አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ቀጣሪ ድርጅቶች ከግል የትምህርት ተቋማት የተመረቁ ተቀጣሪዎችን የትምህርት ማስረጃዎች ሕጋዊነት እንዲያረጋግጡ ተጠየቁ ----------------------------------------------------
የመንግሥትም ሆነ የግል ቀጣሪ ድርጅቶች ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ ሠራተኞቻቸውን እና አዲስ ሠራተኞችን ከመቅጠራቸው በፊት የተቀጣሪዎቹን የትምህርት ማስረጃዎች ሕጋዊነት እና ትክክለኛነት መረጋገጥ እንደሚገባቸው የኢፌዴሪ ትምህርት እና ሥልጠና ባለሥልጣን አሳሰበ።
.....
ተገልጋዮች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች የማረጋገጫ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ባለሥልጣኑ ከመሔዳቸው በፊት የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት አገልግሎቱን ማግኝት እንደሚችሉም ገልጿል።

መስፈርቶቹም፦

1. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊ እና ሬጅስትራር ፊርማ እና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ዲግሪ ከኮፒ ጋር በማያያዝ፤
2. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊ እና ሬጅስትራር ፊርማ እና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ትራንስክሪፕት/Student Copy/ ከኮፒ ጋር በማያያዝ፤
3. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘ ኦሪጅናል ዲፕሎማ ወይም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ከኮፒ ጋር በማያያዝ፤
4. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ከሆነ በትምህርት ምዘናዎች እና ፈተናዎች አገልግሎት ድርጅት ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ ከኮፒ ጋር በማያያዝ፤
5. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው ዲፕሎማ ከሆነ ዲፕሎማው በተገኘበት ክልል የቴክኒክ እና ሙያ ኤጀንሲ ወይም የዞን/የከተማ መስተዳደር የሥራ እና ሥልጠና ቢሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ እንዲሁም የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ(COC) ካገኙበት ማዕከል የተረጋገጠ መሆን አለበት ከኮፒ ጋር በማያያዝ እና
6. የስም ለውጥ ካለ የፍርድቤት ውሳኔ ከኮፒ ጋር በማያያዝ ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ የማስተርስ ዲግሪ ለማረጋገጥ በቅድሚያ የመጀመሪያው ዲግሪ ከላይ በተገለጸው መንገድ መረጋገጥ እንዳለበት የኢፌዴሪ ትምህርት እና ስልጣና ባለሥልጣን አሳስቧል
EBC
https://t.me/lawsocieties
👍3
አለሕግAleHig ️
Photo
ከህገወጦች እራሳችንንና ህብረተሰባችንን ልንከላከል ይገባል!
============ https://t.me/lawsocieties
በህገወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የራሳቸውን ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ በመጠቀም እንዲሁም በአንዳንድ አካባቢዎች በተሽከርካሪ ከቦታ ቦታ በመዟዟር እና ቅስቀሳ በማድረግ ከባለሥልጣኑ የማስተማር ፈቃድ ያገኙ በማስመሰል ህብረተሰቡን በማሳሳት ላይ ይገኛሉ፡፡
ስለሆነም በከፍተኛ የትምህርት ተቋም ተመዝግቦ ለመማር የፈለገ አንድ ተማሪ ለመማር ከመወሰኑና ከመመዝገቡ በፊት ሊማርበት ያሰበው ተቋም፡-
* ለመማር የፈለገው የትምህርት ዓይነት በመረጠው ካምፓስ ፈቃድ ያለው መሆኑን ማጣራት፤
* በመረጠው በተቋሙ ሊማር ያሰበው የትምህርት ዓይነት ያገኘው ፈቃድ ከመቼ እስከ መቼ እንደተሰጠው ወይም የፈቃድ እድሳት የተደረገለትን ጊዜ ማጣራት ፤
* ያገኝው ፈቃድ በትምህርት አሰጣጥ ዘዴ(መደበኛ፣ የርቀት እና ድንበር ተሸጋሪ እና ኦንላይን ) መሆኑን ማጣራት እና
* የተፈቀደለት ተማሪ ብዛት በቁጥር ስንት እንደሆነ ማጣራት ናቸው፡፡
ህብረተሰቡም ስለትምህርት ጥራት እውን መሆን በያግባኛል፣ በባለቤትነት ስሜት በየአካባቢው እንቅስቃሴ ሲያደርግ ህገ-ወጥ የትምህርት ተቋማትን በማጋለጥ ዘብ ሊቆም ይገባል፡፡ ከባለሥላጣኑ ጋር በቅርበት እጅ እና ጓንት በመሆን ይህን ማድረግ ከተቻለ ህገ-ወጥ ተቋማት በተማሪው፣ በወላጆች እንዲሁም በሀገር ላይ የሚያደርሱት ኪሳራ መቀነስ ይቻላል፡፡ህግ የጣሱትንም በፍትሀብሄር እና በወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑና ቅጣታቸውን እንዲያገኙ ለማድረግም ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፡፡
መላው የሀገራችን የህብረተሰብ ክፍል የትምህርት ጥራትን ማረጋግጥ ለአንድ አካል ብቻ የሚተው አለመሆኑን በመረዳት እገዛቸውን አጠናክረው መቀጠል ተገቢ ነው፡፡ እንዲሁም በተለያዩ መዋቅሮች ላይ የሚገኙ የመንግስት አካላትም ከባለሥልጣኑ ጎን በመሆን የትምህርት ጥራትን ለመጠበቅ በተጀመሩ አበረታች ስራዎች ላይ ትብብራቸው ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ አጠናክረው መቀጠል ይጠበቅባቸዋል፡፡ጥራት ያለው የትምህርት ስርዓት እውን መሆን የአንድ ሀገር እድገት እውን ሆነ ማለት ነውና ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋጽኦ በማበርከት የዜግነት ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል፡፡
በኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጣና ባለሥልጣን
ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ
https://t.me/lawsocieties
1👍1
በፌደራል ማናቸውም ፍርድ ቤት የወንጀል ክስ ተመስርቶቦት ጠበቃ ለማቆም የገንዘብ አቅም ከሌሎት ፈፅሞ አይጨነቁ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የተከላካይ ጠበቆች ፅህፈት ቤት በነፃ ሙሉ የጥብቅና አገልግሎት በትጉህ ባለሙያዎቹ ይሰጥዎታል ከእርሶ የሚጠበቀው ለተከሰሱበት የወንጀል ችሎት የመንግስት ጠበቃ ይመደብልኝ በማለት መጠየቅ ብቻ ነው።
https://t.me/lawsocieties
ሃሰተኛ ማስረጃን ለማረጋገጥ የሞከሩ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
.......................
ታህሳስ 27/2015 (ኢዜአ) በኤጀንሲው ዋና መስርያ ቤት ቀርበው ሃሰተኛ የልደት ፣ ፍቺ እና ያላገባ ማስረጃ ለማረጋገጥ የሞከሩ ሶስት ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ገለጸ።

1ኛው ግለሰብ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማው ወረዳ 3 ጽህፈት ቤት የተሰጠ የፍቺ ምዝገባ ሰርተፍኬት አስመስሎ በማሰራት በጥብቅና ውክልና ለማረጋገጥ ታህሳስ 26 ቀን 2015 የቀረበ ሲሆን በተደረገ ማጣራት በእጁ የተገኘው የግለሰቡ የነዋሪነት መታወቂያ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 12 የተሰራ ሃሰተኛና ተመሳስሎ የተሰራ መሆኑ መረጋገጡ ተገለጿል።

2ኛዋ ግለሰብ በየካ ክፍለ ክተማ ወረዳ 1 ጽህፈት ቤት የተሰጠ የልደት እና ያላገባ ማስረጃ እንዲሁም ይህን የነዋሪነት መታወቂያ ተመሳስሎ የተሰራ ታህሳስ 25 ቀን 2015 ይዛ በመቅረብ ለማረጋገጥ ስትሞክር በቁጥጥር የዋለች መሆኑ ተመላክቷል።

3ኛው ግለሰብ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ጽህፈት ቤት በተመሳሳይ ሁኔታ የተሰራ የልደት ማስረጃ ዛሬ ታህሳስ 27 ይዞ በመቅረብ ለማረጋገጥ ሲሞክር በተደረገ የሰነድ ማጣራት ሃሰተኛ መሆናቸው በመረጋገጡ የኤጀንሲው ስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ክፍል በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረገ ሲሆን በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ኤጀንሲው አስታውቋል።

በከተማችን ከግዜ ወደ ግዜ ተመሳስለው የሚሰሩ ሃሰተኛ ሰነዶች እየተበራከቱ የመጡና ከፍተኛ የዘርፉ ስጋት እየሆኑ የመጡ መሆኑ መምታጣቸውን ገልጾ ህብረተስቡ ከመሰል ወንጀል ተግባራት ራሱን እንዲጠብቅና ሃሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ ሲመለከተ ጥቆማ እንዲሰጥ ተቋሙ አሳስቧል።
ሰነዶች ማረጋገጫ
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
👍3
በኑዛዜ የሚከናወኑት ተግባሮች ስጦታ (legacy) ወይንም የክፍያ ደንብ (Rule of partition) ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ሰበር መዝገብ ቁጥር 201100
በመርህ ደረጃ አንድ ሰው ከውርስ ሀብቱ መካከል አንድን ንብረት ለወራሾቹ መስጠቱ የኑዛዜ ስጦታ የማያሰኘው ሲሆን ፣ ይልቁንም ይህ ዓይነቱን ኑዛዜ ሕጉ የሚቀበለው እንደ አንድ የክፍያ ደንብ በመሆኑ አንድ አውራሻ ለወራሹ አንድን ንብረት ቢናዘዝለት የኑዛዜ አፈፃፀም ስጦታ(legacy) አፈፃፀምን መከተል ሳይሆን የክፍያ ደንብ (Rule of partition) በመከተል የሚከናወን ይሆናል፡፡

ሆኖም በኑዛዜው ላይ የሚሰጠው የክፍያ መጠን በመገለፁ ብቻ ሁል ጊዜ የክፍያ ደንብ ሊባል የሚችል ሊሆን አይችልም፡፡ በመሆኑም የተሰጠው የንብረት መጠን ከሟቹ የውርስ ንብረት ጋር ታይቶ ውጤቱም በዚሁ ረገድ መታየት አለበት፡፡
https://t.me/lawsocieties
👍1
ከደረሰኝ ጋር የተገናኙ ወንጀሎች እና ቅጣታቸው
https://t.me/lawsocieties
I. ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ ያለደረሰኝ ግብይት ያከናወነ እንደሆነ ከብር 25ሺ (ሃያ አምስት ሺ ብር) እስከ ብር 50ሺ (ሃምሳ ሺ ብር) የገንዘብ መቀጫ እና ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡

II. በአንድ ግብይት በተሰጡ ተመሳሳይ የደረሰኝ ኮፒዎች ላይ የተለያዩ ዋጋዎችን በመመዝገብ የሽያጭ ዋጋን ያሳነሰ ማንኛውም ሰው ብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እና ከአምስት ዓመት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡

III. የሽያጩ ትክክለኛ ዋጋ ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ ከሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (||) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኞቹ ላይ ከተመለከቱት ከፍተኛው የገንዘብ መጠን እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት የሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡

IV. ግብይት ሳይፈጸም ደረሰኝ የሰጠ ወይም የተቀበለ ሰው ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡

V. በዚህ ተራ ቁጥር (IV) የተመለከተው ደረሰኝ ከብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ የገንዘብ መጠን የያዘ እንደሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (|) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኙ ከተገለጸው የገንዘብ መጠን ጋር እኩል በሆነ የገንዘብ ቅጣት እና ከአስር ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት የሚደረስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡

VI. ባለሥልጣኑ ሳይፈቅድለት የታክስ ደረሰኝ ያተመ ሰው ከብር 300ሺ (ሦስት መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 500ሺ (አምስት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሁለት ዓመት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡

VII. በዚህ ተራ ቁጥር (VI) መሠረት ጥፋተኛ የተባለ ሰው ወንጀሉን ለሁለተኛ ጊዜ ፈጽሞ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ የህትመት መሣሪያው እና የማተሚያ ድርጅቱ ይወረሳል፣ የንግድ ፈቃዱም ይሰረዛል፡፡
(የገቢዎች ሚኒስቴር)
https://t.me/lawsocieties
1🔥1
የወሊድ ፈቃድ
1/ ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ከእርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ አሠሪው ከደመወዝ ጋር ፈቃድ ይሰጣታል፤ ሆኖም ሠራተኛዋ ከምርመራ በኋላ የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ አለባት፡፡

2/ ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ከመውለዷ በፊት ሐኪም እንድታርፍ ካዘዘ አሠሪው ከክፍያ ጋር እረፍት ይሰጣታል፡፡ ሕግ አገልግሎት

3/ ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት የ 30 (ሰላሳ) ተከታታይ ቀናት የቅድመ-ወሊድ ፈቃድ ፣ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ ለ 90 (ዘጠና) ተከታታይ ቀናት የድህረ-ወሊድ ፈቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጣታል፡፡

4, ሠራተኛዋ ከመውለዷ በፊት የወሰደችው የ 30 (ሰላሳ) የሥራ ቀናት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ ካልወለደች እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ከላይ በቁጥር ሁለት ስር በተመለከተው መሠረት እረፍት ልታገኝ ትችላለች፡፡ የ 30 (ሰላሳ) የሥራ ቀናት

የቅድመ-ወሊድ ፈቃዷ ሳያልቅ ከወለደች 90 (ዘጠና) የሥራ ቀናት የድህረ-ወሊድ ፈቃዷ ይጀምራል፡፡

የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 88
https://t.me/lawsocieties
👍6
ህጋዊ መከላከል (Self Defence) በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ
.............
ህጋዊ መከላከል ማንኛውም ሰው እራሱን ወይም ሌላውን ሰው ከማንኛውም ጥቃት የሚጠብቅበት በህግ የተፈቀደ ተግባር ነው፡፡ ሆኖም ህጋዊ መከላከል በህግ በተቀመጠው መልኩ ብቻ መተግበር ያለበት ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ ህጋዊ መካላከልን እንደሚከተለው በዝርዝር እንመለከታለን፡፡

ህጋዊ መከላከል (Self Defence) ምንነት

በ1996 ዓ.ም ከወጣዉ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 78 እንደምንረዳው ህጋዊ መከላከል "የራስን ወይም የሌላዉን ሰዉ መብት ህገወጥ ከሆነ ጥቃት ወይም በቅርቡ ከሚደርስ ሕገወጥ ጥቃት ለማዳን ጥቃቱ እንዳይደርስ ለማድረግ ሌላ መንገድ ሳይኖር ሲቀር ከሁኔታዉ መጠን ባለማለፍ የሚፈፀም ድርጊት ነው”፡፡ የህጋዊ መከላከል ፅንሰ ሀሳብ እንደየ ሀገሩ ህግ የተለያየ አገላለፅ ቢኖረዉም ሁሉም የሚስማሙበት አንድ ዋና ነጥብ አለ፡፡ ይኸዉም ራስን ወይም ሌላዉን፣ የራስን ወይም የሌላዉን ሰዉ ፍትሐዊ መብት ህገወጥ ከሆነ ጥቃት ለመከላከል ከመጠን ባለማለፍ የሚፈፀም የኃይል ተግባር እንደ ወንጀል የማታይና በህግ የተፈቀደ መሠረታዊ መብት መሆኑን ነዉ፡፡

አንድ ድርጊት ህጋዊ መከላከል መሆኑ የሚረጋገጠው በወንጀል ህጉ አንቀጽ 78 ላይ ያሉ ፍሬ ነገሮች መሟላታቸው ሲረጋገጡ ብቻ ነው፡፡ እነዚህ ፍሬ ነገሮችን በዝርዝር ስንመለከት፡-

• አስቀድሞ የተሰነዘረ ወይም በርግጠኛ ሊደርስ የሚችል ህገወጥ ጥቃት መኖር

ህጋዊ መከላከል ለማድረግ በመጀመሪያ ህገ-ወጥ የሆነ ጥቃት መሰንዘር ወይም በእርግጠኝነት በቅርብ ሊሰነዘር እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡ ይህ ህገ-ወጥ ጥቃት ጥቃቱን በሚከላከለው ሰው ላይ ወይም ደግሞ በሌላ ሰው ላይ መድረሱ አሊያም ጥቃቱ በቅርብ ሊደርስ እንደሆነ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ይህም እርግጠኛ ባልሆነ እና ገና ለገና ይደርሳል ብሎ በመገመት ብቻ ህጋዊ መከላከል መውሰድ እንደማይቻል ሚያስገነዝብ ነው፡፡

• ተመጣጣኝ መሆን

አንድ ድርጊት እንደ ህጋዊ መከላከል የሚቆጠረዉ ወይም ህጋዊ መከላከል የሚሆነው መከላከሉ ከተሰነዘረዉ ጥቃት ወይም ሊሰነዘር ከነበረው ጥቃት ጋር ተመጣጣኝ ሲሆን ነዉ፡፡ ህጋዊ መከላከሉ ከጥቃቱ ጋር ተመጣጣኝ መሆን አለመሆኑን ለመወሰን መታየት ያለባቸዉ ብዙ ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎችን ስንመለከት የተሰነዘረው ጥቃት ወይም ሊደርስ የነበረው ጥቃት ክብደት፣ የጥቃት አድራሹ ሁኔታና አቅም፣ አጥቂው የተጠቀመበት መሳሪያ ምንነት፣ ጥቃቱ የተሰነዘረበት ሰው አቅም ከአጥቂው ጋር ሲነጻጸር ያለበት ሁኔታ፣ ለመከላከል የተጠቀመው ዘዴ እና መሳሪያ መታየት ይኖርበታል፡፡ ይህ ማለት አጥቂዉ የሰነዘረዉ ጥቃት ክብደት፣ ጥቃቱ የተሰነዘረበት ሰው መብት እና በዚህ መብት ላይ ሊደርስ የሚችለዉ ጉዳት መጠን ተመርምሮ የጥቃቱ ክብደትና የተጠቂዉ መብት መመዛዘን አለባቸዉ ማለት ነዉ፡፡ ይህም ሲባል የደረሰው ህገ-ወጥ ጥቃት ወይም ሊደርስ የነበረው ጥቃት አነስተኛ መሆን ህጋዊ የመከላከል መብትን ያስቀራል ማለት አይደለም፡፡ የጥቃቱ መጠን ምንም ይሁን ተከላካዩ ጥቃቱን ለማስወገድ ከሚያስፈልገዉ በላይ እስካልሄደ ወይም መከላከሉ ከጥቃቱ መጠን ጋር የተመጣጠነ እስከሆነ ድረስ ማንኛዉንም መብቱን ሕገወጥ ከሆነ ጥቃት መከላከል ይችላል፡፡

አጥቂዉ ጥቃቱን ለማድረስና ተከላካዩም ለመከላከል የተጠቀመበት ዘዴና መሣሪያ ከግምት ዉስጥ መግባት አለበት ሲባል ግን አጥቂዉ የተጠቀመበትና ተከላካዩ የተከላከለበት መሣሪያ የግድ ተመሳሳይ ይሁን ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ተከላካዩ ጥቃቱን ለመከላከል የተጠቀመበት መሣሪያ አጥቂዉ ከተጠቀመበት መሣሪያና ሊደርስ ከነበረዉ ጥቃት ጋር ተመጣጣኝ መሆን አለበት ማለት ነዉ፡፡

