የመረጃ ነፃነት
መንግስትም ከጥቂት መረጃዎች በስተቀር ማለትም የሶስተኛ ወገን መረጃ፣ የሀገሪቱን መከላከያ፣ ደህንነት እና አለም አቀፍ ግንኙነት አደጋ ውስጥ ከሚጥሉ መረጃዎች እና አንዳንድ በህግ በሚስጥር እንዲያዙ ከተከለከሉ መረጃዎች ውጪ ያሉ መረጃዎችን በተጠየቀ ጊዜ የማጋራት ሀላፊነት አለበት፡፡
የመገናኛ ብዙሀን እና የመረጃ ነጻነትን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ፣ አዋጅ ቁጥር 590/2000፤ አንቀጽ 12፣ 16-29
Access to Information
via https://t.me/PublicInformationNoble
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
ማንኛውም ሰው ከማንኛውም መንግስታዊ አካል መረጃን የመጠየቅ፣ የማግኘት እና ይህንንም መረጃ የማስተላለፍ መብት ያለው ሲሆን
መንግስትም ከጥቂት መረጃዎች በስተቀር ማለትም የሶስተኛ ወገን መረጃ፣ የሀገሪቱን መከላከያ፣ ደህንነት እና አለም አቀፍ ግንኙነት አደጋ ውስጥ ከሚጥሉ መረጃዎች እና አንዳንድ በህግ በሚስጥር እንዲያዙ ከተከለከሉ መረጃዎች ውጪ ያሉ መረጃዎችን በተጠየቀ ጊዜ የማጋራት ሀላፊነት አለበት፡፡
የመገናኛ ብዙሀን እና የመረጃ ነጻነትን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ፣ አዋጅ ቁጥር 590/2000፤ አንቀጽ 12፣ 16-29
Access to Information
via https://t.me/PublicInformationNoble
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
👍9❤2🔥1😁1
ውክልና በሕግ ዓይን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
መቼም ሰው፣ ሰው ነውና በሁሉም ቦታ በሁሉም ሰዓት ለመገኘት ጊዜውም አቅሙም የለውም።
ከተፈጥሮ ሰው በተጨማሪም በሕግ መብት እና ግዴታ ያላቸው ተቋማትም በሰው ካልተወከሉ በስተቀር ግዑዝ ናቸውና ሕጋዊ ተግባራትን ለማከናወን አይችሉም።
ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናት እና በሕግ የተከለከሉ ሰዎች ደግሞ ሕጋዊ ተግባራትን ሚያከናውኑት በሞግዚታቸው በኩል ነው።
ከውል ወይም ከሕግ የሚመነጭ የውክልና ሥልጣን እና ሕጋዊ ውጤቶቹ በወካይ፣ በተወካይ እና በሦስተኛ ወገኖች ላይ የሚፈጥሯቸው መብት እና ግዴታዎች በተመለከተ መሠረታዊ ግንዛቤ እንዲኖረን የፍትሐ ብሔር ሕጋችን ስለወኪልነት ያስቀመጣቸውን ድንጋጌዎችን እንቃኛለን።
የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2199 ውክልናን በመተርጎም ይጀምራል። “ውክልና ወካይ ለተወካዩ እንደራሴው ሆኖ አንድ ወይም ብዙ ሕጋዊ ሥራዎችን በወካዩ ስም ለማከናወን ግዴታ የሚገባበት ውል ነው” በሚል ይተረጉመዋል። ውክልና በግልጽ ወይም በዝምታ እንደሚሰጥ ሕጉ ቢፈቅድም የጽሑፍ ውክልና በሚያስፈልግባቸው ጉዳዮች ላይ ግን ውክልናው በጽሑፍ መሆን አለበት። ንብረትን ለማስተዳደር፣ ለመሸጥ፣ መለወጥ፣ በፍ/ቤት ቆሞ መከራከር እና ለመሳሰሉት ጉዳዮች የሚሰጡ ውክልናዎች በጽሑፍ መሆን አለባቸው።
ውክልና የሚፀናው ውክልናን ለማረጋገጥ እና ለመመዝገብ ሥልጣኑ በተሰጠው የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ ወይም በክልል የፍትሕ ቢሮዎች ወይም ይህ ሥልጣን በሕግ በተሰጣቸው አካላት ፊት ተረጋግጦ ሲሰጥ እና ሲመዘገብ ነው።
በፍትሐ ብሔር ሕጋችን ላይ ሁለት የውክልና ዓይነቶች አሉ።
1. ጠቅላላ ውክልና
ከሦስት ዓመት ለማያልፍ ጊዜ ንብረትን የማከራየት፣ ከብድር፣ ከሀብት የተገኘ ገቢን መሰብሰብ እና ማስቀመጥ፣ ለአከራዮች ደረሰኝ የመስጠት መሰል የአስተዳደር ሥራዎችን ብቻ እንዲያከናውን ለወኪሉ ሥልጣን የሚሰጥ ውክልና ነው። የንብረት ሽያጭ እና ባለቤትነትን ወደ ሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ሥልጣን ግን በዚህ ዓይነቱ ውክልና ውስጥ አይካተትም። ሆኖም ለሽያጭ የተመደቡ ዕቃዎችን ወይም ሰብሎችን መሸጥ ግን እንደ አስተዳደር ሥራ ስለሚቆጠር በጠቅላላ ውክልና ሥር ይመደባል።
2. ልዩ ውክልና
ይህ የውክልና ዓይነት ከአስተዳደር ሥራ ውጭ ያሉ ሌሎች ተግባራትን የረጅም ዘመን ኪራይን፣ የባንክ ገንዘብ ማውጣትን፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭን፣ ንብረትን ለብድር ዋስትና ማስያዝን፣ የለውጥ ውልን ከአንድ የአክስዮን ወይም የንግድ ማኅበር መግባትን እና ፍርድ ቤት ቆሞ መከራከርን ይመለከታል።
