አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
አለሕግAleHig ️
ሚዲያዎች ሙያዊ በሆነ ጉዳይ ላይ ዘገባ ሲሰሩ መጠንቀቅ አለባቸው                 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇         በሀገራችን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሠረት ሊጣሉ የሚችሉት የቅጣት አይነቶች የሚከተሉት ናቸው:: ➨መቀጮ (ከ10 ብር - 10,000 ብር) ➨ቀላል እስራት (ከ 10 ቀን - 3 አመት) ➨ፅኑ እስራት (ከ 1አመት - 25 አመት) ➨የእድሜ ልክ እስራት እና ➨የሞት ፍርድ ናቸው በወንጀለኛ…
ተከሳሹ በአንድ መዝገብ ላይ በተለያዩ የወንጀል ድንጋጌዎች የተከሰሰ ሲሆን ቅጣቱ ጣሪያውን (25 ዓመት) ሳያልፍ መወሰን አለበት። ነገር ግን ወንጀሉ የተፈጸመበት ጊዜ የተለያየ ሆኖ ወይንም በተለያዩ የወንጀል መዝገቦች ፋይል ተከፍቶ የግል ተበዳዮችም በእያንዳንዱ መዝገብ ላይ የተለያዩ ሆነው በእያንዳንዱ የወንጀል መዝገብ የተሰጠውን ውሳኔ ለማሳየት ተፈልጎ የተለቀቀ መረጃ እንጅ በወንጀል ህጉ የተቀመጠውን ጣሪያ ባለማወቅ የሆነ አይመስለኝም!

እዚህ ጋር ግን እንደ ጥያቄ መነሳት ያለበት ጉዳይ በአንድ ተከሳሽ ላይ ተጣምሮ በአንድ የወንጀል መዝገብ ላይ ባልቀረበ የተለያየ የወንጀል መዝገብ ላይ የተሰጠ ውሳኔ ከጣሪያው (25 ዓመት) ቢያልፍ አፈጻጸሙ ምን ይሆናል?

የወንጀል ህጉ ያስቀመጠው ጣሪያ ቅጣት በአንድ የወንጀል መዝገብ ላይ ተደራርቦ ለቀረበ ክስ ነው ወይንስ በተለያዩ የወንጀል መዝገቦች ላይ (ፋይል) ለቀረቡ የወንጀል ክሶችም የሚሰራ ነው?

ንጋቱ አማኑኤል
👍16
ፌደራል ፖሊስ የአቪዬሸን አሰራርን ጥሰዋል ባላቸው 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን ተገለጸ።

ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ተጠርጣሪዎቹ ተብለው ከተቀመጡት መካከል
👉 ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣
👉አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣
👉ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣
👉ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣
👉ይዲድያ ነጻነት አበበ እና
👉 እሌኒ ክንፈ ተክለአብ
ናቸው ተብሏል።

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው፥ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።

የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ሃይሎች ተልእኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ ናቸው በሚል በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው የሚያመላክተው።

በወቅቱ የአየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፣ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ማለታቸውንም በምርመራ መዝገቡ አካቷል።

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር መጠቀም ሲገባቸው፣ የሀገር ኩራት እና የራሳቸው ንብረት የሆነውን አየር መንገድ ማንቋሸሻቸው አሳዛኝ ተግባር ስለመሆኑም የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መግለጹ  ተመላክቷል።

በመሆኑም እነዚህ በቁጥጥር ስር የሚገኙ 6 ተጠርጣሪዎችን ቢሮው በተላለፉት የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የበረራ አሰራር ጥሰት ብሎም በሽብር ወንጀሎች የምርመራ መዝገብ ነገ ነሀሴ 20 ቀን 2016 ፍርድ ቤት እንደሚያቀርባቸው ለማወቅ ተችሏል ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።
ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍ/ሕ/ቁ  2035(2)
ለመሰረታዊ የሕግ እውቀት በቴሌግራም
ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE
Legal Information🔵
📞+251920666595
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍191
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ስነስርዓት መመረያ መሰረት ችሎት ላይ መፈፀም ያለባቸው ተግባራት👇👇👇👇👇👇

ለችሎት ክብር ስለመቆም 🧍🧍‍♀
በችሎት ሂደት ፍርድ ፣ ቅጣት፣ ውሳኔ ወይም ብይን ሲነበብ፣ የክስ እና መልስ ቅብብል ሲደረግ ክርክር ሲካሄድ፣ ባለጉዳዪ ምስክር ሲያሰማ ፤ ትእዛዝ ሲሰጥ ውሳኔ ሲነበብ ጉዳዩ የሚመለከተው ባለጉዳይ ቆሞ መከታተል ይኖርበታል
- ዳኛ ችሎት ሲመራ ለችሎት ታዳሚዎች በሚሰማ መልኩ መናገር
- የዳኞች መጠሪያ ስያሜ በተመለከተ እንደ ቅድመ ተከተላቸው የክብር ስማቸውን ለሴት(ክብርት) ለወንድ (ክቡር) በማስቀደም ኃላፊነታቸውን እና ሙሉ ስማቸውን በመግለፅ ተገቢው ክብር መስጠት
በፍርድ ቤቶች ውስጥ የተከለከሉ ተግባራት🚫🚫🚫
-ዳኛው በችሎት እያስቻሉ ችሎትን የሚያውክ የጎንዮሽ ወሬ ማውራት፣መሳቅ ፣ በተንቀሳቃሽ ስልክ ማውራት
- ድምፅ በሚያሰማ እይታን በሚከለክልና የሌሎች ሰዎች ትኩረት በሚስብ መልኩ ጋዜጣ እና ሌሎች ፃሁፎችን በችሎት ማንበብ
-በድምፃ ወይም በምልክት ወይም በማንኛውም ችሎቱን ማወክ ወይም አላስፈላጊ ድርጊት መፈፀሞ
- ከውሃ በስተቀር ሌሎች መጠጦች መጠጣት መመገብ፣ ጫት መቃም፣ ሲጋራ ማጨስ፣ማስቲካ ማኘክ፣ መተኛት
- ቃጠሎ የሚፈጥሩ መሳሪያዎች ይዞ መግባት
- የጦር መሳሪያ ዱላ ወይም ስለታማ የሆኑ መሳሪያዎች መያዝ
- ፍርድ ቤቱ አመራር እና ዳኛው ሳይፈቅድ ችሎቱን በድምፃ ፣ በምስል መቅረፃ ፎቶ ማንሳት
- እንደ ሻንጣ እና ትልልቅ ቦርሳዎች ወይም ለችሎቱ ስነ ስርዐት የማይመቹ ድምፅ መፍጠር የሚችሉ ማንኛውንም እቃዎች ይዞ መግባት
- በችሎቱ ዳኛ ክስ ፣ ቅጣት፣ውሳኔ ብይን ወይም ፍርድ መነበብ ውይም ምስክር መስማት ከተጀመረ በኃላ ማንኛውም ሰው ችሎት አቋርጦ መውጣት
- በችሎት ላይ ዳኛው በተናገረበት ጉዳዮች ትክክል ስለመሆናቸው ወይም ስላለመሆናቸው በአይን ምልክት ፣ በቅንድብ በፊት ገፃታ ወይም ሌሎች እንቅሰቃሴዎች ማሳየት ከዳኛው ወይም ከችሎት ዞሮ ማውራት ከዳኛ ጋር መሟገት
- በህክምና አልተረጋገጠ በስተቀር ምግብ መመገብ
- ተከራካሪ ወገኖች ሳይፈቀድላቸው መናገር ፣ በክርክር ጣልቃ መግባት
- ለችሎቱ ጉዳያቸውን ሲያስረዱ በፍርድ አቤቱ የስራ ቋንቋ አቻ ቃላት ችሎቱን ካላስፈቀዱ በስተቀር ሌሎች ቋንቋቸው መደባለቅ
( እንግሊዝኛ እና የመሳሰሉት ማለቱ ነው)
- በማህበረሰቡ የተለየ ተገቢነት የሌለው ትርጉም የሚሰጠው ጣትን  ባለጉዳይ ወይም ታዳሚ ላይ እየቀሰሩ ማውራት
- የተከራካሪ ስብዕናን ማዋረድ
- ተከራካሪ ወገኖች በችሎት ውስጥ በሚደረግ ክርክር ሃሳባቸውን በቀጥታ ለችሎቱ ከማቅረብ ይልቅ የጎንዮሽ ክርክር ማድረግ
ህፃናትን አስገዳጅ ሁኔታ ከሌለ በስተቀር እና የህፃናት ማቆያ በፍርድ ቤት ከሌለ በስተቀር ህፃናትን ይዞ ወደ ችሎት መግባት የተከለከሉ ድርጊቶች ናቸው

ህሌና ጌታቸው የህግ ቢሮ በማንኛውም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃ እና የህግ አማካሪ
ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍ/ሕ/ቁ  2035(2)
https://wp.me/pfoz3m-6J
ለመሰረታዊ የሕግ እውቀት በቴሌግራም
ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE
Legal Information🔵
📞 #+251920666595
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍212
የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር የጥብቅና ገምጋሚ ኮሚቴ የሬጂስትራር የሙያ ዘርፍ የህግ ሙያ አይደለም ብሎ ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ የተሰጠውን ውሳኔ መሠረት በማደግ ለይግባኝ ሰሚው ችሎት የይግባኝ ቅሬታ የቀ
ረበ ሲሆን።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ የሬጅስትራር ሙያ የህግ ሙያ ነው በማለት ውሳኔውን በሙሉ ድምፅ በመሻር ውሳኔ ሰጥቷል።
👉Thanks to court!!

👉ውሳኔው በአስረጂነት ተያይዟል!! #Tebeka yonas
👍258👎4
የሬጅስትራር_ሙያ_የህግ_ሙያ_ስለሆነ_የሬጅስትራል_የስራ_ልምድ_ያላቸው_የጥብቅና_ፈቃድ_ማውጣት_ይችላሉ።.pdf
477.8 KB
የሬጅስትራር ሙያ የህግ ሙያ ስለሆነ የሬጅስትራል የስራ ልምድ ያላቸው የጥብቅና ፈቃድ ማውጣት ይችላሉ።


በመሆኑም የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴውም ሆነ የጠበቶች አስተዳደር ቦርድ በሬጅስትራል የተገኘ የስራ ልምድ የህግ ሙያ አይደልም የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሳቸው የህግ መሰረት የለውም በማለት ተከታዩ ውሳኔ በሙሉ ድምፅ ተወስኗል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ በቀን 29/10/2015 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እና የፌደራል ጠበቆች አስተዳደር ቦርድ የመዝገብ ቁጥር 18/2015 በሆነው ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ባሳለፈው ውሳኔ የሬጂስትራር ሙያ የህግ ሙያ አይደለም በማለት የደረስበት ድምዳሜ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ውሳኔው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1)መስረት በሙሉ ድምጽ ተሸሯል፡፡

2. የሬጂስትራር ሥራ የህግ ሙያ ነው ተብሎ ተወስኗል፡፡ ስለሆነም የጥብቅና ፍቃድ ስጪው አካል ህጉን ተከትሎ እንዲያስተናግዳቸው ተብሏል፡፡
ሙሉ ውሳኔውን በPDF ለማንበብ እና ዳውሎድ ለማድረግ 👇👇
https://t.me/lawsocieties/9825

ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍ/ሕ/ቁ  2035(2)
https://wp.me/pfoz3m-6J
ለመሰረታዊ የሕግ እውቀት በቴሌግራም
ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE
Legal Information🔵
📞 #+251920666595
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍13
የሬጅስትራር ሙያ የህግ ሙያ ስለሆነ የሬጅስትራል የስራ ልምድ ያላቸው የጥብቅና ፈቃድ ማውጣት ይችላሉ።

በመሆኑም የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴውም ሆነ የጠበቶች አስተዳደር ቦርድ በሬጅስትራል የተገኘ የስራ ልምድ የህግ ሙያ አይደልም የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሳቸው የህግ መሰረት የለውም በማለት ተከታዩ ውሳኔ በሙሉ ድምፅ ተወስኗል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ በቀን 29/10/2015 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እና የፌደራል ጠበቆች አስተዳደር ቦርድ የመዝገብ ቁጥር 18/2015 በሆነው ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ባሳለፈው ውሳኔ የሬጂስትራር ሙያ የህግ ሙያ አይደለም በማለት የደረስበት ድምዳሜ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ውሳኔው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1)መስረት በሙሉ ድምጽ ተሸሯል፡፡

2. የሬጂስትራር ሥራ የህግ ሙያ ነው ተብሎ ተወስኗል፡፡ ስለሆነም የጥብቅና ፍቃድ ስጪው አካል ህጉን ተከትሎ እንዲያስተናግዳቸው ተብሏል፡፡
ሙሉ ውሳኔውን በPDF ለማንበብ እና ዳውሎድ ለማድረግ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/LawSchoolStudents/1849

ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍ/ሕ/ቁ  2035(2)
https://wp.me/pfoz3m-6J
ለመሰረታዊ የሕግ እውቀት በቴሌግራም
ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE
Legal Information🔵
📞 #+251920666595
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍121