አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Live stream scheduled for
የብድር ውል ‼️
(የፍትሐብሔር ሕግ ከቁጥር 2471-2489)
የብድር ውል ምንነት፡- የተለያዩ ፅሑፎች እንደሚያስረዱት ብድርን በተመለከተ ሁሉንም ሊያግባባ የሚችል አንድ ወጥ የሆነ ትርጉም አናገኝለትም፡፡ የፍትሐብሔር ሕጋችን የሚከተለውን ትርጉም ሰጥቶታል፡- “የሚያልቅ ነገር ብድር ማለት ከተዋዋዮቹ አንዱ ወገን አበዳሪው ሌላውን ተበዳሪ ሰው የተበደረውን ነገር በዓይነቱ ለመመለስ ተገዳጅ በማደረግ ገንዘብ ወይም በማገልገል የሚያልቅ ሌላ ነገር ለተበዳሪው ለመስጠትና ሀብትነቱን ለማስተላለፍ የሚገደድበት ውል ነው” ይላል፡፡ ከዚህ ትርጓሜ መረዳት እንደሚቻለው ብድርን በሚመለከት ሕጉ በሚያልቅ ነገር ላይ ብቻ እንጂ ከዛ ባለፈ ማለትም በማያልቅ ነገር ወይም ቋሚ የሆነ ንብረትን የማያካትት መሆኑን ነው፡፡ የድንጋጌውን አጠቃላይ ይዘት ስናይ አመላለሱ በዓይነት ወይም በአገልግሎት ሊሆን እንደሚችል እና ውሉ አስገዳጅ መሆኑንም ያሳያል፡፡
የዉል አመሠራረት፡- የብድር ውል የውል አንድ አካል እንደመሆኑ መጠን አመሰራረቱም ሆነ አፈፃፀሙ በጠቅላላው የውል ሕግ መርሆች የሚገዛ በመሆኑ የብድር ውልን ዝርዝር ድንጋጌዎች ከማየታችን በፊት ስለውል አመሰራረት ባጭሩ አይተን ብናልፍ የተሻለ ግንዘቤን ይፈጥራል፡፡ ዉል ስምምነት ቢሆንም ከሌሎች ስምምነቶች የሚለየዉ በአፈፃፀሙ ከበስተጀርባዉ የሕግ ድጋፍ ያለዉ ስምምነት መሆኑ ላይ ነዉ፡፡

አንድ ውል የሚፀና ውል ነው ለማለት የሚከተሉትን መርሆች ማሟላት አለበት፡- 1ኛ ዉል የሚፈፀመዉ ለመዋዋል ችሎታ ባላቸዉ ሰዎች መካከል ብቻ መሆኑ (እድሜዉ ለአቅመ አዳም/ሄዋን ያልደረሰ ወይም አይምሮዉ ህመም ያለበት ሰዉ ወይም በፍርድ ቤት የተከለከለ ሰዉ ችሎታ እንደሌለዉ ይቆጠራል፡፡) 2ኛ ዉል የሚደረገው በተወያያቹ ነፃ ፍቃድ ብቻ የሚደረግ መሆኑ፡፡ 3ኛ ተወያይ ወገኖች የሚዋዋሉበት ጉዳይ በእርግጠኝነት የሚቻል እና ህጋዊና ሞራላዊ ጉዳይ ላይ መሆን የሚገባው መሆኑ፡፡ 4ኛ የዉል አቀራረጹ ወይም አፃፃፉ (ፎርም) በህግ ተለይተዉ የተቀመጡ ወይም ተዋዋይ ወገኖች ተለይቶ እንዲቀመጥ ከተስማሙበት የዉል ጉዳይ በቀር የተለየ የዉል ፎርም አያስፈልግም፡፡

የአበዳሪና ተበዳሪ ግዴታዎች፡- አበዳሪና ተበዳሪ የራሳቸው የሆኑ ሊያከብሯቸው የሚገቡ ግዴታዎች አሉባቸው፡፡ በቅድሚያ የአበዳሪው ግዴታዎችን ስናይ ሕጉ የአበዳሪውን ግዴታዎች በተመለከተ የሽያጭ ውልን በሚደነግገው ክፍል ላይ የሻጩ ግዴታዎች ተብለው የተገለፁት ደንቦች በአበዳሪ ላይ ተግባራዊ ይሆናሉ ይላል፡፡ በፍትሐብሔር ሕጉ የሻጭ ግዴታዎች ናቸው የተባሉት ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1ኛ ዕቃ የማስረከብ ግዴታ፡- የሽያጭ ውል ከተከናወነ በኋላ ሻጭ የግብይት ምክንያት የሆንውን ዕቃ/ንብረት ለገዥ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡ 2ኛ ስመ-ሀብት የማስተላለፍ ግዴታ፡- ከላይ ለማንሳት እንደተሞከረው የሽያጭ ውል ልዩ መገልጫ ከሆኑት ጉዳዮች ውስጥ ሻጩ የሽጭ ምክንያት የሆነውን ንብረት ስመ-ሀብትን የማስተላለፍ ግዴታ ያለበት መሆኑ ነው፡፡ የባለቤትነት መብት መተላለፍን በተመለከተ የብድር ውል ከሽያጭ ውል ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር የብድር ውሉ በትርጉም ክፍሉ ላይ እንደሰፈረው አላቂ ዕቃን ብቻ የሚመለከት በመሆኑ ዕቃውን ለተበዳሪው በሚያስረክብበት ወቅት የባለቤትነት መብትም አብሮ መተላለፍ መቻሉ ነው፡፡ 3ኛ ዋስትና የመስጠት ግዴታ፡- ሌላኛው የሻጭ ግዴታ ከተሸጠው ዕቃ ጋር በተገናኘ ለሚፈጠሩ ችግሮች ለገዥው ዋስትና የመስጠት ግዴታ ነው፡፡

የተበዳሪውን ግዴታዎች በተመለከተ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ ዕዳውን መልሶ ከመክፈል ጋር የሚገናኝ ነው፡፡ ተበዳሪ የብድር ውል ውስጥ ሲገባ የተበደረውን ነገር በዓይነቱ ለመመለስ ወይም በገንዘብ የሚመለስ ሲሆን እነዚህን በወቅቱ የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡ የብድሩ አመላለስ በማገልገል የሚያልቅ ሲሆን ደግሞ ለአበዳሪው ተገቢውን)
የብድር ማስረጃ፡- ማስረጃ ማለት አንድ በፍርድ ቤት ምርመራ ላይ ያለ በጭብጥ የተያዘ አከራካሪ ጉዳይ እውነት መሆንና አለመሆኑን በሚያሳምን ሁኔታ ማረጋገጥ እንዲያስችል በግብአት የሚቀርብ ፍሬ ነገር ስለመሆኑ ብ/ጀነራል ታጠቅ ታደሰ “የማስረጃ ሕግ መሰረተ ሀሳቦች” በሚለው መፅሐፋቸው ገልፀውታል፡፡ ማስረጃ ማለት ይህ ከሆነ በሁለት ሰዎች መካከል የብድር ውል ተደርጓል ወይስ አልተደረገም የሚለውን ጥያቄ በምን ማረጋገጥ እንችላለን? የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ ቀጥለን እናያለን፡፡ የፍ/ሕጋችን በአን. 2472 ስር የብድር ማስረጃ በሚል ርእስ የሚከተለውን ደንግጓል፡-
(1) በብድር የተሰጠው ገንዘብ ከብር 500 በላይ ሲሆን የብድሩን ውል በፅሑፍ ወይም በፍርድ ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ወይም መሐላ ካልሆነ በስተቀር ለማስረዳት አይቻልም፡፡
(2) ለብድር ውል ማናቸውም ሌላ ዓይነት ማስረጃ ለማቅረብ አይቻልም ፡፡ (3) እንዲሁም ከብር 500 የበለጠ ገንዘብ የመክፈል ነገር በዚህ ዓይነት ይፈፀማል፡፡ በዚህም መሰረት የብድሩ መጠን ብር 500 እና ከዛ በታች ከሆነ በማንኛውም ዓይነት ማስረጃ ለምሳሌ በቦታው የነበረ የሰው ምስክር በመስማት ማረጋገጥ የሚቻል መሆኑን እና መጠኑ ከዛ በላይ ከሆነ ግን ከሦስቱ የማስጃ ዓይነቶች መካከል በአንዱ ካልሆነ በስተቀር በሌላ በምንም መንገድ ማረጋገጥ የመማይቻል መሆኑን ነው መረዳት የሚቻለው፡፡ እነዚህን ሦስት የማስረጃ ዓይነቶች ቀጥለን እንመልከት፡፡
የመጀመሪያውና የበለጠ አስተማማኝ የሆነው ማስረጃ የፅሑፍ ማስረጃ ነው፡፡ ይህም ማለት ገና ከጅምሩ የብድር ውሉ ሲደረግ በፅሑፍ የተደረገ ሲሆን ያንን ፅሑፍ ለፍርድ ቤት በማቅረብ ማስረዳት ይቻላል፡፡ በሌላ አነጋገር ከብር 500 በላይ የሆነ የብድር ውል በፅሑፍ እንዲሆን ሕጉ አስገዳጅ የሚመስል ድንጋጌ ያስቀመጠ በመሆኑ ከላይ ካነሳነው የውል አመሰራረት መርሆች መካከል የተለየ ፎርም የሚፈልግ መሆኑን ማየት ይቻላል፡፡ ሁለተኛው የማረጋገጫ መንገድ በፍርድ ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ነው፡፡ ይህም ማለት ተበዳሪው በፍርድ ቤት ቀርቦ በከሳሹ የቀረበበትን ክስ ማለትም ከከሳሹ ገንዘብ የተበደረ መሆኑን፣ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ በማያሻማ መንገድ ካመነ በቀላሉ የብድሩ መኖር የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡ ሦስተኛውና የመጨረሻው የማረጋገጫ መንገድ በመሐላ የማረጋገጥ ሂደት ነው፡፡ መሐላ ማለት በክርክር ወቅት አንድ ተከራካሪ ወገን በሚያቀርበው ማስረጃ ወይም በሚናገረው ፍሬ ነገር እውነትነትን ለማረጋገጥ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ቅፅ ላይ የሚሰጡት ማረጋገጫ ነው፡፡

የብድር መመለሻ ጊዜ፡- ብድር ውል እንደመሆኑ መጠን ለተዋዋይ ወገኖች ሰፊ ነፃነት መሰጠት አለበት፡፡ በመሆኑም ሕጉ ስለብድር መመለሻ ጊዜ በተዋዋይ ወገኖች የተወሰነ ጊዜ በሚኖርበት ወቅት ይህንኑ ዕውቅና በመስጠት ክፍያው በዛ ጊዜ መሆን እንደሚገባው ሕጉ አፅንኦት ሰጥቶበታል፡፡ ከዚህም ባለፈ ብድሩ ወለድ የሌለበት ከሆነ የተበደረውን ገንዘብ ለመመለስ ማሰቡን ለአበዳሪው ከአንድ ወር በፊት አስታውቆ የመመለሻ ጊዜው ከመድረሱ በፊት ሊመልስለት እንደሚችልም ሕጉ ይደነግጋል፡፡ የብድሩ መመለሻ ጊዜ በተዋዋይ ወገኖች ያልተወሰ በሚሆን ጊዜ ሕጉ ብድሩ በምን ያክል ጊዜ ውስጥ ሊከፈል እንደሚገባው ደንግጓል፡፡ ይኼውም አበዳሪው መልስልኝ ሲል ከጠየቀበት ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መመለስ እንዳለበት ተደንግጓል፡፡.........
