አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማዘመን እና ለማሻሻል የሚረዱ የተለያዩ የሪፎርም ተግባራት
ን በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ የታገዘ ማድረግ ውጤታማ፤ ጥራት ያለው፤ ቀልጣፋ እና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያግዝ ይታመናል፡፡
ፍርድ ቤቱ በዲጂታል የታገዘ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ እውን ለማድረግ የአይሲቲ መሠረተ ልማት ግንባታ የማከናወን፤ የመተግበሪያዎችን የማልማት እና አስፈላጊ ግብዓቶችን የማሟላት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ ቴክኖሎጂውን ከማልማት እና መሠረተ ልማት ከመገንባት ጎን ለጎን የዲጂታል አገልግሎቱን ለመተግበር የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እና የአሰራር ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡
በአዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀጽ 50 መሠረት ፍርድ ቤቶች በቴክኖሎጂ የተደገፈ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸውን አሰራር ስርዓት እንደሚዘረጉ እና የስርዓቱ አተገባበር በመመሪያ እንደሚወሰን ተመልክቷል፡፡
ይህ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የኤሌክትሮኒክ ዘዴ አቤቱታ አቀራረብ፤ ሙግት ማከናወን እና የሪከርድ አሰራር እና አስተዳደር መመሪያ (ረቂቅ) የተዘጋጀውም ይህንኑ በቴክኖሎጂ የታገዘ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ለመምራት የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ለማበጀት ሲሆን በዝግጅት ሂደቱም ከፍርድ ቤት ባሻገር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጎ በግብዓት ከዳበረ በኋላ ይህ ረቂቂ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