocieties
🔴 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የንግድ ፍቃድን ማከራየት ወይም ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ ስለመስጠት ህጉ ምን ይላላል?
************************************************************
የተከበራችሁ የፅሁፋችን አንባቢዎች በመጀመርያ አንድ ድርጊት ወንጀል ነው ለማለት በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ አንቀፅ 23(2) ላይ እንደ ቅድመ ሁኔታው መሟላት ያለባቸውን ሶስት መሰረታዊ ነገሮች ያሉ ሲሆን እነሱም
(ሀ) ድርጊቱ በህግ የተከለከለ መሆኑ እና አስቀጪነቱም በህግ መደንገጉ፣ (ለ) በህግ ማንኛውም ሰው እንዳይፈፀም የተከለከለውን ድርጊት ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት መፈፀሙን የሚያመለክት ሲሆን፣ (ሐ) በህግ አስቀጭነቱ የተደነገገው ተግባር በሚታይ መልኩ ተፈፅሞ ሲገኝ ነው።
የንግድ ፍቃድን ማከራየት ራሱን ችሎ ወንጀል ነው ወይም አይደለም የሚለውን ከላይ በህጉ ከተቀመጡት መስፈርቶች አንፃር ሲታይ የንግድ ፍቃድ ምዝገባና ፍቃድ አዋጅ ቁጥር 980/08 አንቀፅ 22(1) ማንኛውም ሰው የፀና የንግድ ስራ ፍቃድ ሳይኖረው የንግድ ስራ መስራት እንደማይችል በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል። የፀና የንግድ ስራ ፍቃድ ማለት ደግሞ በአዋጅ ላይ እና አዋጁን ለመፈፀም የወጣውን ደንብ እና መመርያ ተከትሎ ለአመልካቹ የተሰጠውን ንግድ ፍቃድን ይመለከታል። በተጨማሪም በአዋጁ አንቀፅ 26 (5) በግልፅ እንደሚያመለክተው ማንኛውም ግለሰብ (የንግድ ፋቃዱ ባለቤት) የንግድ ፍቃዱን ለሌላ ለማንኛውም ሰው እንዲገለገልበት ወይም በመያዣነት እንደያስይዘው ወይም እንዲያከራየው አሳልፎ መስጠት የተከለከለ የወንጀል ድርጊት መሆኑን ህጉ ያስቀምጣል።
የንግድ ፍቃድን አሳልፎ ለሌላ ሰው እንዲጠቀምበት የሰጠ ነጋዴ ምን አይነት ቅጣት ሊደርስበት ይችላል የሚለውን እንመልከት እስኪ ከላይ በአዋጅ አንቀፅ 26(5) ላይ የተቀመጠውን የህግ ክልከላ ተላልፎ የንግድ ፍቃዱን ያከራየ ወይንም በማንኛውም ሌላ መንገድ ለሌላ ግለሰብ እንዲጠቀምበት ያደረገ ነጋዴ ሁለት አይነት እርምጃዎች ሊወሰድበት ይችላል።
የመጀመርያውን በሚመለከት የንግድ እና ኢንዱስትሪ (ፍቃድ የሰጠው ባለስልጣን) የሚወስደው አስተዳደራዊ እርምጃ ነው ይህም በግልፅ በአዋጅ አንቀፅ 26 (5) ላይ የንግድ ፍቃዱ ባለቤት የተሰጠውን የንግድ ፍቃድ አሳልፎ በማንኛውም መንገድ ለሌላ ሶስተኛ ወገን እንዲጠቀምበት ማድረግ እንደሌለበት በነጋዴው ላይ ህጋዊ ግዴታ ያለበት መሆኑን ድንጋጌው ያስቀምጣል።
ነጋዴው ይሄንኑ ግዴታውን የጣሰ እንደሆነ በአስተዳደራዊ እርምጃ ንግድ ፍቃዱ የሚታገድበት ስለመሆኑ የአዋጅ አንቀፅ 29 (1) (ለ) ላይ አስቀምጦ እናገኘዋለን። በመሆኑም ነጋዴው የተሰጠውን የፀና የንግድ ፍቃድ አከራይቶ የተገኘ እንደሆነ የንግድ ፍቃዱን የሰጠው አካል ሊያግድበት ይችላል በሁለተኛ ደረጃ ከላይ በእንቀፅ 26 (5) ላይ የተቀመጠውን ህጋዊ ግዴታ ተላልፎ ንግድ ፍቃዱን ለሌላ ሰው በሽያጭ በማከራየት፣ በስጦታ አለያም በማናቸውም መልኩ በህጉ ከተቀመጡት መንገዶች አሳልፎ ለሌላ ሰው እንዲጠቀምበት ያደረገው ግለሰብ ከ5 እስከ 10 ዓመት ፅኑ እስራት እና ከብር 50‚000 እስከ 100‚000 ሺህ ብር እንደሚቀጣ የአዋጅ አንቀፅ 49(4) ላይ ተደንግጎ ይገኛል በሌላ መልኩ ደግሞ የንግድ ፍቃዱ ተላልፎ የተሰጠው ለውጭ ሀገር ዜጋ ከሆነ ቅጣቱ በመክበድ ከ7-15 ዓመት ፅኑ እስራት እና ከብር 200‚000 እስከ 300‚000 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ስለመሆኑ ተቀምጦ እናገኘዋለን።
የንግድ ፍቃዱን በክራይም ይሁን በማንኛውም ሌላ መንገድ አግኝቶ በግሉ ሲጠቀምበት የተገኘ ግለሰብ በወንጀል ከመጠየቅ እንደማይድን እና ከ7 እስከ 15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲሁም በብር ከ150‚000 እስከ 300‚000 ሺህ ብር እንደሚቀጣ በአዋጁ ተቀምጦ እናገኘዋለን ።
በዚህ ላይ ልናስተውል የሚገባን ነገር ቢኖር ለተፈፀመው ድርጊት የተቀመጠው ቅጣት ፅኑ እስራት እና የገንዘብ መቀጮው በጣምራ መቀመጡን ነው ።
Source:- Federal Justice and Legal Research and Training Institute official
🟢 @lawsocieties
🟡 @lawsocieties
🔴 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties