አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፍትህ ተደራሽነት ላይ ትኩረት የሚያደርግ ዌብነር የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል፡፡

***********************************************************

በኮቪድ -19 ወረርሽን ወቅት የፍትሕ ተደራሽነት ላይ ትኩረት የሚያደርግ በሕግ ባለሞያዎች የተዘጋጀ የዌብነር ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 6/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ላይ ይተላለፋል፡፡

በዚህ ፕሮግራም ላይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር በሀሳብ አቅራቢነት የሚሳተፉ ሲሆን ሌሎች ስመ ጥር የሕግ ባለሞያዎችም የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

ይህን ፕሮግራም ለመከታተል እንዲችሉ የሚከተለው ሊንከ በመክፈት እንዲመዘገቡ ተጋብዘዋል፡፡

https://us02web.zoom.us/webinar/register/WN_f70NDwuJTvqYU3eQ2iDMUg
ህብረተሰቡ የፊት ጭምብሎችን በማድረግ የጀመረዉን በጎ ተግባር በሌሎች ተግባራትም ሊያስቀጥል ይገባል
-----------------------------------------
የኮቪድ-19 ወርርሽን ለመከላከልና ስርጭቱን ለመቀነስ ያስችላሉ ተብሎ በመንግስት ከወጡ መመሪያዎች ዉስጥ አንዱና አስገዳጅ የሆነዉ ከቤት ዉጭ በማንኛዉም ቦታ የፊት ጭምብል የማድረግ መመሪያ በህብረተሰቡ ዘንድ የታየ መልካም ተግባርና ጅምር መሆኑ ከሰሞኑ የታየ ክስተት ሲሆን ህብረተሰቡ አሁንም ሳይዘናጋ በመንግስት የወጡ ህጎችን፣ ደንቦችን እና መመሪያዎችን ጠንቅቆ በማወቅና በባለድርሻ አካላት የሚሰጡ ምክሮችን በመተግበር ከዚህ አስከፊና ህይዎትን ከሚቀጥፍ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ራሱንና ሌሎችን ሊጠብቅ ይገባዋል፡፡
አዲስ የተሻሻለው የንግድ ሕግ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸደቀ

___________________

ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ.ም ከ1952 ጀምሮ በሥራ ላይ የዋለው እና አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የንግድ ሕግ በአዲስ ተሻሽሎ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸደቋል፡፡

በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የህግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማስረጽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በላይሁን ይርጋን ስለጉዳዩ ባነጋገርንበት ወቅት እንደተናገሩት የንግድ ሕጉ በ1952 ከወጣ በኃላ ለግማሽ ምዕተ አመታት ሳይሻሻል የቆየ በመሆኑ አሁን ካለው ዘመናዊ የንግድ ሥርዓት ጋር አብሮ የማሄድ የሕግ ድንጋጌ ያሉት በመሆኑና በሌሎች ምክንያቶች የንግድ ሕጉን ማሻሻል አስፈልጓል ብለዋል፡፡

