Forwarded from Belayneh Alemu
ውድ የ Ale ቤተሰቦች public prosecutor extrinship ላይ የተሰራ ካላችሁ ከጊዜው አንፃር እንደ sample ስለሚጠቅመኝ ትተባበሩኝ ዘንድ ከትህትና ጋር
i know this will be very easy for you.
You can solve difficult cases than this.
🔴Refresh your mind‼️
you can send us you answer
via @Alemwaza
or
share to group
@ALE_lawsocieties
please, indicate the relevant law that you used to answer.

👍1
Forwarded from daniel
selam Ale ye Addis Ababa university yehig temeraqi temariwoch nen .....ena law schoolu ye hig temariwoch endemaymereku tenagrowal...lelaw department simereq egna bcha enkeralen malet new ....ere mefthe felgulin
Forwarded from Tg Sador
ሰላም እባካቹ externship insurance ላይ የሰራቹ ሪፖርት ካላቹ አጋሩን sample እንዲሆነን ።🙏
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አሁን ባለው ሀገራዊ ሁኔታ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል !
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊየን ማቲዎስ የ8ኛ እና የ12 ክፍል ፈተናን በተመለከተ ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደየ ክልሎቹ ዝግጁነት ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
የ12 ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ደግሞ መንግስት የትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የህግ ማስከበርና የፀጥታ ጉዳዮችን እንዳረጋገጠ ይሰጣል ብለዋል።
ተማሪዎች ይህንን ተገንዝበው ለፈተና እየተዘጋጁ እንዲጠባበቁ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ አሳስበዋል።
ምንጭ:- ትምህርት ሚኒስቴር
@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የላዳ ታክሲዎችን የሰረቀው ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጣ
____________
ተከሳሽ በአዲስ አበባ በ4 ክፍለ ከተሞች እየተዘዋወረ የላዳ ታክሲዎችን በተመሳሳይ ቁልፍ በመክፍት ከባድ የስርቆት ወንጀል የሚፈጽመው ተከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው 4 ክስ በጽኑ በእስራት ተቀጣ፡፡
የተከሳሽ ፈለቀ ወንድሙ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 669/3/ ለ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የማይገባውን ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ ከሌሊቱ 9 ሰዓት ሲሆን በ1ኛ ክስ በአቃቂ ቃልቲ ክፍል ከተማ ልዩ ቦታው ገላን ኮንዶሚኒየም ግቢ፣ በ2ኛ ክስ ከሌሊቱ 7 ሰዓት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ክልል ልዩ ቦታ ግሎባል ሆቴል ጀርባ መስቀል ፍላወር አካባቢ፣ በ3ኛ ክስ በንፋስ ስልክ ከፍለ ከተማ ወረዳ 03 ክልል ልዩ ቦታው ሳር ቤት ሸንኮራ ሰፈር እና በ4ኛ ክስ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ክልል ልዩ ቦታው ወጣት ማዕከል እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ በተለያየ ሰዓት እና ቀን በመጠቀም በክስ መዝገቡ ስማቸው የተጠቀሱ 4 ተበዳይ ግለሰቦችን ላዳ ታክሲ መኪና በተመሳሳይ ቁልፍ አስነስቶ በመውሰድ በፈጸመው ከባድ ስርቆት ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት መቅረቡን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
የዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር በችሎቱ የተነበበለት ተከሳሽ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ የክስ መቃወሚያ የለኝም፣ ወንጀል ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለቱ የዐቃቤ ሕግ ምስከሮች ችሎት ቀርበው ተሰምተዋል፡፡ የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተዉ ፍርድ ቤትም ምስክሮቹን ቃል ካዳመጠ በኋላ ተከሳሽን በተከሰሰበት ክስ ጥፋተኛ ብሎታል፡፡
ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን በ11 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎል፡፡

Forwarded from Deleted Account
We strongly against racist law families. it should be. lawyer is neutral from politics and political related things. if you are such a person do not be lawyer. because, lawyer is a rational person in this world.
do not be ethnic based person, do not be language based person ever.
language is mode of communication.
who cares what kind of language i used to communicate, rather i care about what kind of ideas i raised. እኛ ዘረኛ የሕግ ቤተሰቦችን በጥብቅ እንቃወማለን ፡፡ መሆን አለበት. ጠበቃ ከፖለቲካ እና ከፖለቲካዊ ጉዳዮች ገለልተኛ ነው ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰው ከሆንክ ጠበቃ አትሁን ፡፡ ምክንያቱም ጠበቃ በዚህ ዓለም ውስጥ አስተዋይ ሰው ነው ፡፡
ብሔርን መሠረት ያደረገ ሰው አይሁን ፣ ቋንቋን መሠረት ያደረገ ሰው አይሁን ፡፡
ቋንቋ የመግባቢያ ዘዴ ነው ፡፡
ምን ዓይነት ቋንቋ መግባባት እንደጀመርኩ ማን ይጨነቃል ፣ ይልቁንስ ስለ ምን ዓይነት ሀሳቦች እንዳነሳሁ ግድ ይለኛል ፡፡

ፍቃድ ሳይኖረው በንግድ ሥራ ተሰማርቶ የተገኘው ተከሳሽ በገንዘብና ጽኑ እስራት ተቀጣ
__________
የንግድ ፍቃድ ሳይኖረው በእንጀራ ንግድ ሥራ ተሰማርቶ የተገኘው ግለሰብ የ4 ዓመት ጽኑ እስራትና 50‚000 ብር የገንዘብ መቀጮ ተወሰነበት፡፡
የክስ መዝገቡ እንደሚያሰረዳው ተከሳሽ ሚኪያስ ልቅነው ጫኔ በንግድ ምዝገባ እና ፍቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 አንቀጽ 22(1) እና 49(2) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው የቀድሞ ቀበሌ 04 ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የቤት ቁጥሩ 738 በሆነ ቤት ውስጥ የንግድ ፍቃድ ሳይኖረው እንጀራ እየጋገረ በመሸጥ ሥራ ላይ የተሰማራ በመሆኑ በፈጸመው የንግድ ፍቃድ ሳይኖር ንግድ ሥራ ላይ መሰማራት ወንጀል ክስ ተመሰርቶበታል፡፡
ተከሳሽ ያቀረባችው የመከላከያ ምስክሮች ተከሳሹ ወንጀሉን ሰለአለመፈጸሙ ያላስረዱና ተከሳሹም በበኩሉ የቀረበበትን ክስ ማሰተባበል ያልቻለና የዐቃቤ ሕግ ምስከሮች ተከሳሽ ወንጀሉን ሰለመፈጸሙ በሰጡት ቃል ያረጋገጡ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ዐቃቤ ሕግ በተከሳሽ ላይ የጥፋኝነት ዉሳኔ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል በዚህ መሰረት የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 7ኛ ወንጀል ችሎትም ተከሳሽን በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ብሎታል፡፡
በመሆኑም ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ የ4 ዓመት ጽኑ እስራትና 50‚000 ብር ቅጣት ተላልፎበታል፡፡

ግብር የመክፈል ግዴታ እና የህግ ማእቀፉ
****
መንግስት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ አድገትን ለማፋጠን ክፍተኛ ሀላፊነት አለበት፡፡ይሄን ሃላፊነት ለመወጣት መንግስት የራሱ ገቢ ያስፈልገዋል፡፡ የሄንኑ ስራ የሚያከናውንበትን ገቢ ከሚያሰባስበብበት የገቢ ምንጭ መካከል ግብር አንዱና ዋነናው መሆኑ ይታወቃል፡፡ለዚህም ነው ግብር ወይም ታክስ ዋናው የመንግስት የፋይናንስ ምንጭ በመሆን የአንድ አገር ኢኮኖሚ ልማትንና እና እድገት የጀርባ አጥንት ነው ሲሉ በዘርፉ ባለሞዎች የሚገልጹት፡፡
በዚህም ምክኒያት ማንኛውም መንግስት በአለማችን ታሪክ ሀገራት ከተመሰረቱበት ጊዜ ጀምሮ በዜጎች ዕና በመንግስት መካከል በተፈጸመ ማህበራዊ ውል መሰረት ዜጎች መንግስት የሚባለውን አካል ፈጥረው ህይወታቸውን ፣ነጻነታቸውን፣ እና ንብረታቸውን ሊደርስባቸው ከሚችል ማንኛውም ጣልቃ ገብነት እንዲከላከልላቸው በመፈለግ መንግስትን ቃል በማስገባት እነሱም እንደዜጋ መንግስት ለዚሁ አገልግሎት መስጫ ወጪ መሸፈኛ የሚሆነውን የገቢ ምንጭ ስለሚያስፈልገው ግብር መክፈልን እንደግዴታ ወስደው በመስማማት በየግዜው ይሄንኑ ግዴታቸውን በውላቸው መሰረት በመክፈል መንግስትም በበኩሉ ተቀዳሚ እና ጥንታዊ ግዴታው የሆነውን የዜጎችን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ በውሉ መሰረት እንዲከውን ይሆናል፡፡
በዘመናዊው የአለማችን እውነታ ደግሞ መንግስት ጥንታዊ ከሆነው የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ማስከበር አልፎ የህብረተሰብን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት መሰረተ ልማትን ማስፋፋት እና የዜጎችን ሁለንተናዊ እድገትን ለማፋጠን የሚያስፈልጉ ስራዎችን እንዲያከናውን እና ማህበራዊ ፍትህን እንዲያሰፍን ይጠበቃል፡፡ይሄንን ተግባር ለመከወን መንግስት ወጪውን የሚሸፍንበት ይራሱ የገቢ ምንጭ ያስፈልገዋል፡፡ግብር ደግሞ ዋነኛው የገቢ ምንጭ ነው ማለት ይቻላል፡፡ሌላው ገቢ ከመንግሰት አገልግሎት የሚሰበሰብ ክፍያ፣ ከተለያዩ አካለት የሚገኝ እርዳታ፣እና የመሳሰሉትን እንደ የመንገስት የገቢ ምጭ መጥቀስ ይቻላል፡፡
ጠቅለል አድርገን ስናየው ግብር ወይም ታክስ ማለት መንግስት ለጠቅላላው ህብረተሰብ ጥቅም ሲባል የሚያወጣቸውን ወጪዎች ለመሸፈን እንዲችል ማንኛውም ግብር ከፋይ በተለየ ሁኔታ ለከፈለው ግብር በግሉ ቀጥተኛ የጥቅም ጥያቄ ሳያነሳ የሚከፍለው በህግ የተጣለ የግዴታ ክፍያ ነው፡፡ከዚህ ትርጉም ለመረዳት እንደሚቻለው
ግብር በህግ የሚጣል ግዴታ ነው-በፍላጎት ሳይሆን በግዳጅ የሚከፈል ነው፡፡ይሄም ቀድሞ በተደነገገ ህግ መሰረት የሚፈጸም ነው፡፡አለመክፈልም በወንጀል ህግ እና በአስተዳደር ህግ ያስጠይቃል፡፡
ግብር የሚጣለው እና የሚሰበሰበው በመንግስት ብቻ ነው፡፡ግለሰቦች ግብር የመጣል እና ፣ሰብሰብ ስልጣን የላቸውም፡፡
ታክስ የሚከፈለው በታክስ ከፋይ ነው፡፡የተፈጥሮ ወይም በህግ ሰውነት የተሰጠው ሰው ሊሆን የችላል።
ታክስ የሚጣለው እና የሚሰበሰበው ለጠቅላላው ህብረተሰብ ጥቅም ነው።በመንግስት ወጪ ከሚሰጥ አገልግሎት ኁሉም ተጠቃሚ ነው ግብር ከፋዩ ብቻ አይደለም፡፡
ታክስ ከፋዩ ለከፈለው ግብር ቀጥታ ከመንግስት በግሉ ልዩ ጠቅም የመጠየቅ መብት የለውም፡፡ግብር የሚከፍለው መንግስት ለሚያከናውናቸው የልማት ተግባሮች እገዛ የማድረግ ግዴታ ስላለበት ነው፡፡
ግብር ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ያሉት ሲሆን እነሱም ግብር የሚጣልበት የገቢ ምንጭ(tax base) እና የሚጣለው ግብር ወይም ታክስ መጠን(tax rate) ናቸው፡፡ግብር የሚጣልባቸው የገቢ ምንጮች ገቢ የሚያስገኙ ማናቸውም የምርት፣የአገልግሎት እና የንግድ ወይም የስራ ዘርፍ ሲሆኑ የግብር መጠን ደግሞ በእነዚሁ ገቢዎች ላይ የሚጣለው የግብር መጠን ነው፡፡በዚህም ግብር ከፋዩ በገቢው ልክ ግበር የሚከፍል ሲሆን ትንሽ ገቢ ያለው ግብር ከፋይ ትንሸ ግብር የሚከፍል ሲሆን ትልቅ ገቢ ያለው ግብር ከፋይ እንዲሁ ከፍ ያለ ግብር ይከፍላል ማለት ነው፡፡ይህም የግብርን አፈጻጸም ፍትሀዊነት ያሳያል፡፡
የግብር አላማ
ግብር የተለያዩ አላማዎችን ለማስፈጸም የሚሰበሰብ ሲሆን ጥቂቶቹን ለማየት ያክል፡፡
ገቢን ለመፍጠር
ከላይ እንዳነሳነው ግብር ዋነኛው የመንግሰት የገቢ ምንጭ ነው፡፡
የገቢ እና የሀብት ልዩነትን መቀነስ
በሀብታምና በደሀ መካከል ያለውን ልዩነት ለመቀነስ ዕየጨመረ የሚሄድ የታክስ ስርአት ተግባራዊ ያደረጋሉ፡፡በዙሁም መሰረት ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙ ከፍተኟ ታክስ መካከለኛ ገቢ ያላቸው መካከለኛ ታክስ ሲከፍሉ ዝቅተኛ ገቢ የሚያገኙ ደግሞ ከታክስ ነጻ ይደረጋሉ፡፡ከከፍተኛና መካከለለኛ ታክስ ከፋዮች የሚሰበሰበው ገቢ ለዝቅተኛ እና ገቢ ለሌላቸው መደጎሚያ ይሆናል፡፡
ኢኮኖሚን ለማረጋጋት
መንግስት ታክስን በመጠቀም የዋጋ ግሽበትን እና የእኮኖሚን መቀዛቀዝን ለመቆጣጠር ሊጠቀምበት ይችላል፡፡የሄውም የሚፈጸመው የታክስ መጠንን በጨመር ወይም በመቀነስ ወይም አዲስ ታክስ በመጣል ወይም በማንሳት ሊሆን ይችላል፡፡
ጎጂ ወይም መሰረታዊ ያልሆኑ ምርቶችን ፍጆታ መቀነስ
በህብረተሱ ጤና ላይ ችግር ይፈጠራሉ ተብለው ለሚታሰቡ ምርቶች ወይም መሰረታዊ ባልሆኑ ምርቶች ፍጆታ ለመቀነስ መንግስት ታክስን በመጠቀም ከገበያ እንዲገለሉ ማድረግ /እንዲቀንሱ ማድረግ የችላል፡፡ከፍተኛ ታክስ በመጣል አብዛኛው ህብረተሰብ እነኘህኑ ምርቶች ከመግዛት እንዲቆጠብ ማድረግ ይቻላል፡፡
ኢንቨስትመንትን ማበረታታት
መንግስት ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ሴክተሮችን በመለየት ለተወሰነ ጊዜ የታክስ እፎይታ ሊፈቅድ ወይም ታክስ ሊቀንስላቸው የችላል፡፡
ለሀገር ውስጥ ምርት እና አምራቾች ጥበቃ ማድረግ
ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ላይ ከፍ ያለ ታክስ በመጣል ለሀገር ውስጠ ምርት እና አምራቾች ጥበቃ ሊያድርግ ይችላል
የውጭ ንግድን ማበረታታት
የውጭ ንግድን ለማበረታታት እና የውጭ ምንዛሬን ለመጨመር መንግስት ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ከታክስ ነጻ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡
በአገራችን የግብር ወይም የታክስ ስርአት ስናይ በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገመንግሰት እና በታክስ ህግጋት መሰረት መንግስት የተለያዩ የግብር ወይም ታክስ አይነቶችን የሚጥል እና የሚሰበስብ ሲሆን እነዚህን የግብር አይነቶች ስናይ ፣የገቢ ግብር፣የተርን ኦቨር ታክስ፤.የተጨማሪ እሴት ታክስ፤እና ኤክሳይስ ታክስ ይገኙበታል፡፡እያንዳንዱ የግብር አይነት የራሱ የሆነ ባህርያት ያሉት ሲሆን ድምር ግቡ የመንግስትን ገቢ ከፍ በማድረግ መንገሰት መሰረተ ልማት በማስፋፋት እና አጠቃላይ የአገሪቷን ኢኮኖሚ ከፍ እንዲያደርግ ማስቻል ነው፡፡
ግብር መክፈል ግዴታ መሆኑን ከግብር ባህሪት አንጻር ያነሳን ሲሆን በአጋራችን የግብር ህግጋትም ይሄው ተደንግጎ ይገኛል፡፡ የገቢ ግብር በተመለከተ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 7 እና 9 መሰረት ማንኛውም ኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ከኢትዮፕያ ውስጥ ላገኘው ገቢ የገቢ ግብር የመክፈል ግዴታ አለበት እንዲሁም ማነኛውም የኢትዮጵያ ነዋሪ ከየትናውም የአለም አገር ላገኘው ገቢ የገቢ ግብር የመክፈል ግዴታ እንዳለበት በግልጽ ደንግጓል፡፡ከተጨማሪ እሴት ታክስ አንጻር ስናየው በአዋጅ ቁጥር 285/1994 (ከነማሻሻያ አዋጆቹ) አንቀጽ 7 እና ቀጥሎ ባሉ አንቀጾች መሰረት ከእያንዳንዱ ግብር የሚከፈልበት ግብይት ላይ በ15 እና 0 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ መክፈል ግዴታ መሆኑን ደንግጓል፡፡በሌላ በኩል ኤክሳይስ ታክስን ስናይ ህጉ ለህበረተሰብ ጤና ጎጂ የሖኑ እንዲሁም ከመሰረታዊ ፍልጎት ባለፈ የቅንጣት ምርቶች ላይ የሚጣል

የግብር አይነት ሆኖ በኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 አንቀጽ 6 መሰረት እነኝኑ ምርቶች የሚያመርቱም ሆነ ከውጭ የሚያስገቡ አስመጪዎች እንዲሁም ኤክሳይስ ታክስ የተጣለባቸውን አገልግሎቶች የሚሰጡ ሰዎች በህጉ በዝርዝር በተጣለባቸው መጠን የኤክሳይስ ታክስ የመክፈል ግዴታ አለባቸው፡፡እንደማሳ ሶስቱን ያነሳን ሲሆን ሌሎች ከላይ ያነሳናቸው የግብር አይነቶችም እንዲሁ በተመሳሳይ ሁኔታ ግዴታን ይጥላሉ፡፡
በዚሁ አግባብ ግብር መክፈል ግዴታ ከሆነ ግብርን በተገቢው ጊዜ አለመክፈል በህጉ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ሲሆን ጥቂጥ ነጥቦችን ለማንሳት፡፡
በፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቑጥር 983/2008 አንቀጽ 116 እና ቀጥሎ ባሉት ድንጋጌዎች መሰረት ከግብርን አለመክፈል፣ማጭበርበር፣ግብር መሰወር፣ቫት ማጭበርበር እና በጠቅላላለው ከታክስ ጋር ተያይዘው ለሚፈጸሙ ወንጀሎች በእስር እና እንደየ ወንጀሉ ክብደት በብርም የሚያስቀጡ ናቸው፡፡
በኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 አንቀጽ 39 እና ቀጥሎ ባሉት ድንጋጌዎች መሰረት ኤክሳይስ ታክስን አለመክፈል ከሶስት አመት ጽኑ እስራት ጀምሮ በተለያየ ደረጃ በእስር እና በገንዘብ እንደሚያስቀጣ ተደንድንግጓል፡፡
በሁሉም የግብር ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ከወንጀል ተጠያቂነት በተጨማሪ በአስተዳደራዊ ቅጣቶችን ያስከትላሉ እሱም በገንዘብ ፣ከስራው ማገድ እና የመሳሰሉትን አስተዳደራዊ እርምጃዎች ያስከትላል፡፡
ስለዚህ ግብር መክፈል ለሀገር እድገት እና ለዜጎች ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ.ማህበራዊ፣እና ፖለቲካዊ መብቶች መረጋገጥ ካለው ፋይዳ አንጻር አስፈላጊ ከመሆኑም ባለፈ በአንድ ሉኣላዊ አገር ግብርን ለመንግስት መክፈል ግዴታ ሲሆን ይሄን አውቆ በወቀቱ ኣለመክፈል የወንጀል እና አስተዳደራዊ ቅጣቶችን ያስከትላል፡፡ስለዚህ ሁሉም ግብር ከፋይ የሚጠበቅበትን ግብር ሁሉ በጥንቃቄ በወቅቱ መክፈል አለበት፡፡

አለን አለን
priority first‼️‼️‼️
#አገር #ሀገር ይረጋጋ ብለን ነው።
አንዲት ዝንጀሮከእለታት አንድ ቀን ሰውነቷን ሙሉ ብዙ እሾህ ተሰክተውባት እና ተሰግስጎባት አግኝቶ እሾሁን በመንቀል የመጀመሪያ እርዳታ ሊያደርግላት የነበረን ሰው መጀመሪያ የመቀመጫዬ አለች ዝንጀሮ ይባላል‼️
እናም መጀመሪያ #አገር #ሀገር መቀመጫችን መኖሪያችን መቀበሪያችን ይረጋጋ ብለን ነው።
ውድ የአለ ቤተሰቦች በአላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ።
5ኛ አመት ተማሪዎች ተረጋጉ መጀመሪያ #አገር #ሀገር ሰላም ይሁን።
ሰላም ለሀገራችን ህዝቦች ይሁን‼️‼️‼️
አሜን‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
https://t.me/lawsocieties
priority first‼️‼️‼️
#አገር #ሀገር ይረጋጋ ብለን ነው።
አንዲት ዝንጀሮከእለታት አንድ ቀን ሰውነቷን ሙሉ ብዙ እሾህ ተሰክተውባት እና ተሰግስጎባት አግኝቶ እሾሁን በመንቀል የመጀመሪያ እርዳታ ሊያደርግላት የነበረን ሰው መጀመሪያ የመቀመጫዬ አለች ዝንጀሮ ይባላል‼️
እናም መጀመሪያ #አገር #ሀገር መቀመጫችን መኖሪያችን መቀበሪያችን ይረጋጋ ብለን ነው።
ውድ የአለ ቤተሰቦች በአላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ።
5ኛ አመት ተማሪዎች ተረጋጉ መጀመሪያ #አገር #ሀገር ሰላም ይሁን።
ሰላም ለሀገራችን ህዝቦች ይሁን‼️‼️‼️
አሜን‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
Forwarded from Transparency International Ethiopia (TIE)
(በእርስዎ አገላለፅ፣ አሳታፊ ዲሞክራሲ ማለት ምን ማለት ነው?) እንዲሁም የዲሞክራሲ ተቋማትን ለመገንባት ተግዳሮት ወይም እንቅፋት የሆኑ ነገሮች ምንድን ናቸው?)
#መልስ
🔴🔴🔴 የግሌ ሀሳብ እና ነፀብራቅ ነው ተቋሙን አይወክልም🔴🔴🔴🔴🔴🔴
1. አሳታፊ ማለት፤ ከስሙ መረዳት እንደሚቻለው፤ አካታች ወይም አቀፊ ማለት ነው፡፡ ስለዚህም፤ አሳታፊ ዲሞክራሲ ማለት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል እና ህዝብ ያካተተ፤ ያሳተፈ እና ያቀፈ ውሳኔ፤ ምርጫ እንዲሁም መንግስት ሲኖር ነው፡፡
2. የዲሞክራሲ ተቋማትን ለመገንባት ተግዳሮት ወይም እንቅፋት የሆኑ ነገሮች ውስጥ ❌ሙስና እና ❌ዘረኝነት ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ❌ #ሙስናና ❌ #ዘረኝነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፡፡ ሙስና ለግል ጥቅም ከማግኘት ባለፈ ለወዳጅ ዘመድ፤ ለተወለዱበት አካባቢ #ዘር እና #ጎሳ በአድሎአዊ አሰራር የተለዬ ጥቅም እንዲያገኙ የሚደረግ ጥረትን ያካተተ መሆኑ ከዘረኝነት ጋር ስር የሰደደ ቁርኝነት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ #ዘረኝነትም ቢሆን መሰረቱ እና እሳቤው ዘር እና ጎሳ ይሁን እንጅ በተለዬ ሁኔታ የተወለደበትን ዘር እና ጎሳ ቆጥሮ #በሙስና መንስላል በንመጠላጠል የበላይ መሆንን እና ልዩ ተጠቃሚ መሆንን መዳረሻው ያደርጋል፡፡ ስለዚህ በእኔ አመለካከት፣ በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ ❌ሙስና እና ❌ዘረኝነት አሳታፊ ዲሞክራሲ እንዳይኖር እና የዲሞክራሲ ተቋማትን ለመገንባት ተግዳሮት ወይም እንቅፋት ሆነዋል ብዬ እስባለሁ፡፡
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
እናንተስ ምን ትላላችሁ ሀሳባችሁን አጋሩን።
@Transparency_Ethiopia_Bot
and
ethiopiatransparency@gmail.com
https://t.me/TransparencyEthiopia

Transparency International Ethiopia (TIE)
Ethical and corruption free society that upholds integrity and accountability
Contact Us via
@Transparency_Ethiopia_Bot
and
ethiopiatransparency@gmail.com
Contact Us via
@Transparency_Ethiopia_Bot
and
ethiopiatransparency@gmail.com
Forwarded from አለሕግ🔵AleHig
what your short answer❓❓
🔴Refresh your mind‼️
you can send us you answer
via @Alemwaza
or
share to group
@ALE_lawsocieties
please, indicate the relevant law that you used to answer.
🔴Refresh your mind‼️
you can send us you answer
via @Alemwaza
or
share to group
@ALE_lawsocieties
please, indicate the relevant law that you used to answer.
ሰው የመግደል ሙከራ የፈጸመው ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጣ
_________
በልደታ ክፍለ ከተማ ሰው የመግደል ሙከራ የፈጸመው ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ዉሳኔ ተላለፈበት፡፡
የዐቃቤ ሕግ ክስ መዝገብ እንሚያስረዳው ተከሳሽ ቢኒያም ገዛኸኝ ግንቦት 04 ቀን 2011 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 3፡50 ሰዓት ሲሆን በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ቦታው ተካልኝ ግሮሰሪ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የግል ተበዳይን በምላጭ ፊቱን፣ አንገቱንና ጭንቅላቱን በመቁረጥ የቆዳ መሰንጠቅ ጉዳት እንዲደርስበት ያደረገ በመሆኑ በፈጸመው የሰው ግድያ ሙከራ ወንጀል ተከሷል፡፡
ተከሳሽ በችሎቱ ቀርቦ የክስ ተቃውሞ የለኝም ነገር ግን ወንጀሉን አልፈጸምኩም ጥፋተኛም አይደለሁም ብሎ ክዶ የተከራከረ ሰለሆነ በዐቃቤ ሕግ የቀረበበትን ክስ ማስተባበል ይቻለው ዘንድ የመከላከያ ምስክሮቹን እንድያቀርብና እንዲከራከር እድል የተሰጠው ቢሆንም የመከላከያ ምስክር ያላቀረበ ከመሆኑም በተጨማሪ በችሎቱ ቀርቦ ክሱን ማስተባበል አለመቻሉን ከቀረበው የክስ መዝገብ መረዳት ተችሏል፡፡
በተቃራኒው ዐቃቤ ሕግ ተከሳሽ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ የሚያስረዳ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የቀረበለትን ማስረጃ በመመርመር በተከሰሽ ላይ የጥፋተኝነተ ዉሳኔ አስተላልፎበታል፡፡
በመሆኑም የግራ ቀኙን ክርከር የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ የወንጀል ችሎትም ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የ4ተኛ ንግድ ችሎት 21 ፍርዶች ከዚህ በታች ያገኛሉ፡፡
*******************************************************************
የኮ/መ/ቁ 217477
ህዳር 3 ቀን 2013 ዓ/ም
ፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
ልደታ ምድብ 4ኛ ንግድ ችሎት
ዳኛ፡- መካ ነስሩ
አመልካቾች፡- 1 - አቶ ኪዳኔ ዮሃንስ
2 - ወ/ሮ እምሯ አሰፋ ጠበቃ በጋሻው ኃ/ገብርኤል ቀረቡ
ተጠሪ፡- አያት አክሲዮን ማህበር - አልቀረቡም
አቤቱታ አቅራቢ፡- ወ/ሮ ትርሲት ቶሎሳ ኤዳ - ጠበቃ ፋሲካ ገበየሁ ቀረቡ
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ብይን ተሰጥቷል፡፡
ብ ይ ን