በተለምዶ ጠቅላላ ውክልና ተብሎ የሚጠራው ግን ሕጉ ከሚለው አንፃር ሲታይ የአስተዳደር ሥራ እና ልዩ ውክልናን ሥልጣኖችን ጭምር በአንድ ሰነድ ላይ በሰፊ ዝርዝር የሚያካትት ነው።
በሕጉ አገላለጽ ግን የንብረት ባለቤትነትን የማዛወር በወኪሉ ስም የመክሰስ/የመከሰስን እና መሰል የወካዩ መብት እና ግዴታ ላይ ዘላቂ ለውጥ ሊፈጥሩ የሚችሉ ሰፊ ሥልጣኖችን ለተወካዩ የሚሰጠው ግን ጠቅላላ ውክልና ሳይሆን ‘ልዩ ውክልና’ ነው። ልዩ ውክልና የተሰጠው ሰው ውክልናው ላይ የተጠቀሱትን ተግባራት እና ከተግባራቱ ባህሪ ጋር የሚያያዙ አስፈላጊ ነገሮችን ማከናወን ይችላል። ለምሳሌ ንብረት የመሸጥ ውክልና የተሰጠው ሰው የሽያጩን ገንዘብ የመቀበል፣ ንብረቱን የማስረከብ እና ስመ ሀብቱን ለገዢው የማስተላለፍ ከሽያጭ ጋር የተያያዙ ተግባራትን የማከናወን ሥልጣንም አለው።
ወካዩ ለተወካዩ በሰጠው የሥልጣን ገደብ ስር ለሚሠራው ሥራ የሚገደድ ሲሆን ከውክልናው በላይ በቅን ልቦና የሠራውን ሥራም ወካይ በፍ/ብ/ሕ/ቁ በ2207 የማጽደቅ ግዴታ አለበት።
ተወካይ በሕጉ ላይ ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና እንዲኖረው የሚሠራውን ሥራ ሁሉ ለወካዩ ጥቅም እንጂ ለግሉ እንዳያደርግ ተደንግጓል።
ሕጉ ‘እንደ መልካም የቤተሰብ አባት’ ተገቢውን ትጋት እና ጥንቃቄ በማድረግ የውክልናውን ሥራ እንዲሠራ ተወካይ ላይ ግዴታ ጥሏል።
ወካዩ በውክልናው ላይ ከተሰጠው ሥልጣን በላይ ከሠራ ወኪሉ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ተጠያቂነት አለበት። በተጨማሪም ከሥልጣኑ በላይ ወይም በሌለው ሥልጣን የተደረገ ውልም በወኪሉ ወይም መብት ባለው አካል ክስ ከቀረበበት ፍ/ቤት ሊሽረው ይችላል።
ውክልናውን ወካይ መስሎ በታየው ጊዜ የመሻር ሥልጣን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2226(1) ላይ የተሰጠው ሲሆን ወካይ የሞተ፣ በስፍራው ላይ ያለመኖሩ የተረጋገጠ፣ ሕጋዊ ተግባራትን ለመሥራት ችሎታ ካጣ ወይም ከከሰረ በፍ/ብ/ሕ/ግ 2230(1) መሠረት ውክልናው ይሻራል።
በነገራችን ላይ በውክልና ሊደረጉ እንደማይችሉ ሕጉ በግልፅ ካስቀመጣቸው ተግባራት አንዱ ኑዛዜ ማድረግ እና ጋብቻ መፈፀም ሲሆኑ የሚገርመው ጋብቻ መፈፀምን በተመለከተ በተሻሻለው የፌዴራሉ የቤተሰብ ሕጋችን ጋብቻን በውክልና መፈፀም እንደሚቻል ተፈቅዷል። ይህ ሊሆን የሚችለው ግን የፍትሕ ሚኒስትሩ በቂ ምክንያት መኖሩን አምነው ፍቃዳቸውን ሲሰጡ መሆኑ ተደንግጓል።
EBC WORLD
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍12❤1🌚1
የዩቲዩብ ቻናለችንን ሰብስክራይብ
ያላደረጋችሁ፣❓
https://youtube.com/@Lawsocieties
አሁን subscribe አድርጉልን።
በሚል ልዩ የሕግ ጉዳዮች ይዘን ልንመጣ ነው።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@Lawsocieties
https://youtube.com/@Lawsocieties
https://youtube.com/@Lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
subscribe
ያላደረጋችሁ፣❓
https://youtube.com/@Lawsocieties
አሁን subscribe አድርጉልን።
አለሕግ
በሚል ልዩ የሕግ ጉዳዮች ይዘን ልንመጣ ነው።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@Lawsocieties
https://youtube.com/@Lawsocieties
https://youtube.com/@Lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👍9🔥1
ከህግ ውጪ የተቋረጠ የስራ ውል ለሰራተኛው የሚያስገኛቸው ጥቅማጥቅሞች
1 የስራ ስንብት ክፍያ
የስራ ውሉ አላግባብ የተቋረጠበት ሰራተኛ በአዋጅ 1156/11 አንቀፅ 39(1) እና 40(1) መሰረት እንደ ነገሩ ሁኔታ የአንድ አመት ደሞዙን የሚደርስ የስራ ስንብት ክፍያ ያገኛል፡፡
2. የካሳ ክፍያ
የስራ ውሉ አላግባብ የተቋረጠበት ከስራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ በአዋጅ 1156/11 አንቀፅ 43(4)(ለ) መሰረት የካሳ ክፍያ ያገኛል፡፡ሆኖም ካሳው የሰራተኛውን ማዕከላዊ የቀን ደሞዝ ደመወዙ በ180 ተባዝቶ ከሚያገኘው ውጤት መብለጥ የለበትም፡፡
3. ያልተጠቀሙበት የአመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ የሚከፈል ክፍያ
የስራ ውሉ አለአግባብ የተቋረጠበት ሰራተኛ ከስራ ስንብት ክፍያ እና ከካሳ ክፍያ በተጨማሪ ያልተጠቀመበት የአመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ በአዋጅ 1156/11 አንቀፅ 77(4) መሰረት ይከፈለዋል፡፡
4. ክፍያ ለዘገየበት ክፍያ
ሰራተኛው የሚለግበትን የአሰሪ ንብረት መልሶ ክሊራንስ ከጨረሰ በኋላ ሊከፈሉት የሚገቡ ክፍያዎች በ7 ቀን ውስጥ ካልተከፈሉት በአዋጁ አንቀፅ 38 መሰረት እስከ 3 ወር ደመወዝ ሊከፈለው ይችላል፡፡
5.ያልተከፈለው የወር ደመወዝ ካለ ይከፈለዋል፡፡
6. ለተጨማሪ ስራ ክፍያ
ከመደበኛ የስራ ሰአት ውጪ በበአል ቀናት የተሰራ ስራ፤በእረፍት ቀናት የተሰራ ስራ ካለ ለእነኝህ ስራዎች በአዋጅ አንቀፅ 66 እና 68 መሰረት ሰራተኛው ክፍያ ያገኛል፡፡
7. የስራ የምስክር ወረቀት
በአዋጁ አንቀፅ 12(8) መሰረት ሰራተኛው የስራ ልምድ ማስረጃ ያገኛል አንድ የግል ድርጅት ሰራተኛ የስራ ውሉ የህግ ውጪ ሲቋረጥ የሚያገኛቸው ህጋዊ ጥቅማ ጥቅሞች እነዚህ ናቸው፡፡
ማሳሰቢያ :- ይህ ተግባራዊ የሚሆነው ለግል ሰራተኞች ብቻ ነው፡፡
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍9❤2🔥1👏1
የተጠርጣሪ፣ የተከሳሽ እና የታራሚ ልዩነት
ተጠርጣሪ፣ ተከሳሽ እና ታራሚ የሚሉት ቃላቶች በወንጀል ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚነሱ ሲሆኑ ነገር ግን በአብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል በእነዚህ ቃላቶች መካከል ያለውን ልዩነት ባለማወቅ እና ባለመረዳት አንዱን ቃል ለአንዱ በመተካት እና በመቀያየር ሲጠቀምበት ይስተዋላል፡፡ በመሆኑም በዚህ ፅሁፍ የተጠርጣሪ፣ የተከሳሽ እና የታራሚን ምንነት፣ በመካከላቸው ያለውን አንድነት እና ልዩነት ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡
ተጠርጣሪ
ተጠርጣሪ ማለት የወንጀል ድርጊት ፈፅሟል ተብሎ የተጠረጠረ እና በወንጀል ሥነ ሥርአት ህጉ መሰረት ለፖሊስ ወይም በህግ ክስ ለመቀበል ስልጣን ለተሰጠው አካል የወንጀል ክስ አቤቱታ ወይም ጥቆማ የቀረበበት ማንኛውም ሰው ነው፡፡ በዚህም ፖሊስ ተጠርጣሪው የተባለውን የወንጀል ድርጊት ስለመፈፀም ወይም አለመፈፀሙ ማስረጃ የማሰባሰብ እና የምርመራ ሥራ ያከናውናል፡፡ በዚህ መልኩ የሚሰራው ምርመራ ከተጠናቀቀ በኋላ የምርመራ መዝገቡ ለዐቃቤ ህግ የሚቀርብ ሲሆን ዐቃቤ ህግም የቀረበውን ማስረጃ በመመልከት ተጠርጣሪው ወንጀሉን ስለመፈፀሙ የሚያስረዳ በቂ ማስረጃ ያለ ከሆነ በፍርድ ቤት ክሰ ሊመሰርት፣ በተጨማሪነት መቅረብ ያለበት ማስረጃ ካለ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ ሊሰጥ ወይም ማስረጃው አጥጋቢ ካልሆነ የአያስከስስም ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል፡፡
ተጠርጣሪው የተጠረጠረበትን የወንጀል ድርጊት ስለመፈፀሙ የሚያመለክት አጥጋቢ ማስረጃ እስካልተገኘበት ድረስ በቁጥጥር ስር የማይውል ሲሆን የወንጀል ምርመራ በሚደረግበት ወቅትም ተጠርጣሪው እንደተጠረጠረበት የወንጀል አይነት፣ ክብደት፣ የአፈፃፀም ሁኔታ፣ እንደ ተጠርጣሪው ባህሪ እና ሌሎች ሁኔታዎች በፖሊስ ዋስትና፣ በፍርድ ቤት ዋስትና ወይም በማረፊያ ቤት ሆኖ የወንጀል ምርመራ ሂደቱ ሊከናወን ይቻላል፡፡
ተከሳሽ
ተከሳሽ ማለት በወንጀል ድርጊት ተጠርጥሮ በፖሊስ የወንጀል ምርመራ የተጠረጠረበትን የወንጀል ድርጊት ስለመፈፀሙ በቂ እና አሳማኝ ማስረጃ ተገኝቶ በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ያለ እና የፍርድ ውሳኔ ያልተሰጠበት ማንኛውም ሰው ነው፡፡
ተከሳሽ በፍርድ ቤት ዋስትና ወይም በማረፊያ ቤት ሆኖ የወንጀል ክስ ሂደቱን ሊከታተል ይችላል፡፡ ተከሳሽ በክስ መሰማት ሂደት ወቅት ለህዝብ ግልጽ በሆነ ችሎት የመሰማት፣ ክሱ በቂ በሆነ ዝርዝር እንዲነገረው እና በፅሁፍ የማግኘት፣ በተከሰሰበት ወንጀል እንደጥፋተኛ ያለመቋጠር፣ በራሱ ላይ በምስክርነት እንዲቀርብ ያለመገደድ፣ የቀረበበትን ማንኛውንም ማስረጃ የመመልከት እና የቀረበበትን ማንኛውንም ምስክሮች የመጠየቅ፣ ራሱን ለመከላክል የሚያስችለውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ፣ በመረጠው የህግ ጠበቃ የመወከል፣ በተሰጠው ፍርድ ላይ ይግባኝ የማለት እና በመንግስት ውጪ አስተርጎሚ የማግኘት መብት አለው፡፡
ታራሚ
በፌደራል ማረሚያ ቤት አዋጅ ቁጥር 1174/2012 አንቀጽ 2(8) መሰረት ታራሚ ማለት በፍርድ ቤት የተወሰነበትን ፍርድ በማረሚያ ቤት ውስጥ በመፈፀም ላይ የሚገኝ ሰው ነው፡፡ በህገ መንግስቱ እና በዚህ አዋጅ መሰረት ማንኛውም ታራሚ ሰብአዊ ክብሩ በሚጠብቁ ሁኔታዎች የመያዝ፣ ከትዳር ጎደኛው፣ ከቅርብ ዘመዶቹ፣ ከጎደኞቹ፣ ከሀይማኖት አባት፣ ከሐኪም እና ከህግ አማካሪዎቹ ጋር ለመገናኘት እና እንዲጎበኙት እድል የማግኘት መብት አለው፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

👍15👏1
የእሽሙር ማህበር (JOINT VENTURE)
የእሽሙር ማህበር ምንነት
የእሸሙር ማህበር በአዲሱ የንግድ ህግ ከተካተቱ ሰባት የንግድ ማህበር አይነቶች አንዱ ሲሆን ማህበሩ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በመካከላቸው በሚያደርጉት ስምምነት መሠረት የሚያቋቁሙት በሦስተኛ ወገኖች የማይታወቅና የሕግ ሰውነት የሌለው የንግድ ማህበር እንደሆነ በንግድ ህጉ አንቀፅ 234 ስር ተደንግጓል፡፡ ይሁንና የማህበሩ መኖር በሦስተኛ ወገኖች ከታወቀ ጊዜ አንስቶ ማህበሩ ከእነዚህ ወገኖች ጋር በሚኖረው ግንኙነት እንደ ህብረት ሽርክና ማህበር ይቆጠራል፡፡ የእሽሙር ማህበር ከሌሎች የንግድ ማህበራት ከሚለዩት ባህርያት የንግድ ማህበሮች የማስመዝገብ ሥርዓቶች በዚህ ማህበር ላይ ተፈጻሚ የማይሆን መሆኑ ነው፡፡
የእሽሙር ማህበር ባህርያት
የእሽሙር ማህበር መመስረት አንደኛ ሸሪክ ያለው ነገር ግን ሌላኛው ሸሪክ የሌለውን ጠንካራ ጎን ለመጋራት ያስችላል፡፡ ለምሳሌ እውቅና እና መልካም ስም ያለው የንግድ ስም (Brand Name ) ካለው የንግድ ማህበር ጋር ሽርክና የገባ ካንፓኒ ከመልካም ስሙ ተጠቃሚ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ሁለት ሸሪኮች ያሏቸውን ጠንካራ ሀብት (የገንዘብ፣ የእውቀት፣ የቴክኖሎጂ እና የመሳሰሉትን) በማቀናጀት የተሻለ ውጤታማ የሆነ ማህበር ይመሰርታሉ፡፡ የሚከተሉት የእሽሙር ማኅበር ልዩ ባህሪያት ተብለው ሊወሰዱ ይችላሉ፡-
1. ህጋዊ ሰዉነት የሌለዉ ስለመሆኑ
የእሽሙር የሽርክና ማኅበር ህጋዊ ሰዉነት የለዉም ሲባል በሸሪኮች መካከል ያለዉ ግንኙነት ተራ ዉል ግንኙነት ነዉ ማለት ነዉ፡፡ በመሆኑም ሸሪኮቹ የአንድ ተቋም አባላት ሳይሆኑ ተራ ዉል ተዋዋይ ወገኖች ናቸዉ፡፡ ይልቁን ህጋዊ ሰዉነት ስለሌለዉ የንግዱ ስራ የሚሰራዉ በሸሪኮቹ ስም ነዉ፡፡ ስለሆነም እያንዳንዱ ሸሪክ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር ሲዋዋል፣ ዉሉን ሲፈጽም ወዘተ… በራሱ ስም ነዉ፡፡ ይህም የሚሆነዉ የሽርክና ማኅበሩ ለሶስተኛ ወገኖች ስውር ስለሆነ ነዉ፡፡ የእሽሙር ማኅብር ህጋዊ ሰዉነት ስለሌለዉ ሸሪኮቹ የሚያዋጡት ገንዘብ እና ሀብት የማኅበሩ ሊሆን አይችልም፡፡ በመሆኑም በንግድ ህጉ ቁጥር 236/2 ስር እንደተደነገገው ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር እያንዳንዱ ሸሪክ ያዋጣው ንብረት ባለቤት ነዉ፡፡
2. ለሶስተኛ ወገኖች የማይታወቅ መሆኑ
ለሶስተኛ ወገኖች አለመታወቁ (ድብቅ መሆኑ) ያለመመዝገቡ ውጤት ነዉ፡፡ የሕግ ሰዉነት ስለማይኖረዉ እንዲመዘገብ አይደረግም፡፡ ካልተመዘገበ ደግሞ ለህዝብ የሚታወቅበት መንገድ አይኖርም ማለት ነዉ፡፡ እዚህ ላይ የእሽሙር ሽርክና ማኅበር ድብቅነት የመመዝገብ ግዴታ ካለመኖሩ ብቻ የመነጨ ሳይሆን ይልቁንም በህጉ ታዉቆ እና ታስቦበት የተደነገገ ነዉ፡፡ አሰራሩም ያልተለመደ እና ግራ አጋቢ ቢመስልም በሌሎችም አገሮች የተለመደ እንጂ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብቻ ያለ አይደለም፡፡
3. ቅንጅት መፍጠር (Creates Synergy)
የእሽሙር ማህበር በሁለት ወይም ከሁለት በላይ በሆኑ ማህበራት መካከል ሲመሰረት አንደኛው ሸሪክ የሌላኛውን ባህርይ ለመጠቀም ያስችለዋል (extract the qualities of each other)፡፡ እንዲሁም አንዳቸው ያንዳቸውን ጥቅም ለመጋራት ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ከፍተኛ ጥንካሬ ያለው ቅንጅት መፍጠር ይችላሉ ማለት ነው( a joint venture to generate synergies between them for a greater good)፡፡ይህም በተዘዋዋሪ ትልቅ ካፒታልን ለመፍጠር የሚያስችላቸው ሲሆን ወጪያቸውንም እንዲቀንሱ ይረዳቸዋል፡፡
4. ስጋት/አደጋን መጋራት (Risk and Rewards can be Shared)
የእሽሙር ማህበር በአንድ ሀገር ውስጥ ባሉ ድርጅቶች ወይም በተለያዩ ሀገሮች ባሉ ድርጅቶች መካከል ሊደረግ የሚችል ሽርክና በመሆኑ በእነዚህ ሀገሮች ሊኖሩ የሚችሉ የባህል ልዩነቶች (diversifications in culture)፣ የቴክኖሊጂ፣ የመልከዓ መድር አቀማመጥ ጥቅምና ጉዳት (geographical advantage and disadvantage)፣ የተደራሽ ደንበኝ (target audience) ሁኔታዎች በማህበሩ ላይ ሊፈጥር የሚችለው ተፅዕኖ ትኩረት የሚሻ ነው፡፡ በመሆኑም በሸሪኮች መካከል የሚደረግ ስምምነት የአደጋ ስጋቶችን እና ጥቅሞች ለመጋራት ያስችላቸዋል፡፡
5. የተለየ ህግ አለመኖር (No Separate Laws)
የእሽሙር ማህበር የሕግ ሰውነት የሌለው የንግድ ማህበር በመሆኑ ማህበሩን የሚያስተዳድር የተለየ ሕግ አይኖርም፡፡ እንዲሁም ይህን ማህበር በተለየ ሁኔታ የሚያስተዳድር አካልም የለም(no separate governing body which regulates the activities of the joint venture.)፡፡
የእሽሙር ማህበር ጥቅሞች (advantages of a Joint Venture)
1. የምጣኔ ሀብትን ማሳደግ (Economies of Scale)
የእሽሙር ማህበር ሸሪኮች ወይም ድርጅቶች ሀብታቸውን ወይም ካፒታላቸውን በማጣመር ስለሚቋቋሙ ህብረት መመስረታቸው ውስን አቅማቸውን ለማሳደግ ይረዳቸዋል፡፡
2. አዲስ ገበያ መድረስ እና የአውታረ መረቦችን ስርጭት (Access to New Markets and Distribution Networks)
አንድ ድርጅት ከሌላ ድርጅት ጋር የእሽሙር ማህበር ስምምነት ሲያደርግ አንደኛው የሌላኛውን የገበያ እድል የመጠቀም እና የማሳደግ አጋጣሚን ይፈጥርለታል፡፡ ለምሳሌ አንድ የአሜሪካ ካንፓኒ ከህንድ ካንፓኒ ጋር የእሽሙር ማህበር ስምምነት ቢያደርግ በህንድ ውስጥ የሚኖርን ሰፊ፣ የተለያየ የመግዛት ፍላጎት እና አቀም ያለውን ገበያ የመድረስ ጥቅም ያገኛል ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የህንድ ካንፓኒም በአሜሪካ ውስጥ የሚገኝን ጥሩ የመክፈል አቅም ያለውን ገበያ መቀላቀል ይችላል ማለት ነው፡፡
3. ፈጠራን ማሳደግ (Innovation)
የእሽሙር ማህበር ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ከቴክኖሎጂ አንጻር ለማሻሻል እድልን ይፈጥራል፡፡ በመሆኑም የቴክኖሎጂ መሻሻል እና የፈጠራ ስራዎች ማደግ የተሻሉ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ውጤታማ በሆነ ዋጋ( efficient cost) ለማቅረብ ያስችላል፡፡ አለም አቀፍ ድርጅቶች አዳዲስ ምርቶችን በቅናሽ ዋጋ በተሻለ ጥራት እንዲያቀርቡ ያደርጋል ማለት ነው፡፡
4. የማምረቻ ወጪን ማሳነስ (Low Cost of Production)
ሁለት እና ከሁለት በላይ ሸሪኮች ሲጣመሩ ውጤታማ በሆነ ዋጋ ምርትን ለደንበኞች ማድረስ አንዱ አላማቸው ነው፡፡ ይህም የሚሆነው የማምረቻ ዋጋን መቀነስ ሲቻል ነው፡፡ በመሆኑም የማምረቻ ዋጋን በጋራ በመቀነስ የተሻለ ምርት እና አገልግሎትን ለደንበኞች ያቀርባሉ፡፡
የእሽሙር ማህበር ጉዳት (Disadvantages of a Joint Venture)
1. ግልፅ ያለሆነ አላማ፡- ሸሪኮች በእሽሙር ማኅበር ሲጣመሩ አላማቸውን በጣም ግልፅ በሆነ ሁኔታ የማያስቀምጡበት አጋጣሚ በርካታ ነው፡፡ እንዲሁም የማህበሩ አላማ ለሁሉም የማህበሩ አባላት በአግባቡ ላይገለፅላቸው ይችላል፡፡
በመምሪያው ህ/ማ/ማ/ስ/ሂ crt to Amin
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍21❤2
ከሳሽ የሚቀርብን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አስቀድመህ ገምተህ ከክሱ ጋር በመቃወሚያው ላይ የሚኖርህን ማስረጃ ማቅረብ ነበረብህ ሊባል አይገባም።
(ከየተጠቃለሉ የሰበር ውሳኔዎች ከቅጽ 1-23 እና ያልታተሙ ከ2006-2015 መጽሃፍ የተወሰደ) coming soon!
========%%%%%%%===============
ሰ/መ/ቁ.224265፡- ከሳሽ የሆነ ወገን ለክሱ ተከሳሽ የሚያቀርበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አስቀድሞ ገምቶ ለዚህ የሚረዳው ማስረጃ ከክሱ ጋር አያይዞ እንዲያቀርብ አይጠበቅም። ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 245 ድንጋጌ መገንዘብ እንደሚቻለውም መቃወሚያ ሲቀርብ ፍርድ ቤቱ ሌላው ተከራካሪ ወገን በመቃወሚያው ላይ የሚያቀርበውን ክርክር ከሰማ በኋላ መቃወሚያውን ለመወሰን ተገቢ መስሎ የሚገምተው ማስረጃ እንዲቀርብለት ትዕዛዝ እንደሚሰጥና በመጨረሻም የቀረበው መቃወሚያ ከማስረጃው አንፃር መርምሮ ተገቢው ብይን መስጠት ይኖርበታል። ስለሆነም ከሳሽ ላቀረቡት ክስ ከተከሳሽ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተመልክተው መቃወሚያውን ውድቅ ለማስደረግ የበኩላቸውን ክርክር በማቅረብ ክርክራቸውንም በማስረጃ ለማስደገፍ የሚያቀርቡትን ጥያቄ የማስረጃ አቀራረብ ስርዓቱን የተከተለ አይደለም በማለት ማስረጃውን ተቀብሎ ከቀረበው መቃወሚያና ከክሱ ይዘት አንጻር ሳይመረምር ብይን መስጠት ህጉን የተከተለ አይደለም። ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ/ም
ከመላከ ጥላሁን ገጽ ተወሰደ
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍12😁1
ድለላ በተግባር እና በሕግ ዓይን
******************
አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ በ1948 ዓ.ም በታተመው ‘መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ወሀዲስ’ መጽሐፋቸው ‘ደላላ’ የሚለውን ቃል ‘‘በቁሙ መደለል፣ ማታለል፣ መሸንገል” ይሉታል።
ዶ/ር ዕሌኒ ገብረ መድህን ደግሞ በ1991 ዓ.ም ስለኢትዮጵያ የእህል ደላሎች ሚና ባቀረቡት የጥናት ጽሁፍ ላይ ‘ደላላ’ የሚለው ቃል ምንጩ አረብኛ መሆኑንን እና በሐገራችን ብቻ ሳይሆን በናይጄሪያ ‘ዲላላ’ በህንድ ‘ዳላል’ የሚለው ተመሳሳይ ስያሜ እንዳለው ጠቅሰዋል።
ደላሎች ቤት ፤መሬት፣ መኪና፤ ማሻሻጥና ማከራየት ብቻ ሳይሆን ከምንመገበው እህል አንስቶ ሌሎች ቁሳቁሶችን፣ አሠሪና ሠራተኛ፣ የቤት ሠራተኛም ያገናኛሉ። በአምራቹ እና በጅምላ ወይም በችርቻሮ ሻጩ፣ በአጓጓዡ፣ በገዢና በሻጭ መሀከልም አይጠፉም። ሕገ ወጥ ደላሎች ከሕገ ወጥ ተግባራትና ከዋጋ መናር ጋር ብዙ ጊዜ አብረው ሲነሱም ይሰማል። በዛሬው የሕግ ጉዳይ ስለደላሎች ሕጋችን ምን እንደሚል እንመለከታለን።
ከተወሰኑት ልዩ ቁጥጥር ከሚደረግባቸው የመድህን ድለላን የመሰሉ የውስን ግብይቶች ደላላነት በስተቀር በአብዛኛው የተለመደው የድለላ ተግባር እንደሌሎች ሥራዎች የተለየ የትምህርት ማስረጃ፣ ልምድ፣ የመነሻ እርሾ (ካፒታል)፣ ከስነ ምግባር እና ከብቃት አንጻር ማረጋገጫ ፈተና ስለማይጠይቅ እዚያው አካባቢያቸው ካለ መረጃ ተነስተው ወደ ድለላው የሚገቡ ብዙዎች ናቸው።
በየአካባቢያችን እንደምናስተውለው ከገዢ እና ከሻጭ የተሻለ መረጃ ባይኖራቸውም የቤት ኪራይም ሆነ ሽያጭ ዋጋ ወይም የሌሎች አገልግሎቶች ዋጋ የሚወሰነው በገበያው ወይም በሻጩ ሳይሆን በአካባቢው ደላሎች ነው። ይህን የገበያውን ሚና ደላሎች የሚወስኑት የሚያገኙትን አበል ለመጨመር ስለሚመቻቸው እና ዋጋ በጨመረ ቁጥር በመቶኛ የሚያገኙት ክፍያ ስለሚጨምር ነው። በአሁን ጊዜ ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያውን በመጠቀም ከሞባይል ስልክ እስከ ቤት እንደልላለን የሚሉ ደላሎችን እያየን ነው። እግር እስኪነቃ ከመዞር ለደላሎችም ለተጠቃሚውም ይህኛው የተሻለ አማራጭ ይመስላል።
በ2013 ዓ.ም ተሻሽሎ የወጣው የንግድ ሕግ አንቀጽ 54 ስለ ደላሎች እንዲህ ይላል:-
1. ደላሎች ውል ተዋዋዮችን (እንደ ሽያጭ፣ ኪራይ፣ ኢንሹራንስ፣ የማመላለሻ ውል የመሳሰሉትን) የሚዋዋሉ ሰዎችን ፈልገው የሚያገናኙ እና የሚያዋውሉ፣ ድለላን ራሱን የቻለ የሙያ ተግባራቸው አድርገው ጥቅም ለማግኘት የሚሠሩ ሰዎች ወይም ይህንኑ የድለላ ሥራ የሚሠሩ የንግድ ማህበራት ናቸው። ብዙውን ጊዜ እንደምንታዘበው ግን ደላሎች ፈልገውን አያውቁም፤ ገዥ ወይም ሻጭ ነው ፈልጎ የሚያገኛቸው።
2. ድለላ ጥቅም ለማግኘት የሚሰራ ራሱን የቻለ የሙያ ተግባር ሲሆን ደላላው ምንም ያገናኝ ምን በንግድ ሕጉ መሰረት ነጋዴ ነው፤ በመሆኑም የንግድ ፍቃድ ማውጣት አለበት።
የንግድ ፍቃድ ለማግኘት ደግሞ የድለላ ሙያ የሚጠይቀው ልምድ፣ የትምህርት ዝግጅት፣ አስፈላጊ ካፒታል፣ ቋሚ አድራሻ ያስፈልጋል። የንግድ ፍቃዱ በግል ንግድ ወይም በንግድ ማህበርነት የተመዘገበ መሆን አለበት። ስለዚህ እንደማንኛውም የንግድ ስራ ድለላ ከሚያስገኘው ገቢ ላይ ግብር ለማስገበር ያስገኘው ገቢና የሚከፍለው ግብር መታወቅ አለበት።
ተገቢው አካልም ትክክለኛውን አገልግሎት መስጠታቸውንና የግብር ግዴታቸውን መወጣታቸውን ለማረጋገጥ አሠራራቸውን ቁጥጥር ሊያደርግበት ይገባል። በተግባርስ? ሌላ ነው።ጥቂት የድለላ መስኮች ብቻ ናቸው በሕጋዊ መልኩ እየሠሩ ያሉት። የመድህን ዋስትና ደላሎች በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የሚሰጣቸው እና ቁጥጥር የሚደረግባቸው ናቸው።
ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች ቡና፣ ሰሊጥ እና ነጭ ቦለቄ የሚያገበያዩ ደላሎች በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ፍቃድ አውጥተው አባል በመሆን ቁጥጥር እየተደረገባቸው ይሠራሉ።
ለዚህ አይነቶቹ የድለላ ሥራዎች ከፍተኛው የአገልግሎት ክፍያ በሚመለከተው ሕግ ተደንግጓል። ከአምራቹ እስከ ነጋዴው ያለው ረጅም የደላላ ቅብብሎሽ ሰንሰለት በማጠሩና ተገቢ ቁጥጥር የሚደረግበት ውድድር በመሀላቸው በመኖሩ የምርት ገበያው ደላሎች ኮሚሽን የሚያስከፍሉት በሕግ በተገደበ የመቶኛ ስሌት ነው ።
የቁም ከብት ግብይት ላይም በግብይቱ የመሐል ደላሎችን የሚቆጣጠር ተመሳሳይ አዋጅ ወጥቷል። ከእነዚህ ውጪ በተለይ በየሰፈራችን ያሉት የቤት ኪራይ እና ሽያጭ እና ሌሎችም ደላሎች ግን የተወሰኑት ካልሆኑ በስተቀር የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ግብር የሚገብሩ አይደሉም።
አብዛኞቹ ሌሎች የተለመዱ የድለላ ሥራዎች ላይ ግን ፈቃዱን ለማግኘት ሙያው የሚያስፈልገውን መስፈርት የሚጠይቃቸው አካል ባለመኖሩ ልምድና ትምህርቱ እንዲሁም ስነ ምግባሩ የሌላቸው ደላሎችም ሲደልሉ ይታያል። በዚህም የተነሳ በተመጣጣኝ ዋጋ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ አገልግሎታቸውን እንዳናገኝ ሆነናል።
3. የደላላ አበልን በተመለከተ የንግድ ሕጋችን "በደላላው አስማሚነት ውሉን ካስጨረሰ ወይም ካዋዋለ በኋላ የውሉ ግዴታ ቢፈፀምም ባይፈፀምም ደላላው አበሉ ይከፈለዋል" ይላል። በተግባር ግን የሚታየው ደላላው ዋጋ ይናገራል ቤቱን ወይም እቃውን ያሳያል ተከራክረው የሚያስማማቸው ዋጋ ላይ የሚደርሱት ግን ገዥና ሻጭ ወይም አከራይና ተከራይ ናቸው።
4. ሕጉ እንደሚለው በልማድ የታወቀ ካልሆነ ወይም ሌላ ስምምነት ከሌለ ለደላላው አበል የሚከፍለው አገልግሎቱን የጠየቀው ሰው ብቻ ነው። በተግባር እንደምንታዘበው ግን ለአንድ አገልግሎት ደላላው ወይም ደላሎቹ ከሁለቱም ተዋዋዮች አበል ይቀበላሉ። ‘የሚከራይ ቤት አለኝ’ ብሎ አከራዩ ለደላላው ይናገራል። ደላላው ይህን መረጃ ይዞ ተከራይ አያፈላልግም ምን በወጣው! ተከራይ ራሱ ነው ‘ቤት እፈልጋለሁ’ ብሎ የሚመጣው። ሕጉ እንደሚለው ተዋዋዮችን ደላላው ስለማያፈላልግና አገልግሎቱን የሚጠይቁት ተዋዋዮች ስለሆኑ ደላላው ከሁለቱም አበል ይቀበላል።በተጨማሪም በአንድ ግብይት ውስጥ ከሁለቱም ተዋዋዮች በኩል ብዙ ደላሎች ስለሚኖሩ የግብይቱን ዋጋ እና የአበሉን መጠን በማናገር ገዢ ወይም ተከራይ ላይ ጫና ያሳድራል።
5. የአበሉ መጠን በቅድሚያ በስምምነት መወሰን አለበት። ተዋዋዩ እና ደላላው የደለለበትን አበል ይህን ያህል እከፍላለው ብለው ቅድሚያ መስማማት አለባቸው ። በተግባር ግን ይህ ስምምነት በቅድሚያ ስለማይደረግ አብዛኛውን ጊዜ ደላላው ኪራይ ከሆነ የመጀመሪያውን ክፍያ 10 በመቶ ሽያጭ ከሆነ 2 በመቶ ይቀበላል።
6. በንግድ ሕጉ መሰረት የድለላው አበል ላይ በቅድሚያ ስምምነት ካልተደረገ ሕጉ "የደላላው አበል በልማድ መሰረት ይቆረጣል" ይላል። በዚህ ምክንያት ይመስላል በአብዛኛው ደላሎች ቀድመው የአበላቸውን መጠን የማይጠይቁት። አበላቸውም በመቶኛ እንጂ በቁርጥ እንዲሆንም አይፈልጉም። ስለዚህ ለአንድ ቀን ቤቱን አሳይቶ ዋጋ ለተናገረበት ከላይ የጠቀስኩትን የልማድ ዋጋ የመቶኛ ስሌት በሁለቱም ተዋዋዮች በኩል ያሉት ደላሎች ያስከፍላሉ። ይህ የልማድ ዋጋ ለደላሎች ቢመችም ለተዋዋዮች እና ለሻጮች ግን በአብዛኛው ፍትሐዊ ወይም ከተሰጠው አገልግሎት ጋር ተመጣጣኝ አይደለም።
7. ተዋዋዮ እና ደላላው የአበሉን መጠን ቢስማሙም እንኳን የተስማሙበት አበል ከባድ መስሎ ከታየው ወይም ደላላው ከሰጠው አገልግሎት ጋር ተመጣጣኝ አለመሆኑ ሲታየው የንግድ ሕጋችን በአንቀፅ 57 (3) ላይ ለፍ/ቤት የአበሉን መጠን የመቀነስ ስልጣን ሰጥቷል ። በተግባር ግን ደላሎች በዚህም በዚያም ብለው ተመጣጣኝ ሆነ አልሆነ የጠየቁትን ያስከፍላሉ።
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍6
8. የንግድ ሕጉ አንቀፅ 57(4) ደላላው ኃላፊነት አለበት ይላል። ደላላው ለደንበኛው ወይም አገልግሎቱን ለጠየቀው ወገን ያሉበትን ግዴታዎች ተላልፎ የደንበኛውን ጥቅም በሚጎዳ አኳኀን ለሌላ 3ኛ ወገን ጥቅም የሠራ እንደሆነ ወይም ደንበኛው ሳያውቅ ከ3ኛ ወገን ክፍያ ከተቀበለ አበል የማግኘት መብቱ ቀሪ ይሆናል። በተግባር ግን ብዙዎች ደላላ ቢጎዳቸውም ከመበሳጨት በስተቀር በፍርድ ቤት ከሰው በኃላፊነት ካሳ ሲጠይቁ አይታይም።
ለማንኛውም ደላላ ስትጠቀሙ በተለይ አበሉን በተመለከተ በቁርጥ በቅድሚያ ተስማሙ። በመቶኛ ከሆነ አበላቸውን ለመጨመር ዋጋውን ከፍ ሊያደርጉት ስለሚችሉ በቁርጥ አድርጉት። አበሉን ተስማምታችሁም ቢሆን ከሰጡት አገልግሎት ጋር የክፍያው መጠን ከተጋነነ ይገባል ከምትሉት በላይ አልከፍልም በሉ። ጉዳዩ ፍ/ቤት ከደረሰ ሊቀነስላችሁ ይችላል። ቢቻል የንግድ ፍቃድ ባላቸው ደላሎች ተጠቀሙ። ደላላው የሚጠራውን ዋጋ ከማመናችሁ በፊትም በተለያየ ዘዴ የገበያውን ዋጋም ለማጣራት ሞክሩ።
EBC
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
ለማንኛውም ደላላ ስትጠቀሙ በተለይ አበሉን በተመለከተ በቁርጥ በቅድሚያ ተስማሙ። በመቶኛ ከሆነ አበላቸውን ለመጨመር ዋጋውን ከፍ ሊያደርጉት ስለሚችሉ በቁርጥ አድርጉት። አበሉን ተስማምታችሁም ቢሆን ከሰጡት አገልግሎት ጋር የክፍያው መጠን ከተጋነነ ይገባል ከምትሉት በላይ አልከፍልም በሉ። ጉዳዩ ፍ/ቤት ከደረሰ ሊቀነስላችሁ ይችላል። ቢቻል የንግድ ፍቃድ ባላቸው ደላሎች ተጠቀሙ። ደላላው የሚጠራውን ዋጋ ከማመናችሁ በፊትም በተለያየ ዘዴ የገበያውን ዋጋም ለማጣራት ሞክሩ።
EBC
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍9❤4🔥1
ሰ/መ/ቁ 235844 የማይንቀሳቀስ ንብረት በባልና ሚስት ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቢሆንም ከጋብቻ በፊት መፈራቱ ወይም መገዛቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካለ የአንደኛው ተጋቢ የግል ንብረት ነው።
Abrham yohanes
Abrham yohanes
👍23😁1
የሆቴሎች የአለባበስ ሥርዓት ረቂቅ ደንብ ይፋ ሆነ
*
(ኢ ፕ ድ)
በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች የሚደርስባቸውን አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጫናን ያስቀራል የተባለለት ረቂቅ ደንብ ይፋ ተደረገ፡፡
አዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የገፅታና የውበት አጠባበቅ እንዲሁም የጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥነ-ሥርዓት ያወጣውን የደንብ ረቂቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።
በቢሮው የቱሪዝም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኃፍታይ ገ/እግዚአብሔር በወቅቱ እንደገለጹት፤ በባለሙያዎች የሚደርስን ጥቃት የሚያስቀር የአለባበስ ሥርዓት ረቂቅ ደንብ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የደንብ ረቂቁ ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎችም የተካተቱበት ነው፡፡
በሂደቱም የቢሮው የቱሪዝም ባለሙያዎች፣ የኢትዮጵያ መስተንግዶ ማህበር፣ የአዲስ አበባ ሆቴሎችና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር፣ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋም እና የአዲስ አበባ ሆቴሎች ሥራ አስኪያጅ ማህበር እንደተሳተፉበት ገልጸዋል።
እንደ አቶ ሃፍታይ ገለጻ፤ ደንቡ በአዲስ አበባ ያሉ ሆቴሎችና መሰል ተቋማት ወጥ የሆነ ሥርዓት እንዲኖራቸው....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=115367
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
*
(ኢ ፕ ድ)
በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች የሚደርስባቸውን አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጫናን ያስቀራል የተባለለት ረቂቅ ደንብ ይፋ ተደረገ፡፡
አዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የገፅታና የውበት አጠባበቅ እንዲሁም የጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥነ-ሥርዓት ያወጣውን የደንብ ረቂቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።
በቢሮው የቱሪዝም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኃፍታይ ገ/እግዚአብሔር በወቅቱ እንደገለጹት፤ በባለሙያዎች የሚደርስን ጥቃት የሚያስቀር የአለባበስ ሥርዓት ረቂቅ ደንብ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የደንብ ረቂቁ ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎችም የተካተቱበት ነው፡፡
በሂደቱም የቢሮው የቱሪዝም ባለሙያዎች፣ የኢትዮጵያ መስተንግዶ ማህበር፣ የአዲስ አበባ ሆቴሎችና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር፣ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋም እና የአዲስ አበባ ሆቴሎች ሥራ አስኪያጅ ማህበር እንደተሳተፉበት ገልጸዋል።
እንደ አቶ ሃፍታይ ገለጻ፤ ደንቡ በአዲስ አበባ ያሉ ሆቴሎችና መሰል ተቋማት ወጥ የሆነ ሥርዓት እንዲኖራቸው....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=115367
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
👍5👏2😱1

👍4

❤6👍5