አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ንብረቱ ከጋብቻ በፊት በአንደኛው ተጋቢ የግል ንብረት መሆኑ ባልተካደበት ሁኔታ በይዞታ ማረጋገጫ ላይ የሌላኛው ተጋቢ ስም አብሮ መመዝገቡ ንብረቱን የጋራ የማያደርገው ስለመሆኑ የተሰጠ የሰበር ትርጉም። የሰበር ውሳኔው የፍ/ህ/ቁ 1195 ማስተባበል የሚቻልበት አግባብ የሚያሳይ ነው።የፌደራል ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት በፌ/ሰ/መ/ቁ 235844 አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
አዲሱ ህግ ፀደቀ‼️
ተራ አስከባሪ ግብር እንዲከፍሉ ተወሰነ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የታክሲ ተራ አስከባሪ ማኅበራት ከገቢያቸው 20 በመቶውን ለመንግሥት እንዲሰጡ የሚያስገድድ ደንብ አጽድቋል።

ደንቡ ማኅበራቱ “ዝግ እና መደበኛ የባንክ አካውንት" እንዲከፍቱና ከሁለት ዓመት በኋላ “ወደ ሌላ የሥራ ዘርፍ እንዲሸጋገሩ” ግዴታ ይጥላል።

“የተርሚናል አገልግሎት አሠራርና ቁጥጥር” የተሰኘው ደንብ፣ ኢንተርፕራይዝ በማለት የሠየማቸው ማኅበራት የሚደራጁት በከተማዋ የሥራና ክህሎት ቢሮ መስፈርት መኾኑን ታውቋል።

ኢንተርፕራይዞቹ 30 በመቶ  “የግዴታ ቁጠባ” መቆጠብ፣ 50 በመቶውን በተንቀሳቃሽ የባንክ ሒሳብ ማስቀመጥና ያንድ ዓመት ውል መፈረም እንዳለባቸውም ይደነግጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የተርሚናል አገልግሎት አሰራርና ቁጥጥር ደንብ ቁጥር 186/2017 ምን ይላል ?

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 አንቀጽ 95 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ደንብ አውጥቷል፡፡

ደንቡ ምን ይላል ?

በተርሚናል አገልግሎት ሥራ ላይ የሚደራጁ ተርሚናል ኢንተርፕራይዞች የሥራ እና ክህሎት ቢሮ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት እንደሚደራጁ ይገልጻል።

ቀደም ሲል ተደራጅተው በህጋዊ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የተርሚናል ኢንተርፕራይዞች መስፈርቱን አሟልተው ሲቀርቡ ዳግም እንዲደራጁ እንደሚድረገም ያመለክታል።

የአደረጃጀት መስፈርቱን ያሟሉ ማህበራት ሲደራጁ በተርሚናል ኢንተርፕራይዙ ስም መደበኛና ዝግ የሂሳብ አካውንት መክፈት እንደሚኖርባቸውም ይገልጻል።

በተርሚናል አገልግሎት ሥራ የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የሥራ ውል እንዲገቡ ይደረጋሉ።

የሚገቡት ውል ለ1 ዓመት ነው። የስራ አፈጻጸማቸው እየታየ ለአንድ አመት ለአንድ ጊዜ ብቻ ሊታደስ እንደሚችል ደንቡ ይገልጻል።

የተርሚ ማል ኢንተርፕራዞቹ የውል ዘመናቸው ከመጠናቀቁ በፊት የቁጠባ ካፒታላቸውን ታሳቢ በማድረግ ወደ ሌላ የሥራ ዘርፍ የሚሸጋገሩበር ሥራ በሥራና ክህሎት ቢሮ በኩል ይሰራል።

ኢንተርፕራይዞቹ ከሰበሰቡት ጠቅላላ ገቢ 30% (ሰላሳ በመቶ) የግዴታ ቁጠባ ይቆጠባሉ። 50% (ሃምሳ በመቶ) በመደበኛ ተንቀሳቃሽ የባንክ ሂሳብ ውስጥ ገቢ ይደርጋሉ።

የተርሚናል ኢንተርፕራይዞች ከሚያገኙት ጠቅላላ ገቢ ላይ 20% (ሀያ በመቶ) ለመንግስት ገቢ ያደርጋሉ።

(ሙሉ ደንቡ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" በ3 ወራት ውስጥ 943 ፍቺዎች እንዲሁም 53 ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዲፈቻዎች ምዝገባ ተከናውኗል !! "

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከፌደራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት ጋር  የፍቺ እና ጉዲፈቻ ውሳኔዎችን መዝግቦ በአንድ መስኮት አገልግሎት ለመስጠት የጋራ ስምምነት ፈጽመው እየሰሩ ሲሆን ላለፉት 3 ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን አፈፃፀም በጋራ ገምግመዋል።

በዚህም ወቅት በቀረበ ሰነድ 996 ተገልጋዮች በ3 ወራት የኩነት ምዝገባ አገልግሎቱን በፍርድ ቤቶች በአንድ መስኮት ማግኘታቸው ተመላክቷል።

ከዚህም ውስጥ ውሳኔ ያገኙ 943
#ፍቺዎች እንዲሁም 53 ውሳኔ የተሰጠባቸው #ጉዲፈቻዎች በወቅቱ ምዝገባ በማድረግ በአንድ ማዕከል በፍ/ቤቶች አገልግሎት መሰጠቱ ተመላክቷል።

Via
https://t.me/addisvaitalpress/9155

@tikvahethiopia