አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Forwarded from Deleted Account
እንደሚታወቀው የዘንድሮ የትምህርት ዘመን እጅግ የተጣበበ ነበር። የአምስተኛ አመት ትምህርትን ብቻ ሳይሆን የ4ኛ አመት ሁለተኛ ሴሚስተርን ትምህርትን ጭምር ተምረናል። በዚህም ምክንያት ጊዜው ለመውጫ ፈተና ለመዘጋጀት በቂና የተመቸ አልነበረም። የsenior Thesis reaserch titile እንኳን እስገብተን መስራት ከጀመርን አንድ ወር አይሆንም። ስለዚህም የፈተናው ጊዜ በተወሰነ ቢራዘም መልካም ነው።
ተማሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ።
Forwarded from Merge Dare
የለው ዝግጅት ምንም በቂ አይደለም ለዚ ደግሞ የነበረው የ covid 19 እና ተዛማች ውጤቶች የ 5ኛ Year schedule መቃወስ, መደራረብ, ማነስ እና ለ load ዳርጐታል ስለዚ ተረጋግተን ለ Exit እንድናነብ እና ቢያንስ የተረጋጋ የ ፈተና ሞራል እንዲኖረን ግዜ ያስፈልገናል 100% ፤ postponed መሆን አለበት ። በተቻለ መጣን ድምጽ ሁኑን ባይ ነን !
#ተማሪ ከመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ
Forwarded from Solomon Shumetu
እንደት ናችሁ?

የመዉጫ ፈተና ጊዜን በተመለከተ የሚደረጉት የሀሳብ ልዉዉጦችን በተመለከተ፥ እርግጠኛ የሆኑ መረጃዎችን ብቻ ጉዳዩ ላይ የመወሰን ስልጣኑ ካላቸው ሰዎች እየተቀበላችሁ ብታጋሩ መልካም ነው። በጎን ፈተናው አልተራዘመም የሚል የኤጀንሲው ህጋዊ ደብዳቤ፥ በጎን ደግሞ ሊራዘም ስለሚችል ሃሳባችሁን አጋሩን የሚል መልዕክት ትንሽ ግራ ያጋባል።
======
ግራ ከማጋባት በዘለለ ደግሞ እውነት ኤጀንሲው ስብሰባው ከቀናት በኋላ ከሆነ "ምን ይወስናል? ያራዝመዋል? በሚል ሀሳብ ዉሳኔ እስከሚሰጥበት ቀን ያለውን ጊዜ ያለ ምንባብ በሃሳብ ማሰላሰል ብቻ ይባክናል።
======
ካረዘመውም እሰየው! ነገር ግን የማይራዘምበት ሁኔታም ሊኖር ስለሚችል ይህችኑ ያለችውን ጊዜ በአግባቡ መጠቀሙ አይከፋም። ገና ከ10 ቀን በኋላ የሚወሰን ዉሳኔ በመጠበቅ ንባባችን እንዳይስተጓጎል በመስጋት ነው። ስለዚህ ከዚህ ቻናል የሚጠበቀው ዝግጅታችሁ ምን ይመስላል የሚለውን ጉዳይ ብቻ እየጠየቀ ፈተናው ግን በተያዘለት መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ደጋግሞ መለጠፍ ተገቢና ኃላፊነት ያለው ተግባር ይመስለኛል።
Forwarded from Arey Bin
ሶል ልክ ብለሃል፡፡ትላንት የተለጠፈው ደብዳቤ በእጅጉ አወዛግቦናል፡፡የመራዘሙ ጉዳይና አጀንዳ ግን ተማሪውን ከጥናቱ የሚያስተጓጉል አይደለም መሆንም የለበትም፡፡እምድራዘም የሚጠይቁ አካላትኮ የጊዜ እጥረት በመኖሩ ለፈተናው ብቁ ሆኖ ያለመገኘት ስለሚያስከትል ለመዘጋጀት እንድመች እንጅ ለቅንጦት አይደለም፡፡እናም አጀንዳው የበለጠ የሚያጠነክር እንጅ የሚረብሽ ነው ብዬ አላምንም፡፡በሌላ መልኩ ግን የኮንሰርቲየሙ ስብሰባ የሚካሄደው ከነገ አርብ ጀምሮ እንደሁ በኮንሰርቲየሙ ፀሃፊ በኩል እርገጠኛ መረጃ አለን ግን የተለቀቀው ደብዳቤ ምናልባትም በባለፈው በተወሰነው የፈተና ጊዜ ተመስርቶ የተፃፈ ይመስለኛል፡፡ከዚህ ውጪ ግን ተማሪው ራሱን ሊያዘጋጅ ይገባል፡፡መራዘሙ የበለጠ ጊዜውን እምድጠቀምና እንዲረጋጋ ካልሆነ እንጅ ለመዳከሙ ሰበብ ሊሆን አይገባም፡፡በመራዘሙና ባለመራዘሙ ደግሞ ማንም ቢሆን ሃላፊነት የለበትም ህብረቱም ቢሆን ግን የነገሮችንና ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ ወጥ የሆነ የፈተና አሰጣጥ እንድኖርና ሁሉም የህግ ተማሪ ጥቅም የሚከበር እንድሆን የመስራት ግን የህብረቱ ሃላፊነት ነው፡፡
.
.
መልካም ቀን!!!!!!!!
ደሀ ደንብ/ዳኝነት ሳይከፈል፣ በነፃ መዝገብ ማስከፈት/
======================
ክስ ለማቅረብ የፈለገ ወገን ከፍርዱ ለሚያገኘው የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችል የገንዘብ አቅም የሌለው ከሆነ ክሱን ያለዳኝነት ገንዘብ በደሀ ደንብ መሠረት የማቅረብ መብት እንዳለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 215 ተደንግጓል፡፡ ክሱን የሚያቀርበው ወገን ድሀ በመሆኑ ምክንያት የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍል ክሱን አቅርቦ እንዲያሰማ ሊፈቅድለት ይገባል? የሚለው ጉዳይ ሊለይ የሚችልበት ዝርዝር አፈፃፀም ደንቡም ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 እና ተከታዩ ድንጋጌዎች ተመልክቷል፡፡ እነዚህ ደንቦች ተፈፃሚነታቸው ክስ ለማቅረብ በፈለገ የተፈጥሮ ሰውም ሆነ በሕግ ሰውነት ያላቸው ወገኖችም ጭምር ነው፡፡
በዚህም መሠረት ድሀ ነኝ፤ መብቴን ለማስከበር ያለኝ ፍላጐቴ በዳኝነት ገንዘብ እንቅፋት ምክንያት ሊሰናከል አይገባም፡፡ ስለሆነም በድሀ ደንብ መሠረት ክሱን በነፃ እንዳሰማ ይፈቀድልኝ የሚል ማናቸውም ከሳሽ ድሀ መሆኑን ሊያመለክት የሚችል የሚገኝበትን የገንዘብ አቋም ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡ ይህም ከሳሹ የሚገኝበት የገንዘብ አቋም ከተረጋገጠ በኋላ ለክሱ ሊከፈል የሚገባው የዳኝነት ገንዘብ መጠን ከሳሹ ከሚገኝበት የገንዘብ አቋም አኳያ ተገናዝቦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 መሠረት ድሀ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ሊለይ ይገባል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 79555 ቅጽ 14፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215፣ 467
አንድ ሰው በፍርድ ሊያልቅ የሚገባው ጉዳይን ፍርድ ቤት ይዞ ሲቀርብ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ መክፈል ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 215፣ ከ467 እስከ 479 ድረስ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ያሳያሉ፡፡ የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የማይችል ሰው ክስ ለማቅረብ የሚችልበት አግባብ ስለመኖሩም ተጠቃሽ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ፡፡ አንድ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለመክፈል የማይችል ሰው በደሃ ደንብ ክስ ለማቅረብ የሚችል ሲሆን ለመክፈል አቅም እያለው ክስ ያቀረበ መሆኑ ከተረጋገጠ ግን መዝገቡ እንደሚዘጋ፣ የተዘጋ መዝገብ ደግሞ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ /ገንዘቡን/ ለመክፈል ዝግጁ እስከሆነ ድረስ የሚንቀሳቀስለት መሆኑን የሥነ ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች መንፈስና ይዘት ያስገነዝባሉ፡፡
ሰ/መ/ቁ. 52942 ቅጽ 12፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215፣ 467-479
ይግባኝ ዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ለመክሰስ እንዲፈቀድ በቀረበ ጥያቄ ላይ ሊሰጥ የሚችለው ትእዛዝ እንደነገሩ ሁኔታ ሁለት ዓይነት ነው፡፡ አንደኛው ከሣሽ የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችለው የገንዘብ አቅም የሌለው ስለሆነ እንደ ጥያቄው የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍል በነፃ ፋይል ከፍቶ ክሱን ለማቅረብ ይችላል የሚለው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ከሣሹ ድሃ ያለመሆኑ ስለተረጋገጠ ተገቢውን የዳኝነት ገንዘብ ካልከፈለ በቀር በነፃ ፋይል ከፍቶ ክሱን ለማቅረብ አይችልም የሚለው ነው፡፡
በመጀመሪያው አኳኋን ትእዛዝ በተሰጠ ጊዜ በዚህ ትእዛዝ መሠረት ፋይሉ ተከፍቶ ክርክሩ የሚቀጥል ነው፡፡ የክርክሩ ውጤት የሚታወቀው ግራ ቀኙ በሚያቀርቡት የፍሬ ነገርና የሕግ ክርክር ማስረጃ መሠረት ነው፡፡ በመጨረሻው የክርክር ውጤት ተከሣሹ ባይስማማ ክርክሩ ከመጀመሩ በፊት ክሱ ዳኝነት ሳይከፈልበት በነፃ እንዲከፈት መደረጉ የሕግ ድጋፍ አልነበረውም የሚለውን እንደ አንድ የይግባኝ ምክንያት በማድረግ በውሣኔው ላይ ካለው ቅሬታ ጋር አዳምሮ ማቅረብ ይኖርበታል እንጂ ከሥረ-ነገሩ ፍርድ በፊት የይግባኝ አቤቱታ የማቅረብ መብት አይኖረውም፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 320/3/ የተመለከተው ድንጋጌም በዚህ አኳኋን በሚቀርበው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ክልከላ ለማድረግ ነው፡፡
በሌላ በኩል ድሀ ያለመሆንህ ተረጋግጧል፡፡ የዳኝነት ገንዘብ ካልከፈልክ በቀር ፋይል አይከፈትም ለተባለው ከሣሽ ግን ይህ ዓይነቱ ትእዛዝ የመጨረሻ ነው፡፡ ሌላ የሚጠበቅ የሥረ-ነገር ፍርድ የለውም፡፡ ስለሆነም የዳኝት ገንዘብ ለመክፈል አቅም ሳይኖረኝ ክርክሬና ማስረጃዬ በአግባቡ ሳይታይ አቅም እንዳለኝ ተቆጥሮ የዳኝነት ገንዘብ ክፈል መባሌ ተገቢ አይደለም የሚል ከሆነ የተሰጠው ትእዛዝ የመጨረሻ እንደመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 320/1/ መሠረት የይግባኝ አቤትታ የማቅረብ መብት አለው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 23744 ቅጽ 6፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 320
https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties
Forwarded from Hailegiorgis Tefera
የመውጫ ፈተና 2013 እንደሚታወቀው የዘንድሮው አመት ከሌሎቹ ትንሽ ከባድ ይመስላል የተማሪዎች ዘግይቶ መጠራትና የትምህርት መደራረብ በሁሉም ዪኒቨርስቲዎች አለ ማለት ይቻላል . ተፈታታኝ ተማሪዎችም በቂ ዝግጅት አላቸው ለማለት ይከብዳል በአሁን ሰአትም አብዛኞቹ ተማሪዎች apparent እና ሪሰርች በመስራት ላይ ይገኛሉ ጥቂት ግቢዎች ናቸው ቶሎ የጨረሱት እናም በበቂ ሁኔታ ተማሪዎች ተዘጋጅተን ለማለፍ ብሎም ጥሩ ውጤት ለማምጣት ጊዜ ያስፈልጋል ባይ ነኝ ይህ ደግሞ የኔ ሀሳብ ብቻ አይደለም አብዛኛው ተማሪ ቢራዘም የሚፈልግ ነው ምናልባት እስካሁን የጨረሱና ያነበቡ ተማሪዎች ቢራዘምም የሚጎዱ አይመስለኝም ... በመሆኑም ቢራዘም መልካም ነው እንደ አብዛኛው ተማሪዎች ሀሳብ ... እናንተም የቻላችሁትን ብታረጉ ..
Forwarded from Solomon Shumetu
ደገፍኩትም አልደገፍኩትም፥ የመራዘሙ ሃሳብ የሚቀርብበት ምክንያት ትክክል እንደሆነ እስማማለሁ። ነገር ግን የሚራዘም ከሆነ ከነሀሴ 20 በኋላ ሊሆን እንደሚችል ካሉት ልምዶች ቅድመ ግምት መዉሰድ ይቻላል። ምክንያቱም በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አማኞች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የፍልሰታ ጾም ነሀሴ 1 ይጀመርና ነሀሴ 16 ትንሳኤ ይሆናል። በጾም ሰዓት ደግሞ እንኳን ይህን ትልቅ ፈተና የምስለ ፍርድ ቤት ዉድድሮች እንኳን እንዳይካሄዱ ትልቅ ጥረት ይደረጋል።
========
ይህ ሲሆን ደግሞ አዲስ አመትን ከቤት ዉጭ ማሳለፍ ሊከሰት ይችላል። ይህን ላለማድረግ ሲባል ደግሞ ወደ መስከረም ሊሄድም ይችላል። በዚህ ሂደት ዉስጥ ያሉትን ነጥቦች በግሌ ማገናዘብ ያሻል ባይ ነኝ።
በሀሰተኛ ማስረጃ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደባቸው ግለሰብ ከእስር ነፃ ተለቀቁ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሀሰተኛ ማስረጃ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደባቸው ግለሰብ በልዮ ሁኔታ ያለ ቅድመ ሁኔታ ከእስር ነፃ መውጣታቸውን የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት አስታወቀ።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዓለምሸት ምህረቴ ÷በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላ ድንጋይ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ግለሰብ ከአምስት ዓመት በፊት በእንጀራ እናቷ ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ ተገድላለች በሚል ግለሰቧ መሞቷ በሃሰተኛ ማስረጃ ተረጋግጦ ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ተጥሎባቸው ነበር።

ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ የእንጀራ ልጇን ገድላለች በሚል የሰሜን ሸዋ ዞን ዐቃቤ ሕግ የወንጀል መዝገብ ቁጥር 134/2008 ክስ መስርቶባቸው ሲከራከሩ መቆየታቸውን ተገልጿል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የቀረበውን ክስና ማስረጃ በመመርመር ጥፋተኛ ናቸው ብሎ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እና በአምስት ዓመት ከማንኛውም ማህበራዊ ግንኙነት እንዲገለሉ ውሳኔ አስተላልፎ እንደነበር ገልጸዋል።

በተሠጠው ውሳኔ መሠረትም ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ አምስት ዓመት በደብረብርሃን ማረሚያ ቤት በእስር መቆየታቸው ተገልጿል።

ነገር ግን ሞተች ተብላ በሀሰተኛ ማስረጃ የተረጋገጠላት ግለሰብ ከሌላ አካባቢ በሕይወት ቆይታ በቅርብ ጊዜ ወደ ትውልድ አካባቢዋ በመምጣቷ ሞተች ተብላ ጥፋተኛ ያልሆነችን ግለሰብ እንደ ጥፋተኛ ቆጥሮ ማረሚያ ቤት እንድትወርድ ያደረገችው ግለሰብ ማንነቷ በአካባቢው ህብረተሰብ እና በማስረጃ ተረጋግጧል ብለዋል።

በዚህም በሃሰተኛ ማስረጃ ተፈርዶባቸው በእስር የቆዩት ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ በአማራ ክልል የተሻሻለው የይቅርታ አሰጣጥ መወሰኛ መመሪያ ቁጥር 30/2010 መሠረት ጉዳያቸው ለአማራ ክልል ይቅርታ ቦርድ ቀርቦ የክልሉ ምክር ቤት በ29 ቀን 2013ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ወ/ሮ አዛለች ቤተምንዳ በልዮ ሁኔታ ያለ ቅድመ ሁኔታ ከእስር ነፃ እንዲወጡ እና የተጣለባቸው ገደብ እንዲነሳላቸው ወስኗል።

የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው በወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ ላይ የገጠመው ጉዳይ ያለ ማስረጃ የሚታሰሩ ታራሚዎች በሞራል፣በኢኮኖሚ፣በማሕበራዊ፣በ ቤተሰብ ላይ የሚደርስባቸውን ጉዳት ካሳ የሚካሱበት የሕግ ማዕቀፍ የሌሎች አገሮችን ልምድ በመቀመር ማዘጋጀት እንደሚገባ አስተማሪ ሆኖ አልፏል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Source :-FBC
Forwarded from Dinaol Debele
ሰላም እንዴት ናችሁ ?
ተማሪ ዲናኦል ደበሌ እባላለሁ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ነኝ።
በ exit ጉዳይ ላይ የምሰጠዉ ሀሳብ ቢኖር እንደኛ ግቢ ዝግጅታችን ከ100% ቢሰላ 0% ነዉ። ምክንያቱ ደግሞ ወደ ግቢ የገባነዉ ጥር 27 ነዉ። ከገባን ቧኻላም እስከ የካቲት 9 ድረስ የ 4ኛ አመት 1ኛ ሴሚስተር ፈተና ስንወስድ ነበር። የ 5ኛ አመት ኮርስ ከጨረሰን ገና 2 ሳምንታትን ማስቆጠራችን ነው።externship ላይ እያለን ነዉ እሄንን ዜና የሰማነው። ዉሳኔው በተማሪዎች ዘንድ ያልተጠበቀ ነገር እና መደናገጥን አስከትሎባቸዋል። ስለሆነም ዉሳኔዉ እንደ አዲስ ቢታይ እና ቀን ቢጨመር እላለሁ
Forwarded from Deleted Account
እኔ በበኩሌ የፈተና ግዜ ብራዘም ባይ ነን። ምክንያቱም በ2013 የትምህርት ዘመን ሁላችንም እንደ ሀገር ያሳለፍነው በብዙ መጨናነቅነና ውጥረት ውሰጥ ነው። አሁንም ቢሆን አብዛኞቻችን በExternshipና Research ላይ ነን። መራዘሙን 100% እደግፋለሁ። Getahun from Wachemo University.
በሀሰተኛ ማስረጃ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደባቸው ግለሰብ ከእስር ነፃ ተለቀቁ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሀሰተኛ ማስረጃ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደባቸው ግለሰብ በልዮ ሁኔታ ያለ ቅድመ ሁኔታ ከእስር ነፃ መውጣታቸውን የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት አስታወቀ።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዓለምሸት ምህረቴ ÷በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላ ድንጋይ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ግለሰብ ከአምስት ዓመት በፊት በእንጀራ እናቷ ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ ተገድላለች በሚል ግለሰቧ መሞቷ በሃሰተኛ ማስረጃ ተረጋግጦ ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ተጥሎባቸው ነበር።

ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ የእንጀራ ልጇን ገድላለች በሚል የሰሜን ሸዋ ዞን ዐቃቤ ሕግ የወንጀል መዝገብ ቁጥር 134/2008 ክስ መስርቶባቸው ሲከራከሩ መቆየታቸውን ተገልጿል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የቀረበውን ክስና ማስረጃ በመመርመር ጥፋተኛ ናቸው ብሎ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እና በአምስት ዓመት ከማንኛውም ማህበራዊ ግንኙነት እንዲገለሉ ውሳኔ አስተላልፎ እንደነበር ገልጸዋል።

በተሠጠው ውሳኔ መሠረትም ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ አምስት ዓመት በደብረብርሃን ማረሚያ ቤት በእስር መቆየታቸው ተገልጿል።

ነገር ግን ሞተች ተብላ በሀሰተኛ ማስረጃ የተረጋገጠላት ግለሰብ ከሌላ አካባቢ በሕይወት ቆይታ በቅርብ ጊዜ ወደ ትውልድ አካባቢዋ በመምጣቷ ሞተች ተብላ ጥፋተኛ ያልሆነችን ግለሰብ እንደ ጥፋተኛ ቆጥሮ ማረሚያ ቤት እንድትወርድ ያደረገችው ግለሰብ ማንነቷ በአካባቢው ህብረተሰብ እና በማስረጃ ተረጋግጧል ብለዋል።

በዚህም በሃሰተኛ ማስረጃ ተፈርዶባቸው በእስር የቆዩት ወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ በአማራ ክልል የተሻሻለው የይቅርታ አሰጣጥ መወሰኛ መመሪያ ቁጥር 30/2010 መሠረት ጉዳያቸው ለአማራ ክልል ይቅርታ ቦርድ ቀርቦ የክልሉ ምክር ቤት በ29 ቀን 2013ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ወ/ሮ አዛለች ቤተምንዳ በልዮ ሁኔታ ያለ ቅድመ ሁኔታ ከእስር ነፃ እንዲወጡ እና የተጣለባቸው ገደብ እንዲነሳላቸው ወስኗል።

የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው በወይዘሮ አዛለች ቤተምንዳ ላይ የገጠመው ጉዳይ ያለ ማስረጃ የሚታሰሩ ታራሚዎች በሞራል፣በኢኮኖሚ፣በማሕበራዊ፣በ ቤተሰብ ላይ የሚደርስባቸውን ጉዳት ካሳ የሚካሱበት የሕግ ማዕቀፍ የሌሎች አገሮችን ልምድ በመቀመር ማዘጋጀት እንደሚገባ አስተማሪ ሆኖ አልፏል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Source :-FBC
1(አንድ)
#ሰው ነኝ ስል ሀይማኖት የለኝም ማለቴ አይደለም።
#ሰውነኝ ማለቴ ብሔር የለኝም ማለቴ አይደለም።
#ሰውነኝ ስል ልዮነቶችን የማከብር አንድነታችን አብልጦ የሚገዛኝ ነኝ ማለቴ ነው።
#ሰው ነኝ ስል አምላክ የፈጠረውን የሰው ልጅ በየትኛውም ስፍራ ይምጣ፣ ምንም አይነት እምነት ይከተል፣ ቋንቋችን ይለያይ ይመሳሰል:- ጠላቴ ነው ይጥፋ ብዬ በእምነቴ ሀጥያትን፣ በአለምአቀፍ ህግ ወንጀልን እንዲሁም በስነምግባር ነውርን አልፈፅምም ማለቴ ነው።
#ሰውነኝ ስል ነፍሴ ብሔር የላትም ማለቴ ነው።
#ሰውነኝ ስል በተለያዩ አካላት በሆነውም ባልሆነውም የሚነገረኝን ሁሉ እንደወረደ ባለመቀበል፣በስሜት ሳልመራ ለማደርገው እና ለምናገረው ነገር በፈጣሪዬ ትዕዛዝ አንፃር እና በህሊናዬ አመዛዝናለሁ ፣ አገናዝባለሁ ማለቴ ነው።
#ሰው ነኝ ስል ሀላፊ ጠፊ መሆኔን ሳልዘነጋ እስካለሁ በሀገር ውስጥም በውጪም ካሉ የሰው ዘር ወገኖቼን አክብሬ ከሁሉም ጋር በሰላም መኖርን እመርጣለሁ ማለቴ ነው።
#ሰውነኝ ስል ድክመት አለኝ፣ ሰውን ላሳዝን እኔም በሰው ልጎዳ ብችልም ከነስህተታችን ተራርመን ተደጋግፈን መኖር እንደምንችል አምናለሁ ማለቴ ነው።
#ሰውነኝ ማለቴ እርስ በርስ ለመጎዳዳት ፈፅሞ አልተፈጠርንም ብዬ በፅኑ አምናለሁ ማለቴ ነው።
#ሰውነኝ ስል መብትም እንዳለኝ ግዴታም አለብኝ እና ለኔ የምፈልገውን ለሌላው እንዳይሆን አልከላከልም ማለቴ ነው።
#ሰውነኝ ስል የሰላም መኖርያ እንደሚያስፈልገን አውቄ ሀገር ብትፈርስ ተጎጂዎቹ ሁላችንም መሆናችንን ተገንዝቤ ለልጅ ልጆቻችን እና ለመጪው ትውልድ ጭምር ሰላማዊት ሀገር ለማስረከብ ከሀገሬ ጎን እቆማለሁ ማለቴ ነው።
#ሰውነኝ ስል ከአላስፈላጊ መበሻሸቅና ክፉ ቃል ተቆጥቤ በሰከነ መንፈስ ለመፍትሔ እሰራለሁ ማለቴ ነው። ይቀጥላል...

ሰብአዊነት ፓለቲካ አይደለም!
ሰው መሆኔን መች አጣሁት በማለት የቃላት ጨዋታ ላይ ሳናተኩር እንደአፈጣጠራችን ሰው ሆነን እንገኝ!
#ሰውነኝ የፓለቲካ ሀሳብ አይደለም! ይልቁንም ፓለቲከኞችንም ሆነ የሀይማኖት ሰዎችን ፣ ምሁራንንም ሆነ የጥበብ ሰዎችን፣ አባት እና እናቶችን ብሎም መላው በሀገርም በውጪም ያሉ ወገኖችን ከዚህ ሰው ሰው ከማይሸት አካሄዳችን ተቆጥበን፣ ወደ ልቦናችን እና ወደ ስክነት ተመልሰን አንዱ ሲያለቅስ አንዱ የሚስቅበትንና በየተራ እርስ በእርስ የምንሳለቅበትን አካሄድ በማስቆም ሁላችንም አሸናፊ የሚያደርገንን መፍትሔ ሰብአዊነትን በማስቀደም እንድናመጣ እንለምናችኋለን🙏🙏🙏
#ሰው ነኝ
#ሰብእየ
#አንደኖ
#Aninama
#Iamhuman
Via I am Human Movement‼️
https://t.me/NegereFej
https://t.me/NegereFej
New Vacancy ‼️‼️‼️

Position: Lawyer II

Job Time: Full-Time

Job Type: Permanent

Place of Work: Addis Ababa, Ethiopia

Salary: 6,055.00


Application Deadline: Jul, 22/2021 (13 days left)

Accounting and Auditing Board of Ethiopia is looking to hire qualified applicants who fulfill the following requirements 

Level IX

Requirement

LLB/LLM Degree in Law

Experience  0/2 years

Required Number 2

Salary 6,055.00

How to apply

Interested applicants can submit all their necessary credentials such as Educational background, Work experience along with an unreturnable photocopy to the following address:

6 Kilo in front of Egypt Embassy on Leadership Institute Building 4th floor 

Office number 402 

Tel 0111540902 

PO Box 80263
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የፌዴራል_የዳኝነት_አስተዳደር_ዓዋጅ_ቁጥር_1233_2013.pdf
2.1 MB
Federal Judicial Administration Proclamation 1233/2021 - የፌዴራል የዳኝነት አስተዳደር ዓዋጅ ቁጥር 1233/2013
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
Ethiopian Law School Association ..............loading.
we will update you‼️@lawsocieties
Happening Now
የኢትዮጵያ የሕግ ትምህርት ቤቶች ማህበር ምስረታ ጉባኤ እየተካኸደ ነዉ። በጉባኤዉ የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ላይ ዉይይት ይደረጋል ፤ የኮሚቴ አባላት ይመረጣሉ ፤ የማህበሩ መመስረቻ ጽሑፍ ይጸድቃል ፤ የማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና ኦፊሰሮች ይሰየማሉ።

የዚህ ታሪካዊ ጉባኤ አካል በመሆኔ ክብር ይሰማኛል።
via ደሳለኝ ከበደ
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties