አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ምክር ቤቱ ሁለት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጸደቀ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብሔራዊ ክፍያ ሥርዓትን እና የመንግስትና የግል አጋርነት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል፡፡

የአዋጆቹን አስፈላጊነት አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ እንዳሉት፤ የብሔራዊ ክፍያ ሥርዓቱን ደህንነት ለማስጠበቅና በፋይናስ ዘርፉ አስተማማኝና ቀልጣፋ ሥርዓት በመዘርጋት፤ ለውጦችን እና እድገት ታሳቢ ባደረገ መልኩ የክፍያ ስርአቱን ለማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አስረድተዋል፡፡
 
የተከበሩ አቶ ደሳለኝ አያይዘውም፤ የመንግስት እና የግል አጋርነት ረቂቅ አዋጅን በሚመለከት የሀገራችንን የኢኮኖሚ እድገት ለማገዝ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቁመው፤ በመንግስትና በግል ባለሀብቶች በጋራ በሚሰሩ ፕሮጀክቶች ምቹ ምህዳር በመፍጠር፤ ለግል ሴክተሩ የእውቀትና ክህሎት ሽግግር በመፍጠር የፋይናንስ ሴክተሩን ለማሳደግ ጠቃሚ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው፤ የብሔራዊ ክፍያ ሥርዓት የሀገራችንን የፋይናስ ዘርፍ በማገዝ እድገት እና ብልጽግና ለማምጣት እንዲሁም የግል ዘርፉን በማሳተፍ ለኢኮኖሚው እድገት መነቃቀትን የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል የተከበሩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ለመግስት እንደ ሀገር ተግዳሮት የሆነውን ሙስና እና ብልሹ አሰራር ለመከላከል ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በጨረታና በድርድር የሚለው ለኪራይ ሰብሳቢነት በር ስለሚከፍት በረቂቅ አዋጁ ላይ በጨረታ ብቻ በሚል ቢቀመጥ የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ የተከበሩ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የክፍያ ሥርዓት አዋጁ ሙሉ በሙሉ የባንክ ስራን ተክቶ የማይሰራ በመሆኑ ከባንክ በመለስ ያሉ የክፍያ ስርአቶችን የውጭ ባለሃብቶችና ዜጎች እንዲሳተፉ ለማድረግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
 
የባንክ ገዥው የተከበሩ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) አክለውም የብሔራዊ የክፍያ ሥርዓት አዋጁ ስያሜን በተመለከተ፤ በብዙ የአፍሪካ ሀገራትም ጭምር ልምድ በመውሰድ ተሞክሮዎቹ ብሔራዊ የሚለው ስያሜ የጋራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው፤ የመንግስት እና የግል አጋርነት ያደጉ ሀገራት የተጠቀሙበት ሀገራቸውን ለማሳደግ ውጤታማ ስራ የሰሩበት በመሆኑ መንግስትና የግል ሴተክተሩ ተቀራርበው በመስራት ለፕሮጀክቶች ተፈጻሚንት ጉልህ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

የብሔራዊ ክፍያ ሥርዓትን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1282/2015 ሆኖ በሶስት ድምጸ ተአቅቦ፤ በአብላጫ ድምጽ ጸድቀዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ምክር ቤቱ በውሎው፤ የመንግስትና የግል አጋርነትን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1283/2015 ሆኖ በአንድ ተቃውሞ እና በአንድ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቀዋል፡፡

በ መኩሪያ ፈንታ
(ዜና ፓርላማ)፣ ታህሳስ 13፣ 2015 ዓ.ም፤
ParlamaNews
www.hopr.gov.et
https://t.me/lawsocieties
👍2
ከዛሬ ጀምሮ ሲሚንቶ በነጻ ገበያ እንዲ ተወሰነ።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተሻለ በልሁ ከዚህ በፊት የነበረው የሲሚንቶ ሽያጭ መመሪያ መቀየሩን ገልጸዋል።

መመሪያው የሲሚንቶ ዋጋ በመንግሥት ተወስኖ እንዲሸጥ መደረጉ በርካታ ቅሬታዎች ሲነሳበት እንደነበር የጠቀሱት አቶ ተሻለ በዚህም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች፥ ሲሚንቶን በቀላሉ እንዳያገኙ አድርጓቸው እንደነበር ተናግረዋል ።

በተሻሻለው መመሪያ መሰረትም አከፋፋዮችን እና ቸርቻሪዎችን መምረጥ የፋብሪካዎቹ እድል ነው ብለዋል።

የፋብሪካዎቹ የመሸጫ ዋጋ ለጊዜው ምርታማነት እስከሚጨምር ድረስ የፋብሪካ ዋጋ በስድስት ወር አንድ ጊዜ በሚኒስቴሩ እንደሚወሰን ነው የተናገሩት።

መንግስት ከግብይቱ የወጣ ሲሆን በተሻሻለው መመሪያ መሰረትም መንግስት ሽያጩ ያለ ደረሰኝ እንዳይካሄድ ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስረድተዋል። በግብይቱ ውስጥም ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና ደረሰኝ ግዴታ መሆናቸውን ጠቁመዋል። እያንዳንዱ ፋብሪካ የተደራሽነት አድማሱን በማስፋትም አከፋፋዩን የመምረጥ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።

ከዛሬ ጀምሮም ሲሚንቶ በየትኛውም ቦታ ቁጥጥር እና ክትትል ሳይደረግበት በነጻ ገበያ ይካሄዳል ነው ያለው ሚኒስቴሩ። ከፋብሪካ ሲሚንቶ የሚወጣ ማንኛውም ተሽከርካሪ የመዳረሻ ሰነድ መያዝ እንደሚኖርበትም ነው የተናገሩት።(ሼር)
 https://t.me/lawsocieties
👍3
የፉብሪካ የመሸጫ ዋጋ
👍4
220830.pdf
825.3 KB
ከባንክ ሂሳቤ ላይ ገንዘብ አላአግባብ ወጪ በመደረጉ ባንኩ ገንዘቡን እንዲመልስ የሚል ክስ ሲቀርብ የፎረንሲክ ምረመራውን ውጤት ብቻ መሠረት በማድረግ ባንኩን ለክሱ ኃላፊ ማድረግ መሰረታዊ ስህተት ነው።
ሰ/መ/ቁ. 220830 ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም
በወጪ ማዘዣው ላይ የተመለከተዉ ፊርማ በሲስተሙ ላይ ከተመለከተዉ የፊርማ ናሙና ጋር ተመሳሳይ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የወጪ ማዘዣው ላይ የተመለከተዉ ፊርማ ከናሙና ፊርማ ጋር የሚመሳሰል መሆን አለመሆኑ ገለልተኛ በሆነ አካል ታይቶ መረጋገጥ ይኖርበታል።
በመሆኑም ክስ ከቀረበበት ባንክ ዉጪ በሌሎች ባንኮች ከወጪ ማዛዣ ክፍያ ጋር በተያያዘ ልምድ ባላቸዉ የባንክ ባለሙያዎች እንዲታይ በማድረግ ባንኩ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ግዴታዉን የተወጣ መሆን አለመሆኑ ማረጋገጥ ይገባል፡፡ የባለሂሳቡ ባንክ ደብተር ቀርቦ ሂሳቡ ተቀንሶ የተጻፈ መሆን አለመሆኑ ሆነ የባለሂሳቡ መታወቂያ በማየት ባንኩ ያረጋገጠ መሆን አለመሆኑ ደግሞ በሰው ማስረጃ ሆኖ የባንክ ሂሳብ ደብተሩ ካለ በማስቀረብ መረጋገጥ ይኖርበታል።

https://t.me/lawsocieties
👍1👏1
👍1
ታስረው እንዲቀርቡ ታዘዘ።

የፍርድ ቤት መጥሪያ ፈርመው ወስደው ሳይቀርቡ የቀሩት የአ/አ ቤቶች ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት ታስረው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጠ።

የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ዕጣ ተጭበርብሯል ተብሎ የከባድ ሙስና ወንጀል በቀረበባቸው ተከሳሾች ላይ የዓቃቢህግ 2ኛ ምስክር ሆነው የተቆጠሩት የአ/አ ቤቶች ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት መጥሪያ ፈርመው ተቀብለው ባለመቅረባቸው ምክንያት ነው ታስረው እንዲቀርቡ ዛሬ ትዕዛዝ የተሰጠው።

  ትዕዛዙን የሰጠው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

በአ/አ ከተማ በሀምሌ 1ቀን 2014 ዓ/ም ከኮንዶሚኒዬም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር ተያይዞ  ዕጣው ተጭበርብሯል ተብሎ የአ/አ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት  ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱን እና  ምክትል ቢሮ ሀላፊ የሆኑትን አቶ አብርሀም ሰርሞሌን ጨምሮ በአጠቃላይ በ 11 ተከሳሾች ላይ በየደረጃው የከባድ ሙስና ወንጀል ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

ተከሳሾቹ  ወንጀሉን አለመፈጸማቸውንና ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ገልጸው የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዓቃቢህግ ምስክር  እንዲሰሙለት ጠይቆ ነበር።

በዚህ መሰረት ዓቃቢህግ በሀምሌ 1 ቀን 2014 ዓ/ም በአ/አ ከተማ ወጥቶ ከነበረው የ14ኛ ዙር 20/80  እና የ3ኛ ዙር የ40/60  ከኮንዶሚኒዬም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ  ስርዓት ጋር ተያይዞ እንዲሁም  ለምቷል የተባለው ሶፍትዌርን የሚመለከት እና የተደረገ የኦዲት ስርዓትን ላይ ያተኮረ ምስክርነት እንዲሰማለት  የምስክር ጭብጥ  ካስመዘገበ በኋላ በህዳር 22 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ፍርድ ቤቱ የዓቃቢህግ ምስክር ቃል መሰማት ጀምሮ ነበር።

ፍርድ ቤቱ  እስካሁን የ 8 የዓቃቢህግ ምስክሮችን ቃል ያዳመጠ ሲሆን በ2ኛ የዓቃቢህግ ምስክር ሆነው የተቆጠሩት የአ/አ ቤቶች ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት ግን  መጥሪያ ደርሷቸው ፈርመው የወሰዱ ቢሆንም በችሎት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።ፍርድ ቤቱም ግለሰቡ በፖሊስ ታስረው በይደር እንዲቀርቡ ትዕዛዝ  ሰጥቷል።

Via:- Tarik Adugna
https://t.me/lawsocieties
👍31
አከፋፋይ ምረጡ ማለት እና ዋጋ ተምኜላችሁ ሽጡ ማለት ነፃ ገበያ ማለት አይደለም😝‼️

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ፦ ከዛሬ ጀምሮ ሲሚንቶ በየትኛውም ቦታ ቁጥጥር እና ክትትል ሳይደረግበት #በነጻ_ገበያ ይካሄዳል። ስለዚህ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች አከፋፋዮችን እና ቸርቻሪዎችን መምረጥ የፋብሪካዎቹ እድል ነው! የፋብሪካዎቹ የመሸጫ ዋጋ ለጊዜው ምርታማነት እስከሚጨምር ድረስ የፋብሪካ ዋጋ በስድስት ወር አንድ ጊዜ #በሚኒስቴሩ እንደሚወሰን ገልጿል።

#አማካይ_የሲሚንቶ_ዋጋ
- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 590.3ብር
- አሁን ፋብሪካዎች ያስገቡት የመሸጫ ዋጋ ➤ 1014.6ብር
- እንዲሸጡ የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 758.1ብር

ታዲያ ይህ ማለት እኮ መባል ያለበት ሲሚንቶ አምራቾች አከፋፋይ መርጣችሁ በተተመነላችሁ ዋጋ ሽጡ እንጂ በትርጉም ደረጃ #ነፃ_ገበያ ማለት አይደለም!
በዋሲሁን በላይ

https://t.me/lawsocieties
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በፓስተር ዮናታን አክሊሉ፣ በነቢይ ኢዩ ጩፋ እና የሚያገለግሉበት ቤተ ክርስቲያን ላይ ክስ መሠረተች
=======#===
ረቡዕ ታሕሳስ 12 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በፓስተር ዮናታን አክሊሉ፣ በአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተ ክርስቲያን፣ በክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቤተ ክርስቲያን እና በነቢይ ኢዩ ጩፋ ላይ ክስ መሠረተች።

በቤተክርስቲያንቷ ሕግ አገልግሎት መምሪያ በኩል ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት የተላከው ክስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ ንግግርና አደገኛ የሆነ የሃይማኖትን ክብር የሚነካ የአምልኮ ሥርዓትና እምነትን የሚያንቋሽሽ የዘለፋ እና ሐሰተኛ ንግግር በመፍጠር ለሁከትና ብጥብጥ መነሻ የሚሆን ድርጊት በፈጸሙ ግለሰቦችና ተባባሪ ተቋማት ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲጣራ የሚጠይቅ ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የክስ ዝርዝር ከሥር ተያይዟል።
https://t.me/NegereFej
👍12👎5🔥2
220830.pdf
825.3 KB
ከባንክ ሂሳቤ ላይ ገንዘብ አላአግባብ ወጪ በመደረጉ ባንኩ ገንዘቡን እንዲመልስ የሚል ክስ ሲቀርብ የፎረንሲክ ምረመራውን ውጤት ብቻ መሠረት በማድረግ ባንኩን ለክሱ ኃላፊ ማድረግ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው።

በወጪ ማዘዣው ላይ የተመለከተዉ ፊርማ በሲስተሙ ላይ ከተመለከተዉ የፊርማ ናሙና ጋር ተመሳሳይ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የወጪ ማዘዣው ላይ የተመለከተዉ ፊርማ ከናሙና ፊርማ ጋር የሚመሳሰል መሆን አለመሆኑ ገለልተኛ በሆነ አካል ታይቶ መረጋገጥ ይኖርበታል።

በመሆኑም ክስ ከቀረበበት ባንክ ዉጪ በሌሎች ባንኮች ከወጪ ማዛዣ ክፍያ ጋር በተያያዘ ልምድ ባላቸዉ የባንክ ባለሙያዎች እንዲታይ በማድረግ ባንኩ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ግዴታዉን የተወጣ መሆን አለመሆኑ ማረጋገጥ ይገባል፡፡ የባለሂሳቡ ባንክ ደብተር ቀርቦ ሂሳቡ ተቀንሶ የተጻፈ መሆን አለመሆኑ ሆነ የባለሂሳቡ መታወቂያ በማየት ባንኩ ያረጋገጠ መሆን አለመሆኑ ደግሞ በሰው ማስረጃ ሆኖ የባንክ ሂሳብ ደብተሩ ካለ በማስቀረብ መረጋገጥ ይኖርበታል።

ሰ/መ/ቁ. 220830 ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
#Bank #law #lawyer
#SAMUELGIRMA
Join 👈
https://t.me/lawsocieties
👍1
One_person_private_limited_Company_vs_Limited_Liability_Partnership.pdf
174.7 KB
ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (One-person private limited Company) እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር (Limited Liability Partnership)
Via በአበጀ ካሣሁን
👍2
🔷Vacancy for Law office🔷
                                              
1. Junior Accountant
2. Junior Cashier and secretary
3. Accountant 1-2 year experience
4. Guday Asfetsami (ጉዳይ አስፈፃሚ)

👉 How to Apply 👈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
lawsocieties@gmail.com
Or
consultantentrust@gmail.com
Deadline
Jan 10, 2023

Share for your friends
     👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
👍7🥰5
👍5
👍3