አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በሀሰተኛ ማስረጃ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደባቸው ግለሰብ ከእስር ነፃ ተለቀቁ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሀሰተኛ ማስረጃ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደባቸው ግለሰብ በልዮ ሁኔታ ያለ ቅድመ ሁኔታ ከእስር ነፃ መውጣታቸውን የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት አስታወቀ።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዓለምሸት ምህረቴ ÷በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላ ድንጋይ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ግለሰብ ከአምስት ዓመት በፊት በእንጀራ እናቷ ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ ተገድላለች በሚል ግለሰቧ መሞቷ በሃሰተኛ ማስረጃ ተረጋግጦ ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ተጥሎባቸው ነበር።

ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ የእንጀራ ልጇን ገድላለች በሚል የሰሜን ሸዋ ዞን ዐቃቤ ሕግ የወንጀል መዝገብ ቁጥር 134/2008 ክስ መስርቶባቸው ሲከራከሩ መቆየታቸውን ተገልጿል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የቀረበውን ክስና ማስረጃ በመመርመር ጥፋተኛ ናቸው ብሎ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እና በአምስት ዓመት ከማንኛውም ማህበራዊ ግንኙነት እንዲገለሉ ውሳኔ አስተላልፎ እንደነበር ገልጸዋል።

በተሠጠው ውሳኔ መሠረትም ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ አምስት ዓመት በደብረብርሃን ማረሚያ ቤት በእስር መቆየታቸው ተገልጿል።

ነገር ግን ሞተች ተብላ በሀሰተኛ ማስረጃ የተረጋገጠላት ግለሰብ ከሌላ አካባቢ በሕይወት ቆይታ በቅርብ ጊዜ ወደ ትውልድ አካባቢዋ በመምጣቷ ሞተች ተብላ ጥፋተኛ ያልሆነችን ግለሰብ እንደ ጥፋተኛ ቆጥሮ ማረሚያ ቤት እንድትወርድ ያደረገችው ግለሰብ ማንነቷ በአካባቢው ህብረተሰብ እና በማስረጃ ተረጋግጧል ብለዋል።

በዚህም በሃሰተኛ ማስረጃ ተፈርዶባቸው በእስር የቆዩት ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ በአማራ ክልል የተሻሻለው የይቅርታ አሰጣጥ መወሰኛ መመሪያ ቁጥር 30/2010 መሠረት ጉዳያቸው ለአማራ ክልል ይቅርታ ቦርድ ቀርቦ የክልሉ ምክር ቤት በ29 ቀን 2013ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ወ/ሮ አዛለች ቤተምንዳ በልዮ ሁኔታ ያለ ቅድመ ሁኔታ ከእስር ነፃ እንዲወጡ እና የተጣለባቸው ገደብ እንዲነሳላቸው ወስኗል።

የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው በወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ ላይ የገጠመው ጉዳይ ያለ ማስረጃ የሚታሰሩ ታራሚዎች በሞራል፣በኢኮኖሚ፣በማሕበራዊ፣በ ቤተሰብ ላይ የሚደርስባቸውን ጉዳት ካሳ የሚካሱበት የሕግ ማዕቀፍ የሌሎች አገሮችን ልምድ በመቀመር ማዘጋጀት እንደሚገባ አስተማሪ ሆኖ አልፏል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Source :-FBC
1(አንድ)
#ሰው ነኝ ስል ሀይማኖት የለኝም ማለቴ አይደለም።
#ሰውነኝ ማለቴ ብሔር የለኝም ማለቴ አይደለም።
#ሰውነኝ ስል ልዮነቶችን የማከብር አንድነታችን አብልጦ የሚገዛኝ ነኝ ማለቴ ነው።
#ሰው ነኝ ስል አምላክ የፈጠረውን የሰው ልጅ በየትኛውም ስፍራ ይምጣ፣ ምንም አይነት እምነት ይከተል፣ ቋንቋችን ይለያይ ይመሳሰል:- ጠላቴ ነው ይጥፋ ብዬ በእምነቴ ሀጥያትን፣ በአለምአቀፍ ህግ ወንጀልን እንዲሁም በስነምግባር ነውርን አልፈፅምም ማለቴ ነው።
#ሰውነኝ ስል ነፍሴ ብሔር የላትም ማለቴ ነው።
#ሰውነኝ ስል በተለያዩ አካላት በሆነውም ባልሆነውም የሚነገረኝን ሁሉ እንደወረደ ባለመቀበል፣በስሜት ሳልመራ ለማደርገው እና ለምናገረው ነገር በፈጣሪዬ ትዕዛዝ አንፃር እና በህሊናዬ አመዛዝናለሁ ፣ አገናዝባለሁ ማለቴ ነው።
#ሰው ነኝ ስል ሀላፊ ጠፊ መሆኔን ሳልዘነጋ እስካለሁ በሀገር ውስጥም በውጪም ካሉ የሰው ዘር ወገኖቼን አክብሬ ከሁሉም ጋር በሰላም መኖርን እመርጣለሁ ማለቴ ነው።
#ሰውነኝ ስል ድክመት አለኝ፣ ሰውን ላሳዝን እኔም በሰው ልጎዳ ብችልም ከነስህተታችን ተራርመን ተደጋግፈን መኖር እንደምንችል አምናለሁ ማለቴ ነው።
#ሰውነኝ ማለቴ እርስ በርስ ለመጎዳዳት ፈፅሞ አልተፈጠርንም ብዬ በፅኑ አምናለሁ ማለቴ ነው።
#ሰውነኝ ስል መብትም እንዳለኝ ግዴታም አለብኝ እና ለኔ የምፈልገውን ለሌላው እንዳይሆን አልከላከልም ማለቴ ነው።
#ሰውነኝ ስል የሰላም መኖርያ እንደሚያስፈልገን አውቄ ሀገር ብትፈርስ ተጎጂዎቹ ሁላችንም መሆናችንን ተገንዝቤ ለልጅ ልጆቻችን እና ለመጪው ትውልድ ጭምር ሰላማዊት ሀገር ለማስረከብ ከሀገሬ ጎን እቆማለሁ ማለቴ ነው።
#ሰውነኝ ስል ከአላስፈላጊ መበሻሸቅና ክፉ ቃል ተቆጥቤ በሰከነ መንፈስ ለመፍትሔ እሰራለሁ ማለቴ ነው። ይቀጥላል...

ሰብአዊነት ፓለቲካ አይደለም!
ሰው መሆኔን መች አጣሁት በማለት የቃላት ጨዋታ ላይ ሳናተኩር እንደአፈጣጠራችን ሰው ሆነን እንገኝ!
#ሰውነኝ የፓለቲካ ሀሳብ አይደለም! ይልቁንም ፓለቲከኞችንም ሆነ የሀይማኖት ሰዎችን ፣ ምሁራንንም ሆነ የጥበብ ሰዎችን፣ አባት እና እናቶችን ብሎም መላው በሀገርም በውጪም ያሉ ወገኖችን ከዚህ ሰው ሰው ከማይሸት አካሄዳችን ተቆጥበን፣ ወደ ልቦናችን እና ወደ ስክነት ተመልሰን አንዱ ሲያለቅስ አንዱ የሚስቅበትንና በየተራ እርስ በእርስ የምንሳለቅበትን አካሄድ በማስቆም ሁላችንም አሸናፊ የሚያደርገንን መፍትሔ ሰብአዊነትን በማስቀደም እንድናመጣ እንለምናችኋለን🙏🙏🙏
#ሰው ነኝ
#ሰብእየ
#አንደኖ
#Aninama
#Iamhuman
Via I am Human Movement‼️
https://t.me/NegereFej
https://t.me/NegereFej
New Vacancy ‼️‼️‼️

Position: Lawyer II

Job Time: Full-Time

Job Type: Permanent

Place of Work: Addis Ababa, Ethiopia

Salary: 6,055.00


Application Deadline: Jul, 22/2021 (13 days left)

Accounting and Auditing Board of Ethiopia is looking to hire qualified applicants who fulfill the following requirements 

Level IX

Requirement

LLB/LLM Degree in Law

Experience  0/2 years

Required Number 2

Salary 6,055.00

How to apply

Interested applicants can submit all their necessary credentials such as Educational background, Work experience along with an unreturnable photocopy to the following address:

6 Kilo in front of Egypt Embassy on Leadership Institute Building 4th floor 

Office number 402 

Tel 0111540902 

PO Box 80263
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የፌዴራል_የዳኝነት_አስተዳደር_ዓዋጅ_ቁጥር_1233_2013.pdf
2.1 MB
Federal Judicial Administration Proclamation 1233/2021 - የፌዴራል የዳኝነት አስተዳደር ዓዋጅ ቁጥር 1233/2013
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
Ethiopian Law School Association ..............loading.
we will update you‼️@lawsocieties
Happening Now
የኢትዮጵያ የሕግ ትምህርት ቤቶች ማህበር ምስረታ ጉባኤ እየተካኸደ ነዉ። በጉባኤዉ የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ላይ ዉይይት ይደረጋል ፤ የኮሚቴ አባላት ይመረጣሉ ፤ የማህበሩ መመስረቻ ጽሑፍ ይጸድቃል ፤ የማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና ኦፊሰሮች ይሰየማሉ።

የዚህ ታሪካዊ ጉባኤ አካል በመሆኔ ክብር ይሰማኛል።
via ደሳለኝ ከበደ
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት የቀረበባትን ክስ አሸነፈች
*********************************
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት “ ICL ((Israel Chemical Limited)” በተባለ የፖታሽ ማዕድን አውጪ ኩባንያ የተመሰረትባትን ክስ ማሸነፏን የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የማዕድን አውጭ ኩባንያው ኢትዮጵያን የ300 ሚሊዮን ዶላር ክስ የመሰረተ ቢሆንም በትናንትናው ዕለት ኢትዮጵያ በአሸናፊነት ተወጥታለች ተብሏል።

ፍርዱን የሰጠው በሄግ ኔዘርላንድ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤት (Permanent Court of Arbitration) ሲሆን ይግባኝ የማይባልበትን ፍርድ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በክርክሩ ሂደት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ተሳታፊ ለነበሩ ሁሉ የማዕድን እና ነዳጅ ሚንስቴር ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ምንጭ : EBC
የማዕድን እና ነዳጅ ሚንስቴር
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
👍1
የኢትዮጵያ ሕግ ትምሕርት ቤቶች ማሕበር ተመሰረተ።
=================================‼️‼️‼️‼️‼️
ማኀበሩ ሕግ በአገር እድገት ላይ የሚኖረውን ሚና በሕግ ትምህርት አማካኝነት ማሳደግና ማጠናከር፣
በሕግ ትምህርት ቤቶች መካከል ትብብር እንዲኖር ማበረታታት እና የሕግ ትምህርትና ስልጠናን በተመለከተ የልምድ ልውውጥ እንዲሁም በተለያዩ ሐሳቦች ላይ ውይይት የሚደረግበት ነጻ መድረክ ሆኖ ማገልገልና
ሕግ በአገር እድገት ላይ የሚኖረውን ሚና በሕግ ትምህርት አማካኝነት ማሳደግና ማጠናከር እና የመሳሰሉት ዓላማዎቹን ይዞ የኢትዮጵያ የሕግ ትምህርት ቤቶች ማኀበር ዛሬ ሐምሌ 03/2013 ዓ/ም አባል ትምህርት ቤቶችና የፍትህ ዘርፉ ባለድሻ አካላት በተገኙበት በሂልተን ሆቴል ተመስርቷል።
አቶ መስፍን....
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
ከሀምሌ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በግል አቤቱታ አቅራቢነት ክስ የሚመሠረትባቸው የወንጀል ጉዳዮች እና በግለሰቦች መካከል የሚደረጉ እስከ ብር 500,000 የገንዘብ፣ ውልና ብድር የፍትሐ ብሄር ጉዳዮች በፌዴራል ፍርድ ቤት መታየታቸው ቀርቶ በአዲስ አበባ ከተማ እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፀደቀው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/ 2013 አንቀፅ 4 (16) ላይ በግል አቤቱታ አቅራቢነት ክስ የሚመሠረትባቸው የወንጀል ጉዳዮች እንዲሁም በአንቀጽ (5) (1) (ደ) መሰረት በግለሰቦች መካከል የሚደረጉ እስከ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺ) ብር ድረስ የገንዘብ፣ ውልና ብድር የፍትሐ ብሄር ጉዳዮች በአዲስ አበባ ከተማ እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች ከሐምሌ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንዲዳኙ ደንግጓል፡፡

