በፍትሀብሄር ክርክር የሚቀርብ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
ሰዎች በእለት ተእለት በሚኖራቸው መስተጋብር የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በራሳቸው መፍታት ሳይችሉ ሲቀሩ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረባቸው በየእለቱ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ፍርድ ቤት ሲቀርብም ከክስ አቀራረብ ጀምሮ የክርክር ሂደቱ የሚመራበት ሥነ ሥርአት አለው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ አንድ ሰው የፍትሐብሔር ክስ ቀርቦበት መልስ በሚያቀርብበት ወቅት ሊቀርብ የሚችልን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ምንነት እንዲሁም የሚቀርብበት ጊዜና ሁኔታ እንመለከታለን።
የመጀመሪያ ደርጃ መቃወሚያ ምንነት
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ወደ ዋናው ክርክር መግባት ሳያስፈልግ የቀረበው ክስ ውድቅ የሚሆንበትን ምክንያት በመግለፅ ክሱ ውድቅ እንዲሆን በማንኛውም ተከራካሪ ወገን የሚቀርብ መቃወሚያ እንደሆነ ከፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244(1) መረዳት ይቻላል።
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ምክንያቶች
አንድ ሰው የፍትሐብሔር ክስ ቀርቦበት መልስ እንዲያቀርብ በታዘዘ ጊዜ በቀረበበትን ክስ ላይ ከሚያቀርባቸው ክርክሮች መካከል አንዱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነው። የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244(2) የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊቀርብ የሚችልባቸውን ምክንያቶች በዝርዝር አመልክቷል፡፡ ይኸውም፡-
• ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ነገሩን ወይም የቀረበውን ክስ ለመስማት ስልጣን የሌላው ከሆነ
• ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ጉዳይ ከሆነ
• ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሌላ ፍርድ ቤት ቀርቦ በክርክር ላይ ያለ ከሆነ
• አንደኛው ተከራካሪ ወገን በነገሩ የማያገባው መሆኑን በመግለፅ በጉዳዩ ገብቶ መከራከር አይገባውም የሚባል ከሆነ
• ክሱ በይርጋ የታገደ ከሆነ
• ክሱ የተነሳበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ ወይም ለእርቅ የተቀጠረ ከሆነ
ይህን በመግለፅ መቃወሚያ ሊቀርብ ይችላል።
ለቀረበበት ክስ መልስ የሚሰጥ ማንኛውም ወገን ከላይ ከተጠቀሱት መቃወሚያዎች አንዱን ወይም ከአንድ በላይ እንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊያቀርብ የሚችል ሲሆን በተቻለ መጠን በቶሎ ተጠቃለው መቅረብ አለባቸው። አንድ ተከራካሪ መቅረብ ከሚገባው መቃወሚያ ውስጥ አንዱን የተወ እንደሆነ ፍርድ ለመስጠት የሚያሰናክል ካልሆነ በስተቀር መቃወሚያውን ለማቅረብ እንዳልፈለገ እንደሚቆጠር በድንጋጌው ንኡስ ቁጥር 3 ላይ በግልፅ ተመልክቶ ይገኛል፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ በፍርድ ቤት የሚሰጥ ውሳኔና ውጤቱ
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሲቀርብ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ሌላኛው ወገን በጉዳዩ ላይ ያቀረበውን ክርክር ከሰማ በኋላ በቀረበው መቃወሚያ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ማስረጃ እንዲቀርብለት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(1) መሰረት ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተገቢና በቂ በሆነ ማስረጃ የተደገፈ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ባረጋገጠ ጊዜ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ጉዳይ በመሆኑ ወይም ክሱ የተነሳበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ በመሆኑ ወይም ለእርቅ የተቀጠረ በመሆኑ እንደሆነ የቀረበውን ክስ በመዝጋት ባለጉዳዮችን ያሰናብታል። የቀረበው መቃወሚያ ከእነዚህ ውጭ ሆኖ መቃወሚያው ተገቢ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ባረጋገጠ ጊዜ መዝገቡን በመዝጋት ተገቢ መስሎ የታየውን ትእዛዝ ይሰጣል።
ሌላው የቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት አግኝቶ መዝገቡ የተዘጋ እንደሆነ ከሳሽ ክሱን አሻሽሎ በዚያው ጉዳይ መጀመሪያ ክስ ላቀረበበት ፍርድ ቤትም ይሁን ለሌላ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክሱን እንደገና የማቅረብ መብቱ የተረጋገጠ ሲሆን ፍርድ ቤቱም መዝገቡን በሚዘጋበት ወቅት ከሳሽ እንደገና ክስ የማቅረብ መብት እንዳለው በትእዛዙ ላይ መግለፅ እንደሚችል በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(3) ላይ በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል።
በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ መዝገቡን የዘጋው ‘ፍርድ ቤቱ ነገሩን የማየት ስልጣን የለውም’ በሚል መቃወሚያ መሰረት ሲሆን ከሳሽ ከከፈለው የዳኝነት ገንዘብ ላይ የሚቀነሰው ተቀንሶ የተረፈው ገንዘብ እንደሚመለስለት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(4) ላይ በግልፅ ተደንግጓል።
በአጠቃላይ የፍትሐብሔር ክስ የቀረበበት ማንኛውም ሰው ወደ ዋናው ክርክር ከመግባቱ በፊት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244 ሥረ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ባሉ ጊዜ ይህንኑ በመጥቀስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ይህም ወዲያውኑ መቅረብ ያለበት መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

Job Vacancy Notice
Position: Legal Assistant
Location: Bole bulbula, Addis ababa
Compensation: 5,000 birr per month
Job Type: Full-time
Tamiru yacob attorney at law is seeking a dedicated and motivated individual to join our legal team as a Legal Assistant. This is an excellent opportunity for individuals who are looking to start their career in the legal field with no prior experience required. We are committed to providing training and mentorship to help you grow in your role.
Responsibilities:
- Assist attorneys in legal research and document preparation.
- Organize and maintain legal files, documents, and records.
- Draft and proofread legal documents, including contracts, pleadings, and correspondence.
**Background
: LLB from recognisable university
:fluency in the English and amharic languages
: basic computer and typing skills
: No previous working experience required
Interested and qualified applicants can apply through tamiruyac@gmail.com
P.S. we do not accept any applications besides through emails so apply accordingly
Deadline:- september 27, 2023

Position 1: Legal Officer III
Educational back ground: LLB in Law
Relevant Work Experience: Four (4) Years
Additional skill: Excellent written and verbal communication, Basic computer skill ,Knowledge of all applicable laws, rules and regulations, High attention to detail, Strong negotiation skills, Ability to prepare complex legal documents
Required Number: 2
Place of work: Addis Ababa
Position 2: Senior Legal Officer
Educational back ground: LLB in Law
Relevant Work Experience: Six (6) Years

Deadline: September 28, 2023
How to Apply:
Interested applicants, who full fill the aforementioned requirements can submit non-returnable application latter, CV & copies of testimonials accompanied by original documents in person within 10 (TEN) consecutive days from the date of this announcement in the Reporter news paper to:-
Lion insurance Company (S.C) Head office, located at Haile G/slassie Avenue, Lion Insurance Building HR& Facility Management Department 4th floor; Tell: – 0116187000/0116352285 –
Addis Ababa-Ethiopia.
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#Share #ሼር
#አለ_ህግ #Alehig
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

ችሎት መድፈር
ችሎት የፍትህ አደባባይ እንደመሆኑ ሊከበር የሚገባው ነው፡፡ ሆኖም በተለመደው የህብረተሰብ አኗኗር ዘይቤ ስለችሎት ሲነሳ ችሎት እና የችሎት ዳኛን ከማክበር ባለፈ ፍርድ ቤት ገብተው እስኪወጡ ድረስ እታሰር ይሆን ብለው በፍርሀት የሚዋጡ ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ በአንፃሩ በእውቀት ማነስና ሌሎች ምክንያቶች የችሎትን ክብር የማያከብሩ በዛው ልክ ይኖራሉ፡፡ በዚህ አጭር ፅሑፍ የችሎት መድፈርን ምንነትና የሚያስከትለውን ተጠያቂነት እንመለከታለን፡፡
የችሎት መድፈር ምንነት
ጠቅለል ባለ መልኩ ችሎት መድፈር ማለት ለሕግ ወይም ለፍርድ ቤት አለመታዘዝ፣ ለችሎት ክብር መንፈግ ወይም የፍርድ ቤትን ሥራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለማወክ መሞከር አልያም ደግሞ በዳኝነት ሥራው ጣልቃ መግባት እና መሰናክል መፍጠር ነው፡፡ ለፍርድ ቤት አለመታዘዝ የምንለው በችሎት ሂደት ውስጥ በዳኛው የሚተላለፉ ትዕዛዞችን አለማክበር ወይም መተላለፍ ነው፡፡ ለችሎት ክብር መንፈግ ደግሞ ፍርድ ቤት ማህበረሰቡ ፍትሕ የሚያገኝበት ስፍራ በመሆኑ ሊሰጠው የሚገባውን አክብሮት ለተቋሙና ለዳኛው አለመስጠት ነው። በሌላ በኩል ፍርድ ቤትን ማወክ፣ ፍርድ ቤት ስራውን እንዳያከናውን መሰናክል መሆን፣ የዳኝነት ሂደቱ ሊካሄድ በማይችልበት ሁኔታ እንዲቋረጥ ማድረግ ወይም ለማቋረጥ መሞከር አልያም ደግሞ ዳኛው በነፃነት ተግባሩን እንዳያከናውን መሰናክል መፍጠርን የችሎት መድፈር ልንለው እንችላለን።
በኢትዮጵያ የሕግ ማዕቀፍ ችሎት መድፈር ቀጥተኛ ትርጓሜ ተሰጥቶት ባናገኘውም ከአጠቃላይ ስለችሎት መድፈር የሚያነሱት የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 480፣ 481 እና የወንጀል ህግ ቁጥር 449 መንፈስ ሲተነተን ፍርድ ቤቶች በዕለት ተዕለት ተግባራቸው በፍርድ ቤት ውስጥ እና ከፍርድ ቤት ውጪ ሊፈጠሩ የሚችሉ ከችሎት ሂደቱ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው ማንኛውንም የፍትሐብሔርም ሆነ የወንጀል ጉዳይ የዳኝነት ሥራዎችን የሚያውኩ ወይም የሚያደናቅፉ ተግባራትን የሚያካትት ነው፡፡ ይህም በችሎት ውስጥ በተገኘ በማንኛውም ግለሰብ፣ ችሎቱ ከተሰየመበት ጉዳዩ ጋር ግንኙነት ባለው ባለ ጉዳይ፣ ችሎት በመከታተል ላይ ባለ ወይም ሌላ ከችሎቱ ውጭ በሆነ ግለሰብ ቢፈፀም ተጠያቂነት የሚያስከትል ነው። በመርህ ደረጃ በወንጀል የተጠረጠረ ሰው ለጥፋት በሕግ የተቀመጠውን የሕግ ሥርዓት ተክትሎ ማስረጃ በማጣራት በዐቃቤ ሕግ ክስ ተመስርቶና ማስረጃ አቅርቦ ቅጣት የሚወሰን ሲሆን በችሎት መድፈር ሁኔታ ግን ጉዳዩ የሚፈጠረው ችሎት ውስጥ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛውን ወዲያው አስቀርቦ ሊቀጣ ይችላል፡፡
ችሎት መድፈር የሚያስከትለው ተጠያቂነት
በኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ በአንቀፅ 449 መሰረት ማንም ሰው በፍርድ ቤት ምርመራ በሚደረግበት ወይም የፍርድ ሥራ በሚከናወንበት ጊዜ
ፍርድ ቤቱን ወይም የዳኝነት ሥራ በማከናወን ላይ ያለውን ዳኛ በማናቸውም መንገድ፣ የሰደበ፣ ያወከ፣ በችሎቱ ላይ ያፌዘ፣ የዛተ እንደሆነ ወይም
የፍርድ ቤቱን ሥራ በማናቸውም ሌላ መንገድ ያወከ እንደሆነ የችሎት መድፈር ወንጀል ይፈፅማል።
ይህ ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝ ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ሳያደርግ ወዲያውኑ በጥፋተኛው ላይ ቅጣት ሊወስን የሚችል ሲሆን ቅጣቱም ከአንድ አመት የማይበልጥ ቀላል እሰራት ወይም ከሶስት ሺ ብር የማይበልጥ መቀጮ ይሆናል፡፡
ወንጀሉ የተፈፀመው ከችሎት ውጭ ሆኖ ዳኛው ሥራውን እያከናወነ ባለበት ጊዜ ከሆነ ቅጣቱ ከስድስት ወር የማይበልጥ ቀላል አስራት ወይም ከአንድ ሺ ብር የማይበልጥ መቀጮ ይሆናል፡፡ ከችሎት ውጭ ስንል መደበኛ ችሎት ውጪ በዳኞች ፅህፈት ቤቶች ላይ የሚሰሩ የዳኝነት ወይም የምርመራ ስራን ሊያካትት ይችላል፡፡
ወንጀሉ የተፈፀመው በችሎት ወይም በማናቸውም ቦታ የዳኝነት ሥርአት በሚካሄድበት ጊዜ ሆኖ በሀይል ወይም በማስገደድ እንደሆነ አግባብ ያለው የወንጀል ህግ አንቀፅ 441 በተደራቢነት ይፈፀማል፡፡ ይህም በዛቻ፣ በማስገደድ ወይም በሀይል ድርጊት የፍርድ ቤቱ ባለሞያዎች ሥራቸውን እንዳያከናውን ወይም ማድረግ የሌለባቸውን እንዲያደርጉ ማስገደድን ወይም ሰራተኛውን መደብደብ የሚያካትት ሲሆን እንደ ጥፋቱ ክብደት፣ እንደተበዳዩ የሥራ ደረጃ እና ወንጀለኛው ወንጀሉን ለመፈፀም እንደተጠቀመው መሳሪያ ሁኔታ ቅጣቱ ከ5 አመት የማይበልት ፅኑ እስራት ይሆናል፡፡
በሌላ በኩል የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 480 የችሎት ሥነ ሥርአትን ለማስከበር ስለሚወሰዱ እርምጃዎች የደነገገ ሲሆን በዚህም መሰረት የማንኛውም ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ የዳኝነት ሥራ አካሄድ ሥነ ሥርአት ለማስከበር ማንኛውንም አስፈላጊ መስሎ የታየውን እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል አመልክቷል፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ለችሎቱ ክብር ወይም ለዳኝነት ሥነ ሥርአት መልካም አመራር ተቃራኒ የሆነ ጠባይ በሚያሳይ ማንኛውም ተከራካሪ፣ ጠበቃ፣ ወይም በችሎቱ ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም ሰው ተቃራኒ ተግባሩን በሰራበት ጊዜ በያዘው መዝገብ ላይ መቀጮ ሊወስን ይችላል፡፡ አስፈላጊ የሆነው ማናቸውም እርምጃ ሲባል አጥፊውን መገሰፅ፣ ማረም፣ መምከር፣ ማስጠንቀቅ ወይም ከችሎት እንዲወጣ ማዘዝ ሊያጠቃልል ይችላል፡፡ በተጨማሪም በወንጀል ህጉ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የወንጀል ተግባር በተፈፀመ ጊዜ ጥፋቱ በተደረገበት ጊዜ በያዘው ፍትሐብሔር መዝገብ ላይ ወዲያውኑ የእስራት ቅጣት ሊወስን ይችላል፡፡
በአጠቃላይ ችሎት መድፈር በህጉ የሚታይበት ሁኔታ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ማህበረሰቡም የችሎት መድፈርን ምንነት በአግባቡ ተረድቶ ሊያስቀጡ ከሚችሉ አላስፈላጊ ተግባራት እስከታቀበ ድረስ የለምንም ፍርሀት ችሎት መታደም የሚችል መሆኑን ሊያውቅ ይገባል፡፡

በፍትህ ሚኒስቴር በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የሚታዩ የሙስና ወንጀሎች
ዳይሬክቶሬት ጄነራሉ የሙስና ወንጀሎችን በተመለከተ የወንጀል ምርመራ እና ክርክር ሂደትን በበላይነት የሚመራ ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የወንጀል አይነቶች የሙስና ወንጀል ስር የሚወድቁ እና በስራ ክፍሉ የሚመረመሩ እና ክስ የሚመሰረትባቸው የሙስና ወንጀል አይነቶች ናቸው፡፡
o በስልጣን አለአግባብ መገልገል፣
o የመንግስት ወይም ህዝባዊ ድርጅቶች ስራን በማይመች አኳሃን መምራት፣
o አደራ የተሰጠው እቃ ያለ አግባብ ማዘዝ፣
o በስራ ተግባር የሚፈፀሙ የመውሰድና የመሰወር ወንጀል፣
o በስልጣን ወይም በሃላፊነት መነገድ፣
o ያለ አግባብ ጉዳይን ማጓተት፣
o ያለ አግባብ ፈቃድ መስጠት ወይም ማፅደቅ፣
o የስራ ሚስጥርን መግለፅ፣
o በሌለው ስልጣን መጠቀም፣
o በግል ተሰሚነት መነገድ፣
o ጉቦ መቀበል ወይም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መስጠት ወይም መቀበል፣
o አስታራቂ ሽማግሌዎች የሚፈፅሙት ጉቦ መቀበል ወንጀል፣
o በሙስና ወንጀሎች የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ስለመርዳት፣
o በህገ ወጥ መንገድ ዋጋ ያለውን ነገር ያለ ክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ ማግኘት፣ ዋጋ ያለው ነገር ያለ በቂ ክፍያ መስጠት፣
o ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብና ንብረት ይዞ መገኘት፣
o ገንዘብ ማቀባበል፣
o በምርጫ ላይ የሚስጥ መደለያ፣
o በከባድ አታላይነት የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች፣
o በከባድ እምነት ማጉደል የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች፣
o የመንግስታዊ ወይም የህዝባዊ ድርጅት ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት ወደ ሀሰት መለወጥ፣ ማጥፋት ወይም ጉዳት ማድረስ፣ ወይም በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ሙስና ወንጀሎች፣
o ከሙስና ወንጀሎች ጋር በተያያዘ ጠቋሚ፣ ምስክር የሆኑ ሰዎች ላይ የሚደርስ ጥቃትን አስመልክቶ የሚፈጸም ወንጀል
o የሙስና ወንጀሎችን ምርመራ እና ክስ ከማደናቀፍ ጋር ተያይዞ በአዋጁ ቁጥር 433/97 (አዋጅ ቁጥር 883/07 እንደተሻሻለ) የተደነገጉ ወንጀሎች፤ እና
o በልዩ ህጎች የሙስና ወንጀል ተብለው የተደነገጉ ጉዳዮች

East Africa Bottling Share Company - Coca Cola ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
Position: Public Affair & Communications Manager
📚ትምህርት ዓይነት እና ደረጃ:
First Degree in Journalism or English Language and Literature or Public Relations or Law or other Business or Social Science field of studies.
🇪🇹የስራ ቦታ ፡ Addis Ababa
🧭የምዝገባ ጊዜ ፡ እስከ መስከረም 16, 2016
ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ👇
https://tikusjobs.com/job/public-affair-communications-manager/

223425.pdf
942.9 KB
ሕብር ስኳር አክሲዮን ማህበር መፍረስን ተከትሎ በውጤቱ ላይ የተሰጠ ውሳኔ
***
የሠ. መ.ቁ.223425
ህዲር 30/2015 ዓ.ም
1- አንድ የአክሲዮን ኩባንያ የአመሰራረት ሂደት ሊከተለው የሚገባውን ሂደት እና መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች በቀድሞ የንግዴ ህግ ከቁጥር 312 እስከ 324፤ እንዱሁም በአዲሱ የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 ከአንቀፅ 254 እስከ 265 በዝርዝር ተመልክቷል፡፡ በእነዚህ የአመሰራረት ሂደቶች ውስጥ የንግድ ማህበሩ በንግድ መዝገብ ውስጥ መመዝገብ የአክሲዮን ማህበሩ አመሰራረት ሂደት የመጨረሻ ደረጃ ስለመሆኑ ከቀድሞ የንግድ ህግ ቁጥር 323 እና ከአዲሱ የንግድ ህግ አንቀፅ 265 ድንጋጌዎች ይዘት መረዳት ይቻላል፡፡
ተጠሪ አክሲዮን ኩባኒያ በዚህ መልኩ በንግድ መዝገብ ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነት አግኝቷል።
2-ለአክሲዮን ኩባኒያ ምስረታ ገንዘብ ያዋጡ ባለገንዘቦች ለአክሲዮን ግዢ እና ለአገልግሎት ክፍያ የከፈሉት ገንዘብ ክፍያውን ከፈጸሙበት ቀን አንስቶ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለዽ ጋር ተከፍሎኝ ከማህበር አባልነት ልሰናበት የሚል ጥያቄ የማንሳት መብት የሚኖራቸው ከባለአክሲዮኖች የተሰበሰበው ገንዘብ በምስረታ ላይ ባለው ኩባኒያ ስም በተከፈተ ዝግ የባንክ ሂሳብ ውስጥ ከተቀመጠበት ጀምሮ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ኩባንያው ሳይመሰረት በቀረበት ጊዜ ስለመሆኑ የቀድሞው የንግድ ህግ ቁጥር 312(3) ድንጋጌ ያስገነዝባል፡፡ ከዚህ ባለፈ ህጋዊ ስርዓቱን ጠብቆ ከተቋቋመ የአክሲዮን ኩባንያ በዚህ መልኩ ክፍያ የሚጠየቅበት ህጋዊ መሰረት የለም፡፡
3-ኩባኒያው እንዲፈርስ ዳኝነት ጠይቀው በተጠየቀው ዳኝነት መሰረት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ መልሰው ይህንኑ የሚቃወሙበት የሙግት ሥነ ሥርዓት የለም፡፡
Credit Daniel Fikadi / ዳንኤል ፍቃዱ ( ጠበቃ)/

በብድር ውል ላይ ያለው ፊርማ በመካዱ በፎረንሲክ እንዲመረመር ትዕዛዝ ተሰጥቶ ፊርማውን የሚመረምረው አካል በሰነዱ ላይ ያለው ፊርማ የማን እንደሆነ ማረጋገጥ እንደማይቻል ምላሽ ከሰጠ የብድር ውል መኖሩን በብድር ሰነዱ ላይ ባሉት የምስክሮች ቃል ማስረዳት አይቻልም።
ከብር 500 በላይ የሆነ የብድር ገንዘብን ለማስረዳት ሊቀርብ ስለሚገባው የማስረጃ አይነት በፍ/ሕ/ቁጥር 2472/1 ላይ የተዘረዘረ ሲሆን በዚህ ድንጋጌ የብድር ግንኙነት መኖሩን ማስረዳት የሚቻለው በጽሁፍ፤ ወይም በፍርድ ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ወይም በመሃላ ቃል ብቻ ነው፡፡ የብርድ ውል መኖሩን ለማስረዳት ከእነዚህ ሌላ የማስረጃ አይነት ማቅረብ እንደማይቻል ተመልክቷል፡፡e
የብድር ውል በማስረጃነት ቀርቦ ፊርማው ስለተካደ በሳይንሳዊ ዘዴ ፊርማው እንዲመረመር ተድረጎ በሰነዱ ላይ ያለው ፊርማ ፊርማውን የካደው ሰው ፊርማ መሆኑን ማረጋገጥ ካልተቻለ የጽሁፍ የብድር ውል ማስረጃ ሊሆን አይችልም፡፡
በጽሁፍ የተደረገ የብድር ውል ላይ ያለ ፊርማ በተካደ ጊዜ የብድር ውል በጽሁፍ መደረጉን በምስክሮች ማረጋገጥ የሚቻል ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁጥር 2472 አያመለክትም፡፡ ይልቁንም በፍ/ሕ/ቁጥር 2472/2 ለብድር ውል ሌላ ማናቸውንም ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም ማለቱ የብድር ውል በተካደ ጊዜ በብድር ውሉ ላይ የተቆጠሩ ምስክሮችም ቢሆን የብድር ውል ስለመደረጉ ማስረጃ ሊሆኑ እንደማይችሉ አመላካች ነው፡፡
ሰ/መ/ቁጥር 230249 መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ/ም