አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#ፓስፖርት : ፖስፖርት ለማውጣት ፋይዳ መታወቂያ መያዝ የግዴታ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

ከሰኔ 1/2017 ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ ለፓስፖርት አገልግሎት ከሚስፈልጉ ዋና ሰነዶች ውስጥ አንዱ ይሆናል።

ከሰኔ 1 በኃላ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የፓስፖርት አገልግሎት ጥያቄ አቅርበው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ግለሰቦች ፓስፖርት ለመውሰድ ሲመጡ የፋይዳ መታወቂያ ፦
- ልዩ ቁጥር መያዝ፣
- QR ኮዱን በወረቀት አትመው መያዝ፣
- ዲጂታል ኮፒውን በ "Fayda ID" application በኩል መያዝ ወይም ትክክለኛውን QR የያዘ ሌላ አማራጭ ተጠቅመው ይዘው ሲመጡ ብቻ ነው አገልግሎት የሚያገኙት ተብሏል።

@tikvahethiopia
አዋጆች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቁ በኋላ ደንብ እስከሚወጣ ድረስ ረዥም ጊዜ እየወሰደ በመሆኑ አዋጆቹ እየተጣሱ እንደሚገኙ ተገለጸ።

በተለይም በቅርቡ የፀደቀው የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ደንብ ሳይወጣለት በመዘግየቱ ምክንያት በአዋጁ የተከለከሉ ተግባራት እየተፈጸሙ መሆኑን ምክር ቤቱ የከተማና መሰረተ ልማት የ9 ወራት ሪፖርት ባደመጠበት ወቅት አንስቷል።

ምክር ቤቱ እንደ ምሳሌ የጠቀሰው ይኸው አዋጅ 80 በመቶ የሪል እስቴት ግንባታ ሳይጠናቀቅ መሸጥን የሚከለክል ቢሆንም፣ ደንብ ባለመውጣቱ በአሁኑ ወቅት ግንባታ ያልተጀመረባቸው መሬቶች ሳይቀሩ እየተሸጡ እንዲሁም የተለያዩ ድርድሮች እየተካሄዱ መሆኑን አመልክቷል።

አዋጆች በቶሎ ደንብ ሳይወጣላቸው በመዘግየታቸው ክፍተቶች በመፈጠር አዋጁን የሚጥሱ አካላት እየተበራከቱ መምጣታቸው ስጋት እንደፈጠረም ካፒታል ሰምቷል።

በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላት ደንቦችን በማፋጠን የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ጥሪ ቀርቧል።

ይሁን እንጂ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር በበኩላቸው የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ አዋጅ ተዘጋጅቶ እንዲጸድቅ መደረጉንና አዋጁን ተከትሎ የማስፈጸሚያ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ረቂቅ ደንቡን የማዳበር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ በሪፖርታቸው አስታውቀዋል።

አዋጁ በመጽደቁ በሪል እስቴት አልሚዎች እና በቤት ገዥዎች መካከል ለዘመናት ሳይፈቱ የቆዩ ችግሮችን እየተፈቱ መምጣታቸው እና በቀጣይም አዋጁ ሲተገበር ችግሮችን መሰረታዊ በሆነ መልኩ አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል።

Source: capitalethiopia
#Ethiopianbusinessdaily
አንዱ ተጋቢ ከጋብቻ በፊት ባለው ንብረት ላይ ተጨማሪ ግንባታ በጋብቻ ውስጥ ከተደረገ የጋራ ንብረት ሳይሆን ያወጣውን ወጭ ይካፈላል/የፌደሬሽን ም/ቤት ውሳኔ❗️‼️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM