አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
July 19, 2021
🔵Urgent reminding notice♨️♨️
🔴 Dear Ethiopians........⁉️⁉️⁉️
You came naked,
You will go naked.
You arrived weak,
You will leave weak.
You came without money and things,
You will leave forever without money and things.
Your first bath, Someone washed you,
Your last bath, Someone will wash you.

🩸This is life‼️‼️‼️‼️‼️

So why so much malice, so much envy, so much hate, so much resentment, so much selfishness and so much pride⁉️ why, when we have to go empty handed⁉️

BE KIND…........We have limited time on Earth don’t waste it in uselessness.🩸🩸🩸🩸🩸🩸
share share
#share #Share
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
July 19, 2021
July 19, 2021
July 19, 2021
Forwarded from ሕግ ቤት
charge case.docx
11.4 KB
July 19, 2021
July 20, 2021
attorny general regulatin.doc
433 KB
July 20, 2021
ማስታወቂያ ለ5ኛ አመት የ Exit Exam ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ‼️
ፈተናው ይራዘም እያሉ ከዚህም ከዚያም መረጃወችን የሚያንሸራሽራሩ እና ተፈታኞ ተረጋግተው ለፈተና እራሳቸውን እንዳያዘጋጁ ከንቱ ተስፋ ሰንቀው የቴሌግራም ግሩፕ ከፍተው ተፈታኞችን የሚያደናግሩ እንዳሉ እየገለፅን።
ምንም አዲስ ነገር የሌለ በመሆኑ ተረጋግታችሁ ተዘጋጁ፤
ማንኛውም ጥያቄ እና ብዥታ ቢኖር ትክክለኛ የሚመለከተውን ሰው በመጠየቅ እና የዚሁ ቻናል አካል በሆነው @ALE_lawsocieties ላይ በመጠየቅ ትክክለኛ የሚመለከታቸውን ሰዎች ማግኘት ትችላላችሁ።
ተዋክበው ለሚያዋክቡ እራሳችሁን አታጋልጡ።
ሁሌም በእየ አመቱ እንዲህ አይነት ወከባ በመፍጠር የግል ቴሌግራም ግሩፕ አድማቂ ከማድረግ የዘለለ ምንም መፍጠር እና መቀየር የማይችሉ እና ምንም አይነት ውክልና ሳይኖራቸው በግላቸው ተነሳሽነት የግላቸው አጀንዳ ለመፈፀም petition እናሰባስብ 5th year እንዲሁ ቅሬታ Appeal እና መሰል ማሰሚያ በሚል ይቀሳቀሳሉ።
በጣም የግል ቴሌግራም ግሩፕ አባላት (አድማቂ) እንዲበዙላቸው ከመጓጓታቸው የተነሳ ያልተፈጠረ ያልተለወጠ፤ ያልተወሰነን ምንም በሌለበት አዲስ መረጃ አገኘን እንደገና አሳሳቢ ጉዳይ ምናምን እያሉ የብዙሀኑ ጥያቄ እና ፍላጎት በማስመሰል መረጃ በማሰራጨት
ተማሪዎችን ያዘናጋሉ።
የሚመለከተው የመንግስት ክፍል ለሁሉም አራቱም አቅጣጫ ለሚገኙ የሀገሪቱ ተማሪዎች አስፈላጊውን ጠቃሚ የሚለውን ሁኔታ ከህግ ት/ት ቤቱ ሄዶች እና ዲኖች መረጃ በመሰብሰብ እና በጋራ በመወያያት ማለትም በመጨረሻ ከሁሉም የኒቨርሲቲ ከህግ ት/ት የተውጣጡ ሄዶች እና ዲኖች በኮንሰርቲዬም ስብሰባ የሚወሰን ሲሆን እንድታውቁ እንላለን።
🔴ቅሬታ ጥያቄ ካለ ለህግ ት/ትቤታችሁ ሄድ ወይም ዲን ማቅረብ ነው ስርዓቱ።
🔵አዲስ ነገር ከህግ ት/ትቤታችሁ ሄድ ወይም ዲን መጠየቅ ነው ትክክለኛው።
በተረፈ በዚህ ቻናል የሚለቁቁ መረጃዎችን ተከታተሉ።
ተረጋግታችሁ ተዘጋጁ‼️
via Eta.B. Addis Ababa
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
July 20, 2021
July 20, 2021
July 20, 2021
July 20, 2021
July 20, 2021
ሰላም እንዴት ናችሁ!!!!
==============
በቅድሚያ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮችና ኢ/ያዊያን እንኳን ለኢደል አልአድሃ አረፋ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!!!!!!
.
.
ከላይ የተቀመጡ ፅሁፎችን አይቻለሁ፡፡2ቱም መልካም የሚባሉ ናቸው፡፡ነገር ግን የሚያመጡት ውጤት ደካማ ነው፡፡ባቡፈው ጊዜ ማለትም ገና የኮንሰርቲየሙ ስብሰባ ከመካሄዱ አንድ ሳምንም ቀደም ብዬ በዚሁ ገፅ የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ የተማሪውን ዝግጅት በተመለከተ ከሁሉም ዩንቨርስቲዎች መረጃ እንድሰጠንና ለሚመለከተው አካል እንድደርሰው ለማድረግ ሰፊ እድል ተሰጥቶ ነበር፡፡አሁን ፈተናው እንድራዘም እየጠየቃችሁ ያላችቱ አካላትም፡ጭምር በጊዜው ለምን ዝምታን መረጣችሁ??? ደግሞስ ምን የቱዬ ነገር ተፈጠረ ዛሬ ላይ ??? ያኔ ግን ከአስር በላይ ዩንቨርስቲዎች ያሉበትን አቋምና ዝግጅት አሳውቀውን እኛም ለኮንሰርቲየሙ አድረሰን እርሱም በጉዳዩ አምኖበት ለተወሰነ ቀናት እንዲራዘም ወስኖ ነገር ግን ለፈተናዎች ኤጂንሲ አቅርቦት ኤጄንሲውም አሳማኝ ያለውን ም/ት አቅርቦ ባለበት እንደሰጥ ወስኗል፡፡እኛም መረጃውን አድሰናል ተማሪውም በተቻለ መጠን ሙሉ ጊዜውን ተጠቅሞ ለፈተናው ራሱን እንዲያዘጋጅ ጥሪ አድርገናል፡፡
.
.
በሌላ መልኩ ግን በዝግጅት የተሻልን ዩንቨርስቲዎች የሌሎችንም አቅምና ዝግጅት ወርደን እኛን በነሱ ቦታ አስቀምጦ ማየቱ ተገቢ ነው ባይ ነኝ፡፡በግሌ እንዲራዘም አልፈልግም በዝግጅት በኩልም ከሌላው ዩንቨርስቲ በተሻለ መልኩ አርባምንጭ ጥሩ ላይ ነን ብዬ አምናለሁ ተማሪውም መራዘሙን አይፈልግም ብዬ አምናለሁ፡፡ይሁን እንጅ እንደ አገር አቀፍ ፈተና መለመድ የሌለበት የጊዜ አወሳሰን ወጥ የሆነ ስኬጁልና ካሪኩለም በሌለበት፣የህግ ት/ቤቶችና ተማሪው በተለያዬ አቋም ባለበት ተወዳዳሪና ወጥ የሆነ አመዛዘን ማምጣት ከባድ ነው፡፡ጥቂት ዩንቨርስቲዎች ተማሪው ምንም ዝግጅት የለውም እንደውም በሪሰርችና በአፓረንትሺፕ ውጥረት ላይ ነው ት/ቤቶቹ ግን ዝግጁ ነን ይላሉ ይሄ ደግሞ ትልቅ ውድቀትን ያመጣል፡፡
.
.
በመሆኑም እንዲራዘም የሚጠይቁትን አካላት እንደ ጠፋተኛ ማየቱ አግባብ ነው ብዬ አላምንም በነሱ ውደቀት ውስጥ በነሱ የልፋትን ማጣት ውስጥ በነሱ ተስፋ መጨለም ውስጥ በነሱ የ17አመት ድካም ውስጥ ሆነን መለካት አለብን፡፡የነሱ ውድቀትም ይሁን ማለፍ ለሌሎቻችን ተራ ሆኖ ሊታየን አይገባም ይሄ እጣ በኛ ላይ ቢደርስ ምን አይነት ሙድ ውስጥ ልንሆን እንደምንችል መመዘኑ የበለጠ ምክንያታዊ እንዲንሆን ያደርገናል፣እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አይነት አካሄድም ባንከተል ጥሩ ነው፣ውድድሩም ይሁን ፈተናው ከራስጋ ነው በሌላኛው መውደቅ ለመደሰት የሚመስል አይነት አቋም ሊኖረን አይገባም፣ብንችልኮ የራሳችን እህትና ወንድሞች ትግራይ ክልል በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች የነበሩ አሁን ላይ ተስፋ ቆርጠው የሚሆኑት የሚናገሩት የሚወቅሱት አጥተው ያን ሁሉ አመት ደክመው በዝምታ ውስጥ ናቸው፣ይልቅ ማሰብ ከቻልን የነሱም ጉዳይ ስለምን በቸልታ ታዬ፣የሚመለከተው አካል ለምን በቶሎ መፍትሄ አይፈልግም ብለን መጮህና የመፈትሄው አካል በሆናቸው ነበር፡፡እነሱም እንደኛ እኩል ለፍተዋል ጥረዋል ታግለዋል፣እኛ አሁን በጉጉት የምንጠብቀውን ነገም እነሱም መጠበቅና ህይወታቸውን ማስተካኩል ይፈልጋሉ ፡፡ነገር ግን ማን ይናገርላቸው ማንስ ይስማቸው??? ይሄን ትተን ደግሞ ሰላም አካባቢ ያለን ደግሞ በሌላ ውጥረት አልተዘጋጀንም አግዙን ጊዜ ይሰጠንና እንዘጋጅ ሲሉ ስለምን መረዳት እንዳቃተን ግን አልገባኝም፡፡
.
.
እኛ ቢራዘም አንድም የሞራል ውድቀት ነው ሁለትም እንደ አድስ ተመልሰን እምደክማለን፣ሳይራዘም ቢቀርና አህትና ወንድሞቻችን ቢወድቁ ደግሞ ውደቀቱ የሞራል ሳይሆን የአመታት ልፋት ነው የህይወታቸው መስመር ብልሽት ነው፣ንፅፅሩን ለናንተው ትቼው እኛ ብንታገስና የሚመለከተው አካል ተረድቷቸው እኩል ሚዛን ላይ ሆነን ብንፈተን መልካም ነው ባይ ነኝ፡፡መረሳት የሌለበት ግን በዝግጅት በኩል ከየትኛውም በላይ እኛ ዝግጁ ነን፡፡ራስ ወዳድ ላለመሆንና ምክንያታዊነትን በመላበስ ነው ሲቀጥል ባለፈው መራዘሙን የከለከለው ፈተናዎች ኤጄንሲ እንጂ ሁሉም ዩንቨርስቲ ተስማምቶበት የነበረ ጉዳይ ነው፡፡
.
.
ስንፅፍ የማንንም ሞራል ባንነካ ነፃና ገለልተኛ ሃሳባችንን በምክንያት እየረስደገፍን ብንናገር፣የውድድርና የእልክ የመሸናነፍ መድረክ ባናደርገው እላለሁ፡፡
.
.
በመጨረሻ ግን ሁላችንም ከዝግጅት መዘናጋት የለብንም ፈፅሞ ስለመራዘሙ ረስተን ባለንበት አቋም ልናጠና ይገባል፡፡ይህ ውሳኔ የሚወሰነው በማንኛችንም የግል ጩኸት ሳይሆን በሚዛን ነው፣በተረፈ በያላችሁበት ዩንቨርስቲ ዲኖችጋ በቅርበት መረጃ ተለዋወጡ፡፡
.
.
መልካም ጊዜ በያላችሁበት!!!!
አህመድ.M(ከአ/ምንጭ)
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
July 20, 2021
አለሕግAleHig ️
ስለአዲሱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013፡- አንዳንድ ምልከታዎች 1. የአዋጁ መልካም ጎኖች፡- 1.1. የተለያዩ አዋጆችን አንድ ላይ አጠቃልሎ/consolidated/ ለአጠቃቀም ምቹ ማድረጉ፣ 1.2. በፍርድ ሊወሰኑ በሚችሉ ጉዳዮችና በሕገ መንግስታዊ መብቶች ላይ ፍርድ ቤቶች ስልጣን ያላቸው መሆኑን ግልጽ ለማድረግ ጥረት ማድረጉ፣ 1.3. ስለመሰረታዊ የሕግ ስህተት አመላካች ሊባሉ የሚችሉ…
ትክክለኛ እይታና እውነተኛ ሃሳብ ነው፣ የግሌ ትዝብትም ነበር። ከአዋጁ ውስንነት አንፃር እኔ ታዚቢያቸው በፀሐፊው ካልተዳሰሱት ነጥብች መካካል የተወሰኑትን ለማሳየት፦
1. በአዋጁ የትርጓሜ ድንጋጌ ስር አንቀፅ 2(11) ላይ የፃታ አገላለጽ መደንገጉ፣
2. በሌሎች ሕጎች የተጠቀሱ ጉዳዮች የሚል ድንጋጌ በብዙ አንቀፆች ስር አሰልቺ በሆነ መልኩ ተደጋግሞ መደንገጉ፣
3. በአንቀፆች መካከል በአንዳንድ በታዎች የክፍተት (space) አሰጣጡ ወጥነት የጎደለው ድንጋጌዎች የተበታተኑ መሆን፣
4. የፌዴራል ከፍተኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንቶች ስልጣንና ተግባር ተደጋግሞ በአንቀፅ 19(6) እና 20 ላይ መፃፉ። ተመሳሳይ ሃሳብና ድንጋጌ ተደጋግሞ መፃፉ ከredundancy ውጭ የተለየ ፈይዳ የላቸውም
5. የአንቀፅ 26 አርዕስት የአማርኛ ቅጂው ከእንግሊዝኛው ጋር የማይጣጣም መሆኑ፦ አማርኛው ከሰባት ያላነሱ ዳኞች ሲል እንግሊዝኛው with not less than five judges የሚል መሆኑ
በመልካሙ ጌታሁን‼️
#join #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
July 21, 2021
Legal Manager at BGI Ethiopia

Company: BGI Ethiopia

Location: Ethiopia

State: Addis Ababa Jobs

Job type: Full-Time

Job category: Legal Jobs in Ethiopia

Job Description

Purpose of the job

The Legal Manager is responsible for overseeing the legal matters of BGI Ethiopia and subsidiaries in Ethiopia.

Main duties & responsibilities

Provide updates on all changes to laws and regulations within the Country

To support in the drafting, reviewing, negotiation, and finalization of legal documents

Ensure that the company carries its commercial activities in full compliance with internal (Group) policies, codes, and guidelines,

Ensure that the Company and its subsidiaries comply with the Corporate regulations in the Country.

Giving legal advice on all matters requested by the company’s management.

 Overseeing the contract drafting and review process.

Ensure that regulatory policies and procedures have been documented, implemented, and communicated;

Prepare and lodge reports with relevant regulatory and compliance authorities;

 Liase with external regulators

Collaborate with public authorities for the proper introduction of regulatory standards and facilitate discussions;

Periodically review risks to ensure identification of legal and regulatory risks to all commercial teams and design plans to avoid these;

Undertake such other legal tasks as assigned by the Company.

The role is largely office-based, but frequent travel to sites will be necessary.

Job Requirements

In depth knowledge of the laws regulating the brewery sector

 Expert knowledge of professional compliance and investigation standards; and ability to apply policy and legal concepts to issues.

Commitment to the highest ethical and professional standards.

Excellent written and oral communication skills.

Ability to work independently and within a team environment.

Ability to share information and build consensus across stakeholders.

