አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የኮሮና መዳኒት ከወደ አሜሪካ ይፋ ሆነ።

አሜሪካ የፀረ ወባ መድሃኒት ለኮሮና ቫይረስ ህክምና እንዲውል ፈቃድ ሰጠች።

#Coronavirus የአሜሪካ መንግስት እንዳስታወቀዉ ሁለት የፀረ ወባ መድሃኒቶችን ለኮቪድ 19 መፈወሻ ይዉል ዘንድ የአገሪቱ የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር ፍቃድ እንደሰጠዉ ታዉቋል፡፡የአሜሪካዉ የጤና እና የሰዉ ሃይል ዲፓርትመንት ባወጣዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ክሎሮኪን እና ሃይድሮክሲክሎሮኪን የተሰኙት የጸረ ወባ መድሃኒቶች ለኮቪድ 19ን እንደሚፈዉሱ ተረጋግጧል ብሏል፡፡

ባለስልጣኑ እንዳለዉ ሁለቱ የመድሃኒት አይነቶች በህክምና ባለሙያዎች ለህመምተኞች እንዲታዘዙ እና በተለያዩ ሆስፒታሎች እንዲሰራጩ እየተደረገ ይገኛል ነዉ ያለዉ፡፡ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈዉ ሳምንት እነዚህን ሁለት መድሃኒቶች ከፈጣሪ የተሰጡን ሲሉ መግለፃቸዉን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡

በርካታ ተመራማሪዎች እና የዘርፉ ኤክስፐርቶች ግን በመድሃኒቶች ላይ ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ የምርምር ማእከላት በመድሃኒቶቹ ላይ ምርመራ እያደረጉ እንደሚገኙ ዘገባዉ አስታዉቋል፡፡በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ከ140 ሺ በላይ ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ የተያዙባት ሲሆን ከ2 ሺኅ 500 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸዉ አልፏል፡፡

Via #EthioFM
በናትናኤል መኮነን በኩል የደረሰን
አዲሱ የፅዳት ህግ‼️
ግለሰቦች የመኖሪያ አካባቢያቸውን እስከ 20 ሜትር ድርጅቶች ላይ ደግሞ እስከ 50 ሜትር የማፅዳት ኃላፊነት የሚጥለው ረቂቅ አዋጅ ውይይት እየተደረገበት መሆኑ ተገለፀ‼️

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከመንግሥትና የግል ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት አድርጓል።

ረቂቅ አዋጁ ግለሰቦች የመኖሪያ አካባቢያቸውን እስከ 20 ሜትር ድርጅቶች ላይ ደግሞ እስከ 50 ሜትር የማፅዳት ኃላፊነት እንደሚጥልና አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ውለው የሚጣሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች እንደሚከላከል ተገልጿል።

የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሊሴ ነሜ ረቂቅ አዋጁ አገር የጀመረችውን ፅዱና አረንጓዴ ኢትዮጵያን የመፍጠር እንቅስቃሴ የሚደግፍ መሆኑን ገልጸዋል።

ለአንድ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች ለአሰባሰብ አዳጋች እና አካባቢን በመበከል  ማህበረሰቡን ለተለያዩ የጤና ችግሮች እየዳረጉ ስለሆነ መቆም አለባቸው ብለዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ፈቲያ አሕመድ ረቂቅ አዋጁ ረዥም ዘመናት ማገልገል እንዲችል በርካታ ባለድርሻዎችን ያካተተ ውይይት በቀጣይነት እንደሚደረግበት ገልጸዋል።

ደረቅ ቆሻሻ በአካባቢ እና በሰዎች ደህንነትና ጤና ላይ እያስከተለ ያለውን ተፅእኖ እና ጉዳት ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጁ መዘጋጀቱን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
#Ethiofm