ስድብ ተሰድቤያለሁ በሚል ምክንያት ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ።
------------------------------------------------
ተከሳሽ ሀይሉ ዳዲ ሳይና በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 555 (ሐ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሹ በሰው አካል ወይም ጤንነት ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ጥቅምት 20/2013 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 11፡15 ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው “ዕውቀትአምባ ትምህርት ቤት” ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የግል ተበዳይ ወ/ሮ መስታውት ሀይሉን ብሄርን መሰረት ያደረገ ስድብ ሰድባኛለች በሚል ድንጋይ በመወርወር እና አፏን በመምታት የላይኛው የፊት ለፊት ጥርሷ እንዲሰበር እና የታችኛው ከንፈሯ እንዲሰነጠቅ በማድረግ በፈፀመው ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል ።
ለፌደራሉ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ወንጀል ችሎት ህዳር 08/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዐቃቤ ህግ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ለፍርድ ቤቱ ያስረዱልኛል ያላቸውን ዝርዝር የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን ተከሳሽ መከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ከዚህ በፊት የጥፋት ሪከርድ የሌለበት መሆኑ ፣ዝቅተኛ የትምህርት እና የኑሮ ደረጃ ከግምት ውስጥ በማስግባት እና ሶሰት የቅጣት ማቅለያዎች በመያዝ ተከሳሽን ያርማል መሰል አጥፊዎችን ያስተምራል በሚል በ2 ዓመት ከ3 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ።
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

👍1
የኢትዮ-ቴሌኮምን ንብረት የሰረቁት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ፡፡
--------------------------------
ሸሽጉ ካሰዉ እና ሲሳይ ጌትነት የተባሉት 1ኛ እና 2ኛ የዐቃቤ ህግ ተከሳሾች የተከሰሱበትን ወንጀል የፈጸሙት የካቲት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ሲሆን ቦታዉም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 011 ልዩ ቦታዉ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ነዉ፡፡
ሁለቱም ተከሳሽ ግለሰቦች የማይገባቸዉን ብልጽግና ለራሳቸዉ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰዉ ለማስገኘት አስበዉ ንብረትነቱ የኢትዮ-ቴሌኮም የሆነና የህዝብ ስልክ ቋሚ መጠለያ /ቡዝ/ ሆኖ ሲያገለግል የነበረዉን ግምቱ 20000/ሀያ ሺህ ብር/ የሚገመት ብረት ካልተያዙት ግብረአበሮቻቸዉ በመቀናጀት እያንከባለሉ ሲወስዱ በአካባቢዉ ህብረተሰብ ተደርሶባቸዉ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡ ወንጀሉን በዋና አድራጊነት በመፈጸማቸዉም በከባድ የስርቆት ወንጀል ተከሰዋል፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 669/1/ለ ስር የተደነገገዉን በመተላለፋቸዉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዉ መጋቢት 2 ቀን 2012 ዓ.ም ችሎት ቀርበዉ የእምነት ክህደት ቃላቸዉን ሲጠየቁ ሁለቱም ተከሳሾች ወንጀሉን እንዳልፈጸሙና ጥፋተኛም እንዳልሆኑ ክደዉ ተከራክረዋል፡፡
ሆኖም የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ የካ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረቡለትን የሰዉና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ የወንጀሉን መፈጸም ካረጋገጠ በኋላ የጥፋተኝነት ብይን ያስተላለፈባቸዉ ሲሆን ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ባስቻለዉ 1ኛ ወንጀል ችሎት በ5 (አምስት) ዓመት ከ6 (ስድስት) ወራት እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡

Forwarded from Deleted Account
Administrative agancies rule making power at federal and oromia regional state research kalachuh bitilikulign ?
አለም አቀፍ የፍልሰት ስምምነት ሀገራዊ አፈጻጸም በተመለከተ ከባለድርሻ አካለት ጋር ውይይት ተካሄደ
___________
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብሔራዊ የትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ብሔራዊ እና አለም አቀፍ መደበኛ የፍልሰት ቃል- ኪዳን ስምምነት አፈጻጸም ረቂቅ ሪፖርትን በተመለከተ ከባለድርሻ አካለት ጋር ግብዓት የማሰባሰብ ውይይት ተካሄደ፡፡
በመድረኩ የብሔራዊ የትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈትህያ ሰዒድ እንደተናገሩት አገራችን ደህንነቱና ሥርዓቱ የተጠበቀ አለም አቀፍ መደበኛ የፍልሰት ቃል- ኪዳን ስምምነት አፈጻጸም ሰነዱን ከፈረሙ አገራት መካከል እንዷ መሆኗን እና ስምምነቱን ወደ ተግባር ለማስገባት መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ፣ አለም አቀፍና አገር ውስጥ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የተሳተፉት ዘርፍ ብዙ ተግባራት ተከናውናል ብለዋል፡፡
ኃላፊዋ አያይዘውም አገራት በእንቅስቃሴ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን መብት ለመጠበቅ፣ ክብር፣ ደህንነትና ጥቅም የሚያስከብር አገልግሎቶችን የተሻለ ለማድረግ አለም አቀፍ የቃልኪዳን ስምምነት (GCM) በ2018 በሞሮኮ ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት በተቋማቸው የተከናወኑ እና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ተግባራት ሪፖርት የሚያቀርቡበት የአሰራርና አደረጃጀት ሥርዓት የተዘረጋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ ፈትህያ ሰዒድ አክለውም አገራቸን ስምምነት ሰነዱን ከፈረመች ጀምሮ የሕግ ማዕቀፎችን በመፈተሸና በማሻሻል የዜጎችን መብትና ደህንነት የሚያረጋግጡ እንቅስቃሴ ሂደት ውስጥ የገቡ ዜጎቻችን ሆነ ሌሎችን መብቶቻቸውን የሚያረጋግጡ ሆነው እንዲገኙ የተለያዩ አዋጆችን በማውጣት፣ አደረጃጀቶችንና አሰራሮች በመዘርጋት፤ የተግባር ክንውን ሪፖርት ጉዳዩ የሚመለከታቸው መረጃ የሚሰጡ ባለድርሻ አካላትን በማሰባሰብ የተዘጋጀ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር እና ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባስብ የውይይት መድረኩ አላማ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ሰላም ሚኒስቴር፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ፣ የፌ/የከተሞች ስራ እድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ፣ ሴቶችን፣ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር፣ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ፣ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ዜጎች ከተለያዩ አገራት ሲመለሱ የምክር፣ የመጠለያ አገልግሎት የሚሰጡ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅቶችና የሀይማኖት ተቋማት ተወካዮች በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት በማድረግ ተጨማሪ ግብዓት ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም ለሁለት ቀን በሚደረገው የውይይት መድረክ በሀገር ደረጃ በመሪዎች የሚፈረሙ ስምምነቶች ከመፈረም ውጭ ምን ውጤት አመጡ የሚለውን በማየትና የአገራችን ዜጎች መብት፣ ደህንነታቸውን እና እንቅስቃሴያቸውን በተሻለ ደረጃ ለማድረስ እየተሰሩ ያሉ ውጤታማ ስራዎችን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስተዋወቅ ከሌሎች የአለም አገራት ጋር በመቀናጀት፣ ትብብር እና ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል የተሟላ የሰነድ በማዘጋጀት ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል እንደሚላክ ወ/ሮ ፈትህያ አያይዘው ገልጸዋል፡፡

አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት (The right to speedy trial)
--------------------
በወንጀል የፍትህ አስተዳደር ሥርዓት ዉስጥ የዜጎች በአፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት መሰረታዊ የሆነ መብት መሆኑ የሚታወቅ ነዉ፡፡ በመሆኑም በዚህ አጭር ጽሑፍ አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት ምንነትና በአገራችን ብሎም በአለማ አቀፍ ደረጃ ስላለዉ የህግ ማዕቀፍ ለመዳሰስ እንሞክራልን፡፡
አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት ምን እንደሆነ ከማየታችን በፊት የፍትህን ትርጓሜ ማየት ያስፈልጋል፡፡ ፍትህ ምን ማለት ነው የሚለው ጥያቄ እንደ አከባቢውና ጥያቄው የተነሳበት ሁኔታ ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተዛምዶ የሚታይ በመሆኑ የፍትህ ወይም የፍትሃዊነት ትርጉም ወጥ በሆነ አገላለጽ ሁሉንም የሚያግባባ ትርጉም ማግኘት ያስቸግራል፡፡
ቢሆንም የተለያዩ ዘርፎች ከራሳቸው አኳያ የፍትህን አስፈላጊነት ይሁን የፍትህን ምንነት ያስቀምጣሉ፡፡ ለአብነትም በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የሚገኙ አዋቂዎች ፍትህን የሚመለከቱት ከማህበረሰባዊ እኩልነት አክዋያ በመሆኑ ከዚህ አንጻር ፍትህ ሲባል በግለሰቦች ይሁን በማህበረሰቦች መካከል ሊኖር የሚችለውን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ልዩነትን ወደ ጎን በመተዉ በእኩልነት ሊስተናገዱ ማህበራዊ ተሳትፏቸዉም በእኩልነት ሊረጋገጥላቸው እንደሚገባ እና እኩል ሆነው እንዲታዩ ከማድረግ አኳያ ትርጉም ይሰጡታል።
በሌላ በኩል ደግሞ ከኢኮኖሚ ዘርፍ አኳያ የሚመለከቱት ሰዎች ፍትሃዊነትን የሚመለከቱት ከሃብት አያያዝና አጠቃቀም ጋር በማቆራኘት በመሆኑ ፍትሃዊነት ሲባል ተቀራራቢነት ያለው የሃብት አጠቃቀም ወይም ደግሞ ሚዛናዊ የኑሮ ደረጃ መምራት የሚለውን ትርጉም እንዲይዝ አድርገው ይመለከቱታል። በህግ ሰዎች ዘንድ ደግሞ ፍትህ በአብዛኛው በፍርድ ሂደት ያለውን ሚዛናዊነትን ከማስጠበቅ አክዋያ የሚመለከቱት በመሆኑ ሰዎች በህግ እኩል ሆነው ፍርድ ማግኘት በሚገባቸው ጉዳይ ላይ ፍትሃዊ የሆነ ውሳኔ እንዲሰጣቸው የሚያመለክት ትርግዋሜ ይሰጡታል።
አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት ጽንሰ ሀሳብና ያለዉ የህግ ማዕቀፍ
አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት ጽንሰ ሃሰብ በመሰረቱ በሕጉ መሠረት፣ የተከሰሱ ሰዎች ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ግልጽ እና ፍትሃዊ በሆነ ሂደት የመዳኘት እና ተቀባይነት ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ ፍርድ ማግኘት እንዳለባቸዉ የሚያመላክት ነዉ::
እጅግ የተራዘመና የዘገየ የፍትህ ወይም የዳኝነት አሠጣጥ ሂደት ተከራካሪ ወገኖች ላይ ጥርጣሬ እና እምነት ማጣትን ከማሳደሩ እንዲሁም የፍትሕ ስርዓቱን ውጤታማነት እና ብቃት አጠያያቂ ማድረግ ከመቻሉም በላይ “የዘገየ ፍትሕ እንደተከለከለ ይቆጠራል” ከሚላዉ የሕግ ምሁራን አባባል አንጻር ፍትህ እንደተከለከለ ወይም እንደተነፈገ ሊያደርግ ይችላል፡፡
አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት (the right to speedy trial) በህግ ጥበቃ ያለው መሰረታዊ መብት ሲሆን በተለያዩ ሀገራት ህጎችም ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በአሜሪካ (The Sixth Amendment to the U.S.Constitution) በወንጀል የተከሰሱ ሰዎች አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት እንዳላቸው ተደንጓል፡፡ በአፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት ከድሮ ጀምሮ የነበረ መሰረታዊ መብት ሲሆን በእንግሊዝ በንጉስ ሄነሪ ሁለተኛ (1154-1189) ጊዜ እንግሊዛውያን አፋጣኝ ፍትህ ማግኘት እንዳለባቸው በህግ ተደንግጎ ነበር፡፡ በ1215 እ.ኤ.አ ደግሞ ንጉሱ በእጁ የሚገኙ የፍትህ ጥያቄዎችን ማዘግየት እንደማይችል በማግና ካርታ (Magna Charta) በግልጽ ደንግጎ ነበር፡፡
ይህ ፍትህን በአፋጣኝ የማግኘት መብት ዓለም በተለያዩ አለም አቀፍ፣ አሕጉር አቀፍ እና በአገራችን የሕግ ማዕቀፎች ላይ የተረጋገጠ ሲሆን ሁሉም ድንጋጌዎች የፍትሕ ጥያቄ ተገቢና ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ምላሽ ሊሰጠው እንደሚገባ ያለመክታሉ፡፡
ለምሳሌ የሲቪልና የፖለቲካ ምብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን(ICCPR) በአንቀፅ 14 (3)(ሐ) ላይ በወንጀል ጉዳይ ተከሶ የቀረበ ሰው “አግባብ በሆነ ሁኔታ ሳይዘገይ የመዳኘት” መብት ያለው መሆኑን የደነገገ ሲሆን ከአህጉራዊ የሕግ ማዕቀፎች ዉስጥ ደግሞ የአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች ቻርተር(ACHPR) በአንቀፅ 7 (1) (መ) ላይ ማንም ሰው የደረሰበትን በደል ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ አድሎአዊ ባልሆነ ፍርድ ቤት ወይም የፍርድ አካል የመዳኘት መብት እንዳለው አስቀምጧል፡፡
ወደ አገራችን የህግ ማዕቀፍ ስንመጣ አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስሥት በአንቀፅ 20(1) ስር የተከሰሱ ሰዎች ክስ ከቀርበባቸው በኋላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ በመደበኛ ፍርድ ቤት ለህዝብ ገልፅ በሆነ ችሎት የመሰማት መብት ያላቸው መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ከዚህ የሕገ መንግስሥት ድንጋጌ እንደምንረዳዉ የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት መረጋገጥ ያለበት እንደየጉዳዩ ሁኔታ ግልጽ በሆነ ችሎት ሲሆን ይህ ሲባል ከተከሳሹ በተጨማሪ ማህበረሰቡም ስለ ጉዳዩ ሂደት በቂ ግንዛቤ እንዲኖረዉና ፍትህ ሲሰጥ ለመታዘብ ወይም ለማየት እድል ይሰጠዋል፡፡ በሕገ መንግስቱ ከተደነገገዉ ድንጋጌ በተጨማሪ የወ/መ/ስ/ስ/ህጋችንም ላይ ይህንን መሰረታዊ መብት አፈጻጸም የሚያረጋግጡ የተለያዩ ድንጋጌዎች ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ከጌዜ ቀጠሮ ጋር በተገኛኘ፣ ከምርመራ ጊዜና ሪፖርት አደራረግ ጋር በተገኛኘ እንዲሁም ምርመራ ከተጠናቀቀ በኃላም በአቃቤ ህግ በኩልም ሆነ ከፍርድ ቤት በኩል በጉዳዩ ላይ በጊዜ ዉሳኔ መስጠት ስለማሰፈለጉና ፍትህን በጊዜ ከመስጠት ጋር የሚገኛኙ ድንጋጌዎችን እናገኛለን(የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ አንቀጽ 59፣37፣109 እና አንቀጽ 94 እና ተከታዮቹ)፡፡ በአፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት ዳኝነት ወይም የፍትሕ ጥያቄ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ያለመዘግየት ምክንያታዊ በሚባል አጭር ጊዜ ውስጥ ዳኝነት ወይም ፍትሕ የማግኘት መብት ነው፡፡ ይህ መብትም አላስፈላጊና ያልተንዘዙ ቀጠሮዎች እንዲኖሩ በማድረግ ዳኝነት ጥያቄ በቀረበበት ጉዳይ ላይ ውሳኔ የማግኘት መብትን ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት የሚረጋገጠው በህግ የተዘረጋን ስነ ስርዓት ተከትሎ ጉዳዩን ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ መምራት ስንችል ነዉ፡፡
ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ በአፈጻጸም ክፍተቶች ወይም በህግ የተዘረጋን ስነ ስርዓት ሙሉ በሙሉ ተከትለን ባለመሄዳችን ምክንያት የዜጎች በአፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት ጥያቄ ዉስጥ ሲወድቅ ይስተዋላል፡፡
እ.እ.አ በ2014 በተደረገዉ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሪፖርት ላይ በአብዛኛው የፍርድ ሂደት መጓተት የሚከሰተው በተራዘሙ የሕግ ሥነ-ሥርዓቶች፣ በታራሚዎች ብዛት፣ በፍትህ ሥርዓቱ የቅልጥፍና ማነስ ችግር እና በሰው ኃይል እጥረት ሳቢያ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
ቀልጣፋና ፈጣን ዳኝነት በዋናነት የተከሳሹ መብት ቢሆንም የተጐጂዎችና የሕብረተሰቡ ጥቅሞችንና ፍላጐቶችን የሚጠብቅ ነው፡፡ ተከሳሹ ጉዳዩ በተቻለ ፍጥነት ዉሳኔ እንዲያገኝለት እንደሚፈልግ ሁሉ ተበዳዮች/ተጐጂዎችም ጉዳዩ በጊዜ እንዲወሰንላቸዉ ይፈልጋሉ፡፡
ሕብረተሰቡም ቢሆን ጉዳዩ በተራዘመ ቁጥር የህዝብ እና የመንግሥትን ወጪና ጉልበት የሚያባክን በመሆኑ ቶሎ ዕልባት እንዲያገኝ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የቀልጣፋ እና የፈጣን ዳኝነት መርህ እጅግ በጣም ጠቃሚና ወሳኝ የሥነ-ሥርዓት ሕግ መርህ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡

በህገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣዉ ህግ ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የንቃተ ህግ፣ትምህርት ስልጠና ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በህገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣዉን ህግ አስመልክቶ በሀረሪ ክልል ለሶስት ቀናት የዘለቀ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናዉ የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዓቃቢያነ ህግ፣ዳኞች፣ መርማሪ ፖሊሶች፣የገቢዎችና የተለያዩ የባንክ ባለሙያዎችና አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ በክሪ አብደላ በስልጠናዉ ላይ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡
ስልጠናዉ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ አመራሮችና ባለሙያዎች አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን በህገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣዉ ህግ ዙሪያ ለሶስት ቀናት የዘለቀ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ከቀረበ በኋላ በርካታ ሀሳቦች ተሰንዝረዉ ዉይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ በማስመሰል ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ቁጥር 780/2005 ዓ.ም ወጥቶ በስራ ላይ እንደሚገኝ ይታወሳል፡፡
https://t.me/lawsocieties
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የንቃተ ህግ፣ትምህርት ስልጠና ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በህገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣዉን ህግ አስመልክቶ በሀረሪ ክልል ለሶስት ቀናት የዘለቀ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናዉ የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዓቃቢያነ ህግ፣ዳኞች፣ መርማሪ ፖሊሶች፣የገቢዎችና የተለያዩ የባንክ ባለሙያዎችና አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ በክሪ አብደላ በስልጠናዉ ላይ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡
ስልጠናዉ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ አመራሮችና ባለሙያዎች አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን በህገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣዉ ህግ ዙሪያ ለሶስት ቀናት የዘለቀ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ከቀረበ በኋላ በርካታ ሀሳቦች ተሰንዝረዉ ዉይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ በማስመሰል ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ቁጥር 780/2005 ዓ.ም ወጥቶ በስራ ላይ እንደሚገኝ ይታወሳል፡፡
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ስለ ``መሰየም`` መሰረታዊ ነጥቦች እና ህጋዊ ውጤቱ
******
የሰዎች የቀደመ የወንጀል ታሪክ በቀጣይ ህይወታቸው ወይም ኑሯቸው ላይ የሚያስከትለው አሉታዊ ተጽዕኖ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ለአብነት ስራ ለመቀጠር ወይም ለመምረጥና ለመመረጥ ወ.ዘ.ተ ከወንጀል ቅጣት ነፃ መሆን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት በፈጸመው ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ሰው ቅጣቱን ጨርሶ ከማረሚያ ቤት ቢወጣ እንኳን የቀደመ ታሪኩ ተመዝግቦ ስለሚቆይ ከላይ የተጠቀሱትን እና መሰል ተግባራትን ለመከወን እና ለመሳተፍ እንዳይችል ያደርገዋል፡፡
ከዚህም ሌላ ወንጀል ፈጽሞ የተቀጣ ሰው ሌላ ወንጀል ፈፅሞ እንደገና ቢከሰስ የወንጀሉ ሪከርድ እስካለ ድረስ በወንጀል ህግ አንቀጽ 67 መሰረት የቀድሞ የወንጀል ታሪኩ በቅጣት ማክበጃነት ይቀርብታል፡፡
በመሆኑም ቀድሞ በወንጀል ተቀጥቶ ቅጣቱን የጨረሰ ማንኛውም ሰው ታሪኩ የሚፋቅለት በወንጀል ህጉ እና በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ስነ-ስርዓት መሰረት በተቀመጡት ድንጋጌዎች መሰረት አቤቱታውን አቅርቦ የወንጀል ቅጣቱን ጥሎበት በነበረው ፍርድ ቤት ሲሰየም ነው፡፡
መሰየም የተወሰነ የጥፋተኝነት ውሳኔና የተጣለ ቅጣት እንዳልነበር ተቆጥሮ እንዲሰረዝ ያደርጋል፡፡ ይህም ማለት ተጥሎበት በነበረው የወንጀል ቅጣት ምክንያት የገጠሙት ክልከላዎች ቀሪ ይሆናሉ፤ ወንጀልን ፈጽሞ እንደማያውቅ ሰው ተቆጥሮ ከወንጀል ነጻ ምስክር ወረቀት ሊያገኝ እና ስራ ሊቀጠር፣ ምርጫም ሊመርጥ ወይም ሊመረጥ ይችላል፡፡
በወንጀል የተቀጣ ሰው የመሰየም ጥያቄ ሊያቀርብ የሚችለው፡-
• በወንጀል ህግ አንቀጽ 232 /1/ የተወሰነበትን ቅጣት የፈጸመ ወይም ቅጣቱ በይርጋ ወይም በይቅርታ የቀረለት ወይም ፍርዱ ወይም የቅጣቱ አፈፃፀም የታገደለት ወይም በአመክሮ የተለቀቀ ማንኛውም ተቀጪ ህጉ የሚጠይቀውን መስፈርት ካሟላ እንዲሰየምና ንጹህ ስሙ እንዲመለስለት ቅጣቱን ለጣለበት ፍርድ ቤት ጥያቄ ሲያቀርብ፡፡
• ተቀጪው በጽኑ እስራት የተቀጣ፣ ከሀገር እንዲወጣ የተፈረደበት ወይም ንብረቱ እንዲወረስ የተወሰነበት እንደሆነ ቅጣቱ ከተፈፀመበት ወይም በይርጋ ከታገደበት ቀን አንስቶ ወይም ቅጣቱ ተቀጪው ቅጣቱ በይቅርታ በመሻሩ ምክንያት ተቀጪው ከተለቀቀበት ቀን ጀምሮ ወይም ታግዶለት ወይም በአመክሮ ተፈትቶ የፈተናውን ጊዜ በሰላም ጨርሶ እንደሆነ፤ በአመክሮ ከተፈታበት ቀን አንስቶ በትንሹ የአምስት ዓመት ጊዜ ማሳለፍ ይኖርበታል፡፡ ከላይ ከተዘረዘሩት ውጪ ባሉት ሁኔታዎች ማለትም በቀላል እስራት የተቀጣ እነደሆነ በትንሹ የሁለት ዓመት፤ በደንብ መተላለፍ ጥፋት ቅጣት ተጥሎበት የነበረ ሰው ቢያንስ አንድ ዓመት ጊዜ ያለፈው እንደሆነ፡፡
• ሌላኛው መስፈርት ከላይ በተጠቀሱት የአምስት ወይም የሁለት ወይም የአንድ ዓመታት/ ዓመት ጊዜ ገደብ ውስጥ ተቀጪው ምንም ዐይነት ጥፋት ፈጽሞ ሳይከሰስ ወይም አቤቱታ ሳይቀርብበት መልካም ጠባዩን እንደጠበቀ የመኖሩን ጉዳይ ነው፡፡ የተቀጪው ሌላ ወንጀል አለመፈጸም ወይም አለመከሰስ ለጠባዩ መታረም ትልቁ ማሰረጃ ነው፡፡
• አራተኛው መስፈርት ተቀጪው የተወሰነበትን ተጨማሪ ቅጣት ፈጽሞ መገኘት ነው፡፡ ተጨማሪ ቅጣት የሚባሉት እንደ ካሳ፣ የዳኝነት ወይም ኪሳራ ክፍያዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም የወንጀል ቅጣቱን ከመጨረሽ በተጨማሪ ተቀጪው ፍርድ ቤቱ የወሰነበትን ተጨማሪ ቅጣትም ከፍሎ ማጠናቀቅ አለበት፡፡
የቀረበው የመሰየም ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘት ውጤት
...............
አንድ ተቀጪ የመሰየም ጥያቄ አቅርቦ ጥያቄውን ፍርድ ቤቱ ከተቀበለው እና ከሰየመው መሰየሙ የሚያስከትላቸው ውጤቶች በወንጀል ህግ አንቀጽ 235 ንዑስ አንቀጽ ከ1-3 ተመልክተዋል፡፡ እነርሱም፡-
1. የቅጣቱ ፍርድ ከፍርድ የግል ሰሌዳ ይፋቅለታል፣ ለወደፊትም እንዳልተፈረደበት ይቆጠራል የጥፋተኝትና የቅጣት ውሳኔ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል፣
2. በመሰየም የተሠረዘውን ቅጣት አንስቶ ተቀጪውን መውቀስ ወቃሹን በስም ማጥፋት ወንጀል ያስቀጣል፣
3. ተቀጪው ከተሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ተወስኖበት ከነበረው ከመብት፣ ከማዕረግ ወይም የችሎታ ማጣቱ ቀርቶለት ህዝባዊ መብቱንና ቤተሰብ ማስተዳደርና የሙያ ሥራ

👎1
የትራፊክ ምልክት በመንቀል ተሸክሞ ሲሄድ የተገኘው ተከሳሽ በፈፀመው ከባድ ወንጀል በፅኑ እስራት እና በገንዘብ ተቀጣ ።
-------------------------------------------------------
ንብረትነቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመነት ኤጀንሲ የሆነውን የትራፊክ ምልክት በመንቀል ተሸክሞ ሲሄድ የተገኘው ተከሳሽ በፅኑ እስራት እና በገንዘብ ተቀጣ።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው “አመዴ ማዞርያ ” ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ግዛቸው ሚልክያስ ጌታቸው የተባለው ተከሳሽ ጥቅም 06/2013 ዓ.ም በግምት ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ሲሆን ንብረትነቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የሆነ “ቁም!” የሚል የትራፊክ ምልክት ከነብረቱ የዋጋ ግምቱ 8‚317.50 (ስምንት ሺህ ሶስት መቶ አስራ ሰባት ብር ከሃምሳ ሳንቲም) የሚያወጣ ንብረት ተሸክሞ ሲሄድ የተያዘ በመሆኑ በፈፀመው ከባድ የመሸሸግ ወንጀል ዐቃቤ ህግ ተከሳሽ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 683(ሐ) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፏል ሲል ክስ መስርቶበታል።
የፌደራሉ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ወንጀል ችሎት ህዳር 08/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ለተከሳሽ ክሱ ተነቦለት እንዲከላከል ሲጠየቅ ”አውነት ነው ድርጊቱን ፈፅሚያለሁ በዚህም ጥፋተኛ ነኝ ” ሲል የእም ነት ቃሉን ያሰማ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ህግን ዝርዝር የሰው፣ የሰነድ እና የኢግዚቪት ማስረጃዎች ማየት እና መስማት ሳያስፈልገው ፤ ተከሳሹ ገና የ16 ዓመት ታዳጊ መሆኑ ፣ የኑሮ ደረጃው ዝቅተኛ ፣ ከዚህ በፊት የጥፋት ሪከርድ የሌለበት እና ጥፋቱን ማመኑ አራት የቅጣት ማቅለያዎች ተይዘውለት ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን ያርማል መሰል አጥፊዎችን ያስተምራል ሲል በ2 ዓመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት እና 1000( በአንድ ሺህ) ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

Forwarded from dersolgn michael
ስለ እቁብ ዋስትና ጥያቄ አለኝ ጥያቄየም የካርታ ዋስ (የውጭ ዋስ) ባለ እቁቡ እቁቡን በልቶት ምንም ሀብት ሳይተው ቢጠፋ ሙሉውን የተበላውን ብር የሚችለው የካርታ (የውጭ) ዋስ ነው? የውስጥ ዋሶችስ ምነው ጥቅማቸው? እባካችሁ በፍጥነት መልሱልኝ ale በተቻለህ አቅም በፍጥነት ይሁን ከአክብሮትጋ
የእውቅና አሰጣጥና የሶስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ
*******************************************
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የ2013 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ የፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች፣ በዋና መሰሪያ ቤቱ የሚገኙ የስራ ክፍል ኃላፊዎች፣ የየምድብ ችሎቱ አስተባባሪ ዳኞች፣ በየምድብ ችሎቱ የሚገኙ የስራ ክፍል ሃላፊዎች በተገኙበት አካሄደ፡፡
በግምገማው ላይ ባለፉት ሶስት ወራቶች የኮቪድ 19 ቫይረስን በመከላከል የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡ እየተከናወነ የሚገኝ መሆኑን፣ ፍርድ ቤቱ በተለይ የፍርድ ቤቱን ሰራተኞች አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ ስልጠናዎችን ማከናወኑ፣ ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የተሰሩ ስራዎች በጥንካሬ የሚነሱ ጉዳዮች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል አሁንም ቢሆን የሥነ ምግባር ችግሮች እየታዩ የሚገኙ መሆናቸው፣ አገልግሎትን በቀልጣፋና እና በጥራት መስጠት ላይ ችግሮች ያሉ መሆናቸው እንደ እጥረት የተነሱ ናቸው፡፡
የፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር በሰጡት የስራ መመሪያ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱ በጉዳዮች ፍሰት አሰራር የተደረገ እንደሆነ ማድረግ የሚያስፈልግ እንደሆነ፣ የስነ-ምግባር ችግሮች ላይ የተጠያቂነት ባህል ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እና የፍርድ ቤቱ ዳኞች እና ሰራተኞች ውጤታማ እና ቀልጣፋ የዳኝነት አገልግሎት በመስጠት የሕዝብ አመኔታ ለማምጣት እየተሰራ የሚገኘውን ስራ ወደ ተሻለ ደረጃ ሊያሳድጉ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በዚሁ ፕሮግራም ላይ የላቀ አፈጻጸም ላገኙ ባለሞያዎች፣ የዳኝነት አገልግሎቱን ውጤታማ ለማድረግ ልዩ አስተዋጽኦ ላድረጉ ባለሞያዎች እና ጡረታ ለወጡ ሰራተኞች ዕውቅና የመስጠት ተግባር ተከናውኗል፡፡

በረቂቅ የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በአዳማ ከተማ ወርክ ሾፕ ተካሄደ
_________
መድረኩ በረቂቅ የወንጀል ሥነ-ሥርዓት እና የማሰረጃ ሕግ እንዲሁም በህግ የበላይነት እና መልካመ አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ የፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትን ግንዛቤ ማሳደግ ላይ ትኩት ያደረገ ሲሆን በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በጀስትስ ፎር ኦል ፒ ኤፍ ኢትዮጵያ በጋራ ትብብር ተዘጋጅቶ ከኅዳር 12 ቀን 2013 ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በአዳማ ከተማ ተካሂዷል፡፡
የመድረኩ ዓለማም የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ረቂቅ ሕግ ዝግጅት ተጠናቆ እንዲጸድቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራ በመሆ የሕግ፣ የፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ረቂቁን በሚመረምሩት ወቅት ሰለአስፈላጊቱና የተረቀቀበት ሂደት እዲሁም በረቂቁ በተካተቱ አዳዲስ ፅንሰ ሀሰቦች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ዳባ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም ለ60 ዓመታት ገደማ በሥራ ላይ የቆየውን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዐት ሕግ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ሰፊ ጥናት እንደተካሄደ ጠቅሰው ሕጉን የማርቀቅ ሂደቱም ከ10 ዓመታት በላይ ወስዷል በዚህም በርካታ ባለሙያዎች ከፌዴራል እና ከክልል ፍርድቤቶች ፣ከዐቃቤሕግ ተቋም፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የሕግ ባለሙዎች ሲሳተፉበት ቆይቶ በአሁኑ ሰዓት ለምክር ቤቱ ተመርቶ እየታየ ይገኛል ብለዋል፡፡
አቶ ተስፋዬ አያይዘዉም ረቂቅ ሕጉ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት እና ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር የተጣጣመና የተቀመጡ መርሆችንና እሴቶችን ለማስፈጸም የሚያስችል በመሆኑ ዘመናዊና ቀልጣፋ የወንጀል ፍትህ አሰራር እንዲሰፍን ከማድረግ አንፃር ሰፊ እገዛ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የአርቃቂ ቡድኑ አባላት በሆኑት አቶ በላይሁን ይረጋ፣ አቶ እሼቱ ወ/ሰማያት፣ ወ/ሪት ትዕግስት መሐቤ እና ዶ/ር ውብሽት ሽፈራው ሰፋ ያለ ማብራሪያና ገለጻ የተደረገ ሲሆን ረቂቅ የውንጀል ሥነ-ሥርዓት ህጉ ጸድቆ ሥራ ላይ ሲውል ከወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርዐት ጋር ተያይዞ በወንጀል ፍርድ ሂደት ተጠርጣሪዎች እና ተከሳሾች ረዥም ጊዜ ፍትሕ ሳያገኙ የሚቆዩበትን ጊዜ በማሳጠር፣ የፖሊስ እና የዐቃቤ ሕግ ሚናን በማሳደግ ከመደበኛው የክርክር መስመር በተጨማሪ ለሌሎች አማራጭ ዕውቅና በመስጠት ፍርድ ቤት ላይ የሚኖረውን ጫና በመቀነስ ዘመናዊና ቀልጣፋ የፍትህ ስርዓት ለመዘርጋት በሚደረገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል።
እንደ አርቃቂ ቡድኑ አባላት ገለጻም ረቂቅ ሕጉ ከአማራጭ የቅጣት አተገባበር መፍትሄዎች እና በወንጀል ጉዳዮች የአለም ዓቀፍ ትብብርን የሚመለከቱ ጠቅላላ ድንጋጌዎች ጋር ተያይዞ ልዩ ልዩ የትብብር ዓይነቶች የሚፈጸምበትን ሥነ ሥርዓት እና ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠት የሚመለከቱ ዝርዝር ሥነ ሥርዓቶችን አካትቶ እንዲይዝ ተደርጓል በተጨማሪም የወንጀል ፍትሕ ፖሊሲውን ለማስፈጸም የተከሳሽን እና የወንጀል ተጎጅዎችን ሰብዓዊ መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር እንዲሁም የሕግ የበላይነትን ለማስፈን የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ነውም ተብሏል፡፡
በመጨረሻ በመድረኩ የተለያዩ ጥያቄዎችና ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን ከተነሱ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በተነሱ በአርቃቂ ቡድኑ ሰፋ ያለ ገለጻና ማብራርያ ተሰጥቷል፡፡