ለዚህ ብይን መነሻ የሆነው አቤቱታ አቅራቢ ነሀሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በነበረው ክርክር ይህ ፍርድ ቤት የግልግል ጉባኤ አቋቁሟል፡፡ የግልግል ጉባኤውም የካቲት 11 ቀን 2008 ዓ/ም ውሳኔ ሰጥተዋል፡፡ የአሁን አቤቱታ አቅራቢም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት የመቃወም አቤቱታ አቅርበው የነበረ ሲሆን ጉባኤውም ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለኝም በማለት ከዘጋው በኋላ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በማቅረብ ጉዳዩን የግልግል ጉባኤው አይቶ ውሳኔ እንዲሰጥ ትዕዛዝ በተሰጠው መሰረት አቤቱታ አቅራቢ ጉዳዩ ከተፈጸመ በኋላ የቀረበ በመሆኑ ጉዳዩ ሊታይ አይገባም ሚል ውሳኔ ሰጥተዋል፡፡ አቤቱታ አቅራቢም ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ በግልግል ጉባኤው የተሰጠውን ውሳኔ እንዲሻር ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም የግልግል ጉባኤው አቋም ግልጽ በመሆኑ አሁንም ይህን ክርክር በድጋሚ አይተው ከቀድሞ በተለየ እና ያለ ተጽዕኖ ጉዳዩን በገለልተኝነት ውሳኔ ይሰጣሉ የሚል እምነት የለንም፡፡ ስለዚህ አዲስ የግልግል ጉባኤ እንድንመርጥ እንዲወሰንልን፤ አዲስ የግልግል ጉባኤ አይሾምም የሚል ቢሆን የመቃወም አመልካችን የሚወክል አንድም አባል የሌለ በመሆኑ የመቃወም አመልካችን የሚወክል የጉባኤ አባላት እንዲጨመር እና የግልግል ጉባኤ ሰብሳቢ እንደገና እንዲሾ እንዲታዘዝላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡
አመልካቾችም የአቤቱታ አቅራቢ አቤቱታ ደርሷቸው መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጡት አስተያየት አቤቱታ አቅራቢ በአቤቱታቸው ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግልግል ጉባኤን ውሳኔ የተሻረ ስለሆነ ግልግል ጉባኤው ህገ-ወጥነው ቢሉም አመልካቾች ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም በውሳኔው ላይ ቅሬታ ስላደረብን የሰበር አቤቱታ ውጤት አስኪታወቅ የግልግል ጉባኤውም ሆነ ይህ ፍርድ ቤት ሊያዩት አይገባም፡፡ ይህ ፍርድ ቤት እራሱ ያቋቋመውን የሽምግልና ጉባኤ እራሱ እንዲሽር የሚፈቅድ የህግ አግባብ ስለሌለ አቤቱታው ውድቅ ይደረግልን፡፡ የተቋቋመው ጉባኤ የሚነሳበት የህግ ማእቀፍ ካለመኖሩ በተጨማሪ የጉባኤው አቋም አዱላዊ ነው ከማለት በቀር በስነ ስርአት ህግ አካሄድ ክፍተት መኖሩን በማስረጃ ሳይረጋገጥ ጉባኤው ይቀየርልኝ የሚል አሉታዊ አቤቱታ ተቀባይነት የለውም፡፡ አዲሰ የግልግል ጉባኤ ይመረጥ ላሉት አመልካቾች ለዋናው ክርክርም ሆነ ለአቤቱታ አቅራቢ ተቃውሞ ካቀረቡ በኋላ ለተከፈሉ ወጪዎች ኪሳራውን ማን እንደሚሸፍን ያልተመለከተ አቤቱታ ስለሆነ የግልግል ዳኞች የሚቀየሩበት የህግ ማእቀፍ ሳይኖር ይህ ፍርድ ቤት ስልጣን የሌለው ከመሆኑ በተጨማሪ አቤቱታ አቅራቢ በአመልካቾች እና በተጠሪ በገባነው ስምምነት የተቋቋመን ጉባኤ ያለማስረጃ ይቀየር ማለት መብት የላቸውም፡፡ በመሆኑም አቤቱታውን ውድቅ ያድርግልን በማለት አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
በተጠሪ በኩል አቤቱታው የደረሳቸው ቢሆንም አስተያት ባለማቅረባቸው መብታቸው ታልፏል፡፡
ፍርድ ቤቱም የአቤቱታ አቅራቢን አቤቱታ እና የአመልካችን አስተያየት ከህጉ አንጻር እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡
አመልካቾች የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ ስላደረባቸው ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር ማመልከቻ በማቅረባቸው ግልግል ጉባኤው ክርክሩን የሚመራበት አግባብ የሰበር ማመልከቻው ውጤት እስከሚታወቅ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ተደርጎ ጉዳዩ እንዳይቀጥል የዕግድ ትዕዛዝ ባልቀረበበት ሁኔታ ውጤቱ ሳይታወቅ በዚህ ችሎት የቀረበው አቤቱታ እንዳይታይ የሚከለክል ሆኖ አላገኘውም፡፡
ፍርድ ቤት ያቋቋመው የሽምግልና ጉባኤ ራሱ የሚሽርበት ሕግ ስለሌለ አቤቱታው ውድቅ ይደረግልን በማለት በአመልካቾች መቃወሚያ ቀርቧል፡፡የዘመድ(የግልግል) ዳኛ የሚወገድበት አግባብ በፍ/ብሔር ሕግ ቁጥር 3340 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች የተመለከተ ሲሆን የግልግል ዳኛ እንዲሻር ጥያቄ ሊቀርብ የሚገባው ተዋዋይ ወገኖቹ የመወገድ ጥያቄ ለሌላ ባለስልጣን ይቀርባል በሚል አስቀድመው ስምምነት ካላደረጉ ደንነቱን ለሚመሩት የግልግል ዳኞች ሊቀርብ እንደሚገባ፣ ማልከቻው ተቀባይነት የለውም ተብሎ ውሳኔ የተሰጠበት እንደሆነ ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም እስከ አስር ቀን ድረስ ለፍርድ ቤት /ለዳኞች/ መቃወሚያ ሊቀርብ እንደሚገባ በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 3342 ሥር በዝርዝር ተመልክቷል፡፡የህን በተመለከተ በፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተቀመጠ ድንጋጌ ባይኖርም በረቂቅ ላይ ያለው የግልግል ዳኝነት እና የሽምግልና አመራር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ግልግል ዳኛ የሚነሳበት አግባብ በአንቀፅ 14 እና 15 ሥር በዝርዝር ተመልክቷል፡፡ይህንኑም ጉዳይ ሊታይ የሚገባው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንደሆነ ተቀምጣል፡፡የግልግል ዳኞች እንዲሻሩ ጥያቄ ሲቀርብ ተለይቶ ለፌዴራል ክፍተና ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 11(2) ስር የተሰጠው ሥልጣን ባለመሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 14(1) መሰረት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሥልጣን ነው፡፡ይህ ችሎት ራሱ ያቋቋመው የግልግል ጉባኤ እንዲሽር ሥልጣን የለውም በሚል የቀረበው መቃወሚያ በተመለከተ ሌላ መዝገብ ከፍቶ ጥያቄው በዚሁ ችሎት ከሚስተናገድ አስቀድሞ በተከፈተው መዝገቡ ጉዳዩ ቢታይ ተገቢነት አለው ከሚባል በቀር በሕግ የተከለከለ ጉዳይ አይደለም፡፡
በሌላ በኩል የአቤቱታ አቅራቢ ያቀረቡት የመቃወም ማመልከቻ የግልግል ዳኞች በገለልተኝነት ጉዳዩን ተመልክቶ ውሳኔ ሊሰጡ የሚያስችል በቂ የሆነ ምክንያት ካላቸው ለራሳቸው ለግልግል ዳኞቹ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 3342 መሰረት እንዲነሱላቸው ማመልከቻ አቅርበው ውሳኔ ባልሰጡበት አልያም ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውሳኔ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ለዚህ ችሎት የግልግል ዳኞቹ እንዲነሱ ያቀረቡት ጥያቄ ሕጉን የተከተለ ሆኖ ፍርድ ቤቱ አላገነውም፡፡
የአቤቱታ አቅራቢ መቃወሚያ በማቅረባቸው ምክንያት የራሳቸው የግልግል ዳኛ አስቀድሞ ስላልመረጡ እንዲመርጡ ትዕዛዝ እንዲሰጥ በአማራጭ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
የግልግል ጉባኤ በሚሰጠው ፍርድ የመቃወም ማመልከቻ ሦስተኛ ወገን መብቱ ሲነካ ሊያቀርብ የሚችልበት አግባብ መቃወሚያ አቅራቢው በግልግል ዳኞቹ ጉዳዩን አይቶ በገለልተኝነት እና ነፃነታቸውን በጠበቀበት አግባብ አከራክሮ ፍትሐዊ የሆነ ፍርድ ይሰጥልኛል በሚል የሚያምን ከሆነ የግልግል ዳኞች የሰጡት ፍርድ/ውሳኔ/ ላይ የመቃወሚያ ማመልከቻ ተቀብለው የማስተናገድ እና ከሚቀርበው ክርክር አንፃር እልባት የመስጠት ኃላፊነት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ማንኛውም ሠው በሕግ በተዘረጋው ሥርዓት የመዳኘት እና ፍትሕ የማግኘት መብት እንደሚኖረው እና በሕግ ከተመለከተው አግባብ ውጪ በፍርድ ሊያልቅ የሚችል አከራካሪ ጉዳይ ሁሉ የመዳኘት ሥልጣን ያላቸ

ው ፍርድ ቤቶች እንደሆኑ በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 37 እና 79 ሥር በአስገዳጅነት የተደነገገ ጉዳይ ነው፡፡ተዋዋይ ወገኖች በሕግ ክልከላ ያልተደረገበት ጉዳይ ላይ ውልን መሰረት አድርገው በሚያቋቁሙት የግልግል ጉባኤ የመዳኘት ሥልጣኑ በውል ባቋቋሙት ተከራካሪዎች ብቻ የሚወሰን እና የሦስተኛ ወገኖችን መብት የሚነካ ውሳኔ በሰጠ ጊዜ በግልግል ቀርቦ የታየው ጉዳይ በመደበኛ ፍርድ ቤት ቢቀርብ ኖሮ ተመልክቶ ውሳኔ ሊሰጥ የሚችል ፍርድ ቤት የግልግል ዳኞች የሰጡት ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ተመልክቶ ውሳኔ ሊሰጥለት እንደሚገባ ከፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓቱ ሕጉ ድንጋጌዎች አወቃቀር ይዘት መረዳት የሚቻል ነው፡፡
የአቤቱታ አቅራቢ የግልግል ዳኞቹ የሰጡት ውሳኔ መብቴን የሚነካ ነው በሚል ውሳኔው እንዲሰረዝላቸው ለግልግል ጉባኤው መቃወሚያ አቅርበው ጉዳዩ በክርክር ላይ የሚገኝ መሆኑ ሲታይ አሁን አመልካች አስቀድሞ የግልግል ጉባኤው ጉዳዩን በገለልተንነት ተመልክቶ ውሳኔ ሊሰጥልኝ ይችላል በሚል ለመዳነት ጥያቄ ማቅረባቸው በሕግ አግባብ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የመስተት ኃላፊነቱን የተስማሙበት መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ ተጨማሪ የግልግል ጉባኤ አባል ለማቋቋም መነሻ የሆነ ውል በሌለበት ሁኔታ የአሁን አመልካችን የሚወክል የግልግል ጉባኤ አባል ለመምረጥ ያቀረቡት ጥያቄ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም፡፡
ት ዕ ዛ ዝ
1. የአሁን አመልካች የግልግል ጉባኤ አባላት በገለልተንነት ጉዳዩን ሊመለከቱ የማይችሉበት ሕጋዊ ምክንያት ካላቸው ለግልግል ጉባኤው አቅርበው ጥያቄው ተቀባይነት የማይኖረው ከሆነ ብቻ ለፍርድ ቤት በሕጉ በተመለከተው አስር ቀን ውስጥ ሊያቀርቡ ይገባል ተብሏል፡፡
2. የግልግል ጉባኤው መዝገብ በመጣበት አኳኋን ተመላሽ እንዲደረግ ታዟል፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ለመዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የዳኛ ፊርማ አለበት፡፡
-------------------------------------------------------------------------
የኮ/መ/ቁ 260055
ህዳር 03 ቀን 2013 ዓ/ም
ፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
ልደታ ምድብ 4ኛ ንግድ ችሎት
ዳኛ፡- መካ ነስሩ
ከሳሽ፡- ጣና ቁፋሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር - ጠበቃ ሳሙኤል ኃ/ጊዮርጊስ ቀረቡ
ተከሣሽ፡- የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃ እና ሳኒቴሽን
ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት - ነ/ፈጅ መሰረት አሰፋ ቀረቡ
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
ው ሳ ኔ
ለዚህ ውሳኔ መነሻ የሆነው የተከሳሽ ነገረ ፈጅ የካቲት 3 ቀን 2012 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ በከሳሽ እና በተከሳሽ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት አድጁዲኬተር እንዲሾምላቸው ከሳሽ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ፍርድ ቤቱ በሀምሌ 18 ቀን 2010 ዓ.ም ባዋለው ችሎት የአዲስ አበባ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጉዳዩን በገላጋይ ዳኝነት በማየት ለጉዳዩ እልባት የሚሰጥ አዱጂኬተር እንዲሾም በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ጉዳዩን የአዲስ አበባ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በአድጁኬተር እየታየ ይገኛል፡፡ ሆኖም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ በአድጁዲኬተር እንዲታይ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መስከረም ወር 2011 ዓ.ም በወጣው ቅጽ 22 ሰ/መ/ቁ 127459 የአስተዳደር ውሎችን አስመልክቶ በሚነሳ አለመግባባትን አይቶ ለመወሰን ገላጋይ ዳኛ ስልጣን የለውም በማለት ውሳኔ መስጠቱን ተጠሪ ለማወቅ ችሏል፡፡
ከሳሽ ይህ አስገዳጅ የሆነው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እራሳቸው ተካፋይ በሆኑበት ክርክር ጉዳይ መሰጠቱን እያወቁ አድጁኬተር እንዲሾምላቸው አቤቱታቸውን በመጋት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ለዚህ ችሎት አቅርበዋል፡፡ ይህ የከሳሽ ድጊትም ወንጀል ጠቀስ የሆነና በወንጀል ህጉም የፍትህ ስራን በማሰናከል የሚያስቀጣ ድርጊት ነው ፡፡ ይህም በወንጀል ህጉ አንቀጽ 452 (1፣2) አንድ ተከራካሪ ወገን በፍርድ ቤት ቀርቦ እውነት እንዲናገር ታዞ በፍርድ ቤቱ በሚወሰን ጭብጥ ላይ አግባብነት ያላቸውን ፍሬ ነገሮች በሚመለከት እያወቀ ሀሰተኛ ቃል የሰጠ እንደሆነ እና ተከራካሪው ወገን እውነቱን ለመናገር ምሎ ወይም መረጋገጫ ሰጥቶ እንደሆነ በተለይም የተፈለገው ውጤት ተገኝቶ እንደሆነ ከ5 አመት የማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም ከሳሽ የተሳሳተ መረጃ የማቅረብ እና ሀሰተኛ ቃል በመስጠት ወንጀል ጠቀስ ድርጊት በመፈጽማቸው ምክንያት የተሰጠው ውሳኔ በመሰጠቱ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ በ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 6(1,ለ) መሰረት በማንሳት በሐምሌ 18 ቀን 2010 ዓ.ም የአዲስ አበባ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጉዳዩን በገላጋይ ዳኝነት በማየት ለጉዳዩ እልባት የሚሰጥ አድጁኬተር እንዲሾም የሰጠውን ትዕዛዝ እንዲሽርልን በማለት አቤቱታ አቅርበዋል፡፡
የከሳሽ ጠበቃም የተከሳሽ አቤቱታ ደርሷቸው መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም በሰጡት የጽሁፍ መልስ በአቤቱታው አዲስ ተገኝቷል በማለት የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሳኔ ነው፡፡ የሰበር ችሎት ውሳኔዎች የህግ ትርጉም እንጂ ማስረጃዎች አይደሉም፡፡ የሰበር ሰሚ ችሎቱ በሰጠው ውሳኔ የፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ 315 ን መሰረት አድርጎ የአስተዳደር ውሎች በግልግል አይታዩም የሚል የህግ ትጉም ሰጥቷል፤ ይህ ህግ ደግሞ አስቀድሞ የነበረ በመሆኑ ትርጉም ባይሰጥበትም ኖሮ ሊቀርብ ይገባ የነበረ ነው፡፡ ስለዚህ ህግ አላውቅም ነበር ወይም ህጉን ክርክር ዘንቼ ሳላነሳ ቀርቻለሁ የሚል ምክንያት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 6ን መሰረት ተደር ዳኝነት እንደገና እንዲታይ መጠየቅ አይቻልም፡፡ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 6 ፍርድ ቤቶች በህግ አተረጓጎም ረገድ ቢሳሳቱ ሊቀርብ ሚችል ሳይሆን በማስረጃ ረገድ ብቻ ሊነሳ የሚገባ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በነበረው ክርክር ጊዜ ክርክር የተነሳበት ነጥብ አይደለም፡፡ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 6 መሰረት አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈ ነው፡፡ ዳኝነት እንደገና እንዲታይ ሊቀርብ ሚችለው ፍርድ ቤቱ የሰጠው ውሳኔ ሀሰተኛ ማስረጃን መሰረት አድርጎ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ የተከሳሽ ክርክር ከሳሽ የአስተዳደር ውል በግልግል ሊታይ አይገባም ሚለውን የህግ ትርጉም ከሳሽ ስለሚያውቅ ክስ ማቅረብ አልነበረበትም የሚል ነው፡፡ክስ ማቅረብ ሀሰተኛ ምስክርነት ቃል አይደለም፡፡ ውሉንም በተመለከተ የስተዳዳር ውል ያልተባለ፣ ለስራው አፈጻጸም የአስተዳደር መስሪያ ቤቱን ተካፋይነት ሳያቋርጥ የሚጠይቅ ባለመሆኑ የአስተዳደር ውል አይደለም፡፡ በመሆኑም በተመለከቱት ምክንያቶች ተከሳሽ ዳኝነት በድጋሚ እንዲታይለት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል፡፡
ፍርድ ቤቱም ዳግም ዳኝነት ሊታይ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ አቤቱታውን እንደሚከተው መርምሮታል፡፡ ተከሳሽ ዳኝነቱ ዳግም እንዲታይላቸው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 6 መሰረት ያቀረቡት ከሳሽ የአስተዳደር ውሎች በገላጋይ ዳኛ እንደማይታዩ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ራሳቸው ተካፋይ በሆኑበት ክርክር ውሳኔ መስጠቱን እያወቁ ክስ መስርተው ፍርድ ቤቱን በማሳሳት ውሳኔ እንዲሰጥ በማድረጋቸው የወንጀል ተግባር የተፈጸመበት ክርክር ስለሆነ ዳግም ዳኝነት ይታይልን በማለት ነው፡፡ በከሳሽ በኩል ደግሞ ሰበር ሰሚ ችሎቱ የሰጠው የህግ ትርጉም ነው፤ ህጉ ከዚህ ቀደም የነበረ በመሆኑ በክርክር ወቅት ሊነሳ ይገባ ነበር፤ የማቅረቢያ ጊዜው አልፏል፤ ክስ ማቅረብ ሀሰተኛ ምስክርነት ወንጀል ሊሆን አ

👍2
ይችልም በማለት ተከራክረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር የመረመመረ ሲሆን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 6 ፍርዱ ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ የተሰጠው በሀሰት ተዘጋጅቶ የቀረበውን ሰነድ ወይም ሀሰተኛ ምስክርነትን ወይም መደለያን ወይም ወንጀል ጠቀስ የሆነ ተግባርን መሰረት በማድረግ ሲሆንና አቤት ባዩም ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት አስፈላጊውን ትጋት አድርጎ ለማውቅ ያለመቻሉን ለማስረዳት የቻለ ከሆነ ዳግም ዳኝነት እንዲታይለት አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ አቤቱታውም አዲስ ማስረጃ ካገኘበት ወይም መኖሩን ካወቀበት ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ መቅረብ እንዳለበት ተቀምጧል፡፡ ተከሳሽ የወንጀል ድርጊት እንደሆነ ያቀረቡት ከሳሽ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ራሳቸው ተካፋይ በሆኑበት ክርክር ውሳኔ መስጠቱን እያወቁ ክስ መስርተው ፍርድ ቤቱን በማሳሳት ውሳኔ እንዲሰጥ በማድረጋቸው የወንጀል ተግባር የተፈጸመበት ክርክር ስለሆነ በሚል ነው፡፡ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ የተሰጠበት ጉዳይ የአስተዳደር ውሎች ላይ አለመግባባት ሲፈጠር በገላጋይ ዳኛ ሊታይ እንደማይችል የህግ ትርጉም የተሰጠው የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 315(2) ላይ በተደነገገው መሰረት ሲሆን ከሳሽ እና ተከሳሽ በዚህ መዝገብ በነበራቸው ክርክር ህጉን ጠቅሰው ያቀረቡት ክርክር እንደሌለ ከመዝገቡ መረዳት ተችሏል፡፡ በመዝገቡ ላይ ክስ የቀረበበት ወገን መከላከያ ሊያቀርብ ከሚገባ በቀር በሰበር ውሳኔ ስለተሰጠበት ክስ ሊቀርብ ስለማይገባ ፍርድ ቤቱን ማሳሳት ወንጀል ተፈጽሟል ሊባል አይችልም፡፡
በወንጀል ሕግ አንቀጽ 452 ላይ የተመለከተውን የወንጀል ፍሬ ነገር የሚያቋቁም ድርጊት ስለመሆኑ ጉዳዩ የማየት ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ቀርቦ የተሰጠ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከማመልከቻው ጋር አልቀረበም፡፡ በመሆኑም የወንጀል ድርጊት ተፈጽሟል በሚል የቀረበውን አቤቱታ አልተቀበለውም፡፡
በሌላ በኩል ዳግም ዳኝነት ሊጠየቅ የሚችለው ጉዳዩን ካወቀበት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሲሆን ተከሳሸ ለአቤቱታው ምክንያት እንደሆነ ያነሱት የሰበር ውሳኔ በቅጽ 22 ታትሞ የወጣው እና እንደሚታወቅ ግምት የሚወሰደው ከመስከረም ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን አቤቱታው የቀረበው የካቲት 3 ቀን 2012 ዓ.ም በመሆኑ ጊዜውን ጠብቆ የቀረበ አይደለም፡፡ በጥቅሉ ተከሳሽ ያቀረቡት አቤቱታ የህግ ክርክር ላይ በወቅቱ ሰበር ውሳኔ ከመስጠቱም በፊት አቅርበው ሊከራከሩበት ሲችሉ በመሆኑና የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 6 ላይ የተመለከቱትን ሁኔታዎች የማያሟላ በመሆኑ እና በማስረጃ ላይ የተፈጸመ ወንጀል ስለሌለ ፍርድ ቤቱ አቤቱታውን አልተቀበለውም፡፡
ት ዕ ዛ ዝ
1. ተከሳሽ ዳግም ዳኝነት እንዲታይልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡
2. መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የዳኛ ፊርማ አለበት፡፡
--------------------------------------------------------------------------
የኮ/መ/ቁ 262210
ጥቅምት 02 ቀን 2013 ዓ/ም
ልደታ ምድብ 4ኛ ንግድ ችሎት
ዳኛ፡- መካ ነስሩ
ከሣሾች፡- 1 - ሚ/ር አብዲ መሐመድ አብዲ
2 - ሚ/ር አማር አሊ አብዱ
ተከሣሽ፡- ሚ/ር ጀምስ ክረጅቺ
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሠጥቷል፡፡
ፍ ር ድ
ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የከሣሽ ጠበቃ በመጋቢት 10 ቀን 2010 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ ከሳሾች እና ተከሳሽ ታህሳስ 12 ቀን 2008 ዓ.ም አብኮም ኦር ማይኒንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተባለ ኩባንያ አቋቁመን የማዕድን ስራዎችን ስናከናውን ቆይተናል፡፡ ተከሳሽ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ፣ በመመስረቻ ጽሁፍ እና በንግድ ህጉ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እየተወጡ አይደለም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የተከሳሽ ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ አሜሪካ በመሆኑ እና ድርጅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያካሂደውን የማዕድን ማምረት ስራ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ መከታተል አይችሉም፡፡ ሌላው በመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 13 መሰረት የማህበሩን ሂሳብ ኦዲት ማስደረግ እና በበጀት አመቱ ማብቂያ ለጠቅላላ ጉባኤ የማቅረብ ግዴታውን አልተወጣም፡፡ ተከሳሽ በአሜሪካ ሀገር በስራ አስኪያጅነት የሚያንቀሳቅሱት ቤታ ትሬዲንግ የተባለ ኩባንያ ያላቸው ሲሆን ይህ ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ የማዕድን ማምረት ከሚሰራው አብኮም ኦር ማይኒንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ማዕድን ገዝቶ ለገበያ የማቅረብ ስራ ይሰራል፡፡ በዚህም ሀገሪቷ ልታገኝ የሚገባትን የውጪ ምንዛሬ አሳጥቷል፤ የድርጅቱንም ጥቅም ጎድቷል፡፡ በተጨማሪም ማህበሩ ሲመሰረት ለማህበረሰቡ ለልማት ተሳትፎ ለማድረግ የተገባውን ቃል እንዳይፈጸም ስላደረገ የማህበሩ መልካም ስም እና ዝና እንዲቀንስ አድርጓል፡፡ በሌላ በኩል የማህበሩን ገንዘብ ለሶስተኛ ወገኖች ያለ ምንም ምክንያት የሚከፍል መሆኑን ስለደረስንበት የማህበሩ ሂሳብ በገለልተኛ ሂሳብ አዋቂ እንዲጣራልን እንዲሁም ተከሳሽ ከማህበር ስራ አስኪያጅነት ስልጣኑ እንዲነሳልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል ፡፡
የተከሳሽ ጠበቃ በሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ/ም በተፃፈ መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበው ፍርድ ቤቱ ሳይቀበላቸው ቀርቷል፡፡በፍሬ ጉዳዩ ላይ በሰጡት መልስ ፍርድ ቤቱ በሚሾመው ገለልተኛ ኦዲተር የማህበሩ ሂሳብ ቢጣራ ምንም አይነት ተቃውሞ የለኝም፡፡ ከሳሾች በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል ማለት ያቀረቡት ማስረጃ እንደ ማስጠንቀቂያ ሊያሟላ የሚገባውን ነገር ያላሟላ በመሆኑ ከማስረጃነት ሊፋቅ ይገባል፡፡ተከሳሽ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ብቻ ሳይሆን ዋነኛ ባለድርሻም ጭምር ሲሆን የተከሳሽ ዜግነት አሜሪካዊ መሆኑን በማጉላት ሥራውን በአግባቡ ላለመወጣት በምክንያትነት አጉልተው ለማሳየት ይሞክሩ እንጂ ከሳሾችም አሜሪካውያን ዜጎች ናቸው፡፡ የማህበሩ አመራር በከሳሾች ሲመራ የነበረ ሲሆን በእነሱ አመራር ስር ከነበረበት ወቅት ውጪ አንድም ጊዜ ኦዲት ያልተደረገበት አጋጣሚ ስላልነበረ በዚህ ረገድ የቀረበው ሀሰት ነው፡፡ ድርጅቱ ለኦሮሚያ መንግስት ቃል የገባውን ማህበራዊ ግዴታ ለመወጣት እየሰራ ባለበት ወቅት በተለያዩ ፍሬ አልባ ክሶች ድርጅቱን እና ስራ አስኪያጁን በመክሰስ እንቅፋት የሆኑት ከሳሾች ራሳቸው እንጂ ተከሳሽ አይደለም፡፡ አንድ የኩባንያ ስራ አስኪያጅ ከስራው እንዲነሳ የሚጠየቀው ስራውን በአግባቡ ሊመራ ያልቻለ መሆኑ በግልጽ የተረጋገጠ እንደሆነ ብቻ ስለሆነ ከሳሾች ደግሞ ለዚህ ማስረጃ ስላላቀረቡ ክሱ ውድቅ ይደረግልን፡፡ ከሳሾች አቤቱታውን ያቀረቡት ያለባቸውን ዕዳ ላለመክፈል እንዲሁም የድርጅቱን ገንዘብ ያላግባብ ለመጠቀም ካላቸው ፍላጎት ያለምንም ምክንያት ያቀረቡት ጥያቄ ነው፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ይህንን ተመልክቶ ክሱን ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ከክሱ ያሰናብተን በማለት መልሳቸውን አቅርበዋል፡፡ የሠነድ እና የምስክሮች ስም ዝርዝር አያይዘው አቅርበዋል፡፡
ይህ ችሎቱም ግራ ቀኙን ባከራከሩ ፍሬ,ነገሮች ምስክሮቻቸውን አቅርበው እንዲያሰሙ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት አንድ የጋራ ምስክር እና በከሳሾች በኩል አንድ ምስክር አቅርበው አሰምተዋል፡፡የአብኮም ኦር ማይኒንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሂሳብ ማጣራት ተከናውኖ እንዲቀርብ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር የተመደበ ኦዲተር የሂሳብ ማጣራት ሪፖርት አቅርቧል፡፡
ፍርድ