በመቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች፤ ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ካልተመለሱ የጀመሩትን የስራ ማቆም እንደሚቀጥሉ ገለጹ
በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች በትላንትናው ዕለት የጀመሩትን የስራ ማቆም ዛሬም በመቀጠላቸው በከተማይቱ የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ተዘግተው ዋሉ። ዳኞቹ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረቧቸው ጥያቄዎች እስኪፈቱ ድረስ የስራ ማቆማቸውን እንደሚቀጥሉ የትግራይ ዳኞች ማህበር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጿል።
በመቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች ስራቸውን ለማቆማቸው በዋነኛነት የጠቀሱት ምክንያት “የደህንነት ችግር አለብን” የሚል ነው። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫም፤ በመቐለ ሰባት ክፍለ ከተሞች ባሉ ፍርድ ቤቶች እና በከተማይቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚሰሩ ዳኞች “በደህንነት ስጋት” ምክንያት ስራ እንዳቆሙ ማሳወቃቸውን አረጋግጧል።
የትግራይ ዳኞች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ዳዊት ሃይለስላሴ፤ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረቧቸው አምስት ጥያቄዎች ከዳኞች ደህንነት ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የዳኞቹ የመጀመሪያ ጥያቄ በችሎት የሚመደቡ የጸጥታ አስከባሪዎችን የሚመለከት ነው።
🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15997/
@EthiopiaInsiderNews

" ከነገ ግንቦት 21 ጀምሮ ወደ ስራ ገበታ ይመለሳሉ " - ፅ/ቤቱ
ላለፉት 12 ቀናት በስራ ማቆም አድማ የቆዩት የመቐለ ዳኞች ስራ ለመጀመር መግባባት ላይ መደረሳቸው ተነግሯል።
ዳኞቹ ያቀረቡት የደህንነት ስጋት ጥያቄ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚከታተለው በተደረሰው ስምምነት ምክንያት ነው ወደ ስራ ገበታቸው ለመመለስ የወሰኑት።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት " ዳኞቹ ያለባቸው የድህንነት ስጋት በማስመልከት ከፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እና ከፍትህ አካላት አመራሮች ጋር ተወያይተዋል " ብሏል።
" በውይይቱ በዳኞቹ ላይ ያንዣበበው የደህንነት ስጋት በጥልቀት ተዳሷል ፤ ችግሩን ከስሩ በመረዳት ለመፍትሄው ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል " ሲል ገልጿል።
" የደህንነት ስጋቱ በዘላቂነት ለመፍታት የአጭርና የረጅም ጊዜ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። በተደረሰው መግባባት መሰረት የመቐለ ሰባቱ ክፍለ ከተማ ፍርድ ቤቶች ከነገ ግንቦት 21/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ገበታ ይመለሳሉ " ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

The 2025 National Moot Court Competition on International Humanitarian Law Kicks Off at University of Gondar
****
The 2025 International Humanitarian Law (IHL) National Moot Court Competition officially began today, the 27th of May 2025, in Gondar, Ethiopia, marking the 8th edition of this prestigious event. Jointly organized by the University of Gondar, School of Law and International Committee of the Red Cross (ICRC), this year’s competition focuses on the theme: “Protection of Health Care in Armed Conflict.”
Law students from Arbaminch University, Bahir Dar University, Haramaya University, Hawassa University, Jimma University, and the University of Gondar are participating in this important event.

በዓለምአቀፋዊ የሰብዓዊነት ህግጋት ላይ ትኩረት ያደረገው 8ኛው ሀገር አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር ፍጻሜውን አገኘ
****
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህግ ት/ቤት ከዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ጋር በመተባበር በዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊነት ህግጋት ላይ ትኩረት ያደረገው 8ኛው ሀገር አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር በጎንደር አስተናግዷል::
ግንቦት 21/2017 ዓ.ም ፍጻሜውን ባገኘው በዚህ ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምስለ ችሎት ውድድር በትናንትናው ዕለት የጅማ እና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተወዳዳሪ ተማሪዎች ለፍፃሜ ውድድር መድረሳቸው ይታወቃል። በመሆኑም ዛሬ በተደረገው የፍፃሜ ውድድር የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር ባደረጉት ውድድር የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቀዋል፡፡ እንዲሁም የጅማ ዩኒቨርሲቲ እና የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በቅደም ተከተል የሁለተኛና የሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ያጠናቀቁ ሲሆን፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ጥሩ የክርክር ጽሁፍ አቅራቢ ዘርፍ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪ የሆነችው ተማሪ ንያማል ቲቢትሀ ጥሩ ተናጋሪ በሚል ዘርፍ ልዩ ተሸላሚ ሆናለች፡፡ አሸናፊዎች በአፍሪካ ደረጃ ኬኒያ ናይሮቢ ላይ በሚካሄደው አህጉራዊ ፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

