አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ባልደራስ_ለእውነተኛ_ዲሞክራሲ_ፓርቲ_ከ_ኢትዮጵያ_ምርጫ_ቦርድ_በመዝገብ_ቁጥር_207000.pdf
5.2 MB
በባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ እና በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ መካከል በተካሄደ ክርክር የሰበር ችሎት ውሳኔ

ጉዳዩ ለ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ አመልካች (ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክረሲ ፓርቲ) ያቀረባቸው እጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ መከልከላቸውን በመቃወም አመልካች ያቀረበውን አቤቱታ የምርጫ ጉዳዮቸን ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተመልክተው ሰጡትን ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በሚል በሰበር እንዲታረም በመዝገብ ቁጥር 207000 ግንቦት 13 ቀን 2013 ዓ.ም የቀረበ ነው፡፡ ሰበር ችሎቱም አቤቱታውን ተቀብሎ የሰጠውን ውሳኔ ግልባጭ ለመረጃ እንዲሆናችሁ እንዲህ አካፈልናችሁ፡፡

ፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዪኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
የኢትዮጵያ_ምርጫ_ቦርድ_ከ_ሐረሪ_ብሔራዊ_ጉባዔ_መዝገብ_ቁጥር_207036.pdf
11.6 MB
በሀረሪ ሕዝብ ክልል መንግስት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ እና በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ መካከል የምርጫ ጉዳይን አስመልክቶ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 207036 የሰጠው ውሳኔ

የሀረሪ ሕዝብ ክልል መንግሥት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ከክልሉ ውጭ የሚኖር የሐረሪ ሕዝብ ከዚህ ቀደም እንደነበሩት አምስት አገራዊ ምርጫዎች በ6ኛው አገራዊ ምርጫም ከክልሉ ዉጭ ያሉ የብሔረሰቡ አባላት ለሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ሊመርጡ ይገባል በሚል ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የቀረበን አቤቱታ በመመርመር የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጥያቄውን ተቀብሎ ማስተናገድ እንደማይቻል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ቦርዱ የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ የሀረሪ ሕዝብ ክልል መንግሥት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ የይግባኝ ቅሬታውን ወደፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቧል፡፡ የፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 205809 ሚያዚያ 19 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ የምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ የሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል፡፡

ይህን ተከትሎ የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ የይግባኝ ችሎቱ የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ጉዳዩን ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በማቅረቡ ምክንያት የሰበር አቤቱታውን የተመለከተው የፍርድ ቤቱ ሰበር ችሎት በሰ/መ/ቁ 207036 ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠውን የውሳኔ ግልባጭ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

ፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
Attorney | Wegagen Bank S.C

Wegagen Bank S.C

Addis Ababa

Wegagen Bank S.C Vacancy Announcement Position: Attorney Job Purpose: • To handle debt recovery cases, respond to court orders and follow up on criminal cases - Required: 1 - Place of Work: Head Office How to Apply: • Applicants fulfilling the stated criteria could send their applications with CV and copy of testimonials by mail or put in the application Box placed at the entrance of Bank’s Head Quarter Building, located around A.A Stadium until June 3,2021, P.O.Box 1018, Addis Ababa, • Tel: 0115-523800 / 0118-72-02-06
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties https://t.me/lawsocieties
Legal Affairs Directorate Director

Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise

Position: Legal Affairs Directorate Director

Job Time: full-time
Job Type: Permanent

Place of Work: Addis Ababa, Ethiopia

Salary: 16,070.00

Posted date: 8 hours ago

Application Deadline: Jun, 10/2021 (8 days left)

Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise is looking to hire qualified applicants who fulfill the following requirements

Requirement

LLM/ LLB in Law

Experience 

6 years of work experience out of which 2/3 years in a senior position.

Salary 

16,070.00

Place of work 

Addis Ababa

How to apply

Interested applicants should submit all their necessary credentials such as educational background, work experience, cv along with an unreturnable photocopy to the following address:

Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise 1st gate 

Human Resource Management Office 

at Piassa Atkilt tera in front of Khelifa Building 

Tel 0113692213/ 0113692610
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties https://t.me/lawsocieties
Senior Lawyer

Information Technology Park Corporation

Position: Senior Lawyer

Job Time: Full-Time

Job Type: Contract

Place of Work: Addis Ababa, Ethiopia

Salary: 18,411.00

Posted date: 1 day ago

Application Deadline: Jun, 8/2021 (6 days left)

Information Technology Park Corporation is looking to hire qualified applicants who fulfill the following requirements 

Requirement LLB/LLM in Law.

Experince  4/2 years of work experience 

Job Type Contractual 

Salary 18,411.00

Required Number 01
Place of work Addis Ababa Bole sub-city, woreda 11 from Goro square to Tulu Dimtu

How to apply

Qualified applicants who fulfill the above requirements should submit all their necessary credentials such as educational background, work experience along with an unreturnable photocopy to 

Bole sub-city, woreda 11 from Goro square to Tulu Dimtu,

The Park's Management Building 1st floor Finance management / Human Resource office,

Tel 0118332420 or 0118263433

 

Applicants with work experience from non-governmental institutes should bring proof of tax payment.
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties https://t.me/lawsocieties
የቀብድ {Earnest} ምንነት እና ህጋዊ ውጤቱ
♨️♨️♨️🛑🛑🛑🛑🛑👇

ብዙዎቻችን የተለያዩ የሽያጭ ውሎችን ስንፈፅም ቀብድ በሚል የሚከፈል ክፍያ የምንፈፅም ሲሆን ነገር ግን ስለ ቀብድ ምንነትና ውጤት ያለን ግንዛቤ አናሳ ነው። በዚህ ፅሁፍም የቀብድን ምንነትና ህጋዊ ውጤቱን በአጭሩ ለመዳሰስ እንሞክራለን።

የቀብድ ምንነት
🛑🛑♨️👇

በኢትዬጵያ የፍትሀብሄር ህግ ከቁጥር 1883- 1885 ድረስ ባሉት ሶስት አንቀፃች ውስጥ ቀብድን የሚመለከቱ ሀሳቦች የተቀመጡ ቢሆንም "ቀብድ" ለሚለው ቃል ግን የሚሰጡት ትርጉም የለም። እነዚህ ድንጋጌዎችም ቀብድን ከውል ምስረታ ማስረጃነት ገፅታው እና በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንደ አግባብነቱ ቅጣት በመወሰን ቀብድ ያለበት ውል በማናቸውም ጊዜ ቀሪ ሊሆን መቻሉን በመደንገግ ላይ የተወሰኑ ናቸው።

በፍትሀብሄር ህጋችን ላይ ቀብድ (earnest) የሚለው ቃል በግልፅ ትርጓሜ የተሰጠው ባይሆንም በእንግሊዘኛው አነጋገር በblacks law dictionary ውስጥ በተሰጠው ትርጉም መሰረት "ቀብድ ማለት ተዋዋይ ወገኖች ከግዴታቸው እንዳያፈነግጡ ለማድረግ ተብሎ የሚሰጥ የተሸጠ ዕቃ ከፊል ዋጋ ነው። እንዲሁም ዕቃው መሸጡን ለማሳየትና ለማፅደቅ ተብሎ አንዱ ተዋዋይ ለሌላው የሚሰጠው የመተማመኛ ገንዘብ ነው......" በሚል ያስቀምጣል።

ቀብድ አብዛሀኛውን ጊዜ የሚሰጠው ውሉ የሽያጭ ውል ሲሆን ነው። ገዥው በሽያጭ ውሉ ለመገደድ ያለውን ሀሳብ ለማሳየት እና ሻጩ ደግሞ እሸጣለሁ ብሎ የሰጠውን ቃል እንዳያጥፍ ውሉ መፈፀሙ እርግጠኛ በሆነበት ሰዓት አንዱ ወገን ለሌላው ወገን ውሉ ሲደረግ ለማሰር የሚሰጠው ክፍያ ነው።

የቀብድ ህጋዊ ውጤት
♨️♨️🛑🛑🛑👇

#1 ቀብድ ሻጭና ገዥ በተነጋገሩበት ጉዳይ ላይ ውል መፈፀማቸውን እርግጠኛ ሲሆኑ የሚቀባበሉት ገንዘብ በመሆኑ ይህን ማድረጋቸው ገንዘቡን ለመቀባበላቸው ብቻ ሳይሆን ውሉን ለመዋዋላቸውም ማስተባበያ የማይቀርብበት ማስረጃ መሆኑን የፍ/ብ/ህ/ቁ 1883 ይደነግጋል።

ገዥና ሻጭ አንድን ቤት ሲሻሻጡ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1723(1) ስር የተመለከተውን ፎርም ባያሟሉም ሻጭ ለዚሁ የሽያጭ ውል ማስፈፀሚያ ቀብድ መቀበሉ ከተረጋገጠ በማያከራክር ሁኔታ ውሉ መደረጉን ያረጋግጣል። አንድ ውል የህጉን ፎርም ካላሟላ በህግ ፊት የማይፀና ይሆናል ነገር ግን በልዩ ሁኔታ የቀብድ ገንዘብ ክፍያ ካለ ውሉ የህጉን ፎርም ያላሟላ ቢሆንም የቤት ሽያጭ ውል ስለመኖሩ የማያከራክር ማረጋገጫ ስለሆነ ውሉ የፀና ይሆናል። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መዝ/ቁ 56794 ቅፅ 12)

N.B= የተከፈለው ክፍያ ግን ቀብድ መሆኑ በውሉ ላይ ካልተገለፀ በቀር ቀብድ ነው ተብሎ ሻጭ አጠፌታውን እንዲከፍል የማያስገድድ ከመሆኑ በላይ ውሉ መኖሩንም ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም።

#2 የቀብድ ክፍያ መኖሩ የውሉን መኖር የሚያረጋግጥ ብቁ ማስረጃ ቢሆንም ተዋዋይ ወገኖች ውሉን ለማፍረስ ተቃራኒ ስምምነት ካላደረጉ በቀር ቀብድ ተቀባዩ የተቀበለውን ገንዘብ እጥፍ አድርጎ በመመለስ፥ ቀብድ ሰጪው ደግሞ ይህንኑ የሰጠውን ገንዘብ ለተቀባዩ በመልቀቅ ያለሌላ ተጨማሪ ሁኔታ ውሉን የማፍረስና በመካከላቸው የተመሰረተውን ግዴታ ለማስቀረት መብት አላቸው። ይህም አሰራር በቀብድ የታሰረ ውል ከሌሎች ውሎች የሚለይበት ልዩ ባህሪ ነው። (የፍ/ብ/ህ/ቁ 1885)

ፍርድ ቤቶችም በተዋዋይ ወገኖች መካከል ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ሻጩ የቀብዱን አጠፌታ ከፍሎ ውሉን በማፍረስ የሸጠው ቤት እንዲመለስለት ከጠየቀ መወሰን የሚገባቸውና ተገዶ እንዲፈፅምም ማድረግ የሌለባቸው መሆኑ ግልፅ ነው።

N.B= የተደረገው ውል ሊፈፀም የማይችል (impossible)፣ ወደ ገዥ ሊተላለፍ የማይችል እና ህገ ወጥ (unlawful) ከሆነ ግን ውሉ ፈርሶ ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት ከሚመላለሱ በቀር ሻጭም እጥፉን እንዲመልስና ገዢም የከፈለውን እንዲለቅ የሚጣልባቸው ግዴታ የለም።

#3 ውሉ በአግባቡ ከተፈፀመ እና �ለ ቀብዱ ገንዘብ ዕጣ ፋንታ በተዋዋዬቹ መሀል የተደረገ ሌላ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ የቃብድ ሂሳቡ ከጠቅላላው የሽያጭ ዋጋ ላይ የሚታሰብ ወይም እንዲመለስ የሚደረግ ይሆናል። (የፍ/ብ/ህ/ቁ 1884)
በጠበቃ ዘመድኩን ካሱ
በማንኛውም ፍ/ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties https://t.me/lawsocieties
#Urgent!!!!
I am currently working on phd project and am seeking to hire law students who can collect date from the below mentioned offices — with regards to the number of lawyers found in each regions.

Only those who can get the information and located nearby the office areas (amara feteh biro, Oromia feth biro, debub fith biro, Tigray feth biro, ..) leave your number at the below mentioned contact.

Its preferable that the applicants are currently working on their thesis that is related to those offices.

The work should be started on Tuesday. Thus intersted applicants can inbox me (Contact alesocieties2011@gmail.com) ASAP

*Transport allowance and fee will be provided.
*Additional tasks (FOR THE HIRED APPLICANTS) ,with a better payment, might be provided.

Hello if your intersted can you please list down which regional office you can work on

Oromia regional feth bero
Tigray regional feth bero
Debub regional feth bero

@lawsocieties
@lawsocieties https://t.me/lawsocieties
Legal Contracts Advisor

Ethio Telecom

Position: Legal Contracts Advisor

Job Time: Full-Time

Job Type: Permanent

Place of Work: Addis Ababa, Ethiopia

Salary: As per the company scale

Posted date: 1 day ago

Application Deadline: Jun, 14/2021 (8 days left)

Vacancy Code: EVA-Leg-HQ-02-2021

Ethio telecom is looking for qualified applicants who meet the under mentioned requirements. Hence, if you are willing to join this fast-growing company, please apply before the closing date of the vacancy.

General Mission

Under the general direction of Providers or Enterprises Contract Manager, execute legal research which is not complex

Under the guidance of the Manager or Legal Specialist prepare/review supply/partners Agreements

Provide legal advice on national contracts to low or intermediate level management

Contributes to cross-functional actions to enhance the performance of the company

Key Responsibilities

Review the compatibility of provider’s/partners contract having lower contract value

 Prepare data and information as input for contract drafting or addendum to a contract

 Negotiate and verify providers (domestic) contract which has repetitive nature.

Engage in Preparation of draft providers/partners contract and legal opinion to be reviewed by Providers or Enterprise Contract Manager.

Perform other related activities

Participate in legal negotiations

The application of pertinent laws in times of request for legal advice The legality of the contract.

Qualification

Degree In Law (L.L.B)

Required Relevant Experience

2 years experience Legal Contract Activates

Does:

Reports to the providers or Enterprise contract Manager on the achievements of group objectives in terms of quality, quantity, and timeline     

Brings to the provider of enterprise contract manager required information/study/survey for decision making.

Place of Work: – Addis Ababa

Term of Employment: – Permanent

Salary: – As per the company`s salary scale 

How to apply

Interested applicants shall apply online through our website

https://www.ethiotelecom.et/jobs/job-title-legal-contracts-advisor/ 

another way of application is not acceptable.
Applicants must have the required educational qualification and experience.
Applicants who submit false or forged documents will be disqualified at any time confirmed.
Only short-listed applicants will be contacted.   
Female applicants are strongly encouraged to apply. 
@lawsocieties
@lawsocieties https://t.me/lawsocieties
Ethio telecom is looking for qualified applicants who meet the under mentioned requirements. Hence, if you are willing to Join this fast-growing company, please apply before closing date of the vacancy.

   Required qualifications

Job TitleVacancy CodeQualificationRequired Relevant ExperienceLegal Contracts Advisor  EVA-Leg-HQ-02-2021Degree In Law (L.L.B)2 years’ experience Legal Contract Activates

Place of Work: – Addis Ababa

Term of Employment: – Permanent

Salary: – As per company`s salary scale

Opening date: 05-JUN-2021

Closing date: – 14-JUN-2021

General Mission

Under general direction of Providers or Enterprises Contract Manager, execute legal research which are not complex

Under the Guidance of the Manager or Legal Specialist prepare/review supply/partners Agreements

Provide legal advice on national contracts to low or intermediate level management

Contributes to cross functional actions to enhance the performance of the company

Key Responsibilities

Review the compatibility of provider’s/partners contract having lower contract value

 Prepare data and information as input for contract drafting or addendum to a contract

 Negotiate and verify providers (domestic) contract which have repetitive nature.

Engage in Preparation of draft providers/partners contract and legal opinion to be reviewed by Providers or Enterprise Contract Manager.

Perform other related activities

Participate in legal negotiations

The application of pertinent laws in times of request for legal advice The legality of contract.

Does:

Reports to the providers or Enterprise contract Manager on the achievements of group objectives in terms of quality, quantity and timeline     

Brings to the provider of enterprise contract manger required information/study/survey for decision making.

Application Tips

Interested applicants shall apply online through website address; https://www.ethiotelecom.et and other way of application is not acceptable.

Applicants must have the required educational qualification and experience.

Applicants who submit false or forged documents will be disqualified at any time confirmed.

Only short-listed applicants will be contacted.   

Female applicants are strongly encouraged to apply. 

Employment Type: Permanent

Job Title: Legal Contracts Advisor

Job Location: Addis Abeba

Vacancy Code: EVA-Leg-HQ-02-2021

Required Education Level: Degree in Law (L.LB

Required Field of Study: Law

Vacancy Opening Date: 05-June-2021

Vacancy End Date: 14-June-2021

@lawsocieties
@lawsocieties https://t.me/lawsocieties
Director of Legal Services

Addis Ababa Science and Technology University (AASTU)

Position: Director of Legal Services

Job Time: Full-Time

Job Type: Permanent

Place of Work: Addis Ababa, Ethiopia

Salary: 10,906.00

Application Deadline: Jun, 17/2021 (11 days left)

Addis Ababa Science and Technology University (AASTU) is looking to hire qualified applicants who fulfill the following requirements 

Level XVI

Requirement First Degree in Law
Experince  9 years of work experience.
Salary 10,906.00
Required number 1
How to apply

Qualified applicants who fulfill the above requirements should submit all their necessary credentials such as Educational Background, work experience along with an unreturnable photocopy to the following address:

Akaki Subcity Kilinto Woreda 
Down the road from Tirunesh Bejing Hospital,
At the University's Human Resource Management Directorate office number 101
@lawsocieties
@lawsocieties https://t.me/lawsocieties
ጋብቻ በንብረት በኩል ስለሚኖረው ውጤት
♨️🛑♨️♨️♨️♨️♨️🛑🛑🛑👇
ጋብቻ ከሚያስከትላቸው ሕጋዊ ውጤቶች አንደኛው በንብረት ወይም በሀብት ላይ የሚያስከትለው ውጤት ነው፡፡ ማንኛውም ሰው የፈለገው ስራ ላይ ተሰማርቶ ሀብትና ንብረት ማፍራት መብት እንዳለው በህገ መንግስታችን አንቀጽ 41(1)ና(2) ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ሰው የፍላጎቱ በሆነ ስራ ላይ ተሰማርቶ ሀብትና ንብረት ማፍራት ይችላል፡፡በዚሁ መሠረት አንድ ሰው ወደ ጋብቻ ከመግባቱ በፊት በላቡና በወዙ ሰርቶ ያገኘው ወይም በስጦታ ወይም በውርስ ያገኘው ሀብትና ንብረት ሊኖረው ይችላል፡፡ይህን ከትዳሩ በፊት ያገኘውን ሀብትና ንብረት ወደ ትዳር ሲገባ የግል ንብረቱ ሆነው ይቀጥላል፡፡በትዳሩ ውስጥ ከገባ በኋላም ለግሉ በስጦታም ወይም በውርስ ያገኘው ንብረት የግል ንብረት ሆኖ ይቀጥላል፡፡ነገር ግን ተጋቢዎች የግል ንብረታቸው የሆነውን የጋራ ንብረት ነው በማለት ሊስማሙ ይችላሉ፡፡
ተጋቢዎች ትዳር የሚፈጽሙ እስከ መጨረሻው አብሮ ለመኖር መሆኑ እሙን ነው፡፡ በዚህ በትዳር ባሉበት ጊዚያት በግል ንብረትነት ይዘዋቸው ያሉ ንብረቶችን መሸጥ መለወጥ አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህ የግል ንብረቶችና ሀብቶችን በመሸጥ ወይም በመለወጥ የሚገኘው አዲስ ንብረትና ሀብት የግል ንብረት ይሆናል፡፡ ነገር ግን እነዚህ በግል ሀብት የተገዙ ወይም የተለወጡ ንብረቶች የግል ሀብትና ንብርት እንደሆኑ የግል ንብረቱ ባለቤት ለፍ/ቤት የግል ይባልልኝ በማለት ጥያቄ ማቅረብ እና ማፅደቅ አለበት፡፡ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 58(1)ና(2) ይህን ይገልፃሉ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በአንቀጽ 62/2/ መሠረት የጋራ ንብረት ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 37275 ላይ ነአመልካች ሻ/ባሻ ገዛኸኝ ድልነሳው እና ተጠሪ ወ/ሮ ተዋበች ደመቀ መካከል በነበረው ክርክር የአመልካች የግል ንብረት የነበረ ቤት በትዳር ባሉበት ጊዜ ሽጠው በተሸጠው ገንዘብ ሌላ አዲስ ቤት ገዝተዋላል ነገር ግን አመልካች አዲስ የገዙትን ቤት የግል ይባልልኝ በማለት ጥያቄ ለፍርድ ቤት ያላቀረቡ እና ያላጸደቁ በመሆነ የጋራ ንብረት ነው በማለት ወስኖል፡፡
ኑሮ በትዳር ውሰጥ የጋራ ቢሆንም ከላይ በተገለጸው መልኩ ተገቢያዎቹ የግል ንብረቶቻቸውን ይዘው በትዳር በመቀጠል ይችላሉ፡፡ በዚህ ጊዜ እነዚህ ንብረቶችም የሚተዳደሩት በግል የንብረቱ ባለቤት በሆነው ሰው ነው፡፡ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 59 ላይ እያንዳንዱ ተገቢ የግል ሀብቱን እራሱን ለማስተዳደርና ገቢውንም ለመቀበል ይችላል፡፡ እንዲሁም የግል ሀብቱን ራሱ ሊያዝበት ነፃነት አለው በማለት ይገልፃል፡፡ ነገር ግን የግል ንብረቱ ባለቤት የሆነው አንደኛው ተገቢ የግል ንብረቱን በሙሉ ወይም በከፊል ሌላኛው ተጋቢ እንዲያስተዳድርለት እና እንዲያዝበት በጋብቻ ውላቸው ሊወሰን ይችላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ የግል ንብረቱ ባለቤት የሆነው ተጋቢ ሌላኛውን ተጋቢ ስለንብረቱ አስተዳደር ዓመታዊ የሂሳብ መግለጫ መጠየቅ ይችላል፡፡ ይህ ሲሆን ሌላኛው ተጋቢ ሲጠይቅ የይህንኑ የመስጠት ግዴታ አለበት (የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 60(2) )፡፡ እንዲሁም ከተጋቢዎቹ አንዱ የግል ንብረቱንና ሀብቱን በሙሉ ወይም በከፊል እንዲያስተዳድርለት ለሌላኛው ተጋቢ ውክልና መስጠት እንደሚችል በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 61 ላይ ተቀምጧል፡፡
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው በጋብቻ ውስጥ ተጋቢዎች የግል ንብረት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ይህን ንብረት በዋንኛነት የንብረቱ ባለቤት የሚያዝበትና የሚስተዳድረው መሆኑን እንዲሁም የግል ንብረቱ ባለቤት የሆነው አንደኛው ተጋቢ ሌላኛው ተጋቢ እንዲያስተዳድርለት በጋብቻ ውል ወይም በውክልና መስጠት እንደሚችል ተረድተናል፡፡(በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ከአንቀጽ57-61)
ተጋቢዎች በትዳር ከተሳሰሩበት እለት ጀምሮ ህይወታቸውን በጋራ ሲመሩ የጋራ ንብረት ማፍራታቸው አይቀሬ ነው፡፡በጋብቻ ውላቸው ተጋቢዎች ከትዳር በፊት የነበራቸውን የግል ንብረት የጋራ ንብረት ማድረግም ይችላሉ፡፡በጥቅሉ በትዳር ዘመናቸው ተጋቢዎች የግል ንብረትና ሀብት እንደሚኖራቸው ሁሉ የጋራ ንብረትና ሀብት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ከተሻሻለው የቤተሰብ ህጋችን አንቀጽ 57 እና 58 ለመገንዘብ የምንችለው ነገር በትዳር ውስጥ የተፈሩ ሀብቶችና ንብረቶች ፣ ለተጋቢዎቹ በጥቅሉ በውርስ ወይም በስጦታ የተሰጡአቸው ሀብትና ንብረቶች በተጨማሪም የግል ሀብትና ንብረት ተሸጦ ወይም ተለውጦ የተገኘ ንብረት ሆኖ የግል ንብረቱ ባለቤት በፍርድ ቤት ቀርቦ የግል ንብረት መሆኑን ያላጸደቃቸው ንብረቶችና ሀብቶች ሁሉ የጋራ ንብረት እንደሆኑ ይቆጠራል፡፡ከዚህ በተጨማሪ በአንቀጽ 62(1) ላይ ባልና ሚስት ከግል ጥረታቸውና ከግል ወይም ከጋራ ንብረታቸው የሚያገኟቸው ገቢዎች ሁሉ የጋራ ሀብቶቻቸው እንደሚሆኑ ይገልፃል፡፡የግል ንብረት የግል ቢሆንም ከንብረቱ የሚገኝ ገቢ ግን የጋራ ነው፡፡
የንብረት ባለቤትነት የሚገለጹባቸው መንገዶች የተለያዩ ናቸው፡፡ በሀገራቸን የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች እንደ ቤቶችና መኪና የመሳሰሉት ባለቤትነታቸው የሚረጋገጠው በባለቤትነት የምስክር ወረቀት ነው፡፡ በጋብቻ ውስጥ የተጋቢዎች የጋራ ንብረት በአንደኛው ተጋቢ ስም ብቻ ተመዝግቦ ሊገኝ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ አንደኛው ተጋቢ የግል ሀብቱ መሆኑን ካላስረዳ በስተቀር ማንኛውም ንብረት በአንደኛው ተጋቢ ስም ብቻ የተመዘገበ ቢሆንም እንኳን የጋራ ሀብት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡(የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 63(1))
ባልና ሚስት በትዳር ዘመናቸው ወቅት የሚገኘውን ገቢ እያንዳንዳቸው በየራሳቸው ይቀበላሉ፡፡ገቢ ማለት በዚህ አነጋገር ደመወዝ ፣ ከግል ንብረት የሚመነጭ እንዲሁም ከጋራ ንብረት የሚመነጭ ማለት ነው፡፡ በግል የመነጨውን ገቢ የሚቀበለው የገቢው ምንጭ የሆነው ተጋቢ ነው፡፡ ነገር ግን ሌላኛው ተጋቢ ሲጠይቅ ገቢውን የተቀበለው ተጋቢ ያገኘውን የገቢ መጠን ማሳወቅ ግዴታ እንዳለበት በቤተሰብ ሕጉ አንቀፅ 64(3) ላይ ተገልፃል፡፡ የገቢው ምንጭ አንደኛው ተጋቢ ቢሆንም የጋራ ሀብት ስለሆነ ሌላኛው ተጋቢ የማወቅ መብት ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ተጋቢዎቹ ከፈለጉ በየግላቸው የሚገኙትን ገቢ የጋራ የባንክ ሂሳብ በመክፈትማስቀመጥ ይችላሉ፡፡እዚህ ጋር መታወቅ ያለበት በመርህ ደረጃ የገቢው አመንጪ ገቢውን ቢቀበልም በልዩ ሁኔታ (exceptionally) ግን ሌላኛው ተጋቢ ገቢውን ሊቀበል ይችላል፡፡ይህ የሚሆነው በሁለት መልኩ ነው፡፡አንደኛው የገቢው አመንጪ የሆነው ተጋቢ ለሌላኛው ተጋቢ በውል ገቢውን እንዲቀበል ሲፈቅድለት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በፍ/ቤት ትዕዛዝ ነው ፡፡ይህ በፍ/ቤት የሚሰጠው ትዕዛዝ ከባልና ከሚስት አንደኛው ስጠይቅ ነው፡፡በሌላ በኩል ደግሞ ገቢው በሙሉ ወይም በከፊል እንዲከበር በፍ/ቤት ሊታዘዝ ይችላል ፡፡ እዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባው ነገር በሌላ ህጎች መከበር የሌለባቸው ገቢዎችና ንብረቶች የማይከበሩ መሆኑን ነው፡፡ለምሳሌ የጡረታ አበል ሊከበር እንደማይቸል የጡረታና በሌሎች ህጎች የተመለከተ ነው፡፡እንዲሁም በፍታብሄር ስነስርዓት ሕጉም ውስጥ ሊከበሩ የማይችሉ የንብረት ዓይነቶችና የደመወዝ መጠን በአንቀፅ 404 ላይ ተገልፆል ይገኛል፡፡
በኢፌዲሪ ህገመንግስት አንቀፅ 34(1) ላይ ተጋቢዎች በትዳር ዘመናቸው በሁሉ ነገር ላይ እኩል መብት እንዳላቸው ይገልፃል፡፡ እንዲሁም በአንቀፅ 35(7) ላይ ሴቶች ንብረት በማስተዳደር ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው በማለት ደንግጎአል፡፡ እነኚህ የህገ መንግስቱ መርሆች በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 66(1)ላይ በማካተት ባልና ሚስቱ የጋራ ሀብታቸውን በጋራ ያስተዳድራሉ በማለት ገልጾታል፡፡ ስለዚህም በመርህ ደረጃ ባልና ሚስት የጋራ ንብረታቸውን በጋራ ያስተዳድራሉ፡፡ነገር ግን ባልና ሚስቱ በስምምነት የጋራ ንብረታቸውን አንዳቸው እንዲያስተዳድሩ ማድረግ ይችላሉ፡፡ይህም በውል ለአንደኛው ወገን እንዲያስተዳድር ሲሰጥ ነው፡፡ በተለያየ አጋጣሚ (ምክነያት) ከተጋቢዎች አንዱ ችሎታ ሲያጣ ወይም ንብረት የማስተዳደር መብቱ በፍ/ቤት ሊገፈፍ ይችላል፡፡ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሌላኛው ተጋቢ ንብረቱን የማስተዳደር ተግባር ያከናውናል፡፡ በውልም ሆነ ንብረት የማስተዳደር መብቱ በመገፈፉ ወይም ችሎታ በማጣቱ አንደኛው ተጋቢ ንብረቱን በሚያስተዳድርበት ጊዜ ሌላኛው ንብረቱን የሚያስተዳድረው ተጋቢ የንብረቱን አስተዳደር በተመለከተ ለሌላኛው ተጋቢ መረጃ የመስጠት ግዴታ እንዳለበት በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 67 ላይ ተቀምጧል፡፡
ተጋቢዎች በትዳር ተሳስረው የጋራ ንብረት አፍርተው ሲኖሩ ይህን የጋራ ንብረት በጋራ ማስተዳደር እንዳለባቸው ከላይ በተገለጸው መልኩ ለመረዳት ችለናል፡፡ እነዚህን የጋራ ንብረቶች ተጋቢዎቹ በጋራ በሚያስተዳድሩበት ወቅት ንብረቱን መሸጥ መለወጥ ያስፈልጋቸው ይሆናል፡፡ ይህ ጋራ ንብረት መሸጥ መለወጥ ከፈለጉ በሌላ የሕግ የተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር የተጋቢዎቹ የጋራ ስምምነት አስፈላጊ ነው፡፡ በአንቀጽ 68 የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው የጋራ ንብረትና ሀብት ወደሌላ ሶስተኛ ወገን በሽያጭ ሆነ በስጦታ የሚቀየረው በተጋቢዎቹ የጋራ ስምምነት ብቻ መሆኑን ይገልፃል፡፡ እዚህ ላይ በጋራ ንብረት የሆነውን አንደኛው ተጋቢ ሌላኛውን ተጋቢ ፈቃድ ወይም ስምምነት ሳያገኝ ብቻውን ለሌላ 3ኛ ወገን በሽያጭም ሆነ በሌላ መንገድ ቢያስተላልፍ ሌላኛው ተጋቢ ለፍርድ ቤት በሚያቀርበው ጥያቄ ግዴታው እንዲፈርስ መጠየቅ ይችላል፡፡ ይህ ግዴታ እንደፈረሰ የሚጠይቀው ተጋቢ ለፍ/ቤት ጥያቄውን የሚያቀርበው ግዴታው መገባቱን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ወይም በሌላ በማንኛውም ሁኔታ በ2 አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ይህ የተባለው ጊዜ ካለፈ ይህን ጥያቄ ማቅረብ እንደማይቻል በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 69(2) ላይ ተገልፆል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 38126 በአመልካች ዲያቆን ኃ/ጊዮርጊስ ወንድም እና ተጠሪዎች እነ የሺ ተፈሪ መካከል በነበረው ክርክር የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ባለቤት ከሆኑት የጋራ ንብረታቸው የሆነውን ቤት ለአሁኑ አመልካች በ01/03/1995 ዓ.ም ያለ 1ኛ ተጠሪ ፍቃድ ይሸጥለታል፡፡ 1ኛ ተጠሪም በስር ፍርድ ቤት ውሉ ያለ እሳቸው ፍቃድ የተፈጸመ በመሆኑ እነዲፈርስ በማለት በ09/08/1999 ዓ.ም ክስ ታቀርባለች፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የሰበር ችሎት የአሁን 1ኛ ተጠሪ የሆነችው ክስ ያቀረበችው በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 69/2/ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ማለትም ሽያጩን ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ወይም በማንኛውም ሁኔታ በ2 አመት ጊዜ ውስጥ ክሶን ያላቀረበች ስለሆነ (ክሶን ያቀረበችው ከ4 አመት በሆላ ነው) ውሉ እንዲፈርስ ክስ የማቅረያ ጊዜ አልፎል፡፡ ስለሆነም ውሉ አይፈርስም በማለት ውሳኔ ሰጥቶላ፡፡
የሰው ልጅ በዚህ ምድር ላይ ሲኖር እለት በለት ኑሮውን ለመደጎም ወጪዎችን ያወጣል፡፡ በትዳር ውስጥም ተጋቢዎ ትዳራቸውን ለማቃናትና ዘላቂነቱን ለማስቀጠል የተለያዩ ወጪዎች ማውጣታቸው የማይቀር ሀቅ ነው፡፡ በመሆኑም ተጋቢዎች የትዳራቸውን ወጪ ለመሸፈን እያንዳንዳቸው እንዳቅማቸውና ችሎታቸው አስተዋፅኦ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡ የህይወት መንገድ ሁልጊዜም አልጋ በአልጋ አይሆንም ውጣ ውረድ በህይወት ውስጥ ማጋጠሙ አይቀርም፡፡ በዚህ ጊዜ ወደ ብድር እና እዳ መገባት ሊያጋጥም ይችላል፡፡ በትዳር ውስጥም ተጋቢዎቹ ለግላቸው ወይም ለትዳራቸው ሲሉ እዳ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ ይህ በሆነበት ጊዜ እዳውን ለመክፈል እዳው ለግል የተወሰደ ከሆነ ከባለእዳው ተጋቢ የግል ሀብት ይሸፈናል፡፡ ነገር ግን የግል ሀብቱ ይህን ለመሸፈን የማይችል ከሆነ ተጋቢዎች የመረዳዳትና የመተጋገዝ ግዴታ ስላለባቸው ይህ እዳ ከጋራ ሀብታቸው ይከፈላል፡፡ እዳው ግን ለትዳራቸው ጥቅም ከሆነ ከጋራ ሀብታቸው የሚከፈል ይሆናል፡፡ ነገር ግን የጋራ ሀብቱ በቂ ካልሆነ ከተጋቢወቹ የግል ሀብት ይከፈላል፡፡
#legalconsulting limited
@lawsocieties
@lawsocieties https://t.me/lawsocieties
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ጉዲፈቻን አስመልክቶ የህግ ትርጉም ሰጠ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ሰበር ችሎት መጋቢት 02 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት የውጭ ሃገር ጉዲፈቻን በተመለከተ የቀድሞ የቤተሰብ ህግ ደንጋጌን ያሻሻለው አዋጅ ቁጥር 1070/2010 ላይ በመዝገብ ቁጥር 189201 አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ታሪኩ በአጭሩ እንዲህ ቀርቧል፡፡

የውሳኔ ግልባጩን በቴሌግራም ገጻችን

በትዉልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት አሜሪካዊ የሆኑት ወ/ሪት ጥሩነሽ በቀለ ስዩም የወይዘሮ ወይንሸት ደስታ እህት ናቸው፡፡ ወ/ሪት ወይነሽነት በሚኖሩበት ሃገር ሆነው የእህታቸውን የወ/ሮ ወይንሸት ደስታ እና የአቶ ወንድወሰን ታደሰ ልጅ የሆነችዉን ተማሪ ኤፍራታ ወንድወሰንን ወላጆቿ ሊያደርጉላት የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ አሳድገዋል፡፡ በአሜሪካን ሃገር ኤፍራታ ልጃቸው መሆኗን የሚያረጋግጡ ፎርማሊቲዎችን አሟልተው በህጋዊ መንገድ ለመውሰድ እና ለማሳደግ ወደ ተውልድ ሃገራቸው ኢትዮጵያ ይመጣሉ፡፡ ከወላጅ እናትና አባቷ ጋርም የጉዲፈቻ ውል ይገቡና ውሉን የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እንዲያጸድቅላቸው ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ ፍርድ ቤቱም የቀረበውን የጉዲፈቻ ውል ይጽደቅልኝ ጥያቄን የተሻሻለዉ የቤተሰብ ህግና የዉጪ አገር የጉዲፈቻን የሚከለክለውን አዋጅ ቁጥር 1070/2010 በመጥቀስ ወሉን ባለማጽደቅ መዝገቡን ይዘጋል፡፡

አመልካች ወ/ሪት ጥሩነሽ በቀለ ጉዳዩን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ እንዲመለከትላቸው አቤቱታቸዉን ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል የፌዴራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማጽደቅ በተመሳሳይ ውሳኔ አሰናብቷቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ወ/ሪት ጥሩነሽ ሁለቱ ፍርድ ቤቶች የጉዲፈቻ ዉሉን ላለመቀበል መሰረት ያደረጉት አዋጅ 1070/2010 የውጭ ሃገር ጉዲፈቻን ሲከለክል የውጭ ሃገር ተውልድ እና ዜግነት ያላቸውን እንጂ ትውልደ ኢትዮጵያንን አያካትትም፡፡

የህጉ ዓላማ ትውልደ ኢትዮጵያንን (ዳያስፖራን) ታሳቢ ያደረገ አይደለም፡፡ ይህንን መከራከሪያቸውንም ለመደገፍ መንግስት ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ልማትና ኢኮኖሚ፤ በንግድና ኢንዱስትሪ እና በሌሎች ጉዳዮች እንዲሳተፉ በርካታ ፖሊሲዎችን፤ ደንቦችን አውጥቷል፡፡ ከቤተሰብ ህጉ የጉዲፈቻ ጉዳይን የሚመለከቱ አንቀጾችን ያሻሻለው አዲሱ አዋጅ የውጪ ሃገር ጉዲፈቻን ሲከለክል ለህጻናቱ ደህንነትና ጥቅም፤ ህፃናት በማያዉቁት ቋንቋና ባህል እንዲያድጉ በመደረጋቸዉ ለማንነት ቀዉስ፣ ለስነ-ልቦና እና ማህበራዊ ችግር እንዳይጋለጡ ለማድረግ ነው፡፡

የህጉ መንፈስ ይህ ሆኖ ሳለ ወ/ሮ ጥሩነሽ በጉዲፋቻ ከሚወስዷት ታዳጊ ጋር ተመሳሳይ ቋንቋ እና ባህል ያላት እንዲሁም በሚኖሩበት ሃገር ቁጥሩ ብዙ የሆነ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያው ያሉበት በመሆኑ ታዳጊዋ ለተጠቀሰው ችግር ተጋላጭ አትሆንም በማለት የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት የህግ ትርጉም ስህተት ያለው በመሆኑ እንዲታረምላቸው ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ችሎት አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡

ሰበር ችሎቱም የተሸሻላው አዋጅ ቁጥር 1070/2010 ዓ.ም የውጭ ሃገር ጉዲፈቻን ሲከለክል ዓላማው ምን ነበር? ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ያካትታል ወይስ አያካትትም? የሚለውም ጭብጥ ይዞ ጉዳዩን መርምሯል፡፡ ችሎቱ ከዳያስፖራ ጋር የተያያዙ ድንጋጌዎችን ይዘትና ዓላማ ጎን ለጎን ተመልክቷል፡፡ በምርመራ ሂደቱ አዋጁ የውጭ አገር ጉዲፈቻን ሲከለክል ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን አያካትትም በማለት በግልጽ አላስቀመጠም፡፡ ይሁን እንጂ የህግ አውጪው መሰረታዊ ሃሳብ የህጻናቱን ደህንነትና ጥቅም ማስጠበቅ እና በጊዲፈቻ በመሰጠታቸው ምክንያት ሊደርስባቸው ከሚችል የማንነት ቀዉስ፣ የስነ-ልቦና እና የማህበራዊ ችግር መከላከል ነው፡፡ መንግስት ትውልደ ኢትዮጵያውያን በብዙ መልኩ እንዲሳተፉ ጥረት እያደረ መሆኑ እየታወቀ ጉዲፈቻን አስመልከቶ አነሱን ለማግለል ታሳቢ አድርጎ የወጣ ድንጋጌ ነው ለማለት አይቻልም፡፡ በዚህ አግባብ ድንጋጌው ትውልደ ኢትዮጵያንን የሚያካትት አይደለም፡፡

በተጨማሪም ታዳዲዋ ኢትዮጵያዊ ማንነቷን ይዛ በመልካም ስብዕና ለማደግ ምቹ ሁኔታ መኖሩ መልካም አጋጣሚ ሆኖ እያለ የኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራዎች በሃገር እድገትና ብልጽግና እንዲሁም ለወገኖቻቸው ኑሮ መሻሻል ያላቸውን ሚና ባለመገንዘብ የህጻኗን የደህንነት ቀደምትነት መብት በመንፈግ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት ሰበር ችሎቱ ወስኗል፡፡ የስር ፍርድ በቶች የሰጡትን ውሳኔ ሽሯል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም መዝገቡን እንደገና ከፍቶ መስፈርቱ መሟላት አለመሟላቱን በማጣራት ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትn
The Federal Supreme Court of Ethiopia
@lawsocieties
@lawsocieties https://t.me/lawsocieties
Federal Courts Proclamation 1234-2013.pdf
1 MB
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 በነጋሪት ጋዜጣ የታተመ ዋናው ቅጂ
Associate Legal Expert

Date: Jun 8, 2021

Location: Ethiopia, Ethiopia

Organization: African Union Commission - AUC

AU Values

• Respect for Diversity and Team Work • Think Africa Above all

• Transparency and Accountability • Integrity and Impartiality

• Efficiency and Professionalism • Information and Knowledge Shari
Organization Information

Reports to: Project Coordinator – HCSS
Directorate: Office of the Legal counsel
Division: Hybrid Court for South Sudan (HCSS)
Number of Direct Reports: 0
Number of Indirect Reports: 0
Job Grade: P2
Location: Addis Ababa, Ethiopia (with frequent travel to South Sudan)
Purpose of Job

Under the direct supervision of the Project Coordinator, the incumbent will be responsible to properly translate documents, ensure the highest standard of accuracy, and maintain the spirit, context, quality, technical language and nuances of the original version, using precise, clear and proper terminology. He/She will also be responsible to draft regulations, delegations, agreements and other instruments necessary to fulfil the vision and support the implementation of the Hybrid Court for South Sudan.
Main Functions

Assist in the following up on the activities of the HCSS, including monitoring and evaluating progress made in line with a predefined strategic plan.
Suggest new and expand on existing policy areas for planned research.
Contribute in conducting analysis and generate accurate reports in a timely manner for the HCSS internal use.
Assist in setting the overall research direction of a relevant policy area.
Responsible for the delegation and execution of defined research areas.
Participate in the organisation of relevant meetings, congresses and conferences with stakeholders.
Engage with relevant mid-level stakeholders and develop working relationships.
Support the promotion of the activities of the HCSS.
Assist in drafting reports and participate in the preparation of budget and work programmes related to the functioning of the HCSS
Provide technical support to internal and external stakeholders.

Specific Responsibilities

Under the direct supervision of the Project Coordinator, the Associate Legal Expert will be responsible for the following duties:
Assist in drafting internal procedures, protocols and directions for the Court;
Prepare or work on draft Rules of Procedure and Evidence, if necessary, under the guidance of the Senior Legal Expert;
Prepare, in co-ordination with and under the guidance of the Senior Legal Expert, draft Practice Directions on court procedures, including court filings, as may be required;
Provide input and assistance to the Project Coordinator and Senior Legal Experts in developing and drafting other directives, policies, codes and procedures as necessary;
The selected staff member should be willing to be located either in Juba or in Addis Ababa; and
Undertake any other related tasks as requested by the Legal Counsel or Project Coordinator.


Academic Requirements and Relevant Experience

University Bachelor Degree in International Criminal Law/Public International Law with 5 years’ experience as practicing lawyer, legal or special advisor in the fields of justice, rule of law, criminal or international law.
Candidates with a Masters Degree in in International Criminal Law/Public International Law from a recognized institution must have 2 years’ experience as practicing lawyer, legal or special advisor in the fields of justice, rule of law, criminal or international law.
Experience as a legal/special advisor in an international or hybrid criminal tribunal or court is an added advantage;

Required Skills
Proven knowledge of international criminal substantive, criminal procedural case law at international or hybrid criminal tribunals or courts;
In-depth theoretical knowledge of criminal law (both substantive and procedural), including knowledge of international legal procedures and instruments;
Demonstrated ability to find creative and pragmatic solutions in a demanding, dead-line driven environment and to establish and maintain effective, constructive working relationships with people from different national and cultural backgrounds.
Previous experience as a legal advisor during the planning or start-up phase of a court;
Previous experience drafting or amending Rules of Procedure or internal court administration or process documents;
Experience in applying expertise to analysing a diverse range of complex and unusual legal issues and problems, and in developing innovative and creative solutions;
International experience, particularly in crisis areas with multi-national and international organisations;
Good understanding of the political, cultural and security situation of the Horn of Africa, in particular South Sudan;
Ability to perform under hardship and strenuous environment; and
Very good interpersonal and communication skills, both written and oral, in Arabic and English;
Knowledge of other working language of the AU or of the local languages of South Sudan.


Leadership Competencies
Change Management .
Managing Risk.
Core Competencies
Teamwork and Collaboration.
Accountability awareness and Compliance.
Learning Orientation.
Communicating with Influence.
Functional Competencies
Analytical thinking and problem solving.
Job Knowledge and information sharing.
Drive for result.
Continuous improvement focus.

TENURE OF APPOINTMENT:

The Appointment will be made on a fixed term contract for a period of one (1) year, of which the first three (3) months will be considered as a probationary period. Thereafter, the contract may be renewed for a similar period subject to funding availability, satisfactory performance and agreed deliverables.

GENDER MAINSTREAMING:

The AU Commission is an equal opportunity employer and qualified women are strongly encouraged to apply.

REMUNERATION:

The salary attached to the position is an annual lump-sum of US$ 85,212.07 (P2 Step 5) inclusive of all allowances for internationally recruited staff, and US$ 66,751.81 inclusive of all allowances for locally recruited staff of the African Union Commission.

Applications must be made not later than 9 July 2021.
ምክር ቤቱ የፌደራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ - Fana Broadcasting Corporate S.C አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ጉባኤው የፌደራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አፅድቋል፡፡

ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳቡን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አቡ ብርኪ÷ ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ለዝርዝር እይታ ወደ ቋሚ ኮሚቴው በተለያዩ ጊዜያት ከአስረጂዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገበትና በቂ ግብዓትም የተገኘበት መሆኑን ለምክር ቤት አስረድተዋል፡፡

በውይይቱም የጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አገልግሎት ላይ ሰፊ የህግ፣ የአሰራር፣ በአንዳንድ ጠበቆች ላይ የብቃትና የስነ-ምግባር ችግሮች እየተስተዋሉ መምጣቱን በጭብጥነት መለየታቸውን አብራርተዋል፡፡

አያይዘውም የጥብቅና ፍቃዱ ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር መሆኑ አገልግሎቱ በሚጠበቅበት ደረጃ እንዳያድግና የሙያ ነጻነቱን በጠበቀ መልኩ አገልግሎቱ እንዳይሰጥ ማድረጉን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የጥብቅና ህጎች ሀገሪቱ ካለችበት አጠቃላይ ኢኮኖሚዊ፣ ማህበራዊና ፓለቲካዊ እንቅስቃሴዎች አንጻር ሊኖሯት የሚያስፈልጉ የጥብቅና ድርጅቶችን በተደራጀ ሁኔታ የሚመሩ ጠበቆች አለመሆናቸውን በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡

በረቂቅ አዋጁም አንዳንድ አንቀጾችን ሙሉ በሙሉ በሌሎች አንቀጾች ከመተካት ጀምሮ በርካታ ማሻሻያዎች መደረጋቸውንም ነው ባቀረቡት ሪፖርት የጠቆሙት፡፡

በመጨረሻም የፌደራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳዳር ረቂቅ አዋጅ የሀገሪቱን ዜጎች ፍትህ የማግኘት እና የህግ የበላይነት በማረጋገጡ ሂደት ጠበቆችና የጥብቅና ድርጅቶች የሚኖራቸው ድርሻ የጎላ እንዲሆን እንዲሁም የጠበቆችን ብቃትና የስነ ምግባር ችግር የሚፈታ፣ መብትና ነጻነት የሚስጠብቅ፣ የተገልጋዮችን መብት የሚስከብር በመሆኑ ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን እንዲያፀድቀው የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ የፌደራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳዳር ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1249/2013 ዓ.ም አድርጎ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።