አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
FDRE Ministry of Justice/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር
ማስታወቂያ
ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የጥብቅና ፈቃድ መግቢያ ፈተና ለመቀመጥ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟላ ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጲያዊት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. በሕግ ዕውቅና ካገኘ የትምህርት ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ/ች/የኢትዮጵያዊያን መሰረታዊ ሕጎች የሚያውቅና በሙያው ቢያንስ ሶስት ዓመት ልምድ ያለው /ላት/ ወይም በሕግ ዲፕሎማ የተመረቀ/ች/ እና በሙያው አምስት ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ላት/፤
2. ከሚሰራበት መስሪያ ቤት የመልካም ሥነ-ምግባር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል /የምትችል/፤
3. በወንጀል ተከሶ/ሳ ያልተቀጣ/ች፤
4. የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃ እንዲሁም ማንነቱን/ቷን የሚገልፅ መታወቂያ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ የሚያቀርብ/የምታቀርብ፤
5. ከግል መስሪያ ቤት የሚቀርብ የስራ ልምድ የመንግስት ግብር የተከፈለበት መሆን አለበት፤
6. ማንኛውም በሌላ ቋንቋ የተሰጠ የሥራ ልምድና የስነ-ምግባር ማስረጃ በአማርኛ ተተርጉሞ መቅረብ አለበት
7. የመመዝገቢያ 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ መክፈል የሚችል/የምትችል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
 የመመዝገቢያ ቀን ከመስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል።
 የመመዝገቢያ ቦታ ባምቢስ አካባቢ በሚገኘው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስትር የጥብቅና ፈቃድና ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ ነው፡፡
 ኮድ መውሰጃ ቀን ከመስከረም 24 – 25/2016 ዓ.ም ነው፡፡
 ፈተና የሚሰጥበት ቀን መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ይሆናል፡፡
 የፈተናው ቦታ ኮድ በሚሰጥበት ቀን ይገለፃል፡፡ #Ale_Hig #Lawsocieties #Share #ሼር @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ደረሰኞች መያዝ የሚገባቸው መረጃዎች

ደረሰኝ በእቃ ወይም በአገልግሎት ግብይት ላይ ተመስርቶ ከሻጩ አቅራቢው/ለገዥው የሚሰጥ እና ግብይት ስለመፈጸሙ፣ ገንዘብ ስለመሰብሰቡ፣ ዋጋው ስለመከፈሉ ወይም ለወደፊቱ ለመክፈል ውል መግባቱን የሚያሳይ ሰነድ ነው፡፡

በህጉ መሰረት የሽያጭ ደረሰኝ ቢያንስ የሚከተሉትን መሰረታዊ መረጃዎች ሊይዝ ይገባል፡-

1. የአቅራቢው ሙሉ ስም፣ አድራሻ እና የተመዘገበ የንግድ ስም የታተመበት፤

2. የአቅራቢው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቁጥር እና ለታክስ የተመዘገበበት ቀን የታተመበት፤

3. የደረሰኙ ተከታታይ ቁጥር የታተመበት፤

4. የገዥው ሙሉ ስም፣ አድራሻ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤

5. የተገዛው፣ የተሸጠው ዕቃ ወይም የተሰጠው አገልግሎት አይነት እና መጠን፤

6. ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ላይ የሚፈለገውን የተጨማሪ እሴት ታክስ/የተርን ኦቨር ታክስ መጠን፤

7. በፊደል እና በቁጥር የተጻፈ ጠቅላላ የሽያጭ ወይም ግብይት ዋጋ፤

8. ደረሰኙ የተሰጠበት ቀን፤

9. ደረሰኙን ያዘጋጀው ወይም ገንዘቡን የተቀበለው ሰራተኛ ስም እና ፊርማ፤

10. የደረሰኝ አታሚው ድርጅት ስም፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የታተመበት ቀን እና የአታሚው የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ቁጥር፤

11. ደረሰኙ እንዲታተም በገቢዎች ሚኒስቴር የተፈቀደበትን ደብዳቤ ቁጥር እና ቀን ናቸው፡፡


ምንጭ፥ በኢትዮጵያ የገቢዎች ሚኒስቴር ገጽ 🙏🏾
#Ale_Hig #Lawsocieties #Share #ሼር @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
በወንጀል ስነስርአት ይግባኝ የማይባልባቸው ጉዳዮችን ዘርዝር
የቀዳሚ ምርመራ ክስ ግለጹ
በአጭር ሥነ-ሥርዓት እና በተፋጠነ ሥነ-ሥርአት የሚቀርቡ ጉዳዮችን ዘርዝር
የውል መሰረዝ እና መፍረስ አንድነት እና ልዩነት?
ይቅርታ እና ምህረት ልዩነቱ ምንድነው?
Proclmation1072.2018 (1).pdf
809.1 KB
የኤሌትሮኒክ ፊርማ ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 1072/2010
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 358 እና 418 ተፈፃሚ የሚሆኑበት አግባብ ከሰበር ውሳኔዎች ጋር በማገናዘብ
================
የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 8 በመ/ቁ. 32143 እና ቅጽ 7 በመ/ቁ. 25031 በሰጠው ውሳኔ የሁለቱንም ልዪነት ማብራሪያ በመስጠት ትርጉም ሰጥቷል። ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ንብረት ላይ ፍርድ አርፎበታል ከተባለ ይሄው ፍርድ ሊሰረዝልኝ ይገባል የሚለው ወገን አቤቱታ ማቅረብ ያለበት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 358 መሠረት እንጂ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ በ418 መሠረት ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ሁለቱ የሥነ ሥርዓት ድንጋጌዎች የተለያየ ዓላማና ውጤት ያላቸው ስለሆነ ነው፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሠረት አቤቱታ አቅራቢ በዋናው ፍርድ ላይ ምንም ዓይነት ክርክር የሌለውና አፈጻጸም እንዲቀጥል ትዕዛዝ በተሰጠበት ንብረት ላይ መብት አለኝ የሚል ወገን መሆን አለበት፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.358 መሠረት መብቱ የተነካው ወገን ፍርዱን ለሰጠው ፍ/ቤት መቃወሚያ ማቅረብ ይችሏል፡፡

በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 358 መሠረት አቤቱታ /መቃወሚያ/ የሚቀርበው ቀደም ሲል የተሰጠን ውሣኔ ለመቃወም ነው፡፡ መቃወሚያውን ማቅረብ የሚችሉትም ቀደም ሲል በተደረገው ክርክር ተካፋይ ያልነበሩት ወገኖች ናቸው፡፡ ቀደም ሲል በተደረገው የአፈፃፀም ክርክር ተካፋይ የነበረ እና የተወሰነበት ሰው በዚህ ሥነሥርዓት ክርክር ማንሳት የሚችልበት የህግ አግባብ የለም፡፡ ውሳኔ ከተወሰነ በኋላ ተቃዋሚ ሆኖ የሚቀርብበት አግባብ የለም፡፡ ከዚህም በሌላ መንገድ በአፈፃፀም በተያዘ ወይም በተከበረ ንብረት ላይ መብት አለን ባዮች አቤቱታ ማቅረብ የሚችሉት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 418 መሠረት ሆኖ ማቅረብ ያለባቸውም ሣይዘገዩ እንደሆነ በዚሁ ቁ. 418/1/ ተመልክቶአል፡፡ አቤቱታው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 418 መሠረት ዘግይቶ የክርክሩን ውጤት በመጠበቅ ሳይሆን መቅረብ የሚገበውም ንብረቱ መከበሩን እንዳወቀ ነው።
Via Tsegaye Demeke _Lawyer
#ሼር @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የቤተሰብ ሕግ ሐተታ ዘምክንያት.pdf
840.6 KB
የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ማብራሪያ
የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ሕግ.pdf
552.9 KB
የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ሕግ፡- ለዳኞችና ዓቃብያነ ሕግ ሥልጠና የተዘጋጀ
የፍትሐብሔር_ጉዳዮችን_የሚመለከቱ_ፎርሞች.pdf
4.6 MB
የፍትሐብሔር ጉዳዮችን የሚመለከቱ የክስ፣ የመልስ፣ የይግባኝ፣ የአፈጻጸም፣ የሰበር፣ የውሳኔ እና የትዕዛዝ ፎርሞች፡፡