አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
YES I CAN:
በፈጠራችሁ ኣድምጡት ከ እስራኤል የመጣች በኮረና የተያዘች ሴት ናት እስዋ ምትለን መስማት ኣለብን ፈጣሪ ምህረቱን ይስጣት ኣሜን:: via kbrom syum kb yapi bdu law school
@allafrican
Dear ' friends I will like volunteers I just need volunteers who would speak the local language like ' somali ' afar ' tigeringa ' and southern language 'oromifa and others we is live in addis
https://telegram.me/allafrican
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለ፣ በአህጉራችን አፍሪካ፣ እንዲሁም በሃገራችን ኢትዮጵያ ትልቅ ስጋት የደቀነ ወረርሽኝ ነው። በአሁኑ ወቅት ይህን ወረርሽኝ መግታት እና መከላከል ትልቅ ሃገራዊ የትኩረት አጀንዳ ነው። የዜጎችን ህይወት እና ጤና፤ የሃገርን ህልውና እና ደህንነት አደጋ ላይ የጣለውን የዚህን ወረርሽኝ ስርጭት ለመመከት የሁላችንም ጥረት እና ትብብር እጅግ አስፈላጊ ነው።

#Ethiopia : እስካሁን በተለያዩ ሃገራት የተከሰተውን የወረርሽኙን ስርጭት፣ እንዲሁም የአለም ጤና ድርጅት እና የሃገራችን የጤና ባለሞያዎች እና ተቋማት የሚያቀርቡዋቸውን ሞያዊ መረጃዎች እና ምክሮች ከግምት በማስገባት መንግስት ወረርሽኙን ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱ ይታወቃል። ህዝቡ ስለበሽታው መረጃ ኖሮት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዲችል ስለወረርሽኙ ባህሪያት እና መተላለፊያ መንገዶች በየጊዜው ከሚሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በተጨማሪ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የጥንቃቄ እርምጃዎች በየደረጃው እንዲወሰዱ መንግስት ውሳኔ ማስተላለፉ እና መመሪያዎች መሰጠታቸው ይታወሳል።

እነዚህን ውሳኔዎች እና መመሪያዎች ተግባራዊ በማድረግ ረገድ እስካሁን ያለው ሁኔታ በቂ እና አስተማማኝ ነው ለማለት አይቻልም። ይህን ሁኔታ ለመለወጥ አስፈላጊው መረጃ ለህዝቡ እንዲደርስ የሚደረገው ጥረት ተጥናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ነገር ግን ሆን ብለው እና ለህዝብ ደህንነት እጅግ አደገኛ በሆነ መልኩ አግባብነት ባላቸው የመንግስት መዋቅሮች የሚሰጡ መመሪያዎችን እየጣሱ ያሉ ግለሰቦች እና ተቋማት፣ እንዲሁም ሆን ብለው ወረርሽኙን በተመለከተ አደገኛ የሃሰትኛ መረጃ በማሰራጨት ህዝብን በሚያሸብሩ፣ እንዲሁም በዚህ አጋጣሚ አላግባብ የሆነ ትርፍ ለማካበት የአቅርቦት እጥረት የሚፈጥሩ ግለሰቦች እና ተቋማት ከሕገ – ወጥ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ለማሳሰብ እንወዳለን።

የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር ቁጥር 661/2002 ስለተላላፊ በሽታዎች ዝርዝር ድንጋጌዎችን የያዘ ሲሆን፤ይህ አዋጅ በግልጽ እንደሚያስቀምጠው፤ “ማንኛውም ወደ ሀገር የሚገባ ወይም ከሀገር የሚወጣ መንገደኛ ሀገሪቱ በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የጤና አጠባበቅ መስፈርቶች መሠረት….በተላላፊ በሽታ ሲጠረጠር ለምርመራ የመተባበር ግዴታ አለበት”። እንዲሁም “..ወረርሽኝ ካለበት ቦታ የመጣ ሰው ወደ ሀገር አንዳይገባ ሊታገድ ይችላል”፡፡ ይሄው አዋጅ በተጨማሪም “አግባብ ያለው የጤና ባለሙያ በወረርሽኝ ተላላፊ በሽታ የተያዘን ወይም የተጠረጠረን ማንኛውም ሰው ለተወሰነ ጊዜ ተገልሎ እንዲቆይ’’ ማድረግ እንዳለበት፤ በተጨማሪም “በወረርሽኝ ተላላፊ በሽታ የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው

ለምርመራ፣ለሕክምና…ፈቃደኛመሆን” እንዳለበት ተደንግጎዋል። በአዋጁ መሰረት እነዚህን ድንጋጌዎች መጣስ እስከ ስድስት ወር በሚደርስ እስራት ሊያስቀጣ ይችላል።
ከዚህም በተጨማሪ የኢፌድሪ የወንጀል ሕግ፤በአንቀጽ 514 ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ተለላፊ በሽታን ማስተላለፍን በህግ የሚያስቀጣ ወንጀል አድርጎ ደንግጎዋል። ይህን አንቀጽ በመጣስ የሚፈጽም ወንጀል እስከ አስር አመት የሚደርስ የእስራት ቅጣት ሊያስከትል እንደሚችል ሲሆን በተለይም ተላላፊው በሽታ በወረርሽኝ ወይም በኢፒደሚክ መልክ የተከሰተ ሲሆን፣ እንደነገሩ ክብደት ቅጣቱ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ወይም ሞት ሊያስቀጣ እንደሚችል የወንጀል ሕጉ ያሳያል። በተጨማሪም የወንጀል ሕጉ በአንቀጽ 830 የህዝብ ጤና እና ጤናማነትን ለመቆጣጠር በሚል ርዕስ ባሉት ደንጋጌዎች እንደተገለጸው፣ በሽታዎችን በተለይም ተላላፊ በሽታዎችንና ወረርሽኝ ስለመከላከል፣ መኖራቸውን ስለማሳወቅ፣ ለመከላከል የሚረዱ ህክምናዎችን ስለማድረግ ወይም ስለመቆጣጠር የወጣን መመሪያ መጣስ እሰከ ሶስት ወር በሚደርስ እስራት ሊያስቀጣ የሚችል ወንጀል ነው።

በተጨማሪም ለህዝብ ጤና አስጊ የሆን አደጋ እንደሚደርስ በማስፈራራት ሆን ብሎ ህዝብን ያሸበረ ከሶስት አመት በማይበልጥ ቅላል እሰራት ወይም እንደነገሩ ክብደት ከሶስት አመት በማይብለት ጽኑ እስራት ሊቀጣ እንደሚችል የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 485 ተደንግጎዋል።

የኮርኖ ቫይረስ ስርጭትን አስመልክቶ የሚሰጡ የጥንቃቄ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ጥቅሙ በቅድሚያ ለራስ፣ ቀጥሎም በዙሪያችን ላሉ ቤተሰቦቻችን፣ ወገኖችን እና ብሎም ለሃገር ነው። ይህን በመገንዘብ፣ ሁላችንም ተገቢውን ጥንቃቄ አቅም በፈቀደ መጠን እንድናደርግ ጥሪያችንን እያቀረብን፣ ነገር ግን ጉልህ በሆነ መልኩ የቅደመ ጥንቃቄ መመሪያዎችን በመጣስ የህዝብን ጤንነት እና የሃገርን ደህንነት አደጋ ላይ በሚጥሉ ተቋማት እና ግለሰቦች ላይ፤ እንዲሁም የኮሮና ቫይርስ ስጋትን ሰበብ አድርገው ሆን ብሎ ህዝብ የማሸበር ወንጀል በሚፈጽሙ ላይ፣ ከላይ በተጠቀሱት የህግ ድንጋጌዎችና ሌሎች አጋባብነት ያላቸውን ህጎች መሰረት በማድረግ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ በአፋጣኝ ለመውሰድ የምንገደድ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
via ናትናኤል መኮነን
https://telegram.me/lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
👍1
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
Judge Melak:
can you send me address of federal general attorney? post box numbr? phone number?
🛑BREAKING

የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 21 ደረሱ!
የኮሮና መዳኒት ከወደ አሜሪካ ይፋ ሆነ።

አሜሪካ የፀረ ወባ መድሃኒት ለኮሮና ቫይረስ ህክምና እንዲውል ፈቃድ ሰጠች።

#Coronavirus የአሜሪካ መንግስት እንዳስታወቀዉ ሁለት የፀረ ወባ መድሃኒቶችን ለኮቪድ 19 መፈወሻ ይዉል ዘንድ የአገሪቱ የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር ፍቃድ እንደሰጠዉ ታዉቋል፡፡የአሜሪካዉ የጤና እና የሰዉ ሃይል ዲፓርትመንት ባወጣዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ክሎሮኪን እና ሃይድሮክሲክሎሮኪን የተሰኙት የጸረ ወባ መድሃኒቶች ለኮቪድ 19ን እንደሚፈዉሱ ተረጋግጧል ብሏል፡፡

ባለስልጣኑ እንዳለዉ ሁለቱ የመድሃኒት አይነቶች በህክምና ባለሙያዎች ለህመምተኞች እንዲታዘዙ እና በተለያዩ ሆስፒታሎች እንዲሰራጩ እየተደረገ ይገኛል ነዉ ያለዉ፡፡ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈዉ ሳምንት እነዚህን ሁለት መድሃኒቶች ከፈጣሪ የተሰጡን ሲሉ መግለፃቸዉን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡

በርካታ ተመራማሪዎች እና የዘርፉ ኤክስፐርቶች ግን በመድሃኒቶች ላይ ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ የምርምር ማእከላት በመድሃኒቶቹ ላይ ምርመራ እያደረጉ እንደሚገኙ ዘገባዉ አስታዉቋል፡፡በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ከ140 ሺ በላይ ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ የተያዙባት ሲሆን ከ2 ሺኅ 500 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸዉ አልፏል፡፡

Via #EthioFM
በናትናኤል መኮነን በኩል የደረሰን
👍1
የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 25 ደረሱ!
በዓለም የጤና ድርጅት አማካኝነት የተሰጡ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19)ን የሚመለከቱ የምክር ሀሳቦች ፦

➡️ የኮቪድ-19 ቫይረስ ሞቃታማ እና እርጥበት የአየር ጠባይ ባለባቸው አካባቢዎችም ሊተላለፍ ይችላል

➡️ በረዶዋማ እና ቀዝቃዛማ የአየር ጠባይ አዲሱን የኮሮና ቫይረስ ሊያጠፋ አይችልም። ውጫዊው የአየር ሁኔታ ምንም ይሁን ምን መደበኛው የሰውነታችን የሙቀት መጠን ከ 36.5 °C እስከ 37 °C ያህል ሆኖ ይቆያል ፡፡

➡️ ሙቅ በሆነ ውኃ ገንዳ ውስጥ መዘፍዘፍም ከኮሮና ቫይረስ አይከላከልም። ይልቁንስ የሚመከረው ቶሎ ቶሎ እጅን በሳሙና እና ውኃ በደንብ መታጠብን ነው።

➡️ አዲሱ የኮሮና ቫይረስ በወባ ትንኝ ወይም ቢንቢ አማካኝነት ከአንድ ሰው ወደ ሌላኛው አይተላለፍም። በሽታው የሚተላለፈው በበሽታው የተያዘ ሰው በሚስል ወይም በሚያስነጥስበት አልያም ከአፉ እና ከአፍንጫው በሚወጡ እንደ ምራቅ የመሳሰሉ ፈሳሾች ነው።

➡️ የሰውነት ሙቀት መለኪያ መሣሪያዎች አንድ ሰው መደበኛ የሰውነት ሙቀቱ ከፍ ብሎ እንደው ለመለካት አገልግሎት ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ይሁንና መሣሪያው በበሽታ የተያዘውን ሰው ለይቶ ማወቅ አይችልም። ምክንያቱም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የትኩሳት ምልዕክት እስኪያሳዩ ከ 2 እስከ 10 ቀናት ሊወስድ ይችላል።

➡️ አልኮል ወይም ክሎሪን መላ ሰውነትን በመቀባት ሰውነት ውስጥ ዘልቆ የገባ ቫይረስን ለመከላከል አይረዳም። እንደዚህ አይነት ነገሮችን ሲጠቀሙ ደግሞ ዓይን እና አፍ ውስጥ እንዳይገቡ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ይሁንና አልኮል እና ክሎሪን ብዙ ሰዎች የሚነኳቸውን ወለሎች ለማፅዳት አገልግሎት ላይ ሊውሉ ይችላሉ።

➡️ የጉንፋን ወይም ሌሎች የመከላከያ ክትባቶች ከዚህኛው ቫይረስ ሊከላከሉ አይችሉም። ይህ ቫይረስ አዲስ እና ከሌሎች የተለየ ስለሆነ የራሱ ክትባት ያስፈልገዋል።

➡️ ጨዋማ የአፍንጫ ስፕሬ በመጠቀም የኮሮና ቫይረስን መከላከል አይቻልም። ይሁንና አልፎ አልፎ ይህንን የተጠቀሙ እና ጉንፋን የያዛቸው ሰዎች በቶሎ ሲሻላቸው ተስተውሏል።

➡️ ነጭ ሽንኩርት አንዳንድ ፀረ-ተሕዋስያን ሊኖረው የሚችል ጤናማ ምግብ ነው። ሆኖም ነጭ ሽንኩርት መብላት ሰዎችን ከአዲሱ የኮሮና ቫይረስ እንደሚከላከል የተረጋገጠ መረጃ የለም።

➡️ በየትኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች በአዲሱ የኮሮና ቫይረስ ሊጠቁ ይችላሉ። አዛውንቶች እና ቀደም ሲል እንደ አስም ፣ የስኳር በሽታ ፣ የልብ ህመም ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ የበለጠ ተጋላጭ ሲሆኑ ይስተዋላል ፡፡

➡️ አንቲባዮቲክስ መውሰድ ኮሮናን አይከላከልም። አንቲባዮቲክስ የሚወሰደው ባክቴሪያን ለመከላከል እንጂ ቫይረንስ ለመከላከል አይረዳም። ይሁንና በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎች ተያያዥ የባክቴሪያ በሽታዎች ገጥሟቸው ከሆነ አንቲባዮቲክስ እንዲወስዱ ሊደረግ ይችላል።

Via DW
በየኔ ቱዩብ ተለጥፎ ተገኘ
ለኮቪድ-19 የተዘጋጀ መጠይቅ

ይህ መጠይቅ አላማው ህብረተሰቡ የኮሮና ቫይረስ በሽታን( የኮቪድ-19) አስመለክቶ ያለውን የግንዛቤ ደረጃ ለመለካት እና አሰፈላጊውን የማሰተካከያ መንገዶች ለመቀየስ ታስቦ የተዘጋጀ መጠይቅ ነው። መጠይቁን በመሙላት ስለተባበሩን በቅድሚያ እናመሰግናለን። በአንድ መጠይቅ ውስጥ ትክክል ነው ብለው ያመኑትን በሙሉ ይምረጡ


https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScrZgQtb-JcqlRG59TwssT8QqgRchF0n1UScnIv5rEUV8tgqw/viewform


https://telegram.me/lawsocieties

🛑share እናድርግ።
ከፌ/ጠ/ፍ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

የፌዴራል ፍ/ቤቶች ለተጨማሪ 23 የስራ ቀናት በከፊል ዝግ ሆነው ይቆያሉ


ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት
https://telegram.me/lawsocieties