Proclamation_No_1074_2018_Driver’s_Qualification_Certification_License.pdf
628.6 KB
Share 'Proclamation-No.-1074-2018-Driver’s-Qualification-Certification-License-Proclamation.pdf'
ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ከእስር ተለቀው የገና በአልን ከቤተሰቦቻቸው ጋር አሳልፈዋል::
****......
ጠበቃና የሕግ አማካሪ የሆኑት ወንድሙ ኢብሳ እስር ከተፈፀመባቸው ጊዜ ጀምሮ ማህበሩ ተገቢውን ክትትል እያደረገ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።
ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ለኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር አመራር በስልክ እንደገለፁት በእስር ቆይታቸው ይህ ነው የተባለ የአያያዝ ችግር ያልገጠማቸውና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል::
ጠበቃው ችሎት በመድፈር በሚል ታህሳስ 11 ቀን 2015ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ በሚገኘው የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ጋር በተፈጠረ የቃላት ልውውጥ መነሻ ተደርጎ የአራት ወራት እስራት የተፈረደባቸው መሆኑ የሚታወስ ነው::
የይግባኝ ክርክሩም በተሟላ ሁኔታ ታህሳስ 26 ቀን 2015ዓ.ም በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የተደረገ ሲሆን ችሎቱም ከፍተኛው ፍ/ቤት ለችሎት መድፈር መነሻ አድርጌአቸዋለሁ ካላቸው "17 ነጥቦች" 16ቱን ውድቅ በማድረግ የ4 ወራት እስራት ቅጣቱን በመሻር ከ 18 ቀናት እስር በኃላ እንዲለቀቁ ውሳኔ ሰጥቷል::
ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ይህ የእስር ቅጣት ከተላለፈባቸው ቀን ጀምሮ "ከፍተኛ እገዛ" ላደረገላቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር እና ለማህበሩ መሪዎች እንዲሁም በሂደቱ ለተሳተፉ የህግ ባለሙያዎች ምስጋናቸውንም አቅርበዋል:: የጠበቆች ማህበሩ ጉዳዩን የሚከታተሉ እና በችሎት የሚሰየሙ ጠበቆችን ከመመደብ ጀምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግሮችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በቀጣይ ከጉዳዩና ተያያዥ ነጥቦች ዙሪያ የተሟላ ሪፖርት እና አቋሙን ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ይገልፃል::
ለኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
አዲስ አበባ

👍16❤4👎3
የዐቃብያነ_ሕግ_የትምህርትና_ስልጠና_ዋስትና_መመሪያ_ቁጥር_19_2015_ዓ_ም_ታህሳስ_5_2015_ዓ_ም.docx
93.7 KB
መመሪያ ቁጥር ---------------------/2015 ዓ.ምበአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ የተሻሻለው የዐቃብያነ-ሕግ የትምህርትና ስልጠና ዋስትና መመሪያበየደረጃው ባሉ የፍትሕ ቢሮ መዋቅሮች የሚሰሩ ዐቃብያነ-ሕግን የአጭርና የረጅም ጊዜ ትምህርትና ስልጠና ተጠቃሚ በማድረግ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅማቸውን ማጎልበት በማስፈለጉ፤በአጭርም ሆነ በረጅም ጊዜ የዐቃብያነ-ሕግ ትምህርትና ስልጠና አመላመል ዙሪያ እያጋጠሙ ያሉ የተለያዩ ክፍተቶችን የማስተካከሉ አስፈላጊነት ስለታመነበት፤ዐቃብያነ-ሕግ ወደ ትምህርትና ስልጠና ሲገቡ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንዲወዳደሩ ማድረግ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤ የድህረ-ምረቃ ትምህርት እድል ያገኙ ዐቃብያነ-ሕግ የመመረቂያ ማሟያ የምርምር ጽሁፍ ክፍያ ማሻሻያ እንዲደረግበት በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በተወሰነው መሰረት ተገቢውን ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ በተሻሻለው የዐቃብያነ-ሕግ መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር 52/1999 ዓ.ም አንቀጽ 106 ስር በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡
👍7
ኪራይ ውል ሰ/መ/ቁ. 97111 ሐምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም (ያልታተመ)
የኪራይ ውል ጊዜው ካበቃ በኋላ ተከራይ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ሆኖም በማስጠንቀቂያው ላይ አዲሱ የኪራይ መጠን ካልተገለጸ ተከራይ ቤቱን ሳይለቅ ለቆየበት ጊዜ ሊከፍል የሚገባው ክስ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ላለው በድሮው ተመን መሰረት ሲሆን ክስ ቀርቦ መጥሪያ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ደግሞ ሊከፍል የሚገባው በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2950 ንዑስ አንቀፅ 2 መሰረት፣ በአካባቢው ተመሳሳይ የንግድ ቤቶችን በምን ያህል ዋጋ እንደሚከራዩ በባለሙያዎችና ሽማግሌዎች ተጣርቶ ከቀረበ በኋላ በሚቀርበው ሪፖርት መሰረት ነው።
ፍ/ህ/ቁ 2950 /2/

በፍትሐብሔር ክርክር የፍርድ ቤት መጥሪያ ደርሶት በቀነ ቀጠሮ ተከራካሪ ወገኖች አለመቅረብ ህጋዊ አንድምታው ምን ይመስላል?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ፍርድ ቤት አንድ ጉዳይ ማየት እና ውሳኔ ለማስተላለፍ የተለያዩ ቀጠሮዎች እንደሚሰጥ የታወቀ ነው፡፡ የመጀመሪያ ተከሳሽ መከሰሱን አውቆ ለቀረበበት ክስ መከላከያ የሚሆኑ ማስረጃዎችን በፅሁፍ የሚያቀርብበት ነው፡፡ ፍርድ ቤት ተከሳሽ መጥሪያው በአግባቡ ደርሶት መልሱን ይዞ ከቀረበ ፍርድ ቤቱ በስነ-ስርዓት ህጉ 241 እና ተከታዮቹ መሰረት ክሱን ለመስማት ይቀጥራል፡፡
ክስ ለመስማት ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ቀጠሮ ሁለተኛ ቀጠሮ ነው፡፡ በስነ-ስርዓት ህጉ 241 እና ተከታዮቹ መሰረት ክስ መስማት ሁለት ሂደቶችን የያዘ ነው፤ የመጀመሪያው ስለ መጀመሪያ ክስ መስማት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ስለዋናው ክስ መስማት ነው፡፡ የመጀመሪያው ክስ መስማት ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለዋና ክስ መስማት የሚያዘጋጅበት ሂደት ሲሆን፤ ፍርድ ቤት የቀረበውን ክስን እና የተከሳሽን መልስ የሚያነብበት፣ የግራ ቀኙን አቋም የሚሰማበት፣ ተቀዳሚ መቃወሚያ ላይ ብይን የሚሰጥበትና ጭብጥ የሚመሠርትበት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ዋና ክስ መስማት ሂደት ማለትም የተከራካሪ ወገኖችን ክርክር መስማት፣ ምስክሮችን መስማት እና ማስረጃዎችን መርመር እንዲሁም የፍርድ ውሳኔ የሚሰጥበት ሂደት ነው፡፡.
ከሳሽ ወይም ተከሳሽ በየትኛው ቀነ ቀጠሮ መቅረባቸው እጅግ አስፈላጊ ነው? በሁሉም ቀጠሮዎች ወይስ መከላከያ ማስረጃ በሚቀርበበት ወይስ ክስ በሚሰማበት? ወደሚሉት ነጥቦች ስንገባ በእርግጥ ተከራካሪ ወገኖች እራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸው ፍርድ ቤት በሚወስነው በማንኛውም ቀጠሮ ቀን ፍርድ ቤት መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በቀጠሮዎች አለመገኘት የክስ መዝገብ መዘጋት፣ የመከለከያ ማስረጃ የማቀረብና የመከላከል መብትን ማጣት እና ሌሎች ተከራካሪ ወገኖች ቢቀርቡ ሊቀሩ የሚችሉ ትዕዛዞች እንዲሰጡ ይሆናል፡፡
በፍትሐብሔር የሥነ-ሥርዓት ሕጉ እንዲሁም ሰበር በተለያዩ መዝገቦች የሰጣቸውን ውሳኔዎች (ለምሳሌ በመዝገብ ቁጥር 14184፣ 15835፣ 36412፣ 36390፣ 58487 እና 95638) ስንመለከት ለመልስ በተቀጠረበት ቀጠሮ የከሳሽም ሆነ የተከሳሽ አለመገኘት መዝገብ እንዲዘጋ ወይም ክርክሩ ተከሳሽ በሌለበት እንዲታይም የማድረግ ውጤት አይኖረውም፡፡ ከሳሹ ወይም መጥሪያ እንዲያደርስ ታዞ የነበረው አካል ማድረሱን ወይም አለማድረሱን እንዲያረጋግጥ መጥሪያ በመላክ ወይም በሌላ ማንኛውም ዘዴ ማረጋገጥ አለበት፡፡ ተከሳሹ የደረሰው መሆኑን ካረጋገጠ የመጀመሪያ ክስ ለመስማት ቀጠሮ መስጠት የሚችል ሲሆን ተከሳሹ ካልደረሰው ደግሞ ድጋሚ መጥሪያ ለተከሳሹ መላክ ይኖርበታል፡፡
በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ህጉ አንቀጽ 69 መሰረት ፍርድ ቤቱ ቃል/ጉዳዩ ሊሰማ (hearing of suit) በወስነው ቀነ ቀጠሮ ከሳሽ (ክስ ያቀረበው) እና ተከሳሽ ራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸው መቅረብ አለባቸው (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 69) ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ ሊሰማ በተወሰነበት ቀነ ቀጠሮ አለመቅረብ የሚያስከትለው ውጤት እንደ ቀሪው ተከራካሪ ወገን ይወሰናል፡፡ ሁለቱም ተከራካሪዎች ሳይቀርቡ ሲቀር፣ ከሳሽ ሲቀር እና ተከሳሽ ሲቀር ተፈጻሚ የሚሆነው ሥርዓት የተለያየ ነው፡፡
ሁለቱም ወገኖች ሳይቀርቡ የቀሩ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ይዘጋዋል፡፡ ከሳሽ በቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ ተከሳሽ ቀርቦ የቀረበበትን ክስ የካደ ከሆነ መዝገቡን በመዝጋት ተከሳሽን ያሰናብተዋል (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 73)፤ ሆኖም ግን ከሳሽ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በቀዳሚ ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ የቀረበትን በቂ ምክንያት ገልጾ መዝገቡ እንዲታይ አቤቱታ ካቀረበ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሽ የከሳሽ አቤቱታ እንዲደርሰው በማድረግ መዝገቡን እንደገና ከፍቶ ነገሩ እንዲቀጥል ትዕዛዝ በመስጠት ጉዳዩ የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ ይወስናል፡፡
ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ ሊሰማ በተወሰነበት ቀነ ቀጠሮ ከሳሽ ቀርቦ ተከሳሽ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ የፍርድ ቤቱ ቀዳሚ ስራ መጥሪያው ለተከሳሹ መድረሱን ማረጋገጥ ነው (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 70)፡፡ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሽ የላከው መጥሪያ የደረሰው መሆኑን ካረጋገጠ በሌለበት ጉዳዩን መስማት ይቀጥላል፡፡ መጥሪያው ለተከሳሽ በአግባቡ ያልደሰረው መሆኑን ካረጋገጠ ወይም አጠራጣሪ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ሁለተኛ መጥሪያ እንዲላክ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ተከሳሽ መጥሪያው የደረሰው መሆኑ ቢረጋገጥ እንኳን ለተከሳሹ የተሰጠበት ቀን ለክሱ መልስ ለማዘጋጀት በቂ ሆኖ በማይገመት አጭር ጊዜ መሆኑን ፍርድ ቤቱ የተረዳው ከሆነ ፍርድ ቤቱ የክርክሩን መሰማት ለሌላ ቀነ ቀጠሮ ያስተላልፈዋል፡፡ አንድ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ተከሳሾች የተላከው መጥሪያ ለአንዱ ወይም ለአንዳንዶች ሳይደርስ የቀረው በከሳሽ ቸልተኘነት ወይም ጉደለት ከሆነ ፍርድ ቤቱ ከሳሽ መጥሪያ ባልደረሰው ወይም ባልደረሳቸው ተከሳሾች ላይ የቀረበውን ክስ ሊዘጋ ወይም ቀነ ቀጠሮ ሊቀይር ይችላል፡፡
ክርክሩ በሌለበት እንዲቀጥል የተወሰነበት ተከሳሽ በቀጣይ ቀነ ቀጠሮ ቀርቦ በቂ በሆነ ምክንያት በመጀመሪው ቀነ ቀጠሮ ያለመቅረቡን ካስረዳ መከላከያውን አቅርቦ የመከራከር መብት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 72 ይደነግጋል፡፡ እንዲሁም ክርክሩ ሊሰማ በተቀጠረበት ቀን ቀርቦ መልስ ሳይሰጥ ወይም መከራከሪያውን ሳያሰማ በሌለበት ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ መሰጠቱን ካወቀ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተከሳሽ መጥሪያው በሚገባ ያልደረሰው መሆኑን ወይም በቂ ምክንያት በማቅረብ ትዕዛዙ ወይም ውሳኔው እንዲነሳለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 78 መሰረት መጠየቅ ይችላል፡፡ በዚሁ ድንጋጌ መሰረትም ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ያቀረበውን አቤቱታ አግባብ መሆኑን ከተረዳ ለከሳሽ አቤቱታው እንዲደርሰው በማድረግ ትዕዛዙን ወይም ውሳኔውን በማንሳት ክርክሩን እንደገና ስምቶ ይወስናል፡፡
ሆኖም በቂ ምክንያት ምንድን ነው? የሚለው ነጥብ አከራካሪ ሊሆን ይችላል፡፡ የቀረበው ምክንያት በቂ መሆን አለመሆኑ እንደ ጉዳዩ ዓይነት የሚታይ በመሆኑ አንድ ዓይነት ትርጉም መስጠት አይቻልም፡፡ ነገር ግን የተከራካሪ ወገኖች በእኩል የመዳኘት መብት እንዲሁም ተከሳሽ ለቀረበበት ክስ የበኩሉን መልስ የመስጠት መብቱ፤ የመሰማት መሠረታዊ መብት (The right to be heard) ይበልጥ ሊያስከብር በሚችል ሁኔታ መተርጎም አለበት፡፡ እንዲሁም የስነ ስርዓት ህጉ ዓላማን ፍትሐዊ በሆነ ስርዓት በአጭር ጊዜ፣ በአነስተኛ ውጪ እና ድግግሞሽን ባስቀረ ሁኔታ የተከራካሪ ወገኖችን ጉዳይ መቋጨትን በሚያሳካ መልኩ መተርጓም አለበት፡፡
ሳሙኤል ግርማ
ሕግ ባለሙያ እና ጠበቃ
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

👍8
ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረ #ሰራተኛ ሰ/መ/ቁጥር 212420
አሰሪው ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረን ሠራተኛ ለስራው ተስማሚ አለመሆኑን ሳይመዝን ካሰናበተ ስንብቱ #ህገ- ወጥ ነው።
ስንብቱ ህገ-ወጥ በመሆኑ ካሳ የሚከፈለው ሲሆን የስንብት እና የማስጠንቀቂያ ክፍያዎች ግን አገልግልትን ታሳቢ ተደርገው የሚሰሉ በመሆኑ አይከፈሉትም።
የካሳው መጠን ሰራተኛው የሙከራ ጊዜውን (60 ቀናት) ቢጨርስ ሊያገኝ ይችል የነበረውን የ2 ወር ደመወዝ ብቻ ነው።
አብርሀም ዮሀንስ

🔥5👍4
የቁሙ ቀንድ ከበት ማረድ ፤ በባዶ እግር መሄድ ፤ አጭር ቁምጣ መልበስ የተከለከለ ነው!! -
የምስ/ጎጃም ዞን አስተዳደር ም/ቤት የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል ይሕውም፦
1. ያለ እድሜ ጋብቻ እና የህግ ማእቀፍ ያላቸው ሌሎች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ በወጣው ህግ መሰረት ሳይሸራረፍ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንዲሆን ማድረግ፤
2. ከአለባበስ ባህላችን አኳያ በዞናችን ስር ያላችሁ ሁሉም ወረዳዎች የምንመራው ህዝብ አንድም ሰው በባዶ እግሩ እንዳይሄድና ቁምጣ ሱሪ ለብሶ የሚሄድ ሰው እንዳይኖር በቁርጠኝነት መስራት፤
3. ተዝካርን በተመለከተ በተዝካር ስም የሚፈጸም የተንዛዛ ድግስ እንዳይፈጸም ስርአተ በቤተክስቲያን በሚያዝዘው መሰረት ስርአተ ፍትሃት ላደረጉ ካህናት አባቶች ብቻ ቤተክርስቲያን ላይ 1 በግ/ፍየል እና 2 ሌማት ብቻ እንዲቀርብ፤
4. ጋብቻ አንዱ ባህላዊ እሴታችን መሆኑ የሚታወቅ ስለሆነ እና ትውልድ መቀጠል ስላበት ጋብቻ ይቁም አይባልም ነገር ግን በጋብቻ ስም የሚፈጸም የተንዛዛ ድግስን በተመለከተ
ለአጋቢ ሽማግሌዎችና ለቤተሰብ የሚሆን1 በግ/ፍየል እና 2 ሌማት ብቻ እንዲሆን የተወሰነ ስለሆነ እና የቀንድ ከብት ማረድ ፍጹም የተከለከለ መሆኑ ታውቆ በውሳኔው መሰረት በየደረጃው ያላቹህ የፖለቲካ እና የጸጥታ አመራሮች ከፍትህ ተቋሙ ጋር ተቀናጅታቹህ እንድታስፈጽሙ በጥብቅ እያሳወቅን አፈጻጸሙንም በጋራ እየገመገማቹህ የተገኘውን ውጤት እና የመጣ ለውጥ እስከ ጥር15/2015 ዓ/ም እንድታሳዉቁ እናሳዉቃለን፡፡ -
የምስ/ጎጃም ዞን አስተዳደር ም/ቤት

👍21
አንተን ወይም አንቺን በዚህ ቴሌግራም ላይ ያላችሁን ተሳትፎ የሚገልፀው ፎቶ
*A* ነው ወይስ *B*⁉️ የሚወክልዎትን ይምረጡ። https://t.me/lawsocieties

👍3
👍9
ከደረሰኝ ጋር የተገናኙ ወንጀሎች እና ቅጣታቸው
I. ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ ያለደረሰኝ ግብይት ያከናወነ እንደሆነ ከብር 25ሺ (ሃያ አምስት ሺ ብር) እስከ ብር 50ሺ (ሃምሳ ሺ ብር) የገንዘብ መቀጫ እና ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
II. በአንድ ግብይት በተሰጡ ተመሳሳይ የደረሰኝ ኮፒዎች ላይ የተለያዩ ዋጋዎችን በመመዝገብ የሽያጭ ዋጋን ያሳነሰ ማንኛውም ሰው ብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እና ከአምስት ዓመት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡

👍2
III. የሽያጩ ትክክለኛ ዋጋ ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ ከሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (||) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኞቹ ላይ ከተመለከቱት ከፍተኛው የገንዘብ መጠን እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት የሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
IV. ግብይት ሳይፈጸም ደረሰኝ የሰጠ ወይም የተቀበለ ሰው ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
V. በዚህ ተራ ቁጥር (IV) የተመለከተው ደረሰኝ ከብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ የገንዘብ መጠን የያዘ እንደሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (|) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኙ ከተገለጸው የገንዘብ መጠን ጋር እኩል በሆነ የገንዘብ ቅጣት እና ከአስር ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት የሚደረስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
VI. ባለሥልጣኑ ሳይፈቅድለት የታክስ ደረሰኝ ያተመ ሰው ከብር 300ሺ (ሦስት መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 500ሺ (አምስት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሁለት ዓመት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
VII. በዚህ ተራ ቁጥር (VI) መሠረት ጥፋተኛ የተባለ ሰው ወንጀሉን ለሁለተኛ ጊዜ ፈጽሞ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ የህትመት መሣሪያው እና የማተሚያ ድርጅቱ ይወረሳል፣ የንግድ ፈቃዱም ይሰረዛል፡፡
https://t.me/lawsocieties
IV. ግብይት ሳይፈጸም ደረሰኝ የሰጠ ወይም የተቀበለ ሰው ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
V. በዚህ ተራ ቁጥር (IV) የተመለከተው ደረሰኝ ከብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ የገንዘብ መጠን የያዘ እንደሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (|) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኙ ከተገለጸው የገንዘብ መጠን ጋር እኩል በሆነ የገንዘብ ቅጣት እና ከአስር ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት የሚደረስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
VI. ባለሥልጣኑ ሳይፈቅድለት የታክስ ደረሰኝ ያተመ ሰው ከብር 300ሺ (ሦስት መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 500ሺ (አምስት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሁለት ዓመት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
VII. በዚህ ተራ ቁጥር (VI) መሠረት ጥፋተኛ የተባለ ሰው ወንጀሉን ለሁለተኛ ጊዜ ፈጽሞ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ የህትመት መሣሪያው እና የማተሚያ ድርጅቱ ይወረሳል፣ የንግድ ፈቃዱም ይሰረዛል፡፡
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍3
👍4👏1
206006.pdf
826.1 KB
👍10❤1
የቢዝነስ ፕላን (Business Plan) እና የቢዝነስ አዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ማካከል ያለው ልዩነት!
አዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ማካሄድ ማለት ለማከናወን ያሰቡትን የቢዝነስ አይነት (በተለይ አዲስ ቢዝነስ) ጠቅላላ ሁኔታ መዳሰስ ሲሆን ለሚሰራው ቢዝነስ በዛ ያሉ አማራጮች ስለመኖራቸው ማሳየት እና የሚታሰበው ፕሮጀክት ከማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች አንጻር ምን ያህል ተቀባይነት እንዳለው የሚያጣራ ይሆናል፡፡
#ለምሳሌ፡- ከብት ማደለብ የሚባል ቢዝንስ ስለማዋጣቱ ቢጠና እስካልተተገበረ ድረስ ሃሳባዊ ነው፡፡ ነገር ግን በአዋጪነት ጥናት ከዳታ በመነሳት፤ የቀደሙ አቅርቦት እና ፍላጎትን በመለካት፤ የፖሊሲ አማራጮች መኖራቸውን ማጣራት፤ በመጪው ጊዜ አቅርቦት፤ ፍላጎት እና ዋጋ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ትንበያ መስራት፤ ቢዝነሱ ሊገጥሙት የሚችሉትን ስጋቶች መለየት፤ የሚጠበቁ መፍትሄዎችን ማሳየት፤ የፕሮጀክቱን ማህበራዊ ቅቡልነት ማረጋገጥ፤ ቢዝነሱ በገበያ ያለውን ተፎካካሪነት መለካት፤ ወዘተ ነው፡፡
ነገር ግን ፕሮጀክቶች (Business Plan) ገንዘቡ ከየት ተገኝቶ፤ ምን ያህል ሰዎች ተቀጥሮ፤ የት አካባቢ አምርቶ፤ ምን አምርቶ፤ እንዴት ሸጦ፤ እንዴት ማስታወቂያ አሰርቶ፤ እንዴት ምርቱን አከፋፍሎ፤ ስንት ሸጦ፤ በስንት ሸጦ፤ ወዘተ የሚሉ የታክቲክ እና የስትራቴጂ ስልቶችን በመንደፍ ከኢኮኖሚ አንጻር አትራፊ/አዋጪ ማድረግ እንደሚቻል የሚሰራ ሰነድ ነው፡፡
ከብት ማድለብ አዋጪ መሆኑ ሳይጣራ ከብት ለማድለቢያ መኖ የሚገዛበት ቦታ ሊመረጥ አይችልም፡፡ ስለዚህ የቢዝነስ ፕላን (Business Plan) የሚሰራው የቢዝነሱ አዋጪነት (Feasibility Study) ከተረጋገጠ በኋላ ነው፡፡
#ለምሳሌ፡- ኢንቨስትመንት ፍቃድ፤ የቦታ ጥያቄ ወይም ብድር ለመጠየቅ የሚሰራው ጥናት የአዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ነው፡፡ ምክንያቱም የሚሰራው ፕሮጀክት ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ተቀባይነት ያለው መሆኑን እንዲሁም በፖሊሲ የሚደገፍ መሆኑን በማጣራት ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ቢዝነስ ፕላን ቢዝነሱን ላሰበው ሰው ብቻ ከማስፈለጉ በተጨማሪ ዋና አላማው ኢኮኖሚያዊ አዋጪ (ትርፋማ) መሆኑ ብቻ ነው፡፡
The Ethiopian economist views

የዓለማችን የመጀመሪያው “ሮቦት ጠበቃ” ከደንበኛው ጋር ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው
DoNotPay በተባለ የአሜሪካ ኩባንያ የበለፀገው "ሮቦት ጠበቃ" ከደንበኛው ጋር ፍርድ ቤት በመቅረብ ነው ስራውን የሚጀምረው።
ይህ የሮቦት ሥርዓት ከፍጥነት ገደብ በላይ በማሽከርከር የተከሰሰ ደንበኛውን ነጻ ለማውጣት የሕግ ምክር ሊለግስ በቀጣዩ የካቲት ወር ፍርድ ቤት እንደሚቆም ዴይሊ ሜይል አስነብቧል።
ሮቦቱ ይህን ማድረግ የሚያስችለውን አቅም ያገኘው ተጨባጭ የሕግ እውነታዎችን መሠረት አድርጎ በመሠልጠኑ እንደሆነ ተመላክቷል።
ዝርዝሩን ከተከታዩ ሊንክ ያነብቡ https://am.al-ain.com/article/robot-lawyer-takes-first-case

👍15🤩4
#ውክልና
ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳዮቻቸውን ራሳቸው መፈፀም የማይችሉባቸው ሁኔታዎች ሊገጥሟቸው ይችላል፡፡ ለዚህ መፍትሄ ሆኖ በማገልገል ላይ ያለው ውክልና ነው፡፡ ሆኖም ውክልና በዘፈቀደ የሚደረግ ሳይሆን በህግ በተቀመጠው ሥርአት መሰረት የሚፈፀም ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ ስለ ውክልና ምንነት፣ ስለውክልና አይነቶች፣ ስለውክልና ጠቀሜታ እና ውክልና ቀሪ ስለሚሆንባቸው ሁኔታዎች በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡
የውክልና ምንነት
የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 2199 መሰረት ውክልና ማለት ተወካይ የተባለው ሰው ወካይ ለተባለው ሰው እንደርሱ በመሆን አንድ ወይም ብዙ ህጋዊ ስራዎችን በወካዩ ስም ለማከናወን ግዴታ ሚገባበት ውል ነው፡፡ በዚህም ተወካዩ ልክ እንደወካዩ በመሆን የወካዩን ሥራዎች በወካዩ ስም ለማከናወን የሚደረግ ውል ነው፡፡
ውክልና ከልዩ የውል ህጎች ውስጥ አንዱ እንደ መሆኑ መጠን አንድ ህጋዊ ውል ሊያሟላቸው ያሚገባውን በፍትሐብሔር ህጉ በአንቀፅ 1678 ስር የተቀመጡትን መስፈርቶች ሊያሟላ ይገባል፡፡ ይኸውም፡-
👉ውል ለመዋዋል ችሎታ ያለው ሰው መሆን
👉ጉድለት የሌለው ፈቃድ ወይም ስምምነት መኖር
👉በቂ የሆነ እርግጠኝነት ያለው የሚቻል እና ህጋዊ የሆነ ጉዳይ መሆን
👉የውል አፈፃፀም ፎርም በህግ የታዘዘ ሆኖ እንደ ትዛዙ ባይፈፀም ፈራሽነት የሚያስከትል ሲሆን ህግ በሚያዘው ልዩ ፎርም መሆን ናቸው፡፡
የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 2200 ወካይ ለተወካይ የውከልና ስልጣኑን በቃል ወይም በዝምታ ሊሰጥ የሚችል ሲሆን ህጉ የውከልና ስልጣኑ በተለያየ ፎርም መሰጠት አለበት በማለት የሚያዝ ከሆነ ግን ይህ መሟላት ይኖርበታል፡፡
የውክልና አይነቶች
በአጠቃላይ ሁለት አይነት የውክልና ስልጣን ሲኖር ይህም ጠቅላላ እና ልዩ ውክልና በመባል ይታወቃሉ::