Ability to supervise support and professional analyses functions for compliance and ethics programs.

Ability to establish trust and credibility with stakeholders and senior management.

Knowledge of the Group’s ethics and compliance policies, procedures, and programs.

Ability to develop and deliver presentations.

Demonstrated ability to successfully manage a large corporate or centralized institutional legal office.

Knowledge of legal documentation procedures and requirements.

Ability to develop and implement legal strategies and solutions.

Expected Education and Experience

Learned Law Bachelor

6 years of experience of work preferably in a law office.


Method of Application

Submit your CV and Application to yibelu.workineh@Castel-Afrique.com
Use the title of the position as the subject of the email
Closing Date : 23 July. 2021
#join #join #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
July 21, 2021
የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ መፃፍ የሚያስከትው የህግ ተጠያቂነት
ማንኛውም ሰው በግል ከሚኖርበት ቤቱ ጀምሮ በአካባቢዉ እንዲሁም በስራ ቦታው ላይ ታማኝና ሌሎች እምነት የሚጥሉበት ሆኖ መገኘት ይጠበቅበታል፡፡


እምነት የሚጣልበት ታማኝ መሆን መቻል እጅግ በጣም አስፈላጊ ስብዕና በመሆኑ በዚያ ደረጃ ላይ መገኘት በግለሰቡ ላይ ከሚያሳድረው በራስ የመተማመን መንፈስ ሌላ በዙሪያ የሚገኙ ሰዎች ለእርሱ ያላቸው ክብርና የሚሰጡት ቦታ ከፍ እንዲል ያደርገዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ለሰው ልጆች ሁሉ ወሳኝ የሆነው ስብዕና አንድ ጊዜ ከጠፋ በሌሎች ላይ የሚያሳድረው የመከዳት ስሜት በቀላሉ የማይሽር ግለሰቡን ከነበረበት ማህበራዊ ህይወት እንዲገለል የሚያደርግ ይሆናል፡፡ አንድ ሰው ታማኝነቱን ሊያጣባቸው ከሚችሉ ምክንያቶች ውስጥ አንደኛው የሚያዝበት ገንዘብ እንደሌለው እያወቀ ቼክ ፅፎ መስጠት ሊሆን ይችላል፡፡ በመሆኑም በቂ ስንቅ በሌለበት ቼክ ፅፎ የመስጠት ወንጀልን መፈፀም ምንአልባት ለጊዜው መቆየት ቢቻል እንጂ እስከ መጨረሻው በህግ ተጠያቂ ሳይሆኑ መቅረት ስለማይቻል ከምንም ነገር በላይ ታማኝነትን ላለማጉደል እንዲሁም ለወንጀል ቅጣት ላለመዳረግ ደጋግሞ ማስተዋሉ አይከፋም፡፡ በዚህ መነሻነት የሚያዙበት ገንዘብ እንደሌለ እያወቁ ቼክ በመፃፍ የሚፈፀም ወንጀልን በሚመለከት በ1997ዓ.ም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ ላይ የተጠቀሱ ጉዳዮች በከፊል እንመልከት፤
የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ማውጣት በሚለው ርዕስ አንቀፅ 693/1/ ማንም ሰው ቼክ በሚወጣበት ወይም ቼኩ ለባንኩ በሚቀርብበት ጊዜ የሚያዝበት በቂ ገንዘብ አለመኖሩን እያወቀ ቼክ ያወጣ (የሰጠ) እንደሆነ፤ በቀላል እስራት ወይም እንደነገሩ ከባድነት ከ10 አመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትና መቀጮ ይቀጣል፡፡
አንቀፅ 693/2/ አድራጎቱ የተፈፀመው በቸልተኛነት እንደሆነ በመቀጮ ወይም ከ1 አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ያስቀጣል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በተለምዶ ደረቅ ቼክ የሚባለውን ቼክ ፅፎ በሰጠ ግለሰብ ላይ ክስ ቀርቦበት ፍርድ ቤት የሰጠውን የቅጣት ውሳኔ ቀጥለን እናያለን፤
የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ የማውጣት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በቀረበበት ክስ በእስራት ተቀጣ
በ1996ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 693/1/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ የማውጣት ወንጀል የፈፀመዉ ግለሰብ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል\፡፡

አቃቤ ህግ በመሰረተው ክስ መሰረት የ45 አመቱ ጎልማሳ ተከሳሽ አብረሀም ወ/ተንሳይ ቼኩ ለባንክ በሚቀርብበት ወቅት ገንዘብ አለመኖሩን እያወቀ 1ኛ ጥር 05 ቀን 2012ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ክልል ልዩ ቦታው መስቀል ፍላወር ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በነበራቸው የብድር ግንኙነት ምክንያት ለግል ተበዳይ ሚሊዮን ጥላሁን ከቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ካዛንችስ ቅርንጫፍ ከሚገኘው የሂሳብ ቁጥራቸው በቼክ ቁጥር ጂጂ682269 ከሀምሌ 11 ቀን 2012ዓ.ም ጀምሮ የሚመነዘር የገንዘብ መጠኑ 3,400,000 (ሶስት ሚኒየን አራት መቶ ሺህ ብር) የሆነ ቼክ፤ እንዲሁም 2ኛ ተከሳሹ ሰኔ 20 ቀን 2012ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ሲሆን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ክልል ልዩ ቦታው ጎርጎሪዮስ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በነበራቸው የብድር ግንኙነት ምክንያት ለግል ተበዳይ ሚሊዮን ጥላሁን ከቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ካዛንችስ ቅርንጫፍ ከሚገኘው የሂሳብ ቁጥራቸው በቼክ ቁጥር ጂጂ682267 ከሰኔ 20 ቀን 2012ዓ.ም ጀምሮ የሚመነዘር የገንዘቡ መጠኑ 620,000 ( ስድስት መቶ ሀያ ሺህ ብር) የሆነ ቼክ ፅፎ እና ፈርሞ ለግል ተበዳዩ የሰጣቸው ሲሆን የግል ተበዳዩም ጥቅምት 20 ቀን 2013ዓ.ም ቼኩን ለባንኩ ሲያቀርቡ በቂ ገንዘብ አለመኖሩ የተረጋገጠ በመሆኑ ግለሰቡ በፈፀመው የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ በማውጣት ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል፡፡

ክሱን የተመለከተው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ የቀረበበትን የሰው ምስክርና እና የሰነድ ማስረጃ አስመልክቶ ራሱን እንዲከላከል አድርጎ በጉዳዩ ላይ የቀረቡትን ማስረጃዎች መርምሮ ሰኔ 17 ቀን 2013ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ አብረሀም ወ/ተንሳይን በቀረበበት ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ስላገኘው በ6 አመት ፅኑ እስራት እና በ2000 (ሁለት ሺህ ብር) የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
ኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
July 21, 2021
ከሐምሌ 13/2013 ጀምሮ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የወንጀል ጉዳዮች የዳኝነት ስልጣን
**************************************************************
በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ 1234/2013 ዓ.ም ጥር 13/2013ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ የሚታወቅ ሲሆን የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሐምሌ 13/2013 ዓ.ም ጀምሮ ከዚህ በታች በተዘረዘሩ የወንጀል ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ስልጣን አይኖረውም፡፡
 በሌሎች ሕጎች የተጠቀሱ ጉዳዮች እንደተጠበቁ ሆኖ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች እና የድሬደዋ ከተማ ፍርድ ቤቶች በቻርተር አዋጆች ከተሰጣቸው የደንብ መተላለፍና በወ/መ/ስ/ስ/ሕጉ መሰረት ከሚቀርብላቸው ጉዳዮች በተጨማሪ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚቀርቡ የወንጀል ጉዳዮ በከተማ መስተዳደር ፍርድ ቤቶች እንደሚስተናገዱ በአዋጁ አንቀጽ 4(16) የተደነገገ በመሆኑ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሐምሌ 13 ጀምሮ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚቀርቡ የወንጀል ጉዳዮችን ተቀብለው አያስተናግዱም፡፡
በዚሁ መሰረት በፍርድ ቤቱ ከሐምሌ 13 ጀምሮ በወንጀል ሕጉ ላይ የተደነገጉ ከዚህ የሚከተሉት የወንጀል ጉዳዮች አይስተናገዱም፡-
• አንቀፅ 261 በውጭ አገር መንግስት ላይ የሚደረግ የተቃዋሚ ድርጊት
o አንቀፅ 262 የውጭ አገር መንግስትን ግዛት መጣስ
o አንቀፅ 264 የውጭ አገር መንግስታትን ማዋረድ
o አንቀፅ 265 የታወቁ የውጭ አገር ምልክቶች ማዋረድ
o አንቀፅ 266 በመንግስታት መካከል የተቋሙ ድርጅቶችን ማዋረድ
o አንቀፅ 267 የውለታ መመለስ /principle of reciprocity/
o አንቀጽ 380 /2/ ሰነዶችን ማጥፋት
o ወንጀሉ የተፈፀመው በቤተሰብ አባል ፣ ቅርብ ዘመድ፣ በጥቅም ወይም በፍቅር በተሳሰረ ወይም አብሮነት በሚኖር ሰው ላይ ሲሆን
o አንቀጽ 399/1/ በሞያ ወይም በስራ ምክንያት የታወቀ ምስጢር መግለጽ
o አንቀጽ 556/1/ ቀላል አካል ጉዳት ማድረስ
o አንቀጽ 559 /3/ በቸልተኝነት የሚፈፀም ቀላል አካል ጉዳት ማድረስ
o አንቀጽ 560 እጅ እልፊት
o አንቀጽ 580 ዛቻ
o አንቀጽ 583/1/ የመወሰን ችሎታን ማሳጣት ተደራራቢ ሲሆን
o አንቀጽ 593 ወላጆች ልጆቻቸውን ሲጠልፉ
o አንቀጽ 603 የስራ ነፃነት መብትን መጣስ
o አንቀጽ 606 የመጻጻፍ ወይም የግንኙነት ግላዊት መብትን መድፈር
o አንቀጽ 613 /1-4/ ስም ማጥፋትና የሀሰት ሀሜት
o አንቀጽ 615 እና 618 ስድብና ማዋረድ
o አንቀጽ 625 አንድ ሴት ያለባትን ከፍ ያለችግር ወይም ጥገኝነትዋን ምክንያት በማድረግ የሚፈፀም ድርጊት
o አንቀጽ 643/2/ ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆኑ መግለጫዎችና ማስታወቂያዎች
o አንቀጽ 642/2/ ጋብቻን በተንኮል ወይም በማታለል መፈፀም
o አንቀጽ 652/1-2/ አመንዝራነት
o አንቀጽ 658 ቀለብ መስጠት ግዴታን አለመፈፀም
o አንቀጽ 667 የጋራ ንብረት መስረቅ
o አንቀጽ 679 አግኝቶ መደበቅ
o አንቀጽ 680 ወድቆ የተገኘውን ንብረት ለራስ ማድረግ
o አንቀጽ 685 በከብት መንጋ አማካኝነት በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ
o አንቀጽ 686 /1/ በሰው ንብረት ላይ ሁከት ማድረግ
o አንቀጽ 689-691 በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ
o አንቀጽ 700 በህዝብ እምነት በመጠቀም ማታለል
o አንቀጽ 704 ጥቅም ታገኛለህ በማለት ሌላውን ሰው በመደለል ማነሳሳት
o አንቀጽ 705 ችሎታ የሌላቸውን ሰዎች ንብረታቸውን የሚጎዳ ስራ እንዲፈጽሙ ማነሳሳት
o አንቀጽ 717 ግዙፍነት በሌላቸው በሌላ ሰው መልካም ስም ላይ ጉዳት ማድረስ
o አንቀጽ 718 ጉዳትን የሚያደርሱ ሀሰተኛ መግለጫዎች
o አንቀጽ 719 ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር
o አንቀጽ 725 በማጭበርበር እዳ መክፈል አለመቻል፤
ኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ
#Join #Join #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
July 21, 2021