አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የሰበር ችሎት 10 የህግ አተረጓጎም ደንቦች
=================
ህግ እንደማንኛውም የስነ ጽሑፍ ስራ ህግ ለማውጣት ስልጣን የተሰጠው አካል የሚጽፈው ድርሰት ነው፡፡ በመርህ ደረጃ ማንበብ የሚችል ዜጋ ሁሉ (በሙያው መመረቅና መሰልጠን ሳያስፈልገው) ይህን ህግ አንብቦ ይረዳዋል ተብሎ ይገመታል፡፡ ይሁን እንጂ የተጻፈ ህግ ከሌሎች ድርሰቶች በእጅጉ የሚለው የራሱ ባህርይ፣ ዘይቤና የአጻጻፍ ስርዓት አለው፡፡ ስለሆነም በሁሉም ዜጋ ይቅርና ህጉን በሚጽፈው፣ በሚያስፈጽመውና በሚተረጉመው አካል ወጥና ተመሳሳይ መረዳት አይኖርም፡፡ የህጉ ቋንቋ የሚፈጥረው የአረዳድ ልዩነት አንድ ቦታ ላይ ሊቋጭ ስለሚገባው አንደኛው የመንግስት አካል የሚሰጠው ትርጉም ባልተግባቡት ወገኖች መካከል አሳሪ ይሆን ዘንድ ፍርድ ቤት ህጋዊና ህገ-መንግስታዊ ዕውቅናና ብቃት ያለው ተቋም ሆኖ ተቋቁሟል፡፡

ፍርድ ቤትም ቢሆን ግን አንድ ምላስ እንጂ አንድ ራስ የለውም፡፡ አንዲት ድንጋጌ በፌደራልና በክልል፣ በበላይና በበታች ፍ/ቤቶች ብሎም በውስጣቸው በሚገኙት ችሎቶች የተለያየ አንዳንዴም የተራራቀ መልዕክት ታስተላልፋለች፡፡ ሁልጊዜ ይህን መሰሉ አለመናበብ ባይኖርም ክስተቱ አይቀሬ ነው፡፡ አይቀሬነቱ የሚመነጨው ከአንባቢው (ዳኛው) ስህተትና ግድፈት ብቻ አይደለም፤ ከተነባቢው (ከተጻፈው ህግ) ልዩና ውስብስብ ባህርያት ጭምር እንጂ፡፡

የአገራችን የመጨረሻ፤ የበላይ ህግ ተርጓሚ የሆነው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሚና በእያንዳንዱ በቀረበለት መዝገብ ላይ ህጉ ምን እንደሚል ትርጉም መስጠት ብቻ አይደለም። ከዚህ ባለፈ የስር ፍርድ ቤቶች ምን ዓይነት የህግ አተረጓጎም ስልት መከተል እንዳለባቸው ጭምር መመሪያ መስጠት ይጠበቅበታል። ይሄ ደግሞ ወጥነት ከማስፈኑ በላይ የችሎቱን ስራ በእጅጉ ያቀልለታል። ለምሳሌ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ለእያንዳንዱ ድንጋጌ ትርጉም ከመስጠት ባለፈ የስር ፍር ቤቶች ህጉን በምን ዓይነት የአተረጓጎም ስልት መተርጎም እንዳለባቸው አቅጣጭ ቢያስቀምጥ መሰረታዊ የህግ ስህተቶች ቁጥራቸው ይቀንሳል። በተለይ የህግ አተረጓጎም ስልትን የሚገዛ ዝርዝር ህግ በሌለበት /ከተወሰኑት ድንጋጌዎች በቀር/ በአገራችን የስር ፍርድ ቤቶች መከተል ስላለባቸው የህግ አተረጓጎም ስልት ግልጽ አቅጣጫ ማስቀመጥ ችሎት ዋነኛ ሚናው አድርጎ መውሰድ ይኖርበታል።
እስካሁን በሰበር ችሎት በተሰጡ ውሳኔዎች የህግ አተረጓጎም ስልትን በተመለከተ ጎልቶ የሚታይ ባናገኝም በተወሰኑ ውሳኔዎች ችሎቱ የተጠቀማቸው ስልቶች ጠቅለል ባለ አነጋገርም ቢሆን ተገልጸዋል። ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ተጨማሪ ማብራሪያ ሳይታከልባቸው በውሳኔዎቹ ላይ እንደተጠቀሱ እንደሚከተለው ቀርበዋል።

1/ ማራባት

ሰ/መ/ቁ. 79476 ቅጽ 18
ከድንጋጌው ውስጥ “...የሌሎችም ክፍያዎች..” ወይም “.. 0thher payments ~ የሚለው ሐረግ ጠቅላላ ቃል መሆኑ ግልጽ ሲሆን እንዲህ በሆነ ጊዜ ቃሉን ሕግ አውጪው የተጠቀመው ምንን ለማመላከት ነው? የሚለውን ጥያቄ ማንሣቱ ተገቢ ሲሆን የሕግ አተረጓጎም መርሆዎችን መሠረት በማድረግም ምላሹን ማግኘት ይቻላል፡፡ በዚህም መሠረት ከጠቅላላው ቃል በፊት የተዘረዘሩት የቃላት ዝርያ የሚያሣዩትን ሁኔታ በመመልከት ጠቅላላ ቃል ሌሎች ያልተዘረዘሩትን ተመሣሣይ ዝርያ ያላቸውን ቃላት ለመጠቀም ታስቦ የተቀመጠ ነው በሚል እንደሚተረጎም ተቀባይነት ያላቸው የሕግ አተረጓጎም መርሆዎች ያስገነዝባሉ፡፡

2/ ጥብቅ የሕግ አተረጓጐም መርህ

ሰ/መ/ቁ. 98263 ቅጽ 17
በፍርድ ውሳኔ የተሰጠበት ጉዳይ አፈፃፀም ለማስቀረት የፍርድ ባለመብት እና የፍርድ ባለዕዳ የሚያደርጉት የዕርቅ ውል፣ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 276 እና በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 277/1/ የተደነገገውን ጥብቅ መስፈርት የሚያሟላ ባልሆነበት ጊዜ፣ ህጋዊ ውጤትና ተፈፃሚነት እንደማይኖረው የሚያረጋግጥ፣ ጥብቅ የሆነ የሕግ አተረጓጐም መርህ መከተል የፍርድ አፈፃፀም ስርዓቱን ውጤታማና ቀልጣፋ በሆነ ሁኔታ እንዲከናወን ለማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

3/ የቃል በቃል ንባብ /የተናጠል ንባብ/

ሰ/መ/ቁ. 57632 ቅጽ 12
የ2 ዳኞች የልዩነት ሀሳብ
ከላይ ከደረስንበት መደምደሚያ ላይ ለመድረስ ከዚህ በፊት ከላይ ከገለፅናቸው ምክንያቶች በተጨማሪ የአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 9 አቀራረፅ እና የቃል በቃል ንባብ መገናዘብ አለበት የሚል እምነት አለን፡፡

ሰ/መ/ቁ 101271 ቅጽ 16
የአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረታዊ ባህሪና ዓላማ እንደዚሁም ድንጋጌው በአካዳሚክ ሰራተኞች የይግባኝ መብት ላይ የሚኖረውን ሕጋዊ ውጤት ለመረዳት የድንጋጌውን የተናጠል የቃል በቃል ንባብ ማየት ብቻዉን በቂ አይደለም፡፡

4/ ዓላማ

ሰ/መ/ቁ. 93137 ቅጽ 15
የፍ.ስ.ስ.ሕ.ቁ. 6 ዓይነተኛ ዓላማ ተገቢ ሁኔታዎችና ፍሬ ነገሮች ተሟልተው መገኘታቸው ሲረጋገጥ በሀሰተኛ ማስረጃ፣ በመደለያና በመሰል ወንጀል ጠቀስ ድርጊቶች ምክንያት የተዛነፈውን ፍትሕ ወደነበረበት መመለስ ነው፡፡

5/ ተቃራኒ ንባብ

የሰ/መ/ቁጥር 46386 ቅጽ 13
በወንጀል ጉዳይ የተሰጠ ውሣኔ በዚያው ጉዳይ በፍታብሔር በማስረጃነት አግባብነት እና ብቃት የሚኖረው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2149 ተቃራኒው ንባብ ያስገነዝበናል።

6/ ግልባጭ ንባብ

ሰ/መ/ቁ. 49635 ቅጽ 12

በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2278 እንደተመለከተው የተሸጠን ነገር የተረከበ ገዥ የሽያጩን ዋጋ ወዲያውኑ የመክፈል ግዳታ ያለበት በመሆኑና የሽያጩ ዋጋ ያልተከፈለውው ሻጭ የተሸጠውን ነገር ሳያስረክብ በእጁ የማቆየት መብት የሚሰጠው ለመሆኑ የዚሁ ድንጋጌ ግልባጭ ንባብ ስለሚያስረዳ…

7/የተቃርኖ ንባብ

ሰ/መ/ቁ. 54129 ቅጽ 11
የአስተዳደር መስሪያ ቤት መብቱን የሚጠይቀውም ሆነ ግዴታውን የሚወጣው ለሥራ ተቋራጩ ሲሆን የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ግንኙነት ከሥራ ተቋራጩ ጋር ብቻ የሚወሰን መሆኑን ከፍታብሔር ህግ ቁጥር 3205 እና ከፍታብሔር ህግ ቁጥር 3206 የተቃርኖ ንባብና ትርጉም ‛Acontrario reading and Interpretation‛ ለመገንዘብ ይቻላል፡፡

8/ ጥምር /ጣምራ/ ንባብ

ሰ/መ/ቁ. 86398 ቅጽ 17

የመቃወም አቤቱታው እና የማስረጃው ቅጂ የመቃወም ተጠሪ ለሆነው ወገን እንዲደርስ መደረግ የሚገባው መሆኑን ከመግለጽ በስተቀር የመቃወም ተጠሪው የጽሁፍ መልስ እና የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚገባው በእነዚህ ድንጋጌዎች ላይ በግልጽ የተጻፈ ባይሆንም የመቃወም ተጠሪ የሆነው ወገን በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 234 ድንጋጌ መሰረት ለቀረበበት የመቃወም አቤቱታ ያለውን የመከላከያ መልስ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚገባው ስለመሆኑ ከቁጥር 360(1) እና (2) ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል፡፡

9/ አውድ ንባብ

ሰ/መ/ቁ. 67280 ቅጽ 11
ሕግ አውጪው የትምህርት ዝግጅትንና የሥራ ልምድን ለያይቶ እኩል ዋጋ በአንድ አንቀፅ ከሰጠ በኋላ በተከታዩ ድንጋጌ ተመሣሣይ መንፈስ ያለው አንቀፅ ያስቀምጣል ማለት ትርጉም አልባ ከመሆኑም በላይ የሕጎችን አውድ ንባብ (contextual interpretation) ትርጓሜ ያልተከተለ፤ አዋጁ ውጤት እንዲኖረውና በአዎንታዊ መንገድ ታይቶ ሥራ ሊይ እንዲውል ለማድረግ የሚያስችል የአተረጓጎም መንገድ ሆኖ አይገኝም፡፡

10/ ጠቅላላ እና ልዩ ህግ
ሰ/መ/ቁ. 39803 ቅጽ 8
ይሁንና የማይንቀሳቀስ ንብረትን ስጦታ በተመለከተ በተለይ በሚገዛው ከፍ ብሎ በተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2443 እና 881 ዴንጋጌ መሠረት ይህ ሥርዓት መከናወን እንዳለበት አልተመለከተም፡፡ በጠቅላላ ሕግና በልዩ ሕግ መካከል አለመጣጣም ወይንም ልዩነት በሚኖርበት ጊዜ ልዩ ሕግ የበላይ ሆኖ ተፈፃሚነት ሊኖረው እንደሚችል /The Special prevail over the general/ ከሕግ አተረጓጎም መርህ መገንዘብ ይቻላል፡፡

ሰ/መ/ቁ. 24703 ቅጽ 7
የግራ ቀኙን ግንኙነት በተለይ የሚገዛው ልዩ ሕግ የሆነው የንግድ ሕጉ ስለሆነና በጠቅላላ ሕግና በልዩ ሕግ መካከል አለመጣጣም በሚኖርበት ጊዜ ልዩ ሕግ የበላይነት እንደሚኖረው /The special prevails over the general/ ከሕግ አተረጓጐም መርህ መገንዘብ የሚቻል እንደመሆኑ......
By Abraham Yohannes
https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties
👏1
የ2013 አመት የመውጫ ፈተና
Exit Exam
https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties
Forwarded from Arey Bin
ሰላም እንዴት ናችሁ!!!!!
.
.
የ2013 አም የመውጫ ፈተና ተፈታኞችን በተመለከተ.....
.
.
እምደሚታወቀው የመውጫ ፈተናው የሚሰጠው ቀድሞ በተያዘለት ከሃምሌ 27-30 ድረስ ነው የሚል ነው፡፡ነገር ግን አገር አቀፍ ህብረቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ከባለድርሻ አካላትጋ ለመነጋገርና ለመመካከር ያመቸው ዘንድ የሁሉንም ዩንቨርስቲ ያሉበትን አቋምና ዝግጁነት መፈተሽም ማወቅም ይፈልጋል ፡፡በዚህ አጋጣሚ የፊታችን አርብ ጀምሮ ኮንሰርቲየሙ ልዩ ስብሰባውን ያደርጋል፡፡በዚህ ጉዳይላይም አጅንዳ ይዞ እንደሚነጋገርና ውሳኔ እምደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡ይሁን እንጅ የህብረቱ ስራ አስፈፃሚ በስብሰባው ላይ ተሳታፊ ሆኖ ስለሚቀርብ የፈተናውን አሰጣጥና የተማሪውን ዝግጁነት በተጨባጭ በማንሳት ኮንሰርቲየሙ ውሳኔውን ድጋሜ እንዲያየው ማድረግ ይችላል፡፡በርግጥ የተማራዎን ዝግጅት በተመለከተ የዩንቨርስቲ ዲኖች ስለሚገኙ ሊናገሩትና ሊገልፁት ይችላሉ ሆኖም እንደ ህብረትና እንደተማሪ ውክልና ደግሞ ሃሳቡን ማቅረቡ አስላጊ ነው፡፡
.
.
እንደ አርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ የተማሪው ዝግጅት ከሌሎች አንፃር ሲታይ መልካም የሚባል እንደሆነ በነበረን ግምገማ ማረጋገጥ የቻልን ሲሆን ቢራዘም፡ግን የተሻለ እንደሆነ እናምናለን፡፡
.
.
እስኪ የሌሎች ዩንቨርስቲዎች ያላችሁበትን አቋም በተወካዮቻችሁ(በህብረቱ/በማህበራችሁ) አማካኝተንት በውስጥ መስመር አድርሱንና ሃሳቡን አጠቃለን በስብሰባው ላይ ለማንሳት እንሞክራለን፡፡
.
.
አህመድ.M(ከአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ)
የኢ/ህ/ተ/ህ ስራ አስፈፃሚ
#Job opportunities � �

Title : የጠበቃ ረዳት
Type : Part - Time
Place of work : Addis Ababa
Education Background : Law

#Responsibilities
� Preparing various legal documents
� Following Court cases
� Legal Research

Send your application and #CV
on Email � lawyer@samuelgirma.com
Job Vacancy for Attorney @ Ethio Telecom
********************
Ethio Telecom has advertised a number of vacant attorney positions at its head quarter.
(Eductn: LL.B.) (Experience: 2 years) (Nature of emplymnt: permanent)

Application is done online! Follow the link below to see the particulars and to apply for the position

Share it with friends!
@Manaye Abera
https://www.ethiotelecom.et/jobs/job-title-attorney/
Forwarded from Deleted Account
እንደሚታወቀው የዘንድሮ የትምህርት ዘመን እጅግ የተጣበበ ነበር። የአምስተኛ አመት ትምህርትን ብቻ ሳይሆን የ4ኛ አመት ሁለተኛ ሴሚስተርን ትምህርትን ጭምር ተምረናል። በዚህም ምክንያት ጊዜው ለመውጫ ፈተና ለመዘጋጀት በቂና የተመቸ አልነበረም። የsenior Thesis reaserch titile እንኳን እስገብተን መስራት ከጀመርን አንድ ወር አይሆንም። ስለዚህም የፈተናው ጊዜ በተወሰነ ቢራዘም መልካም ነው።
ተማሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ።
Forwarded from Merge Dare
የለው ዝግጅት ምንም በቂ አይደለም ለዚ ደግሞ የነበረው የ covid 19 እና ተዛማች ውጤቶች የ 5ኛ Year schedule መቃወስ, መደራረብ, ማነስ እና ለ load ዳርጐታል ስለዚ ተረጋግተን ለ Exit እንድናነብ እና ቢያንስ የተረጋጋ የ ፈተና ሞራል እንዲኖረን ግዜ ያስፈልገናል 100% ፤ postponed መሆን አለበት ። በተቻለ መጣን ድምጽ ሁኑን ባይ ነን !
#ተማሪ ከመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ
Forwarded from Solomon Shumetu
እንደት ናችሁ?

የመዉጫ ፈተና ጊዜን በተመለከተ የሚደረጉት የሀሳብ ልዉዉጦችን በተመለከተ፥ እርግጠኛ የሆኑ መረጃዎችን ብቻ ጉዳዩ ላይ የመወሰን ስልጣኑ ካላቸው ሰዎች እየተቀበላችሁ ብታጋሩ መልካም ነው። በጎን ፈተናው አልተራዘመም የሚል የኤጀንሲው ህጋዊ ደብዳቤ፥ በጎን ደግሞ ሊራዘም ስለሚችል ሃሳባችሁን አጋሩን የሚል መልዕክት ትንሽ ግራ ያጋባል።
======
ግራ ከማጋባት በዘለለ ደግሞ እውነት ኤጀንሲው ስብሰባው ከቀናት በኋላ ከሆነ "ምን ይወስናል? ያራዝመዋል? በሚል ሀሳብ ዉሳኔ እስከሚሰጥበት ቀን ያለውን ጊዜ ያለ ምንባብ በሃሳብ ማሰላሰል ብቻ ይባክናል።
======
ካረዘመውም እሰየው! ነገር ግን የማይራዘምበት ሁኔታም ሊኖር ስለሚችል ይህችኑ ያለችውን ጊዜ በአግባቡ መጠቀሙ አይከፋም። ገና ከ10 ቀን በኋላ የሚወሰን ዉሳኔ በመጠበቅ ንባባችን እንዳይስተጓጎል በመስጋት ነው። ስለዚህ ከዚህ ቻናል የሚጠበቀው ዝግጅታችሁ ምን ይመስላል የሚለውን ጉዳይ ብቻ እየጠየቀ ፈተናው ግን በተያዘለት መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ደጋግሞ መለጠፍ ተገቢና ኃላፊነት ያለው ተግባር ይመስለኛል።
Forwarded from Arey Bin
ሶል ልክ ብለሃል፡፡ትላንት የተለጠፈው ደብዳቤ በእጅጉ አወዛግቦናል፡፡የመራዘሙ ጉዳይና አጀንዳ ግን ተማሪውን ከጥናቱ የሚያስተጓጉል አይደለም መሆንም የለበትም፡፡እምድራዘም የሚጠይቁ አካላትኮ የጊዜ እጥረት በመኖሩ ለፈተናው ብቁ ሆኖ ያለመገኘት ስለሚያስከትል ለመዘጋጀት እንድመች እንጅ ለቅንጦት አይደለም፡፡እናም አጀንዳው የበለጠ የሚያጠነክር እንጅ የሚረብሽ ነው ብዬ አላምንም፡፡በሌላ መልኩ ግን የኮንሰርቲየሙ ስብሰባ የሚካሄደው ከነገ አርብ ጀምሮ እንደሁ በኮንሰርቲየሙ ፀሃፊ በኩል እርገጠኛ መረጃ አለን ግን የተለቀቀው ደብዳቤ ምናልባትም በባለፈው በተወሰነው የፈተና ጊዜ ተመስርቶ የተፃፈ ይመስለኛል፡፡ከዚህ ውጪ ግን ተማሪው ራሱን ሊያዘጋጅ ይገባል፡፡መራዘሙ የበለጠ ጊዜውን እምድጠቀምና እንዲረጋጋ ካልሆነ እንጅ ለመዳከሙ ሰበብ ሊሆን አይገባም፡፡በመራዘሙና ባለመራዘሙ ደግሞ ማንም ቢሆን ሃላፊነት የለበትም ህብረቱም ቢሆን ግን የነገሮችንና ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ ወጥ የሆነ የፈተና አሰጣጥ እንድኖርና ሁሉም የህግ ተማሪ ጥቅም የሚከበር እንድሆን የመስራት ግን የህብረቱ ሃላፊነት ነው፡፡
.
.
መልካም ቀን!!!!!!!!
ደሀ ደንብ/ዳኝነት ሳይከፈል፣ በነፃ መዝገብ ማስከፈት/
======================
ክስ ለማቅረብ የፈለገ ወገን ከፍርዱ ለሚያገኘው የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችል የገንዘብ አቅም የሌለው ከሆነ ክሱን ያለዳኝነት ገንዘብ በደሀ ደንብ መሠረት የማቅረብ መብት እንዳለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 215 ተደንግጓል፡፡ ክሱን የሚያቀርበው ወገን ድሀ በመሆኑ ምክንያት የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍል ክሱን አቅርቦ እንዲያሰማ ሊፈቅድለት ይገባል? የሚለው ጉዳይ ሊለይ የሚችልበት ዝርዝር አፈፃፀም ደንቡም ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 እና ተከታዩ ድንጋጌዎች ተመልክቷል፡፡ እነዚህ ደንቦች ተፈፃሚነታቸው ክስ ለማቅረብ በፈለገ የተፈጥሮ ሰውም ሆነ በሕግ ሰውነት ያላቸው ወገኖችም ጭምር ነው፡፡
በዚህም መሠረት ድሀ ነኝ፤ መብቴን ለማስከበር ያለኝ ፍላጐቴ በዳኝነት ገንዘብ እንቅፋት ምክንያት ሊሰናከል አይገባም፡፡ ስለሆነም በድሀ ደንብ መሠረት ክሱን በነፃ እንዳሰማ ይፈቀድልኝ የሚል ማናቸውም ከሳሽ ድሀ መሆኑን ሊያመለክት የሚችል የሚገኝበትን የገንዘብ አቋም ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡ ይህም ከሳሹ የሚገኝበት የገንዘብ አቋም ከተረጋገጠ በኋላ ለክሱ ሊከፈል የሚገባው የዳኝነት ገንዘብ መጠን ከሳሹ ከሚገኝበት የገንዘብ አቋም አኳያ ተገናዝቦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 መሠረት ድሀ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ሊለይ ይገባል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 79555 ቅጽ 14፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215፣ 467
አንድ ሰው በፍርድ ሊያልቅ የሚገባው ጉዳይን ፍርድ ቤት ይዞ ሲቀርብ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ መክፈል ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 215፣ ከ467 እስከ 479 ድረስ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ያሳያሉ፡፡ የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የማይችል ሰው ክስ ለማቅረብ የሚችልበት አግባብ ስለመኖሩም ተጠቃሽ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ፡፡ አንድ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለመክፈል የማይችል ሰው በደሃ ደንብ ክስ ለማቅረብ የሚችል ሲሆን ለመክፈል አቅም እያለው ክስ ያቀረበ መሆኑ ከተረጋገጠ ግን መዝገቡ እንደሚዘጋ፣ የተዘጋ መዝገብ ደግሞ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ /ገንዘቡን/ ለመክፈል ዝግጁ እስከሆነ ድረስ የሚንቀሳቀስለት መሆኑን የሥነ ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች መንፈስና ይዘት ያስገነዝባሉ፡፡
ሰ/መ/ቁ. 52942 ቅጽ 12፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215፣ 467-479
ይግባኝ ዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ለመክሰስ እንዲፈቀድ በቀረበ ጥያቄ ላይ ሊሰጥ የሚችለው ትእዛዝ እንደነገሩ ሁኔታ ሁለት ዓይነት ነው፡፡ አንደኛው ከሣሽ የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችለው የገንዘብ አቅም የሌለው ስለሆነ እንደ ጥያቄው የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍል በነፃ ፋይል ከፍቶ ክሱን ለማቅረብ ይችላል የሚለው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ከሣሹ ድሃ ያለመሆኑ ስለተረጋገጠ ተገቢውን የዳኝነት ገንዘብ ካልከፈለ በቀር በነፃ ፋይል ከፍቶ ክሱን ለማቅረብ አይችልም የሚለው ነው፡፡
በመጀመሪያው አኳኋን ትእዛዝ በተሰጠ ጊዜ በዚህ ትእዛዝ መሠረት ፋይሉ ተከፍቶ ክርክሩ የሚቀጥል ነው፡፡ የክርክሩ ውጤት የሚታወቀው ግራ ቀኙ በሚያቀርቡት የፍሬ ነገርና የሕግ ክርክር ማስረጃ መሠረት ነው፡፡ በመጨረሻው የክርክር ውጤት ተከሣሹ ባይስማማ ክርክሩ ከመጀመሩ በፊት ክሱ ዳኝነት ሳይከፈልበት በነፃ እንዲከፈት መደረጉ የሕግ ድጋፍ አልነበረውም የሚለውን እንደ አንድ የይግባኝ ምክንያት በማድረግ በውሣኔው ላይ ካለው ቅሬታ ጋር አዳምሮ ማቅረብ ይኖርበታል እንጂ ከሥረ-ነገሩ ፍርድ በፊት የይግባኝ አቤቱታ የማቅረብ መብት አይኖረውም፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 320/3/ የተመለከተው ድንጋጌም በዚህ አኳኋን በሚቀርበው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ክልከላ ለማድረግ ነው፡፡
በሌላ በኩል ድሀ ያለመሆንህ ተረጋግጧል፡፡ የዳኝነት ገንዘብ ካልከፈልክ በቀር ፋይል አይከፈትም ለተባለው ከሣሽ ግን ይህ ዓይነቱ ትእዛዝ የመጨረሻ ነው፡፡ ሌላ የሚጠበቅ የሥረ-ነገር ፍርድ የለውም፡፡ ስለሆነም የዳኝት ገንዘብ ለመክፈል አቅም ሳይኖረኝ ክርክሬና ማስረጃዬ በአግባቡ ሳይታይ አቅም እንዳለኝ ተቆጥሮ የዳኝነት ገንዘብ ክፈል መባሌ ተገቢ አይደለም የሚል ከሆነ የተሰጠው ትእዛዝ የመጨረሻ እንደመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 320/1/ መሠረት የይግባኝ አቤትታ የማቅረብ መብት አለው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 23744 ቅጽ 6፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 320
https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties
Forwarded from Hailegiorgis Tefera
የመውጫ ፈተና 2013 እንደሚታወቀው የዘንድሮው አመት ከሌሎቹ ትንሽ ከባድ ይመስላል የተማሪዎች ዘግይቶ መጠራትና የትምህርት መደራረብ በሁሉም ዪኒቨርስቲዎች አለ ማለት ይቻላል . ተፈታታኝ ተማሪዎችም በቂ ዝግጅት አላቸው ለማለት ይከብዳል በአሁን ሰአትም አብዛኞቹ ተማሪዎች apparent እና ሪሰርች በመስራት ላይ ይገኛሉ ጥቂት ግቢዎች ናቸው ቶሎ የጨረሱት እናም በበቂ ሁኔታ ተማሪዎች ተዘጋጅተን ለማለፍ ብሎም ጥሩ ውጤት ለማምጣት ጊዜ ያስፈልጋል ባይ ነኝ ይህ ደግሞ የኔ ሀሳብ ብቻ አይደለም አብዛኛው ተማሪ ቢራዘም የሚፈልግ ነው ምናልባት እስካሁን የጨረሱና ያነበቡ ተማሪዎች ቢራዘምም የሚጎዱ አይመስለኝም ... በመሆኑም ቢራዘም መልካም ነው እንደ አብዛኛው ተማሪዎች ሀሳብ ... እናንተም የቻላችሁትን ብታረጉ ..
Forwarded from Solomon Shumetu
ደገፍኩትም አልደገፍኩትም፥ የመራዘሙ ሃሳብ የሚቀርብበት ምክንያት ትክክል እንደሆነ እስማማለሁ። ነገር ግን የሚራዘም ከሆነ ከነሀሴ 20 በኋላ ሊሆን እንደሚችል ካሉት ልምዶች ቅድመ ግምት መዉሰድ ይቻላል። ምክንያቱም በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አማኞች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የፍልሰታ ጾም ነሀሴ 1 ይጀመርና ነሀሴ 16 ትንሳኤ ይሆናል። በጾም ሰዓት ደግሞ እንኳን ይህን ትልቅ ፈተና የምስለ ፍርድ ቤት ዉድድሮች እንኳን እንዳይካሄዱ ትልቅ ጥረት ይደረጋል።
========
ይህ ሲሆን ደግሞ አዲስ አመትን ከቤት ዉጭ ማሳለፍ ሊከሰት ይችላል። ይህን ላለማድረግ ሲባል ደግሞ ወደ መስከረም ሊሄድም ይችላል። በዚህ ሂደት ዉስጥ ያሉትን ነጥቦች በግሌ ማገናዘብ ያሻል ባይ ነኝ።
በሀሰተኛ ማስረጃ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደባቸው ግለሰብ ከእስር ነፃ ተለቀቁ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሀሰተኛ ማስረጃ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደባቸው ግለሰብ በልዮ ሁኔታ ያለ ቅድመ ሁኔታ ከእስር ነፃ መውጣታቸውን የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት አስታወቀ።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዓለምሸት ምህረቴ ÷በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላ ድንጋይ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ግለሰብ ከአምስት ዓመት በፊት በእንጀራ እናቷ ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ ተገድላለች በሚል ግለሰቧ መሞቷ በሃሰተኛ ማስረጃ ተረጋግጦ ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ተጥሎባቸው ነበር።

ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ የእንጀራ ልጇን ገድላለች በሚል የሰሜን ሸዋ ዞን ዐቃቤ ሕግ የወንጀል መዝገብ ቁጥር 134/2008 ክስ መስርቶባቸው ሲከራከሩ መቆየታቸውን ተገልጿል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የቀረበውን ክስና ማስረጃ በመመርመር ጥፋተኛ ናቸው ብሎ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እና በአምስት ዓመት ከማንኛውም ማህበራዊ ግንኙነት እንዲገለሉ ውሳኔ አስተላልፎ እንደነበር ገልጸዋል።

በተሠጠው ውሳኔ መሠረትም ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ አምስት ዓመት በደብረብርሃን ማረሚያ ቤት በእስር መቆየታቸው ተገልጿል።

ነገር ግን ሞተች ተብላ በሀሰተኛ ማስረጃ የተረጋገጠላት ግለሰብ ከሌላ አካባቢ በሕይወት ቆይታ በቅርብ ጊዜ ወደ ትውልድ አካባቢዋ በመምጣቷ ሞተች ተብላ ጥፋተኛ ያልሆነችን ግለሰብ እንደ ጥፋተኛ ቆጥሮ ማረሚያ ቤት እንድትወርድ ያደረገችው ግለሰብ ማንነቷ በአካባቢው ህብረተሰብ እና በማስረጃ ተረጋግጧል ብለዋል።

በዚህም በሃሰተኛ ማስረጃ ተፈርዶባቸው በእስር የቆዩት ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ በአማራ ክልል የተሻሻለው የይቅርታ አሰጣጥ መወሰኛ መመሪያ ቁጥር 30/2010 መሠረት ጉዳያቸው ለአማራ ክልል ይቅርታ ቦርድ ቀርቦ የክልሉ ምክር ቤት በ29 ቀን 2013ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ወ/ሮ አዛለች ቤተምንዳ በልዮ ሁኔታ ያለ ቅድመ ሁኔታ ከእስር ነፃ እንዲወጡ እና የተጣለባቸው ገደብ እንዲነሳላቸው ወስኗል።

የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው በወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ ላይ የገጠመው ጉዳይ ያለ ማስረጃ የሚታሰሩ ታራሚዎች በሞራል፣በኢኮኖሚ፣በማሕበራዊ፣በ ቤተሰብ ላይ የሚደርስባቸውን ጉዳት ካሳ የሚካሱበት የሕግ ማዕቀፍ የሌሎች አገሮችን ልምድ በመቀመር ማዘጋጀት እንደሚገባ አስተማሪ ሆኖ አልፏል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Source :-FBC
Forwarded from Dinaol Debele
ሰላም እንዴት ናችሁ ?
ተማሪ ዲናኦል ደበሌ እባላለሁ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ነኝ።
በ exit ጉዳይ ላይ የምሰጠዉ ሀሳብ ቢኖር እንደኛ ግቢ ዝግጅታችን ከ100% ቢሰላ 0% ነዉ። ምክንያቱ ደግሞ ወደ ግቢ የገባነዉ ጥር 27 ነዉ። ከገባን ቧኻላም እስከ የካቲት 9 ድረስ የ 4ኛ አመት 1ኛ ሴሚስተር ፈተና ስንወስድ ነበር። የ 5ኛ አመት ኮርስ ከጨረሰን ገና 2 ሳምንታትን ማስቆጠራችን ነው።externship ላይ እያለን ነዉ እሄንን ዜና የሰማነው። ዉሳኔው በተማሪዎች ዘንድ ያልተጠበቀ ነገር እና መደናገጥን አስከትሎባቸዋል። ስለሆነም ዉሳኔዉ እንደ አዲስ ቢታይ እና ቀን ቢጨመር እላለሁ
Forwarded from Deleted Account
እኔ በበኩሌ የፈተና ግዜ ብራዘም ባይ ነን። ምክንያቱም በ2013 የትምህርት ዘመን ሁላችንም እንደ ሀገር ያሳለፍነው በብዙ መጨናነቅነና ውጥረት ውሰጥ ነው። አሁንም ቢሆን አብዛኞቻችን በExternshipና Research ላይ ነን። መራዘሙን 100% እደግፋለሁ። Getahun from Wachemo University.