"የገቢ ግብር ቢቀንስ አሰሪዎችም በነጻነት ሰራተኛ እንዲቀጥሩ ያበረታታል ይህም የስራ እድል ፈጠራን ያሳድጋል" -አቶ መርዕድ ፍቅረዮሃንስ
በኢትዮጵያ ሰራተኞች በተደጋጋሚ የሚነሱት ጥያቄዎች ዋነኛው የገቢ ግብር ጉዳይ ነው። የገቢ ግብር በሰራተኛው ላይ ብቻ ሳይሆን በቀጣሪ ድርጅቶች ላይም ከፍተኛ ጫና የሚያደርስ እንደሆነ ባለሞያዎች ይናገራሉ።
መንግስት በአንፃሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና በሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ጭምር በተደጋጋሚ የተጠየቀው የተቀጣሪ ሰራተኛ ገቢ ግብር ቅነሳ ላይ ይኼ ነው የሚባል ምላሽ እስካሁን አልሰጠም።
በዚሁ ጉዳይ ሸገር ኤፍ ኤም የጠየቃቸው የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያው አቶ መርዕድ ፍቅረዮሃንስ የገቢ ግብሩ እርከን ቢስተካከል የሰራተኛ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ባይችል እንኳን የተወሰነ አፎይታ እንደሚሰጥ ያነሳሉ።
ባለሞያው በዝርዝር ምን አሉ ?
"መንግስት ለመጠናቀቅ 38 ቀናት በቀረው በጀት ዓመት ወደ 900 ቢሊዮን ብር ከቀረጥ እና ቀጥታ ካልሆነ ታክስ እንዲሁም 50 ቢሊዮን ብር ከመንግስት እና ከግል ተቀጣሪ ሰራተኞች ለመሰብስብ አቅዶ እየሰራ ነው።
50 ቢሊዮን ብሩን መንግስት የሚሰበስበው ከግል እና ከመንግስት የጡረታ ፈንዶች ነው። በአገር አቀፍ በግል እና በመንግስት የተቀጠሩ 4.4 ሚሊየን ሰራተኞች አሉ። 50 ቢሊዮን ብር የሚሰበሰበውም በሀቅ ከሚከፍሉት ከእነዚሁ ሰራተኞች ነው።
የተቀጣሪ ሰራተኛ ገቢ ግብሩ ቢቀነስ ምን ለውጥ ይመጣል?
የገቢ ግብሩ እርከን ቢስተካከል የ4.4 ሚሊዮን ሰራተኛ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ባይችል እንኳን የተወሰነ አፎይታ ይሰጣቸዋል።
በተጨማሪም አሰሪዎችም በነጻነት ሰራተኛ እንዲቀጥሩ ያበረታታል ይህም የስራ እድል ፈጠራን ያሳድጋል።
መንግስት ግብሩን ቢቀንስ ምንም አያጣም። ሰራተኛው በተዘዋዋሪ መልሶ በአንድም በሌላም መንገድ ለመንግስት ገቢ ማድረጉ አይቀርም።
የጎረቤት አገራትን ተሞክሮ በምሳሌነት ብናነሳ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ዝቅተኛ ክፍያ እየተከፈላቸው ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ናቸው።
ለማሳያም ኬንያ [እናንሳ] የሚቆርጡትን ግብር ከማየታችን በፊት የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማስተካከያ መደረጉን ተከትሎ የኢትዮጵያና የኬኒያ የመገበያያ ገንዘብ ከዶላር አንፃር አቻ መሆናቸው ልብ ማለት ይገባል፡፡
ከግብር አንፃር ስናይ ኬንያ 800 ሺህ ብር ከሚያገኝ ተቀጣሪ ላይ 35 በመቶ ግብር ስትቆርጥ ኢትዮጵያ ከ10 ሺህ 900 ብር ጀምሮ ተመሳሳይ ግብር ትቆርጣለች።
በኢትዮጵያ 600 ብር ከሚያገኝ ጀምሮ የገቢ ግብር ሲቆርጥበት በኬኒያ ግብር የሚቆረጠው 4 ሺህ ብር ከሚያገኝ ደሞዝተኛ ነው።" ሲሉ አስረድተዋል።
ከሰራተኛው ላይ የገቢ ግብር መቀነስ ለምን እንዳልተቻለ ባለፈው የምክርቤት አባላት የገቢዎች ሚኒስቴርን ጠይቆ ገቢዎች ሚኒስቴር በሰጠው ምላሽ የተሰጠውን ሃላፊነት ማስፈፀም እንጂ ይቀነስ፣ ይጨመር የሚልበት ስልጣን እንደሌለው አስረድቷል።
ሰራተኛው እያነሳ ያለው የገቢ ግብር ቅነሳ ጥያቄ ተገቢ ነው ያሉት አቶ መርዕድ ፍቅረዮሃንስ እንዴት ይቀነስ በሚለው ላይ ግን በስፋት መወያየት እና በጥንቃቄ ማየት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
Credit : Sheger FM 102.1
@TikvahethMagazine