አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ከዚህ በላይ በአንቀጽ 1000(1) እና (2) ላይ የተመለከቱት የጊዜ ገደቦች ከሌሎች የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች በተለይም 1ኛ) አንድ ወራሽ የሟች ኑዛዜ ተጠቃሚ መሆን የሚችለው ኑዛዜ በእጁ እንደሚገኝ ለውርስ አጣሪው አቅርቦ ውርስ አጣሪው ኑዛዜውን በሚነበብበት ሰዓት ራሱ ወይም ወኪሉ ካልነበረ ወራሹ ኑዛዜው ከፈሰሰበት ቀን አንስቶ በአስራ አምስት አመታት ውስጥ መቃወሚያ ካላቀረበ ከዚያ በኋላ ሊቀርብ እንደማይችል በፍ/ሕ/ቁ 974(2) የተመለከተው በፍ/ሕ/ቁ 1000(1) ካለው የጊዜ ገደብ ጋር እንዴት ተጣጥሞ ተግባራዊ ይሆናሉ ከሚለው ጋር ጥያቄ የሚያስነሳ ሲሆን በሌላ መልኩ በፍ/ሕ/ቁ 1000(1) እና (2) አተረጓጎምና አፈጻጸም እንዴት መሆን አለበት በሚል አልፎ አልፎ ጥያቄ ሲያስነሳ ይስተዋላል፡፡ ስለዚህ በእነዚህ የሕግ ማዕቀፎች ላይ የተጠቀሱት የጊዜ ገደቦች በተመለከተ መከተል የሚገባንን የሕግ ትርጓሜ እንደሚከተው ለማብራራት ተሞክሯል÷ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 974/2/ ተፈጻሚ የሚሆነው የሟች ውርስ የሚያጣራ ፤በሕግ በኑዛዜ ወይም በፍርድ ቤት የተሾመ የውርስ አጣሪ ፤ሟች አድርጎታል የተባለው ኑዛዜ አግኝቶ የኑዛዜውን ፎርምን የኑዛዜውን ዋጋ መኖር ፤የሟች ያለኑዛዜ ወራሾች ወይም አራት አካለመጠን ያደረሱ ሰዎች ባሉበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 968 በተመረመረበት ሁኔታ ነው፡፡ ሆኖም ግን ኑዛዜ ያለ መሆኑን ለውርስ አጣሪው ሳያሳውቅ ቀጥታ የኑዛዜ ወራሽ መሆኑ እንዲታወቅለት ለፍ/ቤት አመልክቶ የወራሽነት የምስክር ወረቀት በመውሰድ የሟች ንብረት በእጁ ያደረገ ሰው ወይም በሀሰት የሟች ያለኑዛዜ ወራሽ ነኝ ብሎ የሟችን ንብረት ከወሰደው ሰው ለማስመለስ አግባብ የሆነው የይርጋ ገደብ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 968 የተጠቀሰው ሳይሆን በፍብ/ሕ/ቁ 1000/1/ የተመለከተው ተፈጻሚነት ሊኖረው ይገባል፡፡
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ እና 1000/2/ አስመልክቶ የተለያዩ አተረጓገሞች የሚስተዋሉ ሲሆን ለዚህ ጽሁፍ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 30158 ፤26422 እና 34011 በቅጽ 7/6/6/ እንዲሁም በቅጽ 11 በሰ/መ/ቁ 52407 የሰጠውን አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ለመዳሰስ ሞክሬያለው፡፡ በዚሁ አግባብ በፍ/ሕ/ቁ 1000/2/ ላይ ሟች ከሞተ አስራ አምስት አመት በላይ ወይም ተከሳሹ በመብቱ ሊሰራበት ከቻለበት ቀን አንስቶ አስራ አምስት ዓመት ውስጥ ክስ ካልቀረበ አስራ አምስት ዓመት ካለፈው በኋላ ክስ ሊያቀርብ የሚቻለው ከዘር የወረደ ርስት በሆነ ንብረት ላይ ነው፡፡
ርስት የሚለው ቃል በፍ/ሕ/ቁ 1130 እና ስለ ንብረቶች በሚናገረው የፍ/ብሔር የህጉ ክፍል መሬት የሚያመለክት መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ በኢትዮጲያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል የተዘጋጀው የአማርኛ መዝገበ ቃላት ርዕስት የሚለው መሬትን የሚመለከት መሆኑን ጠቅሶ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ በዚሁ አግባብ ከዘር የወረደ ርዕስት የሚለው ቤትን አያጠቃልልም የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ በርዕስት የሚተላለፍ መሬት ብቻ ማለት ሰለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/2/ መሰረት ለተወላጆች የሚተላለፍ መሬት ብቻ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡
በኢፌድሪ ህገ መንግስት መሰረት መሬት የመንግስትና የህዝብ ሀብት በመሆኑ ከዘር የወረደ ርዕስት ካልሆነ በስተቀር በማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/2/ ላይ የተገለጸው የተሻረ እና ተፈጻሚነት የሌለው ነው በማለት አስገዳጅ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ አፈጻጸምን በተመለከተ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 32407 በቅጽ 11 ላይ ትርጓሜ የሰጠ ሲሆን በዚህም መሰረት በወራሾች መካከል የሚነሳ የውርስ ንብረት ክርክር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ በተደነገገው አግባብ በሶስት አመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ያለበት ሲሆን ወራሽ በሆነ እና ወራሽ ባልሆነ ተከራካሪ ወገን መካከል የሚቀርበው የውርስ ንብረት ይገባኛል ጥያቄ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1677 እና 1845 መሰረት በአስር አመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ መብቱ በይርጋ የሚታገድ ይሆናል፡፡
//////
የክፍፍል ጥያቄ በይርጋ የማይታገድ ስለመሆኑ
/////🇪🇹
ወራሾች ተለይተው የውርስ ሀብቱ ድርሻ ታውቆ ግን ክፍፍል ሳይደረግ የቆየ የውርስ ሀብት ያለ እንደሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1062 በተገለጸው መሰረት እያንዳንዱ የጋራ ወራሾች ውርሱን እንከፋፈል በማለት በማንኛውም ጊዜ ለመጠየቅ የሚችሉ በመሆኑ የክፍፍል ጥያቄ በይርጋ የማይታገድ ይሆናል፡፡
//////
መደምደሚያ
///////
በአጠቃላይ አንድ ሰው ከዚህ አለም በሞት የተለየ እንደሆነ የውርስ ጉዳዩን በተመለከተ ወራሽ የሆነ ወገን ኑዛዜን ሚቃወምበት፤የወራሽነት ጥያቄ ሚያቀርብበትና ክፍፍል የሚጠይቅባቸው የጊዜ ገደቦች ከዚህ በላይ በተገለጸው አግባብ ተፈጻሚ ሚሆኑ ሲሆን ባለመብት የሆነ ወገን ጥያቄውን በህጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያላቀረበ እንደሆነ ውጤቱ መብቱን እስከማጣት የሚደረስ ይሆናል፡፡
#like #shareshare ያድርጉ።

(By Muluken Seid Hassen)
source Abyssinialaw.com