አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
December 25, 2023
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
December 26, 2023
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
December 27, 2023
December 27, 2023
የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት
ቀድሞ ይገኝበት ከነበረበት ፒያሳ ኢየሩሳሌም ህንፃ ለቆ ስድስት ኪሎ ምስካየ ኅዙናን መድሃኒአለም ቤተክርስትያን ፊት ለፊት ወደ እቴጌ መነን ትምህርት ቤት በሚወስደው መንገድ ገባ ብሎ በሚገኘውና ከታች በምስሉ ላይ በሚታየው ባለ 5 ፎቅ ህንፃ ላይ የተዛወረ መሆኑን እየጠቆምን ውድ ደንበኞቻችን የተለመደው አገልግሎታችንን በአዲሱ ህንፃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
      
  የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት

https://linktr.ee/alehig
December 28, 2023
☑️1. ህግ ህገ መንግስት
☑️2. አዋጅ/የአለም አቀፍ ስምምነቶች
☑️3. ደንብ
☑️4. መመሪያ
የአለም አቀፍ ስምምነቶችን የህግ ተዋረድ በተመለከተ ወጥ የሆነ መግባባት ባይኖርም በህገ መንግስቱ ኢትዮጵያ የፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የአገረቱ ህግ አካል ይሆናሉ ስለሚል ከአዋጅ ጋር ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ይቀመጣሉ የሚል ሀሳብ አለ፡፡
https://wp.me/pfoz3m-11
December 31, 2023
የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ስለሚቀርብ ክስ
ማንኛውም የፍትሐብሔር ክስ ሲከፈት በፍርድ ቤት ለሚሰጠው የዳኝነት አገልግሎት የዳኝነት እንዲከፈል ይጠበቃል፡፡
ክስ ለማቅረብ የፈለገ ወገን ለሚያገኘው የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችል የገንዘብ አቅም የሌለው ከሆነ ለግዜው የዳኝነት መክፈል ባለመቻሉ ብቻ መብቶቹን እንዳያጣ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህጉ መፍትሄ አስቀምጧል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ስለሚቀርብ ክስ ምንነት እና ስለሚቀርብበት ሥነ ሥርዓት እንመለከታለን፡፡
https://alehig.wordpress.com/blog-2/
January 1, 2024
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
January 1, 2024
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
January 1, 2024
January 2, 2024
Forwarded from ሕግ ቤት
January 2, 2024
January 2, 2024
ስጦታ ፈራሽ የሚሆንባቸው ምክንያቶች

የስጦታ ምንነት

በአጭሩ ለማስቀመጥ ስጦታ ማለት ሰጪው ተቀባይ ለተባለ ሌላ ሰው ከንብረቶቹ አንዱን ያለ ዋጋ የሚለቅበት ወይም ግዴታ የሚገባበት ውል ነው።
በመሆኑም ስጦታ በራሱ ውል ነው ማለት ነው።

የስጦታ ልዩ ባህሪያት

በመርህ ደረጃ ስጦት ግላዊ ተግባር ነው ይህም ማለት ስጪው እራሱ የሚያድረገው ተግባር ነው ማለት ነው። ስጦታ የሚደረገው በወኪሉ ሲሆን ደግሞ የሚሰጠው ንብረት አይነት እና ለማን እንደሚሰጥ በግልጽ ሊመለከት ይገባል። ስጦታ የሚደረገው የሰጪው ንብረት በሆነው ለይ ብቻ ነው።ስጦታ አድርጋለሁ ብሎ የተስፋ ቃል መስጠት በህጉ መሠረት ግዴታን አያስከትልም ከዚህም በተጨማሪ ስጦታ ተቀባዩ ስጦታውን እቀበላለሁ በሚል ሀሳቡን
መግለፅ ይኖርበታል።ስጦታ እንዲቀነስ ወይም እንዲሻር የሚቀርበው ጥያቄ ስጦታው ከተደረገበት ቀን አንስቶ እስከ ሁለት አመት ለዳኞች ካልቀረበ በቀር ዋጋ አይኖረውም።

የስጦታ ሥርዓት ፎርም*

ስጦታ በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ ወይም በሚይንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ ሊደረግ ይችላል።

*1)በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ *

በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በፍትሐብሔር ህግ አንቀጽ 881 ላይ በተደነገገው መሠረት በግልጽ ኑዛዜ ሥርዓት ፎርም መሠረት የሚፈጸም መሆኑን ህጉ ያስረዳል።በሌላ በኩል በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ለይ የሚደረገው ስጦታ በፍ/ህግ አንቀጽ 1723 መሠረት በጽሁፍ ሆኖ በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መሆን አለበት።

*2) በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ለይ የሚደረግ ስጦታ*

በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በሁለት አይነት መልኩ ሊደረግ ይችላል ይህም እጅ በእጅ በሚደረግ ማስተላለፍ ብቻ ወይም ለማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ በሚደረገው ፎርም ሊሰጥ ይችላሉ።

ስጦታ እንደማድረግ የማይቆጠርባቸው ሁኔታዎች ያሉ ሲሆን እነኚህም ሁኔታዎች።

1)ያለ ዋጋ የሚደረግ የአገልግሎት ሥራ ወይም የራሱን እቃ ያለ ዋጋ ዝግጁ ማድረግ ስጦታ አይባልም የፍ/ህግ አንቀጽ 2430።

2)መንፈሳዊ ተግባርን ለመፈጸም የሚደረገው የገንዘብ መክፈል ስራ ስጦታ አይባልም የፍ/ህ አንቀጽ 2432።

3) አንድ ሰው ለሰጪው ወይም ለቤተሰቡ አገልግሎት በልማድ መሠረት ያደረገው የሥራ ዋጋ መክፈል ስጦታ አይባልም የፍ/ህ አንቀጽ 2433።

4)ወራሽነትን አልፈልግም ብሎ መተው ወይም ኑዛዜ የተደረገለትን ስጦታ አልቀበልም ማለት ስጦታ ነው ተብሎ አይቆጠርም የፍ/ህግ 2431።

ስጦታ ፈራሽ የሚሆንባቸው ምክንያቶች*

በሚንቀሳቀስ ወይም በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ለይ የተደረገው ስጦታ በህጉ በተጠቀሱት በተለያየ ምክንያቶ ፈራሽ ሊሆን የሚችሉባቸው ምክንያቶች ያሉ ሲሆን እነኚህም:-

1ኛ የሰጪው አዕምሮ ትክክል አለመሆን

ሰጪው ስጦታውን በሚያድርግበት ወቅት በአዕምሮ መታወክ(ህመም ምክንያት) በፍርድ የተከለከለ ሲሆን ያደረገው ስጦታ ፈራሽ ሊሆን ይችላል ።የፍ/ህ አንቀጽ 2437

2ኛ ግብረ ገብነት የሌለው ወይም ህገ ወጥ ምክንያት ያለበት ስጦታ ፈራሽ ነው። የፍ/ህ አንቀጽ 2438

3)በመንፈስ መጫን ምክንያት የተደረገውን ስጦታ ዳኞች ለመቀነስ ወይም ለመሻር ይችላሉ።የፍ/ህ አንቀጽ 2439

4ኛ በ ፍ/ህ አንቀጽ 2442 ሥር በሚፈቅደው መሠረት ስጦታው የተደረገው በስህተት ወይም በተንኮል የሆነ እንደሆነ ፈራሽ ይሆናል።

5 ስጦታ የተደረገው ክርክር ያለበት ሀብት ላይ ሲሆን ስጦታው ፈራሽ ይሆናል።
Via #lawyerhenoktaye #henoktayelawoffice

Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴

#አለሕግ #Alehig

Subscribe Now!

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
January 3, 2024
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
January 3, 2024
👉👉አደራ እና የወንጀል ኃላፊነት
በወንጀል ሕጋችን 675 መሠረት እምነት ማጉደል ማለት ለራስ ወይም ለሌላ ሰው ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ የሌላ ሰውን ለተወሰነ አገልግሎት (በውሰት) ወይም በአደራ የተቀበለውን ዋጋ ያለው ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ በሙሉ ወይም በከፊል ለራሱ ያደረገ፣ የወሰደ፣ ያስወሰደ፣ የሰወረ፣ ለራሱ ወይም ለሌላ አገልግሎት ያዋለ ወይም መሰል ድርጊቶችን የፈፀመ እንደ ነገሩ ሁኔታ በቀላል እስራት ወይም ከአምስት ዓመት በማይበልጥ እስራት ይቀጣል።
https://wp.me/pfoz3m-1L
January 3, 2024