በ1952 ዓ.ም ጀምሮ የወጣው የንግድ ህግ ይዛቸው የነበሩት 5 መጸሐፍት ሲሆኑ መጽሐፍ 1 ስለ ንግድ ስራ፣ መጽሐፍ 2 ስለንግድ ማህበራት፣ መጽሐፍ 3 ስለማጓጓዣ እና ኢንሹራንስ፣ መጽሐፍ 4 ስለ ባንክና ተላላፊ ሰነዶች እና መጽሐፍ 5 ስለ ኪሳራ ህግ የተጻፉ ድንጋጌዎች መሆናቸውን ጠቁመው በተደረገው ጥናት መጸሐፍት 3 እና 4 የንግድ አካል ሳይሆኑ ራሳቸውን ችለው የፋይናስ አገልግሎት መድብል (code) እንዲሆኑ የተወሰነ መሆኑን እና መጽሐፍት 1፣ 2 እና 5 የንግድ ሕግ ተብሎ እንዲረቀቅ በተስጠው አቅጣጫ መሰረት ረቂቁ ተዘጋጂቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቁን ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም የንግድ ሕጉን የማርቀቅ ሂደት ከ18 አመት በላይ የፈጀ መሆኑን ጠቁመው በማርቀቅ ሂደቱ ሲሳተፉ የነበሩ ባለሙያዎች፣ ድጋፍ ላደረጉ የተለያዩ አካላት እና ሂደቱን ለመሩት የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ FDRE Attorney General የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
አለዎች ስለ ዝግጅታች ሁለ አመሰግናለሁ
please send me short note on
• Legal writing
• Evidence and
• conflict of law
CCI_ለፌደሬሽን_ምክር_ቤት_ያቀረበው_የውሳኔ_ሃሳብ.pdf
3 MB
CCI ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ፡፡
Hi selam nwu? Adisun draft Commercial code, engikizegna tirkgum kaleh lakegne
አለ ሰላም ላንተ ይሁን!! እስቲ ይህን ነገር ፓስትልኝ? እድሌ ከሆነ ይገኝ ይሆናል proclamation № 44/2001 Amhara region: proc to control proliferation and miss use of small arms
👍1
የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ዳኛ የሆኑት ወዳጃችን ዳዊት በዛብህ በአማርኛ የተፃፌ የጁሪስፕሩደንስ መፅሀፍ ይኸው ሼር አድርገው
"መከላከል ከመታከም ይቀላል፣ ቤት መቆየት ሆስፒታል ከመተኛት ይሻላል፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ አድርጎ መተንፈስ በማሽን ከመተንፈስ ይልቃል፣ ስለሆነም እነዚህን እንዲሁም ሌሎችን የመከላከያ መንገዶችን ሳንዘናጋ በመተግበር እራሳችንን እና የምንወዳቸውን ከኮሮና ቫይረስ በሽታ እንጠብቅ።"
ዶ/ር ሊያ ታደሰ (የኢፌዲሪ የጤና ሚኒስትር)
@MoHE_News @MoHE_News
10ኛው የኢትዮጵያ ክልል 'ሲዳማ ክልል' !

የደቡብ ክልልና አዲሱ የሲዳማ ክልል በዛሬው ዕለት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ፊት ቀርበው የስልጣን ርክክብ አካሂደዋል።

ውሳኔውን ተከትሎ ሲዳማ በሀገሪቱ 10ኛው ክልል የሚሆን ሲሆን ፥ የምክር ቤቱ አባላት ለሲዳማ ክልል ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፌዴራልና የክልል ፍ/ቤቶች በመተባበር መንፈስ መስራታቸውን ይቀጥላሉ!

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከክልል ፍርድ ቤቶች ጋር በጋራ ሊሰሩ የሚችሉበት ምህዳር እና የሚያገናኛቸው ሰንሰለት መነሻው ህግመንግስታዊ የዳኝነት ውክልና ስልጣናቸውና አስተዳደራዊ ግንኙነታቸውን ለመወሰን የወጡ ህጎች ናቸው፡፡

የኢፌዲሪ ህገመንግስት ስለፍርድ ቤቶች አወቃቀርና ስልጣን ግልጽ ድንጋጌዎችን ባስቀመጠበት ምዕራፍ ዘጠኝ የፌዴራል ከፍተኛና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ባልተደራጁባቸው ክልሎች የክልል ፍርድ ቤቶች የፌዴራል መጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን በውክልና የተሰጣቸው መሆኑን ይደነግጋል፡፡ ከዚህ በመነሳት የክልል ፍርድ ቤቶች የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሚመለከቷቸውን ጉዳዮች ከክልሉ የዳኝነት ጉዳዮች ጋር ደርበው ይሰራሉ፡፡ ለዚህም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለክልል ፍርድ ቤቶች የበጀት ማካካሻ እንደሚሰጥ ተጠቅሷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የተሰጡ የመጨረሻ ውሳኔዎችን የማየት ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ ይህም ፍርድ ቤቱ የፌዴራል ጉዳዮች ላይ በክልል ጠቅላይ ፍ/ቤቶች የተሰጡ ውሳኔዎችን በይግባኝ፤ የክልል ጉዳዮችን የተመለከቱ ውሳኔዎችን ደግሞ በሰበር ችሎት እንዲያይና ውሳኔውን እንዲያሻሽል ወይም እንዲያጸና ወይም እንዲሽር ያስችለዋል፡፡

በተመሳሳይ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን አደረጃጀትና ዝርዝር የስልጣን ወሰን ለማስቀመጥ የወጣው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁ.25/1988 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ጋር በጋራ ስለሚያገናኟቸው ዳኝነታዊና አስተዳደራዊ ሁኔታዎች ያመላክታል፡፡ ከነዚህም መካከል የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመዝገብ አያያዝና ጠቅላላ አሰራር ከክልል ፍርድ ቤቶች ጋር በመመካከር የሚሻሻልበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡ የክልል ፍርድ ቤቶች የፌዴራል ጉዳዮችን አስመለክቶ ስላከናወኑት ተግባራት በስታትስቲክስ የተደገፈ ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል፡፡

ከዚህም ባሻገር ዓዋጁ በሃገር አቀፍ ደረጃ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት፣ ምክትል ፕሬዝደንትና ዳኞች፤ የፌዴራል ከፍተኛና መጀመሪያ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝደንቶች፤ እና የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንቶች አባል የሚሆኑበት እንዲሁም ሌሎች የፍትህ አካላት የሚሳተፉበት አንድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉባዔ እንደሚኖር ይፈቅዳል፡፡ ይህ ጉባዔም በዳኝነት ስራ አስተዳደር ረገድ ባጋጠሙ ችግሮች ላይ ተወያይቶ መፍትሔ ይሰጣል፡፡ የፍርድ ቤቶችን አስራር ለማሻሻል የሚረዱ መመሪያዎችና ውሳኔዎችን ያሳልፋል፡፡ እንዲሁም አዳዲስ ህጎች እንዲወጡ ወይም ነባር ህጎች እንዲሻሻሉ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሃሳብ ያቀርባል፡፡

ሌላው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በህገመንግስቱና ይህንኑ መሰረት በማድረግ በወጡ ዓዋጆች በተሰጣቸው የዳኝነት ስልጣን በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሚሰጧቸው ውሳኔዎችና ትዕዛዞች በክልል ፍርድ ቤቶች እንዲፈጸሙ የፌዴራሉ ፍርድ ቤቶች ማዘዝ እንደሚችሉም በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት መሰረታዊ የህግ ሃሳቦች የፌዴራልና የክልል ፍርድ ቤቶች የተሳሰሩ መሆናቸውንና የሚያገናኟቸው በርካታ ጉዳዮች እንዳሉ የሚያመላክቱ ናቸው፡፡ ህገመንግስቱ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ የክልልና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በህግ አግባብ የዳኝነት እየሰጡ ቆይተዋል፡፡ በሃገራችን የተዘረጋው ህገመንግስታዊና ፌደራላዊ ስርዓት ተጠናክሮ፤ የክልልና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኝነታዊ ነጻነታቸውን ጠብቀው ፍትህ የመስጠት ሃላፊነታቸውን እየተወጡም ናቸው፡፡ ነጻና ግልጽ፤ ህጋዊና ፍትሃዊ፣ ተደራሽና የህዝብ አመኔታ ያለው ዳኝነት ለመስጠት በየጊዜውና በየሁኔታው የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ለጋራ ግብና ስኬታማነት የስልጣን ሚዛናቸውን ጠብቀው የየራሳቸውን ጥራት እያደረጉም ይገኛሉ፡፡

የፌዴራልና የክልል ፍርድ ቤቶች በውክልና እና በይግባኝ ስልጣናቸው የጋራ ባለጉዳዮች ሊኖሯቸው እንደሚችል የታመነ ነው፡፡ የዳኝነት ውክልና ስልጣን ባልተሰጣቸው ክልሎች እንኳን የፌደራል ፍርድ ቤቶች በተዘዋዋሪ ችሎቶች ዳኝነት ይሰጣሉ፡፡ በቪዲዮ ኮንፈረንስ እና በኢ ፋይሊንግ (የርቀት ችሎት ማእከሎች) በመታገዝም ባለጉዳዮች ባሉበት ከልል ሆነዉ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችሉ አሰራሮችም ተዘርግተዋል፡፡ ይህም በክልል የሚገኙ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ባይ ባለጉዳዮችን ከአላስፈላጊ ወጪ እና እንግልት ለመታደግ ተችሏል፡፡

አስተዳደራዊ ጉዳዮችንም በተመለከተ በትብብር መንፈስ በጋራ ጉባዔ በመምከር፤ በመልካም ተሞክሮ እና በመረጃ ልውውጥ በመታገዝ በመካከላቸው መልካም የግንኙነት ባህል አዳብረዋል፡፡ በዳኝት አገልግሎት አሰጣጥና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ በየጊዜው ምክክር ይደረጋል፡፡ የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ ይካሄዳል፡፡ በሃገራችን ቀልጣፋ፤ ተደራሽ እና የሚሻሻል የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት የጋራ አቋም የተያዘባቸው የመረጃ ልውውጥ ስራዎችም ይከናወናሉ፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወደ ክልሎች እንዲሁም ከክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ወደ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚላኩ ደብዳቤዎችና ማስታወሻዎች የመረጃ ልውውጥን ለማቀላጠፍ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ከማድረግ በዘለለ የሚደረጉት የመረጃ ለውውጦች ተቋማዊና ክልላዊ አደረጃጀት ላይ ጣልቃ በመግባት አሉታዎ ተጽእኖ ለማሳረፍ ታስበው የሚደረጉ አይደሉም፡፡

በተለይም በሃገራችን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታትና ለመከላከል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ባለበት ጊዜ ፍርድ ቤቶች የወረርሽኑ ማሰራጫ ማዕከል እንዳይሆኑ በመደበኛ አገልግሎት አሰጣጣቸው ላይ ለውጥ አድርገዋል፡፡ አስቸኳይነት ያላቸውን ጉዳዮች ብቻ እንዲያዩ በከፊል ዝግ ሆነው እንዲቆዩ በአመራሮቹ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ በዚህ ውሳኔ ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች የወረዱ የስራ አቅጣጫዎችን በደብዳቤ /በማስታወሻ / የክልል ፍርድ ቤቶችና ባለጉዳዮች እንዲያውቋቸው ማድረግ አስፈላጊነቱ አጠያያቂ አይሆንም፡፡ የክልል ባለጉዳዮች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት እንግልት እንዳይደርስባቸውና ለወረርሽኙ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ያግዛል፡፡ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶችም በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ተረድተውና ተገንዘብው በፍርድ ቤቶቻቸው የአሰራር ለውጥና ማሻሻያ እንዲሁም አስተዳደራዊ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ይረዳቸዋል፡፡ ይህም የመረጃ ልውውጥ የክልልም ሆነ የፌዴራል ፍርድ ቤቶቹ የጋራ የዳኝነት ተልዕኳቸውን በተጣጣመና በተናበበ መልኩ እንዲወጡ መልካም እድል ይፈጥርላቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በፌደራልና በክልል መንግስታት ህግ የመተርጎምና ዳኝነት የመስጠት ተልዕኮ የተሰጣቸው ፍርድ ቤቶች በህገመንግስቱ እና ህገመንግስቱን መሰረት አድርገው በወጡ አዋጆች ዜጎች ህጋዊና ፍትሃዊ ዳኝነት የማግኘት መብቶቻቸው እንዲከበሩባቸው በመተባበር መንፈስ መስራታቸውን ይቀጥላሉ፡፡

አካላዊ ርቀታችንን በመጠበቅ፤ አፍና አፍንጫችንን በጭምብል በመሸፈን፤ እጃችንን በሳሙናና በውሃ በተደጋጋሚ በመታጠብ፤ (በተቻለ መጠን) በቤት በመቀመጥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በጋራ እንከላከል!

ፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ቸልተኝነትን እና መዘናጋትን በማስወገድ ከመቼውም ግዜ በላይ በጥንቃቄና በእውቀት የኮሮና ቫይረስን እንቆጣጠረው!
________________

“ብልህ ከሆንክ በሰው ከደረሰው ትማራለህ…” የኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ወረርሽኙ ከፍተኛ ጉዳት በህዝባችን ላይ ከማድረሱ በፊት በርካታ የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች እና የጥንቃቄ መመሪያዎች ላይ የግንዛቤ እና የቅድመ መከላከል ስራ ቢሰራም ቸልተኝነትና መዘናጋት በወለደው ችግር የወረርሽኙ ስርጭት የህይወት ዋጋ እያስከፈለን ይገኛል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ከ8 ሚሊዮን ሰዎች በላይ በቫይረሱ ተጠቅተዋል፤ 436 ሺህ ሰዎች በላይ ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡አሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር በመያዝ ቀዳሚ ስትሆን፥ ካላየው አላምንም ያለችውን ብራዚልን በሁለተኛ ደረጃ፤ ሩሲያን ደግሞ በሦስተኛ ደረጃ አጥቅቷል፡፡

በአገራችን የመጀመሪያው ሰው በኮሮና መያዙ ከተረጋገጠ ከመጋቢት ወር ጀምሮ ባሉት 3 ወራት ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ፣ ህይወታቸውን የሚያጡ፣ በጽኑ ሕክምና ክፍል እየታከሙ ያሉ ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱ እጅጉን እያሳሰበ መጥቷል፡፡

መታዘዝ ከመስማት ይበልጣል እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከሉ ተግባራትን በማክበርና በማስከበር የነገ ተስፋችንን፣ ቤተሰባችንን እንዲሁም የአገራችን ህልውና ብሎም ደህንነት መጠበቅ የሁላችን እዳ እና ግዴታ መሆን አለበት፡፡

ከሁሉም በፊት ዛሬ ጤናችን በእጃችን ሳለ ከቁጥር ጎድለን እንዳንጎድል ቸልተኝነትን በማስወገድ ከመቼውም ግዜ በላይ በእውቀትና በማስተዋል ኮሮናን ልንቆጣጠረው ይገባል፡፡
Selam ye ale betesoch endet nachu..ye serategna wel(form of employment contract in ameharic) kalachu lakulegn pls?
BlueNileMyRiver
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ ቤቶች የኮቪድ-19ን በመከላከል መደበኛ አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸው መመሪያ ለማውጣት ረቂቅ መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑን ገለጸ፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሃገራችንም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቅርብ ጊዜ መፍትሔ እንደማይኖረው ከግምት ውስጥ በማስገባት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ወርሽኙን በመከላከል መደበኛ አገልግሎታቸውን መስጠት የሚችሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እየሰራ ይገኛል፡፡
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በሃገራችን የኮቪድ 19 ወርሽኝን ስርጭት ለመግታትና ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ፍርድ ቤቶች ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው አስቸኳይነት ያላቸው ጉዳዮች ብቻ በተረኛ ችሎት እንዲያስተናግዱ እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም መወሰኑ ይታወቃል፡፡
ነገር ግን ፍርድ ቤቶች ዜጎች በህግ አግባብ ፍትህ የሚያገኙበት ተቋማት እንደመሆናቸው ለረጅም ጊዜ በከፊል ዝግ ሆነው መቆየት እንደሌለባቸው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጽኑ ይገነዘባል፡፡
በመሆኑም ጠቅላይ ፍ/ቤቱ በኮቪድ 19 ዘመን ወረርሽኙን በመከላከል ዜጎች ፍትህ በሚጠይቁባቸው ጉዳዮች ላይ ፍርድ ቤቶች መደበኛ አገልግሎ መስጠት የሚያስችላቸውን ወጥ አሰራር ለመዘርጋት የሚመሩበት ረቂቅ መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ የረቂቅ መመሪያው ዝግጅት ሲጠናቀቅም የህግ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ግብአት እንዲሰጡበት ከተደረገ በኋላ ስራ ላይ እንዲውል ይደረጋል ብሏል፡፡
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከሐምሌ 10 ቀን 2020 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን “በኮሮና ቫይረስ (COVID 19) ምክንያት የተከሰተውን ሀገራዊ ሁኔታ አስመልክቶ ፍርድ ቤቶች ሊመሩበት የሚገባ አጠቃላይ መመሪያ (Comprehensive Guideline)” አውጥቷል እየተባለ የሚሰራጨው መረጃም ትክክል አለመሆኑን ገልጿል፡፡
የ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
በህጻናትና ሴቶች ላይ የሚፈጸመዉ ጥቃት አሰመልክቶ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተሰጠ መግለጫ
****************************************
በህጻናትና ሴቶች ላይ የሚፈጸመዉ ጥቃት ይብቃ የምንልበት ጊዜው አሁን ነዉ ፡፡
****************************************
ዛሬ ዓለማችን ብሎም ሀገራችንን የኮሮና ቫይረስ ተግዳሮት እየተፈታተነን ባለበት ወቅት በህጻናትና በሴቶች ላይ የሚደረሰው ጥቃት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ የገሀድ ነዉ፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ የሁላችንም ኃላፊነት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የህግና የፍትህ አካላት የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ጥረታቸውን ይቀጥላሉ ፡፡

-ለአብነት ባለፉት 3 ወራት ዉስጥ በአስገደዶ መድፈር በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክስ ከተመሰረተባቸው 40 መዝገቦች፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተግዳሮት ውስጥ ሆነንም ቢሆን እስከ አሁን ድረስ 8 መዝገቦች ላይ ዉሳኔ ተሰጥቶባቸዋል። ከእነዚህ ዉስጥ በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው የ64 ዓመቱ ተከሳሽ በአዲስ አበባ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዕድሜያቸው ስምንት እና ዘጠኝ አመት የሆኑ ሁለት ሴት ህፃናቶችን በተለያዩ ቀናቶች ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሞባቸዋል፡፡ፈጽሞባቸዋል፡፡

-በዚህም ተከሳሹ የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 627(1) ተላልፎ በመገኘቱ አራት ክሶችን ተመስርቶበታል፡፡ ጉዳዩ በፍጥነት ወሳኔ እንዲያገኝ በተደረገው እንቅስቃሴ ተከሳሽ የተከሰሰበትን ክስ ሊያስተባብል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን በአራቱም ክሶች ጥፋተኛ ነህ ብሎታል፡፡ በዚህም ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት የተከሰሰበት ድንጋጌ ጣሪያው 25 ዓመት በመሆኑ በ 25 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

-በተመሳሳይ ሁኔታ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ ከህፃንነቷ ጀምሮ ያሳደጋትን የ15 ዓመት የእንጀራ ልጁን የደፈረው ግለሰብ በ11 ዓመት ከ9 ወር ጽኑ እስራትየተቀጡ ሲሆን ቅጣታቸዉም በቂ አይደለምተብሎ በታመነበት ላይ የይግባኝ ክርክራችን ቀጥላል። ይህ ለአብነት ተገለጸ እንጂ በሌሎች የጥቃት ፈጻሚዎች ላይ ተገቢ የህግ ቅጣት እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ ከምንጊዜም በላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

-ሰለሆነም በሴቶችና ህፃናት ላይ በሚፈፀሙ ወንጀሎች ህብረተሰቡ ተጋላጭ እንዲሆን ጥንቃቄእንዲያደርግና ድርጊቱ ተፈፅሞ ሲያገኝም ከመቼውም በበለጥ ከፍትህ አካላት ጎን በመሆንና ይህን አሳፋሪና አሰነዋሪ ወንጀል በማጋለጥ እና ድርጊቱን ባለመተባበር እንዲሁም ለተጎጂዎቹ ምስክር በመሆን የህግ የበላይነት እና ፍትህ እንዲሰፍን የበኩላችን እንድንወጣ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀረባለን።

ኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም

አዲስአበባ
👍1
ምክር ቤቱ በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትሕ ትብብር እና በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ መስጠት ስምምነት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስትና በጅቡቲ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል የተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትሕ ትብብር እና በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ መስጠት ስምምነት ረቂቅ አዋጅን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል ፡፡

ስምምነቱ በአለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን ድንበር ዘለል ወንጀል ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና በሃገራቱ መካከል የሚኖረውን የሰላምና የደሕንነት እንቅስቃሴዎች ለማጠናከርእንደሚያግዝ የገለጹት አምባሳደር መስፍን ቸርነት በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦችን አሳልፎ መስጠት በሁለቱ ሃገሮች መካከል ሰላም፣ ጸጥታንና መረጋጋትን ለማረጋገጥም ሚናው የጎላ እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡

በእንደዚህ አይነት ጉዳዮች ከተለያዩ ሃገራት ጋር ስምምነቶች ተደርገዋል፣ እስካሁን ምን ውጤት ተገኝቷል? የሚሉ ጥያቄዎች ከምክር ቤት አባላት የተነሱ ሲሆን በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ለመያዝ ከተለያዩ ሃገራት ጋር ወንጀለኞችን የመለየት ስራ እንደተሰራና ሃገራቱ አሳልፈው እንዲሰጡ መጠየቁን የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ምክትል አቃቢ ሕግ አቶ ገለታ ስዩምአስረድተዋል፡፡

ምክር ቤቱ አክሎም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስትና በሩዋንዳሪፐብሊክ መንግስት መካከልየተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች በጋራ የጋራ የፍትሕ ትብብርና በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ መስጠት ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል ፡፡

ስምምነቱ በኢትዮጵያና ሩዋንዳ መካከል ካለው ትስስርና ድንበር ዘለል ወንጀሎች ተጋላጭነት አንጻር በተቀናጀ የዘመናዊ ምርመራ ዘዴ፣ መረጃና ማስረጃዎች ሳይጠፉ ምርመራ በማከናዎን ወንጀለኞች ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚያስችልና ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ስምምነት እንደሆነ አምባሳደር መስፍን አብራርተዋል ፡፡ ወንጀለኞች ኢትዮጵያ ከሩዋንዳ ጋር ያላትንና እያደገ የመጣውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከሕግ ለማምለጥ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን የገለጹት አምባሳደር መስፍን፣የስምምነቱ መጽደቅ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ጉልሕ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል ፡፡

ምክር ቤቱ የተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የዕቃዎች ሽያጭ ውሎች ስምምነት ረቂቅ አዋጅንም በሙሉ ድምጽ አጽድቋል ፡፡ ስምምነቱ ለአለም አቀፍ ንግድ ማደግ እና መስፋፋት እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን በማስወገድ የዕቃዎችን አለም አቀፍ ሽያጭ እንደሚያሳልጥ የጠቀሱት አምባሳደር መስፍን ወጪን በመቀነስና ድንበር ዘለል ንግድን በማበረታታት በአለም አቀፍ ደረጃ አስተማማኝ የንግድ ልውውጥ እንደኖር እንደሚያደርግም ነው የገለጹት

ምንጭ፡- ፓርላማ ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም.
via ኢ.ጠ.ዐ. ሕግ