.......................ተበዳሪውም በአበዳሪው ሳይጠየቅ መክፈል ቢፈልግ ለመክፈል ያለውን ሀሳብ ከአንድ ወር በፊት ካስታወቀ በኋላ ዕዳውን መመለስ እንደሚችል እንዲሁ ተደንግጓል፡፡

በብድር ላይ ሊኖር ስለሚችል ወለድ፡- በብድር ውል ላይ ሊኖር ስለሚችል ወለድም ለተዋዋይ ወገኖች ነፃ ፈቃድ የተተወ ጉዳይ ነው፡፡ ብድሩ ወለድ የሚከፈልበት ስለመሆኑ በውሉ በግልፅ ካልተገለፀ ግን ተበዳሪው በምንም መልኩ ወለድ እንዳይከፍል ሕጉ ጥበቃ ያደርግለታል፡፡ ሕጉ በብድር ውሉ ላይ ወለድ ይኑር አይኑር የሚለውን ጉዳይ በተዋዋይ ወገኖች እንዲወሰን ነፃነት የሰጠ ቢሆንም በወለድ መጠኑ ልክ ላይና ስለሚከፈልበት ጊዜ ወይም ወለዱ ስለሚሰላበት ጊዜ ግን ገደብ አስቀምጧል፡፡ በዚህም መሰረት ተዋዋይ ወገኖች የወለዱን መጠን በዓመት ከ12 በመቶ በላይ ማድረግ እንደማይችሉ ገደብ ጥሏል፡፡ እንዲሁም የወለዱ መጠን በውሉ ላይ ካልተገለፀ እና ወለድ የሚከፈልበት ብድር መሆኑ ብቻ ተገልፆ ከሆነ ወይም ወለዱ ከ12 በመቶ በላይ ይሆናል የሚል የውል ቃል ካለ መከፈል የሚችለው የወለድ መጠን በዓመት 9 በመቶ ብቻ እንደሚሆንና የሚሰላውም ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ ብድሩ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር በየዓመቱ መጨረሻ ላይ መሆን ይገባዋል ይላል ሕጉ ፡፡

የብድር አከፋፈል (የሚከፈለው ነገር)፡- በብድር አመላለስ ወቅት ሌላው ግለፅ መሆን ያለበት ጉዳይ ብድሩ በየትኛው ሀገር የገንዘብ ዓይነት ነው? ከብድሩ በኋላ የምንዛሬ ዋጋ መለዋወጥ ቢያጋጥምስ ምን ይሆናል? የሚለው ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የፍትሐብሔር ሕጉ ግልፅ ድንጋጌዎች አሉት፡፡ በዚህም መሰረት የብድር ውሉ የተደረገው በኢትዮጵያ ብር ከሆነ ብድሩ በሚመለስበት ወቅት ባለው ሕጋዊ የኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘብ ወይም ለዚህ የገንዘብ መጠን የሚተካ የውጭ ምንዛሬ በማቅረብ ከዕዳው ነፃ እንደሚሆን ተደንግጓል፡፡ የሚከፈለውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ የብድር ውሉ በሚከናወንበት ጊዜ በትክክል የተበደረውን ያክል እንጂ ሌላ ነገር እንደማያካትትና በመሀል ሊያጋጥም የሚችለውን ወይም ያገጠመውን የገንዘቡ ዋጋ መለዋወጥ ግምት ውስጥ መግባት እንደሌለበትም ሕጉ አያይዞ ይገልፃል፡፡ ብድሩ በውጭ አገር ገንዘብ ተደርጎ ከነበረ ደግሞ ብድሩ በሚከፈልበት ጊዜ በዛ አገር ሕጋዊ መገበያያ በሆነው የገንዘብ ኖት መከፈል ያለበት ሲሆን መጠኑም የተበደረውን ያክል ብቻ መሆን እንዳለበት ሕጉ አመልክቷል፡፡ የብድር ውሉ የተደረገው ከገንዘብ ውጪ ባሉ የሀብት ዓይነቶች በሚሆንበት ጊዜ ለምሳሌ፡- ለምግብ የሚሆኑ ነገሮች፣ ሸቀጦች ወይም መአድናት ሲሆኑ ተበዳሪው በተበደረው ልክ ብዛቱንና ዓይነቱን በመክፈል ከዕዳው ነፃ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ከብድሩ በኋላ በሚኖር የዋጋ መለዋወጥ የብድድር አመላለሱን መጠንና ዓይነት ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ የለም፡፡
federal attorney general
share share
#share #Share
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
👍1
Live stream started
Live stream finished (22 minutes)
ይግባኝ ማስፈቀጃ/በህጉ የተቀመጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድ የሚቀርብ አቤቱታ/
====================
አንድ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈበት ምክንያት በቂ መሆኑን ሲረዳ ይግባኙ እንዲቅርብ ሊፈቅድ እንደሚገባ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 326/1/ ስር ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ፍ/ቤቱ የቀረበለት ምክንያት በቂ መሆን አለመሆኑን በአግባቡ ሊመረምረው ይገባል፡፡ በእርግጥ በቂ ምክንያት የሚባሉት ነገሮች ሕጉ ዘርዝሮ ያላስቀመጣቸው በመሆኑ ለመወሰን አስቸጋሪ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም የምክንያቱ በቂ መሆን አለመሆን በእያንዳንዱ ጉዳይ ከሚቀርቡ ፍሬ ነገሮች ጋር ተገናዝበው ሊመዘኑ ይገባል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 38145 ቅጽ 8፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 326/1/
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ መሠረት ለአንድ ፍርድ ቤት መዝገብ ሹም የተሰጠው ሥልጣን ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ማለፍ አለማለፉን በመመልከት ይግባኝ መዝገቡ እንዲከፈት ማድረግ ሲሆን ይግባኙ ጊዜውን ጠብቆ ያልቀረበ ከሆነ ማመልከቻውን መመለስ፣ ማመልከቻው የተመለሰበት ወገን የይግባኝ ጊዜው ያለፈበት ሕጋዊ ምክንያት ካለው ማስፈቀጃ አቤቱታውን በማቅረብ ይኸው ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድለት ራሱን የቻለ አቤቱታ አቅርቦና ይህ መዝገብ ተከፍቶ ጉዳዩ ለችሎት ቀርቦ ችሎቱ የይግባኝ ማስፈቀጃውን በመመርመር በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 መሠረት ተገቢ ነው ያለውን ትእዛዝ የሚሰጥበት ነው፡፡
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 ድንጋጌዎች ጋር አንድ ላይ ሲነበቡ የመዝገብ ቤት ሹም ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለችሎት እንዲቀርብ የመፍቀድ ስልጣን የሌለው መሆኑን የሚያሳዩ ሲሆን ፋይሉ ተከፍቶ ቀርቦ ከሆነም ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ ይግባኙ የቀረበው ጊዜው ከአለፈ በኋላ ነው በማለት መዝገቡን ከመዝጋት የሚከለክለው አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 61843 ቅጽ 11፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 324-326
🔵Urgent reminding notice♨️♨️
🔴 Dear Ethiopians........⁉️⁉️⁉️
You came naked,
You will go naked.
