አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የጥብቅና ፈቃድ አስተዳደር እና ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የሚያከናውናቸው ተግባር ወይም የሚሰጣቸው አገልግሎቶች እና ኃላፊነቶች
***
1. በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ደረጃ የጥብቅና አገልግሎት ለሚሰጡ ጠበቆች በሕግ መሠረት ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤ ጠበቆችንና የጥብቅና አገልግሎትን ያስተዳድራል፣ይቆጣጠራል፤

2. የጠበቃ ረዳትና የሕግ ጉዳይ ጸሐፊ ይመዘግባል፣ ለሚመለከተው ያሳውቃል፣

3. በጠበቆች ላይ የዲስኘሊን ክስ ያቀርባል፣ ከተገልጋዮች የክስ አቤቱታ ይቀበላል፣ ወክሎ ክስ ለጉባኤ ያቀርባል፣ እስከ ሰበር ይከራከራል፣ ውሳኔዎች ያስፈፅማል፣

4. የጠበቆች የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የሙያና የስነ-ምግባር ብቃት ለማሳደግ፣ ከሚመለከታቸው ጋር ይሰራል፣

5. የጥብቅናው ዘርፍ የአገልግሎት አሰጣጥና የስነ-ምግባር ሁኔታ የተገልጋዮች/ደንበኞች አመኔታ እያረጋገጠ ስለመሆኑ ይከታተላል፣

6. የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ስትራቴጂ አፈፃፀም በመስኩ የሚሰማሩ አካላትን ያስተባብራል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣

7. የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ስርዓት ይዘረጋል አፈፃፀሙን ይከታተላል፣

8. የገንዘብ አቅም የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የሕግ ምክርና የጥብቅና አገልግሎት እንዲያገኙ ለጠበቆች ይመራል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡

የስራ ክፍሉ በዋና መስሪያ ቤቱ ህንጻ እድሳት ምክንያት ፒያሳ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊት ባለው ግዙፍ ህንጻ 6ኛ ፎቅ ላይ መደበኛ አገልግሎቱን እየሰጠ መሆኑን እየገለጽን በቀጣይ ወደ ዋናው መስሪያ ቤት ሲመለስ በፍጥነት የምናሳውቃችሁ ይሆናል፡፡
“የአገር መከላከያ ሀይልን መጉዳት ከ5 ዓመት እስከ 25 ለመድረስ በሚችል ፅኑ እስራት ወይም ነገሩ እጅግ ከባድ በሆነ ጊዜ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ወይም በሞት ይስቀጣል፡፡”

በአገር ላይ የፈፀሙ ወንጀሎች የሚያስከትሉት ቅጣት
መንግስት የህዝቦቹን ሰላም እና ደህንነት የመጠበቅ እንዲሁም ህግን የማስከበር ሀላፊነት የሚወጣ ቢሆኑም በተለያዩ ሁኔታዎች በሀገር ላይ ወንጀሎች ሊፈፀሙ ይችላሉ፡፡የእነዚህ ወንጀሎች መፈፀም በአጠቃላይ በማህበረሰቡ ሰላም፣ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ህይወት ላይ ጉዳት ማስከተሉ አይቀሬ፡፡በመሆኑም መንግስት የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ አስቀድሞ የመከላከል ተፈፅመው ሲገኙም ህግን የማስከበር ሀላፊነት አለበት፡፡በአገር ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ ሶስተኛ መፅሐፍ በመንግስት፣በአገርና በዓለም አቀፍ ጥቅሞች ላይ የሚደረጉ ወንጀሎች በሚል ስር ተካቶ ይገኛል፡፡

በዚህ አጭር የንቃተ ህግ ፅሁፍ በአገር ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እና የሚያስከትሉትን የወንጀል ቅጣት እንዳስሳለን፡፡

በህገ መንግስትና በህገ መንግስት ሥርዓት ላይ የሚደረጉ ወንጀሎች በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ አንቀፅ 238 ስር እንደተደነገገው ማንም ሰው በኃይል፣በዛቻ፣በአድማ ወይም ህገ ወጥ በሆነ ማናቸውም መንገድ የፌደራሉን ወይም የክልልን ሕገ መንግስት ያፈረሰ፣የለወጠ ወይም ያገደ እንደሆነ ወይም በፌደራሉ ወይም በክልል ህገ መንግስት የተቋቋመውን ስርዓት ያፈረሰ ወይም የለወጠ እንደሆነ ከ3 ዓመት እስከ 25 ዓመት ለመድረስ በሚችል ፅኑ እስርት ይቀጣል፡፡ወንጀሉ ሲፈፀም በሕዝብ ደህንነት ወይም ኑሮ ላይ ከፍተኛ ቀውስ ደርሶ እንደሆነ አድራጊው በዕድሜ ልክ እስራት ወይም በሞት ይቀጣል፡፡

