አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 418
አንድ ሰው የመዝገብ ተካፋይ/ተከራካሪ ባይሆንም በክርክሩ ምክንያት የሱ የሆነ ንብረት እንደመያዣ/ ማስከበሪያ በተከራካሪ ወገኖች ቀርቦበት ሊሆን ይችላል። በዚህ ንብረት ላይ ያለውንም መብት ለማስጠበቅ የሚያቀርበው አቤቱታም

1. መዝገቡ አፈፃፀም እስኪደርስ የዘገየው በበቂ ምክንያት መሆኑን ማስረዳት 2. በፅሁፍ ሆኖ ፍርዱን ለሚያስፈጽመው ፍርድ ቤት መቅረብ

3. በንብረቱ ላይ ያለውን የተቀዳሚነት መብት ወይም ባለይዞታነቱን የሚያረጋግጥ የፅሁፍ ማስረጃ አብሮ ማያያዝ አለበት። አቤቱታውን ፍርድ ቤቱ ውድቅ ቢያደርገው አቤት ባዩን በንብረቱ ላይ አዲስ ክስ ከመመስረት አያግደውም።
የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት…
አለ_ህግ #Ale_Hig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏🙏
@Lawsocieties #አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig


Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/

Telegram Channel
https://t.me/lawsocieties

👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆


👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆

#አለ_ህግ #Ale_Hig
ይህ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ሲሆን፣
ለበለጠ መረጃ ግን የህግ ባለሙያ ያማክሩ‼️👈
በአዲሱ ቦሌ ምድብ ችሎት ለተመደቡ ሠራተኞች የሥራ ገለጻ ተደረገ፡፡
**************************************************
በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከህዳር 1/2016 ዓም ጀምሮ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት የሚጀምረውና ለፍርድ ቤቱ 13ኛ ምድብ ችሎት የሆነው ለአዲሱ ቦሌ ምድብ ችሎት አስፈላጊው የሠው ሀይል ምደባ የተደረገ ሲሆን በዚሁ መሰረት ለተመደቡ አስተዳደር ሠራተኞች በተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ፣ በስራ ቦታና ጊዜ በመገኘት ስነ ምግባር በመላበስ ለተገልጋዮች የዳኝነት አገልግሎት እንዲሰጡ እንዲሁም በተሻለ ሁኔታ የፍርድ ቤቱን የለውጥ ተግባራት ማስቀጠል እንደሚኖርባቸዉ በበላይ አመራሮች የስራ ገለጻ ተደርጓል፡፡
የዳኞች ካባ አለባበ
*
**
የፌደራል ፍርድ ቤቶች የችሎት ስርዓት መመሪያ ቁጥር 13/2014 አንቀጽ (1) ማንኛውም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ በጥቁር ካባ መደብ ላይ ከአንገቱ እስከ እግር ሰማያዊ ቀለም ያለው ካባ፣ ከአንገት የሚጀምር አንድ ወርቃማ መነሳነስ እንዲሁም በካባው እጀታ አንድ ሰማያዊ መስመር ያለው ካባ መልበስ እንዳለበት ይደነግጋል፡፡
በተጨማሪም በችሎት ካባ መልበስ ስላለባቸው ተከራካሪዎች እንዲሁም ካባ የማይለበስባቸው በወንጀል ነክ ነገር ውስጥ ገብተው የተገኙ ወጣቶች እና በዳኝነት ስርዓቱ የሚያልፉ ህጻናቶችን በተመለከተ የሚያስችሉ ዳኞች፣ ተከራካሪዎች እና ሌሎች ባለሙያዎች ብቻ ካባ ማድረግ እንደሌለባቸው ይደነግጋል፡፡
በመመሪያው መሰረት የክቡራን ዳኞች የካባ ግዥ የተከናወነ እና ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ13ቱም ምድብ ችሎቶች ለሚገኙ ክብሯን ዳኞች ካባ እየተሰራጨ የሚገኝ ሲሆን በመመሪያው መሰረት እንዲተገብር እናሳውቃለን፡፡

ፍርድ ቤቱ
አለ_ህግ #Ale_Hig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏🙏
@Lawsocieties #አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig


Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/

Telegram Channel
https://t.me/lawsocieties

👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆


👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆

#አለ_ህግ #Ale_Hig
ወጣት የህግ ባለውያ ንጋቱ አበራ ከአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ የህግ ት/ቤት በ2008 ዓ.ም የLLB (የመጀመሪያ) ዲግሪውን እንዲሁም በ2011 ዓ.ም በድጋሚ ከአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ የLLM ዲግሪውን በ (Business Law) አግኝቷል። በስራው ዓለምም በዪኒቨርስቲ መምህርነት እና በአሁኑ ሰአት ደግሞ በአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በዓቃቤ ህግነት እያገለገለ ይገኛል። በተያዘው ዓመትም የፌደራል የጥብቅና ፍቃድ በማውጣት የጠበቆች ማህበርን ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ የነበረ መሆኑን ገልፆአል::  ይሁንና በተደጋጋሚ የራስ ምታት ህመም ምክንያት ወደ ሆስፒታል በመሄድ ምርመራ ሲያደርግ በቀኝ የኋላ የጭንቅላት ክፍል ውስጥ መጠኑ ወደ 5cm*5cm*5cm የሚጠጋ እና በየቀኑ በፍጥነት እየጨመረ የሚሄድ ዕጢ/tumor/ እንዳለ በምርመራ እንደተረጋገጠ ከስራ ባልደረቦቹ የተገኘው የህክምና ማስረጃ ያሳያል።   በሌላ በኩል ከህመሙ ክብደት አንጻር በሀገር ውስጥ ያለው ህክምናም በቂ ስላልሆነ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ መታከም አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው፤ ይህን ወጪ ቤተሰቦቹ መሸፈን የሚችሉት ባለመሆኑ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁ. 1000582396527 በሆነው በስሙ በተከፈተው የባንክ ሂሳብ የእርዳታ ጥሪ ቀርቧል::

   የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  የሂሳብ ቁ. 1000582396527

👉👉ሼር ማድረግም ድጋፍ ነው።👈
#አለ_ህግ #Ale_Hig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏🙏
@Lawsocieties #አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig


Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/

Telegram Channel
https://t.me/lawsocieties

👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆
የመንግስት ( የቀበሌ/የኪራይ) ቤቶችን በተመለከተ የፌደሬሽን ምክር ቤት የሰበር ውሳኔን በመሻር ውሳኔ አስተላለፈ።
ከዚህ ቀደም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስንት ሰሚ ችሎት በሠ/መ/ቁ. 189707 እና በሠ/መ/ቁ. 228002 ጠቅለል ሲደረግ
ቤትን ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት አያጎናጽፍም ሠ/መ/ቁጥር 228002     አንድን ቤት ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት የማያጎናጽፍ በመሆኑ እንዲሁም ቤቱ የቀበሌ / የመንግስት / ቤት መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌሉበትሁኔታ በተቋሙ የመረጃ ስርአት ቅጽ 008 በቀበሌ ቤትነት መመዝገቡ ብቻ ቤቱ በመንግስትየተወረሰ የቀበሌ /የመንግስት ቤት ነው ሊያስብለው አይችልም። በአዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሶ ለረጅም ግዜ በመንግስት እጅ የነበረ ቤትን በሚመለከት በስህተት አላግባብ ያለህጋዊ ምክንያት ተሰጥቷል የተባለው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የመከነና በመንግሰት ባለቤትነት የሚታወቅ ስለመሆኑ በተገለጸበት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት መንግስት የወረሰው መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌለበት ቤቱን የመንግስት ንብረት አያሰኘውም።
የሚል ውሳኔ ወስኖ የነበረ ሲሆን ይህንን ውሳኔ የኢፌድሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ባደረገው 6ተኛ የፓርላማ ዘመን 3ተኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤው በህገ መንግስት አጣሪው በቀረበለት መሰረት በመ/ቁጥር 108/15 የሠ/መ/ቁ .189707 ህገመንግስታዊነት አጣርቶ ውሳኔውን ሽሮታል።
ስለሆነም የመንግስት ቤትን ለረጅም ጊዜ ከአዋጅ 47/67 በኋላ ይዞ ያስተዳድር የነበረ ሁለቱ ቅፃች ቅፅ 003 እና 004 ባይኖሩትም ባለይዞታነቱ ይቀጥላል።
Credit to Daniel Feqadu
አለ_ህግ #Ale_Hig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏🙏
@Lawsocieties #አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig

https://t.me/lawsocieties

Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/

Telegram Channel
https://t.me/lawsocieties

👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆


👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆

#አለ_ህግ #Ale_Hig
" የቤት አከራዮች የተከራዮቻቸውን ማንነነት እና የሚሰሩትን ስራ በደንብ ማረጋገጥ አለባቸው " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ ሀሰተኛ የውጪ ሀገራትና የኢትዮጵያን ገንዘብ በማተም የተጠረጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎች መያዙን አሳወቀ።

በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሰረት መደረጉንም ገልጿል።

ሀሰተኛ ገንዘብ በማዘጋጀት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች የተያዙት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው " ቦሌ አዲስ ትምህርት ቤት " አካባቢ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል።

የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው 3 ግለሰቦች #ሙሉ_ግቢ የመኖሪያ ቤት በመከራየት  ሀሰተኛ ብር እና የውጭ ሀገር  ገንዘቦችን በማተም  እንደሚያሰራጩ እና የከበሩ ማዕድናትን በህገ-ወጥ መንገድ እንደሚያዘዋውሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ክትትልና ባሰባሰበው ማስረጃ ያረጋግጣል።

ህጋዊ አሰራሩን ተከትሎ በተደረገ ብርበራም ተጠርጣሪዎቹ ፦
- ሀሰተኛ ገንዘቦችን ለማዘጋጀት የሚገለገሉባቸውን መሳሪያዎች ፣
- ልዩ ልዩ ኬሚካሎችን  ፣
- በሀሰተኛ መንገድ የታተሙ ገንዘቦች ፣
- በገንዘብ ልክ ተቆራርጠው የተዘጋጁ ወረቀቶች
- የዘንዶ ቆዳዎችን በኤግዚቢትነት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ሀሰተኛ ገንዘብ ከማዘጋጀት በተጨማሪ የፀና የመኖሪያ ፍቃድ ሳይኖራቸው እየኖሩ ያሉና በህገ-ወጥ መንገድ የከበሩ ማእድናትን እንደሚዘዋውሩ በምርመራ ማረጋገጡን ገልጿል።

ፖሊስ የምርመራ መዝገብ በማደራጀትና በማጠናቀቅ ለሚመለከተው የፍትህ አካል በመላክ ክስ ተመስርቶባቸዋል ብሏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ክ/ከተሞች ውስጥ በተመሳሳይ መንገድ ሀሰተኛ ገንዘቦችን ሲያትሙ የተገኙ ግለሰቦች እንደተያዙ አስታውሷል።

" መሰል የወንጀል ድርጊቶች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ ናቸው " ያለው ፖሊስ መኖሪያ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች ለወንጀሉ መስፋፋት ምቹ ሁኔታን እየፈጠሩ መሆናቸውን በመረዳት  የተከራዮቻችውን ማንነነት እና የሚሰሩትን ስራ የማረጋገጥ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስቧል።
@tikvahethiopia
አለ_ህግ #Ale_Hig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏🙏
@Lawsocieties #አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig

https://t.me/lawsocieties

Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/

Telegram Channel
https://t.me/lawsocieties

👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆


👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆

#አለ_ህግ #Ale_Hig