በተጨማሪም የአጥቂዉና የተከላካዩ ጥንካሬና ዕድሜ አብሮ መታየት ያለበት ጉዳይ ነዉ፡፡ ለምሳሌ አንድ የሠላሳ አመት ሰው የአስራ አምስት አመት ልጅ ልትመታው ስትሰነዝር ከምቱ ለመዳን ወይም ምቱን ለመቀልበስ በያዘው የጦር መሳሪያ ተኩሶ ቢመታትና ብትሞት ራስን ለመከላከል የተወሰደ እርምጃ ነው አያስብልም፡፡ ምክንያቱም የተሰነዘረበት ጥቃት፣ ለመከላከል የተጠቀመበት መሣሪያ፣ ከአጥቂዋ ጥንካሬና ዕድሜ አንጻር ሲመረመር የመከላከሉ ድርጊት ተመጣጣኝ አለመሆኑ በግልፅ ይታያል፡፡

• ጥቃቱ እንዳይደርስ ለመድረግ ሌላ መንገድ አለመኖር

ህጋዊ መካላከል ሊደረግ የሚችለው ጥቃተ የተሰነዘረበት ሰው ጥቃቱን ለመቀልበስ ወይም በቅርብ ሊሰነዘር የሚችል ህገወጥ ጥቃትን ለማስቀረት ከህጋዊ መካላከል ውጪ ሌላ አማራጭ የሌለው ከሆነ ብቻ ነው፡፡

ህጋዊ መካላከልና ተጠያቂነት

ህጋዊ የመከላከል እርምጃ ህጉን የተከተለ እስከሆነ ወይም ከአስፈላጊዉ መጠን እስካላለፈ ድረስ ህጋዊ መከላከል የወሰደዉን ሰዉ ሙሉ በሙሉ ከወንጀል ተጠያቂነት ነፃ የሚያደርግ ድርጊት ነዉ፡፡ ሆኖም የመከላከል ሂደቱ ከመጠን ያለፈ ከሆነ እንደተፈፀመው ወንጀል አይነት በወንጀል ህጉ የተመለከተውን ቅጣት ይቀጣል፡፡

በእርግጥ ህጋዊ የመከላከል መብትን ከመጠን በማለፍ ምክንያት ጥፋተኛ የሆነ ሰዉ ፍርድ ቤት እንደመሰለዉ ቅጣት ሊያቀልለት እንደሚችል የወንጀል ህጉ በግልጽ ደንግጎ ይገኛል፡፡ የመከላከል ድረጊቱ ከመጠን ያለፈዉ ጥቃቱ ባስከተለበት ይቅርታ ሊያስገኝ በሚችል ፍርሃት፣ ድንገተኛ ድንጋጤ ወይም በደም ፍላት ምክንያት እንደሆነ ፍርድ ቤት ሙሉ በሙሉ ከቅጣት ነፃ ሊያደርገዉ እንደሚችል በወንጀል ህጉ አንቀፅ 79(2) ላይ ተደንግጓል፡፡

ማጠቃለያ

በኢ.ፍ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ መሠረት ህጋዊ መከላከል በህግ የተፈቀደ መብት ቢሆንም፣ ጥቃት የደረሰበት ሰዉ ወይም ሊደርስበት የነበረ ሰዉ ሁሉ በህጋዊ መከላከል ሰበብ የፈለገዉን ድርጊት ሁሉ ይፈፅማል ማለት አይደለም፡፡ አንድ ሰው በቀጥታ የመከለከል እርምጃ ከመወሰዱ በፊት ሌላ ከጥቃቱ ሊያመልጥ የሚችልበት ዘዴ መፈለግ ያለበት ሲሆን ህጋዊ መከላከሉ አስፈላጊ ከሆነም ሊወሰድ የሚገባዉ መከላከል ከጥቃቱ ጋር ተመጣጣኝ መሆን ይኖርበታል፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
👍5👏1
83771.pdf
196.1 KB
የየሰ/መ/ቁ 83771
በተከራካሪ ወገኖች ክርክር በሚካሄድበት ወቅት በፍ/ቤት ትእዛዝ በተከራካሪ ወገን ስም በባንክ የሚገኝ ገንዘብ ታግዶ እንዲቆይ ተደርጐ ትእዛዙ ፀንቶ በነበረበት ግዜ በገንዘቡ ላይ ወለድ ሊታሰብ ይገባል ወይስ አይገባም በሚል ክርክር የተነሣ እንደሆነ ከጉዳዩ ልዩ ባህሪ ጋር በተገናኘ ፍ/ቤቶች የልዩ አዋቂ ምስክርነትና የባለሙያ ማብራሪያን አስቀርበው በማጣራት ሊወሰኑ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 136 የሰ/መ/ቁ 83771የሰ/መ/ቁ 83771 በተከራካሪ ወገኖች ክርክር በሚካሄድበት ወቅት በፍ/ቤት ትእዛዝ በተከራካሪ ወገን ስም በባንክ የሚገኝ ገንዘብ ታግዶ እንዲቆይ ተደርጐ ትእዛዙ ፀንቶ በነበረበት ግዜ በገንዘቡ ላይ ወለድ ሊታሰብ ይገባል ወይስ አይገባም በሚል ክርክር የተነሣ እንደሆነ ከጉዳዩ ልዩ ባህሪ ጋር በተገናኘ ፍ/ቤቶች የልዩ አዋቂ ምስክርነትና የባለሙያ ማብራሪያን አስቀርበው በማጣራት ሊወሰኑ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 136
👍6
የዚህ ቻናል ስም የቱ ቢሆን ጥሩ ነው ትላላችሁ?
Anonymous Poll
56%
አለ ህግ
35%
ህግ አለ
9%
ሁለቱንም
👍11
እንኳን አደረሳችሁ🙏 መልካም በዓል‼️
........... @lawsocieties ......
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ቤተሰብነታችሁን አረጋግጡ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
https://t.me/lawsocieties
👍11
ስለ_ህግ ለማወቅ አማራጭ መንገድ የሆነውን አለ ህግ ቻናልን ቤተሰብ ይሁኑ።
#ህግ አለን
#ባለሙያ አለን
#ለእናንተ ጊዜም አለን
#ሁሉም አለ
ይህንን ጠቃሚ የህግ ቻናል ለሚወዱት ወዳጅ ዘመድ ሼር በማድረግ መልካም መሆንዎን ያረጋግጡ።
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
👍6
በጣም ጠቃሚ ሰበሮች ስለ ውል ህጎች

የሰበር መዝገብ ቁጥር 26565
ሊፈጠር ወይም ሊከሰት እንደሚችል ቀድሞ ሊገመት ወይም ሊታሰብና ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚቻል ሁኔታ ድንገተኛ ደራሽ ቢሆን እንኳ ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ (Force majeure) ተብሎ የማይወሰድ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ህ/ቁ. 1792(2)

የሰበር መዝገብ ቁጥር 29369
የባለዕዳው ቀጥተኛ የውል ፈፃሚነት ከውሉ ባህሪ አኳያ ማስፈፀም አለመቻል ውሉ እንዲሰረዝ መጠየቅ ሳያስፈልግ ኪሣራ ካለ መጠየቅ ስለመቻሉ ( በውል መሠረት ግዴታውን ያልተወጣ ወገንን አስገድዶ ለማስፈፀም የማይቻል በሆነ ጊዜ በውሉ ግዴታውን የተወጣው ወገን ውሉ ባለመፈፀሙ ምክንያት የደረሰውን ኪሣራ ለመጠየቅ ስለመቻሉ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1771(1) እና (2)

የሰበር መዝገብ ቁጥር 30947
የስልክ ክፍያ እንዲከፈል ለተገልጋይ የተሰጠ ማስታወቂያ ክፍያው እንዲከፈል ለማድረግ እንጂ ክፍያውን ላለመፈፀም ምክንያት ሊሆን አለመቻሉ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1901

የሰበር መዝገብ ቁጥር 31480
ለአቅመ አዳም ካልደረሰ ልጅ ጋር የሚደረግ የመያዛ ውል ተፈፃሚ የማይሆን ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2187/1

የሰበር መዝገብ ቁጥር 12719
በሁለት ወገኖች መካከል የተፈረመ ሰነድን እንደ ህጋዊ ስምምነት ለመውሰድ የፈራሚ ወገኖችን ሃሳብና ፍላጐት መመርመር አስፈላጊ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1734, 1952/1/

የሰበር መዝገብ ቁጥር 20232
የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች የተዋዋይ ወገኖች መብትና ግዴታዎች የሚፈጠሩባቸውና የሚረጋገጡባቸው በመሆናቸው የውል ህግ መሰረታዊ ድንጋጌዎች መሟላታቸው አስፈላጊ ሁኔታ ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ. 715, የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1706, 1679

የሰበር መዝገብ ቁጥር 22448
ፍርድ እንዲፈፀም ለመጠየቅ ችሎታ ያለው ፍርድ የተፈረደለት ሰው /ወገን/ ብቻ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ህ/ቁ. 378/1/

የሰበር መዝገብ ቁጥር 24974
በውል ከተገባ ግዴታ አመዛኙ ክፍል ተፈፀመ ወይም/እና አይነተኛ የሆነ የውል መጣስ ተከስቷል ለማለት ባልተቻለ ጊዜ ውል እንዲሰረዝ ለመወሰን የማይቻል ስለመሆኑየፍ/ብ/ህ/ቁ. 1771,1784, 1785

የሰበር መዝገብ ቁጥር 26996
ውል የተደረገበት ጉዳይ ሊፈፀም የማይችል ሆኖ በተገኘ ጊዜ ተዋዋይ ወገኖችን ወደ ነበሩበት ቦታ የመመለስ ውጤት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1715, 1815

የሰበር መዝገብ ቁጥር 27349
ተዋዋይ ወገኖች በመካከላቸው የሚፈጠርን አለመግባባት በስምምነት ወይም ደግሞ በአስታራቂ አማካኝነት ለመፍታት የተስማሙ ከሆነ ይኼው ስምምነት ተፈፃሚ መሆን ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1765, 1731/1/
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
👍3
በይርጋ የማይታገዱ የፍትሀብሄር ጉዳዬች
🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑♨️♨️♨️

የይርጋ መሰረታዊ ዓላማ ማንኛውም በህግ በግልፅ የተደነገገ መብትና ግዴታ በህጉ በተወሰነው ወይም በተገደበው ጊዜ ውስጥ ስልጣን ላለው አካል እንዲቀርቡ ግዴታን በማስቀመጥ መብቴ ተጣሰብኝ የሚል ወገን ዳተኛ ሳይሆን በትጋት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል መሆኑ ይታወቃል።

ነገር ግን አንዳንድ ጉዳዬች ከንብረቶቹ ልዩ ባህሪና የመንግስት ፖሊሲ አንፃር ህግ አውጪው በይርጋ እንዳይታገዱ አድርጎ ያስቀመጣቸው የፍትሀብሄር ጉዳዬች አሉ። ከእነዚህ መካከል፦

#የመፋለም ክስ ( petitory action)
♨️♨️♨️🛑🛑🛑🛑♨️

ለባለሀብቱ የባለቤትነት መብት ከሚሰጣቸው መብቶች መካከል ንብረቱ ያለ እርሱ ፈቃድ ከህግ ውጪ በሌላ ሰው ወይም ሀይል ከተወሰደ ንብረቱን ካለበት ድረስ በመከታተል የማስመለስ ወይም የመፋለም መብት አንዱ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1206 ድንጋጌ ያስረዳል፡፡

ባለሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን” በሚል ርዕስ  ስር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1192 የተመለከተው በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት በአስር ዓመት የጊዜ ወሰን /ይርጋ/ ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ ያመላከተ ሲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ግን አያሳይም፡፡
👍11👏2
👍72
Live stream started
Live stream finished (1 hour)