የህገ መንግስታዊ ሥልጣንን ተግባራዊነት ማሰናከል ሌላው በወንጀል ህጉ የወንጀል ድርጊት ተብሎ የተፈረጀ ተግባር ሲሆን ማንም ሰው በሀይል ስራ፣በዛቻ፣ወይም ህገ ወጥ በሆነ ሌላ ማናቸውም መንገድ በፌደራል ወይም በክልል ሕገ መንግስት ስልጣን የተሰጠውን አካል ወይም ባለስልጣን ተግባሩን እንዳያከናውን ያደናቀፈ፣የከለከለ ወይም አስገድዶ ውሳኔ እንዲሰጥ ያደረገ እንደሆነ ከ15 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት ይቀጣል፡፡

የጦር መሣሪያ ይዞ በማመፅ፣ ወይም የእርስ በርስ ጦርነት በማስነሳት በመንግስት ላይ የሚደረግ ወንጀል(የወንጀል ህግ አንቀፅ 240) ማንም ሰው አስቦ በህገ መንግስት በተቋቋሙት አካላት ወይም ባለስልጣኞች ላይ ሕዝብ፣ወታደሮች ወይም ሽፍቶች የትጥቅ አመፅ እንዲያነሱ ያደራጀ ወይም የመራ እንደሆነ ወይም ዜጎችን ወይም በአገር ነዋሪ የሆኑትን በማስታጠቅ ወይም አንዱ ወገን በሌላው ላይ የጦር መሣሪያ እንዲያነሳ በማነሳሳት የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲነሳ ያደረገ እንደሆነ ከ10 ዓመት እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ይቀጣል፡፡እንዲሁም ድርጊቱ በሕዝብ ደህንነት ወይም ኑሮ ላይ ከፍተኛ ቀውስ ይስከተለ እንደሆነ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ወይም በሞት ይቀጣል፡፡

የአገሪቱን የፖለቲካ የግዛት አንድነት በመንካት የሚደረግ ወንጀል(የወ/ህግ አንቀጽ 241)
ማንም ሰው በኃይል ወይም በሌላ ማናቸውም ህገ መንግስትን የሚፃረር መንገድ፣በቀጥታ ወይም በእጅ አዙር፣ያገሪቱን ህዝቦች አንድነት እንዲፈርስ ወይም ፌዴሬሽኑ እንዲከፋፈል ወይም ከፌዴሬሽኑ ግዛት ከፊሉ እንዲገነጠል የሚያደርግ ተግባር የፈፀመ እንደሆነ ከ10 ዓመት እስከ 20 ዓመት ለመድረስ በሚችል ፅኑ እስራት ወይም ነገሩ ከባድ በሆነ ጊዜ በእድሜ ልክ እስራት ወይ በሞት ይቀጣል፡፡

የሀገሪቱን መንግስት እንዲሁም ያገሪቱን ምልክቶችና በመንግስት የታወቁ ሌሎች ምልክቶችን መድፈር ማንም ሰው በንግግር ወይም በአድራጎት ወይም በማናቸውም ሌላ አኳኋን በአደባባይ የሀገሪቱን መንግስት ያዋረደ፣የሰደበ፣ስሙን ያጠፋ ወይም በሀሰት የወነጀለ እንደሆነ ከሶስት ወር በማያንስ ቀላል እስራት ወይም ከ500 ብር በማያንስ መቀጮ ይቀጣል፡፡(የወ/ህግ አንቀፅ 244/1) እንዲሁም በተንኮል ፣በንቀት ወይም ይህንን በመሳሰለ በማናቸውም አሳብ በግልጽ የታወቀውን አንድ የአገር ምልክት ማለትም የፌደራላዊት ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ወይም አርማን እንዲሁም የክልላዊ መንግስት ሰንደቅ ዓላማን ወይም አርማን በአደባባይ የቀደደ፣ያቃጠ፣ያጠፋ፣ያበላሸ፣የሰደበ ወይም በማናቸውም ሌላ አኳኋን ያዋረደ እንደሆነ ከሦስት ወር በማያንስ ቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ይቀጣል፡፡(የወ/ህግ አንቀፅ 244/2)
በሀገር ነፃነት ላይ የሚደረግ ወንጀል ማንም ሰው፡-
 የሀገሪቱን ነጻነት አደጋ ላይ ለመጣል ወይም አገሪቱ ሉአላዊቷን እንድታጣ
 የሀገሪቱን ነፃነት አደጋ ላይ ለመጣል የውጪ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በመገፋፋት ወይም
 የውጪ መንግስት የጠላትነት ድርጊት በሀገሪቱ ላይ እንዲፈፅም ወይም ከውጪ ሀገር መንግስት ጋር ጦርነት እንድትዋጋ ወይም የጠላትነት ድርጊት እንድትፈፅም ፣በጠላትነት እንድትከበብ ወይም እንድትያዛ በማሰብ ማናቸውም ድርጊት ያደረገ እንደሆነ ከ5 ዓመት እስከ 25 ዓመት ለመድረስ በሚችል ፅኑ እስራት ወይም ነገሩ ከባድ ሲሆን በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ወይም በሞት ይቀጣል፡፡(የወ/ህግ 246) የአገር መከላከያ ሀይልን መጉዳት (የወ/ህግ አንቀፅ 247/ሀ/ለ/ሐ እና መ) የአገር መከላከያን ሀይልን መጉዳት በሀገር ላይ ከሚፈፀሙ ወንጀሎች አንዱ ሲሆን ማንም ሰው አስቦ፡-
ሀ/ ወታደራዊ ጠባይ ያለውን ወይም ለአገር መከላከያ እንዲሆን የታቀደውን ማናቸውንም የኢኮኖሚ ድርጅት፣የመከላከያ ስራ ተቋም ወይም ሥፍራ፣የመገናኛ ወይም የመጓጓዣ ዘዴ፣ሥራ፣ማከማቻ፣የጦር መሣሪያ ወይም ቁሳቁስ አሳልፎ በመስጠት ፣በማፍረስ፣የተንኮል ሥራ በመፈፀም ወይም ለአገልግሎት እንዳይውል በማድረግ
ለ/ ጠላት ለሆነ ለውጪ አገር መንግስት ወታደሮች በማቅረብ ወይም የኢትዮጵያ ዜጎች ለዚሁ ለጠላት አገር በወታደርነት እንዲያገለግሉ በመመልመል ወይም በማግባባት ወይም ራሱ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ለዚሁ ዓይነት የጠላት አገር መንግስት በመሰለፍ፣
ሐ/የጦር ወታደሩ የጦር አገልግሎት ከመፈፀም እምቢተኛ እንዲሆን፣ወታደራዊ አመፅ እንዲያስነሳ ወይም እንዲከዳ በግልፅ በማነሳሳት ወይም የጦር ወታደርነት ግዴታ ያለበት ሰው ከነዚህ ወንጀሎች አንደኛውን እንዲፈፅም በመገፋፋት ወይም እንዲነሳሳ በማድረግ ወይም
መ/ ለሀገር መከላከያ የሚያገለግሉትን ወታደራዊ የጥንቃቄ እርምጃዎች በማሰናከል ፣በማበላሸት ወይም በማናቸውም ሌላ ዘዴ የተንኮል ድርጊት በመፈፀም በኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ከ5 ዓመት እስከ 25 ዓመት ለመድረስ በሚችል ፅኑ እስራት ወይም ነገሩ እጅግ ከባድ በሆነ ጊዜ በተለይም በጦርነት ወይም ጦር አስጊ በሆነበት ጊዜ እንደሆነ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ወይም በሞት ይቀጣል፡፡
https://t.me/lawsocieties
የፌዴራል ዐቃቤ ህግ 1,500,000.00 ብር ጉቦ በመቀበል የሙስና ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ በተያዘው በገቢዎች ሚንስቴር የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት የኦዲት ዋና መሪ ላይ ክስ መሰረተ
***********

የፌዴራል ዐቃቤ ህግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ሙስና ወንጀል ችሎት በላከው የወንጀል ክስ ላይ ተከሳሽ መላኩ ሸዋረጋ ቤኛ ላይ በ2007 ዓ.ም በስራ ላይ የዋለውን የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 10 (2) ስር የተመለከተውን ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል በመተላለፍ በፈጸመው ወንጀል ክስ ማቅረቡን በክሱ አመላክቷል፡፡

ዐቃቤ ህግ በክሱ የወንጀል ዝርዝርም ተከሳሽ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ገቢዎች ሚንስቴር የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት የኦዲት ዋና መሪ ባለሞያ ሆኖ ሲሰራ በስራ ኃላፊነቱና ግዴታው ማድረግ የማይገባውን በማድረግ የማይገባ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ለሌላ ሰውም ለማስገኘት በማሰብ፣ ኸርበርግ ሮዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለው ድርጅት እ.ኤ.አ ከ2016 እስከ 2018 ላለው የግብር ዘመን የንግድ ስራ ትርፍ ግብር ብር 66,616,818.93 (ስልሳ ስድሰት ሚልዮን ስድስት መቶ አስራ ስድስት ሺ ስምንት መቶ አስራ ስምንት ብር ከዘጠና ሶስት ሳንቲም) እንዲከፍል በገቢዎች ሚንስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ሲወሰንበት የድርጅቱ የአስተዳደር ሰራተኛ በውሳኔው ላይ ለቅ/ጽ/ቤቱ ቅሬታ ሲያቀርብ ተከሳሹ አሰተዳደር ሰራተኛው ያቀረበውን ቅሬታ ውሳኔውን ዝቅተኛ በሆነ መልኩ መወሰን እንደሚቻል እና ለዚህም ብር 1,500,000.00 (አንድ ሚሊየን አምስት መቶ ሺ ) እንዲከፍል ጥቅም በመጠየቅ ከዚህ ክፍያ ውስጥ ብር 1,000,000.00 (አንድ ሚሊየን) በባንክ ለመቀበል ቀሪውን ደግሞ በጥሬ ገንዘብ ለመቀበል በመደራደር ከተስማማ በኋላ በቀን ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 አካባቢ በቦሌ ክፍለ ከተማ ካፒታል ሆቴል ውስጥ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺ) ሲቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘ በመሆኑ በፈፀመው ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል መከሰሱን አትቷል፡፡

የተከበራችሁ የገጻችን ተከታታዮች የክርክር ሂደቱን ተከታትለን መረጃ የምናቀብላቹሁ መሆኑን እንገልጻለን
የተከበራችሁ የገጻችን ተከታታዮች የክርክር ሂደቱን ተከታትለን መረጃ የምናቀብላቹሁ መሆኑን እንገልጻለን
https://t.me/lawsocieties
ሰላም አለ። እንዴት ሰነበትክ? የጠበቆች አስተዳደር ስልክ ቁጥር ይኖርሃል ? በፊት የነበራቸው ቁጥር አይሰራም። አሁን ላይ የሚጠቀሙበት ቁጥር ምናልባት ካለህ ብትልክልኝ?
የተምታታው የ‹ዘር ማጥፋት ወንጀል› አረዳድ በኢትዮጵያ!
በ:- ጥበቡ ኃይሉ

በዚህ ጽሁፍ፤ በዋናነት ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመጣስ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ምንነት በአጭሩ በማየት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የተምታታ የ‹ዘር ማጥፋት ወንጀል› አረዳድ መነሻ ምክንያት እና መፍትሔዎቹን ለመጠቆም ጥረት አደርጋለሁ፡፡

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/1975-confusing-understanding-of-genocide-in-ethiopia
Calling all changemakers! Apply for OD Impact Challenge 2021.

This is a global competition that recognizes and supports the efforts of young changemakers working to bring positive change to their communities.

Apply now to win cash prizes and an all-expenses paid trip to the Netherlands for a one-week mini-MBA course sponsored by Vantage Migration.

Details: https://bit.ly/ODIC2021call
Deadline: December 31, 2020

#ODIC2021 #ODImpactChallenge
የተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች ከፍ ያለ ስነ-ምግባር ተላብሰዉ መስራት ይኖርባቸዋል” ሲሉ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ተስፋዬ ዳባ ገለፁ፡፡
---------------------------------------------------------

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ተስፋዬ ዳባ ይህን ያሉት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከፍትህ ለሁሉም ፕሪዝን ፎሎ ሽፕ ኢትዮጵያ ጋር በጋራ ባዘጋጁትና የዐቃቤያነ ህግ ስብዕና ግንባታ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ለመካከለኛ አመራሮች በተዘጋጀዉ ስልጠና ላይ ተገኝተዉ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነዉ፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በተያዘዉ በጀት አመት የለዉጥ አጀንዳዎችን በመቅረፅ ጉልህ የሆነ ተቋማዊ ለዉጥን ለመፍጠር አየተጋ እንደሚገኝ የገለፁት ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ ከእነዚህ የለዉጥ አጀንዳዎች ዉስጥ አንዱ የዓቃብያነ ህግ የሙያ ማጎልበቻ እኒሼቲቭ መሆኑን በማስታወስ ለዚህም የተቋሙ ባለሙያዎችና አመራሮችን ሞያዊ ብቃት ማጎልበት ዋነኛዉ ተግባር መሆኑን አንስተዋል፡፡

ተቋሙ በእዉነትም ለህግ፣ ለፍትህና ለርትዕ የቆመ የህዝብ አገልጋይ ተቋም እንዲሆን የተቋሙ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዉ ተገቢዉ የሞያ ስነ ምግባር ያላቸዉ ባለሙያዎች ኑረዉት ተዐማኒነት፣ ቅልጥፍናና ዉጤታማትን የሚያሳድጉ ስርዐቶችን ዘርግቶ ሀላፊነቱን መወጣት ይችል ዘንድ የተቋሙ ባለሙያዎችና አመራሮች ከፍ ያለ የዐቃቢያነ ህግ ስብዕናና ስነ-ምግባር ተላብሰዉ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

የስልጠናዉ ዋና አላማ የዐቃብያነ ህግን ስብእና ለመገንባት የሚሰራ ስራ አካል ሆኖ ስብእናና ስነ ምግባርን ለማጎልበት የሚያስችል ሲሆን ከጉዳዩ ጋር በቀጥታ የሚገናኙ አለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ተሞክሮዎች የሚዳሰስበት መሆኑን የገለፁት አቶ ተስፋዬ ሰልጣኞች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አደራ በማለት ለስልጠናዉ መሳካት ድጋፍ ላደረገዉ ፍትህ ለሁሉም ፕሪዝን ፌሎ ሺፕ ኢትዮጵያ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የፍትህ ለሁሉም ፕሪዝን ፌሎ ሽፕ ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ፓስትር ዳንኤል ገብረስላሴ በበኩላቸዉ ፍትህ ለሁሉም ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ጋር በአቅም ግንባታ ስራዎችና በሌሎች ተግባራት ላለፉት በርካታ አመታት አብሮ መስራቱን ገልፀዉ የህግ የበላይነት ልእልና እንዲኖር በሚያስችሉ ቀጣይ ተግባራትም ድርጅታቸዉ ከተቋሙ ጋር በጋራ እንደሚሰራ በመግለፅ ለስልጠናዉ ተካፋዮች እንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ስልጠናዉ ለሁለት ቀናት የዐቃቤ ህግ ስብእና ምንነት፣ ስብእናዉ የተሟላ ዐቃቤ ህግ ባህሪ፣ የዐቃቤ ህግ ስነ ምግባር፣ የዐቃቤ ህግ ነፃነትና ገለልተኝነት፣ በፍትህ ስርዓት ዉስጥ የዐቃቤ ህግ ሚና እና ሰብዐዊ መብትን በማስከበር ሂደት ዉስጥ የዐቃቤ ህግ ሚና በሚሉ ነጥቦች ላይ በአሰልጣኞች ማብራራያዎች ቀርበዉ ዉይይት የሚካሄድበት ይሆናል፡፡
ቼክ ምንድን ነዉ? በቂ ስንቅ የሌለዉ ቼክ መፃፍ በወንጀል ያስጠይቃልን?
------------------------------------

በ1952 ዓ.ም የወጣው የሀገራችን የንግድ ህግ በርከት ላሉ የንግድ ሰነዶች እውቅና የሰጠ ቢሆንም በተግባር ላይ ሰፋ ባለ መልኩ አገልግሎት ላይ እየዋለ ያለው ቼክ የሚባለው የንግድ ሰነድ ነው፡፡ ቼክ ወስብስብ በሆነ የንግድ ስርአት ውሰጥ በጥሬ ገንዘብ በመገበያየት ምክንያት የሚከሰቱ ወንጀሎችንና የንብረት ጉዳቶችን በማስቀረት የተቀላጠፈ የንግድ ስርአት እንዲኖር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

የቼክን ምንነትና ሊይዝ ስለሚገባው ዝርዝር ጉዳይ በሚመለከት የንግድ ህጋችን አንቀፅ 827 ላይ የተገለፀ ሲሆን ከዚህ አንቀፅ ጠቅላላ ይዘት ለመረዳት እንደሚቻለው ቼክ ማለት የከፋዩን ስም፣ የሚከፈልበትን ቦታ፣ቼኩ የወጣበት ቀንና ቦታ እንዲሁም የአውጪውን ፊርማ የያዘ የተገፀው ባንክ ወይም ህግ የባንክን ስራ እንዲያከናውን ስልጣን የተሰጠው መስሪያ ቤት የተወሰነ ገንዘብ ለሶስተኛ ወገን ወይም ለአምጭው ለራሱ እንዲከፍለው የሚያዝ ሐተታ የሌለበት የንግድ ሰነድ (Commercial instrument) ነው ሊባል ይችላል;; በንግድ ህግ ውስጥ አራት አይነት የቼክ አይነቶች ማለትም የስርዝ ምልክት ያለበት ቼክ (Crossed cheque)፣ ከሒሳብ ውስጥ የሚገባ ቼክ (Cheque payable in account)፣ የመንገድ ቼክ (Travellers cheque) እንዲሁም መደበኛ ቼክ የሚባሉት የቼክ አይነቶች የሚገኙ ቢሆንም የዚህ ፅሁፍ ትኩረት ግን የመጀመሪያ ሶስቱን የቼክ አይነቶች ወደጎን በመተው አራተኛው የቼክ አይነት ላይ ማለትም መደበኛ የቼክ አይነት ላይ ይሆናል፡፡

መደበኛውን የቼክ አይነት ምንነት በሚመለከት የንግድ ህጋችን አንቀጽ 827 እና በሚከተሉት አንቀጾች ላይ ተንግጎ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ድንጋጌዎች አጠቃላይ ይዘት ለመረዳት እንደሚቻለው መደበኛ ቼክ ማለት መጠኑ በግልፅ ተለይቶ የተጠቀሰ የገንዘብ መጠን ለአንድ ግለሰብ ወይም ሶስተኛ ወገን እንዲከፈል ለአንድ ባንክ ቤት ወይም ቼክ መከፈልን ጨምሮ በህግ የባንክ ቤት ስራን ለማከናወን ስልጣን ለተወጠዉ ተቋም ሐተታ የሌለበት ትዕዛዝ የያዘ የንግድ ሰነድ ነዉ፡፡

አንድ ቼክ ህጋዊ ነው ተብሎ ክፍያ ሊፈጸምበት የሚችለው በንግድ ህጉ አንቀጽ 827 ላይ የተገለጹትን መግለጫዎች ካሟላ ብቻ ነው;; በዚህ የህግ ድንጋጌ መሰረት አንድ ቼክ ህጋዊ ቼክ ነው እንዲባል አምስት መሰረታዊ መግለጫዎችን ሊይዝ የሚገባ ሲሆን እነዚህ መግለጫዎችም፡
-
1. የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ሃተታ የሌለበት ትእዛዝ;; ይህም ሲባል በቼኩ ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወይም መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ሳይዘረዝር ሊከፈል የሚገባውን የገንዘብ መጠን በግልጽ ሊጻፍበት ይገባል;;
2. ከፋይ የሆነው ተቋም ስም፡፡ በንግድ ህጋችን አንቀጽ 829 መሰረት ቼክን ተቀብሎ ክፍያ ሊፈጽም የሚችለው ባንክ ቤት ወይም በህግ የባንክ ቤትን ስራ ለማከናወን ስልጣን የተሰጠው ተቋም ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ቼኩን ተቀብሎ በቼኩ ላይ የተገለጸውን የገንዘብ መጠን እንዲከፍል የታዘዘው ተቋም በግልጽ በቼኩ ላይ ሊኖር ይገባል;;
3. ገንዘብ የሚከፈልበት ቦታ
4. ቼኩ የወጣበት ቦታና ጊዜ
5. ቼኩን ያወጣው ሰው ፊርማ ናቸው;;

በህግ የተቀመጡትን መግለጫዎች ያላሟላ ቼክ የሚኖረው የህግ ውጤት
በመርህ ደረጃ አንድ ቼክ እንደ ህጋዊ ቼክ ተቆጥሮ ክፍያ የሚፈጸምበት ከላይ የተገለጹትን አምስት መግለጫዎች የያዘ እንደሆነ ብቻ ነው;; ነገር ግን በንግድ ህጉ አንቀጽ 828 ላይ ሁለት ልዩ ሁኔታዎች ተቀምጠዋል፡፡

በዚህ ድንጋጌ መሰረት አንድ ቼክ የሚከፈልነት ቦታ ያልገለፀ እንደሆነ በከፋዩ ስም አጠገብ የተቀመጠው ቦታ የመክፈያ ቦታ ሆኖ ይቆጠራል፡፡ ከከፋዩ ስም አጠገብ ከአንድ በላይ ቦታዎች የተገለፁ እንደሆነ በመጀመሪያ የተመለከተዉ ቦታ ቼኩ ተከፋይ ይሆናል፡፡

ነገር ግን ቼኩ ምንም አይነት ቦታ ያልገለፀ እንደሆነ የከፍዩ ዋና ስራ ማካሔጃ /ዋና መስሪያ ቤት/ የቼኩ የክፍያ ቦታ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
ክዚህ የህግ ግምት ውጪ የተቀሩትን ከላይ የተገለፁትን መስፈርቶችን ያላሟላ ቼክ እንደህጋዊ ቼክ የሚቆጠር ባለመሆኑ ቼክ ከፋዩ ለመክፈል አይገደድም፡፡በመሆኑም የቼክ ተከፋይ የሆነዉ ግለሰብ ቼኩ እንደ ህጋዊ ቼክ ተቆጥሮ ከፋዩ በቼኩ ላይ የተገለፀዉን የገንዘብ መጠን እንዲከፈለዉ ለማስገደድ የሚችለዉ ቼኩ በህጉ ላይ የተገለፁትን መስፈርቶች አሟልቶ የተገኘ እንደሆነ ብቻ በመሆኑ ማንኛዉም ግለሰብ አንድን ቼክ ከመቀበሉ በፊት ቼኩ ከላይ የተገለፁትን ዝርዝር መግለጫወችን የያዘ ስመሆኑ ማረጋገጥ ይኖርበተል፡፡

ከቼክ ጋር ተያይዘዉ የሚፈፀሙ ወንጀሎችና የሚያስከትሉት ቅጣት
ቼክ በርከት ያለ ጥሬ ገንዘብን ከበታ ቦታ ይዞ በመዘዋወር የሚከሰተዉን የአደጋ ተጋላጭነትና በመገበያያ ገንዘብ ላይ የሚደርሰዉን ጉዳት በማስቀረት የንግድ ስርአቱ በተቀላጠፈ መልኩ አንዲከናወን ጉልህ ሚና የሚጫወት ቢሆንም ከቼክ ጋር ተያይዘዉ የሚፈፀሙ ወንጀሎች የንግዱ ማህበረሰብ በቼክ ላይ ያለዉን እምነት በመቀነስ ቼክ ለተቀላጠፈ የንግድ ስርአት የሚያበረክተዉ ጉልህ አስተዋፅኦ ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡

ከቼክ ጋር በተያያዘ በዋናነት የሚፈፀመዉ የወንጀል አይነት ደረቅ ቼክ ማዉጣት ወንጀል ሲሆን ደረቅ ቼክ ወይም በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ ማዉጣት ወንጀል ማለት ቼኩ በሚወጣበት ወይም ለባንክ በሚቀርብበት ወቀት የሚያዝበት በቂ ስንቅ በሒሳብ ወስጥ ሳይኖር ቼክ ማዉጣት ወንጀል እንደሆና ይህ የወንጀል ድርጊት ተፈፅሞ ሲገኝም እስከ አስር አመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ የሚያስቀጣ የወንጀል ድርጊት እንደሆነ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 693 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ሌላኛዉ ከቼክ ጋር በተያያዘ የሚፈፀመዉ የወንጀል አይነት ደግሞ ሀሰተኛ ወይም ህጋዊ ያልሆነ ቼክ የማዉጣት ወንጀል ነዉ፡፡

ሀሰተኛ ቼክ ማለት ቼክን ለማተም ስልጣን ባለዉ ባንከ ቤት ታትሞ ያልተሰጠ ወይም ታትሞ ከተሰጠዉ ጋር ተመሳስሎ የተሰራ ቼክ መሳይ ሰነድ ሲሆን ማንም ሰዉ ይህንን ሀሰተኛ ቼክ የሰራ ፣ የተገለገለ ወይም ህጋዊ አስመስሎ ለሶስተኛ ወገን ያስተላለፈ አንደሆነ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 375ና በሚከተሉት አንቀፆች እንዲሁም በተደራቢነት በወ.ህ.ቁ 692 መሰረት በማታለል ወንጀል ተጠያቂ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ህጋዊ ቼክ ሊኖረዉ ስለማገባ አስገዳጅ መግለጫዎችና ከቼክ ጋር በተያያዘ ስለመፈሙ ወንጀሎች በአግባቡ በመገንዘብ እራሳችንን ከአደጋ እንጠብቅ የእለቱ መልእክታችን ነዉ በሌላ ፅሁፍ እስክንገናኝ ቸር እንሰንብት፡፡
https://t.me/lawsocieties
Forwarded from አለሕግ🔵AleHig
🔴none of us truly wins until we all win🔴
@lawsocieties
#ሁከት_ይወገድልኝ

Legal Consulting Limited
የአንድ ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሰው ይዞታውን ለመንጠቅ ወይም በይዞታው ላይ ሁከት ለመፍጠር የሚፈፀምን ማንኛውንም ድርጊት እንዲቆም ወይም ንብረቱ እንዲመለስለት የሚያቀርበው የይዞታ ክስ
በፍ/ሕ/ቁ. 1149/1/ መሰረት የሁከት ይወገድልኝ ክስ መቅረብ የሚችለው አቤቱታ አቅራቢው ለክርክሩ መነሻ በሆነው ነገር በቀጥታ ወይም በጠባቂ ይዞታ
ሲኖረው ነው፡፡ እንዲሁም የይዞታ ክስ የሚቀርበው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት በወቅቱ ለመያዝ ምንም ዓይነት መብት በሌለው ሰው ላይ ስለመሆኑም*የድንጋጌው መንፈስ ያስረዳል፡፡

የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ አቅራቢ በማስረጃ
ማረጋገጥ ያለበት ንብረቱ በይዞታው ስር የነበረና የሁከት ድርጊት ፈፃሚው የኃይል ተግባር በመጠቀም ወይም በሚስጢር ንብረቱን የወሰደበት መሆኑን
ነው፡፡ ሁከት ተፈጥሯል የሚባለው ባለይዞታ የሆነው ሰው በይዞታው ስር በሚገኘው ንብረት እንዳይገለገልበት ሌላ ሰው ጣልቃ ገብቶበት መሰናክል ሲፈጥርበት ወይም ረብሻ ሲፈጥርበት ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 80241 ቅጽ 15፣ ፍ/ህ/ቁ. 1149(1)

የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ ከሳሹ ማስረዳት ያለበት ባለቤትነት ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እንዳለው ሳይሆን ክስ ያቀረበበት ንብረት ህጋዊ ባለይዞታ መሆኑ በሌላ አነጋገር ሁከት የተፈጠረበትን ነገር በእጁ አድርጎ በእውነት ሲያዝበት እንደነበር ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 38228 ቅጽ 9

ሁከት እንዲወገድ በቀረበ ክስ ተከሳሽ የሚያነሳው የባለቤትነት ክርክር እራሱን የቻለ ባለቤትነት የመፋለም ክስ /petitory action/ በሚመለከተው ላይ አቅርቦ ከሚታይ በስተቀር ሁከት ተፈጥሯል ወይስ አልተፈጠረም ተብሎ ለሚያዘው ጭብጥ ተገቢነት የለውም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 27506 ቅጽ 6

የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሲቀርብ በፍርድ ቤት በጭብጥነት ተይዞ መፈታት የሚገባው ጉዳይ ሁከት አለ ወይንስ የለም? የሚለው ነው፡፡ የውሉ ተገቢውን
የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትሎ አለመደረግ ይዞታው በተጨበረበረ መንገድ ስለመያዙ ወይንም በማናቸውም ሕገወጥ ሁኔታ ስለመያዙና ሁከት እንዲወገድለት ክስ ያቀረበው ከሳሽ በይዞታው በእውነት ሊያዝበት እንደማይችል አያረጋግጥም፡፡

በዚህ ረገድ ውሉ ጉድለት አለበት ከተባለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1808(2) ላይ እንደተመለከተው ውሉ ፈራሽ ነው እንዲባል የክስ ምክንያት ከሚሆን በስተቀር
ሁከት ይወገድልኝ ተብሎ በቀረበ ክስ ላይ ሊስተናገድ የሚችል አይሆንም፡፡
ሰ/መ/ቁ 36645 ቅጽ 9

Source:-Legal Consulting Limited
via Binimos
Dear Lawyers, Good Morning‼️
Forwarded from Deleted Account
አዲስ አበባ የፈተና ጣቢያ ያደረጋችሁ የሕግ መውጫ ፈተና ተንታኞች በሙሉ የመፈተኛ ቦታው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ FBE ካምፓሥ እሸቱ ጮሌ ህንፃ መሆኑን እንገልጻለለን። በ12/04/2013 በ 9:00 ሠዓት ገለጻ ሥለሚሠጥ እንድትገኙ
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza Lawyer)
🔴none of us truly wins until we all win🔴
@lawsocieties
አዲስ አበባ የፈተና ጣቢያ ያደረጋችሁ የሕግ መውጫ ፈተና ተንታኞች በሙሉ የመፈተኛ ቦታው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ FBE ካምፓሥ እሸቱ ጮሌ ህንፃ መሆኑን እንገልጻለለን። በ12/04/2013 በ 9:00 ሠዓት ገለጻ ሥለሚሠጥ እንድትገኙ እናሳስባለን