በዚህ መሰረት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ በሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እያያቸው የሚገኙ በግል አቤቱታ የሚቀርቡ የወንጀል ጉዳዮች እና በሕጉ የተቀመጡ የፍትሐብሔር ጉዳዮች በተጓዳኝ ለሚገኙ ከአዲስ አበባ እና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤቶች በአዋጁ መሰረት በማስረከብ የስራዎችን በአግባቡ ማከናወን እንዲችሉ በርክክብ ሂደቱ ከእያንዳንዱ ተቋማት የሚጠበቅ ተግባርና ኃላፊነት ለማመላከት እንዲቻል መግባቢያ ሰነድ ተዘጋጅቶ መፈረሙን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፍትሃብሄር እና ልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዘርፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ በረከት ማሞ ገልጸዋል፡፡

ሃላፊው አክለውም በአዋጁ መሰረት በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስከስሱ ወንጀሎች እና እስከ 500,000 ብር የሚያወጡ የፍትሃብሄር ጉዳዮች በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መታየታቸው ቀርቶ ከሀምሌ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሁለቱ የፌዴራል ከተማ አስተዳደር ከተሞች ዐቃብያነ ህግ እንዲመራ በመደንገጉ እና ይህንኑ ለማስተግበርም በሚል በተዘጋጀው የመግባቢያ ሰነድ ወደ ተግባር የሚገባው በፈራሚ ተቋማት ስልጣን በተሰጣቸው አካላት ሲፈረም ስለመሆኑ ሰነዱ የሚያመለክት እና በዚሁም መሰረትም ተቋማቱ የመግባቢያ ሰነዱን ተፈራርመው ርክክቡ የተደረገ በመሆኑ ወደ ትግበራ ይገባል ብለዋል፡፡

በዚህ የመግባቢያ ሰነድ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስቀጡ ወንጀሎችን እና እስከ 500,000 ብር የሚደርሱ የፍትሃብሄር ጉዳዮችን በተመለከተ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሲከውናቸው የነበሩ የወንጀል ምርመራ እና ከሶ የማስቀጣት ስራ እንዲሁም የክርክር እና የድርድር ስራዎችን ለአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ህግ ቢሮዎች በማስተላለፍ ስራዎቹ ከቆሙበት እንዲቀጥሉ አዳዲስ አቤቱታዎች እና ክሶችም ወደነዚሁ የከተማ አስተዳደሮች ዐቃቤ ህግ ቢሮዎች እንዲቀርቡ የሚደረግ ሲሆን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከሐምሌ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከላይ የተጠቀሱት ወንጀሎች እና የፍትሃ ብሄር ጉዳዮችን የማያስተናግድ መሆኑ ታውቆ የፍትህ አገልግሎት ተጠቃሚው ማህበረሰው ጉዳዩን በዚሁ አዋጅ የምርመራ እና ከሶ የማስቀጣት ስራውን እንዲሰራ ስልጣን ለተሰጠው የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ ዐቃቤ ህግ ማቅረብ ያለበት መሆኑን አቶ በረከት ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት የቀረበባትን ክስ አሸነፈች
*********************************
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት “ ICL ((Israel Chemical Limited)” በተባለ የፖታሽ ማዕድን አውጪ ኩባንያ የተመሰረትባትን ክስ ማሸነፏን የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የማዕድን አውጭ ኩባንያው ኢትዮጵያን የ300 ሚሊዮን ዶላር ክስ የመሰረተ ቢሆንም በትናንትናው ዕለት ኢትዮጵያ በአሸናፊነት ተወጥታለች ተብሏል።

ፍርዱን የሰጠው በሄግ ኔዘርላንድ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤት (Permanent Court of Arbitration) ሲሆን ይግባኝ የማይባልበትን ፍርድ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በክርክሩ ሂደት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ተሳታፊ ለነበሩ ሁሉ የማዕድን እና ነዳጅ ሚንስቴር ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ምንጭ : EBC
Job Title: Attorney Job
Location: Addis Ababa
Vacancy Code: EVA-Leg-HQ-03-2021
Employment Type: Permanent Required Education Level: BA Degree in Law (L.L.B) or Level V in Law with COC certification Required Field of Study: Law Vacancy Opening Date: 06-Jul-2021 Vacancy End Date: 15-Jul-2021 General Mission • Under general direction of Corporate legal issues manager, tasks part in the overall activates of legal issues relating to corporate matters; • Provides expert advice to management on any legal affairs • Represents the company before the judicial and other tribunals. • Contributes to cross functional actions to enhance the performance of the company. Key Responsibilities • Conducts research on minor corporate legal issues that require engagement of the management; • Under the supervision of legal specialist or the manager, reviews/evaluates the potential legal issues in policy decisions, procedures and manuals of the company and processes measures that may help in filling the gaps observed in the documents. • Under the supervision of legal specialist or the manager, studies problem and bottlenecks faced by the company in statutory regulations and law, internal regulation or policies. • Prepares legal advice and opinion on subjects that are relatively less complex. • Represents the company before the judicial and other tribunals. • Represents the company in out of court settlement negotiations. • Under the supervision of legal specialist or the manager, conducts researches on subjects that may help to improve the safeguarding of the company’s legal interests and its compliance to its policies as well as national laws. • Perform other related tasks as Instructed by corporate legal issues manager. Does: • Reports to the Corporate legal issues manager for the case management and telecom issues in general case management and other decision making. • Brings to the Corporate legal issue section required information/study/survey for decision making. Application Tips Applicants must have the required educational qualification and experience. Female applicants are strongly encouraged to apply. Only short-listed applicants will be contacted
How to apply?

Read the vacancy announcement carefully.

Check the vacancy details with eligibility.

Prepare your CV or Application Details all document must with transcript grade 8th to collage.

Finally, apply as instructed by the authority.  

Interested applicants should submit their CVs as prescribed in the employment notification. Along with supporting documents (educational) in-person via https://www.ethiotelecom.et/jobs/job-title-court-liaison

Application Tips

Applicants must have the required educational qualification and experience.

Female applicants are strongly encouraged to apply.

Only short-listed applicants will be contacted.

Opening date: 06-JUL-2021

Closing date: – 15-JUL-2021
የ6ኛው አጠቃላይ ምርጫ ውጤት‼️
የ6ኛው አጠቃላይ ምርጫ ውጤት‼️
Legal Service Officer


Gomeju Oil Ethiopia


Position: Legal Service Officer

Job Time: Full-Time

Job Type: Permanent

Place of Work: Addis Ababa, Ethiopia

Posted date: 21 hours ago

Application Deadline: Jul, 20/2021 (8 days left)

Gomeju Oil Ethiopia is a privately owned company established in 2016 GC in Ethiopia. The company joined the Oil industry to contribute its part to the ever-increasing demand for energy in the country with a well-organized team of professionals and excellent work experience in the industry, therefore, the company invites competent and qualified candidates for the following vacant position.

Minimum Qualification:

BA Degree in LLB

Work Experience:

Minimum of 4 years experience out of which 2 years as a legal officer in a trading company

Salary: As per the company salary scale and fringe benefits

Work Place: Addis Ababa

Term of Employment: Permanent

How to apply

Qualified applicants are requested to submit their current CV and copies of testimonials within 10 (Ten) working days from this advertisement.

Email: Hrcv@gomejuoil.com

Address:

Gomeju Oil Ethiopia, Head Quarter around Bole Medhanialem Church

Behind Bole Comprehensive High School

Office Tel: +251 116 50 10 10/ +251 116 39 30 35/ +251 116 39 32 58
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties