አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የሞባይል ስልኩ ግድብ ውስጥ የገባበት ባለስልጣን 2 ሚሊየን ሊትር ግድብ ውሃ እንዲለቀቀ አደረገ

ባለስልጣኑ ስልጣንን አለአግባብ በመጠቀም በሚል ከስራ ታግዷል። ለባለስልጣኑ ስልክ ሲባል ከግድብ የፈሰሰው  ውሃ ከ6 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መስኖ የማልማት አቅም ነበረው።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/official-drains-dam-retrieve-phone
ዳኝነትን የሚመለከቱ አባባሎች፣ ተረትና ምሳሌዎች፣
1) ዳኛ ቢያጋድል በዳኛ አህያ ቢያጋድል በመጫኛ፣
2) ዳኛ ለዳኛ ያወርሳል ጉም ተራራ ያለብሳል፣
3)ዳኛ ምን ያደላ ከተረታው ሊበላ፣
4)ዳኛ ሲመረምር ከራስ ይዞ እስከ እግር፣
5)ዳኛ ሲቆጣ ማር ይዞ ከደጁ፣
6)ዳኛ ሲገኝ ተናገር ውሀ ሲጠራ ተሻገር፣
7)ዳኛ ስበር በእጅ ክበር፣
8)ዳኛ ቢንቁ የተያዘ እህል ይወቁ፣
9)ዳኛ አውጥቼ ዘንግ አቅንቼ፣
10)ዳኛ አይነቀፍ እሳት አይታቀፍ፣
11) ዳኛ ካዳላ ጭነት ቀላል፣
12) ዳኛ የወል ምሰሶ የማሃል፣
13) ዳኛ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት፣
14) ዳኛ የፈረደው ስለት የቀደደው፣
15) ዳኛ ያደላበት እሳት የበላበት፣
16)ዳኛ ያፈሰሱለት ፈረስ የከሰከሱለት፣
17) ዳኛ ይመረምራል ጣዝማ ይሰረስራል፣
18) ዳኛ ፍርድ አይከላ እህል ጎታ ይሞላ፣
19) ዳኛና በሬ ሀብታም ናቸው፣
20) ዳኛን ቢንቁ የተያዘ እህልን ይወቁ፣
21)ዳኞች ከመረመሩ ይናገራል ምድሩ ይገናል ነገሩ፣
ሌሎች ካሉ ጨምሩ
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የዋስትና መብት
የዋስትና መብት ማለት በወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ የሚያዝ ሰዉ ከእስር የሚፈታበት ስነ-ስርዓት ነዉ። ማንም ሰዉ ከህጉ ዉጪ መታሰር የለበትም የሚለዉን የህገ መንግስቱ ድንጋጌ የሚረዳ መብት ነዉ። ዋስትናም ፍርድ ቤት ከመቅረብ በፊት ወይም በኋላ ለሰጥ ይችላል። በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ አንቀጽ 28 መሰረት ጽኑ እስራት የማያስቀጣ ወንጀል፣ወንጀል ስለመፈጸሙ ጥርጣሬ ካለ እና ተጠርጣሪዉ ወንጀሉን እንደፈጸመ አጥራጣሪ ከሆነ ፍርድ ቤት መቅረብ ሳያስፈልግ ፖሊስ በዋስትና መልቀቅ እንደሚችል ይደነግጋለ። በዚሁ ህግ አንቀጽ 63 ስር ደግሞ ፍርድ ቤት ሞት ቅጣት ወይም  15  አመት እና ከዛ በላይ ጽኑ እስራት የማያስቅጣ ወንጀል ከሆነ እና ተጎጂዉ ካልሞተ ዋስትና አስፈርሞ መልቀቅ እንደሚችል ያስቀምልጣ።
ዋስትና የሚከለከልባቸዉ ሁኔታዎች
በወ/መ/ስ/ስ/ህግ መሰረት ተጠርጣሪዉ
-ግዴታዉን እንደማይወጣ ከታወቀ
- ቢለቀቅ ሌላ ወንጀል ይፈጽማል ተብሎ ሲገመት
-ማስረጃ ያጣፋል ወይም ያሸሻል ተብሎ ከታመነ
- በዚህ ህግ አንቀጽ 63 እና 28 ላይ የተገለጸዉ በተቃራኒ ተሙዋለቶ ከተገኘ
ከልዩ ህጎች ለምሳሌ የጸረ-ሙስና ልዩ የስነ-ስርዓትና ማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 ከማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 882/2007 መሰረት
-ከ10 አመት በላይ የሚያስቀጣ ወንጀል ከሆነ
-ከ4 አመት በላይ እና ክ10 አመት በታች የሚያስቀጡ ወንጀሎች በተደራራቢነት ተፈጽመዉ ድምራቸዉ ክ10 አመት በላይ ካስቀጣ ዋስትና አይፈቀድም።
ከዚህም በተጨማሪ በሌሎች ልዩ ህጎች በተቀመጡ ምክንያቶች ዋስትና ሊከለከል ይችላል።
ስለ ዋስትና ህግ የሚደነግጉ ህጎች
1. ህገ-መንግስት (አንቀጽ 19)
2. የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ (አንቀጽ 28፣ ከ 63-79)
3. የጸረ-ሙስና ልዩ የስነ-ስርዓትና ማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 ከማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 882/2007
4. የሰበር ዉሳኔዎች ለምሳሌ ያህል ቅጽ 19 መ/ቁጥር 112725
እና የመሳሰሉት ናቸዉ።
የዋስትና መብት በምን ሊቁዋረጥ ይችላል?
1. ክስ ሲቁዋረጥ
2. በመደበኛ ክርክር ዋስትና ሲያዝ የጊዜ ቀጠሮ
3. ከወንጀል ነጻ መባል
4. ጥፋተኝንት ዉሳኔ ተሰጥቶ ተከሳሹ ቅጣቱን እየፈጸመ ፍ/ቤቱ ዋስትና ይመለስ ሲል
5. የዋስትና ይዉረድልኝ ተብሎ ዋሱ ተከሳሹን በችሎት ሲያቀርብ
6. ዋሱ ሲሞት
7. የዋስትና ግዴታ ሳይፈጸም ሲቀር
8. በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 74 መሰረት አዲስ ማስረጃ /ጉዳይ/ሲገኝ እና የመሳሰሉት ናቸዉ።
የዋስትና መያዣ መጠን በምን ይወሰናል?
በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 69 መሰረት
1. የወንጀሉ ክብደት
2. ተጠርጣሪዉ መለቀቁ ለህዝብ አስጊ ከሆነ
3. ተጠርጣሪዉ በተፈለገ ጊዜ የማይቀርብ መሆኑ
4. የተከሳሹ እና የዋሶቹ ሀብት ከግምት ይገባሉ።
የዋሶች ግዴታ
በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 70፦ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ተከሳሹ ፍ/ቤት እንዲቀርብ ማድረግ።
ለዋስትና መያዣነት ምን ሊጠየቅ ይችላል?
በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 69 ስር የተጠቀሰዉ ከግምት ገብቶ
1.ጥሬ ብር
2. የማይንቀሳቀሱ ወይም ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች
3. የስራ ዋስ።
የአካሌ ነጻ ይዉጣልኝ ክስ የት ይቀርባል?
ፖሊስ ማንኛዉንም ተጠርጣሪ 48 ሰአት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ በአቅራቢያዉ ወዳለ ፍ/ቤት ማቅረብ እንዳለበት ህጉ ያስቀምጣል። ይህንም ሳያረግ ከቀረ ተጠርጣሪዉ ሆነ ሌላ ሰዉ ወክሎት አካሌ ነጻ ይዉጣልኝ ማቅረብ እንደሚችሉ የፍትሐብሔር ስነ-ስርዓት ህግ አንቀጽ 177 ጀምሮ ያለዉ ይደነግጋል። ይህን መሰሉንም ክስ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መቅረብ እንዳለበት የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 በአንቀጽ 11(3) ላይ ያስቀምጣል።
የቦሌ/ክ/ከ/የህ/ስ/ህ/ማ/ዳይሬክቶሬት
ዐ/ህግ ዉብአለም መስፍን
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
አፅድቀውታል ፤ ፈርመውበታል !

ዩጋንዳ የ " ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ን ወንጀል የሚያደርገውን ሕግ አፀደቀች።

ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ያፀደቁት / ፊርማቸውን ያኖሩበት የረቂቅ አዋጅ ሕግ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን ሁሉ በዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ነው።

በአንዳንድ ሁኔታዎች ዳግሞ #የሞት ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ።

ረቂቅ ሕጉ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአገሪቱ ምክር ቤት አባላት ተቀባይንት ያገኘ ሲሆን፣ ማሻሻያ እንዲደረግበት ለፓርላማው ተመልሶ ቀርቦ ነበር።

ቀደም ሲል ቀርቦ በነበረው ረቂቅ ሕግ ላይ ማንኛውም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም ከዚሁ ጋር በተያያዘው ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ የሚያደርግ ነበር።

ሆኖም ግም ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ይህ ሰዎች እንዲታሰሩ እና በአካላዊ ገጽታቸው ብቻ እንዲከሰሱ ያደርጋል ሲሉ ሳይቀበሉት ቀርተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ረቂቅ ሕጉ እንዲሻሻል ወደ ፓርላማ መልሰውት ነበር።

በዚህ መሠረት ተሻሽሎ አሁን ላይ የቀረበው ረቂቅ ሕግ፣ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ወንጀልነት ወንድ ከወንድ ጋር በሚያደርገው ወሲባዊ ድርጊቶች ላይ የተወሰነ ሆኗል።

ይህንን ሕግ ተላልፈው የተገኙም እስከ እድሜ ልክ እስራት ይጠብቃቸዋል።

ለከባድ ወንጀሎች ማለትም ወሲባዊ ጥቃቱ #በሕጻናት_ላይ ፣ በአካል ጉዳተኛ እንዲሁም ተጋላጭ በሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ በሚፈፀምበት ጊዜ አሊያም የጥቃት ሰለባዎቹ ለዕድሜ ልክ ህመም የሚዳረጉ ከሆነ በድርጊቱ ፈፃሚ ላይ #የሞት ቅጣትን ይደነግጋል።

ማኅበረሰቡ #በሕጻናት ወይም በሌሎች ተጋላጭ በሆኑ የሕብረተሰቡ አባላት ላይ ማንኛውንም ዓይነት የተመሳሳይ ጾታ ጥቃት በሚያዩ አልያም በሚሰሙበት ጊዜ ለባለሥልጣናት ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ የተመሳሳይ ጾታ ቀድሞም ሕገ ወጥ ተደርጎ ነው የቆየው ፤ ይህ ሕግ ከሕገ ወጥነቱ አልፎ ነገሩን ወንጀልና በተራዘመ እስር የሚያስቀጣ ያደርገዋል።

#ምዕራባውያን ሀገራትና #ተቋማት በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ጉዳይ በዩጋንዳ ፓርላማ የተላለፈውን ውሳኔ ሲቃወሙና ፕሬዜዳንቱ #እንዳይፈርሙ ሲያሳስቡ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
በተሽከርካሪ ሠው በቸልተኝነት ግድያ የተጠረጠረ ሠው የሚከሰሰው በወንጀል ህግ አንቀፅ 543(2) ወይም አንቀፅ543(3) የሚለውን ለመለየት በእግረኛ መንገድ ዜብራ ምልክት መኖር አለመኖሩ አንድ መለያ ነጥብ ነው።ስለሆም ዜብራ ከሌለ በ አንቀፅ 543(2) ድንጋጌ ላይ ያርፋል።

ሠበር ውሳኔ ቁጥር 230508 ነሀሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም
መልስ የማቅረብ መብት መታለፍ ውጤት ሰ/መ/ቁ. 188331

የመከላከያ መልስ የማቅረብ መብቱ የታለፈበት ተከራካሪ ክሱ በሚሰማበት ሆነ በሙግት ጊዜ ማስረጃ የማቅረብ መብቱን ያጣል።
#Click Ethiopian Laws
Africa is leading, Ethiopia is on top

The world’s 10 fastest growing airline brands for 2023:

1. Ethiopian Airlines 🇪🇹
2. Vueling (Spain) 🇪🇸
3. United Airlines
4. China Southern 🇨🇳
5. American Airlines 🇺🇸
6. Korean 🇰🇷
7. Turkish 🇹🇴
8. China Eastern 🇨🇳
9. Alaska 🇺🇸
10.Qatar 🇶🇦

Source: @BrandFinance

Follow National Belt
Federal Income Tax Explanatory Notes.docx
321.9 KB
የኢትዮጵያ የገቢ ግብር ማብራሪያ ፅሁፍ
Ethiopian Federal Income Tax Explanatory Notes
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer and Consultant)
የማስረጃ ህግና ህገ-መንግስቱ.pdf
15 MB