You arrived weak,
You will leave weak.
You came without money and things,
You will leave forever without money and things.
Your first bath, Someone washed you,
Your last bath, Someone will wash you.

🩸This is life‼️‼️‼️‼️‼️

So why so much malice, so much envy, so much hate, so much resentment, so much selfishness and so much pride⁉️ why, when we have to go empty handed⁉️

BE KIND…........We have limited time on Earth don’t waste it in uselessness.🩸🩸🩸🩸🩸🩸
share share
#share #Share
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Attorney
#abay_insurance_s_c
#legal_services
#law
#attorney
Addis Ababa
LLB degree in Law or related fields of studies with relevant work experience
Competence:-
- Special training; Competence in MS Office
- Very high customer Orientation
- Excellent interpersonal communication skill,
- High coordination skill & proactive personality
- Detail orientation & analytical skill
- Excellent English language skill
Minimum Years Of Experience: #1_years
Deadline: July 27, 2021
How To Apply: Send your CV & relevant documents via: geneta@abayinsurancesharecompany.com or in person at Abay Insurance S.C Office, located from Urael Church on the way to Bole Atlas area, near to Atlas traffic light, to the Head office 4th floor, room no. 405 For further information contact Tel. 0116663332
Forwarded from ሕግ ቤት
charge case.docx
11.4 KB
የወንጀል ክስ ፎርም በEnglish version Hypothetical case.
@EthiopianLawStudentsUnion
via about law
👍1
attorny general regulatin.doc
433 KB
የደቡብ ክልል አቃቢያን መተዳደሪያ ደንብ
ማስታወቂያ ለ5ኛ አመት የ Exit Exam ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ‼️
ፈተናው ይራዘም እያሉ ከዚህም ከዚያም መረጃወችን የሚያንሸራሽራሩ እና ተፈታኞ ተረጋግተው ለፈተና እራሳቸውን እንዳያዘጋጁ ከንቱ ተስፋ ሰንቀው የቴሌግራም ግሩፕ ከፍተው ተፈታኞችን የሚያደናግሩ እንዳሉ እየገለፅን።
ምንም አዲስ ነገር የሌለ በመሆኑ ተረጋግታችሁ ተዘጋጁ፤
ማንኛውም ጥያቄ እና ብዥታ ቢኖር ትክክለኛ የሚመለከተውን ሰው በመጠየቅ እና የዚሁ ቻናል አካል በሆነው @ALE_lawsocieties ላይ በመጠየቅ ትክክለኛ የሚመለከታቸውን ሰዎች ማግኘት ትችላላችሁ።
ተዋክበው ለሚያዋክቡ እራሳችሁን አታጋልጡ።
ሁሌም በእየ አመቱ እንዲህ አይነት ወከባ በመፍጠር የግል ቴሌግራም ግሩፕ አድማቂ ከማድረግ የዘለለ ምንም መፍጠር እና መቀየር የማይችሉ እና ምንም አይነት ውክልና ሳይኖራቸው በግላቸው ተነሳሽነት የግላቸው አጀንዳ ለመፈፀም petition እናሰባስብ 5th year እንዲሁ ቅሬታ Appeal እና መሰል ማሰሚያ በሚል ይቀሳቀሳሉ።
በጣም የግል ቴሌግራም ግሩፕ አባላት (አድማቂ) እንዲበዙላቸው ከመጓጓታቸው የተነሳ ያልተፈጠረ ያልተለወጠ፤ ያልተወሰነን ምንም በሌለበት አዲስ መረጃ አገኘን እንደገና አሳሳቢ ጉዳይ ምናምን እያሉ የብዙሀኑ ጥያቄ እና ፍላጎት በማስመሰል መረጃ በማሰራጨት
ተማሪዎችን ያዘናጋሉ።
የሚመለከተው የመንግስት ክፍል ለሁሉም አራቱም አቅጣጫ ለሚገኙ የሀገሪቱ ተማሪዎች አስፈላጊውን ጠቃሚ የሚለውን ሁኔታ ከህግ ት/ት ቤቱ ሄዶች እና ዲኖች መረጃ በመሰብሰብ እና በጋራ በመወያያት ማለትም በመጨረሻ ከሁሉም የኒቨርሲቲ ከህግ ት/ት የተውጣጡ ሄዶች እና ዲኖች በኮንሰርቲዬም ስብሰባ የሚወሰን ሲሆን እንድታውቁ እንላለን።
🔴ቅሬታ ጥያቄ ካለ ለህግ ት/ትቤታችሁ ሄድ ወይም ዲን ማቅረብ ነው ስርዓቱ።
🔵አዲስ ነገር ከህግ ት/ትቤታችሁ ሄድ ወይም ዲን መጠየቅ ነው ትክክለኛው።
በተረፈ በዚህ ቻናል የሚለቁቁ መረጃዎችን ተከታተሉ።
ተረጋግታችሁ ተዘጋጁ‼️
via Eta.B. Addis Ababa
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Babu:
Gys let me tell you one thing there are some student, who don't want to exit, to be extended ena they are confusing us, pleas brothers and sisters don't be confused. We are not sure, exit may extended or may not so please study hard and wait for us.

ስታጠኑ exit እንደማይራዘም አድርጋችሁ አጥኑ or ይራዘማል የሚለው ከአእምሮቹህ አውጡት እና አጥኑ። እኛ የተቻለንን ነው የምናደርገው። Study hard💪💪
ስለአዲሱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013፡- አንዳንድ ምልከታዎች
1. የአዋጁ መልካም ጎኖች፡-
1.1. የተለያዩ አዋጆችን አንድ ላይ አጠቃልሎ/consolidated/ ለአጠቃቀም ምቹ ማድረጉ፣
1.2. በፍርድ ሊወሰኑ በሚችሉ ጉዳዮችና በሕገ መንግስታዊ መብቶች ላይ ፍርድ ቤቶች ስልጣን ያላቸው መሆኑን ግልጽ ለማድረግ ጥረት ማድረጉ፣
1.3. ስለመሰረታዊ የሕግ ስህተት አመላካች ሊባሉ የሚችሉ መስፈርቶችን ማስቀመጡ፣
1.4. የክልል ጉዳዮች ወደ ሰበር ችሎቱ ሊመጡ የሚችሉበትን አግባብ/መንገድ/ ለማጥበብ መሞከሩ፣
1.5. የሰበር ችሎት ውሳኔ አስገዳጅነት የሚጀምርበትን ጊዜ ማሳየቱ (ባይታተምም)፣
1.6. የሰበር ችሎት ውሳኔ የሚቀየርበትን ስርዓት የሕግ ማዕቀፍ እንዲኖረው ማድረጉ፣
1.7. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶችን የስረ ነገር ስልጣን መጨመሩ፣
1.8. የአለም አቀፍ ድርጅቶች በፍትሃ ብሔር ሊከሰሱ የሚችሉበት አግባብ ካለ ክስ ሊቀርብባቸው እንደሚችል የሚያሳይ ድንጋጌ መያዙ፣
1.9. ፍርድ ቤቶቹ በበጀትና በድጋፍ ሰራተኞች አስተዳደር ረገድ ነጻነት እንዲኖራቸው ማስቻሉ፣
1.10. ከዳኝነት አገልግሎት አስጣጥ ጋር በተያያዘ አጋዥ መመሪያዎች ሊወጡ የሚሉበትን አግባብ መደንገጉና እንደ አስማሚ መርና የጉዳዮች ፍስት አስተዳደር ያሉትን አዳዲስ ሀሳቦችን ማካተቱ፣
1.11. ከዳኞች ከችሎት የመነሳትና ከውሳኔዎች/ትዕዛዛት አፈጻጸም ጋር ተያይዞ አስተማሪ ቅጣቶች ሊጣሉ የሚችሉበትን አግባብ የሚያሳዩ ድንጋጌዎችን መያዙ……ወዘተ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

2. የአዋጁ ውስን ድክመቶች
2.1. መግቢያው ላይ ስለአዋጁ ዓላማዎች ሲዘረዝር የፌዴራል ጉዳዮችን ለመለየት ብሎ ያለመጥቀሱ፣(አዋጅ ቁጥር 25/88 ግን ይህንኑ በመግቢያው ላይ ይገለጽና አዲሱ አዋጅ የያዛቸውን ሌሎች ነጥቦችን አይጠቅስም ነበር (ቁንፅል መግቢያ ይዞ ነበር)፣
2.2. የአርትኦት ስራ ግድፈት መኖሩ- የአማርኛም ሆነ የእንግሊዝኛ ፊደላት እና ስርዓተ ነጥብ አጠቃቀም ችግሮች መኖራቸው
ለምሳሌ፡-
o የአማርኛ ስርዓተ ነጥብ የሆነው ነጠላ ሰርዝ በብዙ ቦታዎች ከቃላት እንዲርቅ መደረጉ፣ ባንዳንድ ቦታዎች ደግሞ በነጠላ ሰረዙና በቀጣዩ ቃል ወይም ሐረግ መካከል ክፍተት/ስፔስ/ ሳይኖረው መቅረቱ፣ በቃላት ወይም በሐረጎች መካከልም ስፔስ መኖር ሲገባው መታለፉ፣
o ፌዴራል የሚለው ቃል በብዙ ቦታዎች(ምሳሌ በአንቀጽ 3(1) ፣ አንቀጽ 4 የመጀመሪያው ፓራግራፍ፣ በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 16 ”ዴ“ ከተባለ በኋላ በሌሎች በርካታ ድንጋጌዎች ስር በፊደል ”ደ“ መተካቱ፣ በብዙ አዋጆች የነጋሪት ጋዜጣ ስያሜም ሆነ ተቋማት ስም ሲገለጽ ፌዴራል የሚል እንጂ ፌደራል የሚል ሁኖ አይታይም፣
o አንቀጽ 3 (2) ስር ድንጋጌዎች መባል ሲገባው ደንጋጌወች ተብሎ መታለፉ፣
o በአዋጁ አንቀጽ 5(1(ደ)) ስር ወሳኝ ኩነት የሚለውን ሐረግ ወደ እንግሊዝኛ ሲተርጉም Critical Event ( ስለወሳኝ ኩነቶች የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 760/2004 እንኳን ባለማገናዘብ (Vital Events)) ብሎ ማስቀመጡ፣
o በአንዳንድ ድንጋጌዎች ስር ፍርድ ቤቶች የሚለውን ቃል በፍ/ቤቶች መተካቱ (አዋጅ ላይ አሳጥሮ መፃፍ ተገቢነት የሌለው ከመሆኑም በላይ ወጥነት ያለመኖር)፣ ለምሳሌ በአዋጁ አንቀጽ 17(1(ተ))፣ በአንቀጽ 37(1)(2)(4)
o በአዋጁ አንቀጽ 5(1(ደ)) እቁብ የሚለውን ቃል association በሚል መተርጎሙ(እቁብ በፈረንጅ አገር የሚታወቅ አይመስለኝም፣ አገር በቀል ማህበራዊ ተቋም ስለሆነ እንዳለ ቃሉን Equb ብሎ በአዋጁ ማስቀመጥ የማይቻልበት አግባብ አለ ብዬ ስላላስብኩ)፣
o በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር ስለሚኖሩ ችሎቶች ሲደነግግ(አንቀጽ 25) የፍትሃ ብሔርና የወንጀል የመጀመሪያ ደረጃ ችሎቶች እንዲሚኖሩት መግለጹ በአዋጁ አንቀጽ 8 ስር ከተደነገገው ጋር የማይጣጣም መሆኑ(ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ ደረጃ ያለው ብቸኛው ስልጣን ከስልጣን ይለይልኝ ጋር የተያያዘ ነው)፡፡ በዚህ ረገድ የሚቀርቡ ጥያቄዎች ደግሞ በጣም ውስን( እንዲያውም የማይቀርቡበት የበጀት አመትም ነበር) ስለሆነ ለእነዚህ ጉዳዮች ብሎ የመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን ያለውን ችሎት ማደራጀት የሰው ሃይልን ብክነት ያስከትላል፣(ምናልባት ይህ አባባል በአዋጁ እንዲስፍር የተደረገው ከዚህ በፊት የነበረውን አዋጅ በመቅዳት ሂደት በተፈጸመ ስህተት ወይም ስልጣን ይለይልኝ የሚለው ጉዳይ ስላለ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን ብዥታ ለማስወገድ ሊሆን ይችላል)፣
o በአዋጁ አንቀጽ 23 (1(ሐ)) ስር መጨረሻ ላይ ….13241… የሚለው ቁጥር ያለምክንያት ገብቶ መታተሙ፣
o በአዋጁ አንቀጽ 4(16) ስር በአማርኛው ቅጅ የማስረጃ ሕግ የሚለው ሐረግ በእንግሊዝኛው ቅጅ Procedure Code በሚል የተተረጎመ ሁኖ መታየቱ፣ በዚሁ ድንጋጌ ስር በእንግሊዝኛው ትርጉም ውስጥ የመጀመሪያው ዐርፍተ ነገር ከአለቀ በኃላ አዲስ በሚጀምረው ዐረፍተ ነገር ውስጥ other የሚለው ቃል በ“ካፒታል” O መጀመር ሲገባው በ”ስሞል“ o መጀመሩ፣ እንዲሁም In addition to የሚለው ቃል አርፍተ ነገሩ ባላለቀበት ሁኔታ I በካፒታል ሌተር መጻፏ፣
o በአንዳንድ አንቀጾች ስር ፊደሉ ”ስ ” መሆን ሲገባው ”ሰ“ ተብሎ መጻፉ(ለምሳሌ በአንቀጽ 19(1( ረ)) ስር ….ሰለተፈጻሚነቱም… በሚለው ቃል ስር ያለው፣ በአንቀጽ 36(2) ስር ….ማሰገባት…. የሚለው ቃል፣በአንቀጽ 47(4) …እሰከ…. ፣ በአንቀጽ 55(2) ስር …ለማሰፈጸም… የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
o በአዋጁ አንቀጽ 53 ስር በአማርኛው ቅጅ …ባለሙያዎች… መባል ሲገባው ….ባለሙያወች… መባሉ፣
o በአዋጁ አንቀጽ 50 ስር ቴክኖሎጂ መባል ሲገባው ቴክኖሎጅ መባሉ፣
o በአዋጁ አንቀጽ 26(3) ስር የክልል የሚለው የአማርኛ ቅጅ በእንግሊዝኛው reginal በሚል መተርጎሙ፣
o በአዋጁ አንቀጽ 25(3) ስር በብዙ ቁጥር አገላለጽ በሚገኙ እያለ ማንኛውም ችሎት ብሎ በነጣለ ማስቀመጡ፣
o በአዋጁ አንቀጽ 27(2) ስር የአማርኛው ቅጅ የስር ፍርድ ቤት መዝገብን ሰበር ችሎቱ ማስቀረብ እንደሚችል ሲገልጽ መዝገቡን የሚያስቀርበው በራሱ በኩል መሆኑን በሚያስገነዝብ መልኩ ደንግጎ እያለ በእንግሊዝኛው ቅጂ ግን ችሎቱ መዝቡን የሚያስቀርበው በተከራካሪ ወገኖች በኩልም ሊሆን እንሚችል መደንገጉ፣
o በአንዳንድ አንቀጾች የፍርድ ቤቶቹን ስያሜ በእንግሊዝኛ ሲጠቅስ የመጀመሪያ ፊደላትን ካፒታላይዝ ለምሳሌ በትልቅ ፊደላት/capital letters/ Federal High Court ይልና ትንሽ ቆይቶ ደግሞ በትንሽ ፊደላት(Small) federal high court ብሎ ማስቀመጡ(ምንም እንኳን መሰረታዊ ባይሆንም ወጥነት የሌለው የስም አገላለጽ በመሆኑ ተገቢነት የለውም..)፣
o በአዋጁ አንቀጽ 34(5) ስር የአማርኛው ቅጅ ቀናት ማለት ሲገባው ቀን ብሎ ጠቅሶ ካለፈ በኋላ የእንግሊዝኛው ቅጅ days ብሎ መተርጎሙ፣
o በአንዳንድ ድንጋጌዎች ስር የአማርኛ ቅጂው ላይ ቁጥር ሲኖር ቁጥሩ በኢትዮጵያ(በግዕዝ) አኃዝ እየተቀመጠ ከሄደ በኋላ በአንዳንድ ድንጋጌዎች ደግሞ በፊደል ብቻ የተቀመጠ ሁኖ መገኘት(ለምሳሌ አንቀጽ 52)፣
o በአዋጁ አንቀጽ 53(3) የአማርኛው እና የእንግሊዝኛው ቅጅ የማይጣጣሙ መመስል፣ የአማርኛው ቅጅ እያንዳንዱ የአማካሪ ምክር ቤቱ አባል በግል ደረጃ ኃላፊነቱን ሲወጣ ስለሚኖረው ግዴታ የሚያውጅ የሚመስል ሲሆን የእንግሊዝኛው ቅጅ ግን አማካሪ ምክር ቤቱ እንደተቋም ያለበትን ግዴታ የሚያሳስብ ይመስላል፣
o በአንቀጽ 35(2) ስር የቅጣቱን መጠን ከ፩ሺህ እስከ፫ሺህ ብሎ አስቀምጦ እያለ እና ይህ አገላለጽ መነሻውንና ጣሪያውን የሚያሳይ ሁኖ እያለ በድጋሚ በአርፍተ ነገር ከአንድ ሺህ ብር ያላነሰ ከሶስት ሺህ ብር ያልበለጠ ማለቱ እንዲሁም ከ፫ሺህ እስከ ፯ሺህ የሚለውንም ከሶስት ሺህ ብር ያላነሰ ከሰባት ሺህ ያልበለጠ ብሎ አላስፈላጊ በሆነ አገላለጽ መጠቀሙ፣ በዚሁ ድንጋጌ ስር በቁጥር የተቀመጠውን መነሻ እና ጣሪያውን በአረፍተ ነገር ሲያስቀምጥም ቅንፍ ከፍቶ የዘጋበት ቃል ትክክለኛ ያለመሆኑ(ቅንፉ ሲዘጋ ያልበለጠ በሚለው ቃል መጨረሻ ላይ ያለመቀመጡ፣
o በአዋጁ አንቀጽ 26(4) ስር ባለሰባት ዳኞች ሰበር ችሎት የራሱን ውሳኔ ሊያሻሽል እንደሚችል የሚገልጽ ድንጋጌ እያስቀመጠ በድንጋጌው የመጨረሻ አረፍተ ነገር ፊደል… ያ… ቀሪ ተደርጋ ሊሻሻል ይችላል ተብሎ መቀመጡ፣(ሊያሻሽል……. መባል የነበረበት ይመስለኛል).
2.3 አዋጁ ስለሰበር የሕግ ትርጉም አስገዳጅነት የሚገልጽበት አግባብ ለመደበኛ ፍርድ ቤቶች ብቻ እንደሆነ የሚያስመስል መልዕክት የሚያስተላልፍ መሆኑ
 በአዋጁ አንቀጽ 10(2) ስር የሰበር ችሎቱ የሚሰጠው የሕግ ትርጉም አስገዳጅነቱ በየትኛውም ደረጃ በሚገኝ የፌዴራልም ሆነ የክልል ፍርድ ቤት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በአዋጁ አንቀጽ 2(5) ደግሞ የመጨረሻ ውሳኔ የሚባለው በፍርድ ቤት የተሰጠ ብቻ ያለመሆኑን የሚያስገነዝብ ድንጋጌ ይዟል፡፡ ስለሆነም ሁለቱ ድንጋጌዎች እንዲሁም አንቀጽ 2(4(ሰ)) ድንጋጌ መጣጣም ይገባቸው የነበረ ከመሆኑም በላይ የህግ ትርጉም አስገዳጅ እንዲሆን ከፈለገበት ዓላማና ችሎቱ ሲከተለው ከነበረው፣ አሁንም እየተከተለ ካለው አሰራር አንጻር የሕግ ትርጉሙ ለፍርድ ቤት፣ በሕግ የመዳኘት ስልጣን በተሰጣቸው አካላት፣ ተቋማትና አማራጭ የክርክር መፍቻ ሰጪ አካላት ጭምር አስገዳጅነት እንዲኖረው ግልጽ መደረግ ነበረበት፡፡ ለግልፅነት ብዬ ያነሳሁት እንጂ እነዚህ ተቋማት የሰበር ችሎቱን የህግ ትርጉም ተቀብለው ተግባራዊ ማድረግ አንችልም ማለት ይችላሉ ለማለት አለመሆኑ ይታወቅልኝ፡፡
2.4 መካተት የነበረባቸውን ጉዳዮች የተወ መሆኑ
 የፍሬ ነገር እና የማስረጃ ምዘና ስህተት የሚባለው ምን እንደሆነ ትርጉም ማስቀመጥ ወይም አመላካች ነጥቦችን ጠቅሶ ያለማለፉ፣ በዚህ ረገድ የኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር ተጠቃሽ ነው፡፡
 በሰበር ችሎቱ የተሰጠ የህግ ትርጉም ለአንድ ጉዳይ አስገዳጅ ነው የሚባለው በመሰረታዊ ሕግና በፍሬ ነገሮች መካከል መመሳሰል ሲኖረው መሆን ያለመሆኑን ጠቅሶ ያለማለፉ፣
 የሰበር ችሎቱ ዳኞች በህግ ትርጉሙ የሚገደዱ መሆን ያለመሆናቸው፣(ምንም እንኳን ዳኞቹ ከሌሎች የጠቅላይ ፍርድ ቤት ችሎቶች የተለዬ ስልጣን የሌላቸው መሆኑ ቢታወቅም ለክርክር በር ይከፈት የነበረ ጉዳይ መሆኑ ይታወቅ ስለነበር መፍትሔ ተበጅቶ ቢታለፍ መልካም ነበር)፣
 የሰበር ችሎቱ ውሳኔ ለመቀየር የሚቻልባቸው ምክንያቶች አመላካች በሆነ መንገድ(ለምሳሌ ተቃራኒ ውሳኔ መኖር፣ ሶሺዮ ኢኮኖሚክ ፋክተርስ…) ተጠቅሰው ያለማለፍ፣
 ውሳኔውን ለመቀየር ሲያስፈልግ አቋሙ መያዝ ያለበት ከአምስቱ ዳኞች በስንቱ ዳኞች እንደሆነ ተለይቶ መቀመጥ ነበረበት፣ እንዲሁም ተጨማሪ ሁለት ዳኞች ወደ ችሎቱ የሚገቡበት ከሌሎች የሰበር ችሎቶች ውስጥ ነው ወይስ ከይግባኝ ችሎቶች ጭምር የሚለውም(ምንም እንኳን ሁሉም የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የሚሾመው በተመሳሳይ መመዘኛ ስለሆነና ዳኞችን መመደብ የፍርድ ቤቱ የአስተዳደር ኃላፊነት ቢሆንም ከችሎቱ ልዩ ስልጣን አንጻር ለግልጽኝነት ሲባል ቢቀመጥ መልካም መስሎ ይታያል)፣
 በሰበር ችሎቱ የሚደረገውን የጽሑፍ ክርክር ሬ/ጽ/ቤት ማከናወን የሚችል መሆኑ(በአሰራር ያለ ቢሆንም እንዲሁም ወደፊት በጋይድላይን ሊወጣ የሚችል ቢሆንም)
 አዋጅ ቁጥር 322/95 አዲስ ክልል ሲፈጠር ስለሚኖረው ህጋዊ ውጤት
o ለምሳሌ በዚህ አዋጅ መሰረት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከተቋቋመባቸው ክልሎች አንዱ የደ/ብ/ብ/ሕ/ብ/ክልላዊ መንግስት አንዱ ሲሆን ከዚህ ክልል ውስጥ የሲዳማ ክልል ተፈጥራል፡፡ ስለሆነም የሲዳማ ክልል የደቡብ ክልል አካል ስለነበር በአዋጅ ቁጥር 322/95 መሰረት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተቋቁሞበታል ሊባል ይችላልን የሚለው ጥያቄ በቀላሉ የሚመለስ ነው ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡
 እንዲሁም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተቋቋመባቸው ክልሎች ውስጥ የፌዴራሉን መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስልጣንን በውክልና የሚያዩት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በሚሰጡት ውሳኔ ይግባኙ መቅረብ ያለበት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆን ያለመሆኑም በዚህ አዲስ አዋጅ ምላሽ ማግኘት ይገባው ነበር፡፡ ይህ እንዳይሆን የሚከለክል የሰበር ችሎቱ አስገዳጅ ውሳኔ ስላለ፡፡
2.5 ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮች ያሉበት መሆኑ
አዲሱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ለአዲስ አበባና ለድሬዳዋ ከተማ ፍርድ ቤቶች በወንጀልም ሆነ በፍትሃ ብሔር ጉዳዮች ስልጣን ሰጥቷል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች በኢ.ፌ.ዲ.ሪፐብሊክ ሕግ መንግስት የተቋቋሙ መሆን ያለመሆኑ አከራካሪ ጥያቄ ከመሆኑም በላይ እነዚህ ፍርድ ቤቶች ከፌዴራል ስርዓት ጽንሰ ሀሳብ አንጻርም ፍርድ ቤቶቹ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የተያያዙ ጉደዳዮችን ብቻ ለማየት ስልጣን ከሚኖራቸው በስተቀር የፌዴራል ጉዳዮችን እንዲዳኙ የሚደረግበት የሕግ አግባብ ያለ አይመስለኝም፡፡ እንዲሁም ህገ መንግስቱ የሰበር ሰበር እንደሚኖር የሚያሳይ ድንጋጌ ይዞ እያለና ይህ ደግሞ ሕገ መንግስቱ ሲረቀቅ በነበረው ውይይትም በግልጽ ተነስቶ አረቃቂው አቋም ይዞበት ያለፈው ሁኖ እያለ በአዲሱ አዋጅ የክልል ጉዳዮች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሚታዩበት መንገድ እጅግ ጠባብ እንዲሆን መደረጉ ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ የሚያስነሳ መስሎ ይታያኛል፡፡ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች በርካታ የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ጉዳዮች እንዲመለከቱ እንዲሁም የሰበር ሰበር ስርዓት እድል እጅግ ጠባብ እንዲሆን የተደረገበት አቢይ ምክንያት ግልጽ የሆነ ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ ስላለ ሳይሆን በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ያጋጠመው የመዝገብ ክምችት ይመስለኛል፡፡ የመዝገብ ክምችት ማጋጠም ወደ ፍርድ ቤት የሚመጡትን ጉዳዮች ለመከልከል/ ለመገደብ ወይም የፍርድ ቤቱን ስልጣን ለሌላ አሳልፎ ለመስጠት ህጋዊ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡
3. ማጠቃለያ
ጠንካራ ፍርድ ቤት ለአንድ አገር ብልፅግና ወሳኝ ሚና አለው፡፡ ጠንካራ ፍርድ ቤት የሚኖረው ደግሞ የፍርድ ቤቱን ነፃነትና ገለልተኝነት የሚያረጋግጥ ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ ሲኖርና የወጣው ህግም በትክክል ሲተገበር መሆኑ ይታመናል፡፡ በእኛ አገር ነጻና ገለልተኛ ፍርድ ቤቶች እንደሚኖሩ በሕገ መንግስቱ ጭምር የተደነገገ ቢሆንም በህገ መንግስቱ አግባብ የተቋቋሙ ፍርድ ቤቶች ለበርካታ ጊዚያት የተለያዩ አዋጆች ሲወጡላቸው የነበሩ ከመሆኑ ውጪ ነጻና ገለልተኛ ነበሩ ለማለት አያስደፍርም፡፡ ለዚህ ትልቁ ማሳያ ደግሞ ፍርድ ቤቶቹ የራሳቸውን በጀት ማስመደብና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን የማስተዳደር ስልጣን ያልነበራቸው መሆኑ ነው፡፡ አሁን የወጣው ሕግ ግን እነዚህን ችግሮች አስወግዷል፡፡ ይህም ትልቅ እምርታ ነው፡፡ በዚህም ለፍርድ ቤቶቻችን ነጻነታቸውና ገለልተኝነታቸው ማሳኪያ የሚሆን ትልቁ ሐዲድ ተገንብቶላቸዋል ማለት ይቻላል፡፡ በሐዲዱ መጓዝ እና ወደ መዳረሻው መድረስ ደግሞ የፍርድ ቤቶቹ አመራሮች፣ ዳኞችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ኃላፊነት ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት የአዲሱ አዋጅ ችግሮች መሰረታዊ ሊባሉ የማይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አንድ ህግ በአንድ ተቋም መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ታስቦ ሲወጣ ትልልቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ፣ በአሰራር ሂደት ያጋጠሙትን ችግሮች መቅረፍ እና ረዥም አመታት ሊያሰራ የሚችል/ ዘመን ተሻጋሪ ሁኖ መቀረፅ ያለበት መሆኑ የሚታመን ከመሆኑም በላይ ሕጉን የማርቀቅ ስራም/Drafting Task/ የዘርፉን ጥበብ ባሟላ መልኩ ከአርትኦት፣ ከቋንቋ ትርጉም ግጭትና ከይዘት መጣጣም እና ከሌሎች ተያያዥ ችግሮች የጸዳ እንዲሆን ተገቢው ጥንቃቄ ይጠይቃል፡፡
